cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መፅሐፍቶችን በpdf

"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 517
Suscriptores
+1424 horas
+937 días
+35730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Elegance Unveiled: Modern Gentleman's Guide 🎩✨ 🎩✨ 1. Politeness is the truest form of sophistication. 🎩🤝 2. Chivalry is not outdated; it's timeless respect. ⚔️🕰️ 3. A gentleman's word is his bond. 🤞👨‍💼 4. Manners maketh man. 🍽️🤵 5. Hold doors open, it's a small gesture with big impact. 🚪💼 6. Cultivate a strong handshake; it speaks volumes. 🤝📈 7. Respect others' opinions, even if you disagree. 🗣️🤝 8. Stand tall, speak kindly, and dress the part. 🕴️👔 9. Offer a genuine compliment; sincerity shines. 💬🌟 10. Master the art of conversation; it's a gentleman's tool. 🗨️🎨 11. A gentleman's strength lies in his gentle touch. 💪🤲 12. Listen more than you speak; wisdom comes in silence. 👂🤐 13. Choose quality over quantity in friendships. 👬🌟 14. Apologize sincerely; it's a mark of true character. 🙏😌 15. Embrace responsibility; it's a mark of maturity. 🤔🔄 16. Gentleness is not a weakness; it's a strength. 🌼💪 17. Be punctual; it shows respect for others' time. ⏰👌 18. Treat everyone with kindness; it's a reflection of your character. 🌍💖 19. Admit mistakes gracefully; humility is attractive. 🤷‍♂️😊 20. Cultivate a sense of humor; laughter is a gentleman's ally. 😄🎭
Mostrar todo...
"ሁላችንም ሀሳብ አለን፡፡ ግን ሀሳባችን ዋጋ ያለው አይመስለንም፡፡ ሁልጊዜም ከእኛ የተለዩ፡ ከእኛ የተሻሉ "አሳቢዎች" አሉ ብለን፡ ማሰብን ለማናውቃቸው "ሌሎች" እንተወዋለን፡፡ ወይም "ማሰብ" ምሁራን የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስራ ነው ብለን፡ ላሉብን ችግሮች አንድ መፍትሄ አምጥተው እስኪሰጡን አፍ አፋቸውን እያየን እንጠብቃለን፡፡" አለማወቅ በዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ
Mostrar todo...
እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም! (በዓሉ ግርማ) 👉 እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ... 👉 በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው። ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው... 👉 ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል? 👉 ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው። 👉 ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ! በዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ገፅ 234
Mostrar todo...
👍 1
የሆነ ጊዜ ጓደኛዬ  እግሩን ተሰብሮ ሆስፒታል ተኝቶ ነበር ውጪ በር ላይ የተቀመጠው ወንበር ላይ  ነበርኩ ፣ ፋዘሩ እንባቸውን እየጠረጉ ከተኛበት ክፍል ሲወጡ አየኋቸው ተደናግጬ ዘው ብዬ ገባው ያቃስታል ፤  ምን ሆንክ?  አመመህ ? ስለው እያቃሰተ ስለነበረ ገላመጠኝ እያየኸኝ አይደል አይነት ፋዘር ጋ ምን አወራቹ ? እ ? "እሱ ባክህ  ...... ወንድ ልጅ አይደለህ ጠንከር በል ፣ ቀላል ነገር ነው ብሎኝ ነው ኮስተር ብሎ የወጣው" አለኝ መሃል መሃል ላይ  እያቃሰተ I think አባትነት ጨካኝ መስሎ ተሸሸጎ መባባት ነው አልኩኝ አባትነት ❤ Adhanom Mitiku
Mostrar todo...
👍 3
.... " መጽሐፍት ሲበዛ ረጋ ያሉ መቼም የማይናወጡ ቋሚ ጓደኛ ናቸው ። ተደራሽነታቸው ሰፊ ፣ እጅግ ጥበበኛ ፣ በዛ ላይ ምርጥ አማካሪዎች ፣ እንዲሁም ታጋሽ የመሆን መምህር ናቸው " ( ቻርለስ ኤሎት ) ፍራንሲስ ቤከን ደግሞ እንዲህ ይለናል ፦ " አንዳንድ መጽሐፍት የሚቀመሱ ፣ አንዳንዱ ደግሞ የሚዋጡ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ግን በሚገባ ተላምጠው ለመፈጨት ወደ ውስጣችን የሚላኩ ናቸው " 💚 እያነበብን 📖
Mostrar todo...
እውነት ተረግመናል ? ቁጥር 2 **** ለትንሽ ደቂቃ ራስህን(ንዴትህን) መቆጣጠር ካቃተህ የምትገባበት መቀመቅ ብዙ ነው። ሰሞኑን በእህታች ላይ አትላንታ ውስጥ የተፈፀመው ግድያ የስንቶችን ሕይወት ያቃውስ ይሆን ? እዚህ እኔ የምኖርበት አካባቢ አሰቃቂ የሆነ ግድያ ተፈፅሞ ነበረ ። ስለ ግድያው ከመፃፌ በፊት በብዙ የአውሮፓ ሃገራት በተለይም የስካድኔቪያን ሀገራት (ስዊዲን፣ ኖርዌይና ዴንማርክ) ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት ኦዲን ( Odin) በሚባል አምላክ ያምኑ ነበረ ።ኦዲን የአምላኮች ሁሉ አምላክ ነበረ። የሰው ነፍስ(ደም) ይገበርለት የነበረ ነው። በዛ ዘመን እምነታቸው መተት ተደርጎብኛል ብለው የሚያምኑ ብዙዎች ነበሩ። መተት ያደረገባቸውን ሰው ወዲያው ቢገሉት መተቱ አይለቅም ነበረ። የሚለቀው ወቅት ተጠብቆ በእጁ የሌላ ሰው ደም አስይዞ በጨረቃ ሲገደል ነበረ የሚል እምነት ነበራቸው። አንዳንዶች ደግሞ መተተኛውን ሰው ቆራርጦ መግደል መተቱን ያከሽፋል ብለው ያምኑ ነበረ። አውሮፕያውያን ክርስትናን መቀበላቸው ከአረመኔነት እንዳወጣቸው የሚያስረዱ ብዙ ፅሁፎችና ፊልሞች በአሁኑ ዘመን አሉ ።(ማወቅ የምትፈልጉ ስለ Vikings ጉግል አድርጉ) ። ወደ ዋናው ፅሁፌ ስመለስ ይህንን ዓይነት ተግባር በአሁኑ ዘመን (በሃበሻ)ይፈፀማል ብሎ ማመን ይከብዳል። ግን የፍራንክፈርት አካባቢ የአንድ ሰሞን ወሬ ነበረ ። የሚስቱን አባት ፣ የሰማኒያ ዓመት አዛውንት መተት አድርገውብኛል በማለት ገደላቸው የሚለው ወሬ እንቅልፍ ነስቶን ነበረ የከረመው ። መግደሉ አይደለም ችግሩ የተለያየውን የሰውነታቸውን አካል ቆራርጦ በፌስታል መጣሉ ነበረ አረመኔዎች ያስባለን ። ገዳዩ የጀርመን ፖሊስ ሳያጣራ አይዝምና አስከሬኑ ከተገኘ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ገዳዩ የልጃቸው የቀድሞ ባል ተይዞ አሁንም እስር ቤት ነው። ሟች ከብዙ ሰው ግንኙነት እንዳልነበራቸው ብዙዎች ያወራሉ። እንዲውም ብዙውን ጊዜያቸውን ጫካ ውስጥ ብቻቸውን ነበረ የሚያሳልፉት ይባላል። የገዳይ ከሌላ ሴት የተወለዱ ልጆች በጭንቀት በሽታ እንደሚሰቃዩ ይነገራል። ምንአልባት ገዳይን ስለ መተት ያሳሰበው ይኼ ይሆን ? የሟችን አካላት የቆራረጠበት ምክንያት መተቱን ለማክሸፍ ይሆን? ስለዚህ ጉዳይ ከገዳይ ውጭ የሚያውቅ የለም ። ግን በሰፊው የተወራው ይኼ ነበረ። አንድ በእርግጥ የማውቀው ጉዳይ ገዳይ ጥሩውን ኑሮ ትቶ እስር ቤት ውስጥ እንደሚሰቃይ ብቻ ነው።ሌላው ጊዜው ሲያልፍ እኛን አበሾችን ጫካ ውስጥ ሲያይ የሚደነግጠው ፈረንጅ ቀንሷል።(ከታች ያለው ፎቶ የኦዲን ነው) አምላክ ደህናውን ዘመን ያምጣ!
Mostrar todo...
"The Success Principles™" by Jack Canfield is a comprehensive guide to achieving success and fulfillment in various areas of life. Here are 25 key takeaways from the book : 1.  Take 100% Responsibility : 🌟 Own your life and outcomes by taking full responsibility for your actions, choices, and results. 2.  Clarify Your Vision : 🎯 Define clear goals and create a compelling vision for your ideal future. 3.  Believe in Yourself : 💪 Cultivate unshakable self-confidence and belief in your abilities. 4.  Develop a Success Mindset : 🧠 Adopt a mindset of success and abundance; think and act like a successful person. 5.  Set Clear Goals : 📅 Set specific, measurable, achievable, relevant, and time-bound (SMART) goals. 6.  Create Action Plans : 📝 Break down your goals into actionable steps and create concrete plans to achieve them. 7.  Continuous Learning : 📚 Commit to lifelong learning and personal development. 8.  Seek Feedback and Adjust : 🔄 Be open to feedback, learn from failures, and adjust your approach accordingly. 9.  Practice Persistence : 🏃‍♂️ Develop resilience and persistence to overcome obstacles and setbacks. 10.  Take Consistent Action : 🚀 Take consistent and focused action towards your goals every day. 11.  Manage Time Effectively : ⏰ Master time management and prioritize tasks based on importance and urgency. 12.  Develop Positive Habits : 🌱 Cultivate empowering habits that support your success and well-being. 13.  Surround Yourself with Positive Influences : 🤝 Surround yourself with supportive and positive people who uplift and inspire you. 14.  Practice Gratitude : 🙏 Cultivate a gratitude practice to attract more blessings and abundance into your life. 15.  Visualize Success : 🖼️ Use visualization techniques to mentally rehearse achieving your goals. 16.  Embrace Failure as Feedback : 🚫💪 View failure as a learning opportunity and stepping stone towards success. 17.  Build Resilience : 🌱 Develop emotional resilience to bounce back from challenges stronger than before. 18.  Take Calculated Risks : 🎲 Step out of your comfort zone and take calculated risks to grow and achieve more. 19.  Develop Effective Communication Skills : 🗣️ Learn to communicate assertively and persuasively to build strong relationships. 20.  Network and Build Connections : 🤝 Expand your network and build meaningful connections with others. 21.  Manage Finances Wisely : 💵 Practice financial discipline and manage your money wisely. 22.  Stay Committed to Personal Growth : 🌱 Commit to continuous personal growth and self-improvement. 23.  Celebrate Achievements : 🎉 Acknowledge and celebrate your successes along the way. 24.  Give Back and Contribute : 🤲 Make a positive impact on others and contribute to causes you believe in. 25.  Live with Purpose and Passion : 🔥 Align your actions with your values and live a purpose-driven life filled with passion and fulfillment. These principles from Jack Canfield's book provide a roadmap for achieving success, fulfillment, and personal excellence in all areas of life. Applying these principles can lead to transformative results and a more empowered, purposeful existence.
Mostrar todo...
👍 1
ላብ አደር ነኝ። እንደማንኛውም የድሮ ሰው ተቀጥሮ በመስራት አምናለሁ ፤ እሞክራለሁም ። ዘመን አመጣሽ “የራስ አለቃ” ይሉት ብሂል አይዋጥልኝም ። ሰውማ አለቃ ያስፈልገዋል ። ከሰውም ደግሞ ከስልጣኔ እንዲህ ኋላ የቀረና በድህነት የሚማቅቅ እንደ እኛ አይነት ሰው በጣም አለቃ ያስፈልገዋል ። የሚገስፅ ፣ የሚቀጣ ፣ የሚያበረታታ ፣ የሚሸልም ፣ የሚያስተምር ፣ የሚመክር ፡፡ ችግሩ አለቆች ሁሉ በስፍራቸው አይደሉም። ሁሉም ሰው ደግሞ አለቃ ሊሆን አይችልም። አንዳንዶች ብቻ ለኃላፊነት ተፈጥረዋል። ስልጣኑን ይዘው ከኃላፊነቱ ገሸሽ ያሉ ብዙ ናቸው። የመምራት ክህሎት፣ የማሳወቅ ጉጉትና፣ እንደሰው የማዘን የመረዳት፣ ቀድመው ያወቁትን መንገድ ለጀማሪዎች የማሳየት ችግር ብዙ አለቆች ጋር አለ። በአጋጣሚ ይሁን አመል እንጃ አንድ መስሪያ ቤት ከ2 አመት በላይ በቋሚ ሰራተኛነት አልቆየሁም። ቶሎ ቶሎ መስሪያ ቤት መቀያየር ጥሩም ነው መጥፎም ነው። ጥሩነቱ ስራውን አካባቢውን ተላምዳችሁ በቀላሉ በደመነፍስ ስራን ለመከወን ማስቻሉ ፤ መጥፎነቱ ከባልደረቦችና ከመስሪያ ቤቱ ጋር አጉል ቤተሰባዊነት ተሰምቷችሁ በስራና የግል ሕይወት መካከል ያለችው ስስ ግድግዳ መናዷ። ለእኔ ስራ ስራ ነው! በሁለት የሙያ ዘርፍ ስራ ከጀመርኩ 9ኛ መስሪያ ቤቴን ከተቀላቀልኩ ገና 3 ወር አልሆነኝም።(አሁን ሁለት አመት አለፈኝ ) በአማካይ ከ 6ወር እስከ 2 አመታት በአንድ ቦታ ቆይቻለሁ። በስራ በነበርኩባቸው ቦታዎች ሁሉ ለቅቄ ወደ ሌላው ስገባ ... ነገ እሄዳለሁ በሚል ቸልተኝነት ያበላሸሁትና ያዝረከረኩት ስራ የለም። በሰላማዊ ትግልና በሰላማዊ መንገድ ተመራርቄ "ቸር ይግጠምሽ" ተብዬ ፍፃሜዬን አሳምሬ ነው የተለያየሁት። እጆቼን ብታዩ ሻካራና ስራ የለመዱ ናቸው። የጉልበትም የጭንቅላትም ስራ እሰራለሁ። አንድ ነፍሴን ለማሰንበት ... በግራ በቀኝ ከፊትና ከኋላ ያሉትንም ለማየት! ለስራ አለግምም፣ ሆነ ብዬ አልሰንፍም፣ በቸልተኝነት አላረፍድም ፣ በሰበብ አስባቡ ከስራ ገበታዬ አልቀርም ... ቀን ከለሌሊት ብሰራ ቅር አይለኝም። ቤቴ አምጥቼ፣ እንቅልፌን አጥቼ እሰራለሁ። የማውቀውን አሳውቃለሁ። የማላውቀውን እጠይቃለሁ። ከሚጠበቅብኝ ጊዜ እቀድማለሁ እንጂ አላዘገይም! ከስራ ልምዴ እና ከትምህርት ዝግጅቴ እኩል ሰዎች ስለኔ የሚሰጡት መልካም ምስክርነት ዋጋ እንዳለው እያደር ተገንዝቤያለሁ ። ከሁሉም በላይ ጤነኛ ነኝ። ሰላም አለኝ። ጉልበቴን አዕምሮዬንና ጊዜን አከራይቼ የማድር ለፍቶ አዳሪ ፤ ላብ አደር ነኝ። እድገት ፣ የደመወዝ ጭማሪ ፣ ያልተገባ ጥቅማጥቅም ለማግኘት ለባለቤቶችና ለአለቆች ሳጎበድድ የትም አልተገኘሁም። የሚገባውን ክብርም አልነፍግም ። በስራ ቦታ ያሉ ጥቃቅን ኢ-መደበኛ ቡድኖች ውስጥ የለሁበትም ። እነዚህ ቡድኖች በእምነት፣ በፓለቲካ አቋም፣ ባገር ልጅነት ፣ በፆታ፣ በስራ ደረጃ፣ በሰፈር ወዘተ ... የተደራጁ ሊሆኑ ይችላሉ ብዙም ትርፍ የላቸውም ! ስለዚህ የህሊና ወቀሳ የለብኝም ። ስራዬ ላዬ አተኩሬ ስለፋ ስለምውል ... "ጣሪያ ላይ በሚወድቅ ቅጠልና ፍሬ አልነቃም አስሬ" ምክንያቱም ''እኔ ባለሙያ ነኝ። የትም ብሄድ ሰርቼ ነው የማገኘው '' የሚል ልበ ሙሉነት አለኝ። ስራ ሳልንቅ ፤ ሳልማረር ሰርቼ ነው የምበላው ። ጉልበቴን አእምሮዬንና ጊዜን አከራይቼ የማድር ለፍቶ አዳሪ ላብ አደር ነኝ። ስንፍናን እጠየፋለሁ። ብዙ ነገር ልሆን እችላለሁ ። ሰነፍ ግን አይደለሁም ! “ሊሰራ የማይወድ አይብላ” መርሄ ነው ። ጤና ፣ ጉልበት ፣ ጊዜ ፣ እውቀት ኖሯችሁ የሆነሰው ትከሻ ላይ የተንጠላጠላችሁ ... ሁላችሁ ... ተነሱ ፣ ውጡ ፣ ስሩ ፣ ድከሙ እጆቻችሁን ስራ አስለምዱ ፤ አእምሯችሁ ያስብ ... ከቤት ጀምሩ የበላችሁበትን ፤ የለበሳችሁትን እጠቡ ፤ ቤት ወልውሉ ፤ ቆሻሻ ጣሉ ፤ 'ስራ ብታጡ ስፖርት ስሩ' -እንዳለው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ አደራ ሰው ላይ አትንጠልጠሉ...የሆነ ሰው የለፋበትን ገንዘብ ያለርህራሄ አታውድሙ! በላብ የተቦካ እንጀራ ይጥማል። ሞክሩት። እየለፋችሁ ተመጣጣኝ ክፍያ ያላገኛችሁ አይዟችሁ ልፋታችሁን ቀጥሉ! በርቱ! ጠንካራ ስራ ዛሬ ባይሆንም ውሎ አድሮ ይከፍላል። በእውነት ይከፍላል ። የእጆቻችሁን ስራ የላባችሁን ፍሬ ማንም አይነጥቃችሁም። እርግጥ ነው የሰራ ሁሉ አልበላም። ያልሰራም ጦሙን አላደረም ። እግዚአብሔር የሰጠው ሰጥቶም የባረከለት በልቷልና ! ምስጋና በሃቅ በእውነት በታማኝነት የስራ ገበታቸው ላይ ለተገኙ ጉልበታቸውን አእምሮና ጊዜአቸውን አከራይተው ለሚያድሩ ለፍቶ አዳሪ ላብ አደሮች ። #ከትውስታዬ
Mostrar todo...
ይሉኝተኛ ናት ልብ አላት አዛኝ ልብ ። በልቧ ምክንያት ኪሷ ውስጥ ብር አይበረክትም ። የመጀመርያ ቀን ስናወራ ዋልን ያን ቀን ነው ያወኳት ከዛ እለት ቀጥሎ ብዙ ቀን አገኘኋት ያኔ ያየኋት ልጅ ነች ። እናቷን አሞባት ብር አበድረኝ አለቺኝ ። ባለፈው የሰጠኋትን ስላልመለሰች እየተሳቀቀች ነበር የጠየቀቺኝ ። ብዙ ሰው ጋ ሄድኩ ። የጠየኳቸው ሰዎች እንደኔ ብር አልነበራቸውም ። ለመጀመርያ ግዜ ድህነቴ ታወቀኝ ። የለኝም አላልኳትም... ዝም ነበር ያልኳት ። የለኝም ለማለት ፅፌ ነበር አላኩላትም እንጂ ። ቸገረኝ ላለ ሰው እኔም ቸግሮኛል ብሎ ከመፃፍ አለመፃፍ ይሻላል ብዬ መሰለኝ ። ልትመረኮዝበት ያሰናዳችው ትከሻ መመርኮዣ አጥቶ መሆኑን ማወቅ ምን ያደረጋል ። ከዘጠኝ ቀን በኃላ ብዙ ብር አገኘሁ ብላ ብዙ ብር ላከችልኝ ። አንድ አንድ ልቦች ሲቸገሩ ብቻ አይደለም የሚፈልጉን ። እንዳንድ ነብሶች የዝምታችን ትርጉም ሳንነግራቸው ይገባቸዋል ። Adhanom Mitiku
Mostrar todo...