ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
901
Подписчики
-424 часа
-167 дней
+4030 дней
Архив постов
አንዳንዴ በዑለማዎች መካከል خلاف (ግጭት)ሲፈጠር አቦ ሁሉንም መተው ነው እያሉ ለአላህ የሚሰሯቸውን መልካም ስራዎች ጨምረው የሚተው ሰዎችን አታዩም? እነኝህ ሰዎች ግን እድሜ ተሰተው ለ #73 ሲከፋፈል ቢያዩ ምን ሊሆኑ ነው? ✍️ አቡ ሐይደር አልይ

ክፍል 001 የ ሙስጦላህ ኪታብ   الدرر النقية في شرح المنظومة البيقونية https://t.me/UstazKedirAhmed/10564

ለአላህ ብለን ለወደድነው ሰው መክፈል ያለብን ዋጋ ምንድነው? በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (حفظه الله) 🔷👉 https://t.me/abujemila25 🔷👉https://t.me/abujemila25

تفصيل في مسألة السنة والبدعة! الشيخ عبيد بن عبد الله الجابري رحمه الله.

➺ሰለፎች ለነቢዩ ﷺ ከእኛ የበለጠ ፍቅር ነበራቸው፤ ነገር ግን መውሊድን አላከበሩም። ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ፣ መጀመሪያ የሚፈጽሙት እነርሱ ነበሩ። ስለዚህ ነቢዩን ﷺ መውደድ የሚገለጸው በሱናቸ
➺ሰለፎች ለነቢዩ ﷺ ከእኛ የበለጠ ፍቅር ነበራቸው፤ ነገር ግን መውሊድን አላከበሩም። ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ፣ መጀመሪያ የሚፈጽሙት እነርሱ ነበሩ። ስለዚህ ነቢዩን ﷺ መውደድ የሚገለጸው በሱናቸውን በመከተል እንጂ፣ በሰለፎች ያልተፈጸመ አዲስ አምልኮ በመፍጠር አይደለም። ➺ሰሞኑን አህባሾች መውሊድ ቀርቦዋል እያሉ እያጨበጨቡ ነው . አሏህ ህዳያ ይስጣቸው 🏷ሼር አድርጉላቸው እስቲ ☝️

«የሱና ዑለማኦች መከባበር» ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊይ እንዲህ ይላሉ፦ «ረቡዕ ዕለት ከመግሪብ ሶላት በፊት በነቢዩﷺ መስጊድ ውስጥ ከተከበሩት ሸይኽ አብዱስሰላም አሽሹወይዒር ጋር ተገናኘን። ፊታቸው
«የሱና ዑለማኦች መከባበር» ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊይ እንዲህ ይላሉ፦ «ረቡዕ ዕለት ከመግሪብ ሶላት በፊት በነቢዩﷺ መስጊድ ውስጥ ከተከበሩት ሸይኽ አብዱስሰላም አሽሹወይዒር ጋር ተገናኘን። ፊታቸው በደስታ በራ፤ እጅግ አጥብቀውም አቀፉኝ። እንዲህም አሉ፦ "በአላህ ይሁንብኝ ሸይኻችን! ለእርስዎ ካለኝ ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ ከልቤ ውስጥ ባስገባዎት ደስ ይለኝ ነበር።" ይህም ከእሳቸው መልካም ባህሪና ትህትና የተነሳ ነው። አክለውም፦ "እኔ ወርሃዊ ትምህርቴን (ደርሴን) ከቀኑ 5:30 እስከ መግሪብ ያደረግኩት ከእርስዎ ትምህርት ጊዜ ጋር እንዳይጋጭብኝ ነው" አሉኝ። ​እኔም አልኩ፡ "እውቀት በባለቤቶቹ መካከል እንደ ዝምድና ነው፤ የሱና መሻይኾችን በእሱ (በአላህ) የሚዋደዱ ስላደረጋቸው አላህን አመሰግናለሁ።" ​ጌታዬ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ የሱና መሻይኾችን ሁሉ እርሱ ለሚወደው እንዲወፍቃቸው፣ ስማቸውን እንዲያገዝፍ፣ ማዕረጋቸውን ከፍ እንዲያደርግና በእሱ ዘንድ ባሉት መላእክት ፊት እንዲያወሳቸው እለምነዋለሁ። እንዲሁም የሱና ሰዎችን በሙሉ በመልካም አንድነትና ስምምነት ላይ እንዲረዳቸው አላህን እለምናለሁ።» = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

01 جناية التميع على المنهج السلفي.mp37.96 MB

 بِسْــــمِ ﷲِ الرَّحْمـٰــــــــنِ الرَّحِيمِ የኪታቡ ስም "'ጂናየቱ ተምዩዕ አለል መንሃጂ ሰለፍ" የደርሱ አቅራቢ ኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ የደርስ ብዛት 19     🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abuharisR

ተተኪውን ትውልድ *ፊትና ከሚሞቀው፡ አንድ እንሁንና #ሒዝብያን ይጭነቀው፡ ✍️ ኑረድን አል-አረቢ

إعلام الموحدين بخطورة الشرك.pdf4.30 MB

የሰኞ ፆም እና መውሊድ ~ የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦ 1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?! እናንተ'ኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው። 2. እናንተ'ኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት! ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር አይደለም ወይ? 3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም! ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል። 4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም! የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላልን? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን? {يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ} {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው።} [አልሑጁራት፡ 1] ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782] 5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም! ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ሁሉ ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር። 6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና። 7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም! በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ መፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም። እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሕ ሙኽተሶሪል ኸሊል" የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ? ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም። ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የማለዳ መልእክት (42) ~ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- مَنْ أحبَّ أن يَصِلَ أباهُ في قبرِهِ، فلْيَصِلْ إخوانَ أبيهِ مِن بَعدِه "በመቃብሩ ውስጥ ላለ (ለሞተ) አባቱ መልካም መዋል የሚወድ ሰው፣ ከእርሱ በኋላ ለአባቱ ወንድሞች (ወዳጆች) መልካም ይዋል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ ፣ አልአልባኒይ ፡ 5960] የወላጆች ሐቅ በመሞታቸው አይቋረጥም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህ ሐዲሥ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላም ቢሆን ለእርሱ መልካም ነገርንና ምንዳን ማብዛት የሚቻልበትን ተግባራዊ መንገድ ያሳዩናል። እርሱም የአባትን ወዳጆችና የቅርብ ዘመዶች መዛመድ/መንከባከብ፣ መጠየቅ ነው። ለአባት መልካም ማድረግ በእርሱ ህልፈት የሚያበቃ ሳይሆን፣ በሕይወት እያለ ይወዳቸውና ይዛመዳቸው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። ከዚህም ባሻገር ለወላጆች በማሰብ ሶደቃ ማውጣት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዑምራ ማድረግ፣ ... ከሞቱም በኋላ አጅራቸው እንዲቀጥሉ ከሚያደርጉ ተግባራት ውስጥ ናቸው። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 20 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል ! የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡ “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” ''አሏህን ያዝ ሰበቡን አድርስ የተሻለ ነገር ታገኛለህ ፤ ሁሉም ነገር ከጥረት ጋር መሆኑን ላፍታም ቢሆን አትዘንጋ'' ©

ታከሚ ተክፊሪይ መንሀጅሽ በስሜት በዕልህ ተሞልቶ፣ ዑለማዕ ለመስደብ ምላስሽ ተገርቶ፣ እንደ ሜዳ ላይ ኳስ ንፋስ እንደነፋው፣ ፊክራ ኢልም መስሎ አዕምሮን ሲሞላው፣ ይህ ነው ምልክቱ ማንዘርዘር ማንቀጥቀጥ፣ እዚያም፣እዚህ ገብቶ ነገር መቀላወጥ። ይቀጥፋል፣ይዘልፋል፣ይዋሻል፣ያሷሻል፣ ሰዲቦ፣ያሰዲባል፣ያረክሳል፣ያኮሳል፣ በምላሱ እንደ አዞ ሰው ይሞሸልቃል። አጥንት ሰባሪ ቃላቶች ይመርጣል፣ ከማያልቀው ካዝናው ያርከፈክፈዋል፣ ዝርጠጣ ፣ፉገራ፣ስድብና ሹፈቱ ምልክቱ ሁኗል። ፍንትው ያለ ነበር ያለሽበት ባጢል፣ አጣርቶ ለሚይዝ ለተሰጠው አቅል። የጮኽ አያጣም ነው እና ነገሩ፣ አራጋቢ አገኘሽ ወሬ እሚሾፍሩ፣ አወ:አወ  !!ለአይነታሽ ይመስላል የላቀ፣ አጣርቶ ላላየ ፊትናን ላላወቀ፣ ግን የሱና ወንዶች አዩሽ እና በደንብ፣ እንዲህ ሲሉ ጣሉሽ ከሰለፍይ ወደብ፣ ለማያቅሽ ታጠኝ ምንጭሽ ለጠፋበት፣ ተክፊሪይ ሆይ!በይ ውጭ ከሰለፍይ ማጀት። ወጥ እረገጥ መንገድ የስዲብ ዘለፋ፣ ማንቋሸሽ፣ መሳለቅ በድብቅ በይፋ፣ ከመቸ ወድህ ነው የሚነግሰው ገፍቶ፣ ያውም ከግዙፍ ጋር ፊለፊት ተጋጭቶ፣ መጨራመት እንጂ መትረፍ የለም ከቶ። የዐሊምን ክብር ቀረጫጭሞ በልቶ፤ መንገስ አይገኝም በተራ ቀረርቶ። በወባ በሽታ ተለክፈሽ በጠና፣ ያውም ጨምሮብሽ አክፋሪ ነሽ እና፣ ራስሽ ፈልገሽ ወጣሽ ከጎዳና። ብለው ተፍተውሻል ማንነትሽን አውቀው፣ ዝላይሽ አይጎዳም እውነትሽ ባዶ ነው፣ ደግሞም አጃኢብሽ ያሳቀኝ ተግባር፣ መቸም አራማጂሽ አያውቅም ማፈር፣ መደብ ይመዲባል ለታላቅ ኡለማ፣ ሁሌም ይገርመኛል የተክፊር አላማ፣ ሁለት ነዶ ይዞ ወደ ክምር ጠጋ፣ በቁንፅል እውቀቱ ለመግጠም አሊም ጋ፣ በምላስ ደልሎ ፣ለቅሶንም አክሎ፣ ይነዳቸው ይዟል ሰለፍይ መስሎ። አይ የተክፊር መንሐጅ ያለ መሳይ ሙቶ፣ ማስመሰል ሰለፍይ ፈሩን እጅግ ስቶ። ባህሪሽ ተዘርዝሮ ተቀምጧል በደንብ፣ ተግሳፅ ለሚገባው ፣ከልቡ ለሚያነብ፣ አወ!አይወዲልሽም የዲን ሰው አዋቂ፣ #ተከታይ ብቻ እንጂ አጃቢ አለቅላቂ። ደግሞ ትጮሂያለሽ ጀግና አርበኛ መስለሽ፣ 👉 ነቃ ያለብሽን ቀድመሽ ትነዲፊያለሽ፣       መገን!! መንገዲሽ ግልፅ ነው ማለቃቀስ መቶ፤ አያልቅብሽ ውሸት መሽቶም ሆነ ነግቶ፣ ልብ መግዛት ትተሽ በዚሁ ከቀጠልሽ፣ የያዘሽ በሺታ ቢጫ ወባ ሁኖ ሞተሽ ትቀሪያለሽ፣ ስለዚህ ታከሚ፣ስለዚህ ታከሚ ተክፊሪይ እባክሽ። ✍️ ዑሙ ረያን

والله لتسألنّ أمام الله عن محاربتك للسّلفيين كذبا وزورا! الشيخ ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله.

Repost from ፈዋኢድ
ግን የዛሬ 60/70/80....100 አመት በኋላ የት እንደሆንን ታውቃላቹ? 100 ከፍተኛው ቁጥር መሆኑንም አትዘንጉ ዝቅተኛው ከዚህ ደቂቃ በኋላ ሊሆን ይችላል ለዚህች ህይወት ብለህ እስከ መቼ ማጭበርበር እስከ መቼ ሰዎችን ማስለቀስ እስከ መቼ አሏህን ማመፅ እስከ መቼ የወላጆችን ቀልብ መስበር እስከ መቼ የሰው ሀቅ ይዘህ መጥፋት እስከ መቼ በሰሏት መዘናጋት እስከ መቼ በወለድ መጨማለቅ እስከ መቼ በውሸት መነገድ