uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 389
Obunachilar
-324 soatlar
+2587 kun
+1 43630 kun

Ma'lumotlar yuklanmoqda

O'xshash kanallar
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
Okt '26
Oktabr '26
+968
7 kanalda
Sentabr '26
+1 091
1 kanalda
Get PRO
Avgust '26
+133
1 kanalda
Get PRO
Iyul '26
+112
3 kanalda
Get PRO
Iyun '26
+101
3 kanalda
Get PRO
May '26
+195
4 kanalda
Get PRO
Aprel '26
+193
6 kanalda
Get PRO
Mart '26
+278
7 kanalda
Get PRO
Fevral '26
+590
7 kanalda
Get PRO
Yanvar '26
+363
5 kanalda
Get PRO
Dekabr '25
+129
2 kanalda
Get PRO
Noyabr '25
+394
8 kanalda
Get PRO
Oktabr '25
+570
9 kanalda
Get PRO
Sentabr '25
+710
8 kanalda
Get PRO
Avgust '250
4 kanalda
Get PRO
Iyul '25
+48
2 kanalda
Sana
Obunachilarni jalb qilish
Esdaliklar
Kanallar
21 Oktabr0
20 Oktabr+10
19 Oktabr+10
18 Oktabr+34
17 Oktabr+57
16 Oktabr+177
15 Oktabr+5
14 Oktabr+11
13 Oktabr+7
12 Oktabr+2
11 Oktabr+17
10 Oktabr+71
09 Oktabr+31
08 Oktabr+112
07 Oktabr+223
06 Oktabr+53
05 Oktabr+29
04 Oktabr+25
03 Oktabr+7
02 Oktabr+17
01 Oktabr+70
Kanal postlari
ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥልቅ ግምገማውን በስኬት አጠናቀቀ! ​ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ​የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር፣ የነበሩበትን ክፍተቶች በማስተካከል ይበልጥ ጥንክሮ ለመቀጠል ያስችለው ዘንድ የዕዝ፣ የክፍለ ጦር፣ የኮር እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት ለሶስት ቀናት ሲያካሂደው የቆየውን ጥልቅ ውይይትና ግምገማ በስኬት አጠናቋል። ​በዚሁ መድረክ የክፍለ ጦሩ አመራሮች በትግል ሂደቱ ላይ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ ጽናትና ተጋድሎ በታላቅ ጥንካሬ ተነስተዋል። በተጨማሪም ክፍለ ጦሩ አሁን ላይ ያለበትን ቁመና እና በስራ አፈጻጸም ላይ የተስተዋሉ ችግሮች መታረም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል። ​ያለፉ የአመራር ስልቶችን ይበልጥ ለማስተካከል ያለመ የሂስና ግለ-ሂስ መድረኮች ተፈጥረው፤ ካለፉ ስልቶች የመማር እና የወደፊት ግልጽ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ክፍለ ጦሩ ይበልጥ ጠንክሮ እንዲወጣ ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር። ​በመጨረሻም የክፍለ ጦሩ አመራሮች ላለፉት ጊዜያት የተነሱባቸውን ድክመቶችና ትችቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ፤ በነፍስ፣ በደም እና በአጥንት የተገነባውን የአማራ ህዝብ ትግል ማስቀጠልና የትግሉ አልፋና ኦሜጋ አንድነት መሆኑን በመገንዘብ ቃል የገቡ ሲሆን ክፍለ ጦሩን ለቀጣይ ግዳጅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ የማድረግ ስራም መጠናቀቁን አስገንዝበዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

2
+9
Matn yo'q...
451
3
የአገዛዙ ሠራዊት ሻምበል መሪና ጋንታ መሪ ጓዶቻቸውን ጨምረው ሕዝባዊ ትግሉን መቀላቀላቸው ተገለፀ!! ​ ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ለብልጽግና የአገዛዝ ሥርዓት ተሠልፈው የመከላከያ ሠራዊትን ሲመሩ የ+4
የአገዛዙ ሠራዊት ሻምበል መሪና ጋንታ መሪ ጓዶቻቸውን ጨምረው ሕዝባዊ ትግሉን መቀላቀላቸው ተገለፀ!! ​ ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ለብልጽግና የአገዛዝ ሥርዓት ተሠልፈው የመከላከያ ሠራዊትን ሲመሩ የነበሩት ሻንበል መሪና ጋንታ መሪ ከነጓዶቻቸው አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝን ተቀላቅለው ከሕዝብ ጎን መቆማቸውን ቀጥለዋል። በየቀኑ እየፈረሰ የሚገኘው የአገዛዙ ሠራዊት፡ ፋኖን በመቀላቀል ሕዝባዊ ትግሉን እየደገፈ ሲገኝ፡ ፀረ-ሕዝብ ፖሊሲ የአገዛዝ ስርዓት እያከተመለት እደሚገኝ ከጦር መሪዎቹ ማረጋገጥ ተችሏል። ሕዝባቸውን በክብር ለማገልገል ትግሉን የተቀላቀሉት እጅግ ብዙ ቢሆኑም፡ አመቺ ጊዜና ቦታ እየጠበቁ ፋኖን የሚቀላቀሉ እጅግ ብዙ መሆናቸው ተረጋግጧል። በቀን 10/02/2019 ዓ.ም ከ6ኛ ዕዝ 85ኛ ክፍለ ጦር ወደ አፄ አምደ ጽዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር እና ከአገዛዙ 18ኛ ክፍለ ጦር ወደ ከሠም ፪ኛ ኮር ኃ/ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉ አባላት ዝርዝር ፦ 1. ፶ አለቃ ታደለ አበራ ------ሻንበል መሪ 2. ገዛኸኝ አለሙ-------አባል 3. ፈጠነ ዳኜ--------አባል 4. ፶ አለቃ አሊ መሀመድ-------ጋንታ መሪ 5. አለሙ መኮንን----------አባል 6. አሻግሬ ድንበሩ---------አባል ➠ ይዘው የተቀላቀሉት ንብረት ዝርዝር፦ ● 1 ስናይፐር ● 5 ጥቁር ክላሽኮቭ ● 2 ዶጅ ክላሽኮቭ ● 1 የጦር ሜዳ መነፅር ● በርካታ ተተኳሽና ወታደራዊ ቁሳቁሶች " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
466
4
➶ ድሮን ➶ የጥንቃቄ መልዕክት ⚠️ አሁን ከምሽቱ 2:45 ጀምሮ በሬማ ከተማና አካባቢው የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
➶ ድሮን ➶ የጥንቃቄ መልዕክት ⚠️ አሁን ከምሽቱ 2:45 ጀምሮ በሬማ ከተማና አካባቢው የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
806
5
'' ወይ አላየችው ጉዷን እሱን የወለደች...''😥
'' ወይ አላየችው ጉዷን እሱን የወለደች...''😥
849
6
አሳዛኝ ዜና!!! በወለጋ አድማሱን እያሰፋ እና መልኩን እየቀየረ የቀጠለው       የንጹሃን አማራ ግድያ  ና ማፈናቀል ፣የቤት ና የንብረት ማውደም ፣እንድሁም የጂምላ እስራት ይህ ፀረ -አማራ እና ፀረ -ኢትዮጵያዊ የሆነው የብልጽግና ስርዐት አጠናክሮ ቀጥሎበታል ። ይህ ፀረ -ህዝብ አገዛዝ በተለየ ሁኔታ በተለይም  በምስራቅ ወለጋ ዞን ጭፍጨፋውን ቀጥሏል ሰሞኑን በዛሬው ወራት በኪረሙ ወረዳ እና በጊዳ አያና ወረዳ የንፁሃን ጭፍጨፋና የቤት ቃጠሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በጊዳ አያና ወረዳ ሙሉ በሙሉ እደወደሙ ስንገልፅ የነበሩት ከተሞች ማለትም፦    👉ፈንደቃ ከተማ    👉አንዶዴ ከተማ    👉መንደር3 ከተማ    👉መንደር 22 ከተማ    👉በጭበጭ ጊዮርጊስ እና   👉መለከታ ከተማ ሙሉ በሙሉ እደተቃጠሉና ከጥቃቱም የተረፈ በርክታ ንፁሃኖች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ በስደት ከ65ሺ በላይ የሚገመቱ ንፁሃኖች በጫካ እየተሰቃዩ እደነበሩና አሁንም  በዚሁ ላይ እደቀጠለ ስንገልፅ ነበር። ዛሬ ላይም ይህንኑ ግፍ አጠናክሮ በመቀጠል በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ የስርዓቱ አገልጋይ ሃይል እና የክልሉ ጥምር ገዳይ ሃይል ከአንገር ጉትንና ከኪረሞ ከተማ በመነሳት በከባድ መሳርያ ሰፈሩን በመደብደብ "አሊ" ከተማን ከቤት መውጣት ያልቻሉ አረጋውያንን እና ተማሚዎችን ጨምሮ ቤት ውስጥ እዳሉ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አቃጥለዋል። ይህ በእድህ እዳለ  የአገዛዙ ስራዊት እና የክልሉ ጥምር ሃይል ሚሊሻ ፣ሪፔ ሎላ ፣አድማ ብትን እና ገዳ ኮማንዶ በጥምር በመሆን በኪረሙ ወረዳ ስር ወደሳ ዲማ ቀበሌ በመግባት ንጹሃን አማራ ይላማ ያደረገ የንብረት ዘረፋ ና መፈናቀል ሲያደርጉ ውለዋል ።50 የቀንድ ከብቶች እና 29 ፍየሎች ዘርፈው ወስደዋል።በተጨማሪም አንድ የ76 አመት ሽማግሌ አዛውንት በጥይት ደብዲበው አቁስለው ገደልን ብለው ህደዋል ።ቀሪው ህዝብ በጫካ አሳደውታል። አፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ   ህ/ግንኙነት መምርያ ጥቅምት 10 / 2019
902
7
(ሀገር እና ኪነ-ጥበብ ) ፋኖ አላዓዛር ዳግማዊ ቴድሮስ # ሀገር እና ኪነ-ጥበብ፡ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። * ሀገር ከሌለ ኪነ-ጥበብ አይኖርም፤ ኪነ-ጥበብም ከሌለ ሀገር አይኖርም። * በየትኛውም ከፍታ ላይ የሚኖር የሰው ፍጡር ሁሉ ለኪነ-ጥበብ ይንበረከካል! *ኪነ-ጥበብ በአንዲት ሀገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ። የንቃት ሚና ይጫወታል። የሀገርን እድገት በማሳለጥ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የህዝብን አንድነት በመጠበቅ እና ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ኪነ-ጥበብ አንዲት ሀገርን ከሚመራ መንግስት በላይ ሁኖ ህዝቡን የመምራት አቅም አለው። ይህም ማለት ሀገርን የሚመራ ፓርቲ ወይም መንግስት ህዝቡን ያለ አግባብ ቢበድል፣ የሀገርን እድገት ቢያጓትት እና ጥቅሟን እንደማያስከብር ሲያሳይ፣ ኪነ-ጥበብ ህዝቡን በመቀስቀስና በማንቃት እንዲደራጅ ያደርጋል። በዚህም አስተዳደሩ አካሄዱን እንዲያስተካክል፣ ልማቱን እንዲያፋጥን እና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ከማድረግ አልፎ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት እስከመቀየር የሚደርሱ ሂደቶችን ያከናውናል። ታዲያ ይህ የሚሆነው የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት የሚሹ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ለሀገር የሚጨነቁ የፖለቲካ ልሂቃንና ድርጅቶች ሲቀናጁ ነው። የህዝቦችን ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅም በማጠናከር የጋራ ታሪክና ሀገር እንዲኖራቸው ማድረግ፣ እንዲሁም ቋንቋን፣ ባህልንና ወግን ለዓለም ማስተዋወቅ ይቻለው ዘንድ ኪነ-ጥበብ እንደ አንድ ሀገራዊ እጣ ፈንታ ወሳኝ ተቋም ሆኖ መደራጀት አለበት፤ እራሱን የቻለ ህግ፣ ደንብና መመሪያም ሊኖረው ይገባል። * ኪነ-ጥበብ በዓለም ላይ በደማቅ ቀለም ከተጻፉ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የድል ታሪኮች ሁሉ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። * ከአባቶቻችን ታሪክ መለስ ብለን ስናይ፣ ሀገራቸውን ወሮ ሃብታቸውን ለመዝረፍ፣ ሃይማኖታቸውን፣ ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ሊያጠፋ የመጣውን የውጭ ወራሪ ለመመከት ኪነ-ጥበብ ህዝቡን በማንቃትና በማቀናጀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ጀግኖች በገጠማቸው ጠላት ላይ የሞራል የበላይነት እንዲኖራቸው በማድረግ፣ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀውን ወራሪ ሀይል ጭምር በማንበርከክ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ታሪክ እንዲኖረው አድርጓል። ነገር ግን የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት በማይፈልጉ አካላትና አምባገነን መሪዎች እጅ መውደቁ ሀገርን ጎድቷል። ህዝቦችን ከማጠናከር ይልቅ ማዳከም፣ የጋራ ታሪክ ከመገንባት ይልቅ ባህልና ወግን ማጥፋት፣ እንዲሁም በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በቀለም ልዩነት ህዝቡን መከፋፈልና መጠፋፋት ላይ እንዲሠለፍ ተደርጓል፤ ይህም ሀገራችን አሁን ላለችበት ሁለንተናዊ ቀውስ ተዳርጋለች ። ፖለቲካ ጥበብ፣ ውትድርናም ጥበብ በሆነበት ዓለም ውስጥ በሀገራችን ያሉ የፖለቲካ ልሂቃን ለኪነ-ጥበብ የሚሰጡት ዋጋ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ እናየዋለን። በመሆኑም ኪነ-ጥበብን በአግባቡ በመጠቀም የህዝብንና የሀገርን ሁለንተናዊ ጥቅም ማስከበር፣ ማስተማር እና የጋራ ታሪክና ባህል መገንባት ይቻላል። > የጋራ ታሪክ የሌለው ህዝብ የጋራ ሀገር አይኖረውምና! > ለነፃነታቸው በሚታገሉ ታጋዮች የትግል ጉዞ ውስጥ የረሃብ፣ የውሃ ጥም፣ የጸሀይ፣ የብርድና የድካም ማስረሻ በመሆን፣ እንዲሁም የተሰዉና የቆሰሉ ጓዶቻቸውን ማስታወሻ በመሆን በመዘከር ረገድ ኪነ-ጥበብ የላቀ ድርሻ አለው። ሀገር ያቆመው የአማራ ህዝብ ራሱን ለመከላከል አቅቶት፣ በጠላቶቻችን አጀንዳ በተቀበሉ እና ለሆዳቸው ባደሩ ግለሰቦች ምክንያት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመበር አዳዲስ የሀሰት ትርክቶችን ሲያሰሩበት ቆይቷል። በአለፉት 50-60 ዓመታት በራሱ ወገን ባልሰራው ሲወቀስ፣ ባላደረገው ሲከሰስ በገንዛ ሀገሩ በሰላም እንዳይኖር ተፈርዶበት ቤቱ ከላዩ ላይ ሲቃጠል፣ ሀብቱ ሲዘረፍ፣ በረሃብና በውሃ ጥም ሲቸገር፣ ሲታሰር፣ ሲሰደድ፣ እርጉዞች በጫካ ሲወልዱ እና በጨካኞች ሲታረድ ቆይቷል። ስለዚህ የአማራን ህዝብ እውነተኛ የጋራ ታሪክ የሚጽፍ፣ አንድነቱን የሚያጠናክር፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅሙን የሚገነባ፣ የተጣመሙ ታሪኮችን የሚያቃና የተደራጀና የተቀናጀ የኪነ-ጥበብ እና ሚዲያ ተቋም መገንባት ያስፈልጋል። የአማራን ህዝብ ከጥፋት እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለማዳን እየታገለ ያለው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ዓላማውን ከግብ ለማድረስ እና ህዝቡን ከቀድሞ ችግሮቹ በዘላቂነት ለማላቀቅ የኪነ-ጥበብ ሚና ወሳኝ ነው። የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት የሚሹ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የፖለቲካ ልሂቃን ተቀናጅተው ህዝቦች የጋራ ታሪክና ሀገር እንዲኖራቸው ማድረግ ለነገ የማይባል ተግባር ነው። #ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት! 🙏🙏 #ህሊናችን በተባበረ ክንዳችን! 💪 #ኢትዮጵያ ሀገራችን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራችን፣ #አማራነት ማንነታችን፣ አፋብን መዳኛችን ነው!! *አዲስ ትውልድ ፤ አዲስ አስተሳሰብ ፤ አዲስ ተስፋ!* አላዛር
833
8
Matn yo'q...
731
9
ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከብርቱ ወታደራዊ ተጋድሎዎች ጎን ለጎን በሰሜን ወሎ ዞን ደማቅ ሕዝባዊ ውይይት አካሄደ! በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ከ013 ቀበሌ ነዋሪወች ጋር ስለ አማራ ህዝብ ትግል አላማና ግብ፣ በመልካም አስተዳደር ችግር በተለይ ስለ እርስ በእርስ ግድያ፣ ወደፊት ስለሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱን የመሩት የዳውንት ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ሲሆኑ በመድረኩም የአማራን ህዝብ ትግል አላማና ግብ በማስገንዘብ አሁን ባለንበት ወቅት ማህበረሰቡ እርስ በእርስ የሚጠፋፋበት ሳይሆን አንድ በመሆን ጠላታችንን መገርሰስ መሆን እንዳለበት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የእርስ በእርስ ግድያን ለማስቆም በወረዳው ውስጥ በየቀበሌዉ ያሉ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌወች እና አባት አርበኞች ሰፊ ስራ በመስራት ከሃያ አምስት (25) በላይ በእርስ በእርስ ግድያ ምክንያት ትጥቅ ታጥቀው በዱር በገደል የሚንቀሳቀሱ አካላቶችንን እርቅ በማካሄድ ተመልሰው ከፊሎቹ ቤት ንብረታቸውን እንዲመሩ ሲደረግ ቀሪወቹ ደግሞ ከአባት አርበኛ እና ከመደበኛዉ ፋኖ ጋር በመቀላቀል እየታገሉ እንደሚገኙ ተገልጿል። በልዩ ሁኔታ የሲቭል አስተዳደሩም  እርቅና ድርድር  በማይቀበሉ ሀይሎች ላይ ድርጅቱ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ ለአካባቢው ማህበረሰብ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን   መምሪያ ጥቅት 10/ 2019 ዓ/ም
768
10
+2
Matn yo'q...
772
11
በደቡብ ወሎ መሐል ሳይንት ወረዳ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አራት ንፁሐን ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 7 የሚደርሱ ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። 1ኛ.አንዷለም ጌታቸዉ=(የአማራ ባንክ ጥበቃ)=የተሰዋ 2ኛ. ደረሰ መንግስቴ= (የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ)=የተሰዋ 3ኛ.ቃልኪዳን ፍሰሀ= (በዘንድሮዉ አመት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች) =የተሰዋች 4ኛ.ወይንሸት ላንተነዉ=(የሀይስኩል ተማሪ)=የተሰዋች 5ኛ.ደምሰዉ ንጉሴ= (የአማራ ባንክ ጥበቃ) =ከባድ ቁስለኛ 6ኛ.ዘለቀ ሀይሌ= (የአማራ ባንክ ጥበቃ)=ከባድ ቁስለኛ 7ኛ. እያሱ አለሙ= (የመኪና እረዳት)= ቀላል ቁስለኛ 8ኛ.ሳባ አንባቸዉ=(ሰላማዊ ነዋሪ)= ቀላል ቁስለኛ 9ኛ. እሱባለዉ ንጉስ=( የ8 አመት ህፃን)=የቆሰለ 10ኛ. ሀና በቀለ=(የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ)= ከባድ ቁስለኛ 11ኛ.ስንታየሁ=( ሻሂ ቤት በመስራት ሂወቷን የምትመራ)=
863
12
+3
Matn yo'q...
890
13
#ሲያልቅ_አያምር⚠️ #ፋኖን_የከዳ_አለበት_ዕዳ ➶ ፋኖን ከድቶ ወደ ብልፅግና የገባው #ኮለኔል_ማነገረው_መለሰ በአደረበት ሆቴል ተገድሎ ተገኘ❗️ በደብረብርሀን ብርቱካን ሆቴል አልጋ ቤት ተገድሎ መገ
#ሲያልቅ_አያምር⚠️ #ፋኖን_የከዳ_አለበት_ዕዳ ➶ ፋኖን ከድቶ ወደ ብልፅግና የገባው #ኮለኔል_ማነገረው_መለሰ በአደረበት ሆቴል ተገድሎ ተገኘ❗️ በደብረብርሀን ብርቱካን ሆቴል አልጋ ቤት ተገድሎ መገኘቱን የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል።
1 054
14
እግዞ እግዞ እግዞ **^^ አረ ሰው አለቀ ጎበዝ። እነዚህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው። ጥምር ሀይሉ እንዲህ እየዘረገፋቸው ነው። የአብይ አሕመድ ወንበር ለመጠበቅ እንዲህ ማለቅ ያስፈል
እግዞ እግዞ እግዞ **^^ አረ ሰው አለቀ ጎበዝ። እነዚህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው። ጥምር ሀይሉ እንዲህ እየዘረገፋቸው ነው። የአብይ አሕመድ ወንበር ለመጠበቅ እንዲህ ማለቅ ያስፈልጋልን? አረ ልብ በል ጎበዝ!
1 078
15
አገዛዙ በዛሬው ዕለት በትምህርት ገበታ ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የድሮን ጭፍጨፋ ፈጽሟል! ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የብልጽግና አገዛዝ በደቡባዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ሳና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት+3
አገዛዙ በዛሬው ዕለት በትምህርት ገበታ ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የድሮን ጭፍጨፋ ፈጽሟል! ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የብልጽግና አገዛዝ በደቡባዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ሳና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ተማሪዎችን የጨፈጨፈ ሲሆን፣ በርካቶችንም ከከባድ እስከ ቀላል አካላዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል። በተጨማሪም በዕለቱ ከቀኑ 5:40 ሰዓት ላይ በአንዳቤት ወረዳ ወለሽ ከተማ የሚገኘውን የከተማ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አውድሟል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1 143
16
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ሰፊ ውይይቶች ማድረጉ ተገለፀ!!          ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝና ግሼ አውራጃ መንዝ-ጌራ ወረዳ ከተለያዩ የአገልግሎት ሠጪ ተቋማት ጋራ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ አመራሮች በመሀል ሜዳ ከተማ ሰፊ የውይይት መድረክ አከናወነ። የመንዝ-ጌራ ወረዳ ከተማ ከአገዛዙ ነፃ መውጣቷን ተከትሎ፡ የተለያዩ ተቋማት ለጥቂት ቀናት ስራ አቁመው ስለነበረ፡ ለሕዝብ አገልግሎት ሠጪ ተቋማት እና ቴክኒክና ሙያ ተቋም ወደ ስራቸው ተመልሰው ሰላማዊ አገልግሎት እዲሠጡ በሚያስችል ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ስራ እዲጀምሩ ተደርጓል። በውይይቱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፡ የአማራ ሕዝብ የትግል ምክንያቶች፣ የአታጋይ ድርጅቱ ቁመና፣ የአሠራር መርህ ግልፀኝነት እዲሁም የአደረጃጀት ቅንጅቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ለተነሱትም ጥያቄዎች በቂ ምላሾች ከዕዙ አመራሮች ተሠጥቶባቸው፤ ተቋማቱ በተሟላ ደሕንነት አገልግሎት እዲሠጡ ተደርጓል። በመንዝና ግሼ አውራጃ መሀል ሜዳ ከተማ በብልፅግናው ስርዓት መብቱ ተረግጦ፣ ለሚሊሻ በሚል ስልታዊ የሀብት ምዝበራ በማድረግ፤ ህልውናው አደጋ ላይ እዲወድቅ በርካቶችን አራቁቶ ለእርስ በርስ መጠፋፋት ማጋለጡን ገልፀው፡ አሁን በልጆቻቸው የፖለቲካዊ ትጥቅ ትግል ህልውናው እደሚረጋገጥ እና ከትግሉ ጎን እደሚሠለፉ በውይይቱ አረጋግጠዋል። የብልፅግና የአገዛዝ ስርዓት መብትን ከመንፈግ አልፎ ፀረ-ሕዝብ መሆኑን ተሳታፊዎቹ ሲያረጋግጡ፡ ሠሞኑን በነበረው አውደ ውጊያ የከተማው ከንቲባን፣የከተማው ሠላምና ደህንነት ኃላፊን እና ሌሎችንም ጨምሮ በጫካ ለመሸሸግ ቢሞክርም፡ ፋኖ በፈፀመው ወታደራዊ ስልት ባለ ስልጣናቱን አለመጠበቁና ዋስትና አለመስጠቱ በቂ ማሳያ ሲሆን፡ የፋኖ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የበላይነቱ በተግባር ታይቷል ብለዋል። ተሳታፊወቹ የአማራ የህልውና ትግል የሁላችንም መሆኑን አረጋግጠው፡ም አማራ ህልውናው የሚረጋገጠው፣ መብቱ የሚከበረው፣ ነፃነቱ የሚረጋገጠው ማንኛውም አማራ በተሰማራበት የስራ መስክ የተቀናጀ አደረጃጀት በመፍጠር እና በማገዝ ድሉን ከማፋጠን አልፎ ሠላምን የሚያረጋግጥ መሆኑን በአፅንኦት አስቀምጠው ወደ ስራ እደሚገቡ አረጋግጠዋል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1 062
17
+2
Matn yo'q...
983
18
ሸር ይደረግ 10\02\2019 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለውና የመከላከያ ሰራዊት ዩኒፎርም የለበሰ አባል በቁጥጥር ስር በዋለ ምርኮኛ ላይ የፈጸመውና ሊፈጽም ያሰበው አረመኔያዊ ድርጊት፣ የአገዛዙን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ የወደቀ የስነ-ምግባርና የስነ-ልቦና ደረጃ የሚያሳይ፣ የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀልና አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አካል ነኝ የሚል አካል ምርኮኛን እንደ ማህበራዊ ሚዲያ መጫወቻ በማድረግ "ኮሜንት ላይ 'ግደለው' ካላችሁኝ እገድለዋለሁ" ብሎ የሰውን ሕይወት ለደቦ ውሳኔና ለ'ላይክ' መሰብሰቢያ ሲያቀርብ፣ ሰራዊቱ የስነ-ምግባር አከርካሪው ሙሉ በሙሉ መስበሩንና ከሀገር መከላከያነት አልፎ ወደ የሰፈር ሽፍታና የወንበዴ ስብስብነት መውረዱን ያረጋግጣል። ይህንን አሰቃቂ ድርጊት፣ የስርዓቱን ባህሪና የማህበረሰቡን ተገቢ ሕዝባዊ ቁጣ በጥልቀት የሚያስረዱት ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ተተንትነዋል ያንብቡት፦ የምርኮኞች አያያዝ ውድቀትና የደቦ ፍርድ ድራማ፦ የብልፅግና ሰራዊት የሞራልና የስነ-ምግባር ክስረት። ፩. #የዓለም አቀፍ የጦር ሕጎችና የጄኔቫ ኮንቬንሽን መጣስ በዓለም አቀፍ የጦር ሕግ (Geneva Conventions) መሠረት፣ በጦር ሜዳ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ምርኮኛ (Prisoner of War) ሰብዓዊ ክብሩ ሊጠበቅ፣ ከአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ማሰቃየት ሊከለከል፣ እና ሕይወቱ ሙሉ በሙሉ ዋስትና ሊኖረው ይገባል። * #የመንጋ_ፍርድ_በሶሻል_ሚዲያ፦ በቁጥጥር ስር የዋለን ወጣት በካሜራ ፊት አቁሞ "ተከታዮቼ ግደለው ካሉኝ እገድለዋለሁ" ማለት የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል (War Crime) ፍጹም ማረጋገጫ ነው። * #ሰብዓዊ_ክብርን_ማዋረድ፦ የሰውን ሕይወት ለኮሜንትና ለቲክቶክ መጫወቻ ማድረግ፣ የሰራዊቱን አረመኔነትና ለሰብዓዊ ሕይወት ምንም ዓይነት ዋጋ አለመስጠቱን ያሳያል። ፪. #ሰራዊቱ_የደረሰበት የስነ-ልቦናና የስነ-ምግባር መበስበስ። ይህ አጋጣሚ ድንገት የተከሰተ ነጠላ ድርጊት ሳይሆን፣ አገዛዙ የገነባው ሰራዊት ያለበትን አጠቃላይ የባህሪና የስነ-ምግባር ውድቀት የሚያሳይ ነው፦ * #የቀደሙ_አሰቃቂ_ታሪኮች_ማረጋገጫ፦ ቀደም ሲል በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ በንጹሐንና በፋኖ አባላት ላይ የተፈጸሙት አሰቃቂ ግድያዎች፣ አካል ማጎደልና የቆዳ ገፈፋ ታሪኮች ተራ ወሬ ሳይሆኑ የመሬት ላይ እውነታዎች መሆናቸውን ይህ የቪዲዮ ማስረጃ ምስክር ይሆናል። * #የወታደራዊ_ስነ_ምግባር_ማጣት፦ ሕግ የሚያስከብር፣ የዜጎችን ደህንነት የሚጠብቅና ሙያዊ ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያለው ሰራዊት ሳይሆን፣ የፋሽስታዊው አገዛዝ የሥልጣን እድሜ ለማራዘም ብቻ የተደራጀና መግደልን እንደ ብቸኛ ስራው አድርጎ የወሰደ ስብስብ መሆኑን ያረጋግጣል። ፫. #የካድሬዎችና የ"ከመከላከያ ጎን ነን" ባዮች የሞራል ውድቀት እንዲህ ዓይነቱ አጸያፊና ሕገ-ወጥ ድርጊት በቪዲዮ ተቀርጾ ሲወጣ እንኳን አገዛዙንና ሰራዊቱን "ከመከላከያ ጎን ነን" እያሉ የሚያሞካሹ ካድሬዎችና አክቲቪስቶች የዚሁ አረመኔያዊ መዋቅር አካልና ደጋፊዎች ናቸው፦ * #የሕዝባዊ_ቁጣና_የአገዛዙ_እብሪት፦ ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣቢያስነሳም፣ አገዛዙና ደጋፊዎቹ "ሕዝብ ወዶን ስልጣን አልያዝንም" በሚል እብሪትና የንቀት አመለካከት ግፋቸውን ቀጥለውበታል። * #የደፋሪና_የገዳይ_አጋርነት፦ የዚህን ሰራዊት አረመኔያዊ ድርጊት እያዩ "ከመከላከያ ጎን ነን" ማለት፣ በዜጎች መታረድ፣ መደፈርና በምርኮኞች መበደል ላይ ቀጥታ ተሳታፊና አብሮ አደራጅ መሆን ነው። ፬. #የሰብዓዊ መብት ተቋማትና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ኃላፊነት። ይህ የተቀረጸው የቪዲዮ መረጃ አገዛዙ በንጹሐንና በምርኮኞች ላይ የሚያደርሰውን በደል በግልጽ የሚያሳይ የማይካድ ማስረጃ (Hard Evidence) ነው፦ * #ዓለም_አቀፍ_ምርመራ፦ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፣ የሕግ አካላትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይህንን የጦር ወንጀል በቀጥታ በመመርመር፣ ፈጻሚዎቹንና አዛዦቹን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ግፊት መደረግ አለበት። * #የሕዝቡ_የመጨረሻ_የትግል_አማራጭ፦ ሕግና ሥርዓት በሌለበት፣ የሀገር ሰራዊት በሚባለው አካል አረመኔያዊ ድርጊት በሚፈጸምበት አውድ ውስጥ፣ ሕዝቡ ራሱንና ሰብዓዊ ክብሩን ለማስከበር በፋኖ መሪነት የሚያደርገውን የሕልውና ትግል አጠናክሮ ከመቀጠል ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ያሳያል። #ማጠቃለያ ምርኮኛን ለደቦ ውሳኔና ለሶሻል ሚዲያ መጫወቻ የሚያደርግ ሰራዊት "የሀገር መከላከያ" ሊባል አይችልም! ይህ ድርጊት የስርዓቱን የመጨረሻ የሞራልና የፖለቲካ ውድቀት የሚያሳይ ሲሆን፣ በደሙና በክብሩ ላይ እየተጫወቱ ያሉትን አምባገነኖችና የሥርዓቱን አስፈጻሚዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሕዝባዊ ትግል ማስወገድ የሕልውናችን ዋስትና ነው።
954
19
Matn yo'q...
942
20
የኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ከመማረክ ውጪ አማራጭ የለውም !
የኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ከመማረክ  ውጪ አማራጭ የለውም !
996