fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍሬ ሃይማኖት

ፍሬ ሃይማኖት

رفتن به کانال در Telegram

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

نمایش بیشتر
1 866
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+197 روز
+1430 روز
آرشیو پست ها
✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ አሜን። ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም. | ማክሰኞ 📖 የዕለቱ ወንጌል ማቴዎስ 15፥21–28 > “እወ ጌታዬ፤ ከውሾች እንኳ ከጌታቸው ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ።” > > — ማቴዎስ 15፥27 🌿 የዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርት የከነዓናዊቷ ሴት እምነትና ጽናት ለእኛ ታላቅ ትምህርት ነው። በችግር ጊዜ ተስፋ ሳንቆርጥ፣ በትሕትና እና በጽናት ወደ ጌታ መቅረብ ይገባናል። እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚሰጠንን ምሕረት በእምነት እንጠብቅ። 🙏 የጸሎት ጥሪ ❤️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ማኅበራችንን በጸሎታችሁ አስቡን! እግዚአብሔር የሰንበት ት/ቤታችንን አገልግሎት ይባርክ። ሕፃናቱን በእምነትና በመልካም ሥነ ምግባር ያሳድግ፤ መምህራንንና አገልጋዮችን በጥበብና በትጋት ያጽና። ማኅበራችን በአንድነት እንዲጸናና የተሰጠንን መንፈሳዊ አደራ በታማኝነት እንድንወጣ በጸሎታችሁ አስቡን። 🕊️ የመዝጊያ ጸሎት አቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንደ ከነዓናዊቷ ሴት በእምነት እንድንጸና እርዳን። በችግራችን ጊዜ ተስፋ እንዳንቆርጥ ኃይልን ስጠን። ማኅበራችንን ባርክ፤ ለስምህ ክብር የሚሆን አገልግሎት እንድናቀርብ እርዳን። አሜን። 📢 ይህን መንፈሳዊ መልእክት ለወዳጆቻችሁ ያጋሩ። በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት: የዩቲዩብ ቻናል፡ https://www.youtube.com/@frehaymanot12 የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/frehaymanote የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/share/1CRcXqU4cG/?mibextid=wwXIfr የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@yefrehaymanot?_r=1&_t=ZS-9ARBElH9dEj ድኅረ ገጽ፡ https://frehaymanot.com/

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeGyyRaZ6dR14xVXS1zm3mVe0kUG3vwDAX0rZrxD18ip_smkg/viewform?usp=dialog ውድ የፍሬ ሃይማኖት አባላት ከላይ ያለው ፎርም በሀገር ውስጥም በውጪ ባሉ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለምትማሩ የሰ/ት/ቤታችን አባላት የተዘጋጀ ነው፤ስለዚህ ሁላችሁም እንድትሞሉ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤታችሁ አደራ ትላለች።

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። 📅 የዕለቱ መልእክት | ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. | ሰኞ 📖 የዕለቱ ወንጌል ማቴዎስ 16፥21–28
“ራሱን ይካድ፥ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” — ማቴዎስ 16፥24
🌿 የዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርት የክርስቶስ ተከታይ መሆን በእምነት ቃል ብቻ ሳይሆን፣ በትሕትና፣ በታዛዥነት፣ በትዕግሥትና በፍቅር የሚገለጥ ነው። ጌታችንን መከተል ማለት የራሳችንን ፈቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ማስማማት፣ በመከራ ጊዜ መጽናትና በበጎ ሥራ መትጋት ማለት ነው። 🙏 የጸሎት ጥሪ ❤️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ማኅበራችንን በጸሎታችሁ አስቡን! እግዚአብሔር የሰንበት ት/ቤታችንን አገልግሎት ያበርታ፤ ሕፃናቱን በእምነት፣ በሥነ ምግባርና በመንፈሳዊ እውቀት ያሳድግ። መምህራንንና አገልጋዮችን በጥበብ፣ በፍቅርና በትጋት ያጽና። ማኅበራችን በአንድነት እንዲጸናና የተሰጠንን አደራ በታማኝነት እንድንወጣ በጸሎታችሁ አስቡን። 🕊️ የመዝጊያ ጸሎት አቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ መስቀልህን ተሸክመን በታማኝነት እንድንከተልህ ኃይልን ስጠን። ልባችንን በፍቅርህ ሙላ፤ ማኅበራችንንም ባርክ። ለስምህ ክብር የሚሆን አገልግሎት እንድናቀርብ እርዳን። አሜን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ከታች ባለው ሊንክ በመግባት  ከላይ በስተ ቀኝ በኩል ያለውን ተመዝገብ  የሚለውን በመንካት በመመዝገብ ለ አገልግሎት ብቁ የሚያደርገውን  የ ሰንበት ት\ቤቱን  ዲጂታል መታወቂያ   ያግኙ
https://frehaymanot.com/

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። 📅 ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. 🕊️ እሑድ ⛪ የዕለቱ መታሰቢያ ልደታ ለማርያምና ነቢዩ ኤልያስ። 📖 የዕለቱ ወንጌል ሉቃስ 12፥22–31 🌿 የዛሬ መንፈሳዊ መልዕክት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕለት ኑሮአችን ከመጠን በላይ እንዳንጨነቅ፣ በእግዚአብሔርም እንድንታመን ያስተምረናል። እግዚአብሔር ፍላጎታችንን ያውቃልና በእምነት፣ በጸሎትና በመልካም ሥራ እንመላለስ። 🙏 ዛሬ ጭንቀታችንን ለጌታ እናቅርብ፤ በእርሱም እንታመን። ❤️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ማኅበራችንን በጸሎታችሁ አስቡን! የማኅበራችን አገልግሎት እንዲበረታ፣ ልጆቻችን በእምነትና በሥነ ምግባር እንዲያድጉ፣ መምህራንና አገልጋዮችም በጥበብና በጸጋ እንዲጸኑ ጸሎታችሁን አትለዩን። 🕊️ እግዚአብሔር ለፍሬ ሃይማኖት ሰላም፣ አንድነት፣ ፍቅርና በረከት ይስጥ። አሜን። 🙏 መልካምና የተባረከ የእሑድ ዕለት ይሁንልን።

photo content
+2

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። የ 2019 ዓ.ም የ ፅጌ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት በመደብራችን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል 🥀✨ ‹… በአበባው ወቅት መሆን የ
+9
✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። የ 2019 ዓ.ም   የ ፅጌ  ፆም  የመጀመሪያ ሳምንት   በመደብራችን  ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል  ካቴድራል 🥀✨  ‹… በአበባው ወቅት መሆን የሚገባው ነገር ሁሉ ደረሰ፡፡ የአዕዋፍ ውዳሴ ቃልም በምድራችን ተሰማ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! በአንቺ ሰላምን ማየት እንችል ዘንድ መመለስን ተመለሺ፡፡ ልጅሽን እንዳቀፍሽ፤ ክበቡ ያማረ ወርቅ እንደ ተጎናጸፍሽ የአበባ አክሊል ማርያም ርግቤ፣ ደጌ ሆይ! ነይ፡፡ ሐዋርያት የሚያመሰግኑሽ፤ መላእክት የሚላላኩሽ፤ የሕይወት መሠረት ከሊባኖስ ነይ፡፡ የሴም በረከቱ፤ የአብርሃም መስተንግዶው፤ የይስሐቅ ሽቶው፤ የያዕቆብ መሰላሉ፤ የዮሴፍ አጽናኙ ነይ ....…››አባ ፅጌ💐✨  እንኳን አደረሰን 🥰

የሰንበት ት/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ጉባኤ አገልግሎት ጀመረ መስከረም 24/2019 ዓ.ም የደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት በአዲሱ አወቃቀር የተደራጀው የስራ
የሰንበት ት/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ጉባኤ አገልግሎት ጀመረ መስከረም 24/2019 ዓ.ም የደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት በአዲሱ አወቃቀር የተደራጀው የስራ አስፈጻሚ ጉባኤ አገልግሎት ማከናወን ጀመረ:: የስራ አስፈጻሚ ጉባኤ ከሰንበት ት/ቤቱ ስራ አመራር አባላት ውስጥ በተወከለው በበለጠ ካሳው ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን ፤ ጉባኤው ከሰብሳቢው በተጨማሪ በጸሐፊ እና በሰባት (7) የክፍል ሃላፊዎች የተዋቀረ ነው። ስራ አስፈጻሚ ጉባኤው በስራ አመራር ጉባኤው የሚመረጡ እና ተጠሪነታቸውም ለስራ አመራር ጉባኤው ሆኖ በስራ አመራር ጉባኤው በሚሰጠው አቅጣጫ የሰንበት ት/ቤቱን ዕቅድ በአገልግሎት ክፍሎችን በመጠቀም የሚፈጽም ሲሆን በየሳምንቱ መደበኛ ስብሰባዎችን በማከናወን አገልግሎቱ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል። የስራ አስፈጻሚ ጉባኤው በቀጣይ ክፍሎች አዲስ በጸደቀው መዋቅር መሰረት የንዑስ ክፍሎችን በማደራጀት በሰው ሃብት አስተዳደር ክፍሉ የተመደበላቸውን አገልጋዮች በንዑሳን ክፍላቱ በማደራጀት አገልግሎታቸውን የሚፈጽሙ ይሆናል። እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ፤ ማህበራችንን ያስፋ። የሰንበት ት/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ጉባኤ ጽህፈት ቤት በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት: የዩቲዩብ ቻናል፡ https://www.youtube.com/@frehaymanot12 የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/frehaymanote የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/share/1CRcXqU4cG/?mibextid=wwXIfr የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@yefrehaymanot?_r=1&_t=ZS-9ARBElH9dEj ድኅረ ገጽ፡ https://frehaymanot.com/

Fre- Haymanot .pdf5.34 MB

🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን! 🙏 ✝️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት 📺 የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! ትምህርቶችን፣ መዝሙሮችንና መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ይከታተሉ። 👉 https://www.youtube.com/@frehaymanot12 🌐 ዌብሳይታችንን ይጎብኙ፤ የአባልነት ምዝገባዎንም ያከናውኑ! ይመዝገቡ የሰንበት ት/ቤታችን አባል ይሁኑ የሰንበት ት/ቤታችንን ዲጂታል መታወቂያ ያግኙ 👉 https://frehaymanot.com/ 🔔 ይህን መልእክት ለቤተሰብ፣ ለወዳጅና ለዘመድ ያጋሩ! እግዚአብሔር ይስጥልን! 🙏

.       😭😭😭 የሐዘን መልዕክት 😭😭😭 ""ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው❓❓❓መዝ.88፥48  የወንድማችን የያሬድ አሠፋ ወላጅ እናት በዛሬው ዕለት  ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸውም ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2019ዓ.ም በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል መካነ መቃብር 8:30 የሚፈጸም ስለሆነ የምንችል በሰዓቱ በቦታው  ተገኝተን ሥርዓተ ቀብራቸውን እንድንፈጽም፤ የማንችል ደግሞ በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተን ኃዘንተኞችን እንድናጽናና የአደራ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።  ‼️ አድራሻ፦ ከአንበሳ ጋራዥ ገባ ብሎ ጅጅጋ ማኅበር ከቅዱስ ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት። የሕይወት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር የእናታችንን ነፍስ በአብርሃም፣በይስሐቅና በያዕቆብ አጠገብ በክብር ያሳርፍልን። ከቅዱሳኑ ኅብረት ይደምርልን። ናዛዜ ኅዙናን መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ለቤተ ሰቦቻቸው መጽናናትን ይስጥልን፤ከዳግም ሐዘን ይሰውርልን።

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። 📅 መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. 🕊️ ቅዳሜ — የቅዳሜ ሰንበት ⛪ የዕለቱ መታሰቢያ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅና ቅዱስ ማርቆስ። 📖 የዕለቱ ወንጌል “እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድና በፍቅር መኖር የክርስቲያናዊ ሕይወታችን መሠረት ነው።” 🌿 የዛሬ መንፈሳዊ መልዕክት የተወደዳችሁ ወንድሞችና እኅቶች፣ እግዚአብሔር በፍቅር፣ በአንድነትና በትሕትና እንድንኖር ይፈልጋል። እምነታችን በቃል ብቻ ሳይሆን በመልካም ሥራ፣ በይቅርታና በሌሎችን በመርዳት ይገለጥ። 🙏 ዛሬ ለሌሎች በረከት እንሁን፤ ለሚያስፈልጋቸው እንድረስ፤ በጸሎትም እንጽና። ❤️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ማኅበራችንን በጸሎታችሁ አስቡን! የማኅበራችን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲበረታ፣ ልጆቻችን በእምነትና በሥነ ምግባር እንዲያድጉ፣ መምህራንና አገልጋዮችም በጸጋና በጥበብ እንዲጸኑ ጸሎታችሁን አትለዩን። 🕊️ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅበራችንን ይጠብቅ፤ በፍቅር ያጽናን፤ በመልካም ሥራም ፍሬ እንድናፈራ ይርዳን። አሜን። 🙏 መልካምና የተባረከ የቅዳሜ ዕለት ይሁንልን።

photo content
+7

+9

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን መስከረም 29_01_2019 ዓም   ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ  በ ደብሩ ደጀ ሰላም በተደረገው የ ዕለተ አርብ ጉባኤ     መክፈቻ  መሀረነ አብ ፀሎት እና ፀሎተ ወንጌል   📖 ማቴዎስ 6፥8 “እንግዲህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ አባታችሁ ሳትለምኑት የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።”    በደብሩ ካህናት እና በ ጉባኤው  በታደሙ አባላት እና ምዕመናን   የተደረገ ሲሆን  በመቀጠልም   በ ዘማሪት ቃልኪዳን ደረጄ  ዝማሬ  የቀረበ ሲሆን የዕለቱ ትምህርት  ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕል ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋዋርያት    በሚል  እርዕስ  በ የኔታ ዮሐንስ  የተሰጠ ሲሆን  በመቀጠልም ጉባኤው በፀሎት ተዘግቶል  ለሳምንት በሰላም ያገናኘን https://frehaymanot.com

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። 📅 መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. 🌿 ዓርብ — የዓርብ ጾም 📖 የዕለቱ ወንጌል ማቴዎስ 6፥25 ጀምሮ 🌾 የዛሬ መንፈሳዊ መልዕክት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሕይወታችን ከመጠን በላይ እንዳንጨነቅ፣ በሰማዩ አባታችንም እንድንታመን ያስተምረናል። ስለዚህ በጸሎት፣ በእምነትና በመልካም ሥራ እንመላለስ። 🙏 ዛሬ ጭንቀታችንን ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ በእርሱም እንታመን። ❤️ የፍሬ ሃይማኖት ማኅበራችንንም በጸሎታችሁ አስቡት። የሰንበት ት/ቤታችን አገልግሎት እንዲበረታ፣ መሀበራችን እንዲሰፋ፣ ልጆቻችን በእምነትና በሥነ-ምግባር እንዲያድጉ፣ መምህራንና አገልጋዮችም በጸጋ እንዲጸኑ ጸሎታችሁን አትለዩን።   የ ዛሬ አርብ ጉባኤ እንደይረሳ ማታ 11፡00 – 1፡30  🕊 እግዚአብሔር ለፍሬ ሃይማኖት ሰላም፣ አንድነት፣ ፍቅርና በረከት ይስጥ። አሜን። 🙏 መልካምና የተባረከ የዓርብ ዕለት ይሁንልን።

photo content

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯         🕯🕯🕯ዜና እረፍት🕯🕯🕯 ውድ የፍሬሃይማኖት ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ የ ወንድሞቻችን  አንተነህ ዘውዴ ( መምህር አመሀ ) ገመቹ ዘውዴ እና የ ኃ/ገብሬል ዘውዴ ወላጅ እናት ከዚህ ዓለም ድካም አርፋል። ስለዚህ ዛሬ 9:00 ሰአት በምስራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ስርአተ ቀብሩ ስለሚፈጸም  የቻለ በቀብር ቦታ በመገኘት ያልቻለ በመኖሪያ ቤቻቸው  በመገኘት የሀዘናቸው ተካፋይ እንሁን ። አድራሻ :-መከኒሳ 02 ቀበሌ አካባቢ (ቤታቸው) አምላከ ቅዱሳን የእናታችንን  ነፍስ ይማርልን ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ። አሜን። 📅 መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. 🌿 ሐሙስ ⛪️ የዕለቱ መታሰቢያ አማኑኤል 📖 የዕለቱ ወንጌል “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ።” — ማቴዎስ 6፥33 🌾 የዛሬ መልዕክት ጌታችን ስለ ነገ ከመጨነቅ ይልቅ በእግዚአብሔር እንድንታመን ያስተምረናል። በሕይወታችን እግዚአብሔርን ቀድመን ስንፈልግ፣ እርሱ የሚያስፈልገንን ያውቃል። 🙏 ዛሬ ጭንቀታችንን ትተን በእምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ። ❤️ እንዲሁም የፍሬ ሃይማኖት ማኅበራችንን በጸሎታችሁ አስቡት። የሰንበት ት/ቤታችን አገልግሎት እንዲበረታ፣ ልጆቻችን በእምነት እንዲያድጉ፣ መምህራንና አገልጋዮችም በጸጋ እንዲጸኑ ጸሎታችሁን አትለዩን። 🕊 እግዚአብሔር ለፍሬ ሃይማኖት ሰላም፣ አንድነት፣ ፍቅርና በረከት ይስጥ። አሜን። 🙏 እግዚአብሔር የተቀደሰች ዕለት ይስጠን። አሜን።

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የ2019 የአገልግሎት ዘመን የክፍላት ምደባ ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት እንደምትችሉ እየገለጽን ማንኛውምን ቅሬት ወይም አስተያያት ለማቅረብ የምትፈልጉ አባላት እስከ ዓርብ መስከረም 29 2019 ዓ.ም ድረስ ከ12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤ/ቱ ጽሕፈት ቤት በመገኘት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡ የሰንበት ት/ቤ/ቱ ጽሕፈት ቤት

photo content