uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

General Wingate Polytechnic college-Official channel

General Wingate Polytechnic college-Official channel

Kanalga Telegram’da o‘tish

ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን። የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali General Wingate Polytechnic college-Official channel analitikasi

General Wingate Polytechnic college-Official channel (@wingetpolytechniccollege) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 682 obunachidan iborat bo'lib, Taʼlim toifasida 13 880-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 413-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 682 obunachiga ega bo‘ldi.

19 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 1 810 ga, so‘nggi 24 soatda esa 139 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 46.69% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 22.50% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 6 846 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 3 299 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 46 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን። የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 20 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Taʼlim toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

14 682
Obunachilar
+13924 soatlar
+5307 kun
+1 81030 kun
Postlar arxiv
📢 የማስታወቂያ   በኢንፎርሜሽን እና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ዲፓርትመንት ስር ባሉ Web Design and Database Administration እንዲሁም Hardware and Network Servicing በቀኑ የስልጠና መርሃ ግብር ለመሰልጠን ምዝገባ ያደረጋችሁ በሙሉ ዲፓርትመንቱ ከሚቀበለው አቅም በላይ ከፍተኛ ምዝገባ የተከናወነ በመሆኑ በሁለቱም ሙያዎች የተመዘገባችሁ አመልካቾች ነገ ረቡዕ ጠዋት 3፡30 ላይ በኮሌጁ ተገኝታችሁ የመለያ ምዘና (Screening Exam) እንድትወስዱ እናሳስባለን!፡፡   መለያ ፈተናውን በሰዓቱ በመገኘት እንዲትወስዱ እየገለጽን ፈተናው ላይ ያልተገኘ ተመዝጋቢ በ2ኛ እና 3ኛ ምርጫችሁ የምትመደቡ ይሆናል፡፡ ለሁላቺሁም መልካም እድል እንመኛለን!    የኢንፎርሜሽን እና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት!

ማስታወቂያ   📢 ለባችለር ዲግሪ (BSc) ተመዝግባችሁ ለነራቺሁ በሙሉ!   በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካምፓስ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ፕሮግራም ለመማር ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ አመልካቾች በሙሉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ዝርዝር መርሃ ግብር (Exam Schedule) ከዚህ በታች በተገለጸው  መርሃ ግብር መሰረት የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን።   📅 የትምህርት መስኮች እና የፈተና መርሃ ግብር (Exam Schedule) የትምህርት መስክ (Field of Study)፣ ቀን (Date) እና ሰዓት (Time) 1. አውቶሞቲቭ (Automotive) ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት 2. ህንፃ ኮንስትራክሽን (Building Construction) ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 5:30 ሰዓት 3. ሰርቬይንግ (Surveying) ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 7:30 ሰዓት 4. መንገድ ኮንስትራክሽን (Road Construction) ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 7:30 ሰዓት 5. ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ (Electrical Electronics) አርብ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት 6. ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) አርብ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 5:30 ሰዓት   📌 ለተፈታኞች የሚደረጉ ማሳሰቢያዎች ቦታ፡- ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ካምፓስ የሚይዟቸው ነገሮች፡- ወደ ፈተና ክፍል ሲመጡ የምዝገባ ደረሰኝዎን እና ህጋዊ መታወቂያ ካርድ መያዝዎ ግዴታ ነው። ሰዓት አክባሪነት፡- ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት በቦታው በመገኘት የተመደቡበትን የፈተና ክፍል እንዲይዙ እናሳስባለን።   ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911782985 መደወል ይችላሉ።   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ሰኞ:- ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም በኮሌጁ የ2019 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ተጀመረ!! የወጣቶችን ዕውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻውን እየወጣ የሚገኘው ጀነራል ዊ
+5
ሰኞ:- ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም   በኮሌጁ የ2019 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ተጀመረ!!   የወጣቶችን ዕውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻውን እየወጣ የሚገኘው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል።   አዲስ ተመዝጋቢዎች ወደ ኮሌጁ ሲመጡ በየስልጠና ዘርፎቹ ስለሚሰጡ ሙያዎች በዲፓርትመንት ተጠሪዎች በኩል በቂ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው በዲጂታል የምዝገባ ስርዓት አማካኝነት ምዝገባቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እያከናወኑ ይገኛሉ።   ኮሌጁ ለዚህ የትምህርት ዘመን በ12 ዲፓርትመንቶች እና በ29 የሙያ ዘርፎች ስልጠናዎችን ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን ስልጠናዎቹ በመደበኛው የቀን እና በማታው የኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች የሚሰጡ ይሆናል፡፡በሁሉም የስልጠና መርሃ ግብሮች 2,000 ሰልጣኞችን ብቻ በመቀበል ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ታቅዷል።   ለአዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ከተነሱ 6 ወር ያልሞላቸው 2 የ3x4 ጉርድ ፎቶዎች፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ነው፡፡   ሁሉም ተመዝጋቢዎች በደረጃ 4 ስልጠና ላይ እየተመዘገቡ የሚገኙ ሲሆን፣ ተቋማዊ ምዘናዎችን በየደረጃው በማለፍ በደረጃ 4 ማጠናቀቅ ይችላሉ። የደረጃ 4 ስልጠና እንደየዲፓርትመንቱ ሁኔታ ቢለያይም በአማካይ በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።   ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ሰኞ:- ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም በኮሌጁ የ2019 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ተጀመረ!! የወጣቶችን ዕውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻውን እየወጣ የሚገኘው ጀነራል ዊ
+3
ሰኞ:- ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም   በኮሌጁ የ2019 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ተጀመረ!!   የወጣቶችን ዕውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻውን እየወጣ የሚገኘው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል።   አዲስ ተመዝጋቢዎች ወደ ኮሌጁ ሲመጡ በየስልጠና ዘርፎቹ ስለሚሰጡ ሙያዎች በዲፓርትመንት ተጠሪዎች በኩል በቂ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው በዲጂታል የምዝገባ ስርዓት አማካኝነት ምዝገባቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እያከናወኑ ይገኛሉ።   ኮሌጁ ለዚህ የትምህርት ዘመን በ12 ዲፓርትመንቶች እና በ29 የሙያ ዘርፎች ስልጠናዎችን ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን ስልጠናዎቹ በመደበኛው የቀን እና በማታው የኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች የሚሰጡ ይሆናል፡፡በሁሉም የስልጠና መርሃ ግብሮች 2,000 ሰልጣኞችን ብቻ በመቀበል ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ታቅዷል።   ለአዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ከተነሱ 6 ወር ያልሞላቸው 2 የ3x4 ጉርድ ፎቶዎች፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ነው፡፡   ሁሉም ተመዝጋቢዎች በደረጃ 4 ስልጠና ላይ እየተመዘገቡ የሚገኙ ሲሆን፣ ተቋማዊ ምዘናዎችን በየደረጃው በማለፍ በደረጃ 4 ማጠናቀቅ ይችላሉ። የደረጃ 4 ስልጠና እንደየዲፓርትመንቱ ሁኔታ ቢለያይም በአማካይ በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።

📢 ለአዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች በሙሉ ሰዓቱ ደረሰ! የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ12 የስልጠና ዘርፎች እና በ28 ሙያዎች አዳዲስ ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ሰዓታት ቀርተውታል! 📅 የምዝገባ
📢 ለአዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች በሙሉ   ሰዓቱ ደረሰ!   የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ12 የስልጠና ዘርፎች እና በ28 ሙያዎች አዳዲስ ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ሰዓታት ቀርተውታል!   📅 የምዝገባ ቀን፡- ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም 📄 የሚያስፈልጉ መረጃዎች፡  • ከተነሳ 6 ወር ያልሞላው 2 የ3x4 ጉርድ ፎቶ  • ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት • የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ • የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት   "የወደፊት ስኬትዎ በጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ይጀምራል!"

Sunday: October 11, 2026 The college was awarded the recognition of excellence by the European Union and ETF! General Wingate Polytechnic College has received a Certificate of Commitment to Vocational Excellence, which demonstrates its unremitting efforts to provide world-class, quality and competitive vocational training. Our college has made a great history as a country and as the first institution in East Africa by winning this great international certificate given by the European Union (EU) and the European Training Foundation (ETF). This great recognition was achieved because our college successfully passed rigorous international evaluation criteria in terms of teaching-learning process, industry linkages, leadership skills, digitalization and environmental protection (Greening TVET) practices. The European Training Foundation (ETF) which works on updating and quality assurance of vocational training systems, the European Union (EU) which promotes international technology transfer and quality by supporting the program with budget and technology, and the ETF Network of Excellence (ENE), which connects international vocational training centers and exchanges knowledge, experience and technology, gave this recognition. This certificate of excellence confirms that the quality of training provided by our college is in line with the European standards of excellence, expands the opportunities for international participation and experience of trainers and trainees, creates a favorable environment for working together with European institutions and obtains technical and financial support, and opens doors to create additional potential in education technology, greening and innovation. For this historic victory, the visionary and progressive leaders of our college determined Trainers, diligent workers, hard-working trainees and active partners are the result of the concerted joint efforts and fruitful results. "Information Accessibility through Superior Service"

Sunday: October 11, 2026 The college was awarded the recognition of excellence by the European Union and ETF! General Wingate Polytechnic College has received a Certificate of Commitment to Vocational Excellence, which demonstrates its unremitting efforts to provide world-class, quality and competitive vocational training. Our college has made a great history as a country and as the first institution in East Africa by winning this great international certificate given by the European Union (EU) and the European Training Foundation (ETF). This great recognition was achieved because our college successfully passed rigorous international evaluation criteria in terms of teaching-learning process, industry linkages, leadership skills, digitalization and environmental protection (Greening TVET) practices. The European Training Foundation (ETF) which works on updating and quality assurance of vocational training systems, the European Union (EU) which promotes international technology transfer and quality by supporting the program with budget and technology, and the ETF Network of Excellence (ENE), which connects international vocational training centers and exchanges knowledge, experience and technology, gave this recognition. This certificate of excellence confirms that the quality of training provided by our college is in line with the European standards of excellence, expands the opportunities for international participation and experience of trainers and trainees, creates a favorable environment for working together with European institutions and obtains technical and financial support, and opens doors to create additional potential in education technology, greening and innovation. For this historic victory, the visionary and progressive leaders of our college determined Trainers, diligent workers, hard-working trainees and active partners are the result of the concerted joint efforts and fruitful results.

እሁድ:- ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም   ኮሌጁ በአውሮፓ ህብረት እና በኢ.ቲ.ኤፍ (ETF) የልህቀት እውቅና ተጎናፀፈ!!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ የሙያ ስልጠና ለመስጠት ያላሰለሰ ጥረት ያደረገ መሆኑን የሚያሳይ የሙያ ልህቀት ቁርጠኝነት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።   ኮሌጃችን በአውሮፓ ህብረት (EU) እና በአውሮፓ የስልጠና ፋውንዴሽን (European Training Foundation - ETF) የሚበረከተውን ይህንን ታላቅ ዓለም አቀፋዊ የምስክር ወረቀት በመቀዳጀት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ተቋም በመሆን ታላቅ ታሪክ አስመዝግቧል።   ይህ ታላቅ እውቅና የተገኘው ኮሌጃችን ከመማር-ማስተማር ሂደት፣ ከኢንዱስትሪ ትስስር፣ ከአመራር ብቃት፣ ከዲጂታላይዜሽን እና ከአካባቢ ጥበቃ (Greening TVET) አሰራሮች አንፃር ጥብቅና ጥልቅ የሆኑ ዓለም አቀፍ የመገምገሚያ መስፈርቶችን በስኬት በማለፉ ነው።   ይህንን እውቅና በቅንጅት የሰጡት የሙያ ስልጠና ስርዓቶችን ማዘመንና ጥራትን ማረጋገጥ ላይ የሚሰራው የአውሮፓ የስልጠና ፋውንዴሽን (ETF)፣  ፕሮግራሙን በበጀት እና በቴክኒክ በመደገፍ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ጥራት እንዲስፋፋ የሚያደርገው የአውሮፓ ህብረት (EU) እና ዓለም አቀፍ የሙያ ስልጠና ማዕከላትን በማገናኘት የእውቀት፣ የልምድ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ የሚያደርገው የኢ.ቲ.ኤፍ የልህቀት መረብ (ENE) ድርጅቶች ናቸው፡፡   ይህ የልህቀት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ኮሌጃችን የሚሰጠው የስልጠና ጥራት ከአውሮፓ የልህቀት መሠረቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የሚያረጋግጥ፣ የአሰልጣኞችን እና የሰልጣኞችን ዓለም አቀፍ ተሳትፎና የልምድ ማግኛ እድሎችን የሚያሰፋ፣ ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እና የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፎችን ለማግኘት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እንዲሁም በትምህርት ቴክኖሎጂ፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ (Greening) እና በፈጠራ ስራዎች ላይ ተጨማሪ የላቀ አቅም የሚፈጥሩ በሮች ይከፍታል፡፡   ለዚህ ታሪካዊ ድል የኮሌጃችን ባለ ራዕይ ተራማጅ አመራሮች፣ ቆራጥ አሰልጣኞች፣ ትጉህ ሰራተኞች፣ ታታሪ ሰልጣኞች እና ንቁ አጋር አካላት ያደረጋችሁት የተቀናጀ የጋራ ጥረትና የሰመረ ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እያለን ነገም በአዲስ ታሪክና በድርብ ደማቅ ድል እየተገለጥን ዓለማቀፋዊ ስኬቶችን እንጎናፀፋለን፡፡  ።   ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

እሁድ:- ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ኮሌጁ በአውሮፓ ህብረት እና በኢ.ቲ.ኤፍ (ETF) የልህቀት እውቅና ተጎናፀፈ!! ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ጥራት ያለው
እሁድ:- ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም   ኮሌጁ በአውሮፓ ህብረት እና በኢ.ቲ.ኤፍ (ETF) የልህቀት እውቅና ተጎናፀፈ!!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ የሙያ ስልጠና ለመስጠት ያላሰለሰ ጥረት ያደረገ መሆኑን የሚያሳይ የሙያ ልህቀት ቁርጠኝነት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።   ኮሌጃችን በአውሮፓ ህብረት (EU) እና በአውሮፓ የስልጠና ፋውንዴሽን (European Training Foundation - ETF) የሚበረከተውን ይህንን ታላቅ ዓለም አቀፋዊ የምስክር ወረቀት በመቀዳጀት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ተቋም በመሆን ታላቅ ታሪክ አስመዝግቧል።   ይህ ታላቅ እውቅና የተገኘው ኮሌጃችን ከመማር-ማስተማር ሂደት፣ ከኢንዱስትሪ ትስስር፣ ከአመራር ብቃት፣ ከዲጂታላይዜሽን እና ከአካባቢ ጥበቃ (Greening TVET) አሰራሮች አንፃር ጥብቅና ጥልቅ የሆኑ ዓለም አቀፍ የመገምገሚያ መስፈርቶችን በስኬት በማለፉ ነው።   ይህንን እውቅና በቅንጅት የሰጡት የሙያ ስልጠና ስርዓቶችን ማዘመንና ጥራትን ማረጋገጥ ላይ የሚሰራው የአውሮፓ የስልጠና ፋውንዴሽን (ETF)፣  ፕሮግራሙን በበጀት እና በቴክኒክ በመደገፍ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ጥራት እንዲስፋፋ የሚያደርገው የአውሮፓ ህብረት (EU) እና ዓለም አቀፍ የሙያ ስልጠና ማዕከላትን በማገናኘት የእውቀት፣ የልምድ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ የሚያደርገው የኢ.ቲ.ኤፍ የልህቀት መረብ (ENE) ድርጅቶች ናቸው፡፡   ይህ የልህቀት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ኮሌጃችን የሚሰጠው የስልጠና ጥራት ከአውሮፓ የልህቀት መሠረቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የሚያረጋግጥ፣ የአሰልጣኞችን እና የሰልጣኞችን ዓለም አቀፍ ተሳትፎና የልምድ ማግኛ እድሎችን የሚያሰፋ፣ ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እና የቴክኒክና

የተራዘመ የስልጠና ምዝገባ ማስታወቂያ   🎓 ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ! 🎓   የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካምፓስ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ማሰልጠን እንደሚጀምር ተናግረን ምዝገባውም እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን መግለጻችን ይታወቃል፡፡   ይሁን እንጂ የምዝገባው ጊዜው አጭር ስለሆነ ቢራዘምልን የሚለውን ተደጋጋሚ የእናንተን ጥያቄ ተቀብለን እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም  አራዝመናል፡፡  ስለሆነም ነገ ቅዳሜን ጨምሮ ሰኛ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ መጥታችሁ እንዲትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡   ስልጠናው በማታ እና በቅዳሜና እሁድ (Weekend) ፕሮግራሞች  ሲሆን   🛠 የምንሰጣቸው የትምህርት መስኮች (በBSc Degree) ·        አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ (Automotive Technology) ·        ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ (Manufacturing Technology) ·        ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ (Electrical Electronics Technology) ·        ህንፃ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ (Building Construction Technology) ·        መንገድ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ (Road Construction Technology) ·        ሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ (Surveying Technology) ·        ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (Information Technology)   ✅ የመመዝገቢያ መስፈርቶች ·       12ኛ ክፍልን አጠናቀው የዘመኑን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ፣ ·        በተመሳሳይ ሙያ በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4ን አጠናቀው የብቃት ማረጋገጫ (COC) ደረጃ 4 ያላቸው፣ ·        በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሯቸው የ(CGPA) ውጤታቸው 2.00 እና ከዚያ በላይ የሆኑ።   📌 ለምዝገባ ሲመጡ መያዝ ያለብዎት መረጃዎች ·        የትምህርት ማስረጃ ዋናውና 1 የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከክላሴር ጋር፣ ·        2 ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ·        የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 (በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ CBE 1000328857468 ገቢ የተደረገበት ደረሰኝ)።   📅 የምዝገባ ጊዜ ·       እስከ 04/02/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ!    📍 የምዝገባ ቦታ ·       ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ፅ/ቤት።   📍 ለበለጠ መረጃ  ስልክ ቁጥር 0911782985 ይፍጠኑ! ቦታው ሳይሞላ ዛሬውኑ ይመዝገቡ!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

አርብ:- መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም   ኮሌጁ የተግባር ስልጠናን ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ከኢንዱስትሪዎች ጋር ተፈራረመ!!   ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፋዌ ኢትዮጵያ እና ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት የአጋርነት ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ተቋሙ ውጤታማ የሆነ የሰልጣኞች የተግባር ስልጠና (ኢንተርንሺፕ) ሂደት በኢንዱስትሪዎች ውስጥ እንዲከናወን ለማስቻል ነው።   ይህ ፕሮግራም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን እንዲሁም በፋዌ ኢትዮጵያ ትብብር የሚሰራ ሲሆን ፋዌ ኢትዮጵያ በሁለተኛው ፕሮግራሙ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተለይም ስቲም (STEAM) የሰልጣኞችን አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።   ከነዚህም ተጠቃሚዎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ በተጨማሪም አካል ጉዳተኞች እና ከሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን በማካተት አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።   የፋዌ ኢትዮጵያ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ታደሰ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፣ ኢንዱስትሪዎች በተግባር ስልጠናው ዘርፍ ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው በመግለጽ የዚህ ትልቅ ስራ ባለቤት ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።  በሌላ በኩል የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በበኩላቸው "ኮሌጁ ከኢንዱስትሪው የሚፈልገው እናንተ በምትፈልጉት መልክ እና ቅርፅ የተሰሩ ውጤታማ ሰልጣኞችን ማፍራት ነው፤ ስለዚህም ኢንደስትሪው ሰልጣኞችን በመቅረጽ በኩል የራሱን ኃላፊነት መወጣት አለበት" ብለዋል።   በመድረኩ ላይ የፋዌ ኢትዮጵያን አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ የኢንዱስትሪውን እና የኮሌጁን አቅም የሚገመግም ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።    ከኢንዱስትሪ የመጡ ተወካዮች በሰጡት አስተያየት መሰረት በሰልጣኞች ዘንድ የልል ክህሎት (Soft Skill) እንዲሁም የስራ ስነ-ምግባር ላይ ክፍተቶች እንዳይኖሩ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው እንደሚገባ አንስተዋል።   በመጨረሻም የተግባር ስልጠናውን ውጤታማ ለማድረግና የጋራ አሰራርን ለመዘርጋት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ (MOU) የኢንዱስትሪ ተወካዮች በፊርማ አጽድቀዋል።                                      ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››