cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ለሩህ°ቅመም

مشاركات الإعلانات
1 299
المشتركون
-324 ساعات
+37 أيام
+330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ድንገት በሆነኛው ቀን አንዳንድ ገፆችን ከህይወትህ ላይ ትሰርዛቸዋለህ። ቀልብህ ይወደው የነበረውን ሁሉ ማሳደድ ታቆማለህ። አብሮህ ሳለ ከልብ ላልነበረው ጉዳይ ሁሉ ጀርባህን ትሰጣለህ። ፊትህንም ወደአላህ ብቻ ታዞራለህ። ከልብ የሆነው ብቸኛ ጉዳይህ ወደአንተ እስኪመጣ ልብህን አሳምነህ በትዕግስት ትቆያለህ። አላህም አይቶህ ለቀልብህም ለልብህም በሆነው ብስራት ያበስርሀል። አብሽርልኝ የኔ ጀግና☺️ ታጋሾች ሆይ ትንሽ ጨምሩ ፥ ጥቂት ብቻ ቀረ ብለዋልና ኢብኑል ቀይም። ትንሽ ብቻ ፥ ትንሽ ብቻ ጠብቅ🤍 (አብድልቃድር ኑር)
إظهار الكل...
15🤗 7
በዛም አለ በዚህ በሰበሩን ሰዎች እና ጥለውን በሄዱ ልቦች አማካኝነት በሆነ መልኩ ተገንብተናል። ባላሰብነው መንገድ ጥንካሬንና ቆራጥ መሆንን ተምረናል። ባስቀሩልን ሐዘን ተረማምደን ጀግነናል። በአትችሉም ተነስተን ችለን ተገኝተናል። ክብራችን ላይ በተረማመዱት ልክ ስለክብር የበለጠ አውቀናል። የነሱ ፀያፍ ተግባር ለኛ ከፍታ መሰረት ሆኗል። የነሱ እኛን መጉዳት ማንነታችንን እንድናገኝ መንስኤ ሆኖናል። በነሱ ኩነኔ ተግባር የፅድቅ መንገዱ ገርቶልናል። እናም አንዳንዴ እነዚህ ሰዎች ሊመሰገኑ ይገባል ብዬ አስባለሁ። አላህ እነዚህን ሰዎች ያለምክንያት እንድናውቃቸው አላደረገም። ያለአንዳች ሰበብ እነሱን ገፊ እኛን ደግሞ ተገፊ እንድንሆን አልፈቀደም። ባይገፉን የዛሬውን ማንነታችን ባላገኘን ነበር። በሰአቱ የወደቅን መስሎ ቢሰማንም በጊዜ ውስጥ ግን የሆነው ሁሉ ለኸይር መሆኑን እንረዳለን። እናም እነዚህን ሰዎች ስለስራቸው ባይሆንም እኛ ላይ ስላደረጉት አስተዋጽኦ ግን እናመሰግናለን። እንኳንም አወቅናቹ ፣ እንኳንም ገፋችሁን እንላለን። ምንአልባት እንዲያ ባታደርጉ ዛሬ ላለንበት የመብሰል ደረጃ ባልደረስን ነበር። (አብድልቃድር ኑር)
إظهار الكل...
14👍 7
ወዳጄ! እኚያ የአላህ ነብይ ጧኢፍ ላይ ያን ሁሉ በደልና ግፍ ባስተናገዱበት ክስተት የአላህን ቁጣ ጨምሮ የጧኢፍ ህዝቦች ላይ ያሻቸው እንዲሆንባቸው በመላኢካው ጅብሪል ቢጠየቁ ፥ አይሆንም ያሉበት ታሪክ አዕምሮህ ላይ የሆነ ጭላንጭል እሳቤን አልፈጠረብህም? በዳዮቻቸው ምንም እንዳይሆኑ ያደረጉበት ተአምር አጀብ አላስባለህም? ይልቅ የረሱሊን ምላሽ ወደሐያትህ ስታመጣው ለይቅርታ ዝግጁ ከመሆን በዘለለ የትኛውም ስልጣንና አቅም ቢኖርህ መሻታህን ብቻ ለማስፈፀም ስትል ልትጠቀመው እንደማይገባ የሚጠቁምህ ነው። ከሰው በላይ ነኝ ብለህ በማሰብ በአንደበት ና ተግባርህ ጨቋኝ እንድትሆን የሚያደርግህ ego በረሱሊና በጧኢፍ ክስተት ካልተገራ ሰዉ መሆንም መመራመርም ይጎድልሀልና ግድየለም ራስህን መርምር። ረሱሊ በዛ ሰአት ላይ ከአላህ እገዛ ጋር ያሻቸውን የማስፈፀም አቅሙ ነበራቸው። ነገር ግን ያ አቅም ከሰው በላይ ነኝ ብለው እንዲያስቡ አላደረጋቸውም ፥ ይልቅ ምንም አለማድረግንና ማለፍን እንዲሁም ከአላህ የሆነ ይቅርታን ነበር የጠየቁላቸው። ይህ የነብያቶች መገለጫ ቢሆንም በነሱ መገለጫ የሆነን ትምህርት ካልወሰድክና ካልተመራመርክ ግን ትልቅ ችግር አለና እስቲ ጉዳዩን እሰብበት። እየቻልክ ልታልፋቸው የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች አሉ። መናገር እየቻልክ በዝምታ የምታልፋቸው ብዙ ቦታዎች አሉ። እውነቱን እያወቅክ ባለማወቅ የምታልፈው አጋጣሚ አለ። ለአፀፋ የሚበቃ አቅም አለህ ግና ዟሊሞችህን በይቅርታህ ታልፋቸዋለህ። መተላለፍ ነው የሚያቆየን ወዳጄ! በተለይ በኛ ዘመን ሚያኗኑረን ይኸው ነውና አንዳንዴም የመተላለፍን ጥበብ አክብር። (አብድልቃድር ኑር)
إظهار الكل...
🔥 5👍 2 2
በብዙ ተከበዉ ያላዩት "አንድ" መጥቶ ስለሚሞላዉ ባዶነት ለሚናዉዙ ሥሥ ልቦች ...                        .... የማያዉቁት ጠረን ይናፍቃል። ©samuel_dereje
إظهار الكل...
9👍 1🔥 1
በሐያትህ እንጥፍጣፊ ፍቅር የቀረህ ቢሆን እንኳ ለእርሱ ሰዋው🤍 ሂድ ወደፍቅር አክናፍ እንዳሻህ ብረር ግና መዳረሻህ አላህ ይሁን። ምን ሳይገድህ ያሻህን አፍቅር ግና ያልጎደለ ሙሉ ፍቅርህን በሱ ላይ አርጋ። በዚህ አዲስ አመት ወደአላህ ሂጅራ የምናደርግበት ና ከሱም ጋር የምንቆይበት ይሁን🤍 #1446 (አብድልቃድር ኑር)
إظهار الكل...
19👍 1
Reminder6: Be careful with ur words¡ U never knw how many times it keep repeating in someone's mine. (አብድልቃድር ኑር)
إظهار الكل...
9🔥 2👍 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ተከትሎ እነሆ አዲስ ዜና🤍 እንኳን ለ1446ኛው የሒጅራ አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤍 እስከዛሬ በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። ይኸውም የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ልዩ ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል አርዕስት ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። መልካም ቆይታ! #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #በአብድልቃድር_ኑር #ሐምሌ_20 #z_spicesoul
إظهار الكل...
50.79 MB
🥰 5 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ተከትሎ እነሆ አዲስ ዜና🤍 እንኳን ለ1446ኛው የሒጅራ አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤍 እስከዛሬ በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። ይኸውም የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ልዩ ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል አርዕስት ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። መልካም ቆይታ! #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #በአብድልቃድር_ኑር #ሐምሌ_20 #z_spicesoul
إظهار الكل...
50.79 MB
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ምክንያት በማድረግ እነሆ አዲስ ዜና! በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል ርዕስ ላይ ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። #ሐምሌ_20 #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #አብድልቃድር_ኑር
إظهار الكل...
አለም አቀፍ ሙስሊም ማህበረሰብን መሰረት ያደረገና የዘመኑን የመጠነ የእስልምናን እውቀት በተደራጀ መልኩ ለእውቀት ፈለጊዎች በጥያቄ እና መልስ መልኩ ሊዘጋጅ የታሰበ Islamic Social media ነው። ከስር ያለው ሊንክ የአዳማ የሶፍትዌር ተማሪ ከሆነ አንድ ወንድማችን ተግባር ላይ ሊያውሉ ላሰቡት ኢስላሚክ ፕሮጀክት እንድንሞላው የተላከ ፎርም ነው። ይሄን ዶክመንት እንድትሞሉት የተፈለገበት ምክኒያት አንድ የሙስሊሞ social media ምን አይነት ይሁን?.. በምን አይነት ይዘት የሚለውን ከእናንተ መልሶች በመነሳት ልንሰራው ያሰብነውን project በናንተ በኩል ያለውን ፍላጎት በአማካኝ በስራችን ላይ ለማካተት ነው፤ ያው ስራው ለእናንተው ስለሆነ። ፎርሙ ባስቀመጠላችሁ አማራጭ መሰረት ከስር ባለው ሊንክ በመግባት መሙላት ትችላላችሁ። https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfUESPdeNv197lX8wq5FhfodOCF9Af10qL9DlQEvn7GtVRQ-A/viewform
إظهار الكل...
Islamic Social Media Landscape Survey

Introduction: The Ijtihad project is conducting this survey to better understand how Muslims currently use social media platforms to access and engage with Islamic content, as well as to gather feedback on the desired features and capabilities for an Islamic-focused social media platform. Your responses to this survey will help shape the development of a new social media platform designed specifically to cater to the needs of the Muslim community worldwide. This platform aims to provide a reliable, scholar-verified space for finding authentic Islamic knowledge, participating in meaningful discussions, and strengthening one's faith and connection to the ummah. Purpose: The primary objectives of this survey are to: Identify the most commonly used social media platforms by Muslims and the primary purposes for which they utilize these platforms. Understand the types of Islamic content and discussions that Muslims typically seek out on social media. Assess the current level of satisfaction with the ability to find…

👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.