fa
Feedback
እድገትጮራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት🎓

እድገትጮራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት🎓

رفتن به کانال در Telegram

“Education is the key to unlock the golden door of freedom.” – George Washington Carver

نمایش بیشتر
7 854
مشترکین
+524 ساعت
+297 روز
+14730 روز
آرشیو پست ها
ነገ ሰኞ 11/01/2019 ዓ ም ከ10_12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ደብተር ይሰጣል። ስለዘህ ሁሉም በየክፍሉ በፕሮግራም ይሰጣል ። ከነገ ጀምሮ ትምህርት ሙሉ ቀን ነዉ። እሰካሁን ያልተመዘገበ ነበርም ሆነ አዲሰ ተማሪ ከነገ ጀምሮ ስለሞላ ምዝገባ የለም። የ9ኛ ክፍል የልማት ክፍያ በምሳ ሰዓትና ከትምህርት ሰዓት በኋላ ይከፈላል ። ደረሰኝም ይሰጣል ። ከ2:20 በኋላ አርፍዶ የሚመጣ ተማሪ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ወላጆች ክትትል አድርጉ።ዩኒፎርም በአግባቡ የማይለብስ ነጠቃ ተጀምሯል ። ከ9_12 የስም ስህተት እና የትኛውም ችግር ካለ ለነገ ብቻ 10 ክፍል መምህር ሮቤል እና 9 11 12 ክፍል መምህር በረከት ጋር አስተካክሎ ። ከነገ በኋላ ምንም ችግር ማቅረብ አይቻልም

የ9ኛ ክፍል ብቻ 1 ጉርድ ፎቶ በመያዝና የልማት 1500 ብር በመያዝ 2:30 ተገኙ። ደረሰኝ ለወላጅ መድረስ አሉበት ። ከ10 በላይ ያላችሁ በቀጣይ ፕሮግራም ይወጣል ። 11 አና 12 ክፍል በጠዋት ዩኒፎርም በመልበስ ተገኙ። ካርዱ የሚሰጠው ክረምት ለተማረ ብቻ ነዉ።

11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ክረምት ስትማሩ የነበራችሁ ተማሪዎች ቅዳሜ በቀን 9/01/2019 ካርድ የምትወስዱበት ቀን ነዉ ። ካርዱ የራሱ ጥቅም አለዉ። ከቅዳሜ በኋላ አይሰጥም። በእለቱም የቅዳሜ ትምህርት የሚጀመርበት ስለሆነ ከሌላ ቦታ የመጣችሁ አዲስም ሆነ ነባር ተማሪዎች እንድትገኙ ። በተለይ የክፍል ደረጃ እስከ 30 የሆናችሁ ተገኙ።

ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2
ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን ከመስከረም 7/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ  ሆነው  ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጻል። የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ AMN- መስከረም 6/2019 ዓ.ም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ AMN- መስከረም 6/2019 ዓ.ም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ https://student.ethernet.edu.et/view-placement ላይ ማየት እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ አሳስቧል፡፡ የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያው፤ https://student.ethernet.edu.et/complaints ሲሆን በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን አስገዝቧል፡፡ ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ እንደሚችል ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#ምደባ የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ። ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣
+1
#ምደባ የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ። ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል። ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል። ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን  ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ጥብቅ ማሳሰቢያ _ ፀጉር ሳይስተካከል ዩኒፎርም ሳይለብስ የመጣ ተማሪ ትምህርት ቤት ስለማይገባ ጥንቃቄ ይደረግ _ከትምህርት ቁሳቁስ ወጪ የትኛውም ነገር ይዞ መገኘት በፍፁም የተከለከለ ነዉ። ሞባይል ኢር ፎንና ሌሎችም የሚይዝ ተማሪ ይወረሳል ቀጣይ ሰኔ 5000 ከፍሎ ይወሰዳል ። _ ዩኒፎርም ሹራብ ያለበሰ በእጁ ይዞ የተገኘ ይነጠቃል ። በራሱ ገዝቶ ይለብሳል ። ዩኒፎርም ቀሚስ ያሳጠረ ተማሪ ወይም ሱሪ ከእግሩ ያስጠበበ ወንድ ተማሪ በራሱ ወጪ ይገዛል ።

ወድ ተማሪዎች ነገ ከሁሉም ተማሪ የሚጠበቅና የሚተገበር _ ዩኒፎርም ያለበሰ ፀጉር ያልተስተካከለ ወደ ይመለሳል _ የስም ስህተት እና ሌላ ችግር ያለበት ነገ ብቻ ይስተናገዳል _ ከነገ ጀምሮ ትምህርት ያልተከታተሉ ሙሉ ስሙ ተሸርዞ መሸኛ ይሰጣል _ ነገ ብቻ አየተማራችሁ ደብተር ይሰጣል ። ከነገ ጀምሮ 2:20 ጀምሮ የሚገባ ተማሪ ተመላሽ ይሆናል። _ ሹራብ ራሱ ላይ የሚጠመጥም ያለ ማስጠንቂ ወደ ቤቱ ይሸኛል ። ወላጆችም ተማሪዎችም ትኩረት አድርጉ ህጎች ሁሉ ከነገ ጀምሮ ይተገበራሉ

የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር ተማሪዎች ወ
የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ የመቁረጫ ነጥቡ የተማሪዎች ውጤት፣ የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም እና የሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህን መሰረት በማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

ከ9_12 ክፍል  የትምህርት  ቤታችን ተማሪዎች   ሰኞ  ማለትም  በ4/01/2019  ከጠዋቱ 2:00  ሁሉም   ተማሪ   ዩኒፎርም   በመልበስ  ትምህርት  ቤት   እንድትገኙ።  ዩኒፎርም   ያለበሰ  አይገባም ።   በእለቱ  የተመደባችሁበትን   ሴክሽን   ማረጋገጥና  ወይይት  በማድረግ   ወደ ቤት  ትሄዳላችሁ ።   የስም  ስህተት  ወይም  ስም    ካልተለጠፈ    የሚስተካከለዉ  በእለቱ  ብቻ  ነዉ።

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
+1
ትምህርት ሚኒስቴር፣ የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል። በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስደው በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫቸውን እስካሁን ያላስገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 5 ቀን ማጠናቀቅ ይችላሉ ተብሏል። ተማሪዎች ምርጫቸውን ለማስገባት student.ethernet.edu.et የተሰኘውን ድረ-ገጽ በመጠቀም የራሳቸውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በማስገባት ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ መልዕክት ተላልፏል። #MoE @tikvahethiopia

+4
የ 9ኛ ክፍል አዲስ የተመዘገቡ ተማሪዎች የ Section ምደባ

ለ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ 9ኛ ክፍል አዲስ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን Section እና ሙሉ መረጃ  ከዚህ በላይ ያለውን pdf ፋይል ከፍታችሁ መመልከት ትችላላችሁ በተጨማሪ ሰኞ በየ መማሪያ ክፍላችሁ የሚለጠፍ ይሆናል ::

ከ9_12 ክፍል የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ሰኞ ማለትም በ4/01/2019 ከጠዋቱ 2:00 ሁሉም ተማሪ ዩኒፎርም በመልበስ ትምህርት ቤት እንድትገኙ። ዩኒፎርም ያለበሰ አይገባም ። በእለቱ የተመደባችሁበትን ሴክሽን ማረጋገጥና ወይይት በማድረግ ወደ ቤት ትሄዳላችሁ ። የስም ስህተት ወይም ስም ካልተለጠፈ የሚስተካከለዉ በእለቱ ብቻ ነዉ።

9th new registered 2019.pdf9.45 KB

አስቸኳይ በስብሰባ ምክነያት የነገ ሰኞ ጀምሮ መታወቂያ ይሰጣል የተባለዉ ስለተራዘመ እና የክፍል ድልድል ካለቀ በኋላ መቼ እንደሚሰጥ በቅርብ ቀን ስለምንገልፅ ነገ ሰኞ መምጣት አያስፈልግም ።