en
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

Closed channel

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
548
Subscribers
-224 hours
+177 days
+5730 days
Posts Archive
የተስፋ ብርሃን በወንጀል ለጨቀየች ነፍስ እረ ​ተስፋ አንቁረጥ - ፈጽሞ አንድከም፣ ከአላህ ራህመት - ተስፋ አይታጣም፤ "ደጋግመን ስናጠፋ - እንዴት ይምረናል?" የሚለው ሰይጣን ነው- ሊያርቀን ይጥራል። ​የአላህ ይቅርታ - ባህር ነው ሰፊ፣ የባሪያውን ጥፋት - ቶሎ ብሎ አጥፊ፤ ሺህ ጊዜ ብንወድቅ - ሺህ ጊዜ እንነሳ፣ "ማረኝ" እያልነውም - ተውበትን አንርሳ። ​ጥፋት የሰው ልጅ - ስህተት አይጠፋም፣ አላህ ግን መሐሪ -ወንጀልን አይቆጥርም፤ ባሪያው ተጸጽቶ - እጁን ሲዘረጋ፣ ይቀበለዋል - በራህመት በጸጋ። ​የወንጀል ማጠቢያ - የተውበት መድረሻ፣ ለቆሰለው ልባችን - ይሆናል   ማደሻ፤ ወንጀል እየሰሩ - "ማረኝ" ማለት ነው፣ የአማኞች ጌጥ - ይሄ ጸጋቸው ነው። ​እወቁ ወገኖቼ - ጌታችን አዛኝ ነው፣ ከእናት በበለጠ - ለእኛ ራህሩህ ነው፤ ስለዚህ አንፍራ - ተውበትን አንዘንጋ፣ በእዝነቱ ጥላ ስር - ሁሌም እንጠጋ።

╭─••──═••═─••─╮ ✒️ኡሚዬ ይቅርታ!🖌 ╰─••──═••═─••─╯ ላሳመምኩሽ ህመም ስትወልጂ ላማጥሽው እኔን በማሳደግ ብዙ ለደከምሽው ያኔ ላስቸገርኩሽ ልጅነት ሸውዶኝ ድካም ልፋትሽን እንዳላየው ጋርዶኝ ይቅርታ እልሻለሁ ደግሜ ደግሜ እኔን በማሳደግ ለጨረሽው እድሜ ይቅርታ ጠይቄሽ ጠብቃለሁ ምላሽ እኔን በማሳደግ ለጠቆረው ገላሽ ያኔ ያሳዘንኩሽ የነጠኩሽ ደስታ አሁን ነው የገባኝ ኡሚዬ ይቅርታ! https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk