en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

Open in Telegram

Quality Education

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Amhara Education Bureau

Channel Amhara Education Bureau (@anrse) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 39 236 subscribers, ranking 4 758 in the Education category and 929 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 39 236 subscribers.

According to the latest data from 20 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -125 over the last 30 days and by -9 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 18.20%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.40% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 7 143 views. Within the first day, a publication typically gains 3 690 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“Quality Education”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 21 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Education category.

39 236
Subscribers
-924 hours
-337 days
-12530 days
Posts Archive
"የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል በትምህርት ጥራት ላይ መሠረት መጣል ይገባል" ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ‎ ‎የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ ተቋማት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሂዷል። ‎ ‎በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ​ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ በመተባበር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል እና የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ለቀጣይ ጊዜያት መሠረት መጣል ይገባል ብለዋል። ‎ ‎​በጤናው ዘርፍ የተጀመሩ የጤና ተቋማትም በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለማኀረበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ነው ያሉት። ‎ ‎​በሆስፒታሎች ላይ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጫና ለመቀነስ በጤና ጣቢያዎች በሕክምና ቁሳቁስ ግባት ማሟላት እንደሚገባም ዶክተር ሙሉነሽ አንስተዋል። ‎ ‎የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ​​በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት ከትምህርት ገበታ ውጭ የነበሩ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በተሠራ ሥራ በክልሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ‎ ‎የ​ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት፣ አዳሪ እና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። ‎ ‎የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በጤናው ዘርፍ የሕክምና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የእናቶች እና ሕጻናት ሞት ለመቀነስ መሠራቱንም ገልጸዋል። ‎ ‎​የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የማኅበረሰብ መድኃኒት ቤቶችን በመገንባት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል ብለዋል። ‎ ‎​የጤና ኤክስቴንሽን ሥርዓትን ከመተግበር አንፃር የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለመቅረፍ ቀጣይ በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት። ‎ ‌‎​በግምገማ መድረኩ የማኅበራዊ ዘርፍ ተቋማት ሪፖርት ቀርቦም ውይይት ተደርጎበታል ሲል የዘገበው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው። ጥቅምት 10/2019 -ደብረማርቆስ

photo content
+4

የኢንሸቲቭ ስራዎች በልዩ ትኩረት ይፈፀማሉ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ደብረማርቆስ: ጥቅምት 10/2019(ትምህርት ቢሮ) የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት የ2019 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት ግምገማ በደብረማርቆስ ከተማ አካሂደዋል። ሁሉም የክላስተሩ ተቋማት የሩብ አመት ሪፖርት አቅርበው የተገመገመ ሲሆን የማህበራዊ ክላስተር ጽ/ቤት በሩብ አመቱ የተሰሩ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሪፖርት በጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አባይነህ መላኩ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በሪፖርቱም የኢንሸቲቭ ስራዎችን በጥብቅ ዲስፕሊን ለመምራት ጥረት መደረጉን ተገልጿል። የቀዳማይ ልጅነት በትኩረት ተይዞ እየተሰራበት መሆኑን፤ በዲጅታል አማራ ኢንሸቲቭ ከ900ሺህ በላይ ወጣቶች መሰልጠናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል። ፕሮጀክቶችን የመከታተልና የመደገፍ ስራዎች በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አቶ አባይነህ መላኩ አብራርተዋል። ተግባራትን በየሳምንቱ እየገመገሙ ለመምራት የተደረጉ ጥረቶች፣ የባለሙያዎች ቡድን ለ15 ቀናት ዞንና ከተማ አስተዳደሮችን ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸውን ተገልጿል። በመድረኩ ማጠቃለያም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ እንደገለፁት የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራን ማጠናከር፣ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ ፕሮጀክት በመቅረፅ ሀብት ማፈላለግና የማህበረሰብ ችግሮችን መፍታት፣ የሀብት አጠቃቀምን በጥበብ መምራት፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የዲጅታላይዜሽን ስራዎችን ማጠናከር፣ ኢንሸቲቮችን በልዩ ትኩረት መስራት፣ ተቋም ግንባታ ማጠናከር፣ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ስራ መስራት ላይ ተቋማት እንዲያተኩሩ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። #AmharaEducation #ትምህርትለትውልድ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ 📌 በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/ 📌 በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w 📌 በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau 📌 በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse ያግኙን 📌 በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau 📌 X ገፃችን@amharaeducationbureau

photo content
+6

photo content
+5

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) የሀዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ጉብኝት አደረጉ ጥቅምት 10/2019(ትምህርት ቢሮ): በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ፣ የማህበራዊ ክላስተር የቢሮ አመራሮች፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አባተ፣ የደብረማርቆስ ከተማ ከንቲባ አቶ መልካሙ ሽባባው ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ምክትል ኃላፊዎች የሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ጤና ጣቢያና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ተጎብኝተዋል። #AmharaEducation #ትምህርትለትውልድ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ 📌 በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/ 📌 በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w 📌 በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau 📌 በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse ያግኙን 📌 በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau 📌 X ገፃችን@amharaeducationbureau

photo content
+2

photo content
+9

በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ የነበሩ ታዳጊዎችን ወደ ትምህርት ገበታ መመለስ ተችሏል። ‎ ‎በምሥራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት አጀማመር ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሂዷል። ‎በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በግጭት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ርቀው የነበሩ ታዳጊዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማሌዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን አንስተዋል። ‎ ‎ኀላፊው የትምህርት ሥርዓቱን ሀገር በቀል ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። የትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ እና እያንዳንዱ ዜጋ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል። ‎ ‎የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዋለ አባተ እንዳሉት በዞኑ የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር የመምህራንን ሥነ ልቦና የመመለስ እና የወላጆችን ተሳትፎ የማስደግ ተግባር ተከናውኗል። ‎ ‎ዋና አሥተዳሪው ግብረ ሰናይ ተቋማት ድጋፍ እና እገዛ እንዲያደርጉ በማበረታታት ዞኑን ወደ ቀደመ ተወዳዳሪነቱ መመለስ ይገባልም ብለዋል። ‎ ‎በመድረኩ ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የትምህርት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች የትምህርት ሥርዓቱ እና የተማሪዎች ተሳትፎን ለማሻሻል የሀገር ሽማግሌዎች እና አባቶች የሠሩት ሥራ የሚበረታታ መኾኑን ገልጸዋል። ‎ ‎ትምህርት ተደራሽ ባልኾነባቸው አካባቢዎች ላይ ለመድረስ ከማኅበረሰቡ ጋር በጥምረት እየተሠራ ነውም ብለዋል። ‎ ‎አሚኮ ያነጋገራቸው በመድረኩ የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተተኪ ትውልድን ለማፍራት በሕጻናት ላይ መሥራት እና በትምህርት አንፆ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል። ‎ለዚህም የድርሻቸውን ለማበርከት እየሠሩ መኾናቸውን አረጋግጠዋል። አሚኮ

photo content
+6

ለተሻለ የትምህርት ዕድገት መምህራን ላይ መሥራት ያስፈልጋል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በቅድመ ሥራ ሥልጠና መርሐግብር የሚሰጠውን የመካከለኛ ደረጃ የሥራ እና የተግባር ትምህርት የመምህራን ሥልጠናን ለማካሄድ የሚያስችል የጋራ የውይይት እና የስምምነት መድረክ አካሂደዋል። ስምምነቱ በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እና በክልሉ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ተግባራዊ የሚደረግ ነው። የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አማረ አለሙ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ሙሉ ስብዕና ያለው፣ ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ባለቤት የኾነ፣ በራሱ የሚተማመን እና ለሀገሩ እና ለወገኑ የሚቆረቆር ዜጋ መገንቢያ ማዕከላት መኾናቸውን ጠቅሰዋል። ይህ የሥራ እና ተግባር ትምህርት የመምህራን ሥልጠና የትብብር መድረክ የተሻለ፣ ለራሱ፣ ለሀገሩ እና ለወገኑ የሚጠቅም ትውልድ በመፍጠር ረገድ የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደምስ እንድሪስ ሀገር የምትቀየርበት የትምህርት ሥርዓት በሁሉም መስክ እያደገ፣ እየተቀየረ እና እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰዋል። በተለይም ለተሻለ የትምህርት ዕድገት መምህራን ላይ መሥራት ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በትምህርቱ ዘርፍ በተለይም በመምህራን ልማት ዘርፍ ከአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ መሥራታችን የተሻለ ዕድል አለው ብለዋል። ይህ ስምምነት የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅድመ ሥራ ሥልጠና መርሐግብር የሚሰጠውን የመካከለኛ ደረጃ የሥራ እና ተግባር ትምህርት የመምህራን ሥልጠናን በትብብር ለማካሄድ ያስችላል። አሚኮ

photo content
+9

photo content
+9

ከትምህርተ ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናትን ወደ ትምህርት ገባታ እንዲመለስ ማህበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ። * ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናትን ወደ ትምህርት ገባታ እንዲመለስ ማህበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የምስራቅ ጎጃም ዞን ገለፀ። በምስራቅ ጎጃም ዞን ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚመክር የውይይት መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው። የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አባተ ባለፉት ዓመታት በዞኑ በነበረው ግጭት 723 የትማህርት ተቋማት ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸውና ይህ ሁኔታም የትውልድ ቅብብሎሽን በማቋረጥ በሃገር የትውልድ ግንባታ ላይ የማይተካ ኪሳራ አድርሷል ብለዋል። ‎ ‎በ2019 የትምህርት ዘመን በዞኑ ካሉ 1ሺህ 78 የትምህርት ተቋማት ውስጥ 1ሺህ 67 የትምህርት ተቋማት እንደተከፈቱና 566 ሺህ 712ተማሪዎችን ተቀብለው የመማር ማስተማሩን ስራ እያከነወኑ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል። ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ማህበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪው የዞኑን ትምህርት ወደ ነበረበት የቀደመ ከፍታ ለመመለስ በትብብርና በቅችጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የትምህርት ጉዳይ ለአንድ ተቋምና ለአንድ ግለሰብ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ ሀላፊነት ስለሆነ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን በመጠገንና ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ብሎም ለሰላም ግንባታ ስራው ዘብ በመቆም የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት መሆን እንዳለበት አቶ ዋለ አሳስበዋል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ አቶ መኳንንት አደመ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ‎ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት ፣የህጻናት ጤናና ደህንነት ከለላ መሆኑን ጠቁመው በክልሉ ባለፉት ሶስት አመታት ባጋጠመው የሰላም እጦት ምክንያት በርካታ ህፃናት ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆኑን እና በ2018 የትምህርት ዘመንም በክልሉ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ትምህርት ቤቶች ሳይከፈቱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ‎አቶ መኳንንት አክለውም ትምህርት በማቋረጣቸውም ‎በጻናት ላይ አካላዊና ስነልቦናዊ ጫና ማሳረፉንና የሃገር እድገት እንዲቀጭጭ ተጽዕኖ እንዳያሳርፍ ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባና ትምህርት ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ አለበት ብለዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞን ፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኀላፊዎች ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች ፣የሀይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ነው። ጥቅምት 10/2019_ደብረማርቆስ መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው #AmharaEducation #ትምህርትለትውልድ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ 📌 በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/ 📌 በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w 📌 በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau 📌 በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse ያግኙን 📌 በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau 📌 X ገፃችን@amharaeducationbureau

photo content
+1

photo content
+9

“የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከቀላል ፊዚካዊ ንብረት እና ከብሎኬት ድርደራ ባለፈ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ የማፍራት ታሪካዊ ኃላፊነት ነው” – አቶ አሊ ይማም የደቡብ ወሎ ዞን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ አፈጻጸምን አስመልክቶ ከኮንትራክተሮች ጋር በደሴ ከተማ ውይይት ተካሄዷል። ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለህጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት፣ ለትምህርት ጥራት እና ለቀጣይ የትምህርት ስኬት እጅግ ወሳኝ መሠረት መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በደቡብ ወሎ ዞን በፌዴራልና በወረዳ በጀት በሁሉም ወረዳዎች ሁለት ሁለት ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ሰፊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል። ይሁንና የግንባታ አፈጻጸማቸው በሚጠበቀው ፍጥነት እና ደረጃ ላይ ባለመኘቱ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመሆን ከኮንትራክተሮች ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል። በውይይቱም የጸጥታ ችግሮች፣ በፌዴራል የሚሠሩት ተቋማት የተያዘላቸው በጀት አነስተኛ መሆን፣ እንዲሁም ከክረምቱ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ አንዳንድ የግንባታ ቦታዎች ውኃ የማመንጨት ችግር ማጋጠሙ ለግንባታ መጓተት እንደ ዋና ምክንያትነት በኮንትራክተሮቹ ተነስተዋል በምክክሩ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊ ኮንትራክተሮች ዞኑ መድረክ አዘጋጅቶ ማነጋገሩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ትልቅ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ ያጋጠሙ ውጣ ውረዶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ እና ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ፕላን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይድ እጅጉ በበኩላቸው፣ ተቋራጮች ከሚያገኙት የንግድ ትርፍ ባለፈ ፕሮጀክቶቹ ስትራቴጂካሊ የሚያመጡትን ሀገራዊ ፋይዳ መገንዘብ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል። የፕሮጀክቶቹ መጓተት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በነበሩ ጉድለቶች የተፈጠረ መሆኑን አንስተው፣ በቀጣይ ግንባታዎቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ችግሮችን በጋራ እየፈቱ መሠራት እንዳለበት አቶ ሰይድ ጠቁመዋል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዓለምነው አበራ እንደገለጹት፤ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከመሠረቱ ማለትም ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ መጀመሩን ጠቅሰው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የዚህ ዘመቻ ስራ አፈጻጸም አጠቃላይ በአማራ ክልል 163 ትምህርት ቤቶች የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ በደቡብ ወሎ ዞን 20 በወረዳ እና 20 በፌዴራል ሚኒስቴር ድጋፍ የሚገነቡ 40 ሞዴል ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የወረዳዎች አፈጻጸም በአማካኝ 43 በመቶ ሲሆን የፌዴራል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በኩል 12 በመቶ አካባቢ መሆኑ ተነስቷል። የበጀት አነስተኛ መሆን እና ወቅታዊ ተግዳሮቶች ለዘገየው አፈጻጸም እንደ ምክንያት ቢነሱም፣ ከኮንትራክተሮች ጋር በተደረገው ውይይት በክረምት ወራት የተስተጓጎሉ ስራዎችን በፍጥነት በማካካስ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል። በተለይም ከ85 እስከ 90 በመቶ በላይ አፈጻጸም ላይ የሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጥቅምት ወር መጨረሻ አጠናቆ አገልግሎት ላይ ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። እነዚህን ፕሮጀክቶች አጠናቆ ማስረከብ ለቀጣይ የፌዴራል የልማት በጀቶች መልቀቅ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ፣ የተመደበውን በጀት ሳይመልሱ ቶሎ ፈጽሞ የተሻሉ ፕሮጀክቶችን ለማምጣት የጋራ ቃል መገባቱ ተመላክቷል። የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም ኃላፊነትን መውሰድ ማለት ከተጠያቂነት ማምለጫ ምክንያቶችን ከመደርደር ባለፈ በተግባር አድርጎ ማሳየት መሆኑን አሳሰበዋል። የአጭር ጊዜ የልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ሂደት ውስጥ ትልቁ ትኩረት ትውልድ መገንባት መሆን እንዳበት ተመላክቷል። በተለይም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ እና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች በስተጀርባ ጠንካራ ማጣሪያዎችን ማለፍ እንደሚገባቸው አቶ አሊ ገልጸዋል። በአካባቢው አጋጥመው በነበሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት በስራዎች ላይ የሚከሰቱ መጓተቶችን በቁርጠኝነት መቋቋም እንደሚገባ ተመላክቷል። የበጀት እጥረቶችን እና ሌሎች መሰናክሎችን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማበጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑ አቶ አሊ ጠቁመዋል። ከተጠያቂነት ማምለጥ ሳይሆን የተሰጡ ስራዎችን በታቀደለት ጊዜ እና ጥራት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከቀላል ፊዚካዊ ንብረት እና ከብሎኬት ድርደራ ባለፈ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ የማፍራት ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑንም ነው አቶ አሊ በአጽንኦት የተናገሩት በወረዳዎች፣በኮንተራክተሮች እና በዞኑ መካከል ያለው የግንኙነት ትስስር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ያጋጠሙ ችግሮች በጊዜው እየተፈቱ እንዲሄዱ አቅጣጫ ተቀምጧል። ጥቅምት 9/2019 * የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

photo content
+8

photo content
+9

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ"Imagine1day International" ጋር በመተባበር ለትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ ***** ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ"Imagine1day International" ጋር በመተባበር ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ወሎና ከዋግኽምራ ዞኖች ለተውጣጡ 117 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች፣ ሴት መምህራንና የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የአመራርነት አቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው ከጥቅምት 5 እስከ 8 ቀን 2019 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት የቆየ ሲሆን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች ከመደበኛ አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸው ባሻገር የመማር ማስተማር ሂደቱን በብቃት እንዲመሩ፣ የትምህርት ጥራትን እንዲያሻሽሉና በተቋማቸው ውስጥ ዘላቂ ለውጥ እንዲያመጡ ለማስቻል ያለመ ነው። የImagine1day International ካንትሪ ኦፊስ የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ጀማል ኡመር እንደገለጹት፣ ድርጅቱ በ"Leaders in Teaching Ethiopia (LiTE)" ፕሮግራም አማካይነት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመተባበር የመምህራንን ሙያዊ ብቃት፣ የትምህርት ጥራትና የወጣቶችን የትምህርትና የሥራ ዕድል ለማሻሻል እየሠራ ይገኛል። ስልጠናውም አመራሮች የትምህርት ቤታቸውን የመማር ማስተማር ሂደት በተሻለ አመራርነት እንዲያስተዳድሩና የትምህርት ጥራትን በተግባር እንዲያረጋግጡ ለማስቻል የታለመ መሆኑን አብራርተዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃን አስማሜ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የLiTE ፕሮግራምን ለማስፈጸም ከ"Imagine1day International" ጋር ባደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት በሶስቱ ዞኖች የሚገኙ 31 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመያዝና 16 አሰልጣኝ መምህራንን በመመደብ የሥራ ላይ ስልጠናና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጠቆም፣ ሰልጣኞች ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር በመተርጎም በትምህርት ቤቶቻቸው የሚታይ ለውጥ እንዲያመጡ አሳስበዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለምነው አበራ በበኩላቸው፣ በሀገሪቱ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የትምህርት ቤት አመራሮች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። ስልጠናው የአመራሮችን ተነሳሽነት በመጨመር ለተሻለ የትምህርት ጥራት እንዲሠሩ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው፣ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ አመራሮች ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የLiTE ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ምጣኔ፣ ከፍተኛ የትምህርት ማቋረጥ እና የመሠረተ ልማት ክፍተት ባለባቸው 700 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የ5 ዓመት ፕሮግራም ሲሆን፤ በአማራ ክልል በ82 ትምህርት ቤቶች ላይ እየተተገበረ ይገኛል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት