ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

እድገትጮራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት🎓

እድገትጮራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት🎓

الذهاب إلى القناة على Telegram

“Education is the key to unlock the golden door of freedom.” – George Washington Carver

إظهار المزيد
7 838
المشتركون
-124 ساعات
-237 أيام
+1730 أيام
أرشيف المشاركات
11እና 12 ክፍል ነገ የቅዳሜ ትምህርት ይቀጥላል ። ሁሉም ይገኝ። አቴንዳስ ይያዛል ። 9_10 ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ ይሰጣል ።

የ11 እና 12ኛ ከሰዓት በኋላ ያልተገኛችሁ ወይም ዛሬ ያልፈሰመ ወላጅ ማምጣት ግዴታ ነዉ። የተገኛችሁ ነገ የጠዋት ትምህርት 1:00 በየክፍላችሁ ተገኙ ። ፊርማ አለ።

የመጨረሻ ሀሙስና አርብ የታደሰ ወይም አዲስ መታወቀያ ተጠናቆ ሁሉም ተማሪ መታወቀያ መያዝ አለበት ። ካልሆነ ተማሪ አይደለም ። ሁለት መታወቀያ የተገኘበት በዲስፕሊን ተጠያቂነት አለው

የ11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተማሪዎች የከሰዓት ትምህርት ላይ የማትገኙ ተማሪዎች አተንዳንስ አየተያዘ ስለሆነ ችግር ውስጥ እንዳትገቡ። ከዚህ በኋላ ማክሰኞ እና ሀሙስ ከሰዓት ያልተገኘ በነጋታወ መታወቂያ ተቀምቶ ወላጅ ያመጣል የቅዳሜ ትምህርት ያልተገኘ ሰኞ ክፍል መግባት አይቻልም ። ሁልጊዜ አቴንዳንስ ይያያዛል ። ሰኞ ረቡዐ አና አርብ ሰልፍ ሳይኖር 1:00 ጀምሮ ክፍል መገኘት ፊርማ መፈረም ተገቢ ነዉ።

ያለ ክፍሉ ገብቶ እየተማረ ያለ ተማሪ ካለ ከትምህርት ቤቱ እውቀና ወጪ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ሃላፊነት ትወስዳላችሁ ። ፍተሻም ይደረጋል ። ከእረፍት እና ምሳ ስዓት ወጪ በረንዳ ላይና ወደ መፀዳጃ በት የሚሄድ ተማሪ መታወቂያ ተቀምቶ ወላጅ ያመጣል ።

በቤተ መፅሃፍት እና በየዛፍ ጥላ ስር በምሳ ሰዓት የምታነቡ የምትጠያየቁ ተማሪዎችን በካሜራ እያዬን ነው ። በርቱ ትምህርት ቤቱም ለእነዚ ተማሪዎች የትኛውንም ያሟላል ። ነገ በዉጤቱ ትረኩበታላችሁ። እርስ በርስ ለመጣላት ለመደባደብ መማር አያስፈልግም ። ከተማሪ የሚጠበቀውን ሁሉ አሟሉ። አንድም ተማሪ እንዲወድቅ እና እንዲባረር አንፈልግም ለዚህ ደግሞ የተማሪ ስነ ምግባር ወሳኝ ነዉ። ከዉጪም ከወስጥም የሚታዪ ችግሮች ካሉ ጥቆማ ስጡ። በየመንገዱ የሚከታተሉ አለ። ሞባይል ይዞ የመጣ ደብተር አሟልቶ ያልመጣ አርማ የሌለዉ ዩኒፎርም እና ቀሪ ያለበት ተማሪ በራሱ ከትምህርት ቤት የተባረረ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ። በርካታ ተማሪዎች ለዉጤት መትጋታችሁን እያየን ነዉ። በርቱ የፊታችን ቅዳሜ ትምህርት ይጀመራል ። አቴንዳንስ ይያዛል ። የመመረቂያ ካርድም ይሰጣል ። በእለቱም ከ1:30_2::30 ቀድመዉ ሀደረሱ ለጊዜው ለ11 እና 12 ክፍል Note pad ይሰጣል ።

ዉድ ተማሪዎች እንዴት ናችሁ ጥብቅ ማሳሰቢያ 🏝በየትኛዉም ጊዜ ፍተሻ ሲደረግ ሞባይል ይዞ የተገኘ 5000 ቅጣት አለዉ። 🏝ዩኒፎርም አርማ የሌለው ወይም ሹራብ ብቻ የለበሰ በራሱ ወጪ ይገዛል ። 🏝ደብተር አሟልቶ የማይዝ አርፍዶ የሚመጣ ተማሪ ወላጁን አምጥቶ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። 🏝በየትኛውም የቡድን ወይም እርስ በርስ ፀብ ዉስጥ የተገኘ ከትምህርት ቤት ይታገዳል ። 🏝 በትምህርት ቤት ውስጥና አካባቢው በካሜራ እይታ ውስጥ ነዉ። የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን ጥቆማ የምትሰጡ ቀጥሉ በጣም እናመሠግናለን ። ከትምህርት ቤት ወጪ በየትኛውም ቦታ ችግር ካለ ፖሊስ እና ክትትሎች ስላሉ መረጃ መስጠት ይቻላል ። እነዚህ የሁልጊዜ የጥንቃቄ መረጃ ናቸዉ መልካም ጊዜ። አርብ እለት በማሪያም አካባቢ እርስ በርስ የተጣሉ እና አብረወ የነበሩ ተማሪዎች ረቡዕ 4:00 በዲሲፕሊን ታይቶ ወሳኔዉ የሚሰጥ ይሆናል ። ፀብ ውስጥ የተገኘ መማር አይችልም ።

ዉድ ተማሪዎች ነገ አርብ በኢሬቻ በአል ምከነያት ትምህርት የለም ። ሰኛ በማለዳ ትምህርት ተገኙ።

ሠላም ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ያለ ክፍሉ የተገኘ ተማሪ ከመዝገብ ላይ ይሰረዛል ። ሸሚዝ ብቻ ለብሶ መምጣት ክልክል ነዉ። አረማ የሌለው ሹራብ መልበስ እና ያልተሟላ ደብተር ይዞ መምጣት አይቻልም ።

ሠላም ተማሪዎች እስካሁን ሹራብ ያልወሰደ የመጨረሻ ነገ ይሆናል ። ትምህርት ም አለ።

ማሳሰቢያ ነገ ሰኞ 18-01-2019 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ስላለ ሁሉም ተማሪ በሰአቱ በተመደበበት ክፍል መገኘት ይኖርበታል ስምጠሪ መምህራን በተለየ መልኩ በየክፍሉ ጠዋት ስም ቁጥጥር ስለሚደረግ ያልተገኘ ተማሪ ስሙ የሚሰረዝ ይሆናል ።

የነገ የቅዳሜ ትምህርት አይሰጥም ።

ጥብቅ ማሳሰቢያ 1- ዩኒፎርም በአግባቡ ያለበሰ አና አርማዉን የቀደደ ይነጠቃል በራሱ ይገዛል ። 2_ የልማትና የማጠናከሪያ ክፍያ ሐሙስና አርብ ብቻ ነዉ። 3_ ቀሪ ያለባችሁ በተለይም 11_12ኛ ተማሪ ስሐበዛ ስማችሁ ይሰረዛል ። 4_ መታወቂያ የሚሰጠው እና የሚታደሰዉ ሐሙስና አረብ ብቻ ነዉ።ከሰኞ ጀምሮ ያለመታወቀያ አይገባም ። 5_ያለ ክፍሉ አየገባ አና እስካሁን በተመደበበት ያልተማረ ስሙ ይሰረዛል ። 6_ ከ2:20" በኋላ የሚመመጣ መግቦት አይችልም ። በዉጪም መቆም አይቻልም ። 7_ በየትኛውም ቦታ ፀብ ወሰጥ የተገኘ መማር አይችልም ። 8_እስካሁን ደብተር ያልወሰደ በራሱ ይገዛል። የተሟላ ደብተርና መፅሃፍ የማይዝ ተማሪ መታወቂያቸውን ይወሰድና ወላጅ አምጥቶ ይፈርማል ። 9 _ወደ ቤት ስትሄዱ በየቦታዉ መቆም መጮህ ካለ ከፖሊስ ወጪ የሚከታተሉ አካላት ስላሉ ተጠንቀቁ ። 10_ በየትኛውም ስርቆት እና የትምህርት ቤቱን ንብረት የማይንኸባከብ በር እና መስኮት የሰበረ የይባረራል። 11_ በትምህርት ሰአት ወጪ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ነዉ።

ስልክ ይዞ የተገኘ ተማሪ አይመለስ

የ10 ክፍል ተማሪዎች ነገ ማክሰኞ እና ረቡእ መታወቂያ በማሳደስ የልማት እና የቲቶር ክፍያ በደረሰኝ ቆርጣችሁ ለቤተሰብ ደረሰኝ የሚሰጥ ይሆናል ። 11 ከፍል ነባሩን በመመለስ አዲስ መታወቂያ ይሰጣል 1 ጉርድ ፎቶ ያስፈልጋል ።

ነገ ሰኞ 11/01/2019 ዓ ም ከ10_12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ደብተር ይሰጣል። ስለዘህ ሁሉም በየክፍሉ በፕሮግራም ይሰጣል ። ከነገ ጀምሮ ትምህርት ሙሉ ቀን ነዉ። እሰካሁን ያልተመዘገበ ነበርም ሆነ አዲሰ ተማሪ ከነገ ጀምሮ ስለሞላ ምዝገባ የለም። የ9ኛ ክፍል የልማት ክፍያ በምሳ ሰዓትና ከትምህርት ሰዓት በኋላ ይከፈላል ። ደረሰኝም ይሰጣል ። ከ2:20 በኋላ አርፍዶ የሚመጣ ተማሪ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ወላጆች ክትትል አድርጉ።ዩኒፎርም በአግባቡ የማይለብስ ነጠቃ ተጀምሯል ። ከ9_12 የስም ስህተት እና የትኛውም ችግር ካለ ለነገ ብቻ 10 ክፍል መምህር ሮቤል እና 9 11 12 ክፍል መምህር በረከት ጋር አስተካክሎ ። ከነገ በኋላ ምንም ችግር ማቅረብ አይቻልም

የ9ኛ ክፍል ብቻ 1 ጉርድ ፎቶ በመያዝና የልማት 1500 ብር በመያዝ 2:30 ተገኙ። ደረሰኝ ለወላጅ መድረስ አሉበት ። ከ10 በላይ ያላችሁ በቀጣይ ፕሮግራም ይወጣል ። 11 አና 12 ክፍል በጠዋት ዩኒፎርም በመልበስ ተገኙ። ካርዱ የሚሰጠው ክረምት ለተማረ ብቻ ነዉ።

11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ክረምት ስትማሩ የነበራችሁ ተማሪዎች ቅዳሜ በቀን 9/01/2019 ካርድ የምትወስዱበት ቀን ነዉ ። ካርዱ የራሱ ጥቅም አለዉ። ከቅዳሜ በኋላ አይሰጥም። በእለቱም የቅዳሜ ትምህርት የሚጀመርበት ስለሆነ ከሌላ ቦታ የመጣችሁ አዲስም ሆነ ነባር ተማሪዎች እንድትገኙ ። በተለይ የክፍል ደረጃ እስከ 30 የሆናችሁ ተገኙ።

ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2
ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን ከመስከረም 7/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ  ሆነው  ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጻል። የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences

እድገትጮራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት🎓 - إحصائيات وتحليلات قناة تيليجرام @chora2020