en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Open in Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
899
Subscribers
-224 hours
-167 days
+2730 days
Posts Archive
እውነተኛ የሴት ልጅ ነፃነትና ጥበቃ ሊረጋገጥ የሚችለው ክብሯን ከፍ ባደረገው፣ ከውርደትና ከብልሽትም ጠብቆ በማኅበረሰቧ ውስጥ የተከበረችና ውድ ዕንቁ እንድትሆን ባደረጋት የኢስላም ሸሪዓ ጥላ ስር ብቻ ነው። 📌 قـ✑ــال العلامــة صـالح الفــوزان حفظــہ اللـہ تعـالـﮯ : ☜ المــرأة لا تڪـون حــرة إلا بالتــزام الأحڪـام الشــرعية ⇦ الشــر؏ حــررها مـن الهــوان حــررها مـن الفســاد حــررها مـن ڪـل رذيلـة ❀ ◄ ضبطها ✿ ◄ ڪرمها ❀ ◄ عززهـا ✿ ◄ صانهـا 📑 شـرح ڪـتاب الفتـن والحـوادث [ صـ 34 ] "አንዲት ሴት ነፃ ልትሆን የምትችለው የሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን (አህካሞችን) ሙጥኝ ብላ ስትይዝ ብቻ ነው። ​⇦ ሸሪዓ ከውርደት ነፃ አውጥቷታል፣ ከብልሽት ነፃ አውጥቷታል፣ ከማንኛውም መጥፎ ምግባር (ርኩሰት) ነፃ አውጥቷታል። ​❀ ◄ ስነ-ስርዓት አስይዟታል ✿ ◄ አክብሯታል ❀ ◄ ልዕልናን ሰጥቷታል ✿ ◄ ጠብቋታል ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ​📑 [ሸርሕ ኪታብ አል-ፊተን ወል-ሐዋዲሥ — ገጽ 34] t.me/durusuabihizam t.me/durusuabihizam

​ حُبُ أهل التوحيد، وبغض أهل الشّرك: 👉አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት፦ ​ 👉​ይህ አል-ወላዕ ወል-በራዕ (ለአላህ ሲሉ መወዳጀትና መጥላት) ማለት ነው። እርሱም የተውሒድ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት ሲሆን፤ ለአላህ ሲል ይወዳጃል፣ ለአላህ ሲል ይጣላል። ኢብራሂም (ዐለይሂ አስ-ሰላቱ ወስ-ሰላም) ለአባቱና ለሕዝቦቹ እንዳለው፦ ​{إِنَّا بُرَآءُ مِنْكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ} ​«እኛ ከእናንተ ከአላህም ሌላ ከምትገዙት ሁሉ የጠራን ነን፤ በእናንተ ካድን፤ በእኛና በእናንተ መካከልም ጠላትነትና ጥላቻ ተገለጠ።» ​{وَإِذْ قَالَ إْبْرَاهِيمُ لأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ} ​«ኢብራሂምም ለአባቱና ለሕዝቦቹ፡- እኔ ከምትገዙት ሁሉ የጠራሁ ነኝ ባለ ጊዜ (አስታውስ)።» ​ይህ የኢብራሂም ንግግር ነው፦ {{إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ}} (እኔ ከምትገዙት የጠራሁ ነኝ)፤ ማለትም፦ ከጣዖታት፣ ከዛፎችና ከድንጋዮች ከምታመልኳቸው ነገሮች ሁሉ የጠራሁ ነኝ ማለት ነው። ​{{إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}} ​«ያ የፈጠረኝ ሲቀር» ​እርሱም አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ነው፤ ይህ የ "ላ ኢላሀ ኢልለላህ" (ከአላህ በስተቀር #በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ትርጉም ነው፦ ​{{إِنَّنِي بَرَاءٌ} (እኔ የጠራሁ ነኝ) የሚለው የ "ላ ኢላሀ" (ምንም እውነተኛ አምላክ የለም) ትርጉም ሲሆን፣ ​{{إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}} (የፈጠረኝ ሲቀር) የሚለው ደግሞ የ "ኢልለላህ" (ከአላህ በስተቀር) ትርጉም ነው። ​ ​ حُبُ أهل التوحيد، وبغض أهل الشَّرك، وهى أوثقْ عُرى الإيمان የተውሒድ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት፣ ይህ ነገር ከኢማን ማሰሪያዎች ሁሉ ይበልጥ አስተማማኙ ገመድ ነው። ​ ​የአላህ መልክተኛ (ሰልለላሁ ዐለይሂ ወሰልለም) እንዲህ ብለዋል፦ ​« أَوْثَقُ عُرَى الْإِيمَانِ الْحُبُّ فِي اللَّهِ، وَالْبُغْضُ فِي اللَّهِ» ​«ከኢማን ማሰሪያዎች ሁሉ ይበልጥ አስተማማኝዋ ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት ነው። ​« ثَلاثٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ وَجَدَ حَلاوَةَ الإِيمَانِ: أَنْ يَكُونَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَحَبَّ إِلَيْهِ مِمَّا سِوَاهُمَا، وَأَنْ يُحِبَّ الْعَبْدَ لا يُحِبُّهُ إِلا لِلَّهِ -عَزَّ وَجَلَّ -، وَأَنْ يَكْرَهَ أَنْ يَرْجِعَ فِي الْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنْقَذَهُ اللَّهُ مِنْهُ كَمَا يَكْرَهُ أَنْ يُلْقَى فِي النَّارِ» ​«ሦስት ነገሮች በእርሱ ውስጥ የተገኙ ሰው የኢማንን ጣዕም አግኝቷል፦ አላህና መልክተኛው ከሌላው ነገር ሁሉ ይበልጥ በእርሱ ዘንድ ተወዳጅ መሆን የለባቸው፣ አንድን ባሪያ ለአላህ (ዐዘ ወጀል) ሲል እንጂ ሌላ ለምንም ሳይሆን መውደዱ፣ እና አላህ ከክህደት ካዳነው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን ልክ ወደ እሳት ውስጥ መጣልን እንደሚጠላው አድርጎ መጥላቱ።» ​እነዚህ አላህን፣ መልክተኛውን፣ ዲኑን (ሃይማኖቱን) እና ወዳጆቹን የመውደድ ምልክቶች ናቸው። አላህ (ጀልለ ወዐላ) እንዲህ ይላል፦ ​{{إِنَّمَا وَلِيُّكُمْ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُمْ رَاكِعُونَ}} ​«ረዳታችሁና ወዳጃችሁ አላህ፣ መልክተኛውና እነዚያ የሰገዱ ሆነው ሶላትን የሚሰግዱ፣ ዘካንም የሚሰጡ ምዕመናን ብቻ ናቸው።» ​{{وَمَنْ يَتَوَلَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا فَإِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمْ الْغَالِبُونَ}} ​«አላህንና መልክተኛውን እነዚያን ያመኑትንም ወዳጅ የሚያደርግ ሰው (የአላህ ጭፍራ ነው)፤ የአላህም ጭፍራዎች እነሱ አሸናፊዎች ናቸው።» (የአላህን ወዳጅ ማድረግ ማለት አላህን መውደድ ማለት ነው)። ​ ​ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት ማለት ይህ ነው። ነገር ግን ሰውን ሁሉ የሚወድ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ ለእርሱ መልካም ለዋለለት ሰው ብቻ ውዴታን አሳይቶ፣ የበደለውን ሰው ሙእሚን (አማኝ) ቢሆን እንኳ የሚጠላ ከሆነ፤ ይህ ሰው (ፍፁም) አማኝ አይደለም። ​ምንጭ፦ «ከላ ኢላሀ ኢልለላህ» ትርጉም መልእክት በኢማም ሙሐመድ ቢን ዓብደል ወሃብ ​ ​አብራሪው፦ ታላቁ የፊቅህ ሊቅ ዐላማህ ሸይኽ / ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸው)

🎙በድምፅ እንደምሰሙት ባህር ዳር ከተማ በ08 ቡኻሪ መስጂድ ኢማሙ ከግድያ በአላህ ፍቃድ አመለጡ ። እረተው እንጠንቀቅ በቻልነው አቅም ኢማሞች በዬ ቦታው እየታደኑነው። በያስ ሼርኳን እያደ ርጋችሁ ለሁሉም ይድረስ እባካችሁ። 🔷👉https://t.me/abujemila25 🔷👉https://t.me/abujemila25 ለሁሉም አድርሱልኝ።

🔷 የሰለፎች መንሀጅ በማጥበቅ እና በማላላት መካከል ያለ የፍትህ፣ የሚዛን እና የጥበብ መንገድ ነው!!! አላህ ይችን ዑማ የመካከለኛነት ኡማ አድርጎ መርጧታል። እንዲህም ይለናል፦ ﴿وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَاكُمْ أُمَّةً وَسَطًا﴾ “እንዲሁም መካከለኛ ሕዝብ አድርገን አደረግናችሁ።” (አል-በቀራህ 2፥143) ይህ “ወሰጥ” የሚለው ቃል በሰለፎች ግንዛቤ ፍትህን፣ ሚዛንን፣ ከጫፎች መራቅን እና እያንዳንዱን ነገር በሚገባው ቦታ ማስቀመጥን ያመለክታል። ስለዚህ የሰለፎች መንሀጅ የስሜት መንገድ አይደለም፣ የወገንተኝነት መንገድ አይደለም፣ የተከታዮችን ብዛት የሚለካ መንገድም አይደለም፤ ይልቁንም የማስረጃ፣ የፍትህ፣ የእውቀት እና የጥበብ መንገድ ነው። የሰለፎች መንገድ ከሁለት ጫፎች የጸዳ ነው። ከአንዱ በኩል ያለቦታው ተጥቢቅና ጉሉው፣ ከሌላው በኩል ደግሞ ያለቦታው ማላላትና ተፍሪጥ ነው። አላህ እንዲህ ይለናል፦ ﴿يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ﴾ “የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በዲናችሁ ውስጥ ከመጠን አትለፉ።” (አን-ኒሳእ 4፥171) እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إِيَّاكُمْ وَالْغُلُوَّ فِي الدِّينِ، فَإِنَّمَا أَهْلَكَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمُ الْغُلُوُّ فِي الدِّينِ» “በዲን ውስጥ #ከመጠን ማለፍን ተጠንቀቁ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው በዲን ውስጥ ከመጠን ማለፋቸው ነበር።” ከዚህ የተነሳ ያለቦታው ማጥበቅ የሰለፎች መንገድ አይደለም። #አንዳንዶች የራሳቸውን ፍርድ የሰዎች መመዘኛ ያደርጋሉ። በስሜት በቁጣ እና ሞቅ ሲላቸው ቸኩለው በሰው ላይ #ፍርድ የሚሰጡ አካላቶች እንድሁም የግለሰቦችን ወይም የቡድኖችን ጉዳይ በራሳቸው ግምት በመወሰን ሌሎች ሰዎች ያንኑ ፍርድ ካልተከተሉ ወይም ካልተስማሙ በተመሳሳይ መፈረጅ ይጀምራሉ። አንዳንድ ጊዜ #ኢልዛምን የወላዕና በራዕ መለኪያ ያደርጋሉ።ሰዎችን በቁርአንና በሱና ማስረጃ ሳይሆን #በግለሰብ ውሳኔ ይመዝናሉ። የሰለፎች መንገድ ግን ይህ አይደለም። የሰለፎች መንገድ ሰዎችን በማስረጃ፣በፍትህ እና በእውቀት ይመዝናል። በማጥበቅ ጫፍ የወደቁ #አንዳንድ አካላት #ግለሰቦችን ወይም #ቡድኖችን በመፈረጅ ላይ ከልክ ያልፋሉ። አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ የሰጡትን ፍርድ ካልተከተለ ወይም ተመሳሳይ ውሳኔ ካልደረሰበት በቀላሉ በተመሳሳይ ስም ለመፈረጅ ይቸኩላሉ። እኔ ሙብተድዕ ያልኩትን ካላልክ #ሙብተድዕ ነህ።  እኔ ሙሽሪክ ያልኩትን ካላልክ #ሙሽሪክ ነህ የሚሉ አካላቶች እንደዚህ ያለውን የግዴታ ተከታታይነት (الإلزام) የሰው ታማኝነት ወይም የመንሀጅ መለኪያ ማድረግ ግን ከሰለፎች የፍትህ መንገድ አይደለም። አላህ እንዲህ ይለናል፦ ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَى أَنْفُسِكُمْ﴾ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ምስክሮች ሆናችሁ በፍትህ ጽኑ፤ ምንም እንኳ በራሳችሁ ላይ ቢሆንም።” (አን-ኒሳእ 4፥135) እንዲሁም፦ ﴿وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَى أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَى﴾ ➜ “የአንድ ሕዝብ ጥላቻ ፍትህን እንዳትተዉ አያድርጋችሁ። ፍትህን አድርጉ፤ እርሱ ለተቅዋ ይበልጥ ቅርብ ነው።” (አል-ማኢዳህ 5፥8) በሌላ በኩል ደግሞ ያለቦታው #የሚያላሉና #የሚያግራሩ አካላት አሉ። እነርሱ አንዳንድ ጊዜ ለጥቅም፣ ለስም፣ ለተከታይ ብዛት፣ ለዝና ወይም ለሌሎች ዓለማዊ ግቦች ሲሉ ሀቅን ከመናገር ይቆጠባሉ። ስህተትን በስሙ ለመጥራት ይፈራሉ፣ ባጢልን በባጢልነቱ ለመግለጽ ይዘገያሉ፣ እናም አንድነትን ከሀቅ በላይ ያስቀድማሉ። ነገር ግን አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنْتُمْ تَعْلَمُونَ﴾ “ሀቅን ከባጢል ጋር አትቀላቅሉ። እናንተም እያወቃችሁ ሀቅን አትደብቁ።” (አል-በቀራህ 2፥42) እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «الدِّينُ النَّصِيحَةُ» “ዲን መመካከር ነው።” ስለዚህ ሀቅን መግለጽ ከዲን አካል ነው። ➜ ነገር ግን ሀቅን መግለጽ ማለት #ፍትህን መተው ማለት አይደለም።እንዲሁም ፍትህን መጠበቅ ማለት ሀቅን መደበቅ ማለት አይደለም። የሰለፎች መንሀጅ ሀቅን በእውቀት ላይ ሁነው እንድናገሩ ያዛል። እንደዝሁም ከስህተትም በእውቀትና በፍትህ ያስጠነቅቃሉ። አብደላህ ኢብኑ መስኡድ እንዲህ ብለዋል፦ «الجماعة ما وافق الحق وإن كنت وحدك» “ጀማዓ ማለት ከሀቅ ጋር መሆን ነው፤ ምንም እንኳ አንተ ብቻህን ብትሆንም።” እንዲሁም ሱፍያን አሶውሪ እንዲህ ብለዋል፦ «إذا رأيت الرجل يعمل العمل الذي اختلف فيه وأنت ترى غيره فلا تنهه» “አንድ ሰው በዑለማዎች መካከል የተለያየበትን ጉዳይ ሲሠራ ብታይ አትከልክለው።” ይህም የሰለፎች ፍትህና ሚዛን ነበር፤ ሰዎችን በአንድ ጉዳይ ላይ በችኮላ አይፈርዱባቸውም ነበር፣ እንዲሁም ሀቅን በሰዎች ፍላጎት ምክንያት አይተዉም ነበር። ስለዚህ የሰለፎች መንሀጅ ከጉሉውና ከተፍሪጥ፣ ከማጥበቅና ከማላላት፣ ከችኮላ ፍርድና ከዝምታ፣ ከጭካኔና ከመለሳለስ መካከል የቆመ የፍትህ፣ የሚዛን፣ የእውቀት እና የጥበብ መንገድ ነው። ይህ ነው የአህሉ ሱና ውበት፤ ይህ ነው የሰለፎች ጓዳ፤ ይህ ነው ከሁለቱ ጫፎች መካከል ያለው ቀጥተኛ መንገድ። አላህ እኛን በዚህ የፍትህ እና የሚዛን መንገድ ላይ እንዲያጸናን፣ ከጉሉውና ከተፍሪጥ፣ ከማጥበቅና ከማላላት እንዲጠብቀን፣ ሀቅን በእውቀት እና በጥበብ እንድንናገር እና ፍትህን በሁሉም ሁኔታ እንድንጠብቅ እንለምነዋለን።

🟢 በመጨረሻም ይህ በዝርዝር ያቀረብኩት ወሎ ላይ ያለውን ደውራ በተመለከተ ሲሆን ጅማዎች እና ቡታጅራዎች ከምለው በላይ ደስ አሰኚታችሁናል ። አላህ ይጠብቃችሁ።ሸይኽ ልናመጣ ነው ስንላችሁ እንደ እኛ ተዘጋጁ ስንላችሁ መርሀባ ዝግጁ ነን በማለት ላሳያችሁን የዲን እና የሱና ውደታ ምስጋናችን ከልብ ነው ። ኢን ሻ አላህ  የአላህ ፍቃዱ ከሆነ ሀገር አቀፍ ደውራ አዘጋጅተን የትውውቅ ፕሮግራም  በአንድኛችን የምናደርግ  ያድርገን ።    ከላይ ስማችሁ ያልተጠቀሰ ግን ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ብዙ የለፋችሁና የደከማችሁ መሻይኾች፣ኡስታዞች እና ጀማዓዎች  ትኖራላችሁ አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ ።ልፋታቹሁ መልካም ስራችሁ ሚዛን ላይ የሚጨመር አላህ ያድርገው።
አንሷር ሙሐመድ
🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088

ምስጋናችን ከልብ ነው።
      ​በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን ታላቅ የደውራ ፕሮግራም በሰላም፣ በስኬት እና በደመቀ ሁኔታ እንድንጨርስ የረዳንን ኃያሉን አላህ (سبحانه وتعلى) እናመሰግነዋለን። በመቀጠልም፣ ይህ ፕሮግራም ካለ ምንም እንከን ግቡን እንዲመታ እና ለብዙሃን እህትና ወንድሞቻችን የብርሃንና የእውቀት ምንጭ እንዲሆን በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ፣ በጉልበታችሁ እንዲሁም በሃሳባችሁ ከጎናችን በመቆም ይህ የደውራ ፕሮግራም  እንዲሳካ ላደረጋችሁ  በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ​በተለይም ደግሞ ​ለተከበሩ ሸይኽ  አልዩ አር ራዚሒ ወደ ሀበሻ (ኢትዮጵያ) ለመምጣት መጀመሪያ ከሳዑዲ ወደ ግብፅ ከዚያም ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ አዲስ አበባ ላይ በመስጂዶች ላይ ደዕዋ፣ኹጥባ እንድሁም ኮርስ ለአህለ ሱናዎች ከሰጡ በኋላ ወደ ወሎዋ ምድር ኮንቦልቻ በመምጣት ኮንቦልቻ ላይ ከተለያየ ቦታ የመጡ  ከ1300 በላይ  ለሆኑ መሻይኾች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች ፣ዒልም ፈላጊ ወንድሞች እና እህቶች ለአምስት ቀን በሚያምር እና በቆንጆ አገላለፅ  በመንሀጅ ዙሪያ ፣አንድ ኪታብ በአስማኡ ወሲፋት ዙሪያ  ፣አንድ ኪታብ በሙስጦላሁ አል"ሀዲስ ዙሪያ እና  አንድ ኪታብ በፊቂህ ዙሪያ   በማስተማር  ሲደክሙና ሲለፉ  ካሳለፉ በኋላ በየመሃሉ ላይ የፈተዋ ፕሮግራም ሲሰጡን ነበር።ሸይኽ አላህ ጀዛቸውን  ይክፈላቸው ና የኮንቦልቻውን ፕሮግራም ከጨረሱ በኋላ በደሴ ከተማ ከዝሁር  ሶላት በኋላ በአረብ ገንዳ  እና ከአስር ሶላት በኋላ በመስጂደ አስ"ሱና በሚያምር አገላለፅ ሁሉንም ባቦች በመዳሰስ  የደዕዋ ፕሮግራም  በማድረግ የወሎዉን ደውራ በዚሁ ጨረሱ።ከወሎ ወደ አዲስ አበባ የደዕዋና የኮርስ ፕሮግራም  በድጋሜ አድርገዋል።የአዲስ አበባውን ፕሮግራም ከጨረሱ በኋላ ወደ ቡታጅራ የተላያዩ ኪታቦችን በኮርስ መልኩ ለብዙ መሻይኾችና ኡስታዞች ወሎ ላይ ባስተማሩት መልኩ አስተምረዋል። ከቡታጅራ ከተመለሱ በኋላ ወደ ጂማ ዞን በሁለት ከተማዎች ላይ ወሎ ላይ ባስተማሩት መልኩ አስተምረዋል። ሸይኽ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልኩ ሲያስተምሩ ከቆዩ በኋላ ወደ የመን መዕበር አቅንተዋል።የመን መዕበር በሰላም  መድረሳቸውንም  ለዶ/ር ሰዒድ ሙሳ በላኩት ድምፅ አረጋግጠናል።  አልሀምዱሊላህ ሸይኽ ይህን ሁሉ ውጣ ውረድ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይሉ በዛ ስሙኝ ስሙኝ በሚልና ከምግብ እና ከመጠጥ በላይ በሚጣፍጥ  አገላለፅ ሲያስተምሩን ስለቆዩ ለሸይኽ አልይ ምስጋናችን ከልብ ነው።ሸይኹን አላህ  መልካም ስራቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይቀበላቸው። አሚን   ይሄን ፕሮግራም እዚህ እንዲደርስ ሲወጡና ሲደክሙ  የነበሩ ወንድሞች ለአብነት ያክል:– 1⃣ ወንድም አብዱልፈታህ (ኢብኑ ሙሐመድ ዘይን)  ይሄን ሀሳብ ለወንድሞች በማማከር እና ሸይኽ አልዩ አር"ራዚሒ ቅርብ የሆኑ ወንድሞች ጋር በማውራት የዚህን ፕሮግራም እውን ይሆን ዘንድ ከመጀመሪያዎቹ አወለ ሶፍ ሊሰለፉ ከሚችሉ ወንድሞች ውስጥ ቀዳሚው ነው።አላህ ይቀበልህ ወንድሜ በአካል ባላውቅህም ከልቤ ነው የምወድህ ፣የማከብርህ፣የምሳሳልህ አላህ ይጠብቅህ ። 2⃣ ወንድም ሙሳ (ስሙን እርግጠኛ አይደለሁም) የሸይኽ አልዩ አር"ራዚሒ ቅርብ የሆነና ለዚህ ፕሮግራም መሳከት መሀል ላይ እንደ ሞተር ሆኖ የለፋና የደከመ ወንድም ነው። ወንድማቸን ሙሳ  ከወንድም አብዱል ፈታህ እና ከሸይኽ አልይ ጋር መልዕክቶችን በመለዋወጥ ይህ እቅድ ወደ መሬት ይወርድ ዘንድ በሰፊው የለፋና የደከመ ወንድም ነው። አላህ የአንተን መሰል ወንድሞችን ያብዛልን። 3⃣ ወንድም አህመድ ኑር (አቡ ሻኪራ) ይህ ፕሮግራም ይሳካ ዘንድ የመን ያሉትን ወንድሞች (ከወንድም አብዱል ፈታህ እና ወንድም ሙሳ) እና ሀበሻ ያሉ ወንድሞች ጋር ጊዜውን እና ገንዘቡን መስዋት በማድረግ  በተለያየ ሰዓት ሹራ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ነፍስ ያለው ወንድማችን ነው። ይህ ወንድማችን ለደውራው የሚያስፈልጉ ኪታቦችን አህለል ኸይር በማፈላለግ ከ 154,000 ብር  አውጥቶ ደውራው ላይ በነፃ  ኪታቦቹ እንዲታደሉ ያደረገ ወንድም ነው። አላህ ይጠብቀው ብዙ ሀጃዎች አሉት ዱዓ አድርጉለት ከአይን ይጠብቅህ ወንድሜ አህመድ ኑር ! 4⃣ ዶክተር ሰዒድ ሙሳ ይህ ፕሮግራም ከታሰበበት ሰዓት  አንስቶ  ሸይኹ ወደ የመን እስኪመለሱ ድረስ የለፋ ፣የደከመ፣ለዚህ ፕሮግራም ሲል 23 ቀን ሙሉ  ልጆቹን፣ቤቱን ፣ስራውን  በመተው  ከሸይኹ ጋር አብሮ በሄዱበት ሁሉ ጭርታ እንደይሰማቸው ያደረገ እና የሸይኹን ሙሉ ወጭ የሸፈነልን ውድ ኡስታዛችን ነው። ኡስታዙና ዱክቱር አላህ መልካም ስራህን ይቀበልህ ።በመልካሙ ሁሉ ጀሊሉ ይጠግንህ።ሀጃህንም ይሙላልህ። ሷሊህ ፣ ለኡማው ጠቃሚ፣ ፍሬ የሚያፈሩ እና የአይን ማረፊያ የሆኑ  መልካም ፍሬዎችን ይለግስህ። እነ ቡኻሪ  ሰዒድንም ሱና  ላይ አንበሳ ለሱና የሚለፉና የሚደክሙ ፣  ለቢድዓ  ደግሞ መጋዝ ጀባሩ ያድርጋቸው የአንተ አይነት መሰሎችን ያብዛልን ! 5⃣  የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል ሀላፊዎች ፕሮግራሙ እንደይሳካ ጥረት ያደረጉ አካላቶችን እኛ ፍቃድ ያለን አካል ነን ።ፕሮግራሙ የእኛ ነው ሙሉ ሀላፊነት እንወሰዳለን  በማለት ምንም እንቅፋት እንደይኖር ቀድመው  በማመቻቸት ለዚህ ፕሮግራም የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ማዕከል ነው።ለሀላፊዎቹ ጀዛቸውን አላህ ይክፈላቸው። 6⃣ አቡ ሒበቲላህ፣አቡ አዩብ፣አቡ ማሂ፣አቡ ዒምራን ፣አቡ ሁዘይፋ፣አቡ ረያን ፣አቡ ሹራ፣አቡ ሀፍሷ ፣አቡ ሀሳን ፣አቡ ዑበይዳ፣ኑረዲን አል ዓረቢ  እና ሌሎችም አሁን ላስታውሳቸው  የማልችለው ወንድሞች ለዚህ ፕሮግራም የሚሆነውን ወጪ በማስላት ከራሳቸውም ከሌሎችም በማስተባበር የፋይናንሱን ወጭ የሸፈኑ ወንድሞች ናቸው።  አላህ መልካሙን ሁሉ ያግራላቸሁ ❗️❗️ 7⃣ የኮንቦልቻ የአንሷር መስጂድ ጀማኣዎች: –የአንሷር ጀማኣዎች በጣም የሚያስቀኑና ቅንጅታቸው ልብን የሚያረጥብ ፣ክድሜያቸው በጣም ቆንጆ የሆኑ ወድ እና የተከበሩ ወንድሞች ናቸው። እኚህ ወንድሞች  ሙሉ ከኢትዮጵያ ተጠራርተው የመጡ ወንድሞቻቸውን ደከመኝ፣ሰለቸኝ ሳይሉ፣ቤት፣ ንብረታቸውን እና ስራቸውን ትተው አምስት ቀን ሙሉ  ምንም አይነት ክፍተት ሳይኖር እንግዶቻቸውን ተንከባክበው የሸኙ የወሎዎች አይን ማረፊያ ጀማዓዎች ናቸው። ጀማዓቸውን እና መስጂዳቸውን ከተንኮለኞች ሴራ አላህ ይጠብቅልን። 8⃣  ከተለያየ ቦታ የመጣችሁ መሻይኾች፣ኡስታዞች እና ወንድሞች በሙሉ የቦታው መራቅ ሳይገድባችሁ  ጥሪያችንን አክብራችሁ፣ በሰዓቱ ተገኝታችሁ፣ በስነ-ስርዓትና በትዕግስት ፕሮግራሙን ስለተከታተላችሁ እንድሁም  ድምቀታችን ስለሆናችሁ፤ ​ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ሁላችሁንንም አላህ በሱና ላይ ያፅናንን። ​9⃣  በወንድሞች ጥቆማ መሰረት ጉዳዩ የኛም ነው ብላችሁ ያላችሁን በመዘርጋት ፕሮግራሙ ያለምንም የፋይናንስና የቁሳቁስ እጥረት እንዳይከሰት ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ልግስና እና ድጋፍ ምስጋናችን ከልብ ነው ። አላህ ገንዘባችሁን በረካ ያድርግላችሁ። 1⃣0⃣ ለሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ ወንድሞች ሲካሄዱ የነበሩ ፕሮግራሞችን በድምፅ በመቅዳት  ጥራቱን ጠብቆ ፕሮግራሙ ላይ ላልተሳተፉ ወንድሞች  እንዲደርስ እና  ፕሮግራሙን በቀጥታ ስርጭት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለአለም ህዝብ ተደራሽ ስላደረጋችሁ ምስጋናችን ከልብ ነው።

📌ያ አላህ 👉አንተ ከኔ ሌላ አለህ ብዙ ለማኝ 👉እኔ ካንተ ውጪ የለም የሚሰማኝ 👉መንገድ ጠፍቶብኛል በራህመትህ ጥራኝ 👉የተብቃቃህ ጌታ የከውኑ ባለቤት 👉እጆቼን አንስቼ ኢላሂ እላለሁ እስክትለኝ አቤት 👉ከኔ ይልቅ ለኔ አንተ ስለምታውቅ 👉በመንገድህ ምራኝ ጥፋቶቼን ልራቅ ✍ኮፒ 👉https://t.me/wdumuslimstu

እንደ ሸይኽ ሙዘሚል ፊቂሪ እና አብረውት እንዳሉት ዱዓቶች ሱዳን ላይም ሆነ አለም ላይ የሱፍያን ጥመት በአደባባይ ያጋለጠ አላየሁም።‼️ አሏህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸው ዳዕዋቸውንም በረካ ያርግላቸው። ለአሏህ ብየም እወዳቸዋለሁ‼️ ✍አቡ ሹራ https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

የጁመአ ቀን ሱናወች ~‌ ~ገላን መታጠብ ~ ጥሩ ልብስ መልበስ ~ሽቶ መቀባት (ለወንዶች) ~ ሲዋክ ~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ ~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰለሏሁ፣ዐለይሂ፣ወሰለም) ላይ ሰለዋት ማውረድ። ‌ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ال        لَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

👉የኔና የመሰሎቼ ጥያቄ...⁉️ «ሰው ለምን አምናለሁ⁉️» ------------------------ ለምን ይመስለኛል ሁሉም ልክ እንደኔ፡ ለምን ወንድም ናፍቆ ያማትራል አይኔ፡ ለምን በትዝታ ይሰበራል ጎኔ..!?? ለምን⁉️ ለምን⁉️ ለምን⁉️ ደጋግመው ጎድተውኝ ውስጤ እየታወቀኝ፡ አይጠፉም ከውስጤ ከግራና ከቀኝ!! ለምን ይሆን ሁሌ ሰው የሚናፍቀኝ፡ ምንድነው ያገደኝ ለምን ነው ያልቻልኩት፡ ሰው የሚባል ፍጡር እንደምን አመንኩት!? ምን ይሆን የነካኝ ምንድነው የሆንኩት....!? እኮ እንደት..⁉️ እኔ መልካም ሳስብ ግፍ እየሸለሙኝ፡ ከፊቴ እየሳቁ ከጀርባዬ እያሙኝ፡ ቦታ እምሰጣቸው በጣም አደከሙኝ!! .....እ... እንደት አንድን ስህተት ሁሌም እደግማለሁ፡ በወደድኩት መጠን ሰው ለምን አምናለሁ!? ጤነኛ አይደለሁም!?እውነት ታምሜያለሁ⁉️ ...ታዲያ...!! ወዶ አለማመንን ለምን አል'ለመድኩም፡ ማስመሰል ማታለል ለምንስ አልቻልኩም፡ ከትናንት ጉዳቴ ለምን አልተማርኩም⁉️ ...በሉ እስኪ ንገሩኝ..!? ተቀያይሬያለሁ ከትናንት ዛሬ⁉️ አስከፊ ነው እንዴ ፀባይ ንግግሬ⁉️ ታዲያ ሰው ማመኔ ምን ላይ ነው ችግሬ⁉️ ለምን እከዳለሁ ተረዳኝ ባልኩት ሰው፡ ለምን እጎዳለሁ እጀ ባጎረሰው፡ ለምን ይርቀኛል ዋጋ የሰጠሁት⁉️ ለምን ይጠላኛል በስስት ያየሁት⁉️ ከእንግዲህ በኋላስ ለምን እጎዳለሁ፡ ለምን ተስፋ አልቆርጥም ለምን ሰው አምናለሁ...⁉️ «ለዚህ ጥያቄ መልስ አጣሁኝ እስኪ ተባበሩኝ...⁉️» ....በኑረዲን አል-አረብ... http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

«ለናፈቁ ነፍሶች ..!!» አንዳንድ ናፍቆት አለ..... ድምፅ የሌለው ጩውኸት!! በሰው ልጅ ስሜት ውስጥ እጅግ ግዙፍና ረቂቅ የሆኑ ማዕበሎች አሉ። አንዳንዴ በውስጣችን የሚነሳው የናፍቆት ወጀብ ቃላት ሊሸከሙት ከሚችሉት አቅም በላይ ይሆናል። ሰውን መናፈቅህን በለቅሶ፣ በቃላት መደርደር ወይም ለወዳጅ በማውጋት የምታስታግሰው ከሆነ፣ ያ ቀላል ናፍቆት ነው፤ መውጫ መንገድ አግኝቷልና። ነገር ግን አንዳንድ ናፍቆት አለ፤ አንደበቱ የተለጎመ፣በውስጥህ ላይ የታተመ፣ መውጫና መግቢያው የጠፋው፣ በነፍስህ እልፍኝ ውስጥ ብቻ ታጥሮ የሚብሰለሰል ማዕበል! .....ይህ አይነት ናፍቆት እርሱ ልክ እንደ ሰዓት እላፊ ገደብ በየደቂቃው እየተመላለሰ የልብህን ሰላም ይነሳዋል፤ ነገር ግን ይህንን ስቃይህን ለዓለም የምታሳይበት ምንም ዓይነት ድምፅ የለህም። ይህ ዓይነቱ ናፍቆት ድምፅ የሌለው ጩኸት ይባላል። ከውጭ ሲያዩህ ሙሉ፣ ሳቅህ የማይለይህና ሰላማዊ ሰው ትመስላለህ፤ በውስጥህ ግን በከፈት ፍንዳታው ከኒውክለር አረር የበረታ ሰማይና ምድርን የሚያናውጥ የሚመስል፣ የነፍስህን ግንብ የሚያፈርስ ትልቅ የናፍቆት ጩኸት አለ። በሞት ወይም በሆነ አጋጣሚ ያጣኸውን ሰው፣ የራቀህን የትናንት ውብ ትዝታ እያሰብክ ልብህ በኃይል ይጮኻል፤ ነገር ግን ያ ጩኸት ከአንተ የሕሊና ጓዳ አልፎ ወደ ውጭ አይወጣም። በዝምታህ መሃል የሚፈጠረው ያ የናፍቆት ግፊት፣ በዓይኖችህ መቅበዝበዝና በትርታህ ፍጥነት ውስጥ ብቻ የሚገለጽ የነፍስህ ድምፅ አልባ ጩኸት ነው። ይህ ድምፅ አልባ ጩኸት ግን የድካም መግለጫ ሳይሆን፣ በውስጥህ ስላለው የፍቅር ጥልቀትና ክቡርነት የሚመሰክር ታላቅ ኃይል ነው። የሚናፍቅ ልብ ሕያው ነው፤ ትናንትን በክብር አስቀምጦ ለተሻለ ነገ የሚጓዝ ጽኑ ልብ ነው። ርቀት አካልን እንጂ መንፈስን መቼም ሊያርቀው እንደማይችል ሁሉ፣ ይህ በውስጣችን የሚነሳው የጸጥታ ማዕበልም ነገ በደስታ ለሚደረገው ዳግም መገናኘት ትልቅ የብርታት ስንቅ ይሆነናል። ስለዚህ ይህንን ድምፅ አልባ ጩኸት እንደ መጎዳት ሳይሆን፣ በእኛ ውስጥ ያለውን እውነተኛና ጥልቅ ሰብአዊነት ማረጋገጫ፣ ሕያው ምስክር አድርገን እንቁጠረው። አንደበት ዝም ሲል፣ ልብ ደግሞ ጩኸቱን ያበረታዋል፤ የናፍቆት ሁሉ ከባዱና ማራኪው ጥበብ በዝምታ ውስጥ የሚደረግ የልብ ጉዞ ነው። ነፍስህ ትጮኻለች! ክፉው ናፍቆት ርቀቱ ሳይሆን፣ በውስጥህ የሚነሳውን ታላቅ ማዕበል ለዓለም የምታሳይበት የቃላት አቅም ማጣትህ ነው። ....✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

قال العلامة الفوزان حفظه الله : ‏"لا يعرف قيمة الصحة إلا من ذاق المرض" إعانة المستفيد (١/٨٨)                              

Repost from Dr. Seid Musa
🎙[ بعض فوائد الدورات العلمية للدورة التي أقامها الشيخ علي الرازحي في أثيوبيا ] لفضيلة الشيخ /        محمد بن عبدالله باموسى - حفظه الله - . = የቴሌግራም ቻናል t.me/AbulbukhariSeid

Repost from Dr. Seid Musa
ምስጋና ሁሉ ለአለማት ጌታ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የተገባ ይሁን። ሸይኽ ዐሊ ቢን አሕመድ አር'ራዚሒ (አላህ ይጠብቃቸውና) ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የነበሯቸውን የኮርስ ፕሮግራም ጨርሰው በሰላም የመን መዕበር ደርሰዋል።

ولهذا فواجب أهل العلم، والبصيرة: الغيرةُ على دين الله تعالى، والذبُّ عن حياض السنَّة بحسب المستطاع، ولا يكلف بغير ذلك . وقد أحسن شيخ الإسلام ابن تيمية؛ حين قال : (وقَد يَرَى بَعضُ المُؤمِنينَ مَا في ذَلكَ مِن الخَطَإ، والضَّلَال؛ لَكِن يَهَابُ رَدَّهُ : ”إمَّا خَوفًا أَن يَكُونَ حَقًّا لَا يَجُوزُ رَدُّهُ“ . و”إمَّا عَجزًا عَن الحُجَّةِ، والبَيَانِ“ . و”إمَّا خَوفًا مِن المُنتَصِرينَ لَهُ“ . فيَجِبُ ”نُصحُ المُستَرشِدِ“، و”مَعُونَةُ المُستَنجِدِ“، و”وَعظُ المُتَهَوِّرِ، والمُتَلَدِّدِ“، وبَيَـانُ الصِّـرَاط الُمستَقِيم صِـرَاطَ الَّذينَ أَنعَـمَ اللهُ عَلَيهم مِن النَّبيِّينَ، والصِّدِّيقِينَ، والشُّهَـدَاءِ، والصَّالـحِـيـنَ) انتهى . وأما من لم يدافع عن الباطل، وأهله، وحمِد رد من رد، وأقبل على العلم، ونشره، واشتغل بشأنه؛ فهو على خير كبير . فالقدح في عقيدته - والحال ما سبق-، والاشتغال بالطعن في منهجه، أو سلوكه، أو دعوته إلى الله تعالى؛ لأنه لم يرد على زيد، أوعمرو، ولم يلبِّ الطلبات، ولم يستجيب لتلك الإلزامات ؟؛ فهذا والله من البغي، والظلم، والاستطالة على الخلق بغير حق . ومن ابتلي بمثل هذه المحن؛ فصبر، ولم يجاز على الإساءة بمثلها، بل حفظ لسانه، وصان أعراض إخوانه وإن بغوا عليه؛ كانت له العاقبة الحميدة، وعاد ذامه حامدًا، وهاجره واصلا، وكانت له العقبى الحسنة قال تعالى: (ولمن صبر وغفر إن ذلك لمن عزم الأمور) . كيف وجملة من الخلافات المعاصرة بين من ينتسب إلى مذهب السلف من طلبة العلم: الكلامُ فيها ممَّا يزيدها اشتعالا، وإحراقا، ونارًا، وأُوَارًا؛ لوجود من يبغي في كلامه، أو يتجاوز في بعض أحكامه من الخائضين بحق، أو بغير حق . فمثل هذه (الهيشات) ينبغي للعاقل أن لا يضيع وقته، وعمره فيها؛ فإنه يكثر فيها (الجدال المذموم) الذي يدخل في عموم قول الله تعالى: (ومن الناس من يجادل في الله بغير علم ولا هدى ولا كتاب منير# ثاني عطفه ليضل عن سبيل الله) . وعليه أن يشتغل بالعبادات، ومن أعظمها: العلم النافع درسا، وتعليما، ونشرا، ويعالج ما أمكنه بطريق الحكمة، والموعظة الحسنة كما أمر الله تعالى في قوله: (ادع إلى سبيل ربك بالحكمة والموعظة الحسنة وجادلهم بالتي هي أحسن) . والحَلُّ بإسنادها إلى أولى الأمر وهم العلماء بالكتاب، والسنة، كما أمر الله تعالى عباده في قوله تعالى: {وَإِذَا جَاءَهُمْ أَمْرٌ مِنَ الْأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُوا بِهِ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى الرَّسُولِ وَإِلَى أُولِي الْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ الَّذِينَ يَسْتَنْبِطُونَهُ مِنْهُمْ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ لَاتَّبَعْتُمُ الشَّيْطَانَ إِلَّا قَلِيلً} [النساء: 83]، وغيرها من الآيات . ومن لم يظهر له وجه الصواب لزمه الصَّمت؛ حتى يظهر له الحقُّ بين المختلفين، وهذا فرضه اللَّازم له، ولا يجوز له الخوض بجهل، أو عصبية جاهلية . وأنصح بقراءة رسالة الإمام أبي محمد ابن قدامة رحمه الله في المحنة التي جرت لأهل السنة الحنابلة في القرن السادس في مسألة (تخليد أهل البدع فِي النار ممن وقعوا في الكفر) . هذا: وينبغي لأهل العلم، والعقل، والحكمة معالجة خلافات طلبة العلم النَّافع من أهل السنة والجماعة بما يرجع به المخطئ، ويتوب به المذنب، وتجتمع به الكلمة، والله الموفق، وهو الهادي إلى سواء السبيل . وصلَّى الله وسلم على نبيَّنا محمد، وعلى آله، وصحبه، وسلم . ليلة الثلاثاء ال15/المحرم /1448هـ ════ ¤❁✿❁¤ ════ 🔸 قناة الشيخ. أبي العباس الشحري 🔸 https://t.me/aleabaas

السُّؤال /48/ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ... . سؤال: هل عدم رد طالب العلم على أحد المنحرفين في بلاده الذين كانوا على السنة ثم انحرفوا عنها يُعتبر تخذيلا منه للحق والدعوة؟ مع العلم أن ذلك المنحرف قد رد عليه كثير من المشايخ والدعاة في البلاد وخارجها وبينوا ما عنده من انحراف وضلال. لأن بعضهم حكم على هذا الطالب بأنه مخذل وصار يحذر منه بدعوى أنه اختفى في فتنة ذلك المنحرف ولم يرد عليه ولم ينصر الحق واهله. علما أن ذلك الطالب له ردود كثيرة على كثير من المخالفين ، وله كتابات ومشاركات كثيرة في الرد على المخالف يعني ليس من منهجه ترك الردود والتزهيد فيها . أفتونا مأجورين جزاكم الله خيرا الجواب : الحمد لله رب العالمين، والصلاة، والسلام على أشرف الأنبياء، والمرسلين سيِّدنا محمد، وعلى آله، وصحبه، وسلَّم . أما بعد: فإنَّ الرد على المخالف أصل من أصول الإسلام، وسبيل من أعظم سبل الدعوة إلى الله تعالى . قال الله تعالى: (ادع إلى سبيل ربك بالحكمة والموعظة الحسنة وجادلهم بالتي هي أحسن) . وهو من العمل بشعيرة الأمر بالمعروف، والنهي عن المنكر التي هي من أعظم الشعائر الإسلامية، والحقائق الدينية، قال تعالى: (كنتم خير أخرجت للناس تأمرون بالمعروف وتنهون عن المنكر) . وأصل هذا الباب - لمن قام به على وجهه- من الجهاد في سبيل الله تعالى، وبه تتم حماية الدين من غوائل الانحرف ومسالكه؛ وبه يتحقق الذب عن حمى الشريعة، كتابا، وسنة، وبه تتمُّ حراسة الدِّين . وهذا الباب لابد أن يكون : بـ/1/قصدٍ حسن، وإخلاصٍ لله عز وجل . /2/وأن يكون بعلم تام . /3/ وأن يكون بالتي هي أحسن (إلا الذين ظلموا منهم) . هذه أصول ثلاثة عظيمة متى ما دخل عليها الخلل فسدت هذه العبادة، وكانت وبالا على صاحبها . وكم من قائم بهذه الشعيرة لم يكن له نية صالحة حسنة في إنكاره، أو رده، ولا صدقٌ مع الله تعالى في سعيه، وقيامه؛ فخذل أعظم خذلان، وربما ظهر عليه أهل الباطل المحض؛ لسوءٍ في نيته، وكدرٍ في سريرته، والله لا يحب إلا العمل الصالح الخالص له وحده لا شريك له . وكم من متصدر لهذا الباب، وليس له به علم تام، ولا قدرة على الاستدلال، ولا مكَنَة في ردِّ حجج المخالف؛ فيكون فساده أكثر من إصلاحه، ويكون عونًا لأهل الباطل وهو يحسب أنه يحسن صنعًا . وكم شنَّع المبطلون بكلام ناس - غفر الله لهم- ممَّن لو سكت كان سكوته خيرا له، ولأهل السنة . وقد أحسن في بيان مراتب هذا الباب، وأحوال الناس فيه : شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله؛ فقال : «وليـس كـل من وجـد العِلـم قـدِر على التعبِـيرِ عـنـه، والاحتِجـاجِ لـه؛ فالعِـلـم ”شيءٌ“، وبـيـانـه ”شيءٌ آخـر“، والمناظـرة عنه، وإقامـة دلـيـلِـهِ ”شيءٌ ثالـثٌ“، والجـواب عن حجـةِ مخالِـفِـهِ ”شـيءٌ رابـعٌ“» انتهى . ولهذا منع الإمام مالك رحمه الله بعض تلاميذه الأئمة من الرد على بعض المخالفين . ومما لا يجوز بحال البغي، والاستطالة على النَّاس بحقٍّ، أو بباطل؛ ولهذا كان من أخلاق أهل السنة والجماعة اجتناب هذا : جاء في «العقيدة الواسطِية» في صِـفـةِ أهل السنـةِ والـجـمـاعـةِ، أهـلِ الحديـثِ ما حرفه : «وينهون عن: ”الفخرِ“، و”الخيلاءِ“، و”البغيِ“، و”الاسـتِـطـالـةِ“ على الخلـقِ بِحـق، أو بِغـيرِ حـقٍ» انتهى . ومن البغي والاستطالة إلزام أهل العلم بالردِّ على كلِّ مخالفة، وكل مبطل، وهذا ليس في قدرة البشر؛ فإن قام به من يحسن، سقط الواجب الكفائي عن غيره . فمن حمِد الرد على أهل الباطل، وشكره لم يلزمه أن يرد هو - أيضا-؛ ومن ألزمه بذلك مع حصول الكفاية؛ فهو من نوع الاستطالة على الخلق . كيف إذا كان هذا المطلوب منه عاجزا، أو ضعيفا، أو لا يحسن تحقيق علم هذه المسائل، أو لا يحسن إقامة الدليل، أو لا يحسن كشف شبهة المخالف، ومناقشة دليله ؟! . ولو فتح هذا الباب لم يسلم كبير أحد من أهل العلم . نعم قد يكون بعض الناس مقصِّرا في هذا الباب مع فضله، وعلمه، وقدرته؛ فهذا منه ذنب من الذنوب، وتقصير في الواجب عليه؛ فالواجب في حقِّه: نصحه، وإعانته على فعل ما يجب عليه، والتَّرفُّق به، والصبر عليه . ومن الاستطالة عليه بـ(حق): هجره، والتَّحذير منه؛ لتقصيره في القيام بالواجب عليه . فهذا كالذي رأى في قبلة مسجد انحرافا يسيرا؛ فأراد هدم هذا المسجد وفعل !!، وعطل الجمعة، والجماعة، وربما عجز عن بناء المسجد، وكان يمكنه سلوك طرق أخرى يتحقق بها المقصود الشَّرعيُّ . على أن الانحراف اليسير لا يبطل الصَّلاة !! . فتكون مثل هذه العقوبات من الظلم، والبغي مع ثبوت الذنب على الفاعل المقصِّر في الواجب، وهذا من نوع الاستطالة على الخلق بحقٍّ؛ فتدبر .

ዳሩ ሱና ኦንላይ ቂርአት ከቃኢዳ ጀምሮ በተጅዊድ ያስቀራል። በተጨማሪ የአቂዳና የፊቅህ ኪታቦችን መማር ይችላሉ። ትምህርቱ ሴት በሴት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ፈጥነው ይመዝገቡ። ለመመዝገብ 👉 @Darusun