cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

Show more
Advertising posts
1 704
Subscribers
+224 hours
+27 days
-630 days
Posts Archive
@ፍኖተ ሕይወት ቀጨኔ መድኃኔ ዓለም
Show all...
ꔰ ꔰꔰእንኳን ለእመቤታችን 2031ኛ ዓመት በዓለ ልደት አደረሳችሁꔰ ꔰꔰ ꔰ  #ልደታ_ለማርያም  ꔰ ꔰ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል? ꔰ ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ ፠ #የግንቦት_ልደታ_ለማርያም_ክብረ_በዓልና_የእመቤታችን_በዓላት በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል›› ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ. 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል፤ ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ. 111፥7በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 33ት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ፠ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል?       በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› ይላል፡፡ 1ኛ ዜና 29፥29 ፠ #የእመቤታችን_የልደቷ_ታሪክ የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ‹‹ሐና››ና ኢያቄም/ዮአኪን በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሐና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሐና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ እርግብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡ ስለ ሐና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ፠ #እመቤታችን_የት_ተወለደች? እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሐሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሐሳቦች የሚያነሱ ሲሆን፤ አንደኛዉ ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች›› የሚል ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ሐሳብ ደግሞ ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሐና የክሩሲድ ቤ/ክ በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡ የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፊንቄ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ›› መኃ. 4፥7 የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምሥጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡ ፠ #የልደታ_ለማርያም_በዓል_መቸ_ነዉ? እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ ና7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅ/ ዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬ.ክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀዉልት በማቆም ዐስር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡ #የድንግል_ማርያም_ልደት_ለምን_ይከበራል? * ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅ/ገብርኤል አንደበት‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› በማለት ተነግሯል (ሉቃ 1-14)፤ ምክንያቱም ቅ/ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ፥ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ፤ የድንግል ማርያም ልደትማ ምንኛ የሚያስደስት ይሆን!?፡፡ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡ * የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል * እመቤታችን  ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፤ በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡ * ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት ‹‹መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››፤ ‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››፤ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ››፤ …. ብለዉ የተናገሩላት ቅ/ድ/ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ደስታችንም ነዉ፡፡ (መዝ. 86፥1፣ ኢሳ. 11፥1፣ መኃ. 4፥7)ጂነአ * በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል፤ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል፡፡ ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ግን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን! ፠ #የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር ሐናና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳውያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ፈንድሻ የሚጥሉ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችኹ🙏 ''ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: '' " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " ነገ ሐሙስ ✨ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም 📍በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ልድትዋን እናከብራለን ።
Show all...
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯         🕯🕯🕯ዜና እረፍት🕯🕯🕯 ውድ የፍሬሃይማኖት ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ  የወንድማችን ስንታየሁ ጤናው እናት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል:: ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ በ5:00 ሰዓት ቀብር በምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ስለሚፈፀም ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን አልባሳት ለብሰን ለስርዓተ ቀብሩ እንድንደርስ ይሁን፡፡ አምላከ ቅዱሳን የእናታችንን ነፍስ ይማርልን ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
Show all...
✝️ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ :: -ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን -በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን -አሰሮ ለሰይጣን -አግዐዞ ለአዳም -ሰላም -እምይእዜሰ -ኮነ -ፍሥሓ ወሰላም ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሰይጣንን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20 በዓሉን የደስታ የሰላም የጤና የበረከት ያድርግልን ለሁላችሁም መልካም በዓል እየተመኘን : ካለን ላይ በማካፈል ነዳያንን እንድናስብ:: ሰንበት ትምህርት ቤቷም በምታደርገው የነዳያን እርዳታ አገልግሎት ላይ እንድንሳተፍ ጥሪ እናስተላልፋለን::
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎትና የንስሐ መርከብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ++++++++++++++++++++++++ - ቅዱስነታቸዉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ ስናስብ የእኛን ትንሳኤ እያሰብን ሊሆን ይገባል በማለት ገልፀዋል። - በዕምነት ትንሳኤ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሳኤ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመላለስ መሆን አለበት ብለዋል። - ቅዱስነታቸዉ ከዚህ በማስቀጠል ከህገ እግዚአብሔር በመራቅ ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዉጭ በሆነ ዝሙት ምክንያት በኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የሚሞተዉ ሰዉ ሀገርንና ድንበርን ለመጠበቅ በየጦር ሜዳዉ ከሚያልቀዉ ሰዉ አይተናነስም በማለት ምዕመናን ከዚህ አፀያፊ ተግባት እንዲታቀቡ አባታዊ መልዕክትን አስተላልፈዉ በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ለ2016 ዓመተ ምህረት የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የቅዱስነታቸዉ በረከት ይደርብን። ንቁ ሚዲያ ርቱዕ የቤተክርስቲያን ልሳን።
Show all...
#ቄጤማ_ለምን? ============= #የቄጤማ_ታሪኩ ከኖኅ ዘመን ጋር የተያያዘ ነው:: የጥፋት ውሃ መጉደሉን ለማወቅ #ኖህ_ርግብን በላካት ግዜ ለምለም ቄጤማና የወይራ ቀንበጥን ባፏ ይሃ መጥታለች:: ኖህም: ርግብ #ቄጤማና_የወይራ ቀንበጥ ይዛ መምጣት የቻለችው ውሃው በመጉደሉ መሆኑን ተረድቶ ከመርከብ ወጥቷል :: ቄጤማና ወይራ ለጥፋት ውሃ መድረቅ #ምስራች_መንገርያ እንደሆነ ሁሉ : አሁንም በክርስቶስ ሞት : ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ :: የምስራች መሆኑን #ለመግለጥ_ቄጤማ ይታሰራል:: #ሰንበት_ዓባይ / #ቅዱስ_ቅዳሜ ================== #የፊተኛይቱ_ጥንተ ቅዳሜ : ፈጣሪ ሥራውን ሰርቶ ያረፈባት ሰንበት ናት::#ይህች_ደግሞ ጌታችን የማዳን ሥራውን ፈጽሞ በከርሰ #መቃብር_አርፎ የዋለባት ስለሆነች ነው:: #ቅዳሜ_ስዑር ============ በዓመት አንዴ #ስለምትጾም_ስዑር ቅዳሜ ተብላለች:: የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው:: ስዑር የሚለውን ቃል #በመያዝ_ቅዳሜ ሹር ይሏታል:: የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው:: ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ : ተሀጺባ በደመ ክርስቶስ 🤲 🤲 🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን ⊹ #አሜን🙏³
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች ➬#ቅዳሜ_ሥዑር ( ቅዳሜ ሹር)‼ ➬የዓብይ ጾም #የመጨረሻዋ_ቅዳሜ ብዙ ስያሜ አላት:: ሊቃውንቱ ዓባይ ሰንበት ይሏታል:: ቅዱስ #ቅዳሜም_ትባላለች:: ቀዳም ሥዑር የሚለውን ስያሜ ተከትሎም ምዕመናን ቅዳሜ ሹር ይሏታል:: #ለምለሚቱ_ቅዳሜም የዚህች ቅዳሜ መጠርያ ነው:: የነዚህ ሁሉ #ስያሜዎች_ምክንያት ይሄንን ይመስላል:: #ገብረ_ሰላመ_በመስቀሉ ============== #ቅዳሜ_ጠዋት_በቤተ_ክርስትያን ጸሎት ይከናወናል:: ሥርዓተ ጸሎቱ ሲያልቅ " ገብረ ሰላመ በመስቀሉ" ( #በመስቀሉ_ሰላምን አደረገ ማለት ነው) እየተባለ ቄጠማ ይታደላል:: ምዕመኑም ቄጠማውን በመሰንጠቅ በግንባር ላይ ያስራል:: ለምለም ቄጤማ #ስለሚታደልባት " ለምለሚቱ ቅዳሜ ትባለለች::
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በሰንበት ትምህርት ቤታችን ፍሬ ሃይማኖት ለነዳያን ማስፈሰኪያ አገልግሎት እየተካሄደ ነው:: ሁላችሁም አባላት መጥታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ እንጠይቃለን::
Show all...
የጌታችን የስቅለት በዓል በካቴድራላችን በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እየተከበረ ይገኛል:: እንኳን አደረሳችሁ::
Show all...
ሰላም እንዴት ናችሁ የፍሬ ሃይማኖት ልጆች :- እንኳን አደረሳችሁ :: እነሆ የምግባረ ሰናይ ክፍል ለትንሳኤ የነድያን ምገባ እና ጉብኝት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ::በመሆኑም ሐሙስ አርብ ቅዳሜ እና እሁድ የተለያዩ ስራዎችን ያከናውናል :: ስለሆነም ሁላችንም ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በመገኘት በአገልግሎቱ ተሳታፊ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲንሆን በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። ከሐሙስ ጀምሮ የሚከናወኑ ተግባራት 👉ለነድያን የሚበተኑ አልባሳትን መምረጥ መለየት እና ማስተካከል 👉አካባቢውን ማስተካከል እና ማጽዳት 👉ሽንኩርት መላጥ 👉ከምእመናን የሚመጡ ቁሳቁሶችን መቀበል ✝️ቅዳሜ ለእሁድ አዳር ✝️ 🐂 በሬ ማረድ 🧅 ሽንኩርት ማቁላላት 🥩 ስጋ መክተፍ 🥘 ወጥ መስራት 🥡 ለፀበልተኞች ምግብ መቋጠር 🥡 የተቋጠረው በተመረጡ ቦታዎች መውሰድ እና ማደል ነድያንን ማስፈሰክ ሌሎችም በርካታ አገልግሎቶች ስላሉ ከሐሙስ ጥዋት ጀምሮ ሙሉ ቀን ስላለን እየመጣን ምንተ ንግበር (ምን እናድርግ) እንበል የበዓሉ የበረከት ተሳታፊ እንሁን ሁላችንም እንገኝ በህብረት እናገልግል ። የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል !
Show all...
ሰላም ለእናንተ ይሁን የፍሬ ሃይማኖት አባላት ለትንሳኤ የሚደረገው የነዳያን ምገባ ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ ነው:: ማገዝ እና መርዳት የምትችሉ ሁላችሁም የበረከት ተሳታፊዎች እንደምትሆኑ በትንሳኤው ባለቤት በልዑል እግዚአብሔር ስም አሳስባለሁ::
Show all...
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ የሐመረ ብርሃን የብራና መፅሀፍት ሥራ ድርጅት "ንፁህ ምንጭ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ በዘመናችን ትልቅ ታሪካዊ አሻራ አሳርፎ የሚያልፍ ከሚያዝያ4 - ሚያዝያ13 የሚቆይ ልዩ ዓውደ ርይ በግዮን ሆቴሌ እንዳዘጋጁ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ሲያስተዋውቁ የቆዩ ሲሆን ስለሆነም ለዚህ ተከታታይ 10 ቀን የሚቆይ አውደ ርይ ከሰንበት ት/ቤታችን የቀን አበል እየተከፈላቸው የሚያገለግሉ አባል ስለሚፈልጉ በአወደ ርዩ ላይ እንደ ኤግዚቢተር ለመሳተፍ የምትፈልጉ አባላት በሰንበት ት/ቤታችን ፅ/ቤት መታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ!      ፍ/ሀ/ሰ/ት/ቤት ጽ/ቤት
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"ተፈፀመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል:: የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈፀመ:: መድኃኒት የሚሆን መስቀልም በቀራንዮ ተተከለ::" መልክአ ሥላሴ እንኳን ለጌታችን ጥንተ ሥቅለት አደረሳችሁ:: ለእኛ ሲል የተንገላታ የተሰቀለ አምላካችን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን :: አገልግሎታችንን ይባርክልን::
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሱባኤ ያሬድ ምዝገባ ሊንኩን ተጭነው ይመዝገቡ! https://janderebaw.org/subae-yared በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የጃን ያሬድ የኅብረ ዝማሬ አገልግሎት ክፍል "ሱባኤ ያሬድ" የተሰኘ ኦርቶዶክሳዊ የቅድመ ዘማሪነት መንፈሳዊ ትምህርት አዘጋጅቶአል:: በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሰባኪነት እና ለክህነት አገልግሎቶች የሚያበቁ ትምህርቶች እንዳሉ ይታወቃል:: ለዘማሪነት አገልግሎት ግን ከጥሩ ድምፅና የማገልገል ፍላጎት በስተቀር ምንም ዓይነት የትምህርት ቅድመ ሁኔታ የለም:: ይህ መሆኑም ቤተ ክርስቲያንን ብዙ ዋጋ ያስከፈለና እያስከፈለ ያለ መሆኑ ይታወቃል:: "እነሆ ውኃ" በሚል የአገልግሎት ፍልስፍና የሚመራው ኢጃት በመዝሙር ዘርፍ ለሚያገለግሉ የነገ ዘማርያን "ሱባኤ ያሬድ" በሚል ርእስ ለዘማሪነት የሚያበቃ በመምህራን ተጠንቶ በተዘጋጀና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተመረመረ ሥርዓተ ትምህርት ተከታታይ ሥልጠና አዘጋጅቶአል:: በትምህርቱ እንዲሳተፉ የሚጠበቁት አካላት በሦስት ወገን የተከፈሉ ናቸው 1. የዜማ ጸጋ ያላቸውና ከዚህ በፊት በየትኛውም የቤተ ክርስቲያንዋ የዝማሬ አገልግሎት ላይ የመሳተፍ ዕድል ላላገኙ ታዳጊዎችና ወጣቶች 2. በመዝሙር አገልግሎት ላይ እያገለገሉ ላሉ ዘማርያን 3. የመዝሙር ግጥምና ዜማ ደራሲዎች ፣ የመዝሙር ቀረጻ ስቱድዮ ባለሙያዎች ፣ የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾችና የመዝሙር ሳውንድ ሲስተም ኦፕሬተሮች ናቸው:: በምዝገባ ፎርሙ ላይ በሚደረግ ማጣሪያ የመጀመሪያውን ዙር ሠልጣኞችን የመመልመል ሥራ ይካሔዳል:: በመሆኑም የዜማ ተሰጥኦ ያላችሁ ምእመናን በአእላፋት ዝማሬና መሰል አገልግሎቶች ላይ በዝማሬ ለማገልገል የሚያስችለውን ሥልጠና ከመጋቢት 15 ጀምሮ በዚሁ ገፅ በሚለቀቀው በOnline ቅጽ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን:: #እንዳልዘምር_የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
Show all...
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የፍሬ   ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ  የሰንበት ት/ቤታችን ኪነጥበብ  ክፍል ነጌ እሁድ በፍሬ ሃይማኖት የጽዋ  ጉባኤ ላይ በዕለቱ  የኪነጥበብ ዝግጅቶችን  እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ስለሆነ  ሁላችሁም   በጉባኤዉ ላይ እንድትገኙልን  ሲል  በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም ጠርተነዎታል!! ሌሎችንም ይጋብዙልን!      ፍ/ሀ/ሰ/ት/ቤት ኪነጥበብ  ዋና ክፍል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
አስቸኳይ ማስታወቂያ የመርሃ ግብር ለውጥ ይመለከታል ለአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች በሙሉ የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ጋር በመሆን ለመምህራን ስልጠና አዘጋጅቷል ። በመሆኑም በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ስር ያላችሁ ሰንበት ት/ት ቤቶች  ይሄንን ስልጠና በመውሰድ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። የስልጠናው መርሃ ግብር አይነት       * የማታ ስልጠና ከ12:00 ጀምሮ እስከ 2:00 የሚሰጥበት እለት       *  ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሳምንት 3 ቀን የሚፈጃው ጊዜ          * ለ  አንድ ወር የስልጠናው ቦታ       * አራት ኪሎ       የሚሰጡት ስልጠናዎች    * ትምህርተ ሀይማኖት    *  ስርዓተ  ቤ/ክ    * የቤ /ክ ታሪክ የምዝገባ ጊዜ እስከ መጋቢት 15 /2016 ዓ.ም ብቻ ማስታወሻ ስልጠናው ለጥቂት መምህራን ብቻ ስለሚሰጥ ቀድማችሁ ተመዝገቡ   ለበለጠ መረጃ 0902638177
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ የሰንበት ት/ቤታችን ኪነጥበብ ክፍል አቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ በእሁድ ጉባኤ ላይ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ይገኛል በመሆኑም ዘዉትር እሁድ ልዩ ልዩ የኪነጥበብ ፕሮግራሞች ስላሉን እርሶም መርሀ ግብሩ ላይ እንዲገኙልን በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም ጠርተነዎታል!! ሌሎችንም ይጋብዙልን! ፍ/ሀ/ሰ/ት/ቤት ኪነጥበብ ዋና ክፍል
Show all...