cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሙዚቃ እና ሙዚቀኛን ከ ተሙ ጋር🎙🎨

ካሴት ሙዚቃዊ እይታ የማይዳሰስ የለም ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

Show more
Advertising posts
269
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መንቃት አንጀምርም ወይ ከቁስ ሰው አይበልጥም ወይ ምናለ ከፍቅር በላይ ከ ቁስ ሰው አይበልጥም ወይ… የግጥም ዜማ ደራሲ እና ፕሮዲውሰር አለማየሁ ደመቀ ሊመሰገን ቀን ተቆረጠበት፡፡ "ዮቶር ድግስ" ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ "ዮቶር ድግስ "የተሰኘ ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት  ሰኔ 15/2016 ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ ሊካሄድ  እንደሆነ አዘጋጆቹ ዛሬ ሰኔ 10/2016 በማርየት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ተወዳጁ ግጥም ዜማ ደራሲ እና ፕሮዲውሰር አለማየሁ ደመቀ ለማክበር በርካታ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ፡፡ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ ግርማ ተፈራ ፣ ሀሊማ አብዱራህማን ፣ ሄለን በርሄ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣ መስከረም ኡስማንን ጨምሮ ከ ኢትዮ ለዛ ፣ ሻኩራ ባንድ ፣ ኩርማንባንድ ሆነው ያቀርባሉ ፡፡ የግጥም ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ 250 በላይ የግጥም ስራዎችን ለተለያዩ ድምፃዊያን ያበረከተ ሲሆን በማህበራዊ ጉዳይ ላይም የሰራቸው ስራዎች አሉ፡፡ የኮንሰርቱ አላማ  ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ሥራዎችን፣ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን "ዮቶር 1,ኮብላዩ " ካሕን እና በቅርቡ ለንባብ ያበቃውን "ዮቶር 2,ቶ" ለሥነጽሁፍ አፍቃሪያን ያበረከተውን ላለፉት 25 አመታት በሙያው ፣በክህሎቱ እና በተሰጥኦው አገር እና ወገንን ሲያገለግል የቆየው ደራሲ፣የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ፕሮዲዩሰር እና ድምፃዊ ዓለማየሁ ደመቀን የሚከበርበትና ሁለተኛ መፅሐፉን "ዮቶር 2:ቶ"ን የሚመረቅበት ቀን እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልፀዋል ። የኮንሰርቱ መግቢያ ዋጋ=3000 ነው ተብሏል፡፡ @biggrs @yenevibe
Show all...
የግጥም ዜማ ደራሲ እና ፕሮዲውሰር አለማየሁ ደመቀ ሊመሰገን ቀን ተቆረጠበት፡፡ "ዮቶር ድግስ" ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ "ዮቶር ድግስ "የተሰኘ ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት  ሰኔ 15/2016 ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ ሊካሄድ  እንደሆነ አዘጋጆቹ ዛሬ ሰኔ 10/2016 በማርየት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። የኮንሰርቱ አላማ  ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ሥራዎችን፣ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን "ዮቶር 1,ኮብላዩ " ካሕን እና በቅርቡ ለንባብ ያበቃውን "ዮቶር 2,ቶ" ለሥነጽሁፍ አፍቃሪያን ያበረከተውን ላለፉት 25 አመታት በሙያው ፣በክህሎቱ እና በተሰጥኦው አገር እና ወገንን ሲያገለግል የቆየው ደራሲ፣የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ፕሮዲዩሰር እና ድምፃዊ ዓለማየሁ ደመቀን የሚከበርበትና ሁለተኛ መፅሐፉን "ዮቶር 2:ቶ"ን የሚመረቅበት ቀን እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልፀዋል ። የኮንሰርቱ መግቢያ ዋጋ=2999.00 ብር @biggrs @yenevibe
Show all...
ዳኞች በለውጣቸው ተደስተው ግን የሙዚቃ መሰረታዊ ችግር ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡ ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው ምዕራፍ  በአምስተኛ ሳምንት ስድስት ተወዳዳሪዎችን ይዞ ከኮከብ ባንድ ጋር ውድድሩን አከናውነዋል ፡፡ *ምን አዲስ ነገር ታዬ… - ተወዳዳሪዎች በሁለት ዙር የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ሲያቀርቡ አንደኛው ዙር ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተጫውተዋል እኔን ይመጥነኛል ያሉትን በመድረኩ አቅርበዋል፡፡ - ውድድሩ በሚከናወንበት ቦታ ተመልካች የፋና ላምሮት ወዳጅ ፣የሙዚቃ ሰዎች ፣ በዚህ ውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ ለቀጣዩ ለመዘጋጀት የሚያደርጉ ሰዎች እና ተወዳዳሪዎችን ለመደገፍ የመጡ ሰዎች በቦታው ታድመው ተከታትለዋል ፡፡ - በመድረኩ ከቀረቡ የሙዚቃ ስራዎች መካከል የሰሩት በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር የጋሽ ተስፋዬ ለማ ፣  ተመስገን አፈወርቅ ፣ ብስራት ጋረደው ፣ አበበ ብርሀኔ በቅንብሩ የአበጋዝ ፣  ቴዲ ማክ ፣ ዳግማዊ አሊ እኚህ እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርበዋል፡፡ * ዳኞች ለተወዳዳሪዎች ከስልትም ከስሜትም የሰጡትን አስተያየት ሬንጅ ስፋት ፣ ይበልጥን መስራትን ፣ ለስሜት መጨነቅ ፣ የዜማ ብዛትን መምረጥ ፣ ሪትም ፣ ኪ መረጣ ፣ ውበት የዜማ የድምፅ ፣ የማይክ አጠቃቀም ፣ የባንድ ውህድ ፣ ፍሬዚንግ /የዜማ ሐረጋት ተጀምሮ እስኪያልቅ ያለውን/ ፣ ቅኝት ፣ የድምፅ ከለር ፣ የጉልበት ምጠና እና አጠቃቀም ፣ ትንፋሽ ፣ የድምፅ ቴክኒክ ፣ መረጋጋት ፣ ስሜት ተከትሎ ሙዚቃውን ማቅረብ ፣ ቃላትን አጥብቆ ማለማት ፣ ፍርሀት ፣ አገላለፅ እኚህ እና የመሳሰሉት አስተያየት ተሰንዝረዋል ፡፡ * ኮከብ ባንድ ከተወዳዳሪዎች ወደ 12  ሙዚቃዎች ተጫውተዋል ፡፡ - ቀመር ዩሱፍ/ኦሮምያ/ ፣ ተፈራ ነጋሽ/ምን አምኜ/ ፣ ፍቅር አዲስ ነቃ ጥበብ/ አልገባኝም / ፣ ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ/ አይ ዘመን/ ፣ ትክለለኛው ሙዚቃ የጥላሁን ገሰሰን ደግማ የተጫወተችሁ የዘሪቱ ከበደ/ ወጣትዋ/ ፣ ሚኒልክ ወስናቸው/በሰው ሃገር/ ፣ ጋሽ ሙሐሙድ አህመድ /ፍቅሬ በመሆንሽ/ ፣ እብስት ጥሩነህ/ከመሸህ መጣህ/ ፣ ነፃነት መለሰ / ሁሉን ትቼ/ ሙዚቃዎች በመድረኩ ቀርበዋል፡፡ *ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት አስተያየት ሰተውናል፡፡ - ብሩክ አሰፋ:- ምን ለማሳየት ነው ዜማ መምረጥ ያለብኝ የሚለውንም ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ -የሹም ነሽ ታዬ:-እራሳችሁን ድምፃችሁን የሚፈትሽ ሙዚቃ የምትመርጡትን ሁሉ አስቡበት፡፡ - አማኑኤል ይልማ:- የድምፅ ውበት እና ቅኝት እጅግ ተጠንቅቆ ማቅረብ ይኖርባችኃል፡፡ * በእለቱ ያለፉ እና አንድ ተወዳዳሪ የተሰናበተውን እንጠቁም፡፡ -ጴጥሮስ ማስረሻ - 59968 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ -ናሆም ነጋሽ-59489 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ -ዝንታለም ባዬ-58454 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ -ኤርሚያስ ዳኛው-58368 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ -ዘላለም ፀጋዬ-57980 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ በእለቱ የተሰናበተችሁ ባወፉ በመጡት ዙሮች አስገራሚ እና የተስፋ የተጣለባት በተጨማሪም ከ ዳኞች የተሰጣት ገንቢ አስተያየት በመቀበል በውድድሩ ጥሩ ቆይታ አግርጋለች በስተ መጨረሻ ተናብታለች ተወዳዳሪ ትዕግስት አንተነህ፡፡ * ትዕግስት አንተነህ:-" በጣም አማመሰግናት ድምፃዊ ታምር ግዛው ዲዴፋትስ ውጪ ሀገር ነው የሚገኘሁ እህቴ መልከ ማርያም ጥላዬ ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡"ብላለች፡፡ ፋና ላምሮት አብሮተቱን ገልፆ ከ 7000 ብር ጋር ሸኝቷቷል፡፡ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ ፋና ላምሮት ቸር ያቆየን ቸር እንሰንብት
Show all...
👍 1
ፋና ላምሮት የቅዳሜ ውሎ አጠቃላይ ሁናቴ በምስል👆 ዝርዝር ጉዳይ👇 yenevibe.com ጎብኙን እናመሰግናለን፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ! የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የወንዲ ማክ " ይንጋልሽ " አልበም ቀን ተቆረጠለት፡፡ የድምፃዊ ወንዲ ማክ / ወንደሰን መኮንን " ይንጋልሽ " የተሰኘ አዲስ አልበም ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይለቀቃል።አልበሙ በወን ማክ የዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል። ወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ) በተለያዩ ነጠላ ዜማዎቹ የሚታወቅ ሲሆን ታገቢኛለሽ ወይ ፣  ሸብ አርጋ ፣ ሸንባራንባ ፣ እጅ ወደ ላይ ፣ አባ ዳማ ፣ ገዳይ እና ለመጨረሻ ጊዜ ያወጣው ነጠላ ዜማ ዋንጫ ይሰኛል፡፡ አሁን የራሱን የበኩር አልበም ጨርሶ ለአድማጭ ሊደርስ ቀን ቆርጧል "ይንጋልሽ" ፡፡ @biggrs @yenevibe
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቅዳሜ ምስጋና… ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በብዙ ሊነገርለት የሚገባ በሰራው ልክ ያልተመሰገነ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህር ሆኖ ያገለገለ (የረቂቅ የሙዚቃ አልበም ባለቤት )ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ህዝብን እያገለገለ ያለ ድንቅ ሙዚቀኛ ፡፡ በህዝብ ዘንድ #ጠንካራው #መንፈሴ በተሰኘው ረቂቅ አልበም ይታወቃል፡፡ ፒያኒስት ጋሽ ግርማ ይፍራሸዋ ስለ ሰጠኸን ሙዚቃ ስለ ምትሰጠን ሁሉ ፡፡ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ክፍል ከልብ ያመሰግንሀል፡፡ yenevibe.com @biggrs
Show all...
እንኳን ደስ አለህ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ እና ከጀርባ ሆናችሁ የሰራችሁት ድንቅ የሙዚቃ ከያኒያን፡፡ -በየኔ ቫይብ የኢትዮጲያ የሙዚቃ ሰንጠረዝ አብዛኛውን ሰሞኑን በወጣው የመሳይ ተፈራ የልቤን አልበም ተቆጣጥሯል፡፡ - ናትናኤል ግርማቸው ፅሁፍህ ብርቱ ነው ፣ ታምሩ አማረ ጣቶችህ ምን ጊዜም በበጎ መንገድ ይሞገሳሉ የየኔ ቫይብ ወዳጆች ስለሆናችሁ እናመሰግናለን፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡ ሌሎችንም ተጨማሪ ለማየት👇 • Our Main Website 👉 https://yenevibe.com • Weekly, Monthly & Yearly Charts 👉 https://yenevibe.com/charts • Weekly Music Charts 👉 https://yenevibe.com/weekly-top-hit-songs @yenevibe
Show all...
image_2024-06-14_10-16-03.png8.89 KB
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ድምፃዊ ኤርሚያስ ሙላ እና ድምፃዊት እርገት ሰለሞን ጥምረት … ተወዳጁ ድምፃዊ በራሱ ማህበራዊ ገፅ እንዲህ ሲል ገልጿል "እንዴት አላችሁ ውድ የሙዚቃ አድማጮች ? የፊታችን አርብ ሰኔ 7/2016ዓ.ም "እስከ ወዲያኛው " የተሰኘ የሙዚቃ ቪድዮ ሰርቼ ለናንተ ለውድ አድማጮቼ አደርሳለሁ ። በኤርምያስ ሞላ እና የኢትዮጵያን አይዶል top 5 ተወዳዳሪ በነበረችው በእርገት ሰለሞን(ናኒ) በቅብብል የተሰራ ሲሆን እንደተለመደው ከጀርባ በርካታ ሰዎች ተሳትፈውበታል ። የሙዚቃ ቪድዮን በኤርምያስ ሞላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ እየገባችሁ አድምጡልኝ ። የተሰማችሁን አስተያየት ፃፉልኝ ። ቻናሉን ሰብስክራይብ አድርጉልኝ አመሰግናለሁ" ኤርምያስ ሞላ @yenevibe @biggrs
Show all...
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ፣ ክስተታዊ ጉዳዮች እና በሳምንቱ የተመረጠ እንድታዳምጡ ያዘጋጀነው አለ፡፡ -ሜላት ቀለምወርቅ-"ዋይ'' የተሰኘ ሙዚቃ በቅርቡ ይዛ ስትመጣ በግጥም እና በዜማ ወጣቱ ምረትአብ ደስታ ሲሰራው በቅንብር ሚክስ እና ማስተሪንግ በተጨማሪም ሙዚቃውን ዳይሬክት በማድረግ ሄኖክ ድለቃ ሰርተውታል በቅርቡ ለአድማጭ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ -ሻንበል በላይነህ- ''አይዞሽ አዲስ አበባ'' የተሰኘ የሙዚቃ ስራ ሲሆን ለአድማጮች ጆሮ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ በተጨማሪም ድምፃዊ ሻንበል በላይነህ ሐሙስ ምሽት በራሱ ዩትዮብ ቻናል እንደ ሚለቅ አሳውቋል፡፡ -ቫኑስ ዘይዳ-''ንጉሱ ደገሰ'' የተሰኘ ሙዚቃ ለ አድማጭ አደርሳለሁ ባለው መሰረት ለቆታል አድማስ ኢንተርቴመንት ገብታችሁ ሙዚቃውን ተመልከቱ፡፡ - ተወዳጅዋ ድምፃዊት እየሩስአሌም አስፋው ጄሪ አዲስ ነገር ይዛ እየመጣች ትገኛለች ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ''tik Tok'' በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በጎ ዓላማ ይዛ መታለች የድምፅ ተስዖጦ ያላቸውን ሰዎች ወደ ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራች ትገኛለች፡፡ እናንተም በtik Tok ሶሻል ሚዲያ እየሩስአሌም አስፋው ብላችሁ ተስዖጦአችሁን አሳዩ ፡፡ -ሮፍናን ኑሪ ጉዞውን ወደ አማሪካ 'አትላንታ" ዲጄ ፣ የዜማ የግጥም ደራሲ ፣ የድምፅ ኦድዮ ኢንጅነር  እንዲሁም ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ ከምነው ሸዋ ኢንተርቴመንት  ጋር አንድ ላይ በመሆን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው፡፡ሮፍናን ኑሪ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉለት አልበሞች  የመጀመርያ አልበሙ ነፀብራቅ በኤክትሮኒስ ዳንስ ሚውዚክ በመጠቀም አድርሶን ነበር፡፡ በመቀጠል  ሶስት እና ስድስት ከዛም ባለፈ ዘጠኝ አልበምን ሙዚቃዎችን ወደ አድማጭ አድርሷል፡፡ - ፕርስቲጅ አዲስ ፤ ዛሬም እጅግ ተወዳጅ እና ወጣቱ ሙዚቀኛ የሆነውን  ወጣት ድምፃዊ ዳዊት ፅጌን  ጋብዟል ቀርቧል:: ዳዊት የሥራ እና የህይወት ተሞክሮውን የሚያካፍልበት ሲሆን ከወዳጅ እና ድናቂዎቹ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎችም የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ  4 ,2016 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀቧል። በዕለቱ የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃ-ግብር ተከናውኗል:: * በዚህ ሳምንት ሙዚቃዊ ክስተት ከተነሱት ውስጥ… - የአዲስ አበባ ባህል ፣ኪነ ጥበባት ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል፡፡ዘጠኑ ጋርዱላ ዞን ጋር በመተባበር የደራሼን ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህል እና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙርያ ቦታው ድረስ በመገኘት ጥናት አድርገዋል፡፡ ፊላ ማለት የትንፋሽ የሙዚቃ መሳርያ ሲሆን "ፊላ''ጨዋታ በደራሼ ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ - ታዋቂው አለም አቀፉ ድምፃዊ ዘ-ዊኬንድ( አቤል ተስፋዬ) ስፖቲፋይ  ባስቀመጠው የሙዚቃ ምርጫዎቹ የአንጋፋው አቀናባሪ  የኤሊያስ መልካ ቅንብር  እንደቃል ፣ ነቅቻለሁ አንዲሁም የፍቅር አዲስ "ልዑል ያስወደደኝ" ሙዚቃዎች እና ሌሎች በርካታ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን እንዳካተተ በዚህ ሳምንት የሰማነው ክስተት ነው፡፡ - የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ልዑል አልበም ኮንሰርት የተደረገበት ነበር አጅበውት ኮንሰርቱን የተሳተፉት ሳሚ ዳን እና ሚካኤል በላይነህ ስራዎቻቸውን ከቶራ ባንድ ጋር አቅርበዋል፡፡ -በፕ/ር አሸናፊ ከበደ የተሰየመው በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሰኔ 1/2016 በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ የተከፈተበት ሳምንት ነበር፡፡ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን በህዝብ ዘንድ የሚታወቁበት አንዱ 'እረኛው ባለ ዋሽንት'' በተሰኘው ሙዚቃ ነበር፡፡ * በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ የሙዚቃ አልበም ፡፡ - የድምፃዊ ሳሙኤል ተፈሪ(ሳሞን) ለውጥ የተሰኘ አልበሙ ነው በውስጡ ወደ 15 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲሆሩ ወደ አንቺ ስመጣ ፣ትዝታ ፣ ቻው፣ የምኞት አባት ፣ የመጨረሻ ቀን የመሳሰሉት አሉበት፡፡ በግጥም በዜማ በራሱ ሳሙኤል ተፈሪ (ሳሞን ) የተሰራ ሲሆን በቅንብር ቅዱስ ሐብተስላሴ ፣ ኪሩቤል ባጫ ፣ ዳግማዊ ሀብተስላሴ ፣ በድል አብ ብርሀኑ ፣ እዮብ ወርቁ ተሳትፈዋል በማስተሪንጉ ዜማስ ስቱዲዮ ሰርቶታል ፡፡ Yenevibe.com  ገብታችሁ ጎብኙን እናመሰግናለን፡፡
Show all...
👍 3