cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 705
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
+430 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለድንግል_ማርያም_ቤተ ክርስቲያን_ለተከፈተበትና ለከበረችበት፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም ለሆነ #ለአባ_አበስኪሮን_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ መኰንን አርማንዮስ ካሠቃያቸው #ከአስራ_ስድስት_ሺህ_ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
የ2016 ዓ.ም የጌታችን ዕርገት በዓል በካቴድራላችን በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 6 በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል:: ይህን በዓል ባማረ እንዲከበር ያደረጋችሁት የቤተ ክርስቲያን ጌጥ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የስስት ልጆች እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላችሁ::
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የዕርገት በዓል ከሚከበርባቸው 7ቱ አድባራት መካከል አንዱ በሆነው በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የዕርገት በዓልን ያክብሩ:: እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን እያልን የንግሥ በዓሉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየትኞቹ ገዳማትና አድባራት እንደሚከበር ልንጠቁማችሁ ወደድን። 1)ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ልዩ ስም፦ልደታ ክ/ከ ልደታ 2) አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔዓለም 3)መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ 4) የካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ልዩ ስም፡- የካ ወረዳ 9 5)ጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ 08 6) ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ 7)ገዳመ ኢየሱስ ልዩ ስም፡-ልደታ ክ/ከ ሆላንድ ኤምባሲ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፆችን ይጎብኙለ ሌሎችም ያጋሩ TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን ለታማኛና ተጋዳይ ለሆነ ለምሥራቃዊው አባት #ለቅዱስ ያዕቆብ ፣ ለተመረጠ ኃያል ተጋዳይ #ለአባ_ብሶይ_ለዕረፍታቸው_በዓል፣ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅል ለአጎት ልጅ #ለቅዱስ_ቢፋሞን ምስክር ለሆነበትና ሃይማኖቷ ለጸና ምግባርዋም ለቀና ክርስቶስ ላደረባት #ለመነኰሳዪት_ለቅድስት_ማርታ_ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከቅዱሳን_ከመርቆሬዎስና #ከመቃርስ፣ #ከይስሐቅና_ከዕብሎን_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ #ከአብላርዮስም ከምስክርነቱ መታሰቢያና በጌታችን ስም በባሕር ውስጥ በመስጠም ከዐረፈ #ከቅዱስ_መቃርስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿 TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከዘጠኙ የጌታችን የመድሃኒታችን የኢሱስ ክርቶስ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጌታችን የዕርግት በዓል በካቴድራላችን ይከበራል:: ይህን መልእክት ላልሰማም በማሰማት በዕለቱም ተገኝተን ከበረከቱ እንድንሳተፍ :: ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፆችን ይጎብኙለ ሌሎችም ያጋሩ! TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ_ለዕረፍቱ በዓል፣ በኪም ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ሳኑሲ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን አንገቷን በመቆረጥ ሰማዕትነት ለተቀበለች ተጋድይ ለሆነች #ለቅድስት_ሶፍያ ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከአርቃድዮስ፣ ከእህቱ #የዲሙናስና ከግብጻውያን ከንጉሥ ከዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም ከገድላቸው ፍጻሜ፣ #ከአባ_አሞንና ከሚናስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፆችን ይጎብኙለ ሌሎችም ያጋሩ TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
IMG_8641.JPG2.30 KB
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን መጀመርያ ዘማዊ ሆና በንስሓ ከተመረሰች በኋላ #በትኅርምትና_በተጋድሎ_ለሃያ_አምስት ዓመታት ለጸናች #ለቅድስት_ማርታ_ለዕረፍቷ_በዓል፣ #ለኤጲስቆጶስ_ለአባ_ኤላርዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት #ኮርዮን_ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፆችን ይጎብኙለ ሌሎችም ያጋሩ! TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቃን #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ለአክስት_ልጅ እንደ ነቢዩ ኤልያስ እሳት ከሰማይ አውርደው በሸዋ ክፍለ አገር ፈንታሌ ተራራ ላይ ሰሪቲ ለምትባ ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ አራት መቶ ሰባ ሽህ ሦስት መቶ አጋንንት በአንድ ጊዜ ላጠፋ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቀውስጦስ_ዘመሐግሉ ለመታሰቢያ በዐላቸው በሰላም አደረሰን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን እስራኤል ለተባለው ለያዕቆብ ልጅ ለጻድቁ ለቅዱስ ዮሴፍና ለሚስቱ ለቅድስት አሰኔት ለዕረፍት ቀን መታሰቢያ በዓል፣ ከእርሱ ተአምራት ለተገለጡ ለሶርያ ሰው ለሆነ  ለቅዱስ ለውንትዮስ ለቤተ ክርስቲያኑ ለቅዳሴ ቤቱ በዓልና ለመስተጋድል ለሰማዕት ለቅዱስ ቢፋሞን ለዕረፍቱ መታሰቢያና በስሙ ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የመጀመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከላይኛው ግብፅ ከጣሀ አውራጃ ከሆኑ ከባልጀራሞች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕት ቆዝሞስ ከዕረፍቱ መታሰቢያና፣ ከእስክድርያ ከተማ ሰማዕታትና ከሊቀ ጳጳሳት ቶማስም ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 share contact TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን እስራኤል ለተባለው ለያዕቆብ ልጅ ለጻድቁ ለቅዱስ ዮሴፍና ለሚስቱ ለቅድስት አሰኔት ለዕረፍት ቀን መታሰቢያ በዓል፣ ከእርሱ ተአምራት ለተገለጡ ለሶርያ ሰው ለሆነ  ለቅዱስ ለውንትዮስ ለቤተ ክርስቲያኑ ለቅዳሴ ቤቱ በዓልና ለመስተጋድል ለሰማዕት ለቅዱስ ቢፋሞን ለዕረፍቱ መታሰቢያና በስሙ ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የመጀመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከላይኛው ግብፅ ከጣሀ አውራጃ ከሆኑ ከባልጀራሞች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕት ቆዝሞስ ከዕረፍቱ መታሰቢያና፣ ከእስክድርያ ከተማ ሰማዕታትና ከሊቀ ጳጳሳት ቶማስም ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 share contact TELEGRAM https://t.me/+dGBRFEEgQMk2YjY8 https://t.me/frehaymanote FACEBOOK https://www.facebook.com/frehaimanotss TIKTOK www.tiktok.com/@yefrehaymanot
Mostrar todo...
ስንክሳር 1.jpg4.24 KB
mastawekia.jpg1.33 MB
3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤ 6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
Mostrar todo...
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም እንደምን አመሻችሁ ዉድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፍሬ ሀይማኖት ሰ/ት/ቤት ቤተሰቦች ነገ ማለትም በ25/09/2016 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤታችን ኪነጥበብ ክፍል ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ ልዩ ልዩ የኪነጥበብ ምሽት ዝግጅቶችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችሁዋል.ስለሆነም ሁላችሁም በተዘጋጀዉ ፕሮግራም እንድትታደሙልን ስንል በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን፡፡ አዘጋጅ የኪነጥበብ ዋና ክፍል
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ነሐሴ 10/2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12/2005 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርእሰ መንበርነት መርተዋል። 📌የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።” ሐዋርያት ፳፥፳፰ ©️ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ "ኢንኅድግ ማኅበረነ ፍሬ ሃይማኖት
Mostrar todo...
ርክበ ካህናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሔዳል። በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ ጉባዔያት አንደኛ ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን ይከናወናል። ዘንድሮ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ነገ ግንቦት 21/2016 ዓ/ም የሚጀምር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ተከናውኗል። በተጨማሪም፡- 👉የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21/1951 ዓ/ም ጀምሮ አስቸኳይ ጉባዔያትን ሳይጨምር 128 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል። 👉ከእነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔያት መካከል በቅዱሳን ፓትርያርኮች ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል። 👉አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ/ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል።
Mostrar todo...