ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!! https://t.me/Abumuseab
إظهار المزيد📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን
تُعد قناة ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን (@abumuseab) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 11 064 مشتركاً، محتلاً المرتبة 8 095 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 3 025 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 11 064 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 29 سبتمبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 506، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 17، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 8.65%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 5.32% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 955 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 587 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 8.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Abumuseab”
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 30 سبتمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
جاري تحميل البيانات...
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 30 سبتمبر | +30 | |||
| 29 سبتمبر | +17 | |||
| 28 سبتمبر | +34 | |||
| 27 سبتمبر | +18 | |||
| 26 سبتمبر | +16 | |||
| 25 سبتمبر | +30 | |||
| 24 سبتمبر | +2 | |||
| 23 سبتمبر | +24 | |||
| 22 سبتمبر | +12 | |||
| 21 سبتمبر | +22 | |||
| 20 سبتمبر | +47 | |||
| 19 سبتمبر | +28 | |||
| 18 سبتمبر | +16 | |||
| 17 سبتمبر | +32 | |||
| 16 سبتمبر | 0 | |||
| 15 سبتمبر | +35 | |||
| 14 سبتمبر | +9 | |||
| 13 سبتمبر | +6 | |||
| 12 سبتمبر | +31 | |||
| 11 سبتمبر | +4 | |||
| 10 سبتمبر | +12 | |||
| 09 سبتمبر | 0 | |||
| 08 سبتمبر | +38 | |||
| 07 سبتمبر | +8 | |||
| 06 سبتمبر | +21 | |||
| 05 سبتمبر | +6 | |||
| 04 سبتمبر | +10 | |||
| 03 سبتمبر | +21 | |||
| 02 سبتمبر | +6 | |||
| 01 سبتمبر | +20 |
| 2 | የኢትዮጵያ ሰለፍይ ኡለሞች መስከረም 15/2018 ባደረጉት ስብሰባ፣ በሰለፍዮች መካከል አለመግባባቶች ሲፈጠሩ፤ ጉዳዩ በየአካባቢው ለሚገኙ መሻይኾች እየቀረበ፣ በውይይት እንዲፈታ የጋራ ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት በሰሜን ወሎ፣ በሀራና አካካቢው በአህለሱና ውንድሞቻችን መካከል የተከሰተው አለመግባባት፣ ከላይ በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት ጉዳዩን እንዲያዩ በተመደቡት የአካባቢው መሻይኾች አማካኝነት እንዲታይና መፍትሄ እንዲቀመጥለት ቀደም ሲል በቃል ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፣ አሁንም በፅሁፍ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
የኢትዮጵያ አህለ ሱና ማህበር
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة | 158 |
| 3 | አንተ የዲን ተማሪ ሆይ! በህዝቡ መሃል የነቢዩን (ﷺ) ስም የማያውቅ ትውልድ እያለ እንዴት ትተኛለህ? እንዴትስ ዓይንህን እንቅልፍ ይሞለዋል?!!
—————
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ሙስሊሞችን ከአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር አስተዋውቋቸው። ለሙስሊሞች የአላህን መልእክተኛ ሱናቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ስነ-ምግባራቸውን፣ ዘዴያቸውንና የአኗኗር ዘይቤያቸውን የነበሩበትን ሁኔታ ሁሉ አሳውቋቸው (አስተምሯቸው)። ምክንያቱም ሙስሊሞች አርኣያ አድርገው የሚከተሏቸው ናቸውና፣ ሁኔታውን እና ታሪኩን ያላወቁትን አካል እንዴት አርኣያ አድርጎ መከተል ይቻላል?!፣ በምን ሁኔታ ነው ሊከተሉትስ የሚቻለው?!
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን መልእክተኛ (ﷺ) እንዲከተል ታዞ ግን ደግሞ ስማቸውን እንጂ የማያውቅ ከሆነ (እንዴት ሊከተላቸው ይችላል?)። ጭራሽ ስማቸውንም የማያውቅ አለ፣ በሙስሊሞች ውስጥ የአላህን መልእክተኛ ስም የማያውቅ አለ፣ ይህን በዓይኔ አይቻለሁ በሁለት ጆሮዬም ሰምቻለሁ። አንድ ሆስፒታል ውስጥ አንዲት ሴት ልጇ ምርመራ እየተደረገለት ዶ/ሩ የነቢያችሁ ስም ማነው? አላት፣ ነቢዩ ናቸው ሰለዋት አውርድ አለችው። ዶ/ሩም:- (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስሙ ማነው? አላት፣ እሷም:- ነቢዩ ናቸው ሰለዋት አውርድ አለችው። እኮ ስማቸው ማነው? አላት፣ እንደመጀመሪያው ደጋገመችው፣ ተገርሞባት ነቢዩ ሙሳ ነው? አላት፣ ከዛም ዳግም ነቢያችን ማነው? አላት፣ ነቢያችን ሙሳ (ዐለይሂሰላም) ነው አለች። ከዛም ፈጠን ብላ ወጣች፣ ለዶ/ሩ ይህች ሴት ከወጣች ነቢያችን ሙሳ ነው የሚለው ከልቧም ከአንደበቷም አይወጣምና ጥራትና አስተካክለህ ንገራት አልኩት፣ ተመለሰችና ነቢያችን እኮ ሙሀመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ናቸው ስትባል እንቢ አለች፣ ለምን? ዶ/ሩ መጀመሪያ ነቢያችን ሙሳ ነው ያላትን የምር አድርጋ ይዛ ልቧ እዚያው ላይ ፀና። ይሀውልሽ ነቢያችን እኮ ሙሀመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ናቸው ብሎ ጠንከር አድርጎ ቢሟገታትም እንቢ አለች።
በህዝቡ ውስጥ በትክክል የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስም የማያውቅ አለ፣ እናንተ ምን እየሰራችሁ ነው?! ምን እየሰራችሁ ነው?!! በምንድነው ጊዜያችሁን የምታቃጥሉት? በምንድነው ንብረታችሁን ወጪ የምታደርጉት?! በምንድነው አቅማችሁን የከፋፈላችሁት?! በምንድነው ሀይላችሁን የበታተናችሁት?!
ህዝቡ በዚህ ሁኔታ እያለ፣ አንድም የልጁን እጅ ይዞ ትክክለኛውን ቀጥ ያለውን መንገድ የሚያመላክት አታገኙም ታዲያ እናንተ ምን እየሰራችሁ ነው?! በህዝቡ የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስም የማያውቅ በመኖሩ ሙስሊሙ አያፍርም?! ይህን ተጨባጭ የሚያወቅ የነቢዩ ሙሀመድ (ﷺ) ተከታይ እንቅልፍ ሲተኛ አያፍርም?! እንዴት ይተኛል?! በነቢዩ ህዝብ ውስጥ ይህን ከባድ የሆነን ጉዳይ የሚያውቅ ሰው ዓይኑ እንዴት (በእንቅልፍ) ጨለማ ትረጋለታለች?!
እናንተ የዲን ተማሪዎች ሆይ! ሀይላችሁን በባዶ መበተናችሁ ይብቃችሁ!፣ አቅማችሁን በከንቱ መከፋፋላችሁ (ማባከናችሁ) ይብቃችሁ!! ጌታችሁን አላህን ፍሩት!!… ተግባቡ፣ ተረዳዱ፣ ተጣበቁ፣ በሀቅ ላይ ታላቁን ፈጣሪ ብቸኛ በማድረግ ላይ ታገሱ!! እርሱን አጥብቆ በመያዝ, ወደርሱ ጥሪ በማድረግ ላይ (ታገሱ)። የመልእክተኞች አለቃ የሆኑትን ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አውቆና አጥብቆ በመከተል፣ በሀቅ ላይ በመታገስና ወደሳቸው መንገድ ጥሪ ማድረግ ነው።
የላቀውን አላህን ከገፍላና ከመዘናጋት እንዲያነቃን እለምነዋለሁ!! አብሳሪና አስጠንቃቂ በሆኑት ነቢይና በባልደረቦቻቸው ሁሉ የአላህ ሰላምና እዝነት ይስፈን!!።”
[ከታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን ሙሃደራ ተወሰዶ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው።]
ይሄው ነው እውነታው!! በሀገራችን ስለ ነቢዩ (ﷺ) ሲጠየቅ "አላህም ነቢዩም አንድ ናቸው" የሚል ትውልድ ይዘህ በቁጥሩ ብዛት መሸንገል ትተህ ትክክለኛውን ዐቂዳ እና የሚቃረነውን ነገር አስተምረህ መሰረቱን አስተካክለው። አንድ ሰው ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ሳይችል ለዲን እለፋለሁ ቢል፣ ልፋቱ የውሸት ነው፣ ወይም መንገዱ ጠፍቶታልና ቆም ብሎ ሊያስብበት ይገባል!! ወንድሜ ሆይ! ሳይመሽብህ ያወቅከውን አሳውቅ!!
"ሰለጠንኩ ከተሚይ ነኝ" እያለ፣ ለኩፍር ስርኣት (ለክርስቲያኖች) መቻቻል በሚሉት መጃጃል ስም፣ የጥምቀት ቦታቸውን እያፀዱ በመጨረሻም "አልሀምዱሊላህ ታቦታችን በሰላም ገባ" የሚለውን እስልምናን እና ክርስትናን ለይቶ የማውቅ ትውልድ ከሁሉ በፊት የሀይማኖቱን ህግና ስርኣት ለይቶ እንዲያውቅ ማድረግ ከሁሉ ነገር ይቀድማል!!። እንዲህ ያለ ትውልድ ይዘህ ቅድሚያ ለተውሒድ ስትባል ዓይንህ ሲቀላ ነው ምታሳዝነኝ።
የአንዳንድ ሰዎች ሁኔታ ይገርመኛል! የነቢዩን (ﷺ) ሲራ ያስተምራሉ ዋና ግቡ እና የተደረገው ተጋድሎ መነሻው ግን ተውሒድ እንደሆነ አያስጨብጡም። ቁርኣን ተፍሲር ያስተምራሉ ሰነዳቸው ያልተጣሩ ቂሳዎችን እያራዘሙ ታዳሚውን አፍ ከማስከፈት አልፈው ለታዳሚው ቁርኣን ከላይ እስከታች ተውሒድ መሆኑን አያስጨብጡትም!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa | 443 |
| 4 | || አዲስ ሙሓደራ
🔗« በዓለም አቀፉ ፕሮግራም በOnline የቀረበ ሙሓደራ »
🎙ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል ለተሚይ
🗓 ረቢዕ ሳኒ 15/4/1448
t.me/abdulham/2893
t.me/abdulham/2893 | 823 |
| 5 | ከታች ከተዘረዘሩት ወንጀሎች ውስጥ የትኛውን ወንጀል ነው አላህ በቁርአኑ ውስጥ እንደማይምረው የነገረን።
ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላቹን የሰለፊዮች ቻናሉ ይቀላቀሉ። | 394 |
| 6 | 🔵የዱንያ ስኬት
ከፈጅር በፊት 10፡00 ወይም ከዚያ በፊት ተነስተህ 2 ወይም 4 ረከዓት ወይም የቻልከውን ሰግደህ ዊትር አድርግ። ከዚያም አላህን ኢስቲግፋር ጠይቅ። ፈጅርን በጀመዓ ሰገድ።
በአላህ ፍቃድ በዱንያ ህይወትህ ደስተኛ ህይወትን ታገኛለህ።
ኡስታዝ በሕሩ ተካ ሐፊዘሁላህ
ከሱረቱ አዝዛሪያት ቁጥር 17 እና 18 ማብራሪያ ላይ የተወሰደ
https://t.me/medresetulislah | 1 136 |
| 7 | 🔊 አዲስ ሙሐደራ
ርዕስ፦“ስለ ዱዓእ”
🎙ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁላህ
🕌 ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ!
🗓 ረቢዐ'ሳኒ 14 (1448)
https://t.me/abdulham/2892
https://t.me/abdulham/2892 | 788 |
| 8 | አዲስ ደርስ
📚ኢስቲቃማን በተመለከተ አስር መርሆዎች
✍ፀሃፊው ሼኽ ዐብድረዛቅ አል በድር
ክፍል 9
ዘወትር ዐርብና ቅዳሜ ከዒሻ ቦሃላ ሚቀራ
http://t.me/ibnawolllll | 951 |
| 9 | ሳምንታዊ የእሑድ ደርስ
1. ዑምደቱል አሕካም
🕰 ከ3:30 እስከ 4:45
https://t.me/medresetulislah/11235
🎤 በኡስታዝ፡ ዐብዱልቃዲር ሐሰን ሐፊዘሁሏህ
2. ኢጅማዑል ዑለማኢ ዐለል ሐጅሪ ወትተሕዚሪ ሚን አህሊል አህዋእ
🕰 ከ4:45 እስከ 6:00
https://t.me/medresetulislah/11173
🎤 በኡስታዝ በሕሩ ተካ ( አቡ ዑበይዳ ) ሐፊዘሁሏህ
የሚሰጥ ይሆናል ኢንሻ አላህ
✍️ አል ኢስላሕ መድረሳ
https://t.me/medresetulislah | 738 |
| 10 | ሳምንታዊ የዳር አስ-ሱንና የእለተ እሁድ ደርስ
🕰 ከረፋዱ 3:50 እስከ ዙህር የሚቆይ
በኡስታዝ አቡ ሙዓዝና በኡስታዝ ሻኪር የሚሰጥ
ኪታቦች:-
ኪታብ ①
الحث على المودة والإئتلاف والتحذير من الفرقة والاختلاف
በመወዳጀትና በመግባባት ላይ ማነሳሳትና ከልዩነትና ከቡድንተኝነት ማስጠንቀቅ!!
لفضيلة الشيخ الدكتور ربيع بن هادي عمير المدخلي رحمه الله
የኪታብ pdf ↘️
https://t.me/DarASSunnah1444/15820
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ)
ኪታብ ②
كتاب نور التوحيد وظلمات الشرك في ضوء الكتاب والسنة
የተውሒድ ብርሃንነትና የሺርክ ጨለማነት በቁርኣንና በሀዲስ ብርሃን ሲቃኝ
የኪታብ pdf ↘️
https://t.me/DarASSunnah1444/15819
🎙በኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁላህ) | 739 |
| 11 | 🌸 ጥያቄ 🌸
📖 ወደ አድ ሕዝቦች ተውሒድን እንዲሰብክ የተላከው ነብይ ማነው?
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✅ ትክክለኛውን መልስ በመጫን
📲 ወደ ሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ! | 1 016 |
| 12 | 💎በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዓለም አቀፍ የሙሃዶራ ፕሮግራም
ተጀመረ
ገባ
ገባ
በሉ
↘️↘️↘️↘️
https://t.me/bilalmesji?videochat | 1 259 |
| 13 | 🎧🎧🎧
በየ ሣምንቱ ጁሙዓ ቀን
በዊሽአሞ ቀበሌ በፉርቃን መድረሳ በሀላቢሣ ቋንቋ የሚደረግ ተከታታይ ሣምንታዊ ደዕዋ ነውና አድምጡ ይጠቅማችኋል !!
https://t.me/Abu_hafsa_ibnu_mekino/2783 | 1 005 |
| 14 | ◆ ረሱላች v ን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰሊም)
🚫 በራሳችሁ ላይ ዱዓ አተድርጉ
🚫በልጆቻችሁም ላይ ዱዓ አታድርጉ
🚫በገንዘባችሁም ላይ ዱዓ አታድርጉ
አላህ ተጠይቆ የሚሰጥበትን ሰዓት አትግጠሙ ለእናንተህ እሺ መርሀባ ሊላችሁ።
https://t.me/AbraribnAwal | 1 009 |
| 15 | 🟢አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው
� سؤال وجواب �
↞ ما نصيحتكم للدعاة الذين يستعملون الذكاء الاصطناعي في كتابة الردود والمقالات وينشرونها بأسمائهم؟
▫️إجابة الشيخ العلامة أ .د:
عبد الله بن عبد الرحيم البخاري
حفظه الله ونفع بعلمه
🎙مقتطف من الدرس التاسع من شرح «الأربعون في الأحكام»
•
https://t.me/dr_elbukhary/5261
•
الذكاء الاصطناعي
Artificial Intelligence
(AI)
አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው የሚለቁ ዳዒይ ተብዬዎች
ረድ እና ሌላም ፅሁፍ ይፅፋሉ የሚገርመው
አርቴው ከተሳሳተ እነርሱም ከነ ስህተቱ በጭፍን ተቅሊድ ይለቁታል ወይም ፕሮፋይል ያደርጉታል። ያልሆነውን አስመስለው ያቀርቡታል። እነዚህን ዳዒይ ተብዬ አብረቅራቂዎችን ተጠንቀቁ። የዲን ሿሿ እንዳይሰሯችሁ።
አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ደጅ ላይ የተለጠፈው ያማረ ዳቦ ቢጤ ነው።ፍቶውን የሚመስል ዳቦ ያመርታሉን!? ጠይቋቸው
https://t.me/FATTAWAS | 567 |
| 16 | 👉 የሀራው ጉዳይ ጥንቃቄ ይፈልጋል !
ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን በሙሉ ሁሉም እንደሚያውቀው በቅርቡ በሀራ ሰለፍይ ወንድሞቻችን መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል ። ከዛ በፊት በሀላባ ሰለፍዮች መካከልም የተፈጠረው አለመግባባት እልባት አላገኘም ። እንደዚህ አይነቶቹ አለመግባባቶች ሁሉንም ሰለፍዮች ያሳዘነ መሆኑ ግልፅ ነው ። የሶሞኑ የሀራው አለመግባባት ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅ ፣ ከማጥበብ ይልቅ ወደመስፋት እየሄደ ነው ። ሀላባም ይሁን ሀራ ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በሰለፍዮች መካከል መሆኑ ግልፅ ነው ። አይደለም የሚል ካለ ማንኛው ከሱና እንደወጣ በመረጃ ግልፅ ማድረግ ይኖርበታል ።
የሀራው አለመግባባት ደግሞ በመሻኢኾችና በተማሪዮቻቸው መካከል መሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ። በመሆኑም መሻኢኾቹም ሆኑ ተማሪዮቻቸው አላህን ፈርተው ከስሜት ርቀው ችግሩን በሰከነ መልኩ ለመፍታትና የሰለፍቶችን አንድነት ለመጠበቅ የሚችሉትን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ። አለመግባባቱ ከማንም በፊት ዳዕዋውን ይጎዳል ። ሁሉም ቆም ብሎ ቢያስተውል ለዚህ ዳዕዋ ሰለፎች የከፈሉትን መስዋእትነት አይቶ እኔ የሚለው ስሜት ራስን ከመውቀስ ጋር እንዲጠፋ ማድረግ በተቻለ ነበር ። አሁንም አረፈደም ። መሻኢኾች የተማሪዮቻቸውን ጥፋትና ስህተት ለማረም መንገዱን ከሰሎፎች ተሞክሮ መውሰድ የግድ ነው ። ይረዝምብኛል ባልል በጣም ብዙ ማሳያዎችን በጠቀስኩ ነበር ። ተማሪዮችም የመሻኢኾቻቸውን ስህተትና ጥፋት የሚሉትን በምን መልኩና እንዴት ማረም እንዳለባቸው ከሰለፎቻቸው በቂ ተምሳሌት አለላቸው ።
ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ ነጥብ መከባበር ፣ መተዛዘን ፣ ስህተትን በስተትነቱ መስተካከል ያለበት መሆኑን ማመንና መንገዱን ወደ ቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ ላይ አድርጎ ተሞክሯቸውን መጠቀም ነው ። በመሆኑም ሁለቱም የሱና ወንድሟሟቾች አላህን ፈርተው ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ ምንም አይነት ነገሮችን የሚያባብሱ ነገሮችን ከመፃፍም ሆነ ከመናገር እንዲቆጠቡ በአላህ ስም እጠይቃለሁ ።
ሌላው በየቦታው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ትፈታላችሁ ተብሎ ሀላፊነት የተጣለባችሁ የሀገራችን የሱና መሻኢኾች የሰለፍያን ዳዕዋ እንደ እሳት የሚበላውን የሰለፍዮችን አቅም የሚያዳክመውን ከአላህ እዝነት የሚያርቀውን አሳዛኝ አለመግባባት እንደሰደድ እሳት እየተዛመተ ሰለፍያን ከመብላቱ በፊት ቅድሜያ ሰጥታችሁ እንድትፈቱ ለዚህም የትኛውንም ዋጋ እንድትከፍሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ ።
በመጨረሻም በየትኛውም አካባቢ በሰለፍዮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶች በአላህ ፈቃድ በአጭር ጊዜ ተፈተው ሰለፍዮች ወደ አንድነታቸው እንደሚመለሱ በአላህ ተስፋ እንድናደርግ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ። ለዚህ አላማ የትኛውም ሰለፍይ የትም ሆኖ የሚችለውን እንዲያደርግ አደራ እያልኩ ከዚህ ሰአት ጀምሮ ከየትኛውም አለመግባባቱን ከሚያሰፉ ተግባሮች ተቆጥበን ወደ መግባባት የሚያደርሱ ሰበቦችን በማድረስ ተራ በተራ የሁሉም ሰለፍዮች የደስታ ብስራት የሚነገርባቸውን ቀናቶች እንጠብቅ እላለሁ ። አላህ ይረዳናል ሰለፍዮች አንድ ይሆናሉ ተውሒድና ሱና በሰለፍዮች ጥረትና በአላህ እገዛ የበላይ ይሆናሉ ።
https://t.me/bahruteka | 526 |
| 17 | 👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !
ክፍል አስራ ሁለት
ሰይድ ቁጥብ የነብዩን ሶሓቦች የሚሳደብ ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ ማረጋገጥ !
ሁለተኛ : ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን ሲሳደብ !
ባሳለፍናቸው ክፍሎች ለማየት እንደሞከርነው የነብዩን ሶሓቦች መውደድ ኢማን ሲሆን እነርሱን መጥላት ደግሞ ኩፍርና ኒፋቅ ነው ። ይህ ማለት የሚወዳቸው ሙእሚን ነው ማለት ነው የሚጠላቸው ደግሞ ሙናፊቅ ! ምክንያቱ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ አደራና ኑዛዜ ነው ። ሶሓቦቼን በመጥፎ አታንሱ አትጥሏቸው ብለው አደራ ብለውናልና ። ከዚህም በላይ የወደዳቸው እኔን ለመውደዱ ነው የሚጠላቸውም እኔን ለመጥላቱ ነው ብለውናል ። እንደሚታወቀው ነብዩን መጥላት ኩፍር ነው ። ሶሓቦችን መጥላት ደግሞ ነብዩን መጥላት ነው ።
የነብዩን ሶሓቦች የምንወደው አላህ መርጦ የሳቸው ባልደረባ ስላደረጋቸውና ለእስልምና ህይወታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ እውቀታቸውን ፣ ገንዘባቸውን ጭምር ቤዛ ስላደረጉ ነው ። ለነብዩ ሸሪዓ ብለው ተሰደዋል ፣ ተርበዋል ፣ ተጠምተዋል ፣ ተገርፈዋል ፣ በእሳት ተቃጥለዋል ፣ በመካ ሀሩር የነደደ ቋጥኝ በእነርሱ ደም እንዲቀዘቅዝ ተደርጓል ። ለዚህ ነው አላህ ያላቃቸው ያከበራቸውና ዝናቸው ከፍ እንዲል ያደረገው ። በዚህ አላበቃም አመኞችን በመልካም እንዲያነሱዋቸውና ፈለጋቸውን እንዲከተሉ አዟል ። ይህ ነው የመወደዳቸው ሚስጢር ። ለዚህ ነው ሙእሚን እንጂ አይወዳቸውም ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም የተባለው ።
እነዚህን የአላህ መልእክተኛ ባልደረቦችን ነው ሰይድ ቁጥብ የሚያዋርደውና የሚያንቋሽሸው ። በአላህ ይሁንብኝ የሙሐመድ ሓሚዲን ጥብቅና ባይኖርና ወጣቶች እሱን ሰምተው የሰይድ ቁጥብን ተግባር ቀለል አድርገው በማየት ልባቸው ይታመማል ሳያውቁት ኒፋቅ ሊገባባቸው ይችላል የሚለው ስጋት ባይኖር ኖሮ የሰይድ ቁጥብን ቅርሻት ባልፃፍኩኝ ነበር ። ነገር ግን የዚህ ሰው ማንነት ሙሐመድ ሓሚዲን ከሚለውና ከሚገልፀው በጣም የራቀ ይልቁንም ራሱ አምኖበት በተናገረው ንግግሩና ፅሑፉ የአላህ መልእክተኛን ሶሓቦች የሚያዋርድና የሺዓዎችን አንጀት የሚያርስ በሶሓቦች ክብር ተረማምዶ በራፊዳዎች ሜዳሊያ የተሸለመ ግለሰብ መሆኑ እንዲታወቅ ነው ። ለማንኛውም ማየት ማመን ነውና እስኪ በነብዩ ላይ ይወርድ የነበረውን ወሕይ ከሚፅፉት የነበረውን ፣ የመጀመሪያውን በባህር ላይ የተደረገውን ዘመቻ የመራውን ፣ የምእመናን አጎት የሆነውንና የአላህ መልእክተኛ ዱዓእ ያደረጉለትን ብርቅዬ ሶሓብይ ሙዓውያንና ጓደኛውን ታላቁን ሶሓብይ ዐምር ኢብኑ ዓስም ምን እንደሚላቸውና እንዴት እንደሚያዋርዳቸው እንመልከት : –
"إن معاوية وزميله عَمْراً لم يغلبا علياً لأنهما أعرف منه بدخائل النفوس، وأخبر منه بالتصرف النافع في الظرف المناسب . ولكن لأنهما طليقان في استخدام كل سلاح، وهو مقيد بأخلاقه في اختيار وسائل الصراع . وحين يركن معاوية وزميله إلى الكذب والغش والخديعة والنفاق والرشوة وشراء الذمم لا يملك عليٌ أن يتدلى إلى هذا الدرك الأسفل فلا عجب ينجحان ويفشل، وإنه لفشل أشرف من كل نجاح ".
كتب وشخصيات ص (242)
" ሙዓዊያና ጓደኛው ዓምር ዐልይን ያሸነፉት ከሱ የበለጠ በሰዎች ውስጥ ያለውን በማወቃቸው ወይም በክስተቶች ጠቃሚ የሆነውን መንገድ በመከተል ከሱ የበለጠ እውቀት ኖሯቸው አይደለም ። ነገር ግን እነርሱ ለማሸነፍ የሚያስችለውን የትኛውንም መንገድ በመከተል ልቅ ስለሆኑና እሱ ግን በፍልሚያ ጊዜ መጠቀም ያለበትን መንገድ እንዲመርጥ በባህሪው የተገደበ ስለነበረ ነው ። ሙዓዊያና ጓደኛው ወደ ውሸት ፣ ማታለል ፣ ክህደት ፣ ንፍቅናና ፣ ጉቦ በመስጠት የሰዎችን ጫንቃ ወደመግዛት በተዘነበሉ ጊዜ ዐልይ ወደዚህ ዝቅጠት መዝቀጥ አይችልም ነበርና እነርሱ በማሸነፋቸውና እሱ በመሸነፉ መገረም አያስፈልግም ። መሸነፉ ከየትኛውም ማሸነፍ በላይ ክብር ነበርና " ።
ተመልከቱ ሰይድ ቁጥብ ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን በውሸት ፣ በማታለል ፣ በክህደት ፣ በሙናፊቅነት ፣ ጉቦ ሰጥቶ ሰዎችን በመግዛት ያሸነፉ ብሎ እንዴት እንደሚወርፋቸው ‼ ሱብሓነላህ ! እንዴት ይሆን ነገ አላህ ፊት ከሙዓዊያና ኢብኑል ዓስ ጋር ከሳሽና ተከሳሽ ሆኖ የሚቀርበው ? ለዛው ጠበቃቸው የአላህ መልእክተኛ ሆነው እሱ ነብዩ ለምን ሶሓቦቼን ሰደብክብኝ ሲሉት መልስ ሊሰጥ ! ከዚህ በላይ የሚገርመው ደግሞ የሶሓቦች ጠበቃ የአላህ መልእክተኛ ሆነው የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ ደግሞ ሙሐመድ ሓሚዲን ሆኖ አላህ ፊት መገናኘታቸው ነው ።
አላህ ሆይ አንተ ጠብቀን !
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
https://t.me/bahruteka | 1 181 |
| 18 | فيديو من حسين عبد الله | 765 |
| 19 | فيديو من حسين عبد الله | 1 |
| 20 | የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]
② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]
③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]
④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]
⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]
⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]
ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]
⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]
ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f | 990 |
