cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Arada FM 95.1

This is AradaFm 95.1 Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ @AradaFmbot

Show more
Advertising posts
3 292
Subscribers
+424 hours
+687 days
+29530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 78 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 78 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። በተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ15 ሺህ ጌጋ ዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉን ተናግረዋል። ይህም የዕቅዱን 94 በመቶ መሆኑን ጠቁመው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው አመላክተዋል። ለሀገር ውስጥ ከቀረበ የኃይል ሽያጭ ከ14 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለውጭ ሀገራት ከቀረበው ኃይል ከ78 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። የኃይል ማስተላለፍና ማከፋፈል ሥራዎችን አስተማማኝ ለማድረግ የጥገና ሥራዎች በትኩረት ቢሰሩም በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ዕቅዱን ማሳካት እንዳልተቻለም ጠቅሰዋል። አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!        💬 8545       Telegram:https://t.me/Arada_Fm        Website:https://aradafm.com/        Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/        Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1        Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1        @Arada_Fm
Show all...
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ279 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለመስኖ ልማት ተዘጋጅቷል ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ 279 ሺህ 298 ሄክታር መሬት ለመስኖ ልማት መዘጋጀቱን አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በሃገር አቀፍ ደረጃ 213 ሺህ ሄክታር መሬት ለመስኖ ልማት ለማዘጋጀት ታቅዶ እንደነበርም ነው የገለጸው። ይሁንና ከታቀደው በላይ የ31 በመቶ ጭማሪ የታየበት አፈጻጸም መከናወኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በመስኖ ልማት ስራው 35 ሺህ 700 ሄክታር መሬት በሚኒስቴሩ፥ እንዲሁም 243 ሺህ 598 ሄክታር መሬትበክልሎች መዘጋጀቱ ተገልጿል። በበየነ ወልዴ አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!        💬 8545       Telegram:https://t.me/Arada_Fm        Website:https://aradafm.com/        Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/        Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1        Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1        @Arada_Fm
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በግጭትና ከግጭት ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ሊቆሙ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳሰበ ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም)በግጭትና ከግጭት ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ መንግሥት በአማራና በኦሮሚያ ክልል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የትጥቅ ግጭት የሰብአዊ መብቶች እና ሕጎችን በጣሱ ኃላፊዎችና አባላት ላይ የወንጀል ምርመራና የክስ ሂደት እንዲጀምር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል። ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/share/p/4JgmutzppTtKfwmx/?mibextid=qi2Omg አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!  💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm  Website:https://aradafm.com/  Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/  Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1  Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1  @Arada_Fm
Show all...
👍 1
01:20
Video unavailableShow in Telegram
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ነፍጥ ያነሱ አካላት ወደ ምክክሩ ከመጡ ከለላ የማድረግ ኃላፊነቱ የመንግስት መሆኑን ኮሚሽኑ ገለጸ ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) ነፍጥ ያነሱ አካላት ወደ ምክክሩ የሚመጡ ከሆነ ከለላ የማድረግ ኃላፊነት የመንግስት መሆኑን የኢትዮጵየ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ። የኢትዮጵየ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መሳሪያ ያነሱ አካላት ወደ ምክክሩ መጥተው ያላቸውን ጥያቄዎች አንስተው እንዲወያዩ የአሳታፊነት እና የአካታችነት መርህ እንዳለው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር አምባዬ ኡጋቶ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ አሁንም ለሰላማዊ ውይይት ጥሪውን እያቀረበ መሆኑንም ነው የተናገሩት። ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/aradafm95.1/posts/pfbid08rmfztU74oMyVfbtPXpQiovHN5mkcz8nEZxwFEYFiYvdX1HXHqfypCMqBAL2zthEl አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 53 ሺህ ተማሪዎች ዝግጀት እያደረጉ ነው ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የትግራይ ክልል የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ቁጥር 53 ሺህ ነው ሲል ለአራዳ ገልጿል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ የተፈታኞች ቁጥር በዚህ ደረጃ ከፍ ሊል የቻለው ከዚህ ቀደም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና በጦርነት ምክንያት ፈተና ሳይወስዱ የቀሩ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ኮድ 01 እና ኮድ 07 ተብለው በሁለት ተከፍለው ፈተናቸውን እንደሚፈተኑ ጠቅሰዋል። በተደራራቢ ችግር ሳይፈተኑ ለቀሩ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተና የተሰጠ ቢሆንም ሁሉንም መፈተን ባለመቻሉ አሁን ላይ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን ነው የተናገሩት። ሁሉም ተፈታኞች ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት ፈተናው ይሰጣል ነው የተባለው። በዮሐንስ አበበ አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቤንያሚን ኔታንያሁ በራፋህ የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚቀጥል ገለጹ ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በራፋህ የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስራዔል የምትፈጽመው ጥቃት ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ነው በሚል ውግዘት ቢደርስባቸውም፥ ‘ሃማስን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ’ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የእስራዔል ጦር እሁድ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ 45 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል። ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/aradafm95.1/posts/pfbid0kZqBWHG8fdo1vjRKUDyK5qnBaQcxFqLehkr5sUn5mJvomMoz3A9Ri8WMd8VpBokrl አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...
የኢትዮ-ቱርክ የቢዝነስ ፎረም በአንካራ ተካሄደ ግንቦት 20፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) አንካራ የሚገኘው የኢፌዴሪ ሚሲዮን ከቱርክ የንግድ ማህበረሰብ ማህበር ሙሲያድ ጋር በመተባበር የኢትዮ-ቱርክ የቢዝነስ ፎረም አካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፥ በኢትዮጵያ በርካታ የቢዝነስ እድሎች መኖራቸውን በመጥቀስ፥ የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል። ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/aradafm95.1/posts/pfbid02gchyUdHhgBsbYTVpG4kt1TFJz9sTcYucDqNrvSPuMwVepLwYMSXRaiaK9K6byYVYl አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Show all...