cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞ @orthodox1 ሁሉም እንዲያነበው share ያርጉ ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @drshaye ማናገር ይችላሉ 🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹 Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝ @orthodox1

Show more
Advertising posts
38 052Subscribers
-2324 hours
-1247 days
-45130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ፈራሁ ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣሁ ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራሁ በደሌን ሳትመዝን ግቢ ብትለኝም ኃጢያቴ ከበደኝ አላራመደኝም የሰው ዕድሜው እኮ አጭር ነው ጥቂት ነው እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው? ጉብዝናዬን ዓለም ስቃ ተጫውታበት እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍረት? ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ? እኔ ፈራሁ እንጂ አንተ እኮ አታስፈራም መምጣቴ ነው ደስታህ ፍቅርህ አይታማም ሽምቅቅ አለች ነፍሴ መስቀልህን ሳየው በደሌን አሰብኩት ደምህን እያየሁ ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ? በንጽህናህ ፊት እንዴት እቆማለሁ እንደ መላዕክቱ በምን እጋረዳለሁ ራሴን መሸፈኛ ክንፍ የለኝም እኔ ይታያል ኃጢያቴ የበደል ዕርቃኔ ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ? ጠዋት እና ማታ ለመጣው አንድ ነህ አምሽቶ ለገባም እኩል ትከፍላለህ አብርሃም ወይስሐቅ በድንኳንህ ቢያድሩም በአንተ መንግሥት ግን ከወንበዴ አይቀድሙም ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ? https://youtu.be/yZRhhLT74rY?si=TplnxdckbmIF7GG2
Show all...
ፈራሁ | Ferahu | ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው | Bezawork Asfaw | አዲስ መዝሙር New Orthodox Mezmur | 2024

"ፈራሁ | Ferahu | ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው | Bezawork Asfaw | አዲስ መዝሙር New Orthodox Mezmur | 2024 is licensed under a Creative Commons Attribution Share Alike 4.0 International License. Based on a work at

https://www.youtube.com/watch?v=KdOwdsGMAfE."

Ethiopian Orthodox Tewahedo Song " ፈራሁ | Ferahu | ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው | Bezawork Asfaw | አዲስ መዝሙር New Orthodox Mezmur | 2024 " New Ethiopian Orthodox Tewahedo Mezmur 2023 © Wreb Tube is the only Channel that has exclusive rights for all Lyrics produced by Zemarit Bezawork Asfaw #ይህ_ቪዲዮ_በFacebook_ኮፒ_ራይት_የተመዘገበ_ስለሆነ_አካውንትዎ_እንዳይዘጋ_በFacebook_አይልቀቁት:: " ፈራሁ | Ferahu | ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው | Bezawork Asfaw | አዲስ መዝሙር New Orthodox Mezmur | 2024 " New Ethiopian Orthodox Tewahedo Mezmur 2023

👍 21
╔​✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╗ ❀.  #የማያሳፍር_ራቁትነት . ╚✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╝          ትናንት ሚያዝያ ፬ የመፈጠራቸው ነገ ሚያዝያ ፭ ደግሞ የዕረፍታቸውን መታሰቢያ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የምትዘክርላቸው አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በረከታቸው ይደርብርብን። ★ "ሀለዉ አዳም ወብእሲቱ (ሔዋን) እራቃኒሆሙ ወኢይትኃፈሩ ☞ አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።"  【ዘፍ ፪ ፥ ፳፭】 ሁለት ዐይነት እርቃን አለ  የሚያሳፍር እና የማያሳፍር  የማያሳፍረው ራቁትነት ደግሞ የተፈቀደ እና ያለተፈቀደ ሊሆን ይችላል ዛሬ ላይ ትውልዱ ባልተፈቀደ መንገድ መራቆቱን ሳያፍርበት እንደፋሽንም እንደ ክብርም ይቆጥረዋል በቀደመው ታሪክ የቃየል ልጆች ባልተፈቀደ መራቆት አምላካቸውን ሲያሳዝኑ እንደታዩ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ገልጧል "ርእዩ አዋልዲሁ ለቃየል በዘይሴኒ ሥነ ራእይ እንዘ የሐውራ ዕራቆን ዘእንበለ ሐፍረት  ☞ የቃየን ሴቶች ልጆች ተውበው እርቃናቸውን በመሆን ሳያፍሩ ሲንቀሳቀሱ እዩዋቸው" 【ቀሌ. ፫፥፵፱】 ታዲያ እንዲህ ባለው መንገድ ነውርን እንደ ክብር መራቆትንም  እንደ መሰልጠን ገላ መግለጥ  እንደፋሽን እያዩ የሚኖሩ መጨረሻቸው ኩነኔ እንደሆነ መጽሐፋችን ይመሰክራል  “መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” 【ፊል ፫፥፲፱ 】        ለሰው ልጅ አካሉን ገልጦና ሰውነቱን አራቁቶ ለመታየት የታወቀ (በቂ) ምክንያት ያስፈልጋል፤ ሠለስቱ ምዕት ለመታከም «የሚተኮስ» «የሚታገም» አካል ቢኖር አልያም ከጸበል ሊነከሩና ሊታጠቡ እንጂ በሌላውስ መንገድ በማንም ፊት እርቃን መታየት ክልክል ነው ብለዋል። "ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ።  ☞ ዳግመኛም በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ፤ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ" 【 ሃይ አበው ፳፥፲፪ 】 መራቆት አለመዘጋጀት እፍረት ማሳየት የመዘናጋት በበጎ ምግባር ሳይተጉ የመኖር መገለጫ ነው።   “እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” 【ራእ  ፲፮፥፲፭】         አካልን ራቁቶ  መታየት ቀርቶ  የተራቆተ አካልም ማየት ራሱ   ሲያስነቅፍ ፣ ሲያስቀጣና ሲያስረግም እናያለን በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ ፱ እንደተገለጸው  በኖኅ ልጅ በካም  ላይ የደረሰው የዚህ ማሳያ ነው " ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። " 【ዘፍ ፱፥ ፳ - ፳፯】 እንግዲህ የተራቆተን ማየት በዚህ መጠን የሚያስነቅፍ ከሆነ ተራቁቶ የመታየት ቅጣቱ የከፋ ስለመሆኑ አያጠራጥርም መራቆት የዲያቢሎስ የክብር ልጅ መሆን ነውና ፤ ሰይጣን ማለት በትርጉሙ እሩቅ እም ስብሐተ እግዚአብሔር  【ከእግዚአብሔር ክብር የተራቆተ】ማለት ነውና። የተፈቀደ የማያሳፍርም  ዕርቃን የተባለውና በጥንተ ተፈጥሮ በአዳምና በሴቲቱ ኑሮ የተገለጠው የትኛው ራቁትነት ነው? ① ራቁትነታቸው ከዚህ ዓለም ልብስ ነው አለማፈራቸው ብርሃን ለብሰው ስለነበር ነው ዓለማችን የሚያለብሰን ምድራዊና ቁሳዊ ጊዜአዊና ኃላፊ ትጥቅ ነው መንፈሳዊ ትጥቃችን  ግን ኅልፈትና ውላጤ ከሌለው ሰማያዊ  አባታችን የምንቀበለው ነውና  “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።”  【ኤፌ ፮፥፲፩】 “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤ … በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ” 【ቆላ ፫፥፲፪- ፲፬】 የዓለሙ ልብስ ንፍገት ጭካኔ ቅሚያ ትዕቢት ብልጣብልጥነት ችኩልነትና ጸብእን ነው። ይህን ለብሰው የሚዋጉንን  ሥጋውያኑን በሥጋ ጦር ድል መንሳት እንዴት ይቻለናል?  የሳውልን የጦር ዕቃ የታጠቀ ካባ የለበሰና በአመጽ ወደተመላው እግዚአብሔርን ወደተገዳደረው ጎልያድ  በሥጋዊ መሳርያ ውጣ የተባለው  ብላቴናው ዳዊት መታመኛ ትምክህቱ መከታ ጉልበቱ እግዚአብሔር ስለበር በበትርና በኮሮጆው ጠጠር ዘምቶ  አመጸኛውን ሰልፈኛ ሰው ድል ነስቶታል።  “ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ።” 【፩ኛ ሳሙ. ፲፯፥ ፴፱】 ② አእምሮ ጠባያቸው ያላደፈ በተፈጥሮ እንደ ሕፃን  ስለነበሩ በዕርቃናቸው አይተፋፈሩም ሕጻናት በንጽሕና እንደ መላእክቱ ናቸው የእነርሱ አእምሮ ጠባይ ማደፍ ስላላገኘው ሊቁም «ንጽሖሙ ለሕፃናት በሥጋሆሙ ወነፍሶሙኒ ዘእንበለ ሕማም» ይላል። በዘመነ ሥጋዌው ክርስቶስ አምላካችንም እንደ ሕፃናት መሆን ለክብረ መንግሥቱ እንደሚያበቃ ነግሮናል “ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” 【ማቴ ፲፰፥፫】 መልሶም እንደነርሱ ላሉቱ ስለምትሠጥነና እነርሱኑ ለመሰሉት ስለምትገባዋ ዘልዓለማዊ ርስት ይህን ደግሟል “ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤”   【ማቴ ፲፱፥፲፬】  ያለቂም ያለበቀል የሚኖሩ ክፋትንና ተንኮልን አልመው አስበው ሌላው ይጎዳበት ብለው የማይፈጽሙ እንደወረቀት የሠጧቸውን የሚቀበሉ እንደውኃም ቅርጻቸው ያረፉበትን ሥፍራ የሚመስሉ ልጆች ሕጻናትን መስሎ መኖር የሚማሩትን መያዝ በበጎ አርያነት የሚመሩትን መምሰል በእጅጉ ይገባል ፤ “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”【፩ኛ ጴጥ ፪፥፪-፫】 እንዲህ ያለው የሕጻናት ንጹሕ አይምሮ መያዝ አያሳፍርም። ③ ከልብሰ ኃጢዓት  ተራቁተው ኃፍረተ ነፍስ ሳይኖርባቸው ይኖሩ ነበር ሰው ኃጢዓትን ለብሶ በደል ደርቦ ከመኖር በንሰሐ ቢራቆት ተኮንና የምታፍር ነፍስ የለችውም፤  ይልቁንም የልብ ንጽሕና ማጣት የሕሊና ሞት እንደሚያመጣበት አውቆ በኃጢዓቱ ምክንያት ያገኘውን ቁስለት የልቡናው ሰንኮፍ በንሰሐ ከከከበረች ነፍሱ ቢያርቅ መንገዱን በጥንቃቄ ቢመራና በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ለአምላኩ ቢገዛ በግራ ከሚቆምና ተኮንነው ከሚያፍሩ በመለየት መክበር ይቻለዋል። “እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፥ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፥ ተንቀጥቀጡ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።”   【ኢሳ ፴፪፥፲፩】
Show all...
ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ የማያሳፍር ዕራቁትነት ዘፍ 2፥25

✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን:: ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ / @mahiberetsion እግዚአብሔር ያክብርልን

👍 4 2🙏 1
ሸክም የሆነብንን ኃጢዓት አራግፈንና በደላችንን ከላያችን በማስወገድ ራስን አንጽቶ  ልብን አቅንቶ  ሕይወትን መምራት በዙፋኑ ቀኝ ሳያፍሩ ወደመክበር  ያደርሳል። “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”【ዕብ ፲፪፥፩-፪】 በማያሳፍር ራቁትነት በፊቱ ለመክበር ያብቃን የአቡነ አዳም የእነ ሔዋን በረከታቸው በሁላችን ይደር! ትምህርቱን  ከታች ባለው "ሊንክ በድምጽ ማግኘት ይችላሉ    https://youtu.be/s0ipUnYfRkA?si=pDknHqI_wLvUBx_P
Show all...
ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ የማያሳፍር ዕራቁትነት ዘፍ 2፥25

✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን:: ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ / @mahiberetsion እግዚአብሔር ያክብርልን

👍 2 1
“እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፥ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፥ ተንቀጥቀጡ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።”   【ኢሳ ፴፪፥፲፩】 ሸክም የሆነብንን ኃጢዓት አራግፈንና በደላችንን ከላያችን በማስወገድ ራስን አንጽቶ  ልብን አቅንቶ  ሕይወትን መምራት በዙፋኑ ቀኝ ሳያፍሩ ወደመክበር  ያደርሳል። “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”【ዕብ ፲፪፥፩-፪】 በማያሳፍር ራቁትነት በፊቱ ለመክበር ያብቃን የአቡነ አዳም የእነ ሔዋን በረከታቸው በሁላችን ይደር! ትምህርቱን  ከታች ባለው "ሊንክ በድምጽ ማግኘት ይችላሉ    https://youtu.be/s0ipUnYfRkA?si=pDknHqI_wLvUBx_P
Show all...
ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ የማያሳፍር ዕራቁትነት ዘፍ 2፥25

✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን:: ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ / @mahiberetsion እግዚአብሔር ያክብርልን

𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Θεόδωρος (תאודור )(تواضروس) Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος): ╔​✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╗ ❀.  #የማያሳፍር_ራቁትነት . ╚✞═•┉✽✥⛪✥✽┉•═✞╝          ትናንት ሚያዝያ ፬ የመፈጠራቸው ነገ ሚያዝያ ፭ ደግሞ የዕረፍታቸውን መታሰቢያ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የምትዘክርላቸው አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በረከታቸው ይደርብርብን። ★ "ሀለዉ አዳም ወብእሲቱ (ሔዋን) እራቃኒሆሙ ወኢይትኃፈሩ ☞ አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።"  【ዘፍ ፪ ፥ ፳፭】 ሁለት ዐይነት እርቃን አለ  የሚያሳፍር እና የማያሳፍር  የማያሳፍረው ራቁትነት ደግሞ የተፈቀደ እና ያለተፈቀደ ሊሆን ይችላል ዛሬ ላይ ትውልዱ ባልተፈቀደ መንገድ መራቆቱን ሳያፍርበት እንደፋሽንም እንደ ክብርም ይቆጥረዋል በቀደመው ታሪክ የቃየል ልጆች ባልተፈቀደ መራቆት አምላካቸውን ሲያሳዝኑ እንደታዩ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ገልጧል "ርእዩ አዋልዲሁ ለቃየል በዘይሴኒ ሥነ ራእይ እንዘ የሐውራ ዕራቆን ዘእንበለ ሐፍረት  ☞ የቃየን ሴቶች ልጆች ተውበው እርቃናቸውን በመሆን ሳያፍሩ ሲንቀሳቀሱ እዩዋቸው" 【ቀሌ. ፫፥፵፱】 ታዲያ እንዲህ ባለው መንገድ ነውርን እንደ ክብር መራቆትንም  እንደ መሰልጠን ገላ መግለጥ  እንደፋሽን እያዩ የሚኖሩ መጨረሻቸው ኩነኔ እንደሆነ መጽሐፋችን ይመሰክራል  “መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” 【ፊል ፫፥፲፱ 】        ለሰው ልጅ አካሉን ገልጦና ሰውነቱን አራቁቶ ለመታየት የታወቀ (በቂ) ምክንያት ያስፈልጋል፤ ሠለስቱ ምዕት ለመታከም «የሚተኮስ» «የሚታገም» አካል ቢኖር አልያም ከጸበል ሊነከሩና ሊታጠቡ እንጂ በሌላውስ መንገድ በማንም ፊት እርቃን መታየት ክልክል ነው ብለዋል። "ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ።  ☞ ዳግመኛም በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ፤ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ" 【 ሃይ አበው ፳፥፲፪ 】 መራቆት አለመዘጋጀት እፍረት ማሳየት የመዘናጋት በበጎ ምግባር ሳይተጉ የመኖር መገለጫ ነው።   “እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” 【ራእ  ፲፮፥፲፭】         አካልን ራቁቶ  መታየት ቀርቶ  የተራቆተ አካልም ማየት ራሱ   ሲያስነቅፍ ፣ ሲያስቀጣና ሲያስረግም እናያለን በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ ፱ እንደተገለጸው  በኖኅ ልጅ በካም  ላይ የደረሰው የዚህ ማሳያ ነው " ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። " 【ዘፍ ፱፥ ፳ - ፳፯】 እንግዲህ የተራቆተን ማየት በዚህ መጠን የሚያስነቅፍ ከሆነ ተራቁቶ የመታየት ቅጣቱ የከፋ ስለመሆኑ አያጠራጥርም መራቆት የዲያቢሎስ የክብር ልጅ መሆን ነውና ፤ ሰይጣን ማለት በትርጉሙ እሩቅ እም ስብሐተ እግዚአብሔር  【ከእግዚአብሔር ክብር የተራቆተ】ማለት ነውና። የተፈቀደ የማያሳፍርም  ዕርቃን የተባለውና በጥንተ ተፈጥሮ በአዳምና በሴቲቱ ኑሮ የተገለጠው የትኛው ራቁትነት ነው? ① ራቁትነታቸው ከዚህ ዓለም ልብስ ነው አለማፈራቸው ብርሃን ለብሰው ስለነበር ነው ዓለማችን የሚያለብሰን ምድራዊና ቁሳዊ ጊዜአዊና ኃላፊ ትጥቅ ነው መንፈሳዊ ትጥቃችን  ግን ኅልፈትና ውላጤ ከሌለው ሰማያዊ  አባታችን የምንቀበለው ነውና  “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።”  【ኤፌ ፮፥፲፩】 “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤ … በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ” 【ቆላ ፫፥፲፪- ፲፬】 የዓለሙ ልብስ ንፍገት ጭካኔ ቅሚያ ትዕቢት ብልጣብልጥነት ችኩልነትና ጸብእን ነው። ይህን ለብሰው የሚዋጉንን  ሥጋውያኑን በሥጋ ጦር ድል መንሳት እንዴት ይቻለናል?  የሳውልን የጦር ዕቃ የታጠቀ ካባ የለበሰና በአመጽ ወደተመላው እግዚአብሔርን ወደተገዳደረው ጎልያድ  በሥጋዊ መሳርያ ውጣ የተባለው  ብላቴናው ዳዊት መታመኛ ትምክህቱ መከታ ጉልበቱ እግዚአብሔር ስለበር በበትርና በኮሮጆው ጠጠር ዘምቶ  አመጸኛውን ሰልፈኛ ሰው ድል ነስቶታል።  “ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ።” 【፩ኛ ሳሙ. ፲፯፥ ፴፱】 ② አእምሮ ጠባያቸው ያላደፈ በተፈጥሮ እንደ ሕፃን  ስለነበሩ በዕርቃናቸው አይተፋፈሩም ሕጻናት በንጽሕና እንደ መላእክቱ ናቸው የእነርሱ አእምሮ ጠባይ ማደፍ ስላላገኘው ሊቁም «ንጽሖሙ ለሕፃናት በሥጋሆሙ ወነፍሶሙኒ ዘእንበለ ሕማም» ይላል። በዘመነ ሥጋዌው ክርስቶስ አምላካችንም እንደ ሕፃናት መሆን ለክብረ መንግሥቱ እንደሚያበቃ ነግሮናል “ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” 【ማቴ ፲፰፥፫】 መልሶም እንደነርሱ ላሉቱ ስለምትሠጥነና እነርሱኑ ለመሰሉት ስለምትገባዋ ዘልዓለማዊ ርስት ይህን ደግሟል “ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤”   【ማቴ ፲፱፥፲፬】  ያለቂም ያለበቀል የሚኖሩ ክፋትንና ተንኮልን አልመው አስበው ሌላው ይጎዳበት ብለው የማይፈጽሙ እንደወረቀት የሠጧቸውን የሚቀበሉ እንደውኃም ቅርጻቸው ያረፉበትን ሥፍራ የሚመስሉ ልጆች ሕጻናትን መስሎ መኖር የሚማሩትን መያዝ በበጎ አርያነት የሚመሩትን መምሰል በእጅጉ ይገባል ፤ “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”【፩ኛ ጴጥ ፪፥፪-፫】 እንዲህ ያለው የሕጻናት ንጹሕ አይምሮ መያዝ አያሳፍርም። ③ ከልብሰ ኃጢዓት  ተራቁተው ኃፍረተ ነፍስ ሳይኖርባቸው ይኖሩ ነበር ሰው ኃጢዓትን ለብሶ በደል ደርቦ ከመኖር በንሰሐ ቢራቆት ተኮንና የምታፍር ነፍስ የለችውም፤  ይልቁንም የልብ ንጽሕና ማጣት የሕሊና ሞት እንደሚያመጣበት አውቆ በኃጢዓቱ ምክንያት ያገኘውን ቁስለት የልቡናው ሰንኮፍ በንሰሐ ከከከበረች ነፍሱ ቢያርቅ መንገዱን በጥንቃቄ ቢመራና በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ለአምላኩ ቢገዛ በግራ ከሚቆምና ተኮንነው ከሚያፍሩ በመለየት መክበር ይቻለዋል።
Show all...
ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ የማያሳፍር ዕራቁትነት ዘፍ 2፥25

✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን:: ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ / @mahiberetsion እግዚአብሔር ያክብርልን

#ያንን_ሰው_ባረገኝ  ፣ #ያቺንም_ሴት_በሆንኩ [፩] 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ ምነው እሱን በሆንኩ ያን የቀኝ ወንበዴ ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት በዚያ መንገድማ ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና እኔን ታውቀኝ የለ …  የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች ዋና ያ … ጸጸት ያዘለ በዚያች የጭንቅ ሠዓት «አስበኝ» እያለ ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ ካ’ዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ እኔም እንደ ጥጦስ : ማታዬ እንዲያምር ብትለኝ ምን አለ? … «ከገነት ተጠለል: ዛሬን ከእኔ እደር» 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ ደ’ሞ ይህን ተመኘሁ ለንጊኖስን በሆንኩ ያቺን ዕለተ ዓርብ : ቀራንዮ በዋልኩ ለአመጽ አይደለም : ከከአይሁድ ለማበር አልያም ለመውጋት : ያንተን ጎን በጦር በዚያ መንገድማ አንተን ለማሳመም:  ማን እኔን መሰለ ስንቴ እንዳቆሰልኩህ …  ስንቴ እንደወጋሁህ : እኔን ታወቀኝ የለ! ያ …የጲላጦስ ጭፍራ በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ በጦሩ ቢወጋህ ሳያዝን ሳይራራ  ከቀኝ ጎን አፍስሰህ  ውኃው ከደም ጋራ በፍቅርህ ስታስረው  ዐይኑን ስታበራ ትዕግስትህን ጎትቶት   ባንተ እንደ ተጠራ ምናለ እንደው ’ኔንም … ላንተ ብቻ እንዲያድር : ልቤን ብታበራ 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ የበገና መዝሙር ዲ/ን አቤል ተስፋዬ ላንዴ እስከወዲያኛዉ https://youtu.be/GjZf3fPaeDs
Show all...
የበገና መዝሙር ዲ/ን አቤል ተስፋዬ ላንዴ እስከወዲያኛዉ

🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~~~~~~~~~ ምነው እሱን በሆንኩ ያን የቀኝ ወንበዴ ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት በዚያ መንገድማ ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና እኔን ታውቀኝ የለ …  የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች ዋና ያ … ጸጸት ያዘለ በዚያች የጭንቅ ሠዓት «አስበኝ» እያለ ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ ካ’ዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ እኔም እንደ ጥጦስ : ማታዬ እንዲያምር ብትለኝ ምን አለ? … «ከገነት ተጠለል: ዛሬን ከእኔ እደር» 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ : ዛሬን ከእኔ እደር» ደ’ሞ ይህን ተመኘሁ ለንጊኖስን በሆንኩ ያቺን ዕለተ ዓርብ : ቀራንዮ በዋልኩ ለአመጽ አይደለም : ከከአይሁድ ለማበር አልያም ለመውጋት : ያንተን ጎን በጦር በዚያ መንገድማ አንተን ለማሳመም:  ማን እኔን መሰለ ስንቴ እንዳቆሰልኩህ …  ስንቴ እንደወጋሁህ : እኔን ታወቀኝ የለ! ያ …የጲላጦስ ጭፍራ በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ በጦሩ ቢወጋህ ሳያዝን ሳይራራ  ከቀኝ ጎን አፍስሰህ  ውኃው ከደም ጋራ በፍቅርህ ስታስረው  ዐይኑን ስታበራ ትዕግስትህን ጎትቶት   ባንተ እንደ ተጠራ ምናለ እንደው ’ኔንም … ላንተ ብቻ እንዲያድር : ልቤን ብታበራ 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ምነው በመሰልኳት የቺን አመንዝራ እንደርሷ ላንድ ቀን : ከፊትህ ብጠራ ለዝሙት አይደለም ነፍሴን ለማሳደፍ አልያም ለመርከስ መቅደስክን ለማጉደፍ በዚያ መንገድማ ነውርን በመሸከም : መች ከእርሷ አንሳለሁ ሕግህን በማፍረስ … እኔን ታውቀኝ የለ : ምን እነግርሃለው ያቺን … ድኩም ዘማ በኃጢአቷ ቆስላ በበደሏ ታ’ማ ዓለም ተሰብስቦ ሕይወቷን ሊቀማ እንዲወግሯት ሳትፈርድ ቸርነትህ ቀድማ መሬቱን ስትጭር ድምጽህ ሳይሰማ ነውሯን እንደቀበርክ በከሳሽ ፊት ቆማ ዳግም አትበድዪ : በፍቅር ሂጂ እንዳልካት እንደው የኔንም ነፍስ … ምናለ መልሰህ: እንዲያ በማረካት 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት ✍️๏ በአግናጥዮስ  🖊 ሕዳር ካህናተ ሰማይ ፳፻፲፫ ዓ.ም ተፃፈ ☞ ከምድር ጌጥ ታላቋ ደብረ ሊባኖስ

👍 10 6
🌾 አንተን ማሳዘኔ በደሌ ቢበዛ ባታገኝም ከእኔ የጽድቅ መዓዛ 🌾 በምሕረትህ ብዛት አንተ ይቅር በለኝ ሥራዬን አትይ እኔ ደካማ ነኝ። 🌾 ዘወትር አለቅሳለሁ ድካሜን አውቄ መኖሬ ሲሰማኝ ከቃልህ ርቄ 🌾 በመንገድህ ምራኝ ፊትህን እንዳይ ስለ እናት ብለህ ከኔ አትለይ በዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
Show all...
17🙏 3👍 2
የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ሥርዓተ ቀብርን በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ክቡር አስከሬንም ከሀገረ አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ስርዓተ ቀብራቸው እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም በፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው ገነተ ኢየሱ ቤ/ክ ከ4- 6 ሰዓት ይፈፀማል:: ይህንንም በማስመልከት ለመልዐከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ መታሰቢያ ለማስቀመጥ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቃቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምራል:: በዚህም መሰረት ይህንን የተቀደሰ አላማ ለመደገፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አካውንቶች ገቢ እንድታደርጉ እንጠይቃለን:: 1000614508497 ንግድ ባንክ 179465639 አቢሲኒያ ባንክ መልአከብርሃንሙላት ክበቤ መልአከብርሃን ቄሰ ገበዝ ተቋመ ማህቶት መምህር በላይ ወርቁ የመልዐከ ጸሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ የቀብር አስፈጻሚ አብይ ኮሚቴ
Show all...
👍 4
ምግብ ልብስና ቤታችን የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ትጉህ ኖላዊ  ነው ፤  ነቅቶ የሚጠብቅ ከተራራው ወርዶ፣  ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን በመስቀል መንበር ላይ፣  አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን  መድኃኒታችን መድኃኔዓለም   የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ጸጋችን ተገ’ፎ ፣ ተራቁተን ብንርቅ በቁም ሞትን ለብሰን ፣ በለስ አገልድመን –በኃጢዓት ብንደርቅ በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን ከሸማኔ ጎድጓድ ፣ ከድንግል ተገኝቶ – ራሱን አለበሰን መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ከንቱ ቃል በመስማት ፣ ማረፊያ ስናጣ  ከገነት ተሰ’ደን ፣  ከሰማዩ መንግሥት–ወደ ምድር  ብንመጣ ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር መንግስተ ሰማያት፣ ወንጌልና ተስፋ –እርሱ ነው እግዚአብሔር። መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማይፈርስ ጽኑ  ቤት  ለፈላሲው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ https://youtube.com/watch?v=uHyymObqHQ0&si=VkH5pu91GUt0g8ki ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
Show all...
የሕግ ፍፃሜ 🔴  "መድኃኒታችን" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame |  Medhanitachen l D Zelalem Takele

#like #share #subscribe መድኃኒታችን የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት ትጉህ ኖላዊ  ነው ፤  ነቅቶ የሚጠብቅ ከተራራው ወርዶ፣  ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን በመስቀል መንበር ላይ፣  አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን  መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም  ጸጋችን ተገ’ፎ ፣ ተራቁተን ብንርቅ በቁም ሞትን ለብሰን ፣ በለስ አገልድመን –በኃጢዓት ብንደርቅ በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን ከሸማኔ ጎድጓድ ፣ ከድንግል ተገኝቶ – ራሱን አለበሰን መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም  ከንቱ ቃል በመስማት ፣ ማረፊያ ስናጣ  ከገነት ተሰ’ደን ፣  ከሰማዩ መንግሥት–ወደ ምድር  ብንመጣ ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር መንግስተ ሰማያት፣ ወንጌልና ተስፋ –እርሱ ነው እግዚአብሔር። መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማይፈርስ ጽኑ  ቤት  ለፈላሲው ዓለም  ግጥም መጋቤ ሐዲስ ቴዎድሮስ በለጠ (ዶ/ር) ዜማ  ዘ. ዘውዱ ጌታቸው ክራር ዘ. ዘውዱ ጌታቸው መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ ዋሽንት ኤልያስ ፈቃዱ ድምጽ አጃቢ ዘማሪት መቅደስ ማርዬ ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግና ማስተሪንግ ዘጎላ ሬከርድስ

👍 13
የሕግ ፍፃሜ 🔴  "መድኃኒታችን" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame |  Medhan... https://youtube.com/watch?v=uHyymObqHQ0&si=VkH5pu91GUt0g8ki
Show all...