uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

የኔ ዜማ የአድማጮች የሙዚቃ ምርጫ

የኔ ዜማ የአድማጮች የሙዚቃ ምርጫ

Kanalga Telegram’da o‘tish

- በፌስቡክ👇 https://www.facebook.com/100022318509408/posts/1859085851512014/?app=fbl https://www.facebook.com/share/1AMgudXhJr/ - በቴሌግራም ገፅ👇 https://t.me/biggrs - ቲክቶክ ገፅ 👇 tiktok.com/@temesgen_ukare - በዩትዮብ ተከታተሉን👇 https://youtube.com/@temuyehag

Ko'proq ko'rsatish
289
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
+1230 kun
Postlar arxiv
የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ስርዓትን የሚያሳልጥ አዲስ አፕ ይፋ አደረገ ይህ የቴክኖሎጂ ስርዓት ድረ-ገጾችን፣ የተቋማት ኔትወርኮችን፣ የስማርት ሲቲ መሠረተ ልማቶችን እና የግል መሣሪያዎችን ከሳይበር ጥ
+2
የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ስርዓትን የሚያሳልጥ አዲስ አፕ  ይፋ አደረገ ይህ የቴክኖሎጂ ስርዓት ድረ-ገጾችን፣ የተቋማት ኔትወርኮችን፣ የስማርት ሲቲ መሠረተ ልማቶችን እና የግል መሣሪያዎችን ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የተዘጋጀ ሲሆን፤ እንደ ራንሰምዌር፣ ፊሺንግ፣ ማልዌር እና ዲዶስ (DDoS) ያሉ የሳይበር ስጋቶችን በቀንና በሌሊት የ24 ሰዓት የቅርብ ክትትል በማድረግ አስቀድሞ ለመግታት ያስችላል ተብሏል። የድርጅቱ መግለጫ እንደሚያመላክተው፤ "ኤ አይ ሳይበር ጋርድ" በኢትዮጵያ የቅጂ መብት ሥርዓት የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ የምስክር ወረቀት ያገኘ ሲሆን፤ ለመንግሥት ተቋማት፣ ለባንኮች፣ ለሆስፒታሎች፣ ለዳታ ማዕከላትና ለከተማ አስተዳደሮች አስተማማኝ የሳይበር ጥበቃ ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል። በተጨማሪም ስርዓቱ ጥቃቶች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያዎችን የመስጠት፣ የወረዱ ፋይሎችንና አጠራጣሪ ሊንኮችን የመፈተሽ እንዲሁም አገልግሎቶች ሲቋረጡ በቴሌግራም ወይም በኤስ ኤም ኤስ (SMS) ፈጣን መልእክት የመላክ አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ኢቫንጋዲ አልበም እና ድምፃዊ ኣብረሃም ኣፈወርቂ የሚያስተሳስራቸው ምን ይሁን? በ1994 ዓ.ም መገባደጃ ላይ ለሙዚቃ አፍቃሪያን የቀረበው «ኢቫንጋዲ» አልበም፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ቅንብር  ይዞ የመጣ ልዩ ሥራ ነበር። ወጣቶቹ ድምፃውያን ጎሳዬ ተስፋዬና አለማየሁ ሂርጶ በጋራ ያቀረቡት ይህ አልበም፣ በአጠቃላይ 13 ዘፈኖችን ያቀፈ ሲሆን ከግጥምና ዜማ አመራረጡ እስከ ሙዚቃ ቅንብሩ ድረስ በተለያዩ የጥበብ ማዕከላትን አርጎ የተሞላና ለመመርመር የሚጋብዝ ድንቅ አጠቃላይ ሥራ ሆኖ ተሰርቷል። የአልበሙ ሙሉ የሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንግ በከፍተኛ ጥራት በባለሙያው ኤልያስ መልካ የተከወነ ሲሆን፣ በሥራው ላይ በርካታ ታዋቂ የዜማና የግጥም ደራሲያን ተሳትፈውበታል። በግጥም ድርሰት አለማየሁ ደመቀ፣ መሰለ ጌታሁን፣ አብርሃም አፈወርቂ፣ ደረጀ ተክሉ፣ ቢኒያም አህመድ፣ ማርክ ሞሪሰን እና አብዱ ኪያር ሲሳተፉ፤ በዜማ በኩል ደግሞ አበበ ብርሃኔ፣ አለማየሁ ደመቀ፣ ጎሳዬ ተስፋዬና ኤልያስ መልካ አሻራቸውን አሳርፈዋል። ለመሆኑ ይህንን አልበም ከኤርትራዊው አንጋፋ ድምፃዊ ኣብረሃም ኣፈወርቂ ጋር የሚያስተሳስረው ምስጢር ምንድን ነው? መልሱ ያለው በአልበሙ ውስጥ በተካተተውና በድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ  «ዋ» በተሰኘው ተወዳጅ ሙዚቃ ውስጥ ነው። የዚህ ዘፈን ዜማ ቀጥታ ውርስ የተደረገው ከኣብረሃም ኣፈወርቂ «ኣቤላ» ከተሰኘው የማይረሳ የሙዚቃ ሥራ ሲሆን፣ ኢቫንጋዲ አልበም ላይ ግጥሙ በአለማየሁ ደመቀ ተፅፎ፣ ዜማው በኣብረሃም ተዘጋጅቶ በኤልያስ መልካ ቅንብር ለሕዝብ በቅቷል። ሙዚቃዎችን በድጋሚ መስራት በርካታ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን፣ ዋናው አላማ የጥበቡን ባለቤት ማመስገን፣ ሥራዎቹን ማስታወስና ለአዲሱ ትውልድ ደግሞ የሙዚቃ አቅጣጫ መጠቆሚያ ማድረግ ነው። የ«ዋ» ዘፈንም የኣብረሃም ኣፈወርቂን ጥበባዊ ገደብ የዜማ ሀብት ለአዲሱ ትውልድ በድጋሚ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። መስከረም 27 ቀን፣ ድምፃዊ፣ የዜማና የግጥም ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች የሆነው ኣብረሃም ኣፈወርቂ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየበት 19 ዓመት ሞላው። የስድስት አልበሞች ባለቤት የሆነው ይህ ታላቅ የኪነ-ጥበብ ሰው በተወለደ በ40 ዓመቱ በስደት ቢለየንም፣ በ«ኢቫንጋዲ» እና መሰል አልበሞች ላይ ያረፈው ጥበባዊ አሻራው በሙዚቃ አፍቃሪያን ልብ ውስጥ ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል። ተመስገን ኡካሬ

ምድራዊ መልዓክ…
ምድራዊ መልዓክ…

ሀገራችን ኤልያስ መልካን በምን ያህል ደረጃ አመስግናዋለች? (ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ) ውስጤን እንደ እግር እሳት የሚበላኝ በውስጤ ያለው ቁጭት ልግለፅ ኢትዮጵያ በዘመናዊ ሙዚቃ ታሪኳ ውስጥ እንደ ኤልያስ መልካ ያለ አቀናባሪና የዜማ ደራሲ ማግኘቷ ታላቅ እድል ነበር። ባለፉት በርካታ ዓመታት ና ከዚያም በፊት፣ የዘመኑን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የቃኙ በርካታ የሙዚቃ አልበሞችና ነጠላ ዜማዎች በእርሱ አሻራና አቀናባሪነት ተቀርፆ ለህዝብ በቅተዋል። ዛሬም ድረስ በየቀኑ በበርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ኤፍ ኤም ፕሮግራሞች ላይ እርሱ ያቀናበራቸው ሙዚቃዎች የየዕለት ስራዎች ማጣፈጫ ሆነው ሲደመጡ ኖረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሰጠንን ታላቅ የጥበብ ሀብት ያህል አገራችን ኤልያስን በምን ያህል ደረጃ አመስግናዋለች? በስሙ የታነጸ ዘላቂ ተቋም ወይም አበርክቶውን የሚመጥን ክብር ሰጥተነዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ አሁንም በህሊናዬ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ ከህልፈቱ በኋላ እሱን የሚያስቡና ክብር የሚሰጡ የተለያዩ ፕሮግራሞች ቢኖሩም፣ የሰራቸውን ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ለቀጣዩ ትውልድ በትምህርት ደረጃ ማስተላለፍና የፈጠራ ስራዎቹን አጠናክሮ ማስቀመጥ ላይ ገና ብዙ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉን እገነዘባለው፡፡ የታላቁ አቀናባሪ የኤልያስ መልካ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የሙዚቃ ስቱዲዮ ቁሳቁሶች የት ይገኛሉ? እርሱ የተጠቀመባቸውን የስራ ዘዴዎችና የዜማ ቅንብሮች በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ተቋማት ደረጃ በስርዓተ-ትምህርት ተቀርጸው እየተሰጡ ነው ወይ የሚለው በጥንቃቄ ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ ነው። እርሱን ለመዘከርና ለመጠበቅ የታሰቡ እንደ "ኤልያስ መልካ ፋውንዴሽን" ያሉ ተቋማት ምሥረታና በስሙ የሚከፈቱ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴዎች አሁንም ቢሆን የሁሉም ባለሙያና ጥበብ ወዳድ የተቀናጀ ድጋፍ ይሻሉ። ሙዚቃውን ዕለት ተዕለት ከማዳመጥ አልፈን ለዚህ ዘመን ትውልድ ኤልያስ መልካ ማነው ለማለትና አጠቃላይ የሙዚቃ ንግስናውን በአግባቡ ለመመዝገብ የታሪካዊ ሰነዶችና የምርምር ስራዎች መስፋፋት ወሳኝ ነው። የኤልያስ ስም ከፕሮግራም ማጣፈጫነት ባለፈ፣ የታሪክና የትምህርት ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል የኪነ-ጥበቡ ማህበረሰብና የሚዲያ ተቋማት በጋራ ሊሰሩበት ይገባል። እርሱ ላበረከተልን ጥበብ የምንመልሰው እውነተኛ ክብር፣ ስራዎቹ ሳይረሱና ሳይበላሹ ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተላለፉ በስሙ የቆሙ ዘላቂ ተቋማትን እውን ማድረግ ስንችል ብቻ ነው። በመሆኑም፣ ስለ ኤልያስ መልካ ያለን ፍቅርና አክብሮት በቃላትና በዓመታዊ ሙት ዓመት መታሰቢያዎች ብቻ ሳይወሰን፣ ወደተጨባጭ የተቋም ግንባታና የታሪክ ጥበቃ ሊሸጋገር ይገባል። የሙዚቃ መሳሪያዎቹንና የታሪክ ማስታወሻዎቹን ጠብቆ ከማስቀመጥ ጀምሮ፣ በስሙ የሙዚቃ ማሰልጠኛዎችንና የፋውንዴሽን ስራዎችን እውን ማድረግ የሁላችንም አገራዊና ሙያዊ ሀላፊነት ነው። ኤልያስ መልካን መውደዳችንንና ማከበራችንን በተግባር የምንገልጽበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

ምድራዊ መልዓክ ኤልያስ መልካ

ከማንም በላይ የምወደው በዚህ ደግ እሳቤው ነው፡፡

ሰርተሽ አታፍሪሽው ጌቴ አንለይ እና ኤልያስ መልካ መግባባንት "ሲስት ካልታገስነው ክፉም ቢሆን አልፈን እጓዳ ድረስ ይመጣልናል አንኖርም አርፈን" ሰው እስኪነካቹህ ደግ አትሁኑ እስኪ ስትነኩም ደግ ሁኑ ኤሉዬ  የአለምን ውሎ ያውቀዋል፡፡💔 ለዚህ ነው ከሁሉም ማስበልጠው

ባንተ ልኬት ነው ይንን የማወቀው ዘፈን ክፉ ከሌለው ፃድቅን ይሆናሉ፡፡ የዘፈን ክፋት የሚለካው ሐሳቡ ላይ ነው፡፡ ዘፈን አጢያት አደለም አለቀ

*(ማዘመር እንዲ መዝፈን እንዲያ) ድምፃዊት፡ ብስራት ኃይለማርያክ ግጥም እና ዜማ፡ ኤልያስ መልካ ቅንብር ፡ኤልያስ መልካ አልበም፡ ከምን ነፃ ልውጣ ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ በኤልያስ መልካ አጋፋሪነት የተሰራ ሲሆን ሐሳቦቹ እና የሙዚቃ ግጥሞቹ ትቢታዊ መዳረሻ ያለው ናቸው፡፡ በተለይ "ህሊና" የሰው ልጅን ህሊና የሚገመግም ነው፡፡

ከሙዚቃ ህይወቱ ውጭ! ▪️የራሱ መኪና ነበረችው የሆነ ግዜ ላይ ጓደኞቹ መኪናውን ሲያጧት... መኪናህስ? ብለው ይጠይቁታል... የኤልያስ መልስ አጭር ነበር ለሚያስፈልገው ሰው ሰጥቼዋለሁ! ... ለማን እንደሰጠው ግን አልተናገረም! ▪️የባንክ አካውንት አልነበረውም የሚሰራውን ገንዘብ ቤት ነበር የሚያስቀምጠው...ገንዘብ ፈልጎ የሚመጣ ሰው ቤቱ መጥቶ ይወስዳል :: ▪️ቦሌ አካባቢ አንድ በእድሜ የገፉ አባት ላፕቶፓቸውን ተሰርቀው ሲያለቅሱ ድንገት ኤልያስ ያያቸዋል... እኝህን አባት ዝም ብሎ ማለፍ አልፈለገም...ጠጋ ብሎ ይጠይቃቸዋል የሆኑትን ሲነግሩት እሱም ሙዚቃ ለመስራት የተቀበለው 50ሺ ብር ላይ 2ሺ ብር ብቻ ለራሱ በማንሳት ቀሪውን ለዚህ አባት ይሰጣቸዋል! ▪️ቤቱ የተሰራው ምግብ ሲተርፍ ፍሪጅ ውስጥ አይቀመጥም... ቤቱ መጥተው የሚወስዱ የለመዱ ሰዎች አሉ እነሱ እየመጡ ይወስዳሉ! ▪️ኤልያስ ፊት ማንም ይሁን ሰው ማማት ፈፅሞ አይቻልም... ሲያሙ ከሰማ እንኳን ያንን ሰው ጠርቶ ይሄ ሰው እኮ እንደዚህ እያለ ነው ብሎ ፊት ለፊት ይጠይቀዋል! ▪️ኤልያስ etv ማየት ይወዳል በአንድ ወቅት በ etv ፕሮግራም እየተከታተለ አንዲት ጋዜጠኛ በሆነ ፕሮግራም ላይ ከማህበረሰቡ ባህል ባፈነገጠ መልኩ የተገላለ ጠ አለባበስ ለብሳ ያያታል... በዚህ የተናደደው ኤልያስ በቀጥታ Etv ይሄድና ማናጀሩን አግኝቶ እንዴት እንደዚህ አይነት ከባህል ያፈነገጠ ልብስ ለብሳ ሚዲያ ላይ ታቀርባለች ብሎ ያናግረዋል....! ምን አይነት ሀላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ሰው እንደሆነ አስቡ! ከከተማው መናኝ መፅሐፍ እንዲሁም ከቅርብ የስራ አጋር ጓደኞቹ የተሰጠ ምስክርነት :: 1970 ♾️

ድምፃዊ ፡ ብስራት ሃይለ ማርያም/ቤሪ/ ግጥም ፣ ዜማ እና ቅንብር ፡ ኤልያስ መልካ ርዕስ ፡ ህሊና አልበም ፡ ከምን ነፃ ልውጣ ጉዳዮ ፡ ህሊና ትክክለኛ ገፅዋን ያወራል ፣ የዘር ጉድንን እያከሸፈ ሰውነትን ይበልጥ ያገዝፈዋል … ''ህሊና ካላስተዋለ በላጭ ኩሩ ነኝ ባይ ብዙ አለ ''… በዚህ ሙዚቃ ላይ ሊድ ጊታሩን እንዴት እንደሚያደርጋት ስሙልኝ በቃ የብቃት ጥግ ስትደርስ ይንን ታደርጋለህ ቅንብሮቹ ከ ቀን ወደ ቀን በጣም ይለያሉ ለሙዚቃዎች ሁሉ ይጨነቃል ፡፡ በነገራችን ላይ እሱ ቤት ስትሰራ የነበረች ጀማነሽ የምትባል ቤት ውስጥ የምትሰራ ነበረች ኤልያስ ቤት ከዛ ይንን ሙዚቃ ኤልያስ ያሰማታል :: ጀማነሽም ሙዚቃው ፊደሎቹ ጥርት ስላላሉ ሌላ ቃል መለሰች ኤልያስ እንደዛ አደለም ብሎ ነገራት ግን ኤልያስ መማር ማወቅ ማስተካከል ስለ ገባው የሷን ምክር ሰምቶ አስተካከለው ፡፡ ከምን ነፃ ልውጣ አልበም ህሊናን ከዚህ ጋር ላያይዘው ፈለኩኝ፡፡ ሙዚቃ እና ሙዚቀኛ ከ ተሙ ጋር

ኩኩ ሰብስቤ እና ኤልያስ መልካ «እንባዬ» የሙዚቃ ቪዲዮ ትዝታ «ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው የኔ ትዝታ» ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድንቁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ካረፈ ዛሬ
+1
ኩኩ ሰብስቤ እና ኤልያስ መልካ «እንባዬ» የሙዚቃ ቪዲዮ ትዝታ «ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው የኔ ትዝታ» ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድንቁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ካረፈ ዛሬ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል «እንባዬ» የተሰኘው የታወቀ የሙዚቃ ሥራ በመጀመሪያ በክቡር ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ የተዜመ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ በድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድምፅ እንደ አዲስ የተሠራ ድንቅ ሥራ ነው። ትንሽ ጊዜ ስጠኝ የተሰኘ አልበም ላይ የተካተተ ነው፡፡ ሙዚቃው በቅንብር፣ በድምፅ ጥራትና በእንቅስቃሴ ስልት ተሻሽሎና ተውቦ በመቅረቡ የብዙዎችን ቀልብ ሊስብና ትልቅ ቦታ ሊይዝ ችሏል ይህንን ሙዚቃ እንደ አዲስ አሳምሮ ያቀናበረው ደግሞ ባለብዙ ሙያና ተወዳጁ ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ነበር። ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስለ ኤልያስ ታስታውሳለች፤ «ገና ሙዚቃውን ሲሰማው ደስ አለው፤ የክራሩን ቅኝት እንዴት አድርጎ እንደጨመረበት አሁንም ቢሆን በዓይነ ሕሊናዬ ይታየኛል፤ እሱ ራሱ ሠርቶ እንደ አዲስ ይደሰት ነበር» በማለት ምስክርነቷን ትሰጣለች ሥራውን በበለጠ ለማሳመር የሙዚቃ ቪዲዮ (ክሊፕ) ለመቅረጽ ስታስብ ከኤልያስ ጋር ተወያየች። «ለዚህ ዘፈን ክሊፕ እንስራ፤ አንተ ግራንድ ፒያኖ ላይ ተቀምጠህ ሱፍህን (ቶክሲዶ) አድርገህ በንጋታው ብቅ በል» አለችው። ኤልያስም በደስታ «እሺ እንዴ! ምን ችግር አለው?» ብሎ ተስማማ። ነገር ግን በነገው ዕለት ለቀረጻ ሲመጣ ቱታ አድርጎ ነበር ኩኩም «እንዴ! እንደዚያ ተቀጣጥረን አልነበረም ወይ?» ስትለው፣ ኤልያስ ፈገግ የሚያደርግ ምላሽ አዘጋጅቶ ነበር— «ባክሽን አሰብኩበትና ደከመኝ፤ ፊቴን አዙሬ ፒያኖው ላይ እቀመጣለሁ እንጂ ሙሉ አልታይም» አላት ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/share/p/1Ea7xuvoeJ/?mibextid=wwXIfr

ዛሬ የሙዚቃ ልኳ የኤልያስ መልካ 💔 እናመሰግንሀለን ህልምህን ለማሳካት እስከ ደም ጠብታ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ተመስገን ኡካሬ ይወድሀል፡፡
ዛሬ የሙዚቃ ልኳ የኤልያስ መልካ 💔 እናመሰግንሀለን ህልምህን ለማሳካት እስከ ደም ጠብታ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ተመስገን ኡካሬ ይወድሀል፡፡

ከሚገርሙ የኤልያስ መልካ ስራ🙏 ድምፃዊ፡ ኪዳኔ ሀይሌ ግጥም፡ ኪዳኔ ሐይሌ ዜማ፡ ኤልያስ መልካ ቅንብር፡ በገና ስቱዲዮ ኤልያስ መልካ አልበም፡በፊቅሪ ሸፊተይ ሳክስፎኒስት እንዲሁም ድምፃዊ ኪዳኔ ሀይሌ እና ኤላ ከዚህ ዓለሞ ተለይተዋል ቢሆንም ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡

ገሚገርሙ የኤልያስ መልካ ስራ ድምፃዊ፡ ኪዳኔ ሀይሌ ግጥም፡ ኪዳኔ ሐይሌ ዜማ፡ ኤልያስ መልካ ቅንብር፡ በገና ስቱዲዮ ኤልያስ መልካ አልበም፡በፊቅሪ ሸፊተይ ሳክስፎኒስት እንዲሁም ድምፃዊ ኪዳኔ ሀይሌ እና ኤላ ከዚህ ዓለሞ ተለይተዋል ቢሆንም ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡

የኤልያስ መልካ ስራዎችን የወሰኑትን የመረጥነውን እንጋብዛለን

ኤሉዬ💔💔💔💔 እወድሀለው መልካም እረፍት እንደ ቀልድ ሰባት አመት ሆነህ፡፡ "እንደው ይጓዝ እንጂ የለት ስንቁን ይዞ አንዴ ስለፃፈው ለዚህች ዓለም ጉዞ ንገረኝ ጎዳና ስንቱ ተመለሰ ስንቱ ከ አቀ
ኤሉዬ💔💔💔💔 እወድሀለው መልካም እረፍት እንደ ቀልድ ሰባት አመት ሆነህ፡፡ "እንደው ይጓዝ እንጂ የለት ስንቁን ይዞ አንዴ ስለፃፈው ለዚህች ዓለም ጉዞ ንገረኝ ጎዳና ስንቱ ተመለሰ ስንቱ ከ አቀደበት ካሰበው ደረሰ'' ---------------------------------------- አላዝንም በዛሬው በያዝኩት ጎዳና በሕይወት መንገድ ውስጥ ነገ አዲስ ነው እና ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ግጥም አብታሙ ቦጋለ ዜማ ሚካኤል በላይነህ ቅንብር ኤልያስ መልካ አንተ በሰጠከኝ እምነት እየተጓዝኩ ነው፡፡ ውጤቱ አንተው ነህ

ቶኪቾ ድምፃዊ ዮሐንስ በቀለ(ቶኪቾ) የዘጠናዎቹ ድምቀት፣ የነጎድጓድ ድምፅ ባለቤት ፣ የፍሮ ቢት እና የዳን ሶል ስልቶችን አጥብቆ የሚጫወት ዛሬም ድረስ ድምፁ እንዳለ አምሮበታል ይታያል፡፡ ከአራዳ F
+1
ቶኪቾ ድምፃዊ ዮሐንስ በቀለ(ቶኪቾ) የዘጠናዎቹ ድምቀት፣ የነጎድጓድ ድምፅ ባለቤት ፣ የፍሮ ቢት እና የዳን ሶል ስልቶችን አጥብቆ የሚጫወት ዛሬም ድረስ ድምፁ እንዳለ አምሮበታል ይታያል፡፡ ከአራዳ FM 95.1 ጋር በጥቂቱ ቆይታ አድርገናል ከተመስገን ኡካሬ በቅርቡ ይጠብቁ፡፡❤️