ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

显示更多

📈 Telegram 频道 ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit 的分析概览

频道 ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit (@ortodoxmezmur) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 169 596 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 139,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 140 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 169 596 名订阅者。

根据 19 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 415,过去 24 小时变化为 40,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 12.95%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.01% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 21 967 次浏览,首日通常累积 10 188 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 125。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR”

凭借高频更新(最新数据采集于 20 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

169 596
订阅者
+4024 小时
+1847 天
+41530 天
帖子存档
አለፍኩኝ ድንግል አለፍኩኝ ድንግል ማእበሉን አለፍኩኝ ድንግል ውጣ ውረዱን ምርኩዜ ስለሆንሽ ስጠራ ስምሽን
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል  በእመቤቴ ምልጃ አለፍኩኝ ድንግል  ወንዙን ስሻገር አለፍኩኝ ድንግል  ያባረረኝ ጠላት አለፍኩኝ ድንግል  ቀረ ሰምጦ ባህር አለፍኩኝ ድንግል  ከበሮውን ላንሳ አለፍኩኝ ድንግል  እንደ ሙሴ እህት አለፍኩኝ ድንግል  ምስጋና ልሰዋ አለፍኩኝ ድንግል  ለዓለም እመቤት
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል  ወንድሞች ቢሸጡኝ አለፍኩኝ ድንግል  አሳልፈውኝ አለፍኩኝ ድንግል  በባዕድ ከተማ አለፍኩኝ ድንግል  ድንግል ሾመችኝ አለፍኩኝ ድንግል  በቅን የማመልከው አለፍኩኝ ድንግል  ልጅሽ ክርስቶስ አለፍኩኝ ድንግል  ምልጃሽን አስቦ አለፍኩኝ ድንግል  ሰጥቶኛል ሞገስ
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል  በስምጥ ሸለቆ አለፍኩኝ ድንግል  ሆኜ ባጣብቂኝ አለፍኩኝ ድንግል  የምደገፍበት አለፍኩኝ ድንግል  አንዳች ሳይኖረኝ አለፍኩኝ ድንግል  ባንቺ ተርፌአለሁ አለፍኩኝ ድንግል  ምርኩዝ ሆነሽኝ
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል  ሰው የለኝም እና አለፍኩኝ ድንግል  ድንግል አትራቂኝ አለፍኩኝ ድንግል  አንቺው ነሽ እናቴ አለፍኩኝ ድንግል  የማትሰለቺኝ አለፍኩኝ ድንግል  ውለታዋ ብዙ አለፍኩኝ ድንግል  የድንግል ማርያም አለፍኩኝ ድንግል  እርሷን ለእኔ የሰጠ አለፍኩኝ ድንግል  ይክበር ዘለዓለም ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ጥቅምት ፲ /10/ በዚህች ቀን የቅዱስ ባኮስና ቅዱስ ሰርጊስ መታሰቢያ ነው። ባኮስ እና ሰርጊስ ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው። ጾምን ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር። ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ። እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ። ከቆይታ በሁዋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ። በአዋጅም ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ይገድልም ያዘ። በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት። "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቀያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በሁዋላ ላንተ ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት። መኮንኑም በጽኑ አሰቃያቸው። እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም። ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን 2ቱን ለያዩዋቸው። ቅዱስ ባኮስን ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት። ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው። በአካባባቢውም ባባ እና ማማ የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው። ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው በታላቅ ዝማሬ ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት። ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ በዚህች ቀን እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል። አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች። የመከራ ዘመን ካለፈ በሁዋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል። በረከታቸው ይደርብን!አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

‎ጥቅምት ፲ /10/
‎ ‎በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ ። ‎ ‎ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ ። ‎ ‎መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው ። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️

በወርቅ ቀለም በወርቅ ቀለም ተፅፈሻል ድንግልሆይ ለኔ ተሰተሻል አከብርሻለው እመቤቴ ተስፋ ፅዮን ነሽ ለህይወቴ/2/
አዝ
ተሠናክዮ እንዳልተሠናክዮ እንዳልወድቅ ዘይት መብራቴ እንዳያልቅ ሁኚልኘ ድንግል ብዙ ዎጋ በሩ በእኔ ላይ ዳይዘጋ
አዝ
የቆመ መስሎት የወደቀ የክብሩን ስፍራ የለቀቀ ሲቀና አየሁት አንቺን ይዞ በትር ምልጃሽን ተመርኩዞ
አዝ
እንዳልቀርብሽ ተራቁቼ የጌታን ክብር እረስቼ ቀድመሽ ዉጭሌኘ በጉዞዬ ልጅሽ ነዉና አላማዬ
አዝ
ምልጃሽ ካቀናዉ ጉልበቴን ከባረከልኘ ህይወቴን ብፅህይት እላለው ዘወትር ስላንቺ ይክበር እግዚአብሔር ዘማሪት ፅጌሬዳ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ጥቅምት ፱ /9/ በዚችም ቀን በሕንድ አገር ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ሐዋርያ ቶማስ እንደ ባሪያ ተሽጦ ወደ ሕንድ አገር ከአበኒስ ጋር በገባ ጊዜ አበኒስ ወደ ንጉሥ ጎንዶፎር አቀረበውና ሐናፂ እንደሆነም ለንጉሡ ነገረው ንጉሡም ጠየቀው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም እንዲህ ብሎ ለንጉሥ መለሰለት እኔ የጥርብ ሥራን ሁሉ ቀንበሮችን ሚዛኖችን ሠረገላዎችን መርከቦችን በግንብ ሥራም ቤተ መንግሥትን እሠራለሁ ንጉሡም እጅግ ደስ አለው። ቤተ መንግሥቱንም እንዲሠራለት ከሚሻው ቦታ ወሰደውና ንጉሡ ለራሱና ከእርሱ ለሚሠሩ ሠራተኞች የሚሆን ብዙ ገንዘብን ሰጠው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም ተቀብሎ ሔደ። ገንዘቡ ለድሆች ምጽዋት አድርጎ ሰጣቸው ንጉሱም እጅግ ተቆጣ በሚገድለውም ነገር እስኪመክር ድረስ ሐዋርያ ቶማስን ከአመጣው ከአበኒስ ጋር አሠረው። በዚያችም ሌሊት የንጉሡ ወንድም ጋዶን በድንገት ታመመና ሞተ መላእክትም ነፍሱን ወስደው ተመሳሳይ የሌለው በወርቅና በዕንቍ የተሠራ ቤተ መንግሥትን አሳዩት። ጋዶንም መላእክትን "ይህ ቤተ መንግሥት የማነው አላቸው" መላእክትም ለጋዶን "ሐዋርያ ቶማስ ለንጉሥ ጎልዶፎር የሠራለት ነው" አሉት ከዚህም በኋላ ጋዶን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ያየውንም ሁሉ ለወንድሙ ለንጉሥ ጎልዶፎር ነገረው። በዚያንም ጊዜ ወደ እሥር ቤት ሮጡ ከወህኒ ቤትም አወጡአቸው። ለሐዋርያውም ሰገዱለት የሀገር ሰዎችም ሁሉ ከንጉሥ ጎልዶፎር ጋር አምነው ተጠመቁ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ ባረካቸውና ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

አቤቱ ላንተ አቤቱ ላንተ ለስምህ አለኝ ምስጋና/2/ እንዳንተ ያለ ከአማልክት ማነው ገናና እንዳንተ ያለ እግዚአብሄር ማንስ አለና
አዝ
አቤቱ ማዳንህ በእኛ ላይ ተገልጧል ግዙፉ ተራራ በፊታችን ቀልጧል በግንብ የተሰሩ ብረት የለበሱ የአህዛብ ከተሞች በመዝሙር ፈረሱ
አዝ
ስምንቱን ነፋሳት አንተ ስታዛቸው ውቅያኖስ ባህሩም ይዘላል ፊታቸው ቤልፌጉር አልቻለም አንተን መገዳደር የጥበብ ሀገሯ ታላቅ ነህ እግዚአብሄር
አዝ
በብዙ መጽናናት ህይወቴን መለስካት በቃልህ ወይን ጠጅ ነፍሴን አረካሃት ለዝናም አይደለም ወይም ለሞቅታ የምዘምርልህ ለአምልኮ ነው ጌታ
አዝ
በጥብርያዶስ ባህር ድግስህ ናፍቆኛል ከፈርኦን እንጀራ ፍቅርህ ለይቶኛል የቦኤዝን እርሻ አልቃርምም እኔ ዋናውን አጭዳለሁ ጌታ ነው መድኅኔ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ምስጉን ነው  ምስጉን ነው የተመሰገነ ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ ይመስገን ይመስገንልኝ ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ
አዝ
እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ ያጣሁትን ከአንተ አግኝቻለሁ ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ/2/
አዝ
ማቄን የቀደደው ደስታ አስታጠቀኝ ባዶ የነበርኩት ሁሉ ተሰጠኝ ሰጭም ነሽም እግዚአብሔር ብቻ ነው የሰው ድርሻ በር ማንኳኳት ነው/2/
አዝ
እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም መሰረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም ስትሰጠኝ የሚታየውን እንዳትነሳኝ የዘለዓለሙን/2
አዝ
ቢሰጥ አያልቅበት ለጋስ ክቡር ጌታ ሁሉን ከወነልኝ በልዩ ችሮታ ድሆች ስንሆን ሁሉ አለንና አምላካችን ይድረሰው ምስጋና/2/ ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

‎ጥቅምት ፯ /7/ ‎ ‎በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም
‎ጥቅምት ፯ /7/
‎ ‎በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና። ‎ ‎ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ። ‎ ‎አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ። ‎ ‎ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️

አጋጣሚ_አይደለም አጋጣሚ አይደለም መትረፌ መዳኔ የጌታ ተአምር ነው አረ ይገርማል የኔ ሞት እንቅልፍ ሆነልኝ ጭንቀቴ ቀለለ የረዳኝ ጌታ ነው ውዴ እየተከተለ
አዝ
ማነው በዛ በረሀ ያበላኝ መና ያጠጣኝ ውሀ ማነው የደገፈኝ ጥልቁን ሸለቆ ያሻገረኝ አንተ ነህ ለኔ እናት አባቴ ፍፁም ወዳጄ ስጋና አጥንቴ አይኔ አይነቀል ከዙፋንህ ፊት አያዞርም ፍቅር አይንህ
አዝ
ወሮኝ ድቅድቅ ጨለማ ተስፋዬ መክኖ ልቤ ሲደማ አይቶ ሲፈስ እንባዬ ደመና ጠቅሶ መጣ ጌታዬ ፀሐይ ነውና የብርሀን አምዴ ኢየሱስ ለኔ ህይወት መንገዴ አልተሸነፍኩም ውዴ አግዞኛል መቃብር ከፍቶ ህይወት ሰቶኛል፤
አዝ
ሲለይ ነፍስ ከስጋ በጨለማ ቀን በክፉ አደጋ፤ ዳንኩኝ ሞት እያየኝ የንስሀ እድሜ ጨመረልኝ፤ በፅድቄ አይደለም የተረፍኩት በሱ ፍቅር ነው በሱ ምህረት ብቻዬን ሆኜ ሁሌ ማለቅሰው እየበደልኩት ስላዳነኝ ነው፤
አዝ
ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ ብሎ ጥሎሀል እየታገለ ሲኦል ድል መግዛትህ ባዶ ቀርተሀል ተበዝብዘህ በእራሱ መንግስት ፈጥሮኝ በአላማ የልጁን ህይወት ማንም አይቀማ መቃብር ያልፋል በአገልግሎቴ ተከፍቶልኛል ደጁ የአባቴ ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

‎ ጥቅምት ፮ /6/ ‎በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች። ‎ ‎ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት
‎ ጥቅምት ፮ /6/
‎በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች። ‎ ‎ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር። በዚህም አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ ብላ ተሳለች። ‎ ‎ካህኑ ኤሊም ስትጸልይ ሰምቶ እንዲህ ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔርአምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች ። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ርዕሰ ባህታዊ በቃልና በኑሮ ሆነሀል ምስክር እንደ ፀሐይ አበራህ በእግዚአብሔር ሀገር ሰማያዊ ነህ እንጂ አይደለህም ምድራዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ርዕሰ ባህታዊ
አዝ
በስሙ ለሚያምኑት አማላጅ ሆነሀል በፀሎትህም ሀይል ተማምነንብሀል የክብር ኮከብ ነህ የገዳም መብራት አስተምረኸኛል ምግባር ሃይማኖት
አዝ
የሚያልፈውን አለም የምድሩን ንቀሀል የታመንከው አምላክ ህያው አድርጎሀል በስጋ በነፍስህ እግዚአብሔር ከበረ የማስታረቅን ቃል ባንተ ላይ አኖረ
አዝ
በተጋድሎ ብዛት በፆም በፀሎት ትተጋ ነበረ በፀናች እምነት ስለቃልኪዳንህ በረከት ይወርዳል ያንተ ስም ሲጠራ አጋንት ይርዳል
አዝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእምነት አባት አናብስት አናብርት የታዘዙለት ከኒሳ ተነስቶ ኢትዮጵያ ደረሰ ፀጋው በረከቱ በእኛ ላይ ፈሰሰ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

​​እንኳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን! አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል። አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ። አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው። በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር። በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል። ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል። ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል። ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል። ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ። ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14  💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

‎ጥቅምት ፭ /5/ ‎ ‎አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) ‎ ‎ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: ‎ ‎አባታችን ገብረ መንፈስ ቅ
‎ጥቅምት ፭ /5/
‎ ‎አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) ‎ ‎ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: ‎ ‎አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ልብስ ያልለበሱ ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ናቸው። ‎ ‎የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው። ‎ ‎በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል። ‎ ‎ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡ ‎ ‎የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር እና ፍትሃ ነገስት ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ከንቱ ነኝ ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
አዝ
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ በመጨረሻውም በሞት ተወሰድኩኝ /2/
አዝ
ከጣይቱ በታች አዲስ ነገር የለም ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ /2/
አዝ
ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ አፈር ተጭኗቸው በመቃብር አሉ እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው /2/
አዝ
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩት አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረት ነኝ /2/
አዝ
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር /2/ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

‎ጥቅምት ፬ /4/ ‎ ‎ዳግመኛም በዚህ ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታች
‎ጥቅምት ፬ /4/
‎ ‎ዳግመኛም በዚህ ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት በታኅሣሥ 29 ቀን 312 ዓ.ም ነው፡፡ በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ ‎ ‎በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ነገሥታት ከዕለታት አንደኛው ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ ቤተ መቅደስ እንዲሰሩ አዟቸው በተአምር ቤተመቅደሱን ሰርተዋል። ‎ ‎የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡ ‎ ‎ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን እሁድ ዕለት ዐረፉ፡፡ ከ13 ዓመት በኋላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው የዕረፍታቸው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የተቀበሩበት ቦታም አንድ ነው፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ሳይዛና ይባላል፡፡ ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ስደትሽን ሳስብ ስደትሽን ሳስብ ስለአንቺ ልገፋ ለካስ ስደት አለ ቀን በሰው ሲከፋ ወስዶ ሳያስቀርሽ ወንዝና ጅረቱ ምሳሌ ሆነሻል ድንግል ለፍጥረቱ
አዝ
እንዳልቅበዘበዝ ሁኚ ከአጠገቤ ድንግል ሆይ ስራሽን መዝግቦታል ልቤ በምሕረት ይለፈኝ በፍጹም ይቅርታ እሺ ባዩ ልጅሽ የታቀፍሽው ልጅሽ
አዝ        
ሱላማጢስ ብሎ ሰለሞን ጠራሽ የሰላም መገኛው አንቺ ስለሆንሽ እንበረከካለሁ እሰግዳለሁ ለአንቺ ጠላት እንዳይጥለኝ ጉልበቴን አበርቺ
አዝ
        የኮቲባ ቁጣ ዛቻና ክፋቷ አስተናግዳዋለች ምድር አፏን ከፍታ በአንቺ ላይ ያመጹት በቁጣው ጠፍተዋል ከጥቅልሉ መዝገብ ከሱ ተሽረዋል
አዝ
ለተጠሙት ነፍሳት ያጠጣቸው ጌታ ከጀርባሽ ላይ ሆኖ በዱር ተንገላታ የግብጽን ጣዖታት በግርማው መታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ያለቆች ጌታቸው               ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ጥቅምት ፫ /3/ በዚሕችም ቀን ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖን አረፈ። የዚሕ አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ ያደገ የቤተክርስቲያንንም ትምሕርት ተምሮ ያደገ ነ
ጥቅምት ፫ /3/
በዚሕችም ቀን ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖን አረፈ። የዚሕ አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ ያደገ የቤተክርስቲያንንም ትምሕርት ተምሮ ያደገ ነው። ወደ አስቄጥስ ገዳም በሊቀ ጳጳሳት በአባ ያዕቆብ ገዳም የምንኩስናን ልብስ ለብሶ መነኮሰ ተጋድሎውንም በየጊዜው ጨመረ ሥጋውንም አያደከመ በእርሱ ዘንድ ኖረ። ስለ በጎ ተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ዳግማዊ ሊቀ ጳጳስ አባ ማርቆስ ወደ አባ ያዕቆብ ወስዶት እያገለገለው ከእርሱ ጋር ኖረ። አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜም ካሕናትና ኤጲስቆጶሳት ትሩፋቱንና ያማረ ሥራውን ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሳስቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ እግዚአብሔርንም እያገለገለ የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች። ከዚሕም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ እግዚአብሔርንም ከዚሕ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር በአንድነት አሳረፈው የሹመቱም ወራት አምስት ወር ከዐሥራምስት ቀን ነው። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ዛሬ ምሽት 2:00 በሚጀመረው 14ኛው ዙር Graphics Design ሥልጠና ላይ Day 1 + 2 + 3 ኮርስ በነጻ እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል 🎉 ቀድማቹ ማወቅ ያለባችሁን እና ከየት ወደየት መሄድ
ዛሬ ምሽት 2:00 በሚጀመረው 14ኛው ዙር Graphics Design ሥልጠና ላይ Day 1 + 2 + 3 ኮርስ በነጻ እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል 🎉 ቀድማቹ ማወቅ ያለባችሁን እና ከየት ወደየት መሄድ እንደምትችሉ ጥንቅቅ አድርገን እናሳያችኋለን ። ***************** « I want to attend Day 1+2+3 of Graphics Design Course » ብላቹ ለምትልኩልን link እንሰጣችኋለን የመላኪያ አድራሻ @greenbirdtechnology ላይ ***************** @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥

አዝላው ወረደች አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ /2/ ስደተኛዋ የአምላክ እናት ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት
አዝ
ዓለም በምኗ ታስተናግዳት የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት እነ ኮቲባን እየላከች የአምላክን እናት ተሳደበች እነ ሄሮድስን እየላከች ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ
የክብርን ጌታ ተሸክማ ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ ተንከራተተ ማደሪያ አጥቶ ጌታ ሲወለድ የምሥራች በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
አዝ
ግና መላእክት በሰማያት ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው /2/
አዝ
ዓለም በምኗ ታስተናግዳት የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት እነ ኮቲባን እየላከች የአምላክን እናት ተሳደበች እነ ሄሮድስን እየላከች ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ
የክብርን ጌታ ተሸክማ ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ ጌታ ሲወለድ የምሥራች በረት ሰጠችው ዓለም ታካች ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ጥቅምት ፪ /2/ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ። የከኀዲው ንጉስ ዮስጥያኖስ ሚስት በሃይማኖቷ የቀናች ነበረች። ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም ትወደው ታከብረውም ነበር። በዚ
ጥቅምት ፪ /2/
የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ። የከኀዲው ንጉስ ዮስጥያኖስ ሚስት በሃይማኖቷ የቀናች ነበረች። ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም ትወደው ታከብረውም ነበር። በዚሕም ንጉሱ ሊገድለው እንደሆነ በአወቀች ጊዜ ለአባ ሳዊሮስ እንዲሸሽ ነገረችው፤ አባታችንም እኔ ስለ ክርስቶስ ለሞት የተዘጋጀው ነኝ አለ። ንግሥቲቱና ምዕመናኑም በለመኑት ጊዜ ወደ ግብፅ አገር ተሰደደ። የንጉሱ ወታደሮችም በመካከላቸው ሆኖ ሲጓዝ አላገኙትም ነበር፤ ጌታችን ይሠውረው ነበርና። በአንዲት ቀንም በአስቄጥስ ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በመጻተኛ መነኩሴ አምሳል ገባ። በዚያም ቄሱ ዕጣኑንና ቁርባኑን ሊያሳርግ ጀመረ ሁሉንም ሥርዓት ፈጽሞ እጆቹን ታጥቦ ማኅፈዱን በገለጠው ጊዜ በጻሕሉ ውስጥ የቁርባኑን ኅብስት አላገኘውም፤ ደንግጦም አለቀሰ ለሕዝቡም ወንድሞቼ ይሕ የሆነ በእኔ ኃጢያት ወይም በእናንተ ኃጢያት እንደሆነ አላወቅሁም አላቸው። መልአክም ተገልጦ ይህ የሆነ በኃጢአትሕ ወይም በሕዝቡ ኃጢአት አይደለም ሊቀጳጳሳት አባ ሳዊሮስ እያለ መሥዋዕትን ለማሳረግ በመድፈርሕ ነው አለው። ቄሱም መልሶ ሊቀጳጳሳት መኖሩን አላወቅሁም አለው፤ መልአኩም አባታችን ወደ ቆመበት ቦታ አመለከተው። ቄሱም ከአባታችን ከእግሩ በታች ሰግዶ ቡራኬ ተቀበለ። ወደ ቤተመቅደስም ገባ፤ በኋላም ቄሱ የቁርባኑን ኅብስት በጻሕሉ ውስጥ አገኘው ካሕናቱና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የቁርባኑም ሥርዓት ተፈጸመ። ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገረ ስሐ ሄደ ምዕመናንንም በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው እስከሚያርፍባት የካቲት ወር ዐሥራ አራት ቀን ኖረ። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️