cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስር በመሆን አስፈላጊና አስተማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶችን፦ - ቪድዬዎችን - ኦድዬዎችን - አጫጭር መጣጥፎችን እያዘጋጀ በሀገርኛ ቋንቋ ያቀርባል፡፡

Show more
Advertising posts
4 909
Subscribers
+224 hours
-137 days
-4330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

▯▩ ወይይት ▩▯ "ስቅለት በኢስላም" ◍ ወንድም ኢምራን           🆅🆂 ◍ ወገናችን ሳሚ ◍ ወገናችን ሳለህ ◍ ሌሎችም
Show all...
record.ogg48.89 MB
07:02
Video unavailableShow in Telegram
"እንኳን አደረሳችሁ?" ◍ እኅት ዘሀራ
Show all...
34.71 MB
አልገደሉትም ገቢር አንድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا “ታሪክ”history” ያለፈውን ክስተት የሚተርክ የምርምር ጥናት”study” እና አሰሳ”investigation” ነው፤ በታሪክ ጥናት ውስጥ ለታሪክ ምንጭ የሚሆኑ ሁለት መረጃዎች አሉ፣ አንደኛው ትውፊት”tradition” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሥነ-ቅርስ ጥናት”archology” ነው፤ “ትውፊት” ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል የሚተላለፍ ቅብብል ሲሆን “ሥነ-ቅርስ ጥናት” ደግሞ በተለያየ ቁስ ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች አስሶና ቆፍሮ የሚያቀርብ የታሪክ ምንጭ ነው፤ ትውፊት ሆነ ሥነ-ቅርስ በባህል”culture” ላይ እና በስልጣኔ”civilization” ላይ መሰረት ያደረጉ ግምት”speculation” ናቸው፤ ስለ ኢየሱስ ማንነት በዓለማችን ላይ አንድ አይነት አቋም ያለው የታሪክ ፍሰት የለም፤ አንዱ ሃሳዌ መሲህ ሲለው ሌላው አምላክ ሲለው፣ አንዱ የፈጣሪ እረዳት ሲለው ሌላው ብቸኛ የፈጣሪ ልጅ ይለዋል፤ አንዳንዶች እንደውም በታሪክ ላይ አልነበረም የሚሉም አልታጡም፤ ስለ እርሱ አራቱ ወንጌል ላይ የምናየውም ትረካም ቢሆን እርስ በእርሱ የተዛባ እና በቅብብል የተገኘ እንጂ ግህደተ-መለኮት አይደለም፤ ታዲያ ይህ ዓለማችንን ያነጋገረ የፈጣሪ ነብይ ትክክለኛ ማንነቱን መናገር ያለበት እራሱ ላኪው ፈጣሪ ነው፤ ኢየሱስን የላከው አላህ ስለ ዒሳ ሲናገር፦ 19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ *ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ “የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለትም “የሚከራከሩበት” የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት፤ ይህ “መከራከር” የሚለው ቃል “ሚርያህ” مِرْيَة ሲሆን “ጭቅጭቅ” “ንትርክ” ክርክር” ማለት ነው፤ በዒሳ ጉዳይ ሰዎች በመወዛገብ መጨቃጨቃቸውን፣ መነታረካቸውን እና መከራከራቸውን ያሳያል፤ ዒሳ ካረገበ በኃላ ቁርኣን እስከሚወርድበት ጊዜ አራጥቃና በጥራቃ እየተባባሉ መቅኖ ሲያሳጣቸው እንደነበር ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ አስፍሮታል። “ያ“ በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው” የሚል ነው፤ “እርሱ” በሚለው ቃል ላይ “በ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያመለክተው ስለ ዒሳ አላህ የነገረን ንግግር ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው ማለት ነው፤ “በ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፊ” فِي  ሲሆን “ስለ”about” ማለት ነው፦ That is Jesus, son of Mary. ˹And this is˺ a word of truth, “about” which they dispute. “ቀሰስ” قَصَص የሚለው ቃል “ቀሰሰ” قصص “ተረከ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ትረካ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና ሁሉን የሚያውቅ ስለሆነ ያለፈውን ክስተት “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት በነብያችን”ﷺ” ላይ ይተርካል፦ 11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ስለዚህ ከመልክተኞች ታሪክ አንዱ የዒሳ ታሪክ ስለሆነ ይህ ታሪክ ሲከሰት ነብያችን”ﷺ” በህልውና ደረጃ ስላልነበሩ ሁሉን ዐዋቂው አምላክ ለነብያችን”ﷺ” ይህንን ታሪክ ያወርዳል፤ ይህ ስለ ዒሳ ትረካ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፦ 3፥62 *”ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው”*፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ ሰዎች በዒሳ ጉዳይ ከሚወዛገቡበት፣ ከሚጨቃጨቁበት፣ ከሚነታረኩበት፣ ከሚከራከሩበት ነጥብ አንዱ ዒሳ ተሰቅሏል ወይስ አልተሰቀለም ነው፤ አምላካችን አላህ፦ ዒሳን አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን የገደሉትና የሰቀሉት መስሏቸዋል፦ 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا "እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም" ይህንን መለያየት አስመልክቶ ስለ ወንጌላት ታሪካዊ ዳራና ፍሰት፤ በቁርኣን እና በሐዲስ ያለውን እሳቤ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እንቀጥላለን...... ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
Show all...
አልገደሉትም ገቢር ሁለት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا ነጥብ አንድ "ታሪካዊ ዳራ" ኢየሱስ ከፈጣሪ የሚናገረውን ትምህርት ተሰቶት ነበር፤ ይህ ትምህርት የፈጣሪ ቃል ነው፤ ከእርሱ የሚሰማው ትምህርት የፈጣሪ ወንጌል ነው፦ ዮሐንስ 17:8 *የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና*፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ዮሐንስ 17:14 እኔ *ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ*፤ ዮሐንስ 14:24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ *የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም*። ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ዮሐንስ 12:49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*። ሉቃስ 5፥1 ሕዝቡም *የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ* ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤ ማርቆስ 1፥14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ *የእግዚአብሔርን ወንጌል* እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፡ *በወንጌልም እመኑ* እያለ ወደ ገሊላ መጣ። "በወንጌልም እመኑ" ሲል ከመለኮት የተሰጠውን ወንጌል ብቻና ብቻ ነው፤ ይህንን ወንጌል ለሃዋርያቱ አስተላልፏል፤ "የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ኦሪገን የተሰጠው ወንጌል የአስራ ሁለቱ ወንጌል ሲሆን ጠፍቷል ይለናል። ጄሮም ደግሞ የአስራ ሁለቱ ወንጌል የሃዋርያት ወንጌል እንሆሃነ ተናግሯል፤ ሐዋርያቱ ለደቀመዛሙርቶታቸው ሲያስተላልፉ ቀደ መዛሙርቶቻቸው ይህንን ወንጌል ከሚሰሙት ታሪክ ጋር ቀላቅለው ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ሞክረዋል፦ ሉቃስ 1:1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።”
Show all...
ለምሳሌ፦ አንደኛ በ 50-138 AD የማቴዎስ ተማሪ የነበረው ባስሊዲስ በ 117 AD ላይ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የቀሬናን ስምዖንን እንደሰቀሉት ይናገራል፤ ይህንን ወንጌል በኃላ ላይ የመጡት አበው በ 130-200 AD ይኖር የነበረ ኢራኒየስ፣ በ 150-215 AD ይኖር የነበረ የአሌክሳንድሪያው ክሌመንት ተቃወሙት፤ ብዙ ጊዜ ከባስሊዲስ ወንጌል ላይ 260-340 AD ይኖር የነበረው የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይጠቅስ ነበረ። ሁለተኛ በ 60-135 AD ይኖር የነበረው በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል፤ በሳይናቲከስ ኮዴክስ ላይ ፓሊካርፕ ለፊሊጵስዩስ በጻፈው ፓሊላርፕ 1፥1 ቀጥሎ የበርናባስ መልእክት 5፥7 ይቀጥልል። እዚህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሰቀሉት ይናገራል። ሦስተኛ በ 85-160 AD ይኖር የነበረው የሲኖፕ ማርኮይን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የማርኮናይት ወንጌል በ 1740 AD ከተገኙት የሙራቶሪያን ብጥስጣሽ"Muratorian fragment" አንዱ ነው፤ የካርቴጅ ጉባኤ ከማርኮናይት ግሩፕ ውስጥ የዮሐንስን አፓልካሊፕስ"ራእይ" ተቀብላ በእነርሱ የነበረውን የጳውሎስን አፓልካሊፕስ፣ የጴጥሮስን አፓልካሊፕስ፣ የቶማስን አፓልካሊፕስ፣ የእስጢፋኖስን አፓልካሊፕስ፣ የያዕቆብን አፓልካሊፕስ ደብቃቸዋለች። በማርኮናይት ወንጌል ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የሮማ ወታደር እንደሰቀሉት ይናገራል። አራተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ኤቦን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የኤቦናይት ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። በ 347-420 AD ይኖር የነበረው ጄሮም ኤቦን በዮሐንስ ዘመን ይኖር እንደነበረ መስክሯል። ነገር ግን ኤቦንን በ 36-115 AD ይኖር የነበረው የቆሮጵሮሱ ኤጵፋኒየስ አውግዞቷል።
Show all...
አምስተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ሰርቲዩስ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የሰርቲዩስ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ስድስተኛ በ 36 AD ጀምረው ይኖሩ የነበሩት ናዝራውያን ወንጌል አዘጋጅተዋል፤ ይህ የናዝራውያን ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ናዝራውያን የሙሴን ሕግ ይቀበላሉ፤ የኢየሱስን በድንግና መወለድ ይቀበላሉ፣ የሌሎችን ወንጌላት አይቀበሉም። በግሪክ ኮይኔ የተዘጋጁት ወንጌሎች የትዬለሌ ናቸው፤ እነርሱም፦ የቶማስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የባስሊዲስ ወንጌል፣ የበርናባስ ወንጌል፣ የማርኮናይት ወንጌል፣ የኤቦናይት ወንጌል፣ የሰርቲዩስ ወንጌል፣ የናዝራውያን ወንጌል፣ የጴጥሮስ ወንጌል፣ የያዕቆብ ወንጌል፣ የፊሊጶስ ወንጌል፣ የበርተሎሜዎስ ወንጌል፣ የመቅደላዊት ማርያም ወንጌል፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል፣ የሉቃስ ወንጌል፣ የዮሐንስ ወንጌል የመሳሰሉት ናቸው፣ በቁጥር ወደ 47 ይደርሳሉ፣ ዛሬ የቀኖና ወንጌሎች የተባሉት ኦርጅናል አራቱ ወንጌሎች የለም፣ አራቱ ወንጌላት ተጻፉ የሚባሉት ከ 60-100 AD ሲሆን የእነርሱ የቅጂ ቅጂ ብጥስጣሽ"fragments" እና ደንገሎቹ"papiruses" የሚያሳዩት ግን ከ 200-250 AD ነው፦ የማቴዎስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የማርቆስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የሉቃስ ወንጌል ደንገል 75 የሚባለው በ 250 AD፣ የዮሐንስ ወንጌል ደንገል 46 የሚባለው በ 200 AD ነው፣ ዛሬ ያሉት 5800 ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት ኢየሱስ ካስተማረ ከሶስት መቶ አመት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው፤ ዋና ዋናዎቹ ሳይናቲከስ ጥራዝ በ 330 AD፣ ቫቲካነስ ጥራዝ 350 AD፣ አሌክሳንድሪየስ ጥራዝ 400 AD፣ ኤፍሬማይ ጥራዝ 450 AD ላይ የተዘጋጁ ናቸው። ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ በ 397 AD የካርቴጅ ጉባኤ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የቅጂዎች ቅጂዎች የሆኑትን አራቱን ወንጌሎች ብቻ ቀኖና"canon" አድርጋ ሌሎችን ወንጌሎች "አፓክራፋ" አድርጋለች፤ "አፓክራፋ" የሚለው ቃል "አፓክራፈስ" ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ድብቅ" ማለት ነው፤ ለዛ ነው አምላካችን አላህ፦ "የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?" ብሎ የተናገረው፦ 3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ 5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ “ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን እንዳለ ይህ አንቀጽ ይጠቁማል፤ በወንጌሎች ታሪካዊ ዳራና ፍሰት ዋቢ መጽሐፍት ያደረኩት የአዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑትን የፕሮፌሰር ባርት ሄርማን መጽሐፍት ነው፦ 1. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman 2. The Orthodox Corruption of Scripture: The Effect of Early Christological Controversies on the Text of the New Testament. Oxford University Press, USA. 2011 3. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003 ኢንሻላህ በክፍል ሥስት እንቀጥላለን.... ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
Show all...
25:48
Video unavailableShow in Telegram
سورة الكهف كاملة تلاوة هادئة وراحة نفسية في يوم الجمعة تريح الأعصاب محمد ديبيروف Surah al kahf አዳምጡ
Show all...
68.43 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ሳኡድዎች ይህን መጽሐፍ የምትፈልጉ በቴሌ ግራም አናግሩኝ https://t.me/Zhara_mustefa
Show all...
ሥነ-ጋብቻ ጥናትMatrimony" እንደሚያትተው አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ለመድረስ ከሚታዩ ምልክቶች አንዱ ሐይድ ማየት ነው። "ሐይድ" حَيْض ማለት "የወር አበባ" ማለት ነው፥ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ደግሞ "ሓኢድ" حَائِض ትባላለች። አንዲት እንስት የወር አበባ ልታይበት የምትችለው አማካኝ ዕድሜ ከ 12-13 ሲሆን እንደየ እንስቷ ሁኔታ ከ 12 በታች እስከ 9 ቶሎ ሊመጣ አሊያም ከ 13 በላይ እስከ 16 ሊዘገይ ይችላል። በኢሥላማዊ መዛግብትም አጥ-ጦበሪን ጨምሮ እንደተዘገበው የአንዲት እንስት የወር አበባ የምታየበት ትንሹ እድሜ ዘጠኝ መሆኑ እንዲህ ተዘግቧል፦ አልካፊ ፊ ፊቅህ ኢብነ ሀንበል፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 74፣ ሸርህ አል– ዑምዳ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 480 *"ትንሹ የሴት ልጅ የወር አበባ የምታይበት እድሜ ዘጠኝ ዓመት ነው"*። የጋብቻ ጊዜ በጥንታዊ ጊዜ፣ በዘመናዊ ጊዜ፣ በድኅረ-ዘመናዊ ጊዜ ከትውልድ ወደ ትውልድ፥ ከባህል ወደ ባህል ይለያያል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦ *“ለጋብቻ ትንሹ የዕድሜ ገደብ በፊት 12 ዓመት አልያም ከዚያም ያነሰ የነበረው ሲሻሻል እና ከፍ ሲል ቆይቶ በአብዛኛው አገሮች አሁን በ15 እና በ21 ዕድሜ መካከል ሆኗል"*፡፡ Encyclopedia Britannica 2006 page 171. የጋብቻ ጥናት ምሁር ብራውን ዮናታን፦ *"አብዛኛው የጋብቻ ምሁራን ዓኢሻህ በዘጠኝ ዓመቷ ለዐቅመ-ሔዋን ደርሳለች ብለዋል"*። Brown, Jonathan (2014). Misquoting Muhammad: The Challenge and Choices of Interpreting the Prophet's Legacy. Oneworld Publications. pp. 143–4. ጋብቻ ማለት በሁለት ተቃራኒ መካከል ያለ ስምምነት ነው፥ አንድ ተባእት አንዲትን እንስት አስገድዶ ማግባት ሐላል አይደለም። ነቢያችንም”ﷺ” ዓኢሻን ሊደርሱባት ሲሉ ፈቃደኝነቷን ጠይቀዋታል፦ 4፥19 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! *”ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ ለእናንተ አይፈቀድም”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا አል-ሙሥተድረክ አል-ሐኪም ጥራዝ 4 ገጽ 11 ሰዒድ ኢብን ከሲር ከአባቱ አባቱ ከዓኢሻህ "ረ. ዐ." እንዳስተላለፈው፦ *የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ለአዒሻ እንዲህ አሏት፦ *“በዱንያህ ሆነ በአኺራ የእኔ ባለቤት መሆንን አትፈልጊምን? እርሷም፦ “ወሏሂ እፈልጋለሁ እንጂ” አለች፡፡ እርሳቸውም፦ "አንቺ በዱንያህ ሆነ በአኺራም የእኔ ባለቤቴ ነሽ" አሏት"*፡፡ عن سَعِيدُ بْنُ كَثِيرٍ عَنْ أَبِيهِ ، قَالَ حَدَّثَتْنَا عَائِشَةُ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قال لعائشة -رضي الله عنها-: «أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ تَكُونِي زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ؟» قُلْتُ: بَلَى وَاللَّهِ، قَالَ: «فَأَنْتِ زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ». ሚሽነሪዎች ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" መዳሯ የሚያንገበግባቸው፣ ልወቅልሽ እና ልቆርቆርልሽ የሚሏት አስብቶ አራጅ እና ቅቤ አንጓች ሆነው እንጂ ለእርሷ አስበው አይደለም። እርሷ ጋብቻውን ወዳ እና ፈቅዳ የገባችበት ጉዳይ ነው፥ ለነቢያችን"ﷺ" ልዩ ፍቅር የነበራት ሴት ነበረች፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 43 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በማንም ሴት እንደ ኸዲጃህ ቅናት ተሰምቶኝ ዐያውቅም፥ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ብዙ ጊዜ ያነሷት ነበር። እኔን ያገቡኝ እርሷ በሞተች በሦስት ዓመቷ ነው፥ ከጌታቸው ዐዘ ወጀል ወይንም ከጂብሪል"ዐ.ሠ." እርሷ በጀነት ጨፌ ሥርፋ እንዳላት ይበሰሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ مَا غِرْتُ عَلَى امْرَأَةٍ مَا غِرْتُ عَلَى خَدِيجَةَ، مِنْ كَثْرَةِ ذِكْرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِيَّاهَا‏.‏ قَالَتْ وَتَزَوَّجَنِي بَعْدَهَا بِثَلاَثِ سِنِينَ، وَأَمَرَهُ رَبُّهُ عَزَّ وَجَلَّ أَوْ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ أَنْ يُبَشِّرَهَا بِبَيْتٍ فِي الْجَنَّةِ مِنْ قَصَبٍ‏.‏ በሞተችው ሚስታቸው በኸዲጃህ የምትቀናው ፍቅር ካልሆነ ምንድን ነው? ዓኢሻህ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የነበራትን መስተጋብር ለምእመናን ጋብቻ አርአያ እንዲሆነ ብዙ ጊዜ ታነሳለች። ለምሳሌ አንዲት እንስት ከባሏ ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ውስጥ መታጠብ እንደሚችሉ ለማስተማር እርሷ ከባለቤቷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ትታጠብ እንደነበር ትናገራለች፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 3 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" አል-ፈረቅ በሚባል አንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ قَدَحٍ يُقَالُ لَهُ الْفَرَقُ‏.‏ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 16 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" ከጀናባህ በኃላ በአንድ ገንዳ እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ جَنَابَةٍ‏.‏ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 14 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" በአንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር፥ እጆቻችንን በገንዳ ውስጥ ይተካኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ تَخْتَلِفُ أَيْدِينَا فِيهِ‏.‏
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.