🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Открыть в Telegram
Больше
Страна не указанаКатегория не указана
1 376
Подписчики
+1824 часа
+3637 дней
+64630 дней
Архив постов
Repost from قناة أبو عمران الخميسي لنشر السنة والتوحيد
🖋የዳዕዋ ፕሮግራም ተጀምሯል🖋
ፕ
ሮ
ግ
ራ
ሙ
ተ ጀ ም ሯ ል
🎙 በሸይኽ አወል አል-ኬሚሴ
https://t.me/Abuimran_alkemisse?livestream=c000cfc296392dbf93
Repost from قناة أبو عمران الخميسي لنشر السنة والتوحيد
🖋የዳዕዋ ፕሮግራም ተጀምሯል🖋
ፕ
ሮ
ግ
ራ
ሙ
ተ ጀ ም ሯ ል
በወንድም አቡ ሂበቲላህ
https://t.me/Abuimran_alkemisse
Repost from ABU~MAHI (አቡ_ማሒ)
ፕሮግራም ሊጀምር ነው ገባ ገባ በሉ
ከመረከዝ መናሩ ሱና
መድረኩን በዋናነት የሚመራልን ወንድማችን ኡስታዝ አቡ አዩብ
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris?livestream=a08579d3fbf28966ef
አላህዬ…
ጉዳያችን ከተራራ በላይ ገዝፏል እኛ ግን ለእሱ የሚገባውን ያህል ጥረት እያደረግን አይደለም
አላህዬ ድካማችንን አትመልከት ምህረትህንና ችሎታህን ተመልከተን
አንተ እንጂ ማንም ሊፈታው የማይችለውን የተወሳሰበ ጉዳያችንን አንተ ፍታልን
አላህዬ በራሳችን አቅም የማንችለውን አንተ አቅልልን የተዘጋብንን በሮች ክፈትልን ከማናስበው አቅጣጫ መውጫ አድርግልን
ያረብ እኛን አግዘን አትተወን ጉዳያችንን በኸይር ሁሉ አስተካክልልን ከአንተም የመጣ እርዳታ እንጂ ሌላ አንፈልግም
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
ተጀመረ
አዲስ የኪታብ ደርስ📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎤በኡስታዝ አቡ ኢምራን የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ - - ሸር አድርጉት https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d
✍<የኒቃቢስቷ ንግስት>
➛ከሀያዕ'ዋ ጋራ አጂብ ነው ውበቷ
➛ከሩቅ ይናገራል ግሩም ስረኣቷ
➛ለዛዋ ደስ የሚል ቁጥብ ንግግሯ
➛ሰዎች ማትረብሽ ደሞም በተግባሯ
➛የኒቃቡ ግርማ ቆንጆ አረማመዷ
➛ከሙስሊሞች ኩራት አንዷ'ኮ ነሽ ውዷ
Repost from ፍቅር እስከ ጀነት | ራማስ አል ሀናኒ
🟢 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ !
ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል።
📱 ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ !
ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ 👇
👉 t.me/FKR_ESKE_JENET
የጅሙአ ቀን ወቅተል ኢጃብ የተባለው ሰአት እቤታችሁም ሆናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። በተለይ የጅሙአ የቀኑ መጨረሻ ፀሀይ ልትገባ በምትቃረብበት ሰአት ጌታችሁን በመለመን ላይ በርቱ። ምናልባትም የተለመነ ነገር ሁሉ እሺ ሚባልበት ወቅት ሊሆን ይችላልና።
``
"አስተውሉ! ከመፀፀታችሁ በፊት መልካምን ስራ ፈፅሙ። በዱንያ አትሸወዱ።ምክንያቱም ፦
ጤነኞች መታመማቸው ፤ አዲሶቿ ማርጀታቸው፤ ፀጋዎቿ ማለቃቸው ወጣቶቿ ማርጀታቸው አይቀርምና።"
📚【አዙህዱልከቢር ሊልበይሀቂ (1/197)】
❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም።
2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው
ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም።
ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገረኛ አይታመንምና ነገር የሚያመጣልሽን ሰው ማንንም አትመኝ....!!
ሰወች ነገረኛ የሚሆኑት ወይ ሲቀኑ ወይ እሳቸው ያጡትን ነገር ስታገኝ በምቀኝነት ወይም ደግሞ በጥላቻና በውሸት ነው ።
ደግሞ ለአንች የነገረችሽ ከአንችም ወስዳ ለሌላዋ እንደምትናገር አትዘንጊ!!!
➧አንድ ሴት በኢስላማዊ አደብ ከኖረች የተከበረና በላጭ ኑሮን ትኖራለች፡ በተለይም በህብረተሰቡ ውስጥ የተከበሩና የበላጮችን ኑሮ (ትኖራለች)።
➲ከተፈተነችና ከፊትና ከሸርና ከፈሳድ ተጣሪዎች ጋር አብራ ከቀጠለች ግን ራሷም ትጠፋለች ለሌሎች መጥፋትም ሰበብ ትሆናለች፡፡
➲አንድ ቀን ይህን የዱንያ ህይወት እንደምትተወው ታስታውስ፡ በውብ አካሏ ከነፈታኝ መልኳ ከወንድ ሚፈትን መጋጌጧ ጋር በሷ ላይ አንድ ቀን ይመጣል…
➢ ወደጉድጓድ የምትገባበት
➢ አፈር በሷ ላይ ሚደፋበት
➢ ምስጦች የሚበሏት
➢ ክብሯና ውበቷ ጥሏት ሚሄድበት
➢ በዚህ ጉድጓድ በስራዋ ትያዛለች፡ በዱንያ ላይ ያሳለፈችው ተይዞ!
➲ ከሷ በፊት ህንጻ ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች ነበሩ፡ ከዛም በቀብር ውስጥ መርጊያቸው ሆነ!
➢ሙስሊም ሴት አላህን ትፍራው! ለዚህ ቀንም ትዘጋጅ!>>
📚 ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር (ሀፊዘሁላህ)
Repost from 📌 قَنَاةُ النِّسَاءِ السَّلَفِيَّاتِ🎀
📚سورة الكهف
-
🎤በኡስታዝ ሙስጠፋ ሙሀመድ
📍https://t.me/Asselefya3
Repost from قناة أبو عمران الخميسي لنشر السنة والتوحيد
⚠️ከከሓዲዎች ጋር መመሳሰል ያለው አደጋ
🔰በአለባበሳቸው፣ በጌጣጌጣቸው እና በአቀማመጣቸው ከከሓዲዎች ጋር መመሳሰል ለእነርሱ ያለንን የመወዳጀት ዝንባሌ ያሳያል።
☑️ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ በ«ሙስነድ አሕመድ» እና «ሱነን አቡ ዳውድ» ውስጥ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር رضي الله عنهما በተዘገበ ሐዲስ፦
من حديث عبدالله بن عمر ، أن النبي ﷺ قال:من تشبه بقوم فهو منهم .
«አንድን ሕዝብ የሚመስል ሰው ከእነርሱ ነው» ብለዋል።
🔰ስለዚህ ሙስሊም የሆነ ሰው በአለባበሱ፣ በጌጣጌጡ እና በአቀማመጡ የነቢዩን ﷺ መመሪያ መከተል ይገባዋል። የእስልምና ጠላቶችንም በአለባበሳቸውና በጌጣጌጣቸው መኮረጅ የለበትም።
☑️ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
قال النبي ﷺ: «خير الهُدَى هُدًى محمد ﷺ
«ከመንገዶች ሁሉ የተሻለው መመሪያ የሙሐመድ ﷺ መመሪያ ነው።»
✅አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ﴾
«በእርግጥም በአላህ መልእክተኛ ﷺ ለእናንተ መልካም አርአያ አላችሁ።»
[አል-አሕዛብ፦ 21]
📣ስለዚህ በሁሉም ነገራችን እና እንቅስቃሴዎቻችን ነብዩን መከተል አለብን እንጂ ኩፋሮችን መከተል የለብንም።
📚@من كتاب منكرات شاءعة في المجتمعات. ص١٩
©https://t.me/Abuimran_alkemisse
©https://t.me/Abuimran_alkemisse
➧ሀፍሷ ቢንት ሲሪን አላህ ይዘንላትና አሮጊት(ትልቅ ሴት ሁና) ትሸፈን ነበር።
▪ለሷም አላህ እኮ ትዳር የማይፈልጉ ባልቴቶችን በተመለከተ 《በነሱ ላይ የላይ ልብሳቸውን ቢያስቀምጡ ምንም ችግር የለባቸውም》ይላል ስትባል
➧እሷም 《ግን መጠበቃቸው ለእነሱ የተሻለ ነው》 ይላል እኮ ብላ መልስ ትሰጣለች።
➧እኛስ የት ነን እህቶችዬ ?ራሳችን እንፈትሺ!!
⛔️ስለ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን" ንቅናቄ አመሰራረት፣ ታሪካዊ ዳራና ስለተበላሸው አደገኛ አላማቸው በአላህ ፈቃድ በአጭሩ እንመለከታለን።
⚠️ የኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጥቁር ታሪክና ጠምዛዛው አጀንዳቸው - ክፍል 1 ⚠️
● የኢኽዋኑል ሙስሊሚን (የሙስሊም ወንድማማቾች) ንቅናቄ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ከተከሰቱ እጅግ አደገኛና "ፖለቲካዊ" የጥመት ቡድኖች መካከል ዋነኛው ነው። ይህ ቡድን እንዴት ተመሰረተ? እውነተኛ አላማውስ ምንድነው የሚለውን ስንመለከት?
🏗️ ንቅናቄው በ1928 እ.ኤ.አ (1347 ሂጅሪ) በግብፅ ኢስማዒሊያ ከተማ በሐሰን አል-በና አማካኝነት ተመሰረተ። ሐሰን አል-በና ንቅናቄውን ከመጀመሩ በፊት በ"ሐሳፊያ" በተሰኘው የሱፊያ ጠሪቃ (መንገድ) ውስጥ የሰረጸና በሱፊያ አስተሳሰብ የታነፀ ሰው ነበር።
⛔️ የኢኽዋን መሠረት ከትክክለኛው የነቢዩ (ﷺ) ሱና ይልቅ በሱፊያ ስርአት (መሪን ፍጹም መታዘዝ ወይም 'ተቅሊድ') ላይ የተገነባ ነው። ይህ ደግሞ በቡድኑ ውስጥ ለሚታየው "መሪን ማምለክ" ደረጃ ትልቅ በር ከፍቷል።
ይህ ቡድን የነቢያት ሁሉ ጥሪ "ተውሒድን" (አላህን በብቸኝነት ማምለክና ከሽርክ ማጽዳት) ነበር። ኢኽዋኖች ግን ይህንን ታላቅ መሠረት ወደ ጎን በመተው ዳዕዋቸውን በፖለቲካዊ ስልጣን ላይ ነው የመሰረቱት።
⛔️ የእነሱ ትልቁ ስኬት የሚለካው ስንት ሰው ወደ ተውሒድ ገባ በሚለው ሳይሆን፣ ስንት ሰው የድርጅቱ አባል ሆነና ወደ ቤተ መንግስት ስልጣን ምን ያህል ተቃረብን በሚለው ነው።
⚠️ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ *"ኢኽዋኖች ተውሒድን አያውቁም፤ ተውሒድን የሚማር ሰው ደግሞ አይወዱም፤ ምክንያቱም ተውሒድ ሰውን ይለያል (ሀቅና ባጢልን ይለይባቸዋል)፤ እነሱ ግን የሚፈልጉት የሰውን ብዛት ብቻ ነው።"*
⚠️ የኢኽዋን ንቅናቄና ዓላማው "ስልጣን" ስለሆነ፣ ያንን ስልጣን ለማግኘት ማንኛውንም አይነት የተበላሸ መንገድ ከመጠቀም አይመለሱም።
⛔️ ዋና መገለጫቸው ተልቢስና ማታለል ነው ፦ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ ከሺዓዎች፣ ከሊበራሎችና ከአላህ ጠላቶች ጋር እንኳ ሳይቀር ግንኙነት አንድነት ይፈጥራሉ። ሐሰን አል-በና በሚታወቀው ንግግሩ፦ *"ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ጋር ያለን ጠላትነት የሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካና የድንበር ነው"* በማለት የዲኑን መሠረት (አል-ወላእ ወል-በራእ) የሚንድ ሰው ነው ይሄንን ሰው ነው እንዴ መሪ አድርገው የሀገራችን ኢኽዋኖች የሚንቀሳቀሱት።
🗡️ ኢኽዋኖች ከመጀመሪያው ጀምሮ "" (ድብቅ ወታደራዊ መዋቅር) ነበራቸው። ዓላማቸውም በሙስሊም መሪዎች ላይ በማመፅ ተቃውሞ በመውጣት ስልጣን መቆጣጠር ነው።
⚠️ ይህ የተበላሸው አላማቸው፦ ሰላማዊውን ሙስሊም ማህበረሰብ በገዢዎቻቸው ላይ በማነሳሳት ሀገርን ማተራመስ። ዛሬ በሙስሊሙ ዓለም የምናያቸው አብዛኞቹ አብዮቶች እና ብጥብጦች ምንጫቸው የኢኽዋን አጥፊ አስተሳሰብ ነው።
☣️ እንዲሁም አሁን ላይ እነ ሸይኽ መሀመድ ሀሚዲን ታሪኩን አለባብሰው የሚያቀርቡለት ሰይድ ቁጥብ የ"ተክፊር"የኸዋሪጆችን መርዝ የሚረጭ ዋናው መሪያቸው ነው ከሐሰን አል-በና በኋላ የመጣው ሰይድ ቁጥብ፣ የኢኽዋንን አላማ ይበልጥ ወደ አክራሪነትና ወደ ተክፊር (ሰውን ማክፈር) ቀየረው።
● አጠቃላይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ "ጃሂሊያ" (ካፊር) በማለት መፈረጁ።
● ይህ አመለካከት ደግሞ ዛሬ ዓለምን እያስጨነቁ ላሉት እንደ አልቃኢዳና iss ላሉ ጋጠወጥ ቡድኖች "መንፈሳዊ አባት" እንዲሆን አድርጎታል።
በመጨረሻም የኢኽዋን ቆሻሻ አላማ በአራት ነጥብ እንመለክት
1. እነሱ ዘንድ ስልጣን ከዲን ይቀድማል ፦ ዲን ለእነሱ ለፖለቲካ ስኬት መጠቀሚያ "መሳሪያ" ብቻ ነው።
2. ትልቁ ግባቸው አቂዳን መግደል ነው፦ ሽርክና ቢድዓን ዝም በማለት "ህዝብን እናስተባብር አንድ እናድርግ" በሚል ስሜት ተውሒድን ማዳከምና ትክክለኛውን ዐቂዳ ማጥፋት ነው የሚፈልጉት።
3. ድርጅታዊ አምልኮ ውስጥ የገቡ ናቸው፦ ለድርጅቱ (ለተንዚሙ) የታመነ አማኝን ማፍራት እንጂ ለአላህና ለሱና የታመነ ሙስሊም መገንባት በጭራሽ አይፈልጉም።
4. ሁከትና ብጥብጥ መፍጠርን ይወዳሉ ሙስሊም መሪዎችን በማክፈርና ህዝብን በማነሳሳት ደም መፋሰስን እንደ "ጅሃድ" በመቁጠር በሙስሊሙ መካከል አጥፍቶ መጥፋትና ተቃውሞ ሰልፍ ውጡ በማለት ከባድ ብጥብጥ ይፈጥራሉ።
ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒ (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፦ *"ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ኡመቱን ወደ ኋላ የጎተቱ፣ ለጠላቶች በር የከፈቱና በዲን ስም የሚነግዱ አጭበርባሪዎች ናቸው።"*
ክፍል ሁለት ይቀጥላል ...የዑለሞችን ጠንካራ ትችትና ማስረጃዎችን እንዳስሳለን።
ይሄ ስለ ኢኽዋኖች ሀይላይት ብቻ ነው ሸር በማድረግ በነሱ ለተሸወዱ ሙስሊሞች እንድረስላቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy