cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የነቢያት መንገድ | طريق الأنبياء

❝ ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ❞ [ ሱረቱ ዩሱፍ - 108 ]

Show more
Advertising posts
2 558
Subscribers
+2424 hours
+477 days
+14530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

سورة الكهف كاملة تلاوة هادئة وراحة نفسية في يوم الجمعة تريح الأعصاب محمد ديبيروف Surah al kahf አዳምጡ
Show all...
👍 8
ውይይት እግዚአብሔር ትክክለኛ ስሙ አይታወቅም ሳለህ ወገናችን ስረወርቅ
Show all...
👍 7
ውይይት የአላህ እውቀት መምህር ወሒድ ሳለህ ኢምራን ወገናችን ናቲ
Show all...
👍 7
ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦ ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል። ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም። የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦ ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች። በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦ 2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት። ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን? ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦ ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦ ማቴዎስ 26፥26-27 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28: ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል። ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት!  የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው።                                                                     አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።    ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

👍 13
ተባበሩን ! አዳማ - ቦሌ ክፍለ ከተማ ኸዲጃ መስጂድ እና ዳሩል-ሐዲስ መስጂድ አካባቢ ነው ያገኘናት፤ ብዙ መረጃዎችን ልትሰጠን ስላልቻለች ቤተሰቧ ተጨንቆ እየፈለጋት ሊሆን ይችላል፤ እባካችሁ ቤተሰቧን ምታውቁ ካላችሁ ቀጣይ ባሉት ስልክ ቁጥር ይደውሉልን ! 091 230 6503 ~ የዳሩል ሐዲስ መስጂድ ሙዐዚን 098 666 6047 ~ ናፍያድ ቃሲም ለጊዜው የዳሩል-ሐዲስ ሙዐዚን ቤት ነው ያረፈችው !
Show all...