ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

前往频道在 Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል! @Alazartewodros1 የጥበብ

显示更多

📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览

频道 የጥበብ ማዕድ (@alazartewodros1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 888 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 737,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 342 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 888 名订阅者。

根据 11 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -318,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 4.91%。内容发布后 24 小时内通常能获得 1.90% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 732 次浏览,首日通常累积 283 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል! @Alazartewodros1 የጥበብ”

凭借高频更新(最新数据采集于 12 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

14 888
订阅者
无数据24 小时
-597 天
-31830 天
帖子存档
ወንዶችን ከሴት ፍጥረታት ጋር ስታዩ እድሉን እንደ ገንዘብ ማግኛ means የምትጠቀሙ ሰዎች ኧረ እየተዛዘንን😒

የፈተና አለመኖር ደህና የመሆን ዋስትና አይደለም

አባ (በእውቀቱ ስዩም) አባ ገብረማርያም የአምሳ ስምንት አመት መነኩሴ ናቸው፤ አንድ ማታ፣ ከምሽቱ አምስት ሰአት ተኩል ላይ፣ የንስሀ ልጃቸው ለሆነቸው ወይንሸት ደወሉ፤ “ሀሎ! ወለተማርያም” “አቤት አባ” “ይቅርታ ተመሸ ደወልኩ” “በሰላም ነው አባ?” “ባለቤትሽ ቤት አለ፤? “የለም ፊልድ ወጥትዋል” “ልጆችስ ?” “ተኝተዋል” “በይ ያለሸበትን ክፍል በር ዝጊው” “እ! ዘጋሁት” “ስልክሽን በምን እጅሽ ነው የያዝሽው?” “በቀኝ እጄ ” “ወደ ግራ እጅሽ አዛውሪው” “ማለት ?” “በማንኩሳው ሚካኤል፤ በውስጠጉልቱ ጊዮርጊስ የምልሽን አድርጊ” “እሺ አንዳሉት አድርጊያለሁ” “በቀኝ እጅሽ እስኪብርቶ ይዘሽ ማስታወሻ ትመዘግቢልኛለሽ” “ምንድነው ?” “የሆነ ጊዜ ላይ ሎንዶን የመሄድ እድል ገጥሞኝ፣ ብሪትሽ ላይብራሪ ላይ ከመቅደላ የተዘረፉ ብራናዎችን ሳገላብጥ አንድ ጥንታዊ መጽሀፍ አገኘሁ፤ የመጽሀፉ አስራ ሰባተኛ ገጽ ተገንጥሎ ስመለከት ከነከነኝ ፤ አገር ቤት ስመለስ የብራናውን ቅጂ በየገዳሙ ማፈላለግ ጀመርኩ፤ በመጨረሻ ዲማ ውስጥ አገኘሁት፤ የሚገርምሽ መጽሀፉ በግእዝ የተጻፈ ቢሆንም የተገነጠለው ክፍል ለብቻው በጋፋትኛ ነበር የተጻፈው፤ ታድያ እኔ አባትሽ ጋፋትኛን ለአምሳት አመት አጥንቸ፤ ትርጉሙን ደረስኩበት” “ይቀጥሉ” “ያ ገጽ ታላቅ ምስጢር አዝሉዋል፤ ንጉስ ላሊበላ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሳጥን ሙሉ ወርቅ አልማዝ፤ ዩራኒየም ታንታለም እና ሌሎች የከበሩ ማእድኖችን አንድ ዋሻ ውስጥ አንደደበቀ ይጠቁማል ፤ ይህ ብቻ አይደለም ፤መቅደሶቹን የፈለፈለበት ማሽን ሳይቀር በዚያ ይገኛል፤ ማሽኑ ትልልቅ አለቶችን በቀላሉ አንደ እርሳስ መቅረጽ የሚችል ነው፤ እየሰማሽኝ ነው ?” “አዎ! ይቀጥሉ አባ!” “የብራናውን ጥቆማ መሰረት አድርጌ ስሄድ አገኘሁት፤ ዋሻው ተደብቆ የሚገኘው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ተራራ ግርጌ ነው፤ ” “ይህንን ለኔ ለምንድነው የሚነግሩኝ አባ” አለች ወይንሸት፤ “ሰሞኑን ትንሽ ሲያመኝ አልነበር፤ አንድ የታወቀ ዶክተር ጋር ሂጄ ነበር ዛሬ ጠዋት! በቅርቡ! በሰአታት ጊዜ ውስጥ የመዘንጋት በሽታ አእምሮህን ይቆጣጠረዋል ብሎ አረዳኝ፤ እናም ትውስታየ ሳይከዳኝ ይህንን አገራችንን ከድህነት መንጥቆ የሚያወጣ ሚስጥር አንቺ ጋር ባደራ ላስቀረው ብየ ነው” አሉ አባ ትካዜ በተላበሰ ድምጽ፤ “እሺ የተራራው ስም ምንድነው አባ ?” አለች ወይንሸት፤ አባ በረጅሙ ተነፈሱና መለሱ፤ “የምን ተራራ;?” (ከምናለሽ ተራ እስከ ምንትሴ ተራራ ከሚለው ልብ ሰቃይ መጥሀፌ የተቀነጨበ)

ያልበሰሉ ውሳኔዎችህ ለአንዱ ወገን መዝናኛ ድራማ ነው ቁጭ ብሎ እየሳቀ መጨረሻህን ይመለከታል።

በእውነት አይቼው ካስገረመኝ ፅሁፍ ቸርች ጊቢ ውስጥ "ሙቅና ቀዝቃዛ ሻወር አለ"የሚል ማስታወቂያ!

ቆንጆና ምሁር ሲደበቅ እንቁራሪት የአራዊት ንጉስ ነኝ ይላል።

መስቃ (በእውቀቱ ስዩም) ተፈጥረን በጎግ ማጎግ  ምድር በሰላም ተኝተን አናድር፤ ሀውልታችችን  የቃየን ድንጋይ ስማችን ሽብሩ፤  ኢጄታ ፣  ገላጋይ ነፍስ ሳናውቅ፤ ከነፍሰ ገዳይ ተዋውቀን ከመርባታችን ተላልቀን በጥይት ተገበያይተን በፈንጅ ወረዳ፤  ሰኞ ማክሰኞ ተጫውተን፤ ጎልማሳው  ከሚስቱ  ፅዋ ፣ ተጎንጭቶ  ሳይረካ ከጫጉላ ወደ ጫካ የወጣቱ፤ ለጋ ጣቱ፤ ከቃታ ጋር  ተጣብቆ የብር ቀለበት የት አውቆ፤ የጅራፋችን ድምጽ፤ በጥይት ድምጽ   ተለውጦ ሞፈራችን ተፈልጦ ካረስነው ትልም በላይ፤ የቆፈርነው ምሽግ በልጦ በሙሉ ልብ ለመሞት ፤ በግማሽ ልብ አኖራለን ፤ ደረት መትተን  ጥለን፣ ገድለን፤ ደረት ደቅተን  እንቀብራለን፤ ጎረቤቶቻችን ሁሉ፤  ያምባ ጉዋሮ ቤት ሆነው መኖራችንን ተቀናቅነው፤ ቤት ለእምቦሳ ብንላቸው፤ ወይፈን ሆነው እያደሩ ወደ ስስ ብልታችን  ፣ ቀንዳቸውን እየወደሩ፤ እሳት አንጫጫር ብለው ገልና ፍም ተውሰው በየለቱ ሲጋብዙን፤ እሳተ ጎመራ ጠንስሰው፤ የመላእክት ጭምብል ለብሰው እንኩዋን ከሰው ካውሬ ብሰው፤

አንዳንዴ እንዲው ማታቀውን ሰው አይተህ ስፍስፍ እስክትል አሳዝኖህ አያውቅም??! ያ ይመስለኛል ሰው መሆን!

በህይወቴ መልካም የነበሩ ወዳጆቼን አሁን እርቀውኝ ያሉትን ሳስብ ዓለም ምን ያህል ውሸታም እንደሆነች ነው የምረዳው።       ቀጥሎም እኔን ከኔ በላይ ማንም ሊወደኝ እንደማይችል የወደደኸም ተሰፍሮ የተሰጠው ጊዜአዊ ቀን እንዳለው እርሱ ካበቃ ወዳጅነት ስም እንደሆነ ተረድቻለው።       ለኔ እኔ በቂ ነኝ! ወዳጅህ የምመስልህም ወዳጅህ እንዳልሆንኩ ካሁኑ ተረዳ…

አሉ ደሞ ቀለል ብለን ስለቀረብናቸው ቀላል  አድርገው  የሚያስቡን አቅልለው የሚያዩን  😒😕🤨

ባህር ላይ መኖር ከጀመርክ ዋናተኛ ሆነህ ትቀራለህ! ዋና መቻልህ ባህሩ ባህሪውን ነው እንጂ የሰጠህ አቋርጦ የመውጣቱን ድፍረት አይደለም!            በቀስታ መልካቸው መልክህ ወዛቸው ወዝህ ይሆናል! አንተነትህም ይደፈጠጥና እነርሱን መስለህ ቁጭ ትላለህ። በቶሎ አምልጥ አምልጥ አሁን……

፡ የሰው ልቡ በዓት                እልፍ ነው ማረፊያ፣ ለወዳጅ ጥጥ አልጋ፡              የተቀበቀበ                        በሽቦ መግረፊያ፣ ያ'ነው መኖሪያው ፡                አንዱ ላንዱ ወገን፡ ቢጤውን ጋልቦ ነው፡                ሚመለከት ነገን።    መኖሪያሽ ልቤ ነው ፤ ልቤ ደግሞ ሙሴሽ!            አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

ስለሰጠኸኝም ፡ ስላሳጣኸኝም ነገር ተመስገን።

ገናናነትን ሲጋት ያደገን ህፃን በፍርሐት ሽባ ልታደርገው አትችልም!

ነይ እንሂድ እንሻገር: አላማረም የእኛ ነገር... ብዬ እንዳልዘፍንሽ ተሳስሬያለሁ በምታቂው፡ አይንሽን አቀዋለሁ ልብሽን ግን ጠይቂው: እኔ ጥቅመ ቢስ ነኝ ወደሽኝ ወደሽኝ ዃላ እንዳይሰለችሽ፡ ሀጥያት እንዳትገቢ አይኔን ከአፈሩ ደግሞ እንዳላስመኝሽ፡ አልሄድም አልመጣም ካለሁበት አለሁ፡ በርግጥ... እኔም ሰው ነኝ ሰው እጠብቃለሁ... @dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ              (ግርማዊ ዳግም)

"ነፍስ ካወኩበት ጀምሮ ያሉት አመታቶች ሁሉ እንደ አንድ ረጅም ቀን ነው የምቆጥራቸው አንድን ነገር ሳደርግ ብቻ ብዙ እንደቆየሁ! ለውጥ ከኔ ለምን እንደራቀ አላውቅም። ሳለፋ ፣ ሳልደክም ቀርቼ ግን አይደለም ግን ተመሳሳይ አኗኗር ነው የምገፋው!          ተስፋዬን ግን ምን በላው? ጉብዝናዬስ እንዴት በሽንፈትና በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ተዋጠ? እሺ ዛሬ እንዲ ሆነ ነገስ እንዴት ሊሆን ነው? ምንድነው መዳረሻዬ? ወጣትነቴን ማስበላት ? ፍላጎቴን ወደ ውስጥ መልሶ መዋጥ? ምንድነው ቀጣዩ"???…………

ጠብቀን ጠብቀን፡ የማንኖረውን ከምንኖረው ላይ በትንሽ ሰራርቀን... አለን... ብዙ ቆየን... ከሰማንያዋ እድሜያችን ኖርን ሲቃ ስናስፈለቅቅ፡ አንዳንችን ለአንዳችን ህመም ስናሳብቅ... ኖርን አለን... ብዙ ቆየን.... አደብ አጣን አለማችን ትከንፋለች፡ ሰው ረግጣ ሰውን ጥላ ለሚቆመው ደግሞ ታጨበጭባለች... ኖርን አለን.... ብዙ ቆየን.... ከራሴ ትውልድ ጋር feet ለማድረግ ብሞክርም የቻልኩ አልመስል አለኝ😞 @dagi1u✍ ገጣሚ ዳግም ግርማ             (ግርማዊ ዳግም)

አንዳንዴ እምባህ እንኳን ባዳ ይሆንብሃል ስትፈለገው አብሮህ አይኖርም።

ሃሳባችንን በቀላሉ ምንጭንበትን ሰው እንወደዋለው....አይከራከረንማ

ስትፈልግ ምታገኘው በክብር የያዝከውንና ያስቀመጥከውን ነው ።