cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሰሌዳ | Seleda

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! @seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

إظهار المزيد
Advertising posts
50 519المشتركون
-1024 hour
-297 يوم
+26430 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች🫢 ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ፈጃል ተብሏልሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ተቋም ይህን ግዙፍ አውሮፕላን ለመስራት ተስማምቷል አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች፡፡ የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ እንደ ኑክሌር አይነት ጦርነት ቢነሳ ከአደጋ መጠበቅ የሚቻልበት አውሮፕላን እንዲሰራ ማዘዟ ተገልጿል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ አሜሪካ በ1970ዎቹ የተሰራ የክፉ ቀን መጠለያ አውሮፕላን የሰራች ሲሆን ይህ አውሮፕላን አርጅቷል በሚል አዲስ ልዩ አውሮፕላን እንዲሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለክፉ ቀን ማምለጫ ይሆናል የተባለው ይህ አውሮፕላንም 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይፈጃል የተባለ ሲሆን ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ኩባንያ አዲሱን አውሮፕላን እንደሚሰራው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ኢ-4ቢ የተሰኘ ስያሜ ያለው ይህ አዲስ አውሮፕላን አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2036 ላይ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ አየር ሀይል ንብረት የሆነው ይህ ልዩ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ይዟል ተብሏል፡፡ እንዲሁም አውሮፕላኑ እንደ ኑክሌር ጦርነት፣ አውዳሚ አደጋዎች እና ሌሎች አስጊ ክስተቶች ቢከሰቱ መሪዎች በዚህ አውሮፕላን ላይ በመሆን ትዕዛዝ እና ውሳኔዎችን እንዲያካሂዱ ያገለግላልም ተብሏል፡፡ የመሰብሰቢያ ቢሮዎች፣ የነዳጅ መሙያዎች እና የተግባቦት መሳሪያዎችም ያሉት ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለው የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን ከ2030 በኋላ ከአገልግሎት ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡(Alain)
إظهار الكل...
ታንዛኒያ‼ ታንዛኒያ ውስጥ በከባድ ዝናብ የ115 ሰዎች ሲሞቱ፣ 200ሺሕ የሚሆነት ደግሞ ገፈት ቀማሽ ሆኑ። በድንገተኛው ከባድ ዝናብ 115 ሰዎች ሲምቱ፣ 236 ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ 200 ሺሕ ሰዎች ደግሞ የአደጋው ገፈት ቀማሽ እንደሆኑ ተነግሯል። ዝናቡ ጎርፍ  እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ማስከተሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማጃሊዋ ተናግረዋል። ታንዛኒያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የጎርፍ ጉዳት እየገጠማቸው እንደሚገኝ ቻነልስ ቲቪን ጠቅሶ thiqaheth አስነብቧል።
إظهار الكل...
😢 15👍 3
ሆሳዕና በአርያም 🌴 እንኳን አደረሳችሁ የ “ሆሳዕና በአርያም” በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ ሆሳዕና በአርያም ከፋሲካ በፊት ያለው እና የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሣምንት ሲሆን÷ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው” የሚሉ ትርጉሞችም እንዳሉት የዕምነቶቹ አባቶች ያስተምራሉ። የዕምነቶቹ ተከታዮች በሆሳዕና በአርያም በዓል መሪው ተመሪውን ዝቅ ማለትን ያስተማረበት እና ተመሪውም የሚመራውን ጨርቁን እያነጠፈ እና ዘንባባ እየጎዘጎዘ ያከበረበት የትህትና እና የፍቅር በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ ሆሳዕና በአርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም÷ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡
إظهار الكل...
🔴 የውጪ ባለሃብቶች በተከለሉ የወጪ፣ የገቢ፣  የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ኢንቨስትመንቶች የሚሳተፉባቸው ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው? ከላይ የተያያዘውን መረጃ ይመልከቱ👆
إظهار الكل...
👍 10🤔 1
«ምንም አታመጡም አይነት አካሄድ ከፍላችሁ የማትጨርሱት እዳ ውስጥ ይዞችሁ ይገባል» ስትል አርቲስት ቤዛዊት መስፍን አስጠነቀቀች "እስር ቤት ለሴት ልጅ እጅግ ከባድ ነው" በማለት አስተያየቷን የጀመረችው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን ተዋናይት አዲስአለም ጌታነህ ጨምሮ ሌሎች ጎደኞቼ በገዛ ፍቃዳቸው እና ገንዘባቸው በየ ክፍለሀገሩ በመሄድ ወግ እና ልማዳቸውን ባህላቸውን የሚያስተዋውቁ ምንም ውስጥ የሌሉ ሴቶች ናቸው፣ ከዛሬ ነገ ይፈታሉ ብለን ብናስብም ይሄው እስከዛሬ አልተፈቱም እና እባካችሁ ሰው በሀገሩ በነፃነት እንዲኖር ፍቀዱለት በገዛ ሀገራችን እና ርስታችን አታሸማቁን በሀገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ እንድንሰደድ አታድርጉን! ፍቱልን እህቶቻችን ሰትል አርቲስት ጓደኞቿ እንዲፈቱ በማህበራዊ ገጿ ላይ ያሰፈረችውን ፅሁፍ ፋስት መረጃ ተመልክቷል። እስከ ዛሬ በእህቶቼ ዙሪያ ምንም ያላልኩት ነገሮች እንዳይካበድባቸው በማሰብ ነው በማለት ዝምታዋን መስበሯን ገልጻለች። «ህዝቡን ብታከብሩት እና ብትፈሩት ይሻላል ይሄ ምንም አታመጡም አይነት አካሄድ ከፍላችሁ የማትጨርሱት እዳ ውስጥ ይዞችሁ ይገባል» ስትል ቤዛዊት መስፍን ከዱባይ አስጠንቅቃለች። fastmereja
إظهار الكل...
👍 75😁 22👎 10 10👏 2
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።
إظهار الكل...
👍 10😁 5
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በአገሪቱ የሚዘረጋቸውን የቴሌኮም ታዎሩች ብዛት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በሦስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዱን እንደገለጠ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ኩባንያው ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 2 ሺህ 500 የቴሌኮም ታዎሮች ያሉት ሲኾን፣ 1 ሺህ 500ዎቹ ታዎሮች ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የተከራያቸው ናቸው። ኾኖም መላ አገሪቱን ለመሸፈን 7 ሺህ ታዎሮች እንደሚያስፈልጉት የኩባንያው ሃላፊዎች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ዘገባው፣ በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ግን በኩባንያው እቅዶች ላይ ትልቅ እንቅፋት ደቅነውብኛል ማለቱንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።
إظهار الكل...
👍 26 2
" ኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ይሻል። መፍትሄ እንሻለን " - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ከኑሮ ውድነቱ አንፃር የዘገየው የሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እና የግብር ቅነሳ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ገልፀዋል። " አሁንም በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በልቶ ለመዋል የሚቸገር ሰራተኛ ነው ያለው " ያሉት አቶ ካሳሁን ሰራተኛው ካለው ገቢ አንፃር ችግሩ የሰፋ እንደሆነ አስረድተዋል። እነዚህ ጥያቄዎች በአዎንታዊ መልኩ መታየት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አቶ ካሳሁን " ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል በሚመለከት ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የሚወስን ቦርድ የሚቋቋምበት ደምብ ላይ ጥናት ማድረጋቸውን በቅርቡ አሳውቀውናል " ሲሉ ተናግረዋል። የኑሮ ውድነት በጣም አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ሰራተኛው ችግር ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ " ትክክለኛ ግብር ከፋይ ሰራተኛው ነው። ለመንግስት ቀኝ እጁ በሚከፍለው ግብር ሰራተኛው ነው። የግብር ቅነሳው አንድ እና ሁለት የለውም ዘግይቷል " ሲሉ ጠቁመዋል። አቶ ካሳሁን ፤ ሚያዚያ 23 ቀን በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በሚከበረው ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን (ሜይዴይ) አዳራሽ ውስጥ እንደሚከበር አሳውቀዋል። " አሁንም ቢሆን ባልተመለሱልን ጉዳዮች ላይ ነው የምንወያየው። የቀኑ መሪ ቃል ' ለሰላም እና ለኑሮ ውድነት መፍትሄ እንሻለን ' የሚል ነው ብለዋል። " የሰላም ችግር አለ። ሰራተኞች በአንዳንድ ቦታዎች ይታገታሉ ፣ ይሞታሉ " ያሉት አቶ ካሳሁን ፎሎ ፤ " ይሄ እስከ መቼ ይቀጥላል ? ማንኛውም ማህበረሰብ ላይ እንደሚደርሰው ጉዳት ሁሉ ሰራተኛውም ላይ እየደረሰ ነው ፤ ስለዚህ ለሰላም መፍትሄ መምጣት አለበት " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
إظهار الكل...
👍 52 4😢 4👏 2🔥 1
ሶል በዳይመንድ ሊግ 5ሺ ሜትር አንደኛ በመውጣት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። welcome back sol🥰
إظهار الكل...
👍 24 2👎 1🥰 1
ሊቨርፑል ያከተመለት ይመስላል🥺 35ኛ ሳምንት የእንግሊዘ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ                       ⏰ ተጠናቀቀ    ዌስትሃም ዩናይትድ 2-2 ሊቨርፑል      #ቦውን 43'           #ሮቦርትሰን 48'       #አንቶኒዮ 77'       #አርዮላ (OG) 65' 🏟 ለንደን ስታድየም
إظهار الكل...
😢 11😁 7👍 6👏 1🤬 1