🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
کانال بسته
نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
548
مشترکین
-224 ساعت
+177 روز
+5730 روز
آرشیو پست ها
የተስፋ ብርሃን በወንጀል ለጨቀየች ነፍስ
እረ ተስፋ አንቁረጥ - ፈጽሞ አንድከም፣
ከአላህ ራህመት - ተስፋ አይታጣም፤
"ደጋግመን ስናጠፋ - እንዴት ይምረናል?"
የሚለው ሰይጣን ነው- ሊያርቀን ይጥራል።
የአላህ ይቅርታ - ባህር ነው ሰፊ፣
የባሪያውን ጥፋት - ቶሎ ብሎ አጥፊ፤
ሺህ ጊዜ ብንወድቅ - ሺህ ጊዜ እንነሳ፣
"ማረኝ" እያልነውም - ተውበትን አንርሳ።
ጥፋት የሰው ልጅ - ስህተት አይጠፋም፣
አላህ ግን መሐሪ -ወንጀልን አይቆጥርም፤
ባሪያው ተጸጽቶ - እጁን ሲዘረጋ፣
ይቀበለዋል - በራህመት በጸጋ።
የወንጀል ማጠቢያ - የተውበት መድረሻ፣
ለቆሰለው ልባችን - ይሆናል ማደሻ፤
ወንጀል እየሰሩ - "ማረኝ" ማለት ነው፣
የአማኞች ጌጥ - ይሄ ጸጋቸው ነው።
እወቁ ወገኖቼ - ጌታችን አዛኝ ነው፣
ከእናት በበለጠ - ለእኛ ራህሩህ ነው፤
ስለዚህ አንፍራ - ተውበትን አንዘንጋ፣
በእዝነቱ ጥላ ስር - ሁሌም እንጠጋ።
╭─••──═••═─••─╮
✒️ኡሚዬ ይቅርታ!🖌
╰─••──═••═─••─╯
ላሳመምኩሽ ህመም ስትወልጂ ላማጥሽው
እኔን በማሳደግ ብዙ ለደከምሽው
ያኔ ላስቸገርኩሽ ልጅነት ሸውዶኝ
ድካም ልፋትሽን እንዳላየው ጋርዶኝ
ይቅርታ እልሻለሁ ደግሜ ደግሜ
እኔን በማሳደግ ለጨረሽው እድሜ
ይቅርታ ጠይቄሽ ጠብቃለሁ ምላሽ
እኔን በማሳደግ ለጠቆረው ገላሽ
ያኔ ያሳዘንኩሽ የነጠኩሽ ደስታ
አሁን ነው የገባኝ ኡሚዬ ይቅርታ!
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
