የኔ ዜማ የአድማጮች የሙዚቃ ምርጫ
Open in Telegram
- በፌስቡክ👇 https://www.facebook.com/100022318509408/posts/1859085851512014/?app=fbl https://www.facebook.com/share/1AMgudXhJr/ - በቴሌግራም ገፅ👇 https://t.me/biggrs - ቲክቶክ ገፅ 👇 tiktok.com/@temesgen_ukare - በዩትዮብ ተከታተሉን👇 https://youtube.com/@temuyehag
Show more290
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+1230 days
Posts Archive
ሀገራችን ኤልያስ መልካን በምን ያህል ደረጃ አመስግናዋለች?
(ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
ውስጤን እንደ እግር እሳት የሚበላኝ በውስጤ ያለው ቁጭት ልግለፅ ኢትዮጵያ በዘመናዊ ሙዚቃ ታሪኳ ውስጥ እንደ ኤልያስ መልካ ያለ አቀናባሪና የዜማ ደራሲ ማግኘቷ ታላቅ እድል ነበር። ባለፉት በርካታ ዓመታት ና ከዚያም በፊት፣ የዘመኑን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የቃኙ በርካታ የሙዚቃ አልበሞችና ነጠላ ዜማዎች በእርሱ አሻራና አቀናባሪነት ተቀርፆ ለህዝብ በቅተዋል።
ዛሬም ድረስ በየቀኑ በበርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ኤፍ ኤም ፕሮግራሞች ላይ እርሱ ያቀናበራቸው ሙዚቃዎች የየዕለት ስራዎች ማጣፈጫ ሆነው ሲደመጡ ኖረዋል፡፡ ይሁን
እንጂ የሰጠንን ታላቅ የጥበብ ሀብት ያህል አገራችን ኤልያስን በምን ያህል ደረጃ አመስግናዋለች? በስሙ የታነጸ ዘላቂ ተቋም ወይም አበርክቶውን የሚመጥን ክብር ሰጥተነዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ አሁንም በህሊናዬ ውስጥ ይመላለሳል፡፡
ከህልፈቱ በኋላ እሱን የሚያስቡና ክብር የሚሰጡ የተለያዩ ፕሮግራሞች ቢኖሩም፣ የሰራቸውን ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ለቀጣዩ ትውልድ በትምህርት ደረጃ ማስተላለፍና የፈጠራ ስራዎቹን አጠናክሮ ማስቀመጥ ላይ ገና ብዙ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉን እገነዘባለው፡፡
የታላቁ አቀናባሪ የኤልያስ መልካ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የሙዚቃ ስቱዲዮ ቁሳቁሶች የት ይገኛሉ? እርሱ የተጠቀመባቸውን የስራ ዘዴዎችና የዜማ ቅንብሮች በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ተቋማት ደረጃ በስርዓተ-ትምህርት ተቀርጸው እየተሰጡ ነው ወይ የሚለው በጥንቃቄ ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ ነው። እርሱን ለመዘከርና ለመጠበቅ የታሰቡ እንደ "ኤልያስ መልካ ፋውንዴሽን" ያሉ ተቋማት ምሥረታና በስሙ የሚከፈቱ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴዎች አሁንም ቢሆን የሁሉም ባለሙያና ጥበብ ወዳድ የተቀናጀ ድጋፍ ይሻሉ።
ሙዚቃውን ዕለት ተዕለት ከማዳመጥ አልፈን ለዚህ ዘመን ትውልድ ኤልያስ መልካ ማነው ለማለትና አጠቃላይ የሙዚቃ ንግስናውን በአግባቡ ለመመዝገብ የታሪካዊ ሰነዶችና የምርምር ስራዎች መስፋፋት ወሳኝ ነው። የኤልያስ ስም ከፕሮግራም ማጣፈጫነት ባለፈ፣ የታሪክና የትምህርት ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል የኪነ-ጥበቡ ማህበረሰብና የሚዲያ ተቋማት በጋራ ሊሰሩበት ይገባል። እርሱ ላበረከተልን ጥበብ የምንመልሰው እውነተኛ ክብር፣ ስራዎቹ ሳይረሱና ሳይበላሹ ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተላለፉ በስሙ የቆሙ ዘላቂ ተቋማትን እውን ማድረግ ስንችል ብቻ ነው።
በመሆኑም፣ ስለ ኤልያስ መልካ ያለን ፍቅርና አክብሮት በቃላትና በዓመታዊ ሙት ዓመት መታሰቢያዎች ብቻ ሳይወሰን፣ ወደተጨባጭ የተቋም ግንባታና የታሪክ ጥበቃ ሊሸጋገር ይገባል። የሙዚቃ መሳሪያዎቹንና የታሪክ ማስታወሻዎቹን ጠብቆ ከማስቀመጥ ጀምሮ፣ በስሙ የሙዚቃ ማሰልጠኛዎችንና የፋውንዴሽን ስራዎችን እውን ማድረግ የሁላችንም አገራዊና ሙያዊ ሀላፊነት ነው። ኤልያስ መልካን መውደዳችንንና ማከበራችንን በተግባር የምንገልጽበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው።
ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ሰርተሽ አታፍሪሽው
ጌቴ አንለይ እና ኤልያስ መልካ መግባባንት
"ሲስት ካልታገስነው ክፉም ቢሆን አልፈን
እጓዳ ድረስ ይመጣልናል አንኖርም አርፈን"
ሰው እስኪነካቹህ ደግ አትሁኑ እስኪ ስትነኩም ደግ ሁኑ
ኤሉዬ የአለምን ውሎ ያውቀዋል፡፡💔
ለዚህ ነው ከሁሉም ማስበልጠው
ባንተ ልኬት ነው ይንን የማወቀው
ዘፈን ክፉ ከሌለው ፃድቅን ይሆናሉ፡፡
የዘፈን ክፋት የሚለካው ሐሳቡ ላይ ነው፡፡
ዘፈን አጢያት አደለም አለቀ
*(ማዘመር እንዲ መዝፈን እንዲያ)
ድምፃዊት፡ ብስራት ኃይለማርያክ
ግጥም እና ዜማ፡ ኤልያስ መልካ
ቅንብር ፡ኤልያስ መልካ
አልበም፡ ከምን ነፃ ልውጣ
ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ በኤልያስ መልካ አጋፋሪነት የተሰራ ሲሆን ሐሳቦቹ እና የሙዚቃ ግጥሞቹ ትቢታዊ መዳረሻ ያለው ናቸው፡፡ በተለይ "ህሊና" የሰው ልጅን ህሊና የሚገመግም ነው፡፡
ከሙዚቃ ህይወቱ ውጭ!
▪️የራሱ መኪና ነበረችው የሆነ ግዜ ላይ ጓደኞቹ መኪናውን ሲያጧት... መኪናህስ? ብለው ይጠይቁታል... የኤልያስ መልስ አጭር ነበር ለሚያስፈልገው ሰው ሰጥቼዋለሁ! ... ለማን እንደሰጠው ግን አልተናገረም!
▪️የባንክ አካውንት አልነበረውም የሚሰራውን ገንዘብ ቤት ነበር የሚያስቀምጠው...ገንዘብ ፈልጎ የሚመጣ ሰው ቤቱ መጥቶ ይወስዳል ::
▪️ቦሌ አካባቢ አንድ በእድሜ የገፉ አባት ላፕቶፓቸውን ተሰርቀው ሲያለቅሱ ድንገት ኤልያስ ያያቸዋል... እኝህን አባት ዝም ብሎ ማለፍ አልፈለገም...ጠጋ ብሎ ይጠይቃቸዋል የሆኑትን ሲነግሩት እሱም ሙዚቃ ለመስራት የተቀበለው 50ሺ ብር ላይ 2ሺ ብር ብቻ ለራሱ በማንሳት ቀሪውን ለዚህ አባት ይሰጣቸዋል!
▪️ቤቱ የተሰራው ምግብ ሲተርፍ ፍሪጅ ውስጥ አይቀመጥም... ቤቱ መጥተው የሚወስዱ የለመዱ ሰዎች አሉ እነሱ እየመጡ ይወስዳሉ!
▪️ኤልያስ ፊት ማንም ይሁን ሰው ማማት ፈፅሞ አይቻልም... ሲያሙ ከሰማ እንኳን ያንን ሰው ጠርቶ ይሄ ሰው እኮ እንደዚህ እያለ ነው ብሎ ፊት ለፊት ይጠይቀዋል!
▪️ኤልያስ etv ማየት ይወዳል በአንድ ወቅት በ etv ፕሮግራም እየተከታተለ አንዲት ጋዜጠኛ በሆነ ፕሮግራም ላይ ከማህበረሰቡ ባህል ባፈነገጠ መልኩ የተገላለ ጠ አለባበስ ለብሳ ያያታል... በዚህ የተናደደው ኤልያስ በቀጥታ Etv ይሄድና ማናጀሩን አግኝቶ እንዴት እንደዚህ አይነት ከባህል ያፈነገጠ ልብስ ለብሳ ሚዲያ ላይ ታቀርባለች ብሎ ያናግረዋል....! ምን አይነት ሀላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ሰው እንደሆነ አስቡ!
ከከተማው መናኝ መፅሐፍ እንዲሁም ከቅርብ የስራ አጋር ጓደኞቹ የተሰጠ ምስክርነት ::
1970 ♾️
ድምፃዊ ፡ ብስራት ሃይለ ማርያም/ቤሪ/
ግጥም ፣ ዜማ እና ቅንብር ፡ ኤልያስ መልካ
ርዕስ ፡ ህሊና
አልበም ፡ ከምን ነፃ ልውጣ
ጉዳዮ ፡ ህሊና ትክክለኛ ገፅዋን ያወራል ፣ የዘር ጉድንን እያከሸፈ ሰውነትን ይበልጥ ያገዝፈዋል …
''ህሊና ካላስተዋለ
በላጭ ኩሩ ነኝ ባይ ብዙ አለ ''…
በዚህ ሙዚቃ ላይ ሊድ ጊታሩን እንዴት እንደሚያደርጋት ስሙልኝ በቃ የብቃት ጥግ ስትደርስ ይንን ታደርጋለህ ቅንብሮቹ ከ ቀን ወደ ቀን በጣም ይለያሉ ለሙዚቃዎች ሁሉ ይጨነቃል ፡፡
በነገራችን ላይ እሱ ቤት ስትሰራ የነበረች ጀማነሽ የምትባል ቤት ውስጥ የምትሰራ ነበረች ኤልያስ ቤት ከዛ ይንን ሙዚቃ ኤልያስ ያሰማታል ::
ጀማነሽም ሙዚቃው ፊደሎቹ ጥርት ስላላሉ ሌላ ቃል መለሰች ኤልያስ እንደዛ አደለም ብሎ ነገራት ግን ኤልያስ መማር ማወቅ ማስተካከል ስለ ገባው የሷን ምክር ሰምቶ አስተካከለው ፡፡
ከምን ነፃ ልውጣ አልበም ህሊናን ከዚህ ጋር ላያይዘው ፈለኩኝ፡፡
ሙዚቃ እና ሙዚቀኛ ከ ተሙ ጋር
Repost from Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1
+1
ኩኩ ሰብስቤ እና ኤልያስ መልካ «እንባዬ» የሙዚቃ ቪዲዮ ትዝታ
«ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው የኔ ትዝታ» ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ
ድንቁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ካረፈ ዛሬ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል «እንባዬ» የተሰኘው የታወቀ የሙዚቃ ሥራ በመጀመሪያ በክቡር ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ የተዜመ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ በድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድምፅ እንደ አዲስ የተሠራ ድንቅ ሥራ ነው። ትንሽ ጊዜ ስጠኝ የተሰኘ አልበም ላይ የተካተተ ነው፡፡ ሙዚቃው በቅንብር፣ በድምፅ ጥራትና በእንቅስቃሴ ስልት ተሻሽሎና ተውቦ በመቅረቡ የብዙዎችን ቀልብ ሊስብና ትልቅ ቦታ ሊይዝ ችሏል
ይህንን ሙዚቃ እንደ አዲስ አሳምሮ ያቀናበረው ደግሞ ባለብዙ ሙያና ተወዳጁ ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ነበር። ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስለ ኤልያስ ታስታውሳለች፤ «ገና ሙዚቃውን ሲሰማው ደስ አለው፤ የክራሩን ቅኝት እንዴት አድርጎ እንደጨመረበት አሁንም ቢሆን በዓይነ ሕሊናዬ ይታየኛል፤ እሱ ራሱ ሠርቶ እንደ አዲስ ይደሰት ነበር» በማለት ምስክርነቷን ትሰጣለች
ሥራውን በበለጠ ለማሳመር የሙዚቃ ቪዲዮ (ክሊፕ) ለመቅረጽ ስታስብ ከኤልያስ ጋር ተወያየች። «ለዚህ ዘፈን ክሊፕ እንስራ፤ አንተ ግራንድ ፒያኖ ላይ ተቀምጠህ ሱፍህን (ቶክሲዶ) አድርገህ በንጋታው ብቅ በል» አለችው። ኤልያስም በደስታ «እሺ እንዴ! ምን ችግር አለው?» ብሎ ተስማማ። ነገር ግን በነገው ዕለት ለቀረጻ ሲመጣ ቱታ አድርጎ ነበር ኩኩም «እንዴ! እንደዚያ ተቀጣጥረን አልነበረም ወይ?» ስትለው፣ ኤልያስ ፈገግ የሚያደርግ ምላሽ አዘጋጅቶ ነበር— «ባክሽን አሰብኩበትና ደከመኝ፤ ፊቴን አዙሬ ፒያኖው ላይ እቀመጣለሁ እንጂ ሙሉ አልታይም» አላት
ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/share/p/1Ea7xuvoeJ/?mibextid=wwXIfr
ዛሬ
የሙዚቃ ልኳ
የኤልያስ መልካ 💔
እናመሰግንሀለን ህልምህን ለማሳካት እስከ ደም ጠብታ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ተመስገን ኡካሬ ይወድሀል፡፡
ከሚገርሙ የኤልያስ መልካ ስራ🙏
ድምፃዊ፡ ኪዳኔ ሀይሌ
ግጥም፡ ኪዳኔ ሐይሌ
ዜማ፡ ኤልያስ መልካ
ቅንብር፡ በገና ስቱዲዮ ኤልያስ መልካ
አልበም፡በፊቅሪ ሸፊተይ
ሳክስፎኒስት እንዲሁም ድምፃዊ ኪዳኔ ሀይሌ እና ኤላ ከዚህ ዓለሞ ተለይተዋል ቢሆንም ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡
ገሚገርሙ የኤልያስ መልካ ስራ
ድምፃዊ፡ ኪዳኔ ሀይሌ
ግጥም፡ ኪዳኔ ሐይሌ
ዜማ፡ ኤልያስ መልካ
ቅንብር፡ በገና ስቱዲዮ ኤልያስ መልካ
አልበም፡በፊቅሪ ሸፊተይ
ሳክስፎኒስት እንዲሁም ድምፃዊ ኪዳኔ ሀይሌ እና ኤላ ከዚህ ዓለሞ ተለይተዋል ቢሆንም ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡
ኤሉዬ💔💔💔💔 እወድሀለው መልካም እረፍት እንደ ቀልድ ሰባት አመት ሆነህ፡፡
"እንደው ይጓዝ እንጂ የለት ስንቁን ይዞ
አንዴ ስለፃፈው ለዚህች ዓለም ጉዞ
ንገረኝ ጎዳና ስንቱ ተመለሰ
ስንቱ ከ አቀደበት ካሰበው ደረሰ''
----------------------------------------
አላዝንም በዛሬው በያዝኩት ጎዳና
በሕይወት መንገድ ውስጥ ነገ አዲስ ነው እና
ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ግጥም አብታሙ ቦጋለ ዜማ ሚካኤል በላይነህ ቅንብር ኤልያስ መልካ
አንተ በሰጠከኝ እምነት እየተጓዝኩ ነው፡፡ ውጤቱ አንተው ነህ
+1
ቶኪቾ
ድምፃዊ ዮሐንስ በቀለ(ቶኪቾ) የዘጠናዎቹ ድምቀት፣ የነጎድጓድ ድምፅ ባለቤት ፣ የፍሮ ቢት እና የዳን ሶል ስልቶችን አጥብቆ የሚጫወት ዛሬም ድረስ ድምፁ እንዳለ አምሮበታል ይታያል፡፡
ከአራዳ FM 95.1 ጋር በጥቂቱ ቆይታ አድርገናል ከተመስገን ኡካሬ በቅርቡ ይጠብቁ፡፡❤️
Repost from Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
+1
ጋሽ ጥላሁን እና ‘ሩቅ ምስራቅ ሳለሁ’ ሙዚቃ
መስከረም 18፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ባለ ደማቅ ታሪኩ ድምፃዊ ጋሽ ጥላሁን ገሠሠ የተሰጠውን ዜማ ብቻ አጥርቶ የሚዘፍን ሳይሆን፣ በችሎታውና በስሜቱ አበልፅጎ የራሱን አሻራ የሚያስቀምጥ ሙዚቀኛ ለመሆኑ ማሳያው ‘ሩቅ ምስራቅ ሳለሁ’ የሚለው የማይረሳ ሥራው ነው።
ጃፓኗን ወድጄ በሚል እውነተኛ ታሪካቸው የተዘፈነላቸውና የባለብዙ ታሪክ ባለቤቱ አርቲስት 50 ዓለቃ ሸዋንዳኝ ወልደየስ በሰሜን ሸዋ ቡልጋ አውራጃ በ1926 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
ከዛም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እድገታቸውና የልጅነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት ደግሞ ላምበረት አካባቢ ነበር።
በኋላም በ1940 ዓ.ም የክብር ዘበኛ ሰራዊትን ተቀላቅለዋል። ከሁለት ዓመት በኋላ በ1942 ዓ.ም የአንደኛው ቃኘዉ ዘማች ሆነው እንዲሁም በ1944 ዓ.ም በሶስተኛው የቃኘው ዘመቻ ሁለት ጊዜ ወደ ኮሪያ ዘምተዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/19i4VmgJQq/
የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ
Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1
Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical
Telegram:-https://t.me/Arada_Fm
Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital
Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm
@Arada_Fm
+3
ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ አዲስ ነጠላ ዜማ ሊያወጣ ነው
መስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም)ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ ለሚለቀው አዲስ አልበም መዳረሻ ይሆን ዘንድ "በዚህ ላይ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ በቅርብ ቀናት ለማድረስ ዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህ አዲስ ስራው አድማጮች ዘንድ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ለአልበሙም መዳረሻ ይሆን ዘንድ የተሰራ ነው።
በዚህ አዲስ የሙዚቃ ስራ ላይ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ የግጥም ስራውን እልፍአገድ እምሻው፣ ዜማውን አቡዲ እንዲሁም የሙዚቃ ቅንብሩን ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ) በጋራ ሰርተውታል።
ድምፃዊው ከዚህ ቀደም በፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምፃውያን ውድድር በአስራ ሰባተኛው ዙር የፍፃሜ ተወዳዳሪ ሆኖ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። በተጨማሪም በዚሁ መድረክ በተካሄደው የአምስተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይም በድጋሚ በአንደኝነት በማጠናቀቅ የሙዚቃ ችሎታውን ማሳየት ችሏል።
ተመስገን ኡካሬ
የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ
Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1
Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical
Telegram:-https://t.me/Arada_Fm
Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital
Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm
@Arada_Fm
+3
ድምፃዊ ብስራት ጋረደው ዳግም ተመልሷል!
ዛሬ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን «እሁድን በኢቢኤስ» በተሰኘው ፕሮግራም ላይ ተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ጋረደው እንግዳ ሆኖ የቀረበበትን ውይይት ተከታያለው።
በቆይታውም ስለ ድሮ ሙዚቃዎቹ እና ስለ ግል ሕይወቱ አብራርቷል።ብስራት ጋረደው የራሱን ግጥም እና ዜማ የሰራቸውን ሙዚቃዎች ሲያነሳ "ሁሉም ለኔ እጅግ ተወዳጅ ናቸው" ያለ ሲሆን፤ በተለየ ሁኔታ ግን «ከፍጥረት የግልሽ» የተሰኘችውን ሙዚቃውን በበለጠ ሁኔታ እንደሚወድላት ገልጿል።
ስለ ግል ሕይወቱ በነበረው ጨዋታ፣ ያደገው አዲስ አበባ ጊቢገብርኤል እንደሆነ አውስተው፤ተማሪበነበረበት ጊዜ እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ በትምህርቱ ጎበዝ እንዳልነበረና ከዚያ ጊዜ በኋላ ግን ጉብዝናው እየተለካና እየጨመረ የመጣበት እንደነበር ተናግሯል። ዘጠኛ ክፍል ሲደርስ ወደ መሽታ ክለብ በመግባት የሚወዳትን ሙዚቃ መስራት ጀመረ ጅማሮውም በነ ከኔዲ መንገሻ እና በቴዎድሮስ ታደሰ የሙዚቃ ስራ ጉሮሮውን አሟሽቷል፡፡
ስለ ዘጠናዎቹ ጊዜ ሲጠየቅ ደስ የሚል ነበር ያ ጊዜ አድማጮ ጥሩ ነበር የማይደገም ነው ብዬ አስባለው፡፡
የግጥም እና የዜማ ደራሲነት ጅማሮውን በተመለከተ፣ በድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጀመሪያ አልበም ውስጥ ባካተተው "ሰራት" የሙዚቃ ሥራ እንደነበረ ገልጿል።
የራሱን የመጀመሪያ አልበም "ሳላምንበት" የተሰኘ ከአቀናባሪ ዳግማዊ አሊ ጋር በመሆን ለአድማጮች ያደረሰ ሲሆን፤ ያ አንድ አልበም ዛሬም ድረስ ተወዳጅነቱን እንደጠበቀ ቆይቷል፣ ወደፊትም ይቀጥላል።
አሁን ደግሞ ዳግም ወደ ሙዚቃው ኢንዱስትሪ ተመልሷል። በቅርቡ በአዲስ ነጠላ ሙዚቃ፣ በመቀጠልም በሙሉ አልበም እንደሚመጣ በመግለጽ ለአድማጮቹ መልካም ዜና አበስሯል።ከረዥም ጊዜ በኋላ እንደገና በማየታችን ደስ ብሎናል፤ ኢቢኤስ ቴሌቪዥንንም እናመሰግናለን!
ተመስገን ኡካሬ
