es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

Ir al canal en Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል! @Alazartewodros1 የጥበብ

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram የጥበብ ማዕድ

El canal የጥበብ ማዕድ (@alazartewodros1) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 14 617 suscriptores, ocupando la posición 5 876 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 435 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 14 617 suscriptores.

Según los últimos datos del 02 noviembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -363, y en las últimas 24 horas de -11, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 5.06%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 1.86% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 740 visualizaciones. En el primer día suele acumular 272 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 8.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል! @Alazartewodros1 የጥበብ”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 03 noviembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

14 617
Suscriptores
-1124 horas
-897 días
-36330 días
Archivo de publicaciones
ዝም በይልኝ🤫 ከአለም ከሚመረጥ ሁሉ ባንቺ ገፅ አይኔን አሳረፍኩ፡ በተራሽ አለምን ተወሽልኝ ውክልና ስትሰጪኝ አመንኩ፡ ግና ያሳረፍሽው ፊርማ ቀለም ከመድረቁ፡ ምርጫ አገኘሽ መሰል ገዙሽ በትልቁ፡ መቀየር አይገልፀው ከይሲው እንኳን ደነገጠ፡ እግዜር ሰጠኝ ስትይ ሰምቶ አሁን ሙት.. ስትይኝ.. ተቁነጠነጠ፡ አፍሽ አይያዝም ሆዴሽ ሲጎነጉን ክፋትን ሲያከስል፡ አይገርምሽም እንዴ ? ባንቺ ምክንያት ሴጣንሽ ዝም ሲል። @dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ             (ግርማዊ ዳግም)

፡ እግዜር ለበደሌ        በምድር ሲሰጠኝ                 ምህረት ያጣ ቅጣት ካንቺ ጣለኝና               ሰማንያ ፈረምኩኝ                          በመከረኛው ጣት እና አሁን እንዴት ነው ሚሰረዝ     እንዴት ነው ሚረሳ ታሪክ እንደ'ድሮ ህመም ለሸመተ ላሳደገ ወላጅ ሰላም አበ'ድሮ።      ለቀልድ ነው ጨጓራዬን ስል ባንቺ ምክንያት አይደለም።        አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

ቀበሌና ብዙ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ግን መሶብ ገብተው ለአመት ያህል ልምድ ቢወስዱ ጥሩ ነበር። ትንሽ ትህትናና ስራ ምን እንደሆነ ገብቷቸው እንዲመጡ! #መሶብ_ሁርሶ!

ለሚያደርግልህ ነገሮች ሁሉ ጥፋተኝነት ከሚሰማው ሰው ራቅ መጨረሻው የበዛ ወቀሳ ነው።

ቃል ቀልጦ ተቀርፆ ካስነሳ አንድ ሙት፡ ዝም ብሎ ያለውን ተናገር አትበሉት.... ተግባር እርቃለች ማን ይድረስ ተጉዞ፡ ሁሉ መካሪ ሆኗል ዲስኩር ጢባጢቤ ይመታል ጠልዞ፡ ስኬት ይመስለናል ሱፍ መሀል መደበቅ፡ ሲያምረን አይን አናቅም ሀሉን መነካካት... ሁሉን ማጨማለቅ... ደርሰን የት እንረፍ ከአለም አዲስ አልቋል፡ መመሳሰል ብቻ ጥሬው ከብስሉ አንድ ላይ ታጭቋል፡ እውቀት አመለጠች በቀዳዳ ወጥታ፡ መስከን መንናለች በሀገሬው ሁካታ። @dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ                (ግርማዊ ዳግም)

በስተመጨረሻ መልካም ቀኖችና ብዙ ውለታዎች ይረሱና ጨካኝና መጥፎ ተብለህ ትጠራለህ።

፡ የተዋቀረ እልፍኝ           በካስማ ምሶሶ                     እንዳይሆን ፍርስራሽ ድጋፍ ለቁመናው          የሰዎችን መኖር                  ይፈልጋል ትንፋሽ!!!             አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

"ከደሞዝ ቀን በቀር ሁሉ ነገር ይረሳል"!       "እንቅልፍ እና እድሜ" በእውቀቱ ስዩም

አቅመ ደካማው አጠገብ የተወጠሩ ጅማቶቹን በተደለደለ ሰውነት ላይ አሳየ! ይህ ግን ትልቅነቱ ከአዛውንቱ አንፃር ነበር። ሱ አንድ ሰዓት የስፖርት ስራ ከሚበልጡት ሚግ ተዋጊዎች ሚያስጥሉት መስሎታል።

መኖሩን ነበረን ይተርፋል ለአዳም፡ ግን...ስብአዊነትን ፍፁም አያስከዳም፡ በጦርነት ውሀ መርከብ ለማንሳፈፍ፡ ሟቹ በዝቷል እና ያመጣል መቀሰፍ፡ ሰላም ይሁንልን አንፈልግም ወደብ፡ አንሙት ይቅርበን ጊዜ መጥቷልና የሚያሳጣን አደብ... ለሞቱትስ ?...😭 @dagi1u

ከስር ወደ ላይ ነው ደረጃ የሚካብ፡ ሲደባበቁብህ ተደብቀህ እለፍ ልብ በል እንደ እባብ፡ ልክ እንደ መዶሻ ልክ እንደ ሚስማር ጫፍ፡ ዝም በል ታገሰው ያነቀህን መዳፍ፡ ከአለም አብልጠህ ፈጣሪህን ካድም፡ ግርግር አታብዛ ከፈረሱ በፊት ጋሪው እንዳይቀድም፡ ልጎሙን ጨብጠው መሪህ ይሁን እምነት፡ ፍላጎትህ ታይቶ ይጨመራልና የንሰሀ አመት... ጎማውን አጠንክር ህሊናህን ቅጣ፡ ብቻ ግን አደራ ለመን-ገንዘብ-ብለህ ከመስመር አትውጣ!። @dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ               (ግርማዊ ዳግም)

እጅግ ንፁህ ውሃ ህይወት የለበትም ለአሳዎችም አልተተወም! ለተለያዩ ሰዎች ግን መዝናኛ ነው።

ጫካውን ማቋረጥ የግድ ከሆነ አውሬውን ማላመድ ትልቁ ስራህ ነው።

: ባለው ሰው ሲኮራ          ወደብ ባህር ጠቅሶ እኛ ከማን አንሰን     ቀይ ደም ባህር አለን                     ያልተገታ ለቅሶ!         አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

ከባድ ሸክም ተሸክማቹ ታውቃላቹ? ሸክሙን ሚያሸክማቹ ሰው ከመሬት አንስቶ ትከሻቹ ላይ ካኖረ በኋላ የራሱን መንገድ ይጓዛል። ሸክም የተሸከመ ሰው Ultimate goalኡ ሸክሙን ሚጥልበት ቦታ ነው። ሸ
ከባድ ሸክም ተሸክማቹ ታውቃላቹ? ሸክሙን ሚያሸክማቹ ሰው ከመሬት አንስቶ ትከሻቹ ላይ ካኖረ በኋላ የራሱን መንገድ ይጓዛል። ሸክም የተሸከመ ሰው Ultimate goalኡ ሸክሙን ሚጥልበት ቦታ ነው። ሸክሙ ከብዶት ወደ ሰማይ ማየት ተስኖት አቀርቅሮ መሬት መሬት እያየ እንኳን በምናቡ የሚያስበው የመጨረሻዋን ቦታ ነው። ደሞም የሆነ ሰዓት አለ መጓዝ የሚያቅትህ፣ ላበት አይንህ ውስጥ ገብቶ የሚያቃጥልህ፣ መንገድ ማየት ተስኖህ ከሰው ጋ ስትጋጭ ያሰውም እያየ ገጭቶህ አንተን ጥፋተኛ አድርጎ የሚሰድብህ፣ ከሰውዬው ግጭት ተንገዳግደህ ሃይል የምትሰበስብበት፣ ምትጓዘውን energy በመንገዳገድ የሚያልቅብህ፣ ........ ደሞም ከሸክም የሚያስጠላው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ? «ሸክም ሲበዛብህ ህመምህ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ መሆኑ ነው።»የሸክምህን ክብደትና የመጣህበት ሩቅ መንገድ ሳያውቁ የሚሳለቁብህን ችላ በላቸው፤ እነሱን ለማየት ስትዞር የዛለው አንገትህ ሊቀጭ ይችላል። ሸክም የተሸከመ ሰው የሰው ብዛት ባለበት ቦታ አይጓዝም ምክኒያቱም መድረሻው ሩቅ ይሆንበታል። በመሃል እየተጓዝክ ሸክሙ ሲያስጨንቅህ ለማልቀስ ትፈልጋለህ.... ግን ለቅሶም energy ይፈልጋል ከአፍህና ከአፍንጫህ የሚወጣው ቁና ሚያሰፍር ትንፋሽ እንጂ የማልቀስ አቅም አይደለም። አንድ ቀን ታርፋለህ አይዞህ መንገድህን ቀጥል።                                  ✍️ Henok

ሀዘን የቤት ወገን ደስታ መንገደኛ፡ እንግዳ ነው ለሀገር ከሁሉ የሚተኛ፡ አለምን ግርግር ገብስሶ ሲያምሳት፡ ታስተናግዳለች አዬ ልብ ምስኪን ናት... ደስታ የፋታ ወሬ ሆያ ሆዬ ቁስል፡ ለካስ የሀዘን ፋታ ነው እረፍትን የሚስል፡ በከንቱ መደለቅ እንደ ዘለአለም ድል፡ እውነቱ...ሀዘን እየመራ ደስታን ሊደብቅ ነው የተሰጠው እድል። @dagi1u✍ ገጣሚ ዳግም ግርማ             (ግርማዊ ዳግም)

በዚህ ዘመን ቁምነገርህ ቀልድ እንዳይሆን ቁምነገር አድርገህ አታውራው! ቀልድህ ግን ተመልካች ካገኝ ቁምነገር ሆኖ ካንተ በላይ ታዋቂ ሆኖ ታገኘዋለህ።

📚 ጥሪ ወደ ሞት  📚 📝ደራሲ:- አህመድ ሁስ ( ሻድ ) 📜ይዘት:- እውነተኛ ታሪክ 📖የገፅ ብዛት:- 141 📆 ዓ.ም :- 2018 🖨 ዕትም :- 13.9MB 💭Type :- #pdf #ጥሪ_ወደ_ሞት

ደገስኩልሽ በደም እንባ ለቅሶ ወይን... ተመልከቺው የእኔን አይን... አልወደድሽልኝም ልፋቴን ያጣፈጥኩትን ድግሴን፡ ልቤን ነበረ የቀቀልኩት አላየሽም በእግር ማንከሴን? አላየሸም መተናነሴን ? ድር ማጌን ነካካው ትራፊ የለበስኩትን ፈትለ በርኖስ፡ በራሴ ድግስ ጎዳ ዘግቼ አልወጣም ድንበር ልክ እንደ ዋኖስ፡ የለሽም ቀርተሻል ለግብዣው ድፍን ሀገር ተገኝቶ፡ ሀገሬ አንቺ ነሽ ቀልቤ ተሰቀለ አንድ ሀገሩን አጥቶ፡ ጠምቄ ነበረ መጣሽ ብዬ በደም እንባ ለቅሶ ወይን.... ግን አላየሽው የኔን አይን.... የለሽም በቦታው ጀግና ነሽ እውነትም... እንዳልድን... አቆሰልሽኝ አደል አልሞ ተኳሽ ሰው አይሞትበትም። @dagi1u✍ ገጣሚ ዳግም ግርማ             (ግርማዊ ዳግም)

፡ እንዲ በላቸውማ… የገፈተርነው ሰው           እንዴት ጸና ቢሉ                          ለሰዎች ተረፈ ከድጥ ጭቃ መሐል             ስለተረገጠ       ጉብታ ሆኖ ነው                     ተመርጦ ያለፈ!         ገና አናበራለን አትገረምም!!!         አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ