ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 393
Subscribers
+724 hours
+2667 days
+1 44330 days
Loading data
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
October '26Oct '26
October '26
+959
in 6 channels
September '26
+1 091
in 1 channels
Get PRO
August '26
+133
in 1 channels
Get PRO
July '26
+112
in 3 channels
Get PRO
June '26
+101
in 3 channels
Get PRO
May '26
+195
in 4 channels
Get PRO
April '26
+193
in 6 channels
Get PRO
March '26
+278
in 7 channels
Get PRO
February '26
+590
in 7 channels
Get PRO
January '26
+363
in 5 channels
Get PRO
December '25
+129
in 2 channels
Get PRO
November '25
+394
in 8 channels
Get PRO
October '25
+570
in 9 channels
Get PRO
September '25
+710
in 8 channels
Get PRO
August '250
in 4 channels
Get PRO
July '25
+48
in 2 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 20 October | +1 | |||
| 19 October | +10 | |||
| 18 October | +34 | |||
| 17 October | +57 | |||
| 16 October | +177 | |||
| 15 October | +5 | |||
| 14 October | +11 | |||
| 13 October | +7 | |||
| 12 October | +2 | |||
| 11 October | +17 | |||
| 10 October | +71 | |||
| 09 October | +31 | |||
| 08 October | +112 | |||
| 07 October | +223 | |||
| 06 October | +53 | |||
| 05 October | +29 | |||
| 04 October | +25 | |||
| 03 October | +7 | |||
| 02 October | +17 | |||
| 01 October | +70 |
Channel Posts
ከደብረብርሃን ወደ አንኮበር የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ መካናይዝድ ጦር፡ በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ክፉኛ ተመቶ ወደ መጣበት ተመለሰ!!
ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
ሁለት ዙ-23፣ አንድ ቢኤም እና አንድ መድፍ ከ40 መኪና በላይ እግረኛ ጦር ይዞ ከደብረብርሃን ከተማ ወደ አንኮበር ከተማ ያቀናው የአገዛዙ መካናይዝድ ጦር በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በደፈጣ ተመትቶ ሲሸነፍ ወደመጣበት መመለሱን የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አስታወቀ።
በቀን 09/02/2019 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ኃይል ወደ ደብረብርሃን አምጥቶ ሙሉ መካናይዝድ አሠልፎ አንኮበር ከተማ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጦር፡ በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ክፉኛ መመታቱ ተገለፀ። ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገው ከባድ አውደ ውጊያ ሸንፈት የተከናነበው የአገዛዙ ጦር በርካታ ሙትና ቁስለኛ ማስተናገዱ ታወቀ።
በዚሕም ከባድ ውጊያ የአገዛዙ ጦር መሸነፉን ተከትሎ ተስፋ በመቁረጡ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አካባቢ ከአንኮበር ቤተ መንግሥት፤ ከአንኮበር መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቅርሶችን እና የከተማዋን የባንክ ገንዘቦችን ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ከቁስለኞቹ ጋር በ40 መኪና ጭኖ ወደ መጣበት ደብረብርሃን መመለሱ ተረጋግጧል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
| 2 | No text... | 480 |
| 3 | #አሳዛኝ_ዜና
በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ዋቤና ሺርካ ወረዳዎች
ክርስቲያኖች መገደላቸው ተገለጸ።
በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች ተገደሉ።
1️⃣ኛ. ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም በሺርካ ወረዳ
1. ጌቱ አሰፋ የተባለ ግለሰብ የእርሻ ሥራ(አዝመራ) ላይ እያለ የተገደለ ሲሆን፣ ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው በታጣቂዎች ተወስደዋል። ይህ ወንጀል የተፈጸመውም በቀን 7 ሰዓት ላይ ነው።
በተጨማሪም በቀን 7/02/2019 ዓ.ም. እንደገና በሺርካ ወረዳ ለሊት በሄላ ዘንባባ ቀበሌ፦
1. አቶ ዘውዴ ኃብቴ
2. ወ/ሮ አስራሱ ተስፋዬ ተገድለዋል።
በተጨማሪም፦
1. አቶ ፍርዴ አሰፋ
2. አቶ ገናና አሰፋ
3. አቶ እፋ ዘነበ
4. አቶ አስናቀ ዘውዴ
5. ወ/ሮ ወጋየሁ መርሻ በታጣቂዎች ተወስደዋል/ታግተዋል)
እንዲሁም፦ ካህን/ቀሲስ/ ናርዶስ አሰፋ ጉዳት ደርሶበት (ተቆስለው) በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።
2️⃣ኛ. በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም.፦
1. አቶ ዘነባ ነጋሽ
2. አቶ ሳሙኤል ዋሌ
3. አቶ ብሩህ አበራ ተገድለዋል።
በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በተደጋጋሚ በሚከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ምዕመናን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገደሉ፣ ከቀያቸው እና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ እንዲሁም ለከፍተኛ ችግሮች እየተጋለጡ የሚገኙ በመሆኑ፣ የሚመለከተው አካል እነዚህን ችግሮች አጣርቶ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ ከቀያቸው እና ከንብረታቸው ለተፈናቀሉም አስፈላጊው ጥበቃና ክትትል ተደርጎላቸው ወደ ቀያቸውና ንብረታቸው እንዲመለሱ አስፈላጊው ድጋፍ እንያረግላቸው፣ እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኙ ለቀሩት ሕዝብ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው አበክረን(አጥብቀን) እንጠይቃለን።
ሕይወታቸው ያለፈውን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን አፀደ በገነት ያኑርልን፣ ቆስለው በሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ ላይ የሚገኙትንም አምላክ ይፈውስልን።
እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነትን ይሰጠን።
መረጃው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚዳያ ነው። | 724 |
| 4 | No text... | 664 |
| 5 | Sent from WhatsApp
wa.me/12027133367 | 795 |
| 6 | መረጃ ሸዋ!!
ጠላት ከደብረብርሀን ወደ ጣርማበር መስመር እየወጣ ነው! ጥንቃቄ
ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም | 869 |
| 7 | ተጠናክሮ የቀጠለው የንፁኋን ጭፍጨፋ!!!
ጥቅምት 9 / 2019 ዓ.ም
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ መንደር ሶስት ቀበሌ በስራ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን በግፍ ረሽነዋል።
ዛሬ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ከአንገር ጉትንና ከተለያዩ ቦታዎች በመሰባሰብ በአንዶዴና በበጭበጭ ጊዮርጊስ ሲንቀሳቀስ የነበረ የክልሉ ገዳይ ሀይል በጭበጭ ጊዮርጊስ አከባቢ ሰብል በመሰብሰብ ላይ
ያሉ ገበሬዎች የጥይት ሩምታ በማውረድ ከቦታው አሳደዋቸው ይገኛሉ።
በመቀጠልም ይህ ገዳይ ሀይል ወደፊት በመቀጠል መንደር 3 ቀበሌ በመግባት ቦለቄ በመውቃት እና በቆሎ በመሸልቀቅ ላይ ያሉ 13 ንፁኋን አማሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽነዋል።
አፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ
ህ/ግንኙነት መምርያ | 857 |
| 8 | የአገዛዙን ፀረ-ህዝብ ወረራ ለመመከት የደራ ወረዳ የአባት አርበኞች ጦር በድምቀት ተደራጀ!!
ጥቅምት 9 / 2019 ዓ.ም
====== //=========
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሐቤቴ አውራጃ ደራ ወረዳ የአገዛዙን ፀረ-ህዝብ አካሄድና በህዝብ ላይ የሚፈጸመውን በደል በቁርጠኝነት ለመመከት የሚያስችል ብቁ የሆነ የአባት አርበኞች ጦር ተደራጀ።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ነፃ በወጡ አካባቢዎች አስተማማኝ ጦርን የማደራጀትና ህዝባዊ ውይይቶችን የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በዚሁ መሠረት በደራ ወረዳ ሰረርኩላ ክላስተር 4 ሻለቃ የአባት አርበኞች ጦር ተደራጅቷል። ከዚህ ቀደም በደራ ወረዳ ቱቲ ክላስተር ሥር 6 ሻለቆች መደራጀታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ይህ የማደራጀትና የማሰልጠን ሥራ ተጠናክሮ በመቀጠል በደራ ወረዳ በሰረርኩላ ክላስተር ሻለቃ 7፣ ሻለቃ 8፣ ሻለቃ 9 እና ሻለቃ 10 መደራጀታቸው ተገልጿል።
የደራ ወረዳ ህዝብ በብልፅግና አገዛዝ በቀየው በርካታ በደልና እንግልት የደረሰበት መሆኑን በመገንዘብ፤ አሁን ላይ ራሱን ከጥፋት መታደግና መደራጀት ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል። በዚህም መሠረት ህዝቡ በነቂስ በመነሣትና በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ባወረደው መመሪያ መሠረት በሰፊው እየሰለጠነና እየተደራጀ ይገኛል።
በዚህ የማደራጀትና የውይይት መርሃ-ግብር ላይ የድርጅት፣ የዕዝ፣ የኮርና የክ/ጦር አመራሮች የተገኙ ሲሆን፤ ሰፊ ስልጠናና አቅጣጫ ሰጥተዋል። አመራሮቹ በወቅቱ እንደገለጹት፣ ህዝቡ ህልውናውን ለማስከበር ያለው ተነሳሽነትና ሞራል እጅግ ልዩና አበረታች ነው ብለዋል።
በዕለቱም የተደራጀው የአባት አርበኞች ጦር መሪዎቻቸውን በመምረጥ ማንኛውንም ድርጅታዊ ግዳጅ ለመወጣት እና የህዝብን ህልውና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር ያላቸውን ከፍተኛ ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
" ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ | 1 032 |
| 9 | No text... | 977 |
| 10 | ጣረሞት ላይ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ቀን በቀን በምት እና በመኮብለል እየፈረሰ ነው።
==================
ጥቅምት፦ 09/ 2019 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በሰናን አባጅሜ ንስሮች ቀን እንዳይንቀሳቀስ ሌት እንቅልፍ እንዳይተኛ የተከለከለው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት ቀን በቀን እየፈረሰ ትግሉን እየተቀላቀለ ይገኛል።
1. ሀመድ አረቡመር
2. ኡመር ጃፋር
3. ታጁ ቀመር
4. አብረማን ጀማል➡️ጋንታ መሪ የነበረ
. ኤልያስ ከሊፉ➡️ጋንታ መሪ የነበረ
117ኛ ክፍለ ጦር የ5ኛ ሻለቃ አባል የነበሩ አምስት የስርዓቱ አገልጋይ የመከላካያ ሰራዊት አባሎች ስናን ረ/ገብያ መሽጎ ጣረሞት ላይ ከሚገኘው ሰራዊት በመኮብለል ከጀግኖቹ የስናን አባጅሜ ሻለቃ ልጆች ጋር በሰለም ተገናኝተው የእንኳን ደና መጣችሁ አቀባብል ተደርጎላቸዋል።
መረጃው:- የስናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግሰት ሚዲያ እና ግንኙነት ነው
ድሉ ይቀጥላል!
አንድነታችን የትብብራችን ውጤት ነው!
| 1 070 |
| 11 | No text... | 980 |
| 12 | በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሐቤቴ አውራጃ ላይቤት ወረዳ ኮላሽ ቀበሌ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ!!
ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም
በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ በቅርቡ ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው የላይቤት ወረዳ ኮላሽ ቀበሌ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት መካሄዱ ተገለጸ።
በተካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት፤ ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ስለ አደረጃጀት፣ ስለ ሕዝባዊ ትግሉ እና ስለ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ውይይትና ምክክር አድርገዋል። በነበረው ሕዝባዊ መድረክ ላይ ስላለፈው የትግል ጉዞ የተገመገመ ሲሆን፤ ሕዝቡ ላነሳቸው ጠንካራ ጥያቄዎች ግልፅ ምላሽ ሲሰጥ፡ ለአደረጃጀቱ ጥንካሬ የጠቆሙት ምክሮችን በመቀበል የጋራ አቋም ተቀምጧል።
በነቂስ ወጥቶ የተሳተፈው የኮላሽ ቀበሌ ሕዝብ በበኩሉ፣ ፋኖ ባለፉት የትግል ጉዞዎች ላደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ አድናቆቱን ሲገልፅ፡ ፀረ-ሕዝቡ የብልፅግና ሥርዓት ሕዝባዊ ተቋማትን ማፍረስ፣ አርሶ አደርን ማሰቃየትና መዝረፍ፣ እንዲሁም ሌሎች አሰቃቂ ድርጊቶች መፈጸሙን ሕዝቡ በመድረኩ አንስቷል። በዚህም ምክንያት ከዚህ በኋላ የሚደረገው ትግል ይበልጥ ሕዝባዊ መሆን እንዳለበት የጠቆመው ሕዝቡ፤ የአባት አርበኛ እና ሌሎች አደረጃጀቶች ተጠናክረው በመዋቅር መታገል የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል።
የዕዙ አወያይ አመራሮችም ሕዝቡ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት እና በቀጣይ ሊሠሩ የሚገቡ መሠረታዊ ሥራዎች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱን አጠናቀዋል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ | 1 062 |
| 13 | No text... | 1 024 |
| 14 | የአፋብን የፖሊት ቢሮ አባልና ም/አዛዥ ለወታደራዊ ጉዳዮች ኃላፊ እንዲሁም የምዕራብ ግንባር ዋና አዛዥ አርበኛ ዝናቡ ልንገረው፣የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ 3ኛ ዕዝ ም/አዛዥ ለወታደራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው ፣የበላይ 3ኛ ዕዝ አካል የሆነው የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በሊሁን ጌታቸው ፣የመይሳው 2ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ጌታቸው አማረን ጨምሮ ሌሎች የኮሩ እንዲሁም የቋራ ኦሜድላና የአድዋ ክፍለጦር አመራሮች በጎንደር ሰማይ ስር!
በአንድነት ወደፊት !
ድል ለአማራ ፋኖ | 1 096 |
| 15 | የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ነፃ ባወጣት ታሪካዊቷ ዘመሮ ከተማ፡ ከሕዝብ ጋር ሰፊ ውይይቶችን አካሄደ!!
ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም
በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ጀብድ ተሰርቶባት ከአገዛዙ የስቃይ ቀንበር ነፃ የወጣችው ታሪካዊቷ ዘመሮ ከተማ፣ ነፃነቷን ተከትሎ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን እያካሄደች ይገኛል።
ከተማዋ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ በዕዙ ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ሰፊና ጥልቅ ውይይቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን፣ ህዝቡም ለትግሉ በሚጠቅም መልኩ ገንቢ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን እየሰጠ ይገኛል። ለቀናት የዘለቀው ይህ ሰፊ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ የማህበረሰብ አያያዝን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን፣ በወረዳውና በከተማዋ የሚከናወኑ ሰላማዊ የደህንነት ስራዎችን እንዲሁም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን እንቅስቃሴ በስፋት በመገምገም ሕዝባዊ ውሳኔዎች ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩም ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሁሉ ያለምንም ስጋት በነፃነት ስራቸውን እንዲጀምሩ ጥብቅ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን፣ ህዝቡም ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት መጀመሩ የፋኖን ሕዝባዊነትን እና አብዮታዊ ታማኝነት በተግባር ያሳየ ታላቅ ምዕራፍ ሆኗል።
ይሕንን ተከትሎ የዕዙ አደረጃጀት በከተማዋ የአፋብን መዋቅር እየተደራጀ መሆኑ ተረጋግጧል። በቀጣይ ለታላላቅ የተቋማት ስራዎች እና ለአካባቢው መሪዎች የሚሰጡ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሲገለፅ፤ ዕዙ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሁሉ የሕግ አሠራር እዲከበር ግልጽ አቅጣጫ አስቀምጧል። በዚህም መሰረት በሚመለከታቸው አካላት ጥልቅ ውይይቶች ተደርገው የአደረጃጀት ስራዎች እና የሕዝብ ተሳትፎዎች በነፃነት እደሚቀጥሉ ተብራርቷል።
በመጨረሻም መድረኩ ላይ የተገኙ የከተማዋ ነዋሪዎችና ተሳታፊዎች እንዳሉት፤ ፋኖ የሚታገለው ለሕዝብ መሆኑን የአማራ ህዝብ በውል የሚያውቀው ሀቅ ቢሆንም፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ከሚሉት በተቃራኒው፡ በአካልና በተግባር በታየው ምግባር ይበልጥ ስናይ፣ ፋኖ የሚኖረው ለዕውነትና በዕውነት መሆኑን አረጋግጠናል እና ሁልጊዜም ከእናንተ ጎን እንቆማለን ሲሉ ገልጸዋል።
" ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ | 1 033 |
| 16 | No text... | 980 |
| 17 | ሰበር ዜና! ትብብር ለህልውና” ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢኦ ንግግር ምላሽ ሰጠ!
የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና (ትብብር ለህልውና) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢኦ ከሲ-ስፓን (C-Span) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ግጭት የሰጡትን አስተያየት አስመልክቶ ይፋዊ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ትብብር ለሕልውና ባወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ “ትብብር ለህልውና” የሚያካሂዳቸው ራሱን የመከላከል ወታደራዊ እርምጃዎች አገሪቱን የመከፋፈል ወይም የመበታተን “ገንጣይ” ዓላማ የሌላቸው መሆኑን አስታውቋል።
ለሰላማዊ እርቅና ድርድር ተደረጉ የተባሉ ጥረቶች በብልፅግናው ስርዓት ውድቅ ከተደረጉ በኋላ እርምጃው የመጨረሻ አማራጭ ሆኖ እንደተወሰደ ተገልጿል። በመሆኑም እንቅስቃሴውን “ገንጣይ” ብሎ መፈረጅ በህግም ሆነ በፖለቲካ ትክክል አለመሆኑንና የትብሩ ዋና ዓላማ አካታች የዲሞክራሲ ሽግግር ማምጣት መሆኑን አብራርቷል።
በተጨማሪም የትብብር ለሕልውና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች “ሽብርተኝነት” ብሎ መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ የብልፅግናው ስርዓት በቁጥጥር ስር ባሉ ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጭምር ዘመናዊ መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ይገኛል ተብሏል። ይህ ዓይነቱ ፍረጃ የብልፅግናው ስርዓት የጦርነት አጀንዳውን ያለ ምንም ተጠያቂነት እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑም ተመልክቷል።
በመጨረሻም “ትብብር ለህልውና” አሜሪካ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሚዛናዊና ገንቢ አቋም እንድትከተል ጥሪ አቅርቧል። | 1 156 |
| 18 | No text... | 1 111 |
| 19 | ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ💪 ይችላል ስልህ በኩራት ነዉ ደረቴን ነፍቼ ማለት ነዉ | 1 047 |
| 20 | ሰበር ዜና!
ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 15ኛ ኮር በምስራቅ ግንባር አጅባር ወረዳ ላይ ታላቅ ገድል ፈፀመ!
የትብብር ለሕልውና አካል የሆነው አፋብን በምስራቅ ግንባር በጠላት ላይ ታላቅ የበላይነትን እየተቀዳጀ ይገኛል። ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ጥቅምት 08/2019 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ ቀጠና አጅባር ወረዳ ላይ በ15ኛ ኮር ነበልባሏ 156ኛ ታቦር ክፍለጦር ሬሽን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመዋል።
15ኛ ኮር 156ኛ ታቦር ክፍለጦር ከሰኞ ገበያ እስከ ሸንጎ ደፈር ጫፍ ድረስ ባደረገችዉ የአዉደ ዉጊያ ዉሎ የሬሳ ክምር አሸክማ ወደጉሬዉ መልሳዋለች። በርካታ የአገዛዙን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ሲጓጓዝበት የነበረዉ ሶስት ካሶኔ መኪና በቆንጆቹ ቀጨም መደረጉን የ15ኛ ኮር ቃል አቀባይ መረጃዉን አድርሷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ
ጥቅምት 08/ 2019 ዓ/ም | 1 210 |
