fa
Feedback
Abu Hayder Aliy

Abu Hayder Aliy

رفتن به کانال در Telegram

نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
569
مشترکین
+1224 ساعت
+187 روز
+4930 روز
آرشیو پست ها
🛑 من كـــــــان يعبد محمــــداً ﷺ فإن محمداً ﷺ قـد مـ ـات و من كان يعبـــد اللّه فإن اللّه حـي لا يمـ ـوت 🍁⁉️ الشيخ صالح العصيمي حفظه اللّه ➥

photo content
+2

🛑 إمــرأة تذهب إلى رجل أجنبي ليعلمها القيادة ⁉️ الشيخ محمد بن صالح العثيمين رحمه اللّه https://t.me/abu_hayder_aliy

🛑 الغلـــ ـو في النبــــي ﷺ 🍁⁉️ الشيخ صالح الفوزان حفظه اللّه https://t.me/abu_hayder_aliy

Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል 🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

አዳምጡ ሙስጦፋ አብደላህ ስለ ሸይኽ ረቢዕ አላህ ይዘንላቸውና ታላላቅ ዖለማዎች ውዳሴ የቸሩትን ታላቅ ዓሊም ምን ያክል ክብር በሚጥስ መልኩ ሲናገር ! አላህ ልቦና ይስጠው ለሱም ለተከታዮቹም هذا هو عين التطاول በተለያየ ጊዜ የፊትና ሰዎች አይወጡም ራሲኽ የሆኑ ዑለማዋች ላይ በምላሳቸው ድንበር ያለፉ ሲሆኑ ቢደመጡ እንጂ ወይ በክብራቸው ላይ በመረማመድ ወይም እነሱን ከድንበር በላይ ከፍ በማድረግ https://t.me/ustaz_kadir_Farwa_grerup

القارئ: ياسر الدوسري 🍃  أرح سمعك 🥀 إن الله وملائكته يصلون على النبي https://t.me/abu_hayder_aliy

Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿 ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰 «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ   🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ ﷺ 🌹 .................🌹 ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹  ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹 በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!                 https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

    🎁የሰርግ ፕሮግራም💍🎁 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የወንድማችን አቡ አብደላህ እና የዉዷ እህታችን ኡሙ አብደላህ የሰርግ ፕሮግራም አስመልክቶ  የተዘጋጀ ታላቅ የደአዋ ፕሮግራም ሙሺሪት ሙሺራዉ بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير ⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ➊ ሸይኽ ሰኢድ አቡ ሙሀመድ 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ➋ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ                🔖ርዕስ ​"በሰዓቱ ❸ ኡስታዝ አቡ አምር 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❹ ወንድም  አቡ ሂበቱላህ 🔖ርዕስ "በሰዓቱ ❺ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን             🔖ርዕስ በሰዓቱ ❻ ወንድም አቡ ሹራ 🔖ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❼ ወንድም ኑረድን አቡ ፋሩቅ 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል ❽ ኡስታዝ አቡ ሶፍያን 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል ❾ ወንድም አንሶር ሙሀመድ 🔖 ርዕስ "የመልካም ሚስት መገለጫ" 📖ቲላዋ የሚጋብዙ ወንድሞች 🎤አቡ ኢምራን 🎤ወንድም አቡ ሀይደር 🎤 ወንድም አቡ ፈዉዛን 🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ ማሂ 🗓ቀን እለት ሀሙስ ምሽት             ⏰ ሰአት           🇪🇹በኢቶ 3:00            🇸🇦በሳዑዲ 9:00              🇵🇸በዱባይ 10:00 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇                 👇👇👇👇👇 https://t.me/+yxwTU-Sx-7szZGVk https://t.me/+yxwTU-Sx-7szZGVk

ሰው መሳይ በሸንጎ ~ ከውጭ ትጥቅ አሳማሪ ብንሆንም፣ ውስጣችን ክፋት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት ያረገዘ ከሆነ ራሳችንን እየሸወድን ነው። ለአላህ እንደሆነ የሚሰወረው ነገር የለም። የውስጣችንም እንደ ውጫችን
ሰው መሳይ በሸንጎ ~ ከውጭ ትጥቅ አሳማሪ ብንሆንም፣ ውስጣችን ክፋት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት ያረገዘ ከሆነ ራሳችንን እየሸወድን ነው። ለአላህ እንደሆነ የሚሰወረው ነገር የለም። የውስጣችንም እንደ ውጫችን ግልፅ ነው። ለሰዎች ጥሩ መስሎ ለመታየት ከመልፋት ይልቅ የእውነት ጥሩ ሆኖ መገኘት ነው ትርጉም ያለው። መቼስ መሆንና መምሰል የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ግልፅ ነው። ከሰው ፊት ጤነኛ፣ ኸይረኛ፣ አላህን ፈሪ የምንመስል ከሰው እይታ ገለል ስንል ሰቅጣጭ ወንጀሎችን የምናጨማልቅ ብዙ ሰዎች አለን። አውዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "በአደባባይ የአላህ ወሊይ፣ በድብቅ ግን ጠላቱ አትሁን።" [አዝ-ዙህድ፣ ኢማም አሕመድ] በዚህ ዘመን እንደ ልብ ትኩረት ያጣ ነገር የለም። ለውጫዊ ገፅታችን የምንጨነቀውን ሩብ ታክል እንኳ ለልባችን እያሰብን አይደለም። ልብ ካልተገራ እና አላህን ከመፍራት ከተራቆተ ደግሞ ሌላው ሰውነት ቀፎ ነው፣ ቢከፍቱት ተልባ! ብዙዎቻችን ሰው ሰው እንሸታለን እንጂ ሰውነት አጥተናል። እንደ ሰው እንተውናለን እንጂ ባህሪያችን ከአው^ሬ የከፋ ሆኗል። በልብስና በምላስ የተሸፈነው አው^ሬነታችን በተለያዩ ክስተቶች ጥፍሩን ቀስሮ፣ ጥርሱን አግጥጦ ሲወጣ እየታየ ነው። ሁላችንም ሰባኪ ሆነናል። በምናውቃት መስራት ላይ ግን የለንም። እንዲሁ ወሬ ብቻ! ኢላ መታ?! (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 03/2015) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ!!!! "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው፣ ያንን መልካም ስራ እንደሰራው ሰው አይነት ምንዳ (አጅር) አለው።"

የኢትዮጵያን ፖለቲካ አጥብቄ እንድጠላው የሚያደርገኝ ህዝቡን እንዳለ በከፍተኛ የዘረኝነት ልክፍት ያበላሸ በመሆኑ ነው። ዘረኝነትኮ ማንም ጋር ሊኖር ይችላል። አንድ ሰው ግጭት ወይም ሌላ ሰበብ ኖሮት የዘር መድሎ ቢያሳይ ስሜታዊ የሚያደርግ ወቅታዊ ክስተት ቢገጥም ነውና የሆነ መልክ አለው፣ ዑዝር ባይሆንም። ምንም ያላደረገን አካል እንዲሁ ዘሩ ስለተየ ብቻ ማንገላታት፣ ከዚህም አልፎ ህይወቱን መቅጠፍ፣ ንብረቱን መዝረፍ ምን ምክንያት ሰበብ ሊሆነው ይችላል?! በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ችግሩ በዚህ ደረጃ ደርሶ እንኳ በደዕዋ ላይ የተሰማሩ አካላት ችግሩን ለመጋፈጥ ድፍረትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌላቸው መሆኑ ነው። አላሁልሙስተዓን!! ወላሂ ጤነኛ ያልሆነ የዘር ውግንና ለምንቆረቆርለት ህዝብም አይጠቅምም። ወገናችን ሌሎች ዘንድ በጅምላ እንዲጠላ ነው የሚያደርገው። የዘር ጥቃት የተዳፈነ እሳት ነው። ወቅት እየጠበቀ ይቀጣጠላል። ለማጥፋትም አይመችም። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወንድምህን በዳይም ተበዳይም ቢሆን እርዳው።" አሉ። "ተበዳይ ሲሆንስ እሺ። በዳይ ሲሆን እንዴት ነው?" ተብለው ሲጠየቁ "ከበደሉ (እንዲታቀብ) እጁን ልትይዘው ነው" አሉ። እንደ ሙስሊም የህይወታችን መርህ ሊሆን የሚገባው ይሄ ነው። አጥፊዎች እህት ወንድሞቻችን ቢሆኑ እንኳ ውግንና ሳይዘን በፍትህ ልንቆም ይገባል። ተጎጂዎች ጠላቶች ቢሆኑ እንኳ ጥላቻችን ፍትህ እንድናዛባ ሊያደርገን አይገባም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

Repost from N/a
⭕️ይህ መልዕክት ለሱና ቻናል ባለቤቶች ⭕️ ➲ ቻናላችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ  መልክ ጀምረናል 🛑በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  ⚡️ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا ۝ يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ﴾. فقوله تعالى: ﴿وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا﴾، أي: قولوا قولًا مستقيمًا موافقًا للحق، قولًا طيبًا نافعًا، بعيدًا عن الكذب والغيبة والنميمة والسب والشتم وسائر الكلام السيئ. فالمؤمن ينبغي أن يحفظ لسانه، فإذا أراد أن يتكلم سأل نفسه: هل هذا الكلام خير أم شر؟ هل يرضي الله أم يسخطه؟ فإن كان الكلام خيرًا تكلم، وإن كان شرًّا أمسك. وقد قال النبي ﷺ: «مَن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليقل خيرًا أو ليصمت». ومن أعظم الأحاديث في بيان خطورة الكلمة قول النبي ﷺ: «إن العبد ليتكلم بالكلمة من رضوان الله، لا يلقي لها بالًا، يرفع الله بها درجات، وإن العبد ليتكلم بالكلمة من سخط الله، لا يلقي لها بالًا، يهوي بها في جهنم». رواه البخاري. تأملوا هذا الحديث، عباد الله! قد يتكلم الإنسان بكلمة طيبة يرضى الله عنها، ولا يظن أن لها شأنًا كبيرًا، فيرفع الله بها درجاته. فقد تكون كلمة نصح، أو كلمة تعليم، أو كلمة إصلاح بين الناس، أو كلمة تفرّج عن مسلم كربته، أو كلمة تذكّر بالله والآخرة. وفي المقابل، قد يتكلم الإنسان بكلمة سيئة تسخط الله، ولا يهتم بها ولا يظن أنها خطيرة، فتكون سببًا في هلاكه ودخوله النار. فلا تقل: إنها مجرد كلمة! فإن الكلمة قد تكون عظيمة عند الله، وقد ترفعك درجات، وقد تكون سببًا في هلاكك. ولهذا قال الله تعالى: ﴿مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ﴾. فكل كلمة يتكلم بها الإنسان مكتوبة عليه. https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

የሰዎች ህይወት እና ንብረት በሌላው ላይ ሐራም ነው! ~ ከአቡ በክረህ (አላህ ይውደድላቸው) ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ " إِنَّ دِمَاءَكُمْ وَأَمْوَالَكُمْ وَأَعْرَاضَكُمْ بَيْنَكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا، فِي شَهْرِكُمْ هَذَا، فِي بَلَدِكُمْ هَذَا " “ደማችሁ (ሕይወታችሁ)፣ ንብረታችሁ እና ክብራችሁ በእናንተ ላይ እርም (የተከለከለ) ነው፤ ልክ በዚህ ወራችሁ እና በዚህ አገራችሁ ውስጥ ይሄ ቀናችሁ እንዳለው ክብር።” [ቡኻሪይ (39) ከዘገቡት ሐዲሥ የተወሰደ ነው። ሙስሊምም (2816) ዘግበውታል።] * ቡኻሪይ (7078) ውስጥ በሚገኝ ሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ የሚል አለ፦ " وَأَبْشَارَكُمْ، عَلَيْكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا " “አካሎቻችሁም እንዲሁ እንደዚህ ቀናችሁ ክብር የተከበሩ ናቸው።” * በተጨማሪም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ " لَا تَرْجِعُوا بَعْدِي كُفَّارًا، يَضْرِبُ بَعْضُكُمْ رِقَابَ بَعْضٍ " “ከኔ በኋላ ከፊላችሁ የከፊሉ አንገት የሚሰይፍ ከሃዲዎች ሆናችሁ አትመለሱ።” [ቡኻሪይ (67 እና 7078] እና ሙስሊም (1679) ዘግበውታል።] የቃላት መፍቻ፦ = 1. “ይሄ ቀናችሁ” የተባለው ዙልሒጃ አስር ሲሆን የዒደል አድሓ የመጀመሪያው ቀን ነው። 2. “በዚህ ወራችሁ” የተባለው የተከበረው የዙልሒጃ ወር ነው። 3. “በዚህ ሃገራችሁ” የተባለው የተከበረው የአላህ ቤት፣ የተከበረችዋ መካ ለማለት ነው። ከሐዲሡ የሚወሰዱ ትምህርቶች፦ = 1. የሙስሊሞች ደም ፈፅሞ ሊደፈር የማይገባው እርም እንዲሁም በጣም የተከበረ እንደሆነ፣ 2. የሰዎችን ንብረትና ክብር መዳፈር ክልክል እንደሆነ እና 3. የሙስሊም ደሙ፣ ንብረቱ እና ክብሩ ከተከበረው ሃገር፣ ከተከበረው ወር እና ከተከበረው ቀን ክብር በላይ እንደሆነ እንወስዳለን። ዐብዱላህ ብኑ ዐምር ብኒል ዓስ (አላህ ይውደድላቸው) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ " وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَقَتْلُ مُؤْمِنٍ أَعْظَمُ عِنْدَ اللهِ مِنْ ‌زَوَالِ ‌الدُّنْيَا " “ነፍሴ በእጁ በሆነችው (ጌታዬ) እምላለሁ! አንድን አማኝ መግደል አላህ ዘንድ ከድፍን ዓለም መጥፋት የከፋ ነው።” [ነሳኢይ (3986) ዘግበውታል።] * ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም እንዲሁ ሊበደሉ አይገባም። ይህንን የሚመለከት ማስረጃ ሌላ ጊዜ አቀርባለሁ፣ ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ሰደቃ የሚሰጥ የሆነ ሰው የሚሰጠው ሰደቃ በምስኪኑ እጅ ከማረፉ በፊት በአላህ እጅ ላይ እንደሚያርፍለት ቢያውቅ ኖሮ ተቀባዩ  ከሚያገኘው የደስታ ስሜት የበለጠ ሰጪው  ይደሰት ነበር።» 📚 ۞ مدارج السالكين【1/26】۞

“ከነብዩ ﷺ ቤተሰቦች እና ከተከታዮቻቸው ውስጥ ‘መውሊድ ይፈቀዳል’ ያለ አንድ እንኳን እንደሌለ ከተገለፀልህ ከነሱ ውጭ ያሉትን አቋም ልታውቅ ከፈለግክ ከሁሉም ሙስሊሞች ዘንድ ቢድዐ በመሆኑ ላይ ኢጅማዕ እንዳለ አረጋግጠንልሃል እንላለን፡፡” [ገፅ፡ 1091] 8. መውሊድ ውስጥ ሺርክ ወይም ሌላ ጥፋቶች ከሌሉበትስ ይፈቀዳል? ሸውካኒይ፡- “ ‘መውሊዱ ላይ ለምግብ መሰባሰብና ዚክር ብቻ ከሆነ ይፈቀዳል፣ አብረውት የሚያጅቡት ነገሮች ክልክል መሆናቸው ክልክልነቱን አያስይዝም’ የሚሉ ሰዎች ማመሀኛ ፉርሽነቱ ከዚህ ላይ ግልፅ ይሆንልሀል፡፡ ምክንያቱም እኛ እራስህ እንዳመንከው መውሊድ ቢድዐ ከመሆኑ ጋር በልምድ ከብዙ መጥፎ ነገሮች ጋር የተቆራኘና ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ ሆኗል እንላለንና፡፡ ደግሞም ከምግብና ከዚክር ውጭ ያሉ ነገሮችን የማያካትቱ መውሊዶችን ማግኘት ከቀይ ድኝ የበለጠ ፈታኝ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1090 - 1091] “የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ ጋር ሲነፃፀሩ ጥቂቶች ከመሆናቸው ጋር ለምግብና ለዚክር ብቻ በሚል መስፈርት ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ ይሄው አሳውቀንሃል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት ላይ አንድም አይፃረርም፡፡ ዛሬ የሚከሰተው የዚህ አይነቱ (ጥፋቱ የበዛበት) መውሊድ ግን በወጥ ስምምነት የተከለከለ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1098 - 1099] “ወደ ጥፋት የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋትና ወደማይፈቀድ ነገር መንጠላጠያ ገመዶችን መቁረጥ ብዙሃን ምሁራን እርግጠኛ ከሆኑባቸው ወሳኝ ሸሪዐዊ መርሆዎች ውስጥ ነው፡፡ አንተ እራስህ እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ቀርቶህ ከሆነ ይህንን ሐቅ አትክድም፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] 9. መውሊድ የልዩነት መንስኤ ነውን? ሸውካኒይ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል፡፡ በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] 10. መውሊድ ውስጥ አስቀያሚ ጥፋቶች ከኖሩበትስ? ሸውካኒይ፡- “ሀሳቡ ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ በርግጥም አሳውቀንሃል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ አንድም የሚወዛገብ የለም፡፡ የዚህ አይነቱ ዛሬ እየተከሰተ ያለው መውሊድ በዑለማእ ስምምነት ክልክል ነው፡፡ ርእሱ የፈቃጆቹን ንግግሮች እያቀረቡ ዘለግ ባለ መልኩ መመለስ የሚጠይቅ ቢሆንም ለጊዜው እዚህ ላይ ይበቃናል፡፡” ከዚያም በሙታን ላይ የሚፈፀመውን ሺርክና የጣኦት አምልኮ ጠቅሰው በጥብቅ ከኮነኑ በኋላ “እኛ ማስጠንቀቅና ማድረስ እንጂ ሌላ አቅም የለንም፡፡ ይህንን ይሄው አድርገናል፡፡ አላህ ሆይ! ለዲንህ ተቆጣ! ከነዚህ ቀብር አምላኪ ሸይጧኖች ቆሻሻም አፅዳው፡፡ ከነዚህ የጠንካራውን እምነት ንፅህና ካጠለሹ ቆሻሻዎችም አሳርፈን፡፡” [ገፅ፡ 1095 - 1101] (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 25/2012) = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ሸውካኒይ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት) ~ ሙሐመድ ብኑ ዐሊ አሽ-ሸውካኒይ በ1250 ሂ. የሞቱ ታላቅ የመናዊ ዓሊም ናቸው፡፡ በሰፊው የሚታወቁ ስለሆኑ እሳቸውን በማስተዋወቅ ረጅሙን ፅሑፌን ይበልጥ ማስረዘም አልሻም፡፡ ሸውካኒይ መውሊድ ላይ እጅግ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ዛሬ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው መውሊድ ተኮር ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን በመምዘዝ በሸውካኒይ ንግግር ምላሽ እሰጣለሁ፡፡ ሙሉ ንግግራቸውን መመልከት የፈለገ ሰው “አልፈትሑ ረባኒይ ሚን ፈታዋ አልኢማሚ ሸውካኒይ” በተሰኘው የፈትዋ መድብላቸው ውስጥ ሁለተኛውን ጥራዝ ከገፅ 1087 - 1101 ድረስ መመልከት ይችላል፡፡ (ፅሑፉ ስለ ረዘመ ዐረብኛውን ማካተት አልቻልኩም፡፡) 1. መውሊድ የሸሪዐ መነሻ አለውን? ሸውካኒይ፡- “እስካሁን ድረስ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከኢጅማዕም፣ ከቂያስም (ንፅፅራዊ ምልከታም) መሰረት እንዳለው የሚያመላክት መረጃ አላገኘሁለትም፡፡” [ገፅ፡ 2/1087] 2. መውሊድን ሰለፎች ያውቁታል? ሸውካኒይ፡- “እንዲያውም ከዘመናት ሁሉ ምርጡ በሆነው (የሶሐቦች) ዘመንም፣ ከነሱ ቀጥሎ በነበሩትም፣ ቀጥሎ በነበሩትም (ዘመን) እንዳልነበር ሙስሊሞች ወጥ አቋም ይዘዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡)” [ገፅ፡ 2/1087] 3. ቢድዐ በመሆኑ ላይ ልዩነት አለ? ሸውካኒይ፡- “ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድ እንኳን የተቃወመ የለም፡፡” [ገፅ፡ 2/1088] “ይሄ ነገር ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሁሉም ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳለበት አረጋግጠንልሃል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] 4. መውሊድን በሚደግፉ መሻይኾች ማስፈራራት ያዋጣል? ሸውካኒይ፡- “በምርጡ ነብይ ﷺ የማያሻማ ምስክርነት ቢድዐ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ተነግሮ ሳለ የመውሊድን ቢድዐ መሆን ካመነ በኋላ ይፈቀዳል የሚል ሰው የተናገረው ከንፁሁ ሸሪዐ ጋር የሚፃረር ንግግር ነው፡፡ ያለ አንድ ተጨባጭ እውቀታዊ መነሻ ቢድዐን ወደተለያዩ ክፍሎች ለከፈለ ሰው በጭፍን ከመከተል ያለፈ ነገርም የለውም፡፡ የትኛውንም አቋም ይቻላል የሚልን ሰው ይህንን ቢድዐ በተለየ የሚመለከት ማስረጃ ካቀረበ በኋላ እንጂ አንቀበለውም፡፡ … እንጂ ‘እከሌ እንዲህ አለ’፣ ‘እከሌ እንዲህ አይነት ኪታብ አዘጋጅቷል’ የሚል ባዶ ንግግር ፋይዳ የለውም፡፡ ሐቅ ከየትኛውም አካል ይበልጣልና፡፡” [ገፅ፡ 2/1088 - 1089] “ከነሱ (ከፈቃጆቹ) ውስጥ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፡፡ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም፡፡” [ገፅ፡ 2/1094] ኢብኑ ሐጀር እንዳደረገው የዓሹራን ፆም ማስረጃ ማድረግ፣ ወይም ሲዩጢ እንዳደረገው ከነብይነት በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ ማውጣታቸውን መመርኮዝ ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ነገር ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡ [ገፅ፡ 1095] 5. መውሊድ የብዙሃን ሙስሊሞች ድጋፍ ነበረውን? ሸውካኒይ፡- “በሰዎች ንግግሮች ላይ የምንመረኮዝ ከሆንና የእንቶ ፈንቶ ጅራቶችን የምንጨብጥ ከሆንን መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ‘ይፈቀዳል’ ባዮቹ ከሙስሊሞች በአቋም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ …” [ገፅ፡ 2/1087-1089] “ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1095 – 1099] (አስተውሉ! ይህ እንግዲህ በሸውካኒ ዘመን ነው፡፡ የሞቱት በ1250 ሂ. ሲሆን ሁለት መቶ አመት ሊሞላቸው ጥቂት ነው የቀራቸው፡፡ ሱፊያ ደፋር ነውና የዛሬን የመውሊድ ጨፋሪዎች በመመልከት ሸውካኒን “ውሸታም ነው” እንዳይሉ እሰጋለሁ፡፡) 6. መውሊድ እንዴት ተስፋፋ? ሸውካኒይ፡- “ግና ቢድዐን በማፅናትም ሆነ በማጥፋት ላይ ንጉሳን ተፅእኖ አላቸው፡፡ ይህንን ቢድዐ (በሱኒው ዓለም ውስጥ) የፈጠረው ያ ንጉስ (ሙዞፈር) ሲሆን ኢብኑ ዲሕያ ደግሞ ‘አተንዊር ፊ መውሊዲል በሺር ነዚር’ የተሰኘ ኪታብ በማዘጋጀት አግዞታል፡፡ ሰውየው በዘገባ እውቀት ላይ የጠለቀ ከመሆኑም ጋር በዚህ ኪታቡ ግን ግልፅ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ለዚህ ስራው - ኢብኑ ኸሊካን እንደጠቀሱት - አንድ ሺህ ዲናር በንጉሱ መሸለሙ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የዱንያ ፍቅር ከዚህም በላይ ያደርሳል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] “የቢድዐ ስርጭት ከእሳት ስርጭት የፈጠነ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መውሊድ፡፡ ምክንያቱም የመሃይማን ነፍሶች ጥግ የደረሰ መናፈቅን ይናፍቁታልና፡፡ በተለይ ደግሞ ከምሁራን፣ ከክቡራንና መሪዎች በርከት ያለ ሰው ከተካፈለበት በኋላ ይሄ ቢድዐ ወሳኝ ከሆኑ ሱናዎች ይመስላቸዋል፡፡ … እንደ መውሊድና አምሳያዎቹ ያሉ ለሐራም ነገሮች የሚያመቻቹ የጥፋት መዳረሻዎች መሃይሞች ፈጥነው እንደሚገቡባቸው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በዒልም፣ በክብርና በስልጣን ዝና ያለው ሰው መካፈል ሲታከልበት ሐራም ነገሮችን እንደ ፈጣሪ ትእዛዛት ሲፈፅሙ፣ በድንቁርናና በጥመት ሸለቆች ውስጥ ገብተው ሲዘባርቁ፣ “የተከበሩ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተገኝተዋል” እያሉ ከተቃውሞ ሲያመልጡ የባሰ ይሆናል፡፡ መሃይሙ ህዝብ ይቅርና አንዱ በዒልም ፍለጋ ላይ ገኖ የወጣ ሰው አንዳንድ የኢጅቲሃድ እውቀቶችን ለመማር ከፊቴ ተቀምጦ ነበር፡፡ በዚህ ወር ከተከናወኑ መውሊዶች ውስጥ በአንዱ አዳር ላይ እንደተካፈለ ሲነግረኝ ተቃወምኩት፡፡ አንገሸገሸኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተካፍለዋልኮ’ አለኝ፡፡ በነዚህ ታዋቂ ሰዎች ፊት የነበረውን አፈፃፀም ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡- ‘እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እየዘፈኑና እያዳመጡ መንዙማውን አንድ ዱርየ አነበበ፡፡ ከዚያም አንዱ ልክ ከእስር የተነሳ ይመስል አፈፍ ብሎ ተነስቶ “መርሐባ ያ ኑረ ዐይኒ፣ መርሐባ” (እንኳን መጣህ ያይኔ ብርሃን እንኳን መጣህ!) ሲል ታዳሚው በመላ ታዋቂዎቹን ጨምሮ ተከትለውት ቆሙ፡፡ እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቆሞ ማጓራት ያዘ፡፡ አንዱ ታዳሚ ደክሞት ቢቀመጥ ከታዋቂዎቹ ውስጥ አንዱ ንዴቱ ከፊቱ ላይ እየታየ ‘ተነስ! ጨዋታኮ አይደለም!’ ብሎ ጮኸበት፡፡ ቃል በቃል! የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚያች ሰዓት ከነሱ ዘንድ እንደደረሱ ጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ ከዚያም ተጨባበጡ፡፡ ከመሀይማን ከፊሎቹ በእጆቻቸው ሽቶ በመያዝ በፍጥነት ቀቡ፣ ተቀቡ፡፡ ልክ የሳቸውን ﷺ መገኘት ለመጠቀም፡፡’ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! የዲን ክብር የት ገባ?! ይህም ከጠፋ አይናፋርነት፣ ግብረ ገብነት፣ ህሊና የት ገባ?” [ገፅ፡ 2/1089 - 91] 7. መውሊድን የነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ይደግፉታል? መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች “ከኛ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወድ ላሳር!” የሚሉ ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር የነብዩ ﷺ ዘሮች ሙእሚኖች ከሆኑ ለነብዩ ﷺ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው፡፡ መውሊዱ የፍቅር መገለጫ ቢሆን ኖሮ ከማንም ቀድመው ባከበሩት ነበር፡፡ ግን ከነሱ የተገኘው መውሊድን ማክበር፣ ማስከበር፣ ለሱ ሽንጥን ገትሮ መሟገት ነውን? ሸውካኒይ፡- “ከነብዩ ﷺ ንፁሕ ቤተሰብም ይሁን ከተከታዮቻቸው ይህ ነገር እንደሚፈቀድ የተናገረ አንድም ፊደል አላገኘንም፡፡ እንዲያውም ይህቺ ቢድዐ ከተከሰተች ጀምሮ ወደ ጥፋቶች ከሚያሻግሩ አስቀያሚ መዳረሻዎች አንዷ እንደሆነች ንግግሮቻቸው ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1089]