cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰሌዳ | Seleda

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! @seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Show more
Advertising posts
50 256Subscribers
+2124 hours
-317 days
+15330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በመላው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ  መሆኑም ተመላክቷል፡፡ እስከዛ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ  ተቋሙ ጠይቋል፡፡
Show all...
👎 23👏 5😁 4👍 2
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። ኮሚሽኑ በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል። በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል። በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጫችን መዘገቡ ይታወሳል ። ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
Show all...
👍 23👏 3 2
ተፈታለች ማለቴ ተፈቷል😎 በሁለት ቦታዎች ስሙን ና ማንነቱን ቀይሮ ሴት መስሎ ተይዞ የነበረው ቢኒያም ዛሬ ተፈቷል። ከዛሬ 6 ወር በፊት በጋምቤላ ሴት መስሎ ተቀጥሮ 2 ቀን ስራ እየሰራ እንዳለ በሰራተኞቹ ጥቆማ የተያዘው ተይዞ ነበር። ከዚያ ሲወጣ ደግሞ ከቀናት በፊት በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ  ሴት ነኝ ብሎ ህብረተሰቡን ሲያታልል ለ2ኛ ጊዜ ተይዞ ነበር:: ዊጉን ሲያወልቅ ያለው ገፅታ በፎቶ ተያይዟል። wasumohammed
Show all...
😁 26🤬 5👍 3🤔 1😢 1
ህጋዊ የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ስራቸው በመቋረጡ የተነሳ ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ መክፈል ሊያቆሙ መሆኑን አስታወቁ የቫሞስ እና የሀበሻ የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እንዳስታወቁት ከታህሳስ ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ግብረ ሐይል በማቋቋም እንዲዘጋ መደረጉን ተናግረዋል፡፡የቫሞስ ኢንተርቴይመንት ስራ አስኪያጅ አቶ የኔብልህ ባንታየው እና የሀበሻ ስፖርት ውርርድ ስራ አስኪያጅ አቶ መርሻ ቡዛየሁ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከ5 ዓመት በፊት በብሄራዊ ሎተሪ ፍቃድ የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በሀገር ውስጥ 156 እና 166 ቅርንጫፎች እንዳሏቸው እና ከ1ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችም የስራ እድል የፈጠረ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡የሀበሻ ስፖርት ውርርድ ስራ አስኪያጅ አቶ መርሻ ቡዛየው ከታህሳስ ወር ጀምሮ ድርጅቶቹ መዘጋታቸውን እና ያለምንም ስራ ለሰራተኞቻቸው እንዲሁም ለቤት ኪራይ እየከፈሉ እንደቆዩም ገልፀዋል፡፡ የስፖርት ውርርድ ተቋማቱ በብሄራዊ ሎተሪ መመሪያ መሰረት ከ21 ዓመት በታች እና ተማሪዎች እንዳይገቡ የሚለውን መመሪያ መፈፀማቸውን እና ለዚህም ብለው ከ340 በላይ የጥበቃ ሰራተኞች ቀጥረው እንዳይገቡ ይከለክሉ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ የቫሞስ ኢንተርቴይመንት ስራ አስኪያጅ አቶ የኔብልህ ባንታየሁ አክለውም በስፖርት ውድድር ዘርፍ ውስጥ 8 መቶ ድርጅቶች ህጋዊ መሆናቸው ተነግሮናል፤ ሌሎቹ 3ሺ የሚሆኑት ግን በህገወጥ ስራ የተሰማሩ መሆናቸው ከተለየ የህጋዊነት አግባብ ያለን ድርጅቶች ወደ ስራችን እንድንመለስ መልስ ይሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል፡ መልስ በመጠበቅ አራት ወራት እንደቆዩ ለሰራተኞቻቸው ሲከፍሉት የነበረውን ወርሀዊ ደሞዝ ከዚህ በላይ መክፈል የማይችሉበት ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አቶ የኔብልህ ባንታየሁ እና አቶ መርሻ ብዙአየሁ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።በቅሬታ አቅራቢዎቹ ዘንድ ህጋዊ የስፖርት ቤቶች ይከፈትልን የሚሉ አቤታታዎች ቢኖሩም ዘርፉ መዝጋቱ የሚደግፉና ቁጥጥሩ የላላ በመሆኑ ታዳጊዎች ላልተገባ ሱሱ ተዳርገዋል ሲሉ የሚደመጡም አሉ። ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 17👎 4
ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ በኦንላይን ተመዝግበው ባሉበት እንዲመጣላቸው የሚያስችል አገልግሎት ተጀመረ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን በኦንላይን ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ካሉበት ሆነው በማዘዝ ባሉበት የማድረስ ሥራ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ የሕትመት ሥራ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ሲከናወን የቆየ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎችም አገልግሎቱን ለማግኘት በአካል መገኘት ይኖርባቸው ነበር። አሁን ግን ዜጎች አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የኦንላይን ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብር እና በባንክ መክፈል እንደሚቻል ተጠቁሟል። የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች card-order.fayda.et ድረ ገጽ ላይ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ሲገለፅ ፥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ባሉበት ቦታ እንዲመጣላቸው ማዘዝ ይችላሉ ተብሏል። ዜጎች ምዝገባ ከማድረጋቸው በፊት የፋይዳ ቁጥራቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ መልዕክት በስልካቸው ስለመላኩ ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸውም ነው የተገለፀው።
Show all...
👍 17👎 4😁 2
18 እግረኞች ተቀጡ! ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ 18 እግረኞች መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሳወቀ። መገናኛ ሾላ አካባቢ በተደረገ ቁጥጥር 10 እግረኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ያቋረጡ በደንብ ቁጥር 395/2009 መሠረት 40 ብር ሲቀጡ 8 እግረኞች ገንዘብ ባለመክፈላቸው ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ቀደም ሲል አደባባይ የሚያቋርጡ፣ ዜብራ ጠብቀው የማይሻገሩ እንዲሁም የትራፊክ መብራት ለማያከብሩ እግረኞች ግንዛቤ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
Show all...
👍 30😁 26👎 10 2
ቻይናዊው ወጣት በኪሩቤል ግርማ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ሰበረ ቻይናዊው ወጣት ውሃን ከአፍ ለረጅም ጊዜ በማንቆርቆር/መርጨት ተግባር በኪሩቤል ግርማ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊ ልዩነት ሰብሮታል። ኪሩቤል ግርማ ውሃን ለ56 ሰከንድ ከ36 ማክሮ ሰከንድ ያክል ከአፉ በመርጨት ነበር በዓለም የጊነስ ቡክ መዝገብ ላይ ስሙ የሰፈረው። የ35 ዓመቱ ቻይናዊ ማ ሁዊ ለ5 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ ከ88 ማይክሮ ሰከንድ ያህል ያለማቋረጥ ውሃ ከአፉ በመርጨት ተዓምር አስብሏል። የማ ሁዊ ድርጊት በሰው ልጅ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው አስብሎታል። ውሃን ለረጅም ጊዜ በአፍ የመርጨት ተግባር ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ጥበብ ሲሆን በብዛት የተጠጣን ውሃ በአፍ በኩል መልሶ በማውጣት ወደ ውጭ የመርጨት ስልት ነው። ድርጊቱን በማንኛውም ሰው ሊከወን የማይቻል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከፍተኛ የጡንቻ ቁጥጥርና ምጠና ክህሎት እንደሚያስፈልገው ባለሙያዎች ይናገራሉ። ቻይናዊው ወጣት ይህን ክብረ ወሰን ለመስበር 4 ሊትር ተኩል ውሃ መጠጣቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል። (አዲስ ዋልታ)
Show all...
👍 15🤔 8😁 4 1🔥 1🥰 1
የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ ጠባቂዎች ላልተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ ተብላችኋል ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ በተለቀቀ የተሳሳተ መረጃ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ዳጉ ጆርናል ከአዲስአበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰምቷል። በዛሬዉ እለትም ይህን መረጃ የሰሙ በርካታ ሰዎች ወደ ባንቢስ አቅንተዉ ወረፋ መያዛቸዉን ዳጉ ሰምቷል። የአዲስአበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰዎች ላተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ ሲል አሳስቧል፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ኮርፖሬሽኑ ነዋሪውን በተለይም ተመዝግቦ የሚጠባበቀውን የቤት ባለቤት ለማድረግ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ከምንጊዜውም  በተሻለ መልኩ እየሰሩ እንደሚገኝ የገለጸም ሲሆን ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ አስገንዝቧል። ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 21👎 3🥰 1
ይህንን እንኳን ልታስተባብል አትችልም 😤 የኢምሬትስ አዉሮፕላን በሞስኮ አዉሮፕላን ማረፊያ ጉዳት ደረሰበት ተባለ ንብረትነቱ የኢምሬትስ የሆነዉ ሱፐር ጃምቦ 360 የተሰኝ አዉሮፕላን በሞስኮ ዴሞዴዶቮ አዉሮፕላን ማረፊያ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል፡፡ አዉሮፕላኑ ጉዳት የደረሰበት ለመነሳት በሚዘጋጅበት ወቅት በተሽከርካሪ ተገጭቶ እንደሆነ ታወቋል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የ ኢኬ134 በረራ መሰረዙን አየር መንገጉ አስታዉቋል፡፡ በግጭቱ በመንገደኞች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም፡፡ የኢምሬትስ አየር መንገድ ከዩክሬን ጦርነት በኋላ በርካታ በረራዎችን ወደ ሞስኮ በማድረግ የሁለቱ ሀገራት ግንኑነት እንዲጠናከር ስለማድረጉ ይነገራል፡፡ ethiofm
Show all...
😁 14👍 3🤔 1
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!