ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Open in Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
319
Subscribers
-124 hours
-27 days
+5430 days
Posts Archive
ከልብ የመነጨ ዱዓ፦
👉 አላህ ሆይ! እነዚህን ባሮችህን አስደስታቸው፣ጭንቃቸውን ግፈፍላቸው፣ተስፋቸውንና ምኞታቸውን ሁሉ አሳካላቸው፣ጀነትንም መኖሪያቸውና ማረፊያቸው አድርግላቸው፣ከማንኛውም ህመምና በሽታ አርቃቸው ያረብ፤ በ ጀነትም ውስጥ ከእነሱ ጋር አሰባስበኝ።
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ያስደሰተውን ይረሳል
....የደግነት ውለታ ቢረሳም ደግ ሆነን ለመረሳት እንወስን...
በመልክምነታችን ሰዎች ላያመሰግኑን ቢችሉ ወይም ውለታህን ላያስተውሱት ቢችሉም አትፍረድባቸው ሰዎች ከጠቀማቸዉ ይልቅ የተጠቀመባቸውን ፣በፍቅር ከተንከባከባቸው ይልቅ የበደላቸውን አይረሱም።
⭕️በህይወት ሳለን በሚዛን እንኑር አንዳንዱ ጋር ቸኩለን አንዳንዱ ጋ ፈጥነን ዋጋ አንክፈል።
.....አንዳንዱ ጋር ጠግበን አንዳንዱ ጋ ትህትናችን በዝቶ እንዳያስገምተን።
....አንዳንዱ ጋር ጥያቄ አብዝተን አንዳንዱ ጋ ደግሞ ዝምታችን በዝቶ ፊት እንዳያስነሳን እንጠንቀቅ!!
⭕️አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አብዝተን አንዳንዱ ጋ ደግሞ ግዴለሾች ሆነን ሰው እንዳናስመርር.......
#አንዳንዱ ጋር ጨዋነታችን በዝቶ አንዳንዱ ጋ ብልግናችን ጎልቶ ሰው እንዳንረብሽ ራሳችንን እንፈትሽ!!
⭕️አንዳንዱ ጋር አማኝነታችን ከልክ አልፎ አንዳንዱ ጋ አህዛባዊ ባህሪያችን አነጋጋሪ ሆኖ ሰው እንዳናወዛግብ
.... አንዳንዱ ጋር ቸርነታችን አንዳንዱ ጋ ስስታችን ሰው አስገርሞ እንዳያስገምተን በማስተዋል እንኑር።
✅የሰው ልጅ በባህሪው ያሳቀውን ይረሳ ይሆናል እንጅ ያስለቀሰውን ግን በፍፁም አይረሳምና መጥፎ ሆነን ከምንታወስ ደግ ሆነን ሰው እንድረሳን ፈቃደኞች እንሁን እላለሁ!!
...N.....✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«የነብዪﷺ ታላላቅ ዘመቻዎች ሲወሱ»
❶➛በሁለተኛው አመተ-ሒጅራ «ታላቁ የበድር ጦርነት»።
❷➛በሶስተኛው አመተ-ሒጅራ «የዑሁድ ዘመቻ»
❸➛በአራተኛው አመተ-ሒጅራ«የበኒ ነድር ዘመቻ»
❹➛በአምስተኛው አመተ-ሒጅራ«የኹንደቅ ጦርነት/የአህዛብ ዘመቻ»
➎➛በስድስተኛው አመተ-ሒጅራ «የሁደይቢያ ስምምነት»
➏➛በሰባተኛው አመተ-ሒጅራ «የኸይበር ዘመቻ»
❼➛በስምንተኛው አመተ- ሒጅራ «የመካ መክፈት ድል እና የሁነይን ዘመቻ»
❽➛በዘጠነኛው አመተ-ሒጅራ «የተቡክ ዘመቻ»
➒➛በአስረኛው አመተ-ሒጅራ «አሳዛኙ የስንብት ሐጂ»
➓➛በአስራ-ዓንደኛው አመተ-ሒጅራ «አለም የጨለመችበት ክስተት #የነብዩﷺ_ህልፈት»
....ኑረዲን አል-ዓረብ...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ይቆጥቡ ይሸለሙ¡
~
ገንዘባችሁን ባንክ ውስጥ ዘግታችሁ ብታስቀምጡት በየቀኑ እየሞተና ዋጋው እየረከሰ እንደሚሄድ አልገባችሁም? ዛሬ ባንክ ውስጥ የከተታችሁት መቶ ሺህ ብር ነገ ሳንቲም እንደሚሆን አልተረዳችሁም? የዋጋ ንረት የተቀመጠውን ብራችሁን በየቀኑ እየበላው፣ የመግዛት አቅሙን ደግሞ መሬት ላይ እየጣለው ነው!
ዝም ብሎ ባንክ የተቀመጠ ብር ሀብት ሳይሆን የጅልነት ቁጠባ ነው። ገንዘብ የሚጠበቀውና የሚያድገው በስራ ላይ ሲውል ብቻ ነው።
ነገ ዋጋ የሌለው ወረቀት ይዛችሁ ከመቆጨታችሁ በፊት፣ ብራችሁን ከባንክ አውጡና አሁኑኑ ወደሚጨበጥ እቃና ሀብት ቀይሩት!
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች
ኡስታዝ ዐብደ ሸኩር (አቡ ፈውዛን)
ርዕስ:- ትክክለኛው የደስታ መገኛ
በአቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስ ቻናል
በቀን 12/11/2018 የተደረገ ሙሀደራ
https://t.me/Abu_Fehd_Online_Market
Repost from TewhideAcadamy
140 ሓዲሶች ክፍል 1
ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ ሑዘይፋ መስጂድ
የኪታቡን ፒዲኤፍ ለማግኘት
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/8600
Repost from Dr. Seid Musa
በደዕዋህም ህዝብን አስቀድም። አንዳንዶች ህዝብን በማንቃት መሰረታዊ ጉዳይ ላይ የረባ ተሳትፎ ሳይኖራቸው በፊትና ጊዜ ከፊት የሚሰለፉ አሉ። ወንድሜ ሆይ! ከልቤ ነው የምመክርህ። የምታምንበትን ሐቅ አግባብ በሆነ መልኩ ማድረሱ እንዳለ ሆኖ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሰፊውን ህዝብ የሚጎዳ ወይም የዘነጋ አካሄድ እንዳይኖርህ አስተውል።
8. እራስህን ለመቻል ጣር:—
በዱንያህ እራስህን ለመቻል የምትችለውን ሰበብ አድርስ። መቼም በራስ የመብቃቃትን ዋጋ አልነግርህም። ከሰው የሚጠብቅ ሰው አቋሙን ለድርድር ያቀርባል። የማያምንበትን ያራምዳል። ዛሬ ስንቶች መሰሉህ በሚውሉልህ ውለታ እጅህን ጠምዝዘው፣ ሐያእ አስይዘው የአቋማቸው ማራመጃ ሊያደርጉህ የሚጥሩት?! ስለዚህ ለቀልብህ ሰላም፣ ለደዕዋህ ንፅህና ስትል እራስህን ለመቻል ሞክር። ዛሬ ባይሆንልህ እንኳ በሚገባ አስብበት።
9. ከመንጋዊ አስተሳሰብ ራቅ:—
ስትወድም፣ ስትጠላም፣ ስትቀርብም፣ ስትርቅም፣ ስታደንቅም፣ ስታወግዝም አላህን እየፈራህ ይሁን፡፡ ውስጥህን ሳታዳምጥ፣ በተቅዋ ሳትፈትሽ ሌሎች ስላደረጉ በመንጋ አትነዳ፡፡ አላህን ፈርተህ ስለምታራምደው አቋም ትችት አያስፈራህ፤ ጭብጨባም አይሙቅህ፡፡ ዋናው ነገር ከጌታህ ዘንድ የማያሳፍርህ መሆኑን ገምግም፡፡ ከዚያ በመለስ ያለው ሁሉ እዳው ገብስ ነው፡፡
10. የኢኽላስህን ነገር አደራ
ዲንን መማርም ህዝብን ማስተማርም ልክ እንደ ሶላቱ፣ እንደ ፆሙ ትልቅ ዒባዳ ነው። ልክ ለሶላትና ለፆምህ ኢኽላስ እንደሚያስፈልግህ በመማርና ማስተማር ላይም ኢኽላስን አትዘንጋ። በደዕዋህ ስምና ዝና፣ ከንቱ ውዳሴ የምትሻበት ከሆነ አትጠራጠር አደጋ ላይ ነህ። ልፋትህም ፍሬ አያፈራም። ደግሞም እወቅ! ኢኽላስና እልህ፣ ትጋትና ብሽሽቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አላህን ከማሰብ ይልቅ ሌሎችን ማብሸቅ፣ ከንፁህ እሳቤ ይልቅ እልህን ብቻ ማሰብ ልፋትህን መና የሚያስቀር ነው። በሌላ በኩል ደዕዋን እንጀራቸው ያደረጉ ሰዎች አሉ። የደዕዋቸው የትኩረት መስክ ሰፊው ህዝብ ሳይሆን ብር ያለው ላይ የሚያነጣጥሩ፣ ህዝብን ችግሩን እየነገሩ ስሜቱን መጋፈጥ ሳይሆን የእለት ደስታውን በማስቀደም መወደስና መደነቅን የሚሹ ሰባኪዎች ከብዙም የበዙ ናቸው። የነዚህን ሰዎች ጥፋት አትድገም። ብልጥ ማለት እራሱ ላይ እስከሚደርስ ሳይጠብቅ ከሌሎች ሁኔታ የሚማር ነውና።
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Dr. Seid Musa
ጥቂት ነጥቦች፣ ለዒልም ፈላጊዎች
~~~~~~~~~~~~~~
መቼም የዒልም አንገብጋቢነት ለማናችንም የሚሰወር አይደለም። በተለይም በዚህ ጅህልና በተንሰራፋበት፣ ውዝግብ በነገሰበት፣ ሺርክና ቢድዐ በተስፋፋበት ዘመን የእውቀት አስፈላጊነት ለማንም አይሰወርም። ሰው ሁሉ ማወቅን ይመኛል። ነገር ግን እውቀት በትጋት እንጂ በምኞት አይገኝም። ምኞታችንን እውን ለማድረግ እንቅፋቶች ቢበዙብንም የምንችለውን እናድርግ። በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጥቂት ማለት ወደድኩኝ።
1. መማርን አትሰልች፡-
ቁጭ ብለህ ኪታብ ተማር። ዒልምን ለመቅሰም ቀዳሚው መንገድ ከሚያስተምር ብቁ ሰው ዘንድ መቅራት ነው። ባይሆን የሚያስተምርህ ሰው በእውቀቱ ብቁ፣ በአካሄዱ ጤነኛ መሆን አለበት። “ይሄ እውቀት ዲን ነው። ዲናችሁን ከማን እንደምትወስዱ አስተውሉ” ይላሉ ኢብኑ ሲሪን ረሒመሁላህ።
- ባይሆን ቅደም ተከተል ጠብቅ። ያላቅምህ ዘለህ ከፍ ያለ ኪታብ አትጀምር። አቅምህን አገናዝበህ ከስር ጀምረህ ተማር።
- ባይሆን ስትቀራ የለብ ለብ ሳይሆን አድምተህ ቅራ። “ይህን ኪታብ ጨርሻለሁ” ለማለት ሳይሆን በኢኽላስ ቅራ። ለሌሎች ለማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ ቅራ። የቀራሀውን ሙራጀዐ (ክለሳ) ማድረግ ይልመድብህ። የዛሬው ኪታብ በሚገባ ከተያዘ በቀጣይ የምትማረው ኪታብ ክብደት በብዙ ይቀንሳል። ሙሉ በሙሉ አዲስ አይሆንብህም። አያያዝህ ለብ ለብ ከሆነ ግን ኢኽላስህን ታጣለህ። ከሰው ዘንድ ታፍራለህ። ጊዜህንና ልፋትህን ታባክናለህ።
2. አዳምጥ፡-
ቁጭ ብለህ የምትማርበት በአቋሙ ጤነኛ፣ በእውቀቱ ብቁ ሰው ካላገኘህ እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ። ዘመናችን ዒልም ለሚፈልግ ሰው መንገዶቹ የገሩበት ዘመን ነው። የታላላቅ ዑለማዎችን ትምህርቶች ከቤትህ ቁጭ ብለህ እያዳመጥክ መከታተል ትችላለህ። ዐረብኛው የሚቸግርህ ከሆነ የምታምናቸውን ኡስታዞች ትምህርት በተገራልህ ቋንቋ ቤትህ ሆነህ በድምፅ መከታተል ትችላለህ። ስለዚህ በቴሌግራም፣ በዋትሳፕ፣ … ወይም ከጓደኛ በመቀባበል ወጥረህ ተማር።
ሪኮርድ መከታተልን የሚነቅፉ ሰዎች ሊገጥሙህ ይችላሉ። “እርሱኮ ሪኮርድ እንጂ ሸይኽ የለውም” ሊሉህ ይችላሉ። ለእንዲህ አይነት ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ከስሜቱ ጋር ያልገጠምክለት ሰው አቃቂር ማውጣቱትን አያቆምም። የውንጀላው መነሻ በአመዛኙ አካሄድህ ከአካሄዳቸው አለመግጠሙ ነው። የነሱን ሰዎች በጭፍን እንድትከተል ለሚሹ አካላት ቅንጣት ታክል ቦታ አትስጣቸው። በሽተኛ ወይም ብቁ ያልሆነ ሰው ዘንድ ተቀምጠህ ከምትማር ያለ ጥርጥር ሁነኛ የሪኮርድ ደርሶችን ብትከታተል ይመረጣል።
3. አንብብ፡-
ኪታቦችን አንብብ። ሹሩሓትን አገላብጥ። ፈታዋዎችን ተመልከት። ካለህ በቀጥታ ኪታቦችን ተጠቀም። ከሌለህ መክተበተ ሻሚላን ተጠቀም። እንዲያውም መክተበተ ሻሚላ በዚህ ዘመን ትልቅ ኒዕማ ነው። አጠቃቀሙን ቻልበት። ከዚህ የተረፈውን ኢንተርኔት ተጠቀም። ጎግልን ጎልጉል። ፒዲኤፍ አውርድ። በዚህ ዘመን ጦለበተል ዒልም ሆኖ አነሰም በዛ እነዚህን የማይጠቀም ለማግኘት ይከብዳል። በነዚህ ሰበቦች መጠቀምህን ሊያጣጥል የሚሞክር ካለ እራሱን በከንቱ የሚቆልል ግብዝ ነው።
በተቻለ መጠን ንባብ ላይ ብቻ ጥገኛ አትሁን። ስለዚህ ቀጥታ መማር ስትችል ንባብ ላይ ብቻ አትንጠልጠል። ቁጭ ብሎ መማር ከተገኘ “ማር ሽጠው ምን ይበሉ?!” ባይሆን ደርስህን እየተከታተልክ ከዚያም ንባብህን እንደማዳበሪያ ተጠቀመው።
ልብ በል! በንባብ ዒልም መቅሰምህን የሚነቅፍ ይገጥምሃል። እርግጥ ነው ንባብ ቁጭ ብሎ እንደመማር አይደለም። ይሄ ተጨባጭ ሐቅ ከመሆኑም ባለፈ ዑለማዎች የሚያስረግጡትም እውነት ነው። ነገር ግን የዑለማዎቹ ሃሳብ “አታንብቡ” ለማለት አይደለም። ይህ ቢሆንማ ለምን ኪታብ ይፃፋል? ከንባብ የተኳረፉ ወይም ልብ ወለድ የሚያሳድዱ፣ በእንቶ ፈንቶ የተጠመዱ ሰዎች ንባብህን ስለተቹ ጆሮ አትስጣቸው። የማውቃቸው ተግባራዊ ምሳሌዎች ስላሉኝ ነው ይህን መጥቀሴ። እንዲያውም በንባብ እውቀትን የሚቀስሙ ሰዎችን የሚያጣጥሉ አካላትን ታዘብማ። “እኛ ቀጥታ ቀርተናል” የሚል ጉራ ከመንፋት በዘለለ ቁጭ ብለው በስርአት ሲማሩ አታያቸውም።
ባይሆን የምታነበውን እያስተዋልክ። ጤነኛ ስራዎችን እየመረጥክ። የበሽተኞችን ስራ በመከታተላቸው የተነሳ ስንቶች አፈንጋጭ አስተሳሰብ ላይ ወድቀዋል?!
4. ተግባር አይነተኛ መገለጫህ ይሁን፡-
የምንማረው ለመስራት ነው። ከዚያም ባለፈ እውቀታችንን ለማስረፅ ከሚጠቅሙን ሁነኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ባወቅነው መስራት ነው። የማይተገበር እውቀት በቀላሉ ይረሳል። ቢኖርስ ምን ሊረባ? ስለዚህ እውቀትህን በተግባር አጅበው። በብዙ መልኩ ታተርፍበታለህ።
5. የተማርከውን አስተምር፡-
እውቀትን ከሚያሰርፁ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ማስተማር ነው። በማስተማር ከተማሪዎች በበለጠ የሚጠቀሙት አስተማሪዎች ናቸው። በተግባር ጀርበው። የመማር አንዱ አላማም አውቆ ማሳወቅ ነው። ስለዚህ ያወቅከውን አካፍል። ቁርኣን ከቀራህ አስቀራ። ከዚያ ያለፈ አቅም ካለህ በደርስ፣ በሙሓዶራት፣ በፅህፈት፣… አስተምር። ታገል። ያለህን ታዳብራለህ። ክፍተትህን ለመመልከት እድሉን ታገኛለህ። ለተሻለ ትነሳሳለህ። በሐቅ ላይ ጂሃድ ታደርጋለህ። የልፋትን፣ የማስተማርን ጣእም ታጣጥማለህ።
6. ከጭፍን ተከታይነት ውጣ:—
ዑለማዎችን ውደድ። በእውቀታቸው፣ በግንዛቤያቸው ታገዝ። ባይሆን በስሜት መርጠህ አትግፋ፣ በጭፍን መርጠህ አትከተል። በመላው ዓለም እጅግ በርካታ የሱና ዑለማዎች እንዳሉ እየታወቀ አንተ ከሸይኽ ፉላን ውጭ ዓሊም የሌለ የሚያስመስል ሁኔታ እንዳይኖርህ ተጠንቀቅ። ሰለፊ የሆንከው ቁርኣንና ሐዲሥን በቀደምቶች ግንዛቤ ልትከተል፣ ከዑለማዎች ትንታኔ ውስጥ ከስሜት ነፃ ሆነህ ሚዛን የሚደፋውን ልታስቀድም እንጂ የሌሎችን ዑለማዎች ሃሳብ ቸል በማለት አንድ ዓሊም ላይ ተገድበህ የወደደውን ልትወድ፣ የጠላውን ልትጠላ፣ በሱ ቀጭን መስመር ላይ ተገድበህ ወላእና በራእ ልትቋጥር አይደለም። መቼስ አቡ ሐኒፋን፣ ማሊክን፣ ሻፊዒይን፣ አሕመድን በጭፍን መከተል ተወግዞ አልባኒን፣ ኢብኑ ባዝን፣ ዐባድን፣ ፈውዛንን፣… በጭፍን መከተል እንደማይቻል አይሰወርህም። ልክ እንዲሁ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊን በጭፍን አትከተል። “መዳኺላ” እያሉ ለሚያጠለሹ አካላት ሰበብ እንዳትሆን ተጠንቀቅ። ዑበይድ አልጃቢሪን፣ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲን፣… በጭፍን መከተልም የተለየ ብይን እንደሌለው አይጠፋህም። ልብ በል! የተቅሊድ ቡላና ዳለቻ የለም። ያለበለዚያ የሐጁሪን ጭፍን ተከታዮች አንድ ጥፋት እየደገምክ እንደሆነ እወቅ።
7. ሰፊውን ህዝብ አስቀድም:—
መቼም ህዝባችን ያለበትን ሰፊ የግንዛቤ ክፍተት አታጣውም። ይህ ከሆነ ወንድሜ ሆይ! ከራስህ ጥቅም ይልቅ የህዝብን ጥቅም አስቀድም። በዱንያህ ልትቸገር፣ ከጎንህ የሚቆም አጋር ልታጣ ትችላለህ። ቢሆንም ለዘመናት የደከምክበትን ሸሪዐዊ እውቀት እንደዋዛ ገሸሽ አድርገህ ዱንያ ውስጥ አትስመጥ። በተማርከው ወገንህን ለማገልገል የምትችለውን ሁሉ አድርግ። በዒልም ተቋማት ውስጥ አመታትን አሳልፈው በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ የሌላቸውን ወንድሞች ማየት ያሳዝናል።
👉 እነዚህን ከላይ ያሉ ፒድኢፎች Download አድርገን እናንብባቸው።በአላህ ፈቃድ ብዙ ነገሮችን እንማራለን ኢንሻአላህ።
Repost from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ]
የዒልም ደረጃ !
ታላቁ የኢስላም ሊቅና ሶሃባ አብዳላህ ኢብኑ አባስ ! ከጓደኞቻቸው ነገሮችን ፈጥኖ የመረዳት ልዩ ችሎታ ፣ የላቀ ዕውቀት ፣ ጥበብንና ብልሃትን የተላበሱ እንደነበሩ ከሶሃቦች የተመሰከረላችው ድንቅ የነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ባልደረባ ነበሩ።ከመሆኑም ጋር አንድ ጊዜ እሳቸው የማያውቁትን ሓዲስ አንድ የነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረባ እንደሚያውቅ ወሬ ሰምተው ስላደረጉት ጥረት እንዲህ ሲሉ ዘግበዋል።
በቀትር የመኝታ ሰአት ❨ቀይሉላ❫ ወደ እሱ ቤት ሄድኩ።ከቤቱ በር ላይ ካባዬን አንጥፌ እስኪነቃ ጠበቅኩት።ንፋሱ አቧራውን እያነሳ ያለብሰኝ ነበር።ብፈልግ ኖሮ እንዲፈቅድልኝ በጠየቅሁትና ያለምንም ጥርጥር ያስገባኝ ነበር። እኔ ግን እንቅልፉን መጨረስ ይችል ዘንድ መጠበቁን መረጥኩ።ሰውየውም ከቤቱ ሲወጣ እንደዚያ ሆኜ ሲያየኝ ’ አንተ የነብዩ አጎት ልጅ ! ምን ነካህ ? ብትልክብኝ ኖሮ እኔው ራሴ እመጣ አልነበር ?! አለ።ወደ አንተ መምጣት ያለብኝ እኔ ነኝ።እውቀት ተፈልጎ እንጂ እንዲሁ ራሱ አይመጣም ! አልኩት።ከዚያም ስለሐዲሱ ጠይቄው ከእሱ ተማርኩ ይላሉ።ታላቁ ሶሃቦ አብደላህ ኢብኑ አባስ።
ሶሃቦች ስንትና ስንት የዕውቀት ጥግ ላይ ደርሰው ፣ ስንትና ስንት ሐዲሶችን ለዑማው አስተላልፈው ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደረሶች ሰብስበው እያስተማሩ እንኳን ለዒልም ከነበራቸው ጉጉትና ክብር እነሱ ማውቁትን የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ንግግር አለ ከተባሉ ስንትና ስንት ኪሎ ሜትሮች ሄደው ያቺን አንዲትን ሓዲስ ተምረው ይመለሱ ነበር።ባለንበት ዘመን ዒልምን ላለመማር ምንም ምናቀርበው ዑዝር በሌለበት አላህ በያዝነው ሞባይል ዐለም ላይ ካሉ ዑለማዎች አገናኝቶን ሲያበቃ የኛ በዚህ ልክ ከኢልም መራቅና አለመማራችን የሚያሳዝን ነው።አላህ ያግራልን።
ከተወሰነ ጭማሪ ጋር ከሐያቱ ሶሃባ መፅሐፍ የተወሰደ።
✍ ሙሐመድ ኢብን ፈድሉ
~ https://t.me/Darutewhide
Repost from ከ ቁርአን አያህ...
በትምህርትሽ፣ በሪዝቅሽ፣ በትዳርሽ ወይም በህይወትሽ ተስፋ ስትቆርጪ ይህንን የአላህ ፕሮሚስ (መፍትሄ) አስቢ፡-
وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ
«አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ካላሰበበትም በኩል ይረዝቀዋል...» (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ 65:2-3)
እዚህ አያህ ላይ አላህ የተጠቀመው "መኽረጃን" የሚለውን ቃል ነው። ይህ ማለት ልክ በትምህርትሽ ፌል አድርገሽ ወይም ውጤትሽ ዝቅ ብሎ መውጫው ሲጠፋሽ፣ አሊያም #ዕድሜሽ እየገፋ ሄዶ የትዳር አጋር የሚጠይቅሽ አጥተሽ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በሆንሽበት ሁኔታ ላይ፣ አላህ ካንቺ አቅምና ግምት ውጪ የሆነ አዲስ መውጫ በር በድንገት ይከፍትልሻል ማለት ነው።
ሌላው አስገራሚ ቃል ደግሞ "ሚን ሐይሱ ላ ያሕተሲብ" (ካላሰብሽበት/ካልጠበቅሽው አቅጣጫ) የሚለው ነው። ያንቺ አእምሮ የሚፈልገው መፍትሄ በሰዋዊ ስሌትሽ 'በትምህርቴ ውጤቴ ከተስተካከለ ወይም ይሄን ሰው ካገባሁ ብቻ ነው የምደሰተው' ብለሽ ባሰብሽው ጠባብ መንገድ ብቻ ነው፤ የአላህ እቅድ ግን ያንቺ ስሌትና ሎጂክ ፈጽሞ ሊደርስበት የማይችለውን—ምናልባትም ካላሰብሽው መስክ አዲስ የስራ/የትምህርት እድል በመስጠት ወይም ጨርሶ በማታውቂው መንገድ ምርጥ የትዳር አጋር በመላክ—ተአምራዊ በር መክፈት ነው።
so, ኡኽታዬ... የአንቺ ስራ ነገሮች እንዴት እንደሚፈቱ መጨነቅ ሳይሆን፣ አላህን መፍራትና እሱን መታዘዝ (ተቅዋን) ይዘሽ መቆየት ብቻ ነው። መንገዱንና መውጫውን እሱ ራሱ በትክክለኛው ሰዓት ያሳይሻል።
just በአላህ ትዕዛዝ ላይ ቀጥ በዪ .... እሱ ካላሰብሽበት አቅጣጫ በሩን ይከፍተዋል 🚪🔓
🍂 ከ ቁርአን አያህ..Share & Join: @Ke_quran_ayah
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
ኡስታዝ ላስታውስህ!
አንተ ዲናዊ ትምህርትን በማስተማር ላይ የተሰማራሃው ወንድሜ ስለያዝከው ስራ ታላቅነትና ከፍ ያለ ደረጃ ሰፊ ማብራሪያ የምትሻ አይመስለኝም። ባይሆን የተከበርከው ኡስታዝ ሆይ! የኢኽላስን ነገር አደራ አደራ አደራ እያልኩ ከታች በሰፈሩት ነጥቦች ላስታውስህ ወደድኩ።
1. የምትሰጠው ሸሪዓዊ ትምህርት የአላህ ፊት ብቻ የሚፈለግበት ትልቅ አምልኮ መሆኑን ተገንዝበህ ይህንን የሚያበላሹ ወይም የሚያጓድሉ እሳቤዎችን ከልብና አዕምሮህ አውጥተህ ልትጥላቸው ይገባል።
2. የምትሰጠው ደርስ ጥንቃቄ የተሞላበትና በቂ ጥናት ያደረግክበት መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብሃል። ማለትም ትምህርቱን ከማቅረብህ በፊት "እኔ ምን ያክል ተገንዝቤዋለሁ?" የሚለውንና በምን መልኩ ማቅረብ እንዳለብህ በቂ ዝግጅት ልታደርግ ይገባል።
3. ስለማታቀው ወይም እርግጠኛ ስላልሆንክበት ነጥብ ስትጠየቅ "አላቅም! አላሁ አዕለም" ማለት ይልመድብህ። አረ አንዳንዴ ስለምታቀውም ጉዳይ "አላሁ አዕለም" በማለት ተማሪዎችህን "አላቅም" ማለት ብታስተምራቸው መልካም ነው።
4. እንደሚታወቀው ሰዎች ስንባል አንዳችን ከአንዳችን ያለን የዕውቀት አይነትና መጠን ይለያያልና አደራ አደራ የምልህ ምንም ያህል የተማሪዎች ግፊት ቢኖርብህም እንኳ የማይመጥንህንና አሳምረህ የማታቀውን የዕውቀት ዘርፍም ይሁን አጀንዳ አስተምራለሁ አብራራለሁ ብለህ እንዳትጣጣር።
ምክኒያቱም ይህን ማድረግህ የሚከተሉትና መሰል ከባባድ አደጋዎችን ያስከትልብሃልና፦
1ኛ በአላህ ላይ ያለዕውቀት ለመናገር ሊያጋልጥህና አላህ እርም ካደረጋቸው ከባባድ ጥፋቶች፣ የሽርክ ታላቅ ወንድም ከሆነውና { وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ } ከሚለው ውስጥ ሊዘፍቅህ ይችላል።
2ኛ ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው ዕውቀታዊ አመኔታ ሊሳሳና ምናልባትም አሳምረህ በሚገባ ያስተማርካቸው ትምህርቶችህም ሁሉ ሳይቀሩ ለሰዎች ተደራሽ እንዳሆኑ እንቅፋትና ታላቅ ግርዶሽ ሊሆንብህ ይችላል።
3ኛ የማታቀው ነጥብ ውስጥ ገብተህ በግምት ማውራት ከለመደብህ "አላቅም" የሚለው ወይም የአላዋቂነትህ ባህሪ እየደበዘዘ ሂዶ ይጠፋብህ ወይም ትረሳውና እራስክን እንደ ሙሉ ዓሊም ትቆጥራለህ። ይህ (الجهل المركب) ደግሞ መዘዙ የከፋ መሆኑ አይሰወርህም ብየ አስባለሁ።
4ኛ ይህ በዙሪያህ ባሉ ሰዎች ግፊትና ሞራል ተነሳስተህ እንደዋዛ የተያያዝከው የማታቀውን ጉዳይ የመዳፈር አደጋ ባንተ ላይ ብቻ የሚቆም ጥፋት ሳይሆን ነገ ከነገ በኋላ ያለ በቂ ዕውቀት የገባህበትን አጀንዳ ወዳጅነትና ጠላትነት መስርተህበት የሙስሊሞች መከፋፈል መንስኤ ልትሆን ትችላለህ።
ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ በሀገራች ሀበሻ በሰለፊያ ስም እየተፈለፈሉ ያሉ ጀማዓዎችን ተመልከት። አዎ! አሁን ያለው የአንጃዎች መበራከት ከተፈጠረባቸው ምክኒያቶች አንዱና ግንባር ቀደሙ ኡስታዞች በሚያቁት ነጥብ ብቻ አለመገደባቸውና በማይመጥናቸው ወይም በቂ ግንዛቤ በሌላቸው መንሃጃዊ አጀንዳ ውስጥ ገብተው የተሳሳተ አቋም በመያዛቸውና በዚህም ፈር የለቀቀ ድምዳሜያቸው ወዳጅነትና ጠላትነትን መመስረታቸው ነው።
አንድ ሸይኽ ስለሆነ የዕውቀት ዘርፍ ለምሳሌ በበሐዲስ ወይም በተፍሲር ሰፊ ጥናት አደረገ ማለት "እርሱ የማያቀው የዕውቀት ዘርፍ የለም" ማለት አይደለም። እንደዚሁ አንድ ኡስታዝ የሆነ ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ስለወጣና አማረኛን ከሽኖ ስለተናገረ መንሃጃዊ ግንዛቤው የተስተካከለ ነው ማለትም አይደለም። ስለሆነም ሁሉም ባወቀውና በአቅሙ ልክ ቢተነፍስ መልካም ነው እላለሁ። አላሁ አዕለም!
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from አዋሽ 7 የሱና መድረክ - ዓፋር منصة السنة في أواش ٧ - عفر
ሱፍያ እና ሰለፍያህ ,,{{በሸኽ ሙሐመድ ወሌ ረሂመሑሏህ ተዓላ!!}}⤴️⤴️⤴️
https://t.me/Selefia_Dawa_Be_Logia_Ena_Samara
Repost from 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
🔖አላህ አበባዎችን ሲፈጥር ከቦታቸዉ
ሳይንቀሳቀሱ ባሉበት ሆነዉ መልካም መዓዛን እንዲሰጡ አድርጓ ነዉ።ከቦታቸዉ ከተንቀሳቀሱ ይጠወልጋሉ መዓዛቸዉ ይጠፋል ይሞታል ሙስሊም ሴቶችም ከቤታቸዉ ጋ እንዲህ ናቸዉ።Repost from Zplay
⭕️አዲስ የቻናል ምዝገባ!
📣 ለኢስላሚክ ቻናል ባለቤቶች በሙሉ
📣 ቻናላችሁን በአጭር ጊዜ የምታሳድጉበትና ወደ ብዙ ሰዎች ዘንድ የምትደርሱበትን ምርጥ ዕድል ይዘንላችሁ መጥተናል‼️
✅ መሟላት ያለባቸዉ መስፍርቶች:-
1️⃣ ኢስላሚክ ቻናል የሆነ❴ጀማሪ ብትሆኑም❵
2️⃣ እዚህኛው👇 ፎልደር ላይ ቻናላቹ ያልተካተተ ብቻ
⭕️ቻናላችሁ እንዳለ ለማወቅ👉 አንድ ጊዜ ተጫኑ
3️⃣ ለንግድና ማስታወቂያ ያልተከፈተ።
✅ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ከታች ባለው አድራሻ ቻናላችሁን ማስመዝገብ ትችላላችሁ👐
ለመመዝገብ👉 @ISLAM_WAVE1 ⚡
Repost from N/a
+3
⚠️ ሁለተኛ ዙር የምዝገባ ፕሮግራም ⚠️
🔋✅ የዕውቀት ጉዞዎን በ«ዙል ቢጃደይን» ይጀምሩ!
ንፁህ የሆነችውን የሰለፎች መንገድ በቅደም ተከተል (ሲልሲላ) ለመማር ለሚጓጉ በሙሉ፤ በቤታችሁ ሆናችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑበትን የ ONLINE መድረሳችንን ይቀላቀሉ።
በ«ዙል ቢጃደይን የ ONLINE መድረሳ» የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር ~ኢን ሻ አላህ~
🕋 ▬ተውሒደል ኡሉህያ ▬ 🕋
🔴 ኹዝ ዐቂደተክ
🔴 ሠላሠቱል ኡሱል
🔴 ቀዋዒዱል አርበዕ
🔴 አል ዋጂባት
🔴 ኪታቡ ተውሒድ
🔴 ከሽፉ ሹብሀት
🔴 ማዕና ላኢላሀ ኢለላህ
🌙 ▬ አስማእ ወሲፋት ▬🌙
🔵 ሉመዓቱል ኢዕቲቃድ
🔵 ዐቂደቱል ዋሲጥያ
🔵 መንዙመቱ ሱለሚል ኡሱል
🔵 ላምየቱ ኢብኒ ተይሚያህ
🔵 ሀኢየቱ ኢብኒ አቢ ዳውድ
🛤 ▬▬ መንሀጅ ▬▬ 🛤
🟢 ሚን ኡሱሊ ዐቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀመዓ
🟢 ሸርሑ ሱና
🟢 ኩን ሰለፍያ
🟢 ሚንሀጁ ፊርቀቲ ናጂየቲ
⚖️ ▬▬▬ ፊቅህ ▬▬▬⚖️
🟣 መቶ ሀዲስ
🟣 አርበዑን አን-ነወዊያ
🟣 ሹሩጡ ሶላት
🟣 ኡምደቱል አሕካም
🟣 አዱሩሱል ሙሂማ
🟣 ሚንሀጁ ሳሊኪን
📖 ▬▬▬ ሲራ ▬▬▬ 📖
🔶 ኡርጁዘቱል ሚኢያ
🔶 ኹላሶቱ ኑሪል የቂን
🔶 ሲረቱል ሙስጠፋ
🛡 ▬▬አዝካር ▬▬🛡
💎 አዝካሩ ሶባሕ ወል መሳዕ (ሊሸይኽ ረስላን - ከሒፍዝ ጋር)
💎 ሂስኑል ሙስሊም (ከሒፍዝ ጋር)
🚨 ማሳሰቢያ:
① ሁሉም ኪታቦች ሲቀሩ ተስሚዕ ማድረግ ግዴታ ነው። ሌሎች ኪታቦችን እንደ ሁኔታው እየታዩ የሚጨመሩ ይሆናል፣ ኢን ሻ አላህ።
② ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ሳይሞላበዎት ይመዝገቡ
③ ሴቶች በሴቶች ፣ ወንዶች በወንዶች ግሩፕ ብቻ ነው መከታተል የምትችሉት።
ለሌሎች ሼር አድርጉት👉 ለመመዝገብ: @Ansi8800 👉 የቴሌግራም ግሩፓችንን ለመቀላቀል: https://t.me/zulbijadeyinnn0088 አላህ የዒልም ጉዞን ያግራልን!
Repost from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ]
ዳዕዋ ላይ ስትሰማራ አቃቂር ይፈለግልሃል ! ያለ ብቻ ሳይሆን የሌለም ይለጠፍብሃል !
🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ
~ t.me/Darutewhide
