Comparative Religion
رفتن به کانال در Telegram
{እዚሁ ውስጥ ያላችሁ ክርስቲያን ወገኖቻችን በእስልምና ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ,መስለም ከፈለጋችሁ እና በተጨማሪ ነፃ የምክር አገልግሎት ከፈለጋችሁ በውስጥ መስመር ጥቆማ መስጣት ትችላላችሁ ።} @AMDALA6_BOT
نمایش بیشتر4 412
مشترکین
-424 ساعت
+17 روز
-5830 روز
در حال بارگذاری دادهها
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
نوامبر '26نوامبر '26
نوامبر '26
+25
در 1 کانالها
اکتبر '26
+52
در 2 کانالها
Get PRO
سپتامبر '26
+92
در 3 کانالها
Get PRO
اوت '26
+150
در 4 کانالها
Get PRO
ژوئیه '26
+158
در 1 کانالها
Get PRO
ژوئن '26
+218
در 3 کانالها
Get PRO
مه '26
+142
در 1 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+75
در 1 کانالها
Get PRO
مارس '26
+80
در 7 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+102
در 3 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+103
در 2 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+86
در 3 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+87
در 4 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+106
در 7 کانالها
Get PRO
سپتامبر '25
+100
در 6 کانالها
Get PRO
اوت '25
+198
در 7 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+307
در 6 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+221
در 5 کانالها
Get PRO
مه '25
+414
در 4 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+531
در 4 کانالها
Get PRO
مارس '25
+518
در 2 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+418
در 3 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+772
در 1 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+546
در 2 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+691
در 2 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+77
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+96
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '24
+138
در 2 کانالها
Get PRO
ژوئیه '24
+51
در 2 کانالها
Get PRO
ژوئن '24
+60
در 4 کانالها
Get PRO
مه '24
+306
در 7 کانالها
Get PRO
آوریل '24
+144
در 6 کانالها
Get PRO
مارس '24
+129
در 3 کانالها
Get PRO
فوریه '24
+126
در 3 کانالها
Get PRO
ژانویه '24
+80
در 4 کانالها
Get PRO
دسامبر '23
+127
در 4 کانالها
Get PRO
نوامبر '23
+60
در 3 کانالها
Get PRO
اکتبر '23
+268
در 1 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 07 نوامبر | +6 | |||
| 06 نوامبر | +1 | |||
| 05 نوامبر | +1 | |||
| 04 نوامبر | +5 | |||
| 03 نوامبر | +3 | |||
| 02 نوامبر | +6 | |||
| 01 نوامبر | +3 |
پستهای کانال
13/ (ገጽ 199)፦ በሱረቱል አዕራፍ (7፡16) ላይ ኢብሊስ ለአላህ «بِمَا أَغْوَيْتَنِي» (ስላጠመምከኝ/በጥመት ስለፈረድክብኝ) ያለውን፣ ጸሐፊው «ሙስሊሞች በአማርኛ ስላጠመምከኝ ብለው የተረጎሙት ውሸት ነው፣ አረብኛው ስላሳሳትከኝ ነው የሚለው፣ ስለዚህ አላህ አሳሳች ነው» ብሎ የዐረብኛ ሊቅ መስሎ ተከራክሯል። የዐረብኛ ፊደል መለየት የማይችል ሰው የቁርኣን ተፍሲር ሊቃውንትን «አረብኛ አይችሉም» ማለቱ አስቂኝ ድፍረት ነው።
14/ (ገጽ 209)፦ ይህ ደግሞ በዩቲዩብ ላይቭ ላይ እንኳን ለመናገር ፈርቶ የሸሸው ታላቅ ሌብነት ነው! «ቁርኣን መላእክት 2፣ 3 ወይም 4 ክንፍ ብቻ ነው ያላቸው ይላል (ሱራ 35፡1)፣ ሐዲስ ግን ጅብሪል 600 ክንፍ አለው ይላል፤ ስለዚህ ይጋጫሉ» ብሎ ጽፏል። ይህን ለማለት ግን የሱረቱ ፋጢር (35፡1) አንቀጽን መጨረሻ ሆን ብሎ በመቀስ ቆርጦ ጥሎታል! ምክንያቱም አንቀጹ ቀጥሎ፦ «يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ (አላህ በፍጥረቱ ላይ የሚሻውን ይጨምራል!)» ይላል! ይህችን ዓረፍተ ነገር ቢያስገባት ክሱ ስለሚፈርስ ቆርጦ ደብቋታል!
15/ (ገጽ 214)፦ የነቢዩ (ﷺ) ደረት በልጅነታቸው በመላእክት መከፈቱንና መታጠቡን የሚገልጸውን ተአምራዊ ክስተት፣ «ሰይጣናዊ የጥንቆላ ልምምድ (Shamanism) ነው» ብሎ ጽፏል። ይህን ሲል ግን በራሱ መጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ሕዝቅኤል (11፡19 እና 36፡26) ላይ እግዚአብሔር «የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ፣ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ» እንዲሁም በትንቢተ ዘካርያስ (3፡4) ላይ የካህኑን እድፋም ልብስ አውልቀው ኃጢአቱን እንዳራቁለት የተጻፈውን መለኮታዊ ተምሳሌት ዘንግቶ የገዛ መጽሐፉን ወግቷል።
16/ (ገጽ 285)፦ በሱረቱል ሐاقه (69፡44–46) ላይ «በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤... ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡» የሚለውን አንቀጽ፣ ከኸይበር መርዝ ጋር ለማገናኘት ሲል «ሙሐመድ ከኸይበር በኋላ ወዲያውኑ የልብ ደም ሥሩ ተቆርጦ ሞተ» የሚል ትርክት ፈጥሯል። ነቢዩ (ﷺ) የኸይበርን የተመረዘ ሥጋ ከቀመሱ በኋላ ለ3 ዓመታት (ከ7ኛው እስከ 11ኛው ዓመተ ሂጅራ) በሙሉ ጤንነት ኖረው፣ መካን ከፍተው፣ በርካታ የቁርኣን ምዕራፎች ወርደውላቸው፣ ዲኑ ተሟልቶ መሞታቸውን ከአንባቢው ደብቋል።
17/ (ገጽ 298)፦ በሱረቱ آل ዒምራን (3፡54) ላይ «وَمَكَرُوا وَمَكَرَ اللَّهُ» (አይሁዶችም) አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው፡፡) የሚለውን አንቀጽ፣ ከፊቱ ያለውን «እነሱ አሴሩ» የሚለውን ቆርጦ በመጣል «አላህ ከአጭበርባሪዎችና ከአሳሳቾች ሁሉ በላጭ ነው» ብሎ ተርጉሞታል! በዐረብኛ «መክር» ለተንኮለኞች አጸፋ መመለስን (እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ «ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ» — 2ኛ ሳሙኤል 22፡27) እንደሚያመለክት እያወቀ ቃሉን አዛብቷል።
18/ (ገጽ 325 vs 330)፦ በአንድ ምዕራፍ ውስጥ በ5 ገጽ ልዩነት እርስ በርሱ የተጋጨበት አስቂኝ ቅጥፈት ደግሞ ይገርማል! በገጽ 325 ላይ ነቢዩ (ﷺ) ሥጋው እንደተመረዘ በተአምር አላወቁም ለማለት ሲል፦ «አንድ ጉርሻ አጣጥሞ መብላት በጀመረበት ወቅት ነው መርዙን በጣዕሙ ያወቀው» ብሎ ጻፈ። ከ5 ገጽ በኋላ በገጽ 330 ላይ ደግሞ «ታዲያ አብሮ የበላው ቢሽር ወዲያው ሲሞት ነቢዩ ለምን ወዲያው አልሞቱም?» የሚለውን ጥያቄ ለመሸሽ ሲል፣ በገጽ 325 የጻፈውን ረስቶ፦ «ሙሐመድ ትንሽ አኘከው እንጂ አልዋጠውም፣ ተፋው (he did not swallow it, spat it out)» ብሎ ጻፈ! ሳይውጡት የተፉት ምግብ እንዴት ከ3 ዓመት በኋላ የልብ ደም ሥርን ይቆርጣል?
19/ (ገጽ 340–341)፦ በቁርኣን የተጠቀሰው «አል-ወቲን» እና በሐዲስ የተጠቀሰው «አል-አብሀር» አንድ ናቸው ብሎ ለመከራከር፣ ቀደም ሲል «የተረት ተረት ጸሐፊዎች ናቸው፣ ነቢያቸውን ለመሸፈን የሚጽፉ ናቸው» እያለ ሲሳደብባቸው የነበሩትን እነ ኢብኑ ከሲርን እና ኢብኑል ቀይምን በገጽ 334 እና 340 ላይ፦ «ታላቁ ኢማም ኢብኑ ቀይም... ከምንም በላይ ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ከሲር የአረብኛውን ቃል በደንብ አብራርቶታል» እያለ በምስክርነት ተማጽኗቸዋል!
ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እንዲሁም ክርስቲያን ወገኖቻችን ! ይህ ከባሕር በጭልፋ የተቀዳ 19 ነጥብ ብቻ ነው! ይህ ሰው 358 ገጽ ሙሉ እንዴት ጥቅሶችን እየቆረጠ፣ ትራስን ወደ ልብስ፣ መደገፍን ወደ መንቀጥቀጥ እየቀየረ እንዳጭበረበረ የሚያሳየው ሙሉው የምላሽ መጽሐፋችን በሚቀጥለው ሳምንት በአላህ ፍቃድ በነጻ ይለቀቃል! ሼር በማድረግ እውነቱን ለሁሉም አድርሱ!
https://t.me/Yahyanuhe
| 2 | «የጽልመቱ ጥላ» ወይስ «የቅጥፈቱ ጥላ»?! - ጸሐፊው አንባቢን ለማታለል ሆን ብሎ የፈጸማቸው 19 ሌብነቶች!
አንድ ሰው በሃይማኖት ዙሪያ መጽሐፍ ሲጽፍ ቢያንስ ለሚጠቅሳቸው ምንጮችና ለአንባቢዎቹ ታማኝ መሆን ይጠበቅበታል። የ«የጽልመቱ ጥላ» ጸሐፊ ግን አንባቢው የዐረብኛም ሆነ የእንግሊዘኛ ምንጮችን ተመልሶ አያጣራም በሚል ንቀት፣ 358 ገጽ ሙሉ በመቀስ የተቆራረጡ ጥቅሶችን፣ የተፈበረኩ ታፔላዎችንና የተገለበጡ ትርጉሞችን አጭቆታል። ሙሉው የምላሽ መጽሐፋችን ከመውጣቱ በፊት፣ የሰውዬውን የቅጥፈት ጥግ የሚያሳዩ 19 እጅ ከፍንጅ የተያዙ ማጭበርበሮችን ከነገጻቸው እንሆ፦
1/ (ገጽ 9–10)፦ ነቢዩ (ﷺ) «ለጣዖቷ አል-ዑዛ ነጭ በግ ሰውተዋል» ለማለት ሲል፣ በእስልምና የሐዲስ ሊቃውንት ዘንድ በውሸታምነቱ (መትሩክ/ዷዒፍ) የሚታወቀውን የሂሻም ኢብኑ አል-ከልቢን «ኪታቡል አስናም» የተባለ የፈጠራ ወሬ እንደ ትክክለኛ (ሰሒሕ) ኢስላማዊ ማስረጃ አድርጎ አቅርቧል። አንባቢው የዘገባውን ደካማነት እንዳያውቅ ሲል ሆን ደግሞ ብሎ ምንጩን ደብቆ አታልሏል።
2/ (ገጽ 14)፦ በሱረቱ አል-ኢኽላስ (112፡1) ላይ «አላህ አንድ ነው» የሚለውን የአማርኛ ትርጉም ለማጣጣል፣ የዐረብኛው «أَحَدٌ» (አሐድ) የሚለው ቃል «አንድ ማለት ሳይሆን ከብዛት ውስጥ አንዱ ማለት ነው» ብሎ ዓይን ያወጣ የቋንቋ ውሸት ጽፏል። በዐረብኛ «አሐድ» ማለት ምንም አቻ፣ ክፍልፋይና ሁለተኛ የሌለው ፍጹም አንድ ማለት ሲሆን፣ ጸሐፊው ግን አንባቢን ለማሳሳት የቃሉን ትርጉም ገልብጦ ተርጉሞታል።
3/ (ገጽ 17)፦ ነቢዩ (ﷺ) በሒራ ዋሻ የመጀመሪያው መገለጥ የመጣላቸው «በእውናቸው ሳይሆን በሕልማቸው (በቅዠት) ነው» ብሎ ለማታለል፣ በታሪክ መጽሐፍ (ኢብኑ ኢስሐቅ) ላይ የሚገኘውን «ተኝቼ ሳለሁ» የሚል ደካማ ወሬ አምጥቶ ከስሩ "Sahih Muslim 160a" የሚል የውሸት ታፔላ ለጥፎበታል! ሰሒሕ ሙስሊም 160a ላይ ግን «ተኝቼ ሳለሁ» የሚል አንድም ቃል የለም፤ የአንድን መጽሐፍ ጥቅስ በሌላ መጽሐፍ ስም መለጠፍ የጠራራ ፀሐይ ሌብነት ነው።
4/ (ገጽ 25–27)፦ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነቢዩን «የሞተ እስኪመስለው ድረስ ጨምቆ ከለቀቀው በኋላ፣ በጉልበቱና በሁለት እጆቹ በዳዴ እየተንፏቀቀ ወደ ኸዲጃ ሄደ» ብሎ የሌለ ታሪክ ፈጥሯል። በየትኛውም የሐዲስ መጽሐፍ ላይ ነቢዩ (ﷺ) ከሒራ ተራራ ወርደው እስከ መካ ድረስ «በዳዴ እየተንፏቀቁ ሄዱ» የሚል ዘገባ የለም፤ ጸሐፊው ነቢዩን ለማንቋሸሽ ከራሱ ጭንቅላት ፈጥሮ የጨመረው ቅጥፈት ነው።
5/ (ገጽ 43)፦ የመካ ቁረይሾች ነቢዩን (ﷺ) «ድግምተኛ ነው» ማለታቸውን ጠቅሶ፣ «በሙሐመድ ጊዜ የነበሩ ሰዎች እንኳ መገለጡ በድግምት እንደሆነ ተስማምተዋል» ብሎ ደምድሟል። ነገር ግን በዚያው በጠቀሰው ታሪክ ውስጥ የቁረይሾቹ መሪ ወሊድ ኢብኑል ሙጊራህ «የሙሐመድን ንግግር ሰምቻለሁ፣ የድግምተኛም የጠንቋይም ንግግር አይደለም! ነገር ግን ሕዝቡን ከእሱ ለመከፋፈል ሲባል ድግምተኛ በሉት» ብሎ የመከረውን ክፍል ሆን ብሎ ቆርጦ ደብቆታል።
6/ (ገጽ 58–59)፦ ይህ የጸሐፊው የእውቀት ክፍተት እና የሌብነት ጥግ የታየበት ክፍል ነው! ነቢዩ (ﷺ) «መገለጥ በመጣላቸው ቁጥር በሴት ልብስ ውስጥ ተደብቀው ይንቀጠቀጡ ነበር» ለማለት ሲል፣ ሰሒሕ ኢብኑ ሂባን 5843ን ጠቅሶ፦ "Aisha said... I saw the Messenger of Allah shivering over them (ሲንቀጠቀጥባቸው አየሁት)" ብሎ ጽፏል። ትክክለኛው የኢብኑ ሂባን 5843 ሐዲስ ግን ስለ መገለጥም ሆነ ስለ መንቀጥቀጥ ፈጽሞ አያወራም! ዓኢሻ (ረ.ዐ) ምስል ያለበትን መጋረጃ ቆርጣ ሁለት ትራሶች (ውሳደተይን) እንደሰራችና ነቢዩም በትራሶቹ ላይ ሲደገፉ (የርተፊቁ / يَرْتَفِقُ) አየኋቸው ነው የምትለው! ጸሐፊው «መደገፍ» (የርተፊቁ) የሚለውን ከ«መንቀጥቀጥ» (የርተዒዱ) ጋር አምታቶ፣ «ትራሶቹ» የሚለውን ደግሞ ቆርጦ በመጣል «በሴት ልብስ ውስጥ ሲንቀጠቀጥ» ብሎ አንባቢውን በጠራራ ፀሐይ አጭበርብሯል!
7/ (ገጽ 96 እና 111 vs 274)፦ በገጽ 96 እና 111 ላይ ዓኢሻና ሰሐቦቹ «ሰይጣን (ቀሪን) ስላለባቸው እንድትዋሽ ያደርጋታል፣ ስለዚህ የተናገሩት ሐዲስም ሆነ ቁርኣን ሊታመን አይችልም» ብሎ ጽፏል። በዚያው መጽሐፍ በገጽ 274 እና 330 ላይ ግን ነቢዩ በመርዝ መታመማቸውን ለማስረዳት ሲፈልግ፦ «ዓኢሻ የተናገረችውን አለማመን እንዴት ይቻላል? እሷ ውሸታም ከሆነች ማን ሊታመን ይችላል?» ብሎ ከራሱ ጋር ተጋጭቷል!
8/ (ገጽ 123 እና 167)፦ የሱኒ ሙስሊሞችን ለመተቸት «የእናንተው ሶሒሕ መጻሕፍት ናቸው» እያለ፣ በሱኒ ሙስሊሞች ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸውን የሺዓ መጻሕፍት (እንደ አል-ካፊ እና ሐያቱል ቁሉብ) ከ8 ጊዜ በላይ በማስረጃነት ጠቅሷል። ይህ ልክ አንድ ሙስሊም የኦርቶዶክስን እምነት ለመተቸት የይሖዋ ምስክሮችን ወይም የሞርሞኖችን መጽሐፍ እንደ ማስረጃ እንደመጥቀስ ያለ የአካዳሚክ ማጭበርበር ነው።
9/ (ገጽ 97-99)፦ ጸሐፊው በሰሒሕ አል-ቡኻሪ 3286 ላይ የሚገኘውን «ማንኛውም የአዳም ልጅ ሲወለድ ሰይጣን በጣቱ ይወጋዋል፣ ዒሳና እናቱ መርየም ሲቀሩ» የሚለውን ሐዲስ ጠቅሶ፣ «ሙሐመድም ሲወለድ ሰይጣን ወግቶታል፣ ስለዚህ የሰይጣን ተጽዕኖ አለበት» ብሎ ደምድሟል። ይህን ሲል ግን ሁለት ታላላቅ ማጭበርበሮችን ፈጽሟል፦ አንደኛ፣ በዚያው በጠቀሰው ሐዲስ ላይ ይህ የሰይጣን መውጋት «ሕፃኑ ሲወለድ የሚያሰማው የመጀመሪያ ጩኸት (ልቅሶ) ምክንያት» መሆኑንና በነቢያት ሕይወት ላይ ምንም የኃጢአትም ሆነ የሰይጣን የበላይነት እንደማያመጣ የተገለጸውን ቆርጦ ጥሏል። ሁለተኛ፣ በዚህ ሐዲስ መሠረት ከዒሳ (ዐ.ሰ) በስተቀር በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኙት ታላላቅ ነቢያት ሁሉ (አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ሰለሞን፣ መጥምቁ ዮሐንስ) ሲወለዱ አልቅሰዋልና እነሱንም «ሰይጣን የወጋቸውና የሰይጣን ተጽዕኖ ያለባቸው ናቸው» ብሎ የገዛ ነቢያቱን በሙሉ አብሮ ወግቷል!
10/ (ገጽ 156–157)፦ ስለ «ገራኒቅ» (የሰይጣን ጥቅሶች) ክስ ሲጽፍ፣ ታላቁ ሊቅ ኢማም አል-ቁርጡቢ ይህ ታሪክ «መሠረት የሌለው ደካማና ውድቅ (ዷዒፍ)» መሆኑን መናገራቸውን በገጽ 157 ላይ ራሱ ጠቅሶ ሲያበቃ፣ ያንኑ ውድቅ የተባለ ተረት ግን የምዕራፍ 6 ዋና ማስረጃ አድርጎ አቅርቦታል!
11/ (ገጽ 166)፦ «ኢብሊስ ከመላእክት ወገን ነበር ወይስ ከጂኒ? ቁርኣን ይጋጫል» ብሎ ለማታለል፣ በዐረብኛ ሰዋስው የሚታወቀውን «ኢስቲስናእ ሙንቀጢዕ» (ከተለየ ወገን ነጥሎ ማውጣት) ሕግ ደብቋል። በሱረቱል ከህፍ (18፡50) ላይ አላህ «ኢብሊስ ከጂኒዎች ነበር» ብሎ በግልጽ ማስቀመጡን እያወቀ፣ ከመላእክት ጋር አብሮ ስለነበረ ብቻ በጥቅል ትዕዛዝ መካተቱን እንደ ግጭት አድርጎ አቅርቧል።
12/ (ገጽ 272–273 እና 278)፦ ነቢዩ (ﷺ) በለቢድ ኢብኑ አል-አዕሰም ድግምት (ሲሕር) ተደርጎባቸው በነበረ ጊዜ፣ ድግምቱ የነበረው በሰውነታቸው (ከሚስቶቻቸው ጋር በነበራቸው ግንኙነት) ላይ ብቻ እንጂ በአእምሯቸውና በወሒይ (በመገለጥ) ላይ ምንም ተጽዕኖ እንዳልነበረው የሐዲስ ሊቃውንት ያስቀመጡትን ማብራሪያ ቆርጦ በመጣል፣ «ቁርኣንን የተቀበለው በድግምት እየቃዠ ነው» ብሎ ቀጥፏል። | 250 |
| 3 | "የተከታዮቻቸው ደህንነት ያሰጋቸው ነብዩ መሐመድ (ሰአወ) “ራሳችንን ለመከላከል አላህ ብርታቱን እስኪሰጠን ድረስ ወደ ሀበሻ ሀገር ሄዳችሁ እዛ ቆዩ። የሀቀኞች ሀገር ናት። ንጉሷም ፍርድና ፍትህ አዋቂና አስተዋይ ስለሆነ በሱ ዘንድ ማንም አይበደልምና አትሰጉ” ብለው ወደ ኢትዮጵያ ሸኟቸው።
በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ በስደት የመጡት ሙስሊሞች 150 ያህል ነበሩ። ከነዚህ ስደተኞች ውስጥ የነብዩ መሐመድ (ሰአወ) አሳዳጊ (ሞግዚት) የነበረችው በረካ ኡሙ አይመንን ጨምሮ 21 ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነበሩ። ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ አፄ ኦስሀማ (ነጃሺ) በክብር ተቀብሎ የስደተኝነት መብትና ከለላ ሰጣቸው፡፡"
ደራሲ፦ አብዱልፈታህ ሁልዳር
የመጽሃፉ ስም፦ ስልጤነት እና ኢትዮጵያዊነት
ምዕራፍ አንድ ገፅ 45
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir
ቻናል t.me/αmdαlα nαsi | 321 |
| 4 | ⚠️ አስተውሉ❗️
ከሚከተሉት ነቢያት (الأنبياء) ውስጥ ሱረቱል አንቢያ (سورة الأنبياء) ላይ ስማቸው ያልተጠቀሰው የትኛው ነው?
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ነው
ተቀላቀሉ➢@mustefa_Apologetics | 64 |
| 5 | «ጨለማን በጨለማ ማራቅ አትችልም፤ ብርሃን ብቻ ነው የሚያርቀው። ጥላቻንም በጠቃሚ ፍቅር እንጂ በቲፎዞ አታጠፋውም።»
ለመጥፎ ነገር ምላሽ በመጥፎ ነገር ሳይሆን በመልካምነትና በእውነት ብቻ መስጠት ነው።ቻናል t.me/αmdαlα nαsir
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir | 586 |
| 6 | ከሳውዲ አረቢያ ቀጥሎ እስልምና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተሰበከውና የተስፋፋው በአክሱም ዘመነ መንግስት ነበር።
እስልምና በተሰበከ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጣኦት አምላኪ የነበሩት፣ በመጠጥ፣ በቁማርና በማህበራዊ ዝቅጠት ውስጥ ወድቀው የነበሩት፣ ሴትን ልጅ ከነህይወቷ ይቀብሩ የነበሩትና የባሪያ ንግድ በስፋት ያካሂዱ የነበሩት የአረቢያ ምድር ገዥዎች፤ ከአንድ አላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ የሚሰብከውን፣ መጠጥና ቁማርን የሚጠየፈውንና የሚቃወመውን፣ ለማህበራዊ ፍትህ የሚታገለውን፣ ሴቶችን እንደ ሰው ልጅ የሚቀበለውንና እንደ እናት የሚያከብረውን፣ ባርነትን የሚያወግዘውንና ያለመደብና ዘር መድሎ የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው ብሎ የሚሰብከውን እስልምናን መቀበልና መታገስ አልቻሉም።
ህብረተሰቡን አነሳስቶና አሳምኖ ባህላቸውንና ልማዳቸውን ከማጥፋቱ በፊት እስልምናን በአንጭጩ ለመቅጨትና ሃይማኖቱን የተቀበሉ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ቁጥራቸው በዝቶ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት እምነታቸውን በኃይል ለማስለወጥ ወይም ለመግደል ወስነው ማሳደድ ጀመሩ።
——————————
ደራሲ፦ አብዱልፈታህ ሁልዳር
የመጽሃፉ ስም፦ ስልጤነት እና ኢትዮጵያዊነት
ምዕራፍ አንድ ገፅ 32 | 870 |
| 7 | 📸የአይን ፈተና 👀👀⁉️
📟#ስንት ቁጥር #እየታይችሁ ነው⁉️
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ነው
ተቀላቀሉ➢@mustefa_Apologetics | 76 |
| 8 | «አላህ አደምን በመልኩ ፈጠረው»
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ጌታዬ ሆይ መልሴን እንደ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ የሰላ ሰይፍ አድርግልኝ።
ነቢዩ (ﷺ) ስለ አደም አፈጣጠር ሲናገሩ እንዲህ አሉ፦«አላህ አደምን በራሱ መልክ ፈጠረው። ቁመቱም ስድሳ ክንድ ነው።»
(ቡኻሪይ 6227)
በሌላ ሐዲስ ደግሞ እንዲህ አሉ፦ «ከወንድሙ ጋር የተጣላ ሰው ፊቱን አይምታው። አላህ አደምን በመልኩ ፈጥሮታልና። (ሙስሊም 2612)
♦️ በሁለቱም ሰሂህ ሐዲሶች ላይ የተጠቀሰው የአረቢኛ ቃል «ሱራህ» ሲሆን ትርጉሙም መልክ ማለት ነው።
♦️ ኢብን ተይሚያህ ሐዲሱን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦ «በዚህ ሐዲስ ሱራህ ተብሎ የተገለፀው ቃል እንደ ሌሎቹ የአላህ ባህርያት ከፍጡራን ጋር በስም ብቻ የሚመሳሰል ነው።
አላህ አዋቂ ነው፣ ሰሚ ነው፣ ተመልካች ነው፣ ፊት አለው፣ እጅ አለው፣ እግር አለው፣ ከአርሹ በላይ ነው ሲባል ከፍጡራን ጋር ከስም የዘለለ ይመሳሰላል ማለት አይደለም።
ማንኛውም ህልውና ያለው አካልም መገለጫ መልክ ወይም ገፅታ አለው። መልክ ወይም ገፅታ የሌለውን ነገርም አልለ ማለት አንችልም።
ይህ ሐዲስም በተለያዩ ሰሃባዎች የተላለፈና በቀደምት ሰለፎች ምንም ጥያቄ ያላስነሳ ነው።
ነገርግን በ300 ሒጅራ በኋላ የተነሱት ጀህሚያዎች ቃሉ አላህን ከፍጡራን ጋር ያመሳስላል በማለት የተሳሳተ ትርጓሜ ውስጥ ገቡ።» (ነቅድ አል-ተዕሲስ 3/282,396)
♦️ ኢብን ቀይምም እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክ መኖር ከሁለት እጆቹ ከጣቶቹ ወይም ከዓይኖቹ የተለየ እንግዳ ነገር አይደለም። የሚለየው መልክ የሚለው ቃል በቁርአን አለመጠቀሱ ብቻ ነው። ነገርግን በተረጋገጠ ሐዲስ የመጣ ስለሆነ እንዴት የሚል ጥያቄ ሳናነሳ እንቀበለዋለን።» (ተዕዊል ሙኽተሊፍ አል-ሐዲስ 221)
♦️ ኢብን ባዝም ስለ ሐዲሱ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦ «ዑለማዎች እንደፈሰሩት አላህ አደምን የማየት የመስማት የመናገር ችሎታን ሰጥቶታል። እነዚህ ባህሪያት ደግሞ የአላህም ናቸው። ነገርግን የአላህ ባህሪያት ፍፁማዊ ሲሆን የፍጡራን ግን የተገደበ ነው።»
(መጅሙዕ አል-ፈትዋ ኢብን ባዝ 4/226)
♦️ ኢብን ዑሰይሚንም እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ አደምን በመልኩ ፈጠረው ማለት ከእሱ ጋር በስም የሚመሳሰል ባህሪያትን ሰጥቶታል ማለት እንጅ አምሳያው ነው ለማለት አይደለም። ለምሳሌ ጀነት የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ሙሉ ጨረቃን ይመስላሉ ተብሏል። ነገርግን በመልክ አንድ ናቸው ማለትን አያስይዝም።» (ሸርህ አል-አቂዳል አል-ወሰጢያህ 1/107)
ጥቅምት 1/2/2019
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir | 1 067 |
| 9 | ጥያቄ ተሳተፉ‼
ከአላህ ውጭ ባለ ፍጡር መማል "ሺርክ" ነው።⁉
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ቻናል ነው ➢@mustefa_Apologetics | 87 |
| 10 | ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በእስልምና ታሪክ ልዩ እና የተከበረ ስፍራ ቢኖረውም የሀገሪቱ የታሪክ አስተምሮ የተመሠረተው ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት በሚል የተሳሳተ አስተሣሰብ ላይ በመሆኑ ይህን ግዙፍ ሚና እና ተግባር የታሪካችን ላይ ቆርጦ በመጣሉ ሀገሪቱ በእስልምና ታሪክ እና በአለም ሙስሊሞች ፊት ያላትን የተከበረ ስፍራ እና ግርማ ሞገስ እንዳትጎናፀፍ እና ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት ሆኖባት ቆይቷል፡፡
የመፅሐፉ ስም ሥልጤነት እና ኢትዮጵያዊነት
ደራሲ ~አብዱልፈታህ ሁልዳር
ገፅ ~9
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir | 1 024 |
| 11 | በዚህ ቻናል ውስጥ በእንደዚህ አይነት የሚመጣላችሁ የማስታወቂያ ልንኮች ከእኔ ሰይሆን ቴሌግራም እራሱ የሚያስተዋውቃቸው ናቸው እና እኔን አይወክሉም። | 1 039 |
| 12 | ጥያቄ⁉ እውነት/ሀሰት
ኢሥላም የሚለው ቃል ቋንቋዊ ትርጉሙ "መታዘዝ" ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ለብቸኛው ፈጣሪያችን "ለ-አሏህ" እጅ መስጠት መታዘዝ በትዕዛዙ ማደር ማለት ነው⁉ | 96 |
| 13 | ሚስተ እንደተ ቀበጢ ~ እጬኛው ባታኔ፡
አፊየ ጋር ላጂጎት ~ ቦዝገብ አንዘሌኔ።
የደፈ አይኒቃቅሊ ~ የታቼን ሴስትናይ፡
አፍየ አሽረ ጋር~ ለመልከት ዬለቢይ፡
የባደቴ ሚካተ ~ ጭልመ ጠበቀተይ።
<--------------------------------------->
በኒጠን በጪንቂ ~ ቲታፈስ ሂምበ፡
አውጄ ሆንኮንታሌ ~ ሬሬ ቲላጥናበ፡
አለፉያን መጤን ~ ሀምድ የግባይ ለጎሽተ።
<--------------------------------------->
አውጄ ደቺ ሶጃን ~ ቢዤ አጠቀሌነ፡
ሜጠቀነ አገድነ ~ ቅጦ በዘመድነ፡
ተነበሪ አጠቀሌን ~ አላን ላሹክርነ።
<--------------------------------------->
በተጋደልነይ ባድ ~ ቅጦ በቃነነ፡
ፈገግ እላን ደቺ ~ ቂጦ በቃነነ።
<------------------------------------->
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir
ቻናል t.me/αmdαlα nαsir | 1 104 |
| 14 | ጥያቄ ተሳተፉ‼
ከአላህ ውጭ ባለ ፍጡር መማል "ሺርክ" ነው።⁉
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ቻናል ነው ➢@mustefa_Apologetics | 138 |
| 15 | ቴሌግራም Premium የምትጠቀሙ ካላችሁ ቴሌግራም ቻናላችንን boost በማድረግ ለቀጣይ ስራዎቻችን ያግዘን ዘንድ ተባባሩን።//t.me/boost/comparativeRelgion።
የእናንተ አንድ booster ለቻናሉ እይታ ትልቅ ድርሻ ነው። ጀዛከሏሁ ኸይረን። | 1 104 |
| 16 | ጥያቄ ተሳተፉ‼
ከአላህ ውጭ ባለ ፍጡር መማል "ሺርክ" ነው።⁉
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ቻናል ነው ➢@mustefa_Apologetics | 33 |
| 17 | ለምን ጨረቃን ታመልካላችሁ ¹?
እናንተ ሙስሊሞች ጨረቃን ጠብቃችሁ ትፆማላችሁ ጨረቃን ጠብቃችሁ ታፈጥራላችሁ(ትፈታላችሁ) ይህ ጨረቃን ማምለክ አይሆንምን? ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት
በዚህ ርዕስ ለሚነሳው የሚሽነሪዎች ትችት በማያዳግም መልኩ በሁለት ክፍል ማብራሪያ አስቀምጠናል።ይሄንን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ ለሌሎችም ያስነብቡ።
------------------------------------------------
➔ 1«ለምን ጨረቃን ታመልካላችሁ¹?»
➔ 2«ለምን ጨረቃን ታመልካላችሁ²?» | 1 160 |
| 18 | ፈጥኖ ማን ይመልስ !
1ኛ ጥያቄ፦ ያለ አባት ልጂ የወለደች ሴት ማን ትባላለች⁉
የካፊሮች ቅጥፈት መልስ የሚሰጥበታ ቻናል ነው➥@mustefa_Apologetics | 69 |
| 19 | አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድና የተከበራ የንፅፅር ቻናሎች ዌብ ቤተሰቦቼ
ዛሬ በንፅፅሩ ዙሪያ ፈር ቀዳጅ የሆኑት የተወዳጁ ኡስታዛችን➥Eliyah Mahmoud ቻናል የማሳደግ ቻሌጅ ጀምረናል እና ቻናላቸው ላይ ቃላት የማይገልጻዋቸው ትምህርቱች አሉ ጎራ በሉ👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/+ZWiY9YmksY0xOGVk | 1 |
| 20 | በንፅፅር ዘርፍ ጥያቄ ላለችሁ እና መሰራት አለበት የምትሉዋቸውን ጥያቄዎች ካሉ አንድ ሰዎ እስከ አምስት ጥያቄዎችን የሚያቀርብበት ሁኔታ ተመቻችቷል። ስለሆነም ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ(link) ነክታችሁ አጠር እና ግልፅ በሆነ መልኩ ጥያቄያቹሁን በቀረቡ ተረቁጥሮች ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ። ከጥያቄዎቹ መሃል ወሳኝ ወሳኞችን መርጠን ከተለያዩ ኡስታዞች ጋር በመሆን ምላሽ እንሰጥባቸዋለን።
https://forms.gle/aUdcqJAcLuJDZmNv6
ጥያቄ አለኝ ለሚል ሁሉ ፎርሙን ያዳርሱ። | 1 174 |
