fa
Feedback
General Wingate Polytechnic college-Official channel

General Wingate Polytechnic college-Official channel

رفتن به کانال در Telegram

ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን። የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام General Wingate Polytechnic college-Official channel

کانال General Wingate Polytechnic college-Official channel (@wingetpolytechniccollege) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 13 132 مشترک است و جایگاه 15 190 را در دسته آموزش و رتبه 2 604 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 13 132 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 24 سپتامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 805 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 32 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 52.45% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 21.93% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 6 871 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 873 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 24 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን። የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 25 سپتامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته آموزش تبدیل کرده‌اند.

13 132
مشترکین
+3224 ساعت
+3467 روز
+80530 روز
آرشیو پست ها
አርብ፡- መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም   ኮሌጁ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር የቤከሪ ሰልጣኞች አስመረቀ!!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፑራቶስ (Puratos Bakery School Charity Organisation) ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን 24 የመጀመሪያ ዙር የቤከሪ ሙያ ሰልጣኞች ዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።   በኬክ፣ ዳቦ እና ቸኮሌት አሰራር የሰለጠኑት እነዚህ ተመራቂዎች የብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘናን ሙሉ በሙሉ ያለፉ ሲሆን የትምህርት ወጪያቸውም ሙሉ በሙሉ በፑራቶስ ተቋም የተሸፈነ ነው።   በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር አኔሊስ ቨርስቲሼል (Annelies Verstichel)፣ የፑራቶስ ድርጅት መስራችና ሃላፊ ኤዲ ቫን ጆል ስግርስ (Jole segeres)፣ የተለያዩ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣ የኮሌጆች አመራሮች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ታዳሚ ሆነዋል።   የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ይህ ስልጠና የመንግሥትና የግል ተቋማትን (PPP) አጋርነት በማጠናከር የክህሎት ክፍተቶችን ለማስቀረት ታስቦ የተዘጋጀ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ማሸጋገር ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዲኑ አክለውም ሰልጣኞቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ከመመረቃቸው በፊት ሙሉ በሙሉ በካርፉር (Carrefour) ኩባንያ የሥራ ዕድል ማግኘታቸው የትብብሩን ስኬታማነት እንደሚያሳይ አብራርተዋል።   ኮሌጁ በቀጣይም ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና በመስጠትና የሰልጣኞችን ቁጥር በማሳደግ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ሙያተኞችን ለማፍራት እየሰራ ይገኛል፡፡    ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ማክሰኞ:- መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ኮሌጁ ከባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ አካሄደ!! ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ ከተማ፣ በኮልፌ ቀራንዮ እና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች ስር ከሚገኙ ከ20 በላይ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ጋር በዛሬው ዕለት ስኬታማ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ ይህ የባለድርሻ አካላት መድረክ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል በሚደረገው ዝግጅት ዙሪያ፣ በቀጣይ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በጋራ ለሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎች አተገባበር ሂደት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለውን ትግበራ ይበልጥ ለማጠናከርና ግንዛቤን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉትና የውይይቱን ዋና ዓላማ ያብራሩት የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ጀቤሳ ሙላቱ ሲሆኑ የመድረኩ አካል በሆነው መርሃ ግብርም የኮሌጁን የስኬት ጉዞ እና አሁን ያለውን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስገነዝብ ሰፊ ገለጻ ቀርቧል፡፡ በሌላ በኩል በ2018 ዓ.ም በነበሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ የመጡ ለውጦችን፣ እንዲሁም የታዩ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን በዝርዝር በሰነድ ያቀረቡት ደግሞ የኮሌጁ የምክር እና ስራ ትስስር ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አዲሱ አዝመራው ናቸው፡፡ አቶ አዲሱ አያይዘውም በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትብብር ለማከናወን የታቀዱ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማመላከት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ተሳታፊ ርዕሳነ መምህራኑም ከኮሌጁ ጋር በቅርበት በመቀናጀት ዘመኑን የዋጀና ብቁ ሀገር ተረካቢ ኃይል ለማፍራት፣ የጋራ ቁሳዊና ሰብዓዊ ግብዓቶችን እንዴት አቀናጅተን መጠቀም እንችላለን በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል፡፡ በተለይም በተማሪዎች ዘንድ የሙያ ስልጠናን በተመለከተ ግንዛቤ በመፍጠር የጎላ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ገንቢ ሀሳቦች ተንሸራሽረዋል፡፡ በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ቅዳሜ:- መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ∙ም   ማስታወቂያ   ምዝገባችሁን ላላከናወናችሁ ነባር ሰልጣኞች በሙሉ  የማጠናቀቂያ ምዝገባ ማስታወቂያ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም ስልጠናችሁን የምትከታተሉ እና በተለያዩ ምክንያቶች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ያልተመዘገባችሁ የቀን፣ የማታ እና የዊኬንድ ነባር ሰልጣኞች በሙሉ የማጠናቀቂያ ምዝገባ የሚከናወነው በቀጣዮቹ መስከረም 11 እና 12 ቀን 2019 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በኮሌጁ ግቢ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። ለማታ ሰልጣኞች የተሰጠ ልዩ ማሳሰቢያ፡- በተጠቀሱት ሁለት ቀናት (መስከረም 11 እና 12) የማታ ሰልጣኞች ምዝገባ እስከ ምሽቱ 12፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል። ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- ·        ከተጠቀሰው የማጠናቀቂያ ጊዜ (ከመስከረም 12) በኋላ ለሚመጣ ማንኛውም ሰልጣኝ የቅጣት ክፍያ የሚኖር መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ·        ሰልጣኞች ለምዝገባ ሲመጡ የመመዝገቢያ ክፍያ ደረሰኝ እና ያሳደሱትን የኮሌጁን መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው። የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለነባር ዊኬንድ ሰልጣኞች ምዝገባ ማስታወቂያ     የነባር ዊኬንድ ሰልጣኞች ምዝገባ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ መግለፃችን ይታወቃል።   ሆኖም መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም እሁድ ቀን በመሆኑና የባንክ አገልግሎት ስለማይኖር ሁላችሁም ነባር የዊኬንድ ሰልጣኞች  ምዝግባችሁን ነገ ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም  እንዲታጠናቅቁ እንገልጻለን።   ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- ምዝገባውን ለማከናወን የመመዝገቢያ ክፍያ በመክፈል የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ማቅረብና ማስመዝገብ አለባችሁ። ማንኛውም ሰልጣኝ ወደ ኮሌጁ ሲመጣ የኮሌጁን መታወቂያ ይዞ መምጣትና ማሳደስ ይጠበቅበታል። የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ማክሰኞ:- መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ∙ም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ጥሪ ቀረበ!! የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቻቸው ጠብቀው በሰላም እንዲከ
+1
ማክሰኞ:- መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ∙ም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ጥሪ ቀረበ!! የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቻቸው ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የሁሉም ወገን ንቁ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ተገለጸ። በውይይቱ ወቅት እንደተገለፀው በመስከረም ወር የሚከበሩት እነዚህ ታላላቅ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የሕዝቦች የጋራ አብሮነትና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ ናቸው ተብሏል። በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ መንግሥት የጸጥታና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን የመስራት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ዜጎች ደግሞ ከስጋትና ከከፋፋይ አስተሳሰቦች የጸዳ አቀባበል በማድረግ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባልም ተብሏል። በበዓላቱ የሚገለጹት የእርቅ፣ የይቅርታና የአብሮነት እሴቶች ለሀገራዊ መግባባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተጠቁሟል። በመጨረሻም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ እያንዳንዱ ዜጋና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪ ተላልፏል። በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት

ማክሰኞ:- ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ∙ም   ኮሌጁ የ«ጽናት ቀን»ን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ!!   ከ200 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች እና በቋሚነት ድጋፍ ለሚደረግላቸው 13 ህፃናት ቤተሰቦች የበዓል መዋያ ስጦታ ተበርክቷል፡፡   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ «የጽናት ቀን»ን እና መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ውስጥ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የደግነት ባህልን የሚያጎላ አርአያነት ያለው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናውኗል።   በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በኮሌጁ ውስጥ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው ከ200 በላይ ሰራተኞች እንዲሁም ኮሌጁ በየወሩ በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ ለሚያሳድጋቸው 13 ህፃናት ቤተሰቦች የበዓል መዋያ የሚሆን የዘይት እና የዱቄት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።   የዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ዋና ዓላማ ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት  በኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ያሉ የሥራ ባልደረቦችን መደገፍ፣ በስራ ቦታ ላይ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን ማጠናከር እንዲሁም «የአንዱን ችግር ሌላው በመጋራት» የጽናትና የአንድነት መንፈስን ማጎልበት እንደሆነ ተገልጿል።   በዕለቱ እንደተገለፀው «ጽናት» በፈተናዎች ፊት ተስፋ አለመቁረጥና ወደፊት መጓዝ ብቻ ሳይሆን እጅ ለእጅ ተያይዞ አብሮ ማደግ፣ እርስ በርስ መደጋገፍና አብሮነትን ማጠናከር ጭምር በመሆኑ በተቋሙ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ወንድማማችነትና አብሮነት የበለጠ ያጠናከረና ለመጪው አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋንና ተነሳሽነትን ይፈጥራል ተብሏል።   የስጦታው ተጠቃሚ የሆኑ የኮሌጁ ሰራተኞችና የህፃናት ቤተሰቦችም በተደረገላቸው ድጋፍና በተቸራቸው ወንድማማችነታዊ ፍቅር የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸው ለኮሌጁ አመራሮችና ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።   «ጽናት ማለት በፈተና ፊት አለመቆም፤ አብሮነትን በማጠናከር ወደፊት መጓዝ ነው!»    "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ማክሰኞ:- ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ∙ም ኮሌጁ የ«ጽናት ቀን»ን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ!! ከ200 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች እና በቋሚነት ድጋፍ ለሚ
+5
ማክሰኞ:- ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ∙ም   ኮሌጁ የ«ጽናት ቀን»ን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ!!   ከ200 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች እና በቋሚነት ድጋፍ ለሚደረግላቸው 13 ህፃናት ቤተሰቦች የበዓል መዋያ ስጦታ ተበርክቷል፡፡   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ «የጽናት ቀን»ን እና መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ውስጥ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የደግነት ባህልን የሚያጎላ አርአያነት ያለው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናውኗል።   በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በኮሌጁ ውስጥ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው ከ200 በላይ ሰራተኞች እንዲሁም ኮሌጁ በየወሩ በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ ለሚያሳድጋቸው 13 ህፃናት ቤተሰቦች የበዓል መዋያ የሚሆን የዘይት እና የዱቄት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።   የዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ዋና ዓላማ ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት  በኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ያሉ የሥራ ባልደረቦችን መደገፍ፣ በስራ ቦታ ላይ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን ማጠናከር እንዲሁም «የአንዱን ችግር ሌላው በመጋራት» የጽናትና የአንድነት መንፈስን ማጎልበት እንደሆነ ተገልጿል።   በዕለቱ እንደተገለፀው «ጽናት» በፈተናዎች ፊት ተስፋ አለመቁረጥና ወደፊት መጓዝ ብቻ ሳይሆን እጅ ለእጅ ተያይዞ አብሮ ማደግ፣ እርስ በርስ መደጋገፍና አብሮነትን ማጠናከር ጭምር በመሆኑ በተቋሙ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ወንድማማችነትና አብሮነት የበለጠ ያጠናከረና ለመጪው አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋንና ተነሳሽነትን ይፈጥራል ተብሏል።   የስጦታው ተጠቃሚ የሆኑ የኮሌጁ ሰራተኞችና የህፃናት ቤተሰቦችም በተደረገላቸው ድጋፍና በተቸራቸው ወንድማማችነታዊ ፍቅር የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸው ለኮሌጁ አመራሮችና ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅ

ሰኞ:- ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ∙ም ኮሌጁ ጳጉሜ 3 «የጽናት ቀን»ን በደመቀ ሁኔታ አከበረ!! ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጳጉሜን ወር የስያሜ መገለጫ አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከ
+5
ሰኞ:- ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ∙ም   ኮሌጁ ጳጉሜ 3 «የጽናት ቀን»ን በደመቀ ሁኔታ አከበረ!!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጳጉሜን ወር የስያሜ መገለጫ አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበሩ ከሚገኙት ሁነቶች መካከል ጳጉሜ 3 «የጽናት ቀን»ን በኮሌጁ ግቢ ውስጥ በልዩ ሁኔታ አክብሯል።   ዕለቱ የሀገር ፍቅር፣ የአንድነት እና የጽናት ተምሳሌትና ወካይ መገለጫ በሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ-ስርዓት የተጀመረ ሲሆን የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሕዝብ መዝሙር ዘምረዋል።   ጽናት የትልቅ ራዕይ መሠረት፣ የለውጥ ኃይል እና የዘላቂ ስኬት መንገድ መሆኑ በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ ተነስቷል። የኮሌጁ ማህበረሰብም እስካሁን ያለውን ትጋት በጽናት በማስቀጠል ለተቋሙ ሁሉን አቀፍ ለውጥ በማምጣት በሀገራዊ ዕድገት ላይ ጉልህ ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።   ኮሌጁ ተቋማዊ አቅሙን አጠናክሮ ብቁና የላቀ ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፍራት የትውልድ ግንባታ ሀላፊነቱን በጽናት ሲወጣ የቆየ አንጋፋ ተቋም ነው።   በዛሬው ዕለትም በ2018 ዓ.ም የነበሩ ስኬቶችን በጽናት አስቀጥሎ ጥራት ያለው ስልጠናን ለመስጠት፣ ተቋሙን ለማዘመን፣ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አምራች ኢንተርፕራይዞች ሐብት እንዲፈጥሩ ለማድረግ ሁሉም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ኪዳኑን አድሷል።   በመጪው 2019 ዓ.ም አዲስ የስልጠና ዘመንም የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ በበለጠ ቁርጠኝነት፣ በጽናትና በትብብር አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን ተገልጿል፡፡ ጽናት በፈተና ፊት አለመቆም፤ ራዕይን ይዞ ወደፊት መጓዝ ነው!   "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ሰኞ:- ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ∙ም የነባር ሰልጣኞች ምዝገባ ማስታወቂያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የሥልጠና ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!!! በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም ስልጠናችሁ
ሰኞ:- ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ∙ም   የነባር ሰልጣኞች ምዝገባ ማስታወቂያ   እንኳን ለ2019 ዓ.ም የሥልጠና ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!!!   በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም ስልጠናችሁን የምትከታተሉ የቀን፣ የማታ እና የዊኬንድ ነባር (ተሻጋሪ) ሰልጣኞች በሙሉ አዲሱ ዓመት የስኬት፣ የዕድገት እና የላቀ ውጤት የምታስመዘግቡበት የተግባር ዘመን እንዲሆንላችሁ እየተመኘን ከዚህ ጋር በተያያዘው የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ መሠረት በኮሌጁ ግቢ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።   የቀን እና ማታ ሰልጣኞች የምዝገባ ፕሮግራም ከመስከረም 4ቀን እስከ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም እንዲሁም የዊኬንድ ሰልጣኞች የምዝገባ ጊዜ ደግሞ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። ከተጠቀሰው ጊዜ አልፎ ለሚመጣ ማንኛውም ሰልጣኝ የቅጣት ክፍያ የሚኖር መሆኑን እናሳውቃለን።   ጥብቅ ማሳሰቢያ፡ ምዝገባውን ለማከናወን የመመዝገቢያ ክፍያ በመክፈል የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ማቅረብና ማስመዝገብ አለባችሁ። ማንኛውም ሰልጣኝ ወደ ኮሌጁ ሲመጣ የኮሌጁን መታወቂያ ይዞ መምጣትና ማሳደስ ይጠበቅበታል። የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

🚀 ጳጉሜ 1የ'ዕምርታ ቀን' 🌟   ከተቋማዊ ደማቅ ስኬቶች መካከል በማንኪያ!   ጳጉሜ 1 "የዕምርታ ቀንን" ስናስብ ኮሌጃችን በተሰናባቹ የበጀት ዓመት በቴክኖሎጂ ማምረት፣ በፈጠራ እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ያስመዘገበውን አኩሪ ስኬት በስሱ እንቃኛለን፡፡   በዘንድሮው ዓመት ጉዟችን ምን አሳካን?     ⚙️ቴክኖሎጂና ፈጠራ፡- በአሰልጣኞቻችንና ሰልጣኞቻችን የተሰሩ ዘመናዊ የማምረቻ ቴክኖሎጂዎችን እና ሀገር በቀል ፈጠራዎችን ወደ ገበያ ማስገባት ችለናል።   🤝 የገበያ ትስስር፡- ምርቶቻችንን በኤግዚቢሽኖች በማስተዋወቅ እኛን የሚያምኑ አዳዲስ አጋሮችን አፍርተናል፤ የደንበኞቻችንንም አድማስ በከፍተኛ ሁኔታ አስፍተናል።   🏭 የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን፡ አብዛኛዎቹ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ ከ338 በላይ ኢንተርፕራይዞች በ4ቱ የድጋፍ አግባቦች መሰረት የቴክኒክና ሙያ እገዛ በማድረግ በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ደማቅ አሻራ አሳርፈናል፡፡   ትናንት ያስመዘገብነው ስኬት ለዛሬ ጥንካሬያችን፣ ለነገው ደግሞ የላቀ ጥልቅ ልምዳችን ነው!!   መልካም የዕምርታ ቀን!

እሁድ:- ጵጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ∙ም   የኮሌጁ ዲራፍቲንግ ሰልጣኞች በጃይካ (JICA) አገር አቀፍ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር የዓመቱ ምርጥ አሸናፊ ሆኑ!!   በጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (JICA) አስተባባሪነት በተካሄደው የ2026 ዓመታዊ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር (Architectural Design Competition) የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኞች በሁለቱም የውድድር ዘርፎችና በልዩ የዓመቱ ምርጥ ዲዛይን ዘርፍ የ1ኛ ደረጃ አንጸባራቂ ድልን በመቀዳጀት የዋንጫና የልዩ የልዩ እውቅና ባለቤት ሆኑ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙና የድራፍቲንግ የስልጠና ዘርፍ ባላቸው ሦስት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች (ጀነራል ዊንጌት፣ ተግባረ-እድ እና አቃቂ) መካከል በደረጃ 4 በተካሄደው በዚህ ውድድር የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተወዳዳሪዎች የላቀ ብቃታቸውን በማስመስከር  ከፍተኛ ውጤቶችን አስመዝግበዋል፡፡   ሰልጣኞቹ በቅልቅል አገልግሎት ህንፃ ዲዛይን (Mixed-Use Design) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ያለውን እንዲሁም በሕዝባዊ አገልግሎት ቦታዎች ዲዛይን (Public Area Design) ደግሞ 1ኛ ደረጃን  ይዞ በማጠናቀቅ አሸናፊ  ሆነዋል፡፡   የዓመቱ ልዩ የዲዛይን እውቅና (Best Perspectives Award 2026) ላይ ደግሞ የኮሌጁ ሰልጣኝ የሆነቺው ሜሮን ደገፉ የዓመቱ ምርጥ የዲዛይን አሸናፊ በመሆን የኮሌጁን ስም በደማቅ ቀለም አፅፋለች፡፡ በዛሬዋ ልዩ የእምርታ ቀን በሆነቺው ዕለት በ'ክሬቲቭ ሀብ ሴንተር' (Creative Hub Center) በተካሄደው  የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር መድረክ ላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች፣ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች፣ የጃይካ (JICA) አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   ውድድሩ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን የእውቀት ሽግግር ማፋጠን፣ የፈጠራ ክህሎታቸውን ማሳደግ እና የሥራ ፈጠራ እድሎችን ማጠናከር (Knowledge Sharing and Entrepreneurship Pathways for TVET Students) ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።   በዕለቱ በተካሄደው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የዓመቱ ምርጥ የዲዛይን አሸናፊ ለሆነችው ሰልጣኝ ሜሮን ደገፉ የዋንጫ፣ የታብሌት፣ የእውቅና ሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁ የኮሌጁ ሰልጣኞችም የዋንጫ፣ የገንዘብና የተለያዩ የስልጠና ቁሳቁስ ማበረታቻ ተሸላሚ ሆነዋል።   ይህ የተመዘገበው አንጸባራቂ ድል ኮሌጃችን ጥራት ያለውና በገበያው ዘንድ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረትና ለሙያ ስልጠና የሰጠውን  ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ነው ተብሏል።   "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ሐሙስ:- ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ∙ም   በፋዌ (FAWE) እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የኮሌጁ አሰልጣኝና ሰልጣኝ እውቅና ተበረከተላቸው፡፡   ኮሌጃችን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል (AICC) በተካሄደው የፋዌ (FAWE) እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን 2ኛ ምዕራፍ የ2026 ዓመታዊ የሰልጣኞች ጉባኤ ላይ በዛሬው ዕለት ተሳትፏል።   የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም (FAWE) ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚተገብረው ይህ የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተተገበረባቸው ሁለት ተቋማት አንዱ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 59 የኮሌጁ ሰልጣኞች የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ናቸው።   በጉባኤው ላይ "የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን የተቅጣሪነት እና የስራ ፈጠራ እድሎች ማጠናከር" (Strengthening Employability and Entrepreneurship Pathways for TVET Students) በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት የተካሄ ሲሆን በውይይቱ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ከፋዌ፣ ከኢንዱስትሪው ዘርፍ እና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ አመራሮች ተሳትፈዋል።    ውይይቱ ሰልጣኞችን ከገበያው ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ክህሎት በማስጨበጥ፣ የኢንዱስትሪ ትስስርን በማስፋት እና ለግል ስራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዙሪያ ያተኮረ ነበር።   ከዕለቱ መርሃ-ግብር ክንዋኔዎች መካከል አንዱ የእውቅና እና ሽልማት ስነ-ስርዓት ሲሆን በዚህም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በላቀ ስራ ሰልጣኞችን በማብቃትና በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የኮሌጁ የፊዚኮ-ኬሚካል አሰልጣኝ ወ/ሮ ጸሐይ አህመድ የታብሌት ሽልማት ሲበረከትላቸው በተመሳሳይ ከተቋማችን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበቺው ሰልጣኝ ሀና ቢራራ የስማርት ፎን ማበረታቻ ተሰጥቷታል፡፡     ፋዌ (FAWE) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች በሚገኙ 6 ፖሊ ቴክኒኮች ላይ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው፡፡     "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"