ar
Feedback
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

الذهاب إلى القناة على Telegram

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

تُعد قناة ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa (@ibnshifa) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 452 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 110 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 1 758 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 452 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 01 أغسطس, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 332، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 11، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 12.66‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 5.13‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 2 463 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 998 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 0.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 02 أغسطس, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

19 452
المشتركون
+1124 ساعات
+797 أيام
+33230 أيام

جاري تحميل البيانات...

سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
أغسطس '26
أغسطس '26
+11
في 13 قنوات
يوليو '26
+427
في 71 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+601
في 116 قنوات
Get PRO
مايو '26
+127
في 113 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+177
في 121 قنوات
Get PRO
مارس '26
+458
في 112 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+476
في 117 قنوات
Get PRO
يناير '26
+190
في 73 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+318
في 101 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+191
في 97 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+265
في 115 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+232
في 119 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+154
في 80 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+409
في 121 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+282
في 117 قنوات
Get PRO
مايو '25
+177
في 116 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+241
في 115 قنوات
Get PRO
مارس '25
+315
في 101 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+385
في 123 قنوات
Get PRO
يناير '25
+1 036
في 117 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+226
في 112 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+251
في 95 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+340
في 96 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+155
في 72 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+130
في 73 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+151
في 84 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+218
في 89 قنوات
Get PRO
مايو '24
+260
في 98 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+439
في 111 قنوات
Get PRO
مارس '24
+476
في 86 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+229
في 69 قنوات
Get PRO
يناير '24
+295
في 72 قنوات
Get PRO
ديسمبر '23
+285
في 76 قنوات
Get PRO
نوفمبر '23
+333
في 79 قنوات
Get PRO
أكتوبر '23
+365
في 62 قنوات
Get PRO
سبتمبر '23
+358
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '23
+460
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '23
+316
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '23
+390
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '23
+393
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '23
+302
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '23
+256
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '23
+258
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '23
+305
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '22
+330
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '22
+340
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '22
+490
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '22
+275
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '22
+201
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '22
+278
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '22
+186
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '22
+290
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '22
+305
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '22
+665
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '22
+52
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '22
+94
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '21
+168
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '21
+92
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '21
+130
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '21
+185
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '21
+363
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '21
+268
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '21
+281
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '21
+992
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '21
+725
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '21
+634
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '21
+582
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '21
+850
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '20
+9 649
في 0 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
01 أغسطس+11
منشورات القناة
እኛስ በጥላው ስር የምንሆንበት ከየትኛው የመልካም ስራ አይነት አለንበት?! እራሳችንን እንፈትሽ!! ————— አቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:- “ሰባቶቹን አላህ ጥላ በሌለበት ቀን በጥላው ስር ያደርጋቸዋል፣ 1, ፍትሃዊ መሪ፣ 2, አላህን በማምለክ (በዒባዳ) ያደገን ወጣት፣ 3, ልቡ ወደ መስጂድ የተንጠለጠለን ሰው፣ 4, ሁለት ለአላህ ብለው የሚዋደዱ ሰዎችን በእርሱ ጉዳይ ዱኒያ ላይ የተሰባሰቡ ሆነው በሞት ምክንያት የተለያዩ፣ 5, የመልካም ዝና (የተከበረ) ቤተሰብ አባልና የቁንጅና ባለ ቤት የሆነች ሴት ለሀራም ነገር ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያላትን ወንድ፣ 6, ቀኝ እጁ የምትሰጠውን ግራ እጁ እስከማታውቅ ሶደቃን ደብቆ ለአላህ ብሎ የሰጠን ሰው፣ 7, ብቻውን ገለልተኛ ቦታ ሆኖ አላህን በማስታወስ ዓይኖቹ ያነቡን ሰው።” [ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል] ታላቁ ሊቅ ኢብን ረጀብ አል-ሀንበሊ (ረሂመሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:- “ከእነዚህ ከሰባቶቹ የመጀመሪያው ፍትሃዊ መሪ ነው የተጠቀሰው። እርሱም በእለተ ትንሳዔ ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ አላህ ዘንድ ቅርብ ነው። እርሱም ከአር-ረህማን ከቀኙ በኩል በሚንበር ላይ ነው። ይህ እድልም ስሜቱን አላህን ከማመፅ በመቃረኑ ምክንያት ነው፣ በቁጣ ጊዜም ሆነ በሌላ ጊዜ ያሻውን ለመወሰን ሙሉ ስልጣን እያለው ስሜቱ ወደ ጥፋት እየጠራችው በመታገሱና ስሜቱን በመቆጣጠሩ ምክንያት ነው። ፍትሃዊ መሪ ማለት ዱኒያ በሁሉ ነገሯ ወደ ራሷ ጠርታው እኔ የዓለማቱን ጌታ አላህን እፈራለሁ! ያለ ነው። እንዲህ ያለው መሪ ለአላህ ባሮች እጅግ ጠቃሚ ነው!። እርሱ ከተስተካከለ በጥበቃው ስር ያለው ሁሉ ይስተካከላል። በእርግጥ እንዲህ ያለው መሪ ‘ምድር ላይ የአላህ ጥላ ነው’ የሚልም ተዘግቧል፣ ምክንያቱም ፍጡሮች ሁሉ በእርሱ ጥላ ስር ይጠለላሉና በእነርሱ ፍትሃዊ ሰው ከሆነ አላህ  በጥላው ስር እንዲጠለል ያደርገዋል።” [ፈትሁ'ል ባሪ ሊብን ረጀብ ጥራዝ 4/59] ➣ ታላቁ ፈቂህ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በእርሱ ምክንያት ተሰባስበው በእርሱም ምክንያት የተለያዩ…’ ማለት:- ለአላህ ብሎ በመዋደድ ምክንያት ዱኒያ ላይ ተሰባስበው ውዴታቸው ሞት እስከሚለያያቸው ድረስ ቀጥለው በዚያው ሁኔታ እያሉ በሞት የተለያዩ ማለት ነው። ይህ የሚያመለክተው ለአላህ ብለው የሚዋደዱ ሰዎች ውዴታቸውን አንዳችም ዱኒያዊ ጉዳይ እንደማያቋርጠው ነው። እነርሱ የሚዋደዱ እንደሆኑ ይቀጥላሉ ውዴታቸውንም ሞት እንጂ አያቋርጠውም!። አንዳቸው በሌላኛው ላይ ቢሳሳት (ስህተት ቢፈፅምበት) እንኳን አለያም አንዱ በሌላው ላይ (ከወንድማዊ) ሀቁ ቢያጎድልበት ይህ አያንገበግባቸውም (ለእንዲህ ያለው ነገር ትኩረት ሰጥተው አይጣሉም) ምክንያቱም ለአላህ ብለው ነው የተዋደዱት፣ ነገር ግን ስህተቱን ያስተካክልለታል ያጎደለበትን (ወንድማዊ መብቱን) ግልፅ ያደርግለታል፣ ምክንያቱም ይህ ሙሉ ከሆነው ምክክር ነው። አላህ እኛንም አጠቃላይ ሙስሊሞችንም ለአላህ ብለው ከሚዋደዱት፣ በመልካም ነገርና አላህን በመፍራት ከሚረዳዱት እንዲያደርገን እንጠይቀዋለን!!።” [ሸርህ ሪያዱ ሷሊሂን ጥራዝ 2/155] ❓የቂያማ እለት የተጠቀሰው ጥላ የአላህ ጥላ ወይስ የፍጡር ጥላ ነው?! ታላቁ ፈቂህ ኢብኑ ዑሰይሚን (ዐለይሂ ረህመቱላህ) እንዲህ አሉ:- “በዚያች ከባድ ቀን ፍጥረታትን ከፀሃይ ሊከላከል የሚችል አንዳች ነገር የለም!። ዛፍም ድንጋይም ሆነ የተገነባ ነገር… ሌላም ነገር የለም። ነገር ግን አላህ ከፍጡራኖቹ የፈለገውን መርጦ የሚያጠልልበትን ጥላ ነገር ይፈጥራል፣ በእርሱም ጥላ በሌለበት ቀን በጥላው ስር ያደርጋቸዋል። ይህ ነው የሀዲሱ ትርጉም ሌላ ትርጉም ሌኖረውም አይፈቀደም!።” [ሸርህ ሪያዱ ሷሊሂን ጥራዝ 2/155] ልብ በሉ!:- አላህ ለእለተ ትንሳዔ የሚፈጥረው የሆነ ራሱን የቻለ ጥላ ነገር ነው እንጅ የአላህ የዛቱ ጥላ ነው ማለት አይደለም!። አላህ ሆይ! ወደር የሌለህ አዛኝ ነህና በእዝነትህና በይቅር ባይነትህ ጥላ በሌለበት ቀን በጥላው ስር ከምታደርጋቸው ደጋግ ባሮችህ አድርገን!! ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

2
لا يوجد نص...
702
3
ምርጫው የእናንተ ነው የተመቻቹን ንኩት👇👇👇
281
4
እጅግ በጣም ውድ የሆነውን ሉ'ል ማን ይግዛው?! ——— በአንድ ወቅት አንድ በአደን ስራ የሚተዳደር አዳኝ ሰው ነበረ ይባላል፣ ይህ ሰው የሚተዳደርበት የአደን ስራ ብዙ ጊዜ የሚሳካለት አንዲት ዓሳ አድኖ መያዝ ብቻ ነው፣ ያቺን ዓሳ ከሚስቱ ጋር በመመገብ ይብቃቃሉ፣ አላህ በሰጠው ነገርም ደስተኛ ሆነው ያሳልፋሉ። ከእለታት አንድ ቀን አድኖ ባመጣት ዓሳ ውስጥ ሚስቱ ዓሳውን ስታፀዳ አንዲት እጅግ በጣም ውድና እንደ ሌሎች ሉሎች የማትገኝ ውድ ሉል አግኝታ ለባልየዋ ያገኘችውን ሉል በደስታ ወስዳ ትሰጠዋለች፣ ባልም ይህቺን ሉል ለመሸጥ ሉልና እንቁ ወደሚሸጥበት አንድ ሱቅ ይሄዳል፣ የሱቁ ባለቤትም ቤቴን ጨምሬ ያለኝ ንብረት ሁሉ ብሸጥ ይህን መግዛት አልችልም በማለት አንድ ከፍተኛ አቅም አለው ወደሚባል ሉልና እንቁዎች የሚሸጡበት ማእከል ይልከዋል። እዚያም በተመሳሳይ ይህ ሉል እጅግ በጣም ውድ ነውና ነጋዴዎች ሊገዙህ አቅማቸው ስለማይችል ወደ አሚሩ (የሀገሩ መሪ) ሂድ እሱ ይገዛሃል ይለዋል። ወደ አሚሩ ሲሄድ ይህ ለረጅም ጊዜ ስፈልገው የከረምኩት ግን ደግሞ ላገኘው ያልቻልኩት ውድ ሉል ነውና የምከፍልህ የሚመጥነው ገንዘብ ስለሌለ ወደ ካዝናው (ንብረት ግምጃ ቤት) በመግባት የፈለግከውን ነገር ይዘህ እንድትወጣ ለ6:00 ሰኣታት ያህል የመቆየት ጊዜ እሰጥሃለሁ ይለዋል። 🔶 በ6:00 ሰኣታት ውስጥ ከመንግስት ቤት ካለው ንብረት ምን ይዞ ሊወጣ ይችላል፣ ብላችሁ ገመታችሁ?! ወደ ካዝናው (ግምጃቤት) ተከፍቶላት ገባ፣ ሲገባ የተለያዩ የእንቁ አይነቶችና ወርቅን ጨምሮ ተቆልሎ የተቀመጡ የንብረት አይነቶችን ተመለከተ። አለፍ ሲል እጅግ ልዩ የሆኑ ተዘጋጅተው የተቀመጡ የምግብ አይነቶችንና ባማረ መልኩ ተነጥፎ የተቀመጠም አልጋ አገኘ። ምግቡን ሲያይ የምፈልገውን ነገር ተሸክሜ ለመውጣት የሚያስችለኝ ጠንካራ አቅም እንዲኖረኝ ቀድሜ ምግብ ልብላ አለ፣ ምግብ ሲበላ ብቻ 2:00 ሰኣታትን አቃጠል። የተሻለ ብርታት አንዲኖረኝ በዚህ ባማረ አልጋ ትንሽ አረፍ ብዬ ልነሳ ብሎ ተጋደመ፣ በእንቅልፉም ቅልጥ አለና ከጥበቃዎቹ መጥተው የተሰጠህ ሰኣት አልቋል ተነስ ውጣ አሉት። አረ ምንም አልያዝኩም ትንሽ ደቂቃዎችን እንኳ ስጡኝ ብሎ ቢማፀንም የተሰጠህ ሰኣት አብቅቷል እያሉ ያን ውድ ሉል ሰጥቶ የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ ባለመጠቀሙ ምንም ሳይዝ ገፈታትረው አስወጡት። ቂሳው እዚህ ላይ አበቃ። ነገር ግን ዋናው ቁምነገር አላበቃም:- - ሉል ማለት በየትኛውም ሚዛን መግዣ ተመን የሌላት ሩህ (ነፍስህ) ናት… - የተለያየ ንብረት ያለበት ካዝና ዱኒያ ናት… - እንቁ ማለት ደግሞ መልካም ስራ ነው… - ምግቡና ፍራሹ ደግሞ በዚህች ዱኒያ የሰው ልጆችን የሚያታልለው ነገር ነው… - 6:00 ሰኣታት መቼ እንደምታልቅ የማታውቃት የተሰጠችህ እድሜህ ናት… - መልካም ስራን አታዘግይ!፣ ጊዜው አብቅቷል ተነስ የምትባልበት ቀን ሳታውቀው ይመጣልና። = እናስተውል!! ይህቺ ናት አጭር የዱኒያ ህይወትና ሸንጋዮቿ መልካም ስራዎች የምንሰራበትን ውድ ጊዜ ነገ… ከነገ ወዲያ… እሰራለሁ እያልን የሚያቃጥሉብንና በገንዘብ መተመን የማትችለዋን ህይወታችን ተቃጥላብን ተነስ ጊዜህ አብቅቷል የምንባለው!! ✍🏻በኢብን ሽፋ ከዐረቢኛ መልክት ወደ አማርኛ የተመለሰች #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
3 129
5
لا يوجد نص...
1 644
6
وصية المحدثين بعضهم لبعض في إظهار السنة وترك مداهنة أهل البدع والأهواء و كان بينهم مودة ورحمة . كتب الإمام الحافظ إسحاق ابن راهويه إلى الإمام الحافظ أبي زرعة الرازي : " إني أزداد بك كل يوم سرورا فالحمد لله الذي جعلك ممن يحفظ سنته وهذا من أعظم ما يحتاج إليه اليوم طالب العلم، وأحمد بن إبراهيم لا يزال في ذكرك الجميل حتى يكاد يفرط وإن لم يكن فيك بحمد الله إفراط وأقرأني كتابك إليه بنحو ما أوصيتك من إظهار السنة وترك المداهنة فجزاك الله خيرا فدُم على ما أوصيتك فإن للباطل جولة ثم يضمحل وإن ممن أحب صلاحه وزينه وإني أسمع من إخواننا القادمين ما أنت عليه من العلم والحفظ فأسرّ بذلك." مقدمة الجرح والتعديل لابن أبي حاتم الرازي.
916
7
🔷ውርደት ለቢድዓ ባለቤት ሰጂዚይ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አለ:- "የሱና ባለቤቶችን መንገድ የተቃረነ አካል ሁሉ ፣ በደንብ ካስተዋልከው (አንድ ቀን) የሚጋለጥበት (መጥፎ ስራ) ከእርሱ ዘንድ ይኖራል። የሱና ባለቤቶች ግን የሚጋለጡበት (መጥፎ ስራ) የላቸውም። ምክንያቱም (በዲኑ ላይ) አዲስ ነገር አልፈጠሩምና።" رسالته لأهل الزبيد (ص/٢٩٥) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
984
8
‏قال السجزي رحمه الله: "ولكل مخالف للسنة وطريقة أهل الأثر ما يفتضح به عند التأمل، وأهل الأثر لا فضيحة عليهم لأنهم لم يحدثوا شيئا". رسالته لأهل زبيد ص٢٩٥
827
9
🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ? አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ
🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ? አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ በአውራ ጣታቹ ስትፈልጉ በቀለበት ጣታቹ ብቻ በፈለጋቹት ጣታቹ ጆይን(JOIN) የምትለዋን ምልክት በመንካት ወደ ኢትዮጵያ የሰለፊዮች ቻናል ተቀላቀሉ🇸🇦
147
10
🔷ከልጆች ይልቅ ለገንዘብ ትኩረት መስጠት ያለው ጉዳት ሸይኽ ብን ኡሰይሚን - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :- "ሰዎች ሆይ! ማህበረሰባችንን ብንፈትሽ ፣ ብዙዎቻችን  ከቤተሰቦቻችን ይልቅ ስለ ገንዘባችን ይበልጥ ትኩረት እንደምንሰጥ እናገኘዋለን። ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንዳለብን ፤ እንዴት ማሳደግ እንደምንችል ፤ እንዴት ማሻሻል እንደምንችልና እንዴት መጠበቅ እና እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ሰውነታችንን እና አእምሯችንን  ጠምደነዋል። ስለ ቤተሰቦቻችን ግን አንጨነቅም። ስለእነርሱም አንጠይቅም። ስለአመጣጣቸው ወይም ስለአካሄዳቸው ወይም  ስለጓደኞቻቸው ስለባልደረቦቻቸው አንጠይቅም። ይህ ትልቅ ስህተትና ግልጽ የሆነ አለማወቅ ነው። ምክንያቱም ለአንድ ሰው ቤተሰብ ማሰብ ግዴታና  እነርሱን መንከባከብ የበለጠ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የእነርሱ መልካም መሆን  የወደፊቱ ትውልድ መልካም መሆን ማረጋገጫው ነው። የእነርሱ መበላሸት ደግሞ የወደፊት ትውልድ መበላሸት ማረጋገጫው ነው። እኛ እንደ ሙስሊም በሀይማኖቱ  እና በመልካም ስነ ምግባሩ ቸልተኛ የሆነ ትውልድ ከእኛ መካከል እንዲፈጠር እንፈልጋለን?" الضياع اللامع (١٠٠/٦) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
1 110
11
لا يوجد نص...
1 114
12
ቀብር እስከ ምትገባ ድረስ እውቀት ፈልግ ——— ኢማሙ አሕመድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይሉ ነበር:- «እኔ ቀብር እስከምገባ ድረስ እውቀትን እፈልጋለሁ።» [መናቂቡል ኢማሙ አሕመድ 1/37] ኢማሙ አሕመድ (ረሂመሁላህ) ይህን ካሉና ከዒልም ካልተብቃቁ አንተስ ማን ነህ?? ይልቅ የተማርከውን አስተምር እንጂ ከዒልም የሚብቃቃ እንደሌለ እወቅ!! ✍🏻ኢብን ሽፋ #join ↘️↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
2 181
13
✨ውዱእን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ከመልሳቸው ጋር በቀላሉ ለማግኘት ⤵️⤵️⤵️ ❸❸,ኒያ ለዉዱእ መስፈርት ነውን? ያለ ኒያ ዉዱእ ያደረገ ሰው ፍርዱ ምንድነው? ❸❹,ሲዋክ መጠቀም ሁሌም የተወደደ ሆኖ ሳለ መቼ ነው በጣም የሚወደደው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/22 ❸❺,የተሟላው የነብያችን ዉዱእ አደራረግ ምን አይነት ነው? ❸❻,መግሞጥሞጥ እና ወደአፍንጫ ውሃን ስቦ ማውጣት በዉዱእና በትጥበት ጊዜ ፍርዱ ምንድነው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/23 ❸❼,ዉዱእን ከ3 ጊዜ በላይ ማድረግ እንዴት ይታያል? ❸❽,ከአንድ ጊዜ በላይ ጭንቅላትን ማበስ እንዴት ይታያል? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/24 ❸❾,ከእንቅልፉ ተነስቶ በእጁ እየዘገነ መታጠብ የፈለገ ሰው ምን ማድረግ አለበት? ❹0,በዉዱእ ጊዜ ጣትን ፈልፍሎ ማጠብና በደንብ ውሃን ወደ አፍንጫ መሳብ ፍርዱ ምንድነው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/25 ❹❶,በዉዱእ ጊዜ ፂም ያለው ሰው ከፂሙ ስር ያለውን ክፍል ውሃ ማስነካት አለበት? ❹❷,በዉዱእ ጊዜ ፂምን ፈልፍሎ ማጠብ ፍርዱ ምንድነው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/26 ❹❸,በዉዱእ ጊዜ ሰውነትን አሽቶ ማጠብ ግዴታ ነው? ❹❹,ዉዱእ ላይ በቀኝ መጀመር ግዴታ ነውን? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/27 ❹❺,በዓማማ ላይ ማበስ እንዴት ይታያል? ❹❻,ለሴት ልጅ( ሻሽን ይመስል)ፀጉሯን በሸፈነችበት ነገር ላይ ማበስ እንዴት ይታያል? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/28 ❹❼,ውድእ ላይ ቅደም ተከተልን መጠበቅ ፍርዱ ምንድነው? ❹❽,በዉዱእ ላይ ቢስሚላህ ማለት ፍርዱ ምንድነው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/29 ❹❾,በዉዱእ ላይ ለመግሞጥሞጥ እና ወደ አፍንጫ ውሃን ስቦ ለማውጣት የተለያየ ውሃ መጠቀም እንዴት ይታያል? ❺0,ዉዱእ ላይ ማከታተል እንዴት ይታያል? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/33 ❺❶,ከዉዱእ ቡሃላ ሚባለው ዚክር ምንድነው? 👇👇👇 https://t.me/sheriawihggatochnbemasreja/34
1 400
14
አንድ ሰው በወዳጁ ዲን ላይ ነውና ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት!! ————— ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ፣ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “አንድ ሰው በወዳጁ ዲን ላይ ነው፣ አንዳችሁ ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት።” [ትርሚዚይና አቡ ዳውድ የዘገቡት ሲሆን፣ አልባኒ በሶሂህ አልጃሚዕ ላይ ሀሰን ነው ብለውታል።] ሸይኽ ዐብዱልሙህሲን አል_ዐባድ (ሀፊዘሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:- ይህ ማለት አንድ ሰው ወዳጅ አድርጎ ከያዘ እርሱም በስነ-ምግባሩ፣ በባህሪውና በዒባዳው የዚያ ወዳጁ አምሳያ ይሆናል ማለት ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "አንዳችሁ ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት።" ማለታቸው:- ጥሩ ወዳጅ እንጂ አይምረጥ፣ አላህን በመታዘዝ ላይ አጋዥ የሚሆነውን ወዳጅ ይምረጥ፣ አላህን በማመፅ ላይ አጋዥ የሚሆነውን ወይም አላህን ወደ ማመፅ የሚጎትተውን ሰው አይምረጥ፣ አልያም ጠንካራ ከሆነው (አቋሙ) አስወጥቶት ለዝንባሌው ሰበብ የሚሆነውን ሰው አይምረጥ ማለት ነው። ምክንያቱም አብዛኛው ፈተና ብዙ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሸረኛ ሰዎችን በመቀላቀል ነው። የሚጠቅመው ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸውን፣ በዲናቸው ቀጥ ያሉ ሰዎችን መምረጥ ነው። ለዚህም ነው (አላህ ጥራት ይገባውና) እንዲህ ያለው:- الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ «ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» ዙኽሩፍ 67 የተለያየ ዝንባሌ ያለባቸውን ሰዎች መወዳጀት ለሚወዳጃቸው ሰው መዘንበልም ሰበብ ይሆናሉ። በሰዎች ላይ ግድ የሚሆነው በዲኑ፣እንዲሁም አላህን በመታዘዙ ሰላም እንዲሆን በዲኑ ላይ ቀጥ ያለን ሰው መወዳጀት ነው። ወዳጁም አላህን በመታዘዝና በዲኑ ላይ መፅናትን የሚጨምርለት (ጥሩ ወዳጅ ሊመርጥ ይገባል)። [ሸርህ ሱነን አቢ ዳውድ ድምፅ 65/548] አሁን ያለንበት ተጨባጭም ይህ ነው!። ብዙ ሰዎች፣ በተለይ ወጣቶች ወደ ሀራም ነገር የሚሄዱት እንዲሁ በራሳቸው ተነሳሽነት ብቻ አይደለም። የተበላሸ አመለካከት ያላቸው ሀራሙ ሀላል፣  ሀላሉ ሀራም፣ ሱናው ቢድዐ፣ ቢድዐው ሱና የሚመስላቸውን ሰዎች ጓደኛና ወዳጅ በማድረጋቸው ምክንያት ነው። በአንዴ እንኳን ይዘዋቸው ባይሄዱ በሂደት እንዲሄዱ ያደርጓቸዋል። ወደ ተለያዩ ቢድዓዎችና ድንበር ማለፎች፣ ወደ ዚና፣ አስካሪ መጠጥ፣ ጫት ቤት፣ ሺሻ ቤት ቀስ በቀስ እየጎተቱ ይወስዷቸዋል። ከዚያ በኋላ ለዲናቸው የነበራቸው ክብር፣ ለሀራም ነገር የነበራቸው ጥንቃቄ ሀያእ ድራሹ ይጠፋና "ላይፍ እኮ ነው" ማለት ይጀምራሉ። ስትመክራቸውም "በሰው ላይፍ አትግባ" ይሉሃል። ምን አይነት የዘቀጠ ላይፍ ነው?!፣ ምን አይነት የኋልዮሽ የሆነ ላይፍ ነው?!፣ ምን አይነት ወደ ቁልቁል የሚያወርድ ላይፍ ነው?!፣ ከቁልቁለቶች ሁሉ የከፋው ቁልቁለት ወደ ጀሀነም የሚያወርደው ቁልቁለት ነው!!። ይህ ነው በዚህን ጊዜ ለምናየው የሙስሊም  ሴቱም ወንዱም ወጣት ሀያእ የለሽ ህይወት፣ እንደ ዱር እንሰሳት እርቃናቸውን ለመሄድ ሰበብ የሆነው። ይህ መጥፎ ወደ ጥፋት የሚወስዱ ጓደኞችን ወዳጅ አድርጎ መያዝ ነው የት ይደርሳሉ የተባሉ ለስንት አላማ የምትመኛቸው ወጣቶች የጫት ገረድ እንዲሆኑ ያደረጋቸው፣ ጫት ሺባ አድርጎ እንዲያስቀምጣቸው አድርጓቸዋል። ✔️ አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው የሚወደውን ሰው ሊመርጥ ይገባል። ሲወድም ሆነ ሲጠላ በጭፍን ሳይሆን ለአላህ ብሎ መሆን አለበት፣ በማስረጃ ሊወድ በማስረጃ ሊጠላ ይገባል። በጭፍን በውዴታው ሊታወር አልያም በጭፍን ሊጠላም አይገባውም!!። እንዲህ ያለው ጭፍን አመለካከት ነው ለድንበር ማለፍም ሆነ ወደታች ለመዝቀጥ ሰበብ የሚሆነው። ለዚያም ነው ብዙ ጊዜ ባጢል የያዙ ሰዎች ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው የሚባሉ ሰዎችን በመጠቀም ከትክክለኛው መንገድ ህዝቡን የሚያስቱት። አንዳንድ ሰዎችም ሀቁ ይህ ነው ተብሎ ሲነገራቸው የሚወዱት አካል በተፈተነበት ባጢል እውነታውን እያወቁት ተከትለውት ሲፈተኑበት ይታያል። ወደታች ሲዘቅጡ ያዘቅጧቸዋል፣ ወደላይ ድንበር ሲያልፉም ድንበር ያሳልፏቸዋል። ይህ መሰረቱ የተበላሸ ውዴታ ነው!። መሰረቱ የተስተካከል ውዴታ ማለት ለአላህ ብለህ የምትወደው ውዴታ ነው። አንድን ሰው ለአላህ ብሎ የሚወደው አካል ደግሞ ተወዳጁ ከሀቅ አፈንግጦ ወደባጢል የሚያመራ ከሆነ ለአላህ ብሎ ትቶት ትክክለኛ ማስረጃ ያለውን እውነታ ይከተላል። ይህ ነው መሰረቱ የተስተካከለው ውዴታ ማለት!። ብዙ በዲናቸው (በመንሃጃቻው) ጠንካራ የነበሩ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ከቢድዐ ሰዎች ጋር ተቀራርበው ወዳጅ ሆኑና ተሸማተሩ፣ እንኳን እነሱ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሊናገሩ ይቅርና በመንሀጁ ጠንካራ ሰለፊይ የሆነ ሰው በቢድዐ ሰዎች ላይ ሲናገር  ከነዚያ ከቢድዐ ሰዎች ቀድመው ለቢድዐ ሰዎች ሲከላከሉና የተለያየ ምክንያት ሲደረድሩላቸው ትመለከታለህ። ለዚህም ነው ደጋግ ቀደምቶች የቢድዐ ሰዎችን ወዳጅ አድርገው ሊይዙ ይቅርና “ከቢድዐ ሰው ጋር የተቀማመጠ ሰው በእርግጥ ዲኑን በማፍረስ ላይ ተባብሯል።" ይሉ የነበረው። አላህ የምናስተውልበትን ልቦና እና መልካም ወዳጅ ይስጠን!፣ እኛንም ለወዳጆቻችን መልካም ያድርገን!!። ✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
2 336
15
አንድ ሰው በወዳጁ ዲን ላይ ነውና ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት!! ————— ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ፣ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “አንድ ሰው በወዳጁ ዲን ላይ ነው፣ አንዳችሁ ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት።” [ትርሚዚይና አቡ ዳውድ የዘገቡት ሲሆን፣ አልባኒ በሶሂህ አልጃሚዕ ላይ ሀሰን ነው ብለውታል።] ሸይኽ ዐብዱልሙህሲን አል_ዐባድ (ሀፊዘሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:- ይህ ማለት አንድ ሰው ወዳጅ አድርጎ ከያዘ እርሱም በስነ-ምግባሩ፣ በባህሪውና በዒባዳው የዚያ ወዳጁ አምሳያ ይሆናል ማለት ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "አንዳችሁ ምን አይነት ሰው ወዳጅ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት።" ማለታቸው:- ጥሩ ወዳጅ እንጂ አይምረጥ፣ አላህን በመታዘዝ ላይ አጋዥ የሚሆነውን ወዳጅ ይምረጥ፣ አላህን በማመፅ ላይ አጋዥ የሚሆነውን ወይም አላህን ወደ ማመፅ የሚጎትተውን ሰው አይምረጥ፣ አልያም ጠንካራ ከሆነው (አቋሙ) አስወጥቶት ለዝንባሌው ሰበብ የሚሆነውን ሰው አይምረጥ ማለት ነው። ምክንያቱም አብዛኛው ፈተና ብዙ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሸረኛ ሰዎችን በመቀላቀል ነው። የሚጠቅመው ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸውን፣ በዲናቸው ቀጥ ያሉ ሰዎችን መምረጥ ነው። ለዚህም ነው (አላህ ጥራት ይገባውና) እንዲህ ያለው:- الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ «ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» ዙኽሩፍ 67 የተለያየ ዝንባሌ ያለባቸውን ሰዎች መወዳጀት ለሚወዳጃቸው ሰው መዘንበልም ሰበብ ይሆናሉ። በሰዎች ላይ ግድ የሚሆነው በዲኑ፣እንዲሁም አላህን በመታዘዙ ሰላም እንዲሆን በዲኑ ላይ ቀጥ ያለን ሰው መወዳጀት ነው። ወዳጁም አላህን በመታዘዝና በዲኑ ላይ መፅናትን የሚጨምርለት (ጥሩ ወዳጅ ሊመርጥ ይገባል)። [ሸርህ ሱነን አቢ ዳውድ ድምፅ 65/548] አሁን ያለንበት ተጨባጭም ይህ ነው!። ብዙ ሰዎች፣ በተለይ ወጣቶች ወደ ሀራም ነገር የሚሄዱት እንዲሁ በራሳቸው ተነሳሽነት ብቻ አይደለም። የተበላሸ አመለካከት ያላቸው ሀራሙ ሀላል፣  ሀላሉ ሀራም፣ ሱናው ቢድዐ፣ ቢድዐው ሱና የሚመስላቸውን ሰዎች ጓደኛና ወዳጅ በማድረጋቸው ምክንያት ነው። በአንዴ እንኳን ይዘዋቸው ባይሄዱ በሂደት እንዲሄዱ ያደርጓቸዋል። ወደ ተለያዩ ቢድዓዎችና ድንበር ማለፎች፣ ወደ ዚና፣ አስካሪ መጠጥ፣ ጫት ቤት፣ ሺሻ ቤት ቀስ በቀስ እየጎተቱ ይወስዷቸዋል። ከዚያ በኋላ ለዲናቸው የነበራቸው ክብር፣ ለሀራም ነገር የነበራቸው ጥንቃቄ ሀያእ ድራሹ ይጠፋና "ላይፍ እኮ ነው" ማለት ይጀምራሉ። ስትመክራቸውም "በሰው ላይፍ አትግባ" ይሉሃል። ምን አይነት የዘቀጠ ላይፍ ነው?!፣ ምን አይነት የኋልዮሽ የሆነ ላይፍ ነው?!፣ ምን አይነት ወደ ቁልቁል የሚያወርድ ላይፍ ነው?!፣ ከቁልቁለቶች ሁሉ የከፋው ቁልቁለት ወደ ጀሀነም የሚያወርደው ቁልቁለት ነው!!። ይህ ነው በዚህን ጊዜ ለምናየው የሙስሊም  ሴቱም ወንዱም ወጣት ሀያእ የለሽ ህይወት፣ እንደ ዱር እንሰሳት እርቃናቸውን ለመሄድ ሰበብ የሆነው። ይህ መጥፎ ወደ ጥፋት የሚወስዱ ጓደኞችን ወዳጅ አድርጎ መያዝ ነው የት ይደርሳሉ የተባሉ ለስንት አላማ የምትመኛቸው ወጣቶች የጫት ገረድ እንዲሆኑ ያደረጋቸው፣ ጫት ሺባ አድርጎ እንዲያስቀምጣቸው አድርጓቸዋል። ✔️ አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው የሚወደውን ሰው ሊመርጥ ይገባል። ሲወድም ሆነ ሲጠላ በጭፍን ሳይሆን ለአላህ ብሎ መሆን አለበት፣ በማስረጃ ሊወድ በማስረጃ ሊጠላ ይገባል። በጭፍን በውዴታው ሊታወር አልያም በጭፍን ሊጠላም አይገባውም!!። እንዲህ ያለው ጭፍን አመለካከት ነው ለድንበር ማለፍም ሆነ ወደታች ለመዝቀጥ ሰበብ የሚሆነው። ለዚያም ነው ብዙ ጊዜ ባጢል የያዙ ሰዎች ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው የሚባሉ ሰዎችን በመጠቀም ከትክክለኛው መንገድ ህዝቡን የሚያስቱት። አንዳንድ ሰዎችም ሀቁ ይህ ነው ተብሎ ሲነገራቸው የሚወዱት አካል በተፈተነበት ባጢል እውነታውን እያወቁት ተከትለውት ሲፈተኑበት ይታያል። ወደታች ሲዘቅጡ ያዘቅጧቸዋል፣ ወደላይ ድንበር ሲያልፉም ድንበር ያሳልፏቸዋል። ይህ መሰረቱ የተበላሸ ውዴታ ነው!። መሰረቱ የተስተካከል ውዴታ ማለት ለአላህ ብለህ የምትወደው ውዴታ ነው። አንድን ሰው ለአላህ ብሎ የሚወደው አካል ደግሞ ተወዳጁ ከሀቅ አፈንግጦ ወደባጢል የሚያመራ ከሆነ ለአላህ ብሎ ትቶት ትክክለኛ ማስረጃ ያለውን እውነታ ይከተላል። ይህ ነው መሰረቱ የተስተካከለው ውዴታ ማለት!። ብዙ በዲናቸው (በመንሃጃቻው) ጠንካራ የነበሩ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ከቢድዐ ሰዎች ጋር ተቀራርበው ወዳጅ ሆኑና ተሸማተሩ፣ እንኳን እነሱ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሊናገሩ ይቅርና በመንሀጁ ጠንካራ ሰለፊይ የሆነ ሰው በቢድዐ ሰዎች ላይ ሲናገር  ከነዚያ ከቢድዐ ሰዎች ቀድመው ለቢድዐ ሰዎች ሲከላከሉና የተለያየ ምክንያት ሲደረድሩላቸው ትመለከታለህ። ለዚህም ነው ደጋግ ቀደምቶች የቢድዐ ሰዎችን ወዳጅ አድርገው ሊይዙ ይቅርና “ከቢድዐ ሰው ጋር የተቀማመጠ ሰው በእርግጥ ዲኑን በማፍረስ ላይ ተባብሯል።" ይሉ የነበረው። አላህ የምናስተውልበትን ልቦና እና መልካም ወዳጅ ይስጠን!፣ እኛንም ለወዳጆቻችን መልካም ያድርገን!!። ✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
1
16
لا يوجد نص...
1 229
17
🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ
135
18
የሸረኛ (በተንኮል) የተሞላ ሰው ነገር… ——— ታላቁ ዓሊም ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ሸረኛ (በተንኮል) የተሞላ ሰው ሸሩን ወደ ሰዎች በማድረሱ ጠዓምና እረፍት ያገኛል። የብዙ ሰዎች ሰላማዊ መሆንና ከእርሱ ሸር ሰላም ሆነው የሚውሉበት ቀን አያስደስተውም። (ሸሩን ሳያደርስባቸው የሚውልበት ቀን ደስተኛ አያደርገውም)” [መዳሪጁ ሳሊኪን 1/290] አላህ ይጠብቀንና እንዲህ ያሉ የሰው ሸይጧን የሆኑ ሰዎች ናቸው በሙስሊሙና በሰለፊያው ጀመዓ ሸራቸውን ለመበተን ሌት ከቀን የሚኳትኑት!። እንዲህ አይነት ሸርን ተፈጥሯቸው ያደረጉ ሰዎችን ጀመዓውን ለተለያየ አደጋ እንዳያጋልጡ በጥንቃቄ መመልከቱ ተገቢ ነው!!። #Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
2 417
19
‏قال العلامة ابن القيم -رحمه الله-: " والشرير يجد لذة وراحة في إيصال شره للناس ، وكثير من الناس لا يهنأ له عيش في يومٍ لا يؤذي فيه أحداً ". 📚مدارج السالكين (٢٩۰/۱)
1 486
20
ተስፋ አትቁረጥ!! ይልቅ ፈጣንና ብልህ ሁን!! ——— ኢማም ዐብዱ'ል ዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም!!። የቢድዓ ሰዎች ርስበርሳቸው ይተባበራሉ ተስፋ አይቆርጡም፣ ይልቁንም በሁሉም መዳረሻዎች ወደ ጥመት ይጣራሉ፣ በማህበራዊ ሚዲዎች፣ በቲቪ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሃፎች… ይጣራሉ። ይህ እንግዲህ ባጢል ነው። ወደ እሳት ነው የሚጣሩት። እነዚያ ወደ ጀነት የሚጣሩ ሰዎች ከነሱ የተሻለ የሚጓጉ ጀግናና ፈጣን ሊሆኑ ይገባል!!።” [አት-ተዕሊቅ ዐለ ነድወቲ ዘካት ከሚለው ካሴት] ኢማም ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) ይህን ያሉበት ወቅት ሶስት አስርተ አመታት ገደማ ነበር። ዛሬ ነገሩ ሸይኹ ከተናገሩትም በርትቷል። የቢድዓ ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችንም ሆነ ሌሎችን የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም የሱንና ሰዎች እንዳይታዩና ሀቅን እንዳያሰራጩ ጥረታቸውን ተያይዘውታል። ነፍሲያ፣ ስሜትና ቡድንተኝነት የሚጋልባቸው ሰዎች ብሰዋል። በተቻላቸው ሁሉ ሱንናን ይዋጉበታል፣ እስልምና ስሙ እንጂ እንዳይቀር ይተጋሉ፣ (ምክንያቱም ቢድዐና ስሜታዊነት ሲስፋፋ እስልምና ስሙ እንጂ ተግባሩ እየቀረ ይሄዳል።) ባለ በሌለ ሀይላቸው ድፍን ጥቁር የሆነን ውሸት በሰለፊዮች ላይ በመዋሸትም ያጠለሹዋቸዋል!። የሚስኪኑን ለዲኑ የሚጨነቀውን ህዝብ ልብ አውቀው እውነት ሊመስለው በሚችለው ነገር ላይ በሱኒዮች ላይ ውሸት ቀጥፈው ያቀርቡለታል። ሀራሙን ከሀላል፣ ሀላሉን ከሀራም በማደባለቅ ያመሳስሉበታል። ሳያጣራም ይከተላቸዋል፣ እውቅናም ይሰጣቸዋል። ከምንም በላይ እውቅናን ፍለጋና ሚዲያን ለማግኘት ይተጋሉ። ታዲያ እውቅናንና ሚዲያን ባገኙ ቁጥር ሱኒዮችን ለማጠልሸትና ሰዎች ዘንድ የሀቅ ሰዎች እንዳይታወቁ ሰዎች ወደ እነሱ ሄደው ሀቅን እንዳይማሩ ለመሸፈን፣ መንገድ ለመዝጋት ነው የሚጠቀሙት። ፈፅሞ እንግዳነትና ባይተዋርነት ተሰምቶህ ተስፋ ልትቆርጥ አይገባም!!። ይልቅ ሰበቡን ካደረስክ ዲኑን እንደሚረዳው በአላህ ላይ ፅኑ እምነት ኖሮህ ከምንጊዜውም በላይ ልትነቃና ለህዝባችን በተቻለህ ሁሉ እውነቱን ግልፅ ልታደርግለት፣ ግልፅና ተጨባጭ ማስረጃዎችን ልታስጨብጠው ይገባል። አላህን (ተባረከ ወተዓላ) በሐቅ ላይ ፅናት ልንጠይቀው፣ በሀሳብና በእውቀት በተቻለን ሁሉ ርስበርሳችን ልንደጋገፍና ልንተዛዘን ፍቅር ሊኖረን!! ልንበረታታ ይገባል!!። ✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
2 863