ar
Feedback
ማራናታ.....MARANATHA

ማራናታ.....MARANATHA

الذهاب إلى القناة على Telegram

ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደምመስላቸው ጌታ ሰለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንድደርሱ እንጅ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሰለ እናንተ ይታገሳል።2ኛ ጴጥ 3፥9 ገና በጣም ጥቅት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም። ዕብራ 10፥37 የመወያያ ግሩፕ👇 @Marantawoch Inbox Comment @Thaddyapostolic

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ማራናታ.....MARANATHA

تُعد قناة ማራናታ.....MARANATHA (@maranathawoch) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 17 750 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 534 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 1 949 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 17 750 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 22 سبتمبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 520، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 9، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 19.16‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 8.32‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 401 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 476 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 27.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደምመስላቸው ጌታ ሰለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንድደርሱ እንጅ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሰለ እናንተ ይታገሳል።2ኛ ጴጥ 3፥9 ገና በጣም ጥቅት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም። ዕብራ 10፥37 የመወያያ ግሩፕ👇 @Marantawoch Inbox Comment @Thaddyapostolic

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 23 سبتمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

17 750
المشتركون
+924 ساعات
+1257 أيام
+52030 أيام
أرشيف المشاركات
ዘማሪ: መሰረት መሰለ አስኮ ፂሆን አጥቢያ
አንድ የሚመራኝ አለ በራሱ ፍቃድ አንድ የሚመራኝ አለ በራሱ ሀሳብ ስወጣ ሚመራኝ ስገባ ሚመራኝ ኢየሱስ የእረኛዬንም ድምፅ ለይቼ አውቀዋለው ከሌሎቹ ድምፆች ፈጥኜ እርቃለው አስተማሪዬ ነው ሁሌ ከኔ አይርቅም በእጆቹ ይዞኛል ማንም አይነጥቀኝም እረኛዬ አይደል ሞያተኛ ትቶኝ አይሸሽም በምንም ሁኔታ ይቀድመኛል ደግሞ ይከተለኛል በመታመን ሆኖል የእኔ መግባት መውጣት ልቤ ያረፈበት እውነተኛ እረኛ ታማኝ ጠባቂዬ አይደክም አይተኛ ዘላለሜን የሚያውቅ የሚሸከመኝ ኢየሱስ አምላኬ ነው ሚያሰማራኝ እረኛዬ…..

🎤 Singers: ቃሊቲ አምልኮ ህብረት  ብዙ ምህረት ብዙ ቸርነት እንዳረክለት ምስጋናዬን አምልኮዬን እሰጥሀለው ያለስስት ይበዛል እንጂ እየጨመረ ያንተ ውለታ መች ተዘመረ ከምለው በላይ በልቤ ያለው የሱስ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው 1  የይሉኝታን ገደብ ሰው ምን ይለኛል ክልል አልፌ ከሚያመልኩህ ጋራ ለአንተ ከሚሰግዱ አብሬ ተሰልፌ ክብሬን እየጣልኩ በእውነት በመንፈስ ልቤን ላፍስስልህ እንዳያውም እንዲያው ነኝ ክብርህ ተጠርቶማ መች ያስችለኛል አቤት ለእኔ ያደረከው የሱስ እጅግ ብዙ ነው ብቆጥረው ከቁጥር ያልፋል ባወራው መሽቶ ይነጋል ጨለማ የተገፈፈለት ብርሃን የወጣለት ቢዘምር ለተማረ ሰው ክብሩን ቢጥል ሲያንስ ነው ቢያወራ ደግሞ ደጋግሞ ያለፈውን ታሪክ አስቦ  ሊሸሸግ የማይቻልን አደረክ የሱስ ድንቅህን ዝፋንህ ይታወድ የምስጋናን ሽቶ ላፍስስ በፊትህ የተወደደውን የሚቃጠል መስዋዕት ይሽተት ያረግልህ ስብ የበዛበተን የሰባውን ፍሬ የከንፈሬን ፍሬ አልወጣልህ አለኝ አልጠገብኩም ገና ዘምሬ ዘምሬ በክብር ከፍ ከፍ ላለው ለእግዛብሄር እዛምራለው ሀይሌ ነው የኔ ዝማሬ ያዳነኝ ከጨካኝ አውሬ

የማለዳ ትምህርት በጽድቅ የበረታ ሰው ክፍል ዘጠኝ የታመነ ምስክር " ...ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሀይልን ትቀበላላችሁ ።በእየሩሳሌም ፣በይሁዳ ፣በሠማሪያ ፣እስከምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ!!!!    🌹ሐዋ1:8🌹 " 💠 አንድ ሰው በጽድቅ ሲበረታ ለእግዚአበሐር የታመነ ምስክር ይሆናል ። ይህ የሚሆነው በኢየሱስ ስም ጥምቀት ያገኘነውን ከጽድቅ የሆነውን በጎ ህልውና ውጠት ማለትም በጎነት ስናገር ወይንም ስመሰክር ነው ። " ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:21) ⛎ የሚንመሰክረው ይህ በስሙ ጥምቀት ያገኘነው በጎነት ከመንፈስ ቅዱስ ወይንም ከተቀበልነው ኃይል ጋር ሲዋሄድ ነው ። መመስከር ማለት ደግሞ ያገኘነውን የእግዚአብሔርን በጎነት መናገር ማለት ነው ። " እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:9) ⛎ በጽድቅ የበረታ ሰው የታመነ ምስክር ይሆናል ስባል እንደ ነብዩ ኢሳይያስ በመንፈስ ቅዱስ እሳት / በፍም / ከንፈሩ ስነካ ኃጢአቱ ከተሰረየለት በኋላ ሰማይን ያለበትን ሁነታንና በዙሪያው ያሉትን ከጽድቅ ፈቀቅ ያሉትን የእግዚአብሔርን በጎነትን ያልቀመሱትን በማየት እነን ላከኝ በማለት ለአምላካዊ ጥሪ መልስ መስጠት ስችል ነው። ♑️ ኢሳይያስን ለጥሪው ምላሽ እንድሰጥና በነፍሳት ቅናት ተይዘው ራሱን በመሰዋት ለወንጌል እስከሞት ድረስ ያደረገው እሱ በመንፈሳዊ አይን ያያቸው ነገሮች ናቸው ። እነዚህም ፦ 1⃣ ወደ ላይ አየ እግዚአብሔርን በክብሩ ዙፋን 2⃣ ወደ ራሱ አየ ከንፈሩ የረከሰበት ሰው መሆኑን 3⃣ ዙሪያውን አየ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል መቀመጡን ወይም መኖሩን ። ኢሳይያስም ልክ ይህንን ስያይ የነፍሳት ሸክም ይሰማው ጀመረና ጩኸቱን ቀጠለ ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ሥራውን ቀጠለ ። ሐዋሪያትም የደረሰባቸው መልካም እጣ ፋንታቸው ይህ ነበር ። ዛሬ ላለን ለእኛም ይህ ነው ያለን በጎነቱንስ እንደሆነ ቀምሰናል ። በስሙ ተጠምቀናል ህልውናችንን በደሙ አጥበናል በስሙ ጥምቀት ። አሁን እንግድህ ራሳችን ሰተን ለአምላካዊ በጎ አገልግሎት እንድንለይ ፤ ለተጠራንለትም ዓላማ እንድንቆም ፤ እንደ ኢሳይያስ አምላክን በክብሩ ዙፋን ፥ ዙሪያችንን ፥ አልፎም ተርፎ ራሳችንን አይተን ወዮልኝ ❗️በማለት  ራሳችን ለይተን የእውነተኛ ወንጌል ምስክሮች እንድንሆን ጌታ ኢየሱስ ይርዳን ። አሜን ❗️ ይቀጥላል..... @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH inbox @Thaddyapostolic group @MARANTAWOCH

ይህን ነበር #በAI የተሰራ መዝሙር ነገር ግን ባለማወቃችሁ በsocial media ላይ ሰርታችሁ የምትለጠፉ ወንድሞችና እህቶች ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር አታድረጉ:ተጠንቀቁ:: @maranathawoch

አነጋግሮታል ነገሬን
የምህራብ ማስ ኳየር መዘምራን በመርካቶ ሳሌም የመዝሙር ፌስቲቫል ላይ የዘመሩት ድንቅ ዝማሬ
እናገራለው ህይወትን በሞተው ነገር ላይ እኔ አውጃለው ሰላምን ባወከኝ ነገር ላይ ያበቃ ነገር የለም*2 ያለቀ ነገር የለም*2 እግዛብሄር አላለም እርሱ አልችልም አላለም እርሱ አብቅቷል አላለም በቃ አለቀ አላለም ይችላል ታሪክ መስራት ይችላል ይችላል ተአምር መስራት ይችላል ይችላል ማይቻለውን ይችላል ያልታየውን ያደርጋል ያልታሰበው ማህበሉን ፀጥ ወጀቡን ዝም የሚያደርገው የኔ ጌታ ነው ተራራዬን ሲያነጋግረው ደልዳላ ሜዳ አሁን ሊሆን ነው አነጋግሮታል ነገሬን ቃል ወቶበታል የስልጣን የኔማ በእርሱ አይን ቀላል ነው ታ ያበቃ ነገር የለም ….. ጌታ ነኝ ብሎ ፊቴ የቆመ በክንዱ ብርታት የተማመነ ግዙፍ ተራራ ቢያክልም እንኳን ሜዳ ይሆናል በቃሉ ስልጣን

ለሁሉ ይድረስ "
እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ
በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:3) ✍ እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ የሰማይ ልጀች ነን:: ማሳሰቢያው ከዚህ በፍትም ተገልጾ እንደነበረ ይህ በድምፅ ያለ  መዝሙር  Original Song ሲሆን ግን በsocial media ላይ#በAI[Artificial_intellengence ] ተሰርተዋል:: ስለዚህ የዚህ መዝመር #copy የሰራህ/ሽ ወንድም/እህት ለምንድነው ያረከው/ያረክሽው???? #
ትልቅ_ሰህተት ሰለሰራህ/ሽ ከእግዚአብሔር ምህረትን ጠይቅ/ቂው::
@maranathawoch

አልሰግድም_New_Apostolic_Church_Songs_Apostolic_Church_of_Ethiop.m4a9.37 MB

ካንተ_የተነሳ_ነው_Live_worship_song_Apostolic_Church_of_Ethiopia,_Goro360p.mp319.25 MB

የለም ሌላ
የአስኮ ፂሆን አጥቢያ መሃንየም መዘምራን
1. ከጥንት የነበረው ያለ የሚኖረው በራሱ ተማምኖ እኔ እኔነኝ ያለው በምስሉም እንደ ሰው የባርያን መልክ ይዞ ቀራኒዮ የዋለ ለመስቀል ሞት ታዞ ማነው ታድያ ህይወት ነኝ የሚል ኢየሱስን የሚመስል እዚያጋማ የለም ሌላ/4* ማነው እውነተኛ በፍቅሩ ሚያስጠጋ ተፈፀመ ብሎ ሌሊቱን ያነጋ እዚያጋማ የለም ሌላ/4* 2. ዛሬም የሚናገር በከበረው ደሙ ድንቅ መካር ሀያል የተባለ ስሙ በዘመናት መሃል የሚኖር በክብር በቅዱስ መንፈሱ ዛሬም የሚፈጥር ማነው ታድያ ህይወት ነኝ የሚል ኢየሱስን የሚመስል እዚያጋማ የለም ሌላ/4* ማነው በብርሃን የሚኖር ተከቦ በዙፋኑ ያለ ሞትን ታሪክ አርጎ እዚያጋማ የለም ሌላ/4* ክብሩ ጋ ዙፋኑ ጋ ግርማዊነት ስልጣኑ ጋ እዚያጋማ የለም ሌላ/4* የለም ሌላ! የለም ሌላ ሆ! የለም ሌላ! የለም ሌላ ሆ!

በ 2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  (ASTU) ለተመደባችሁ ወንድሞች እና እህቶች በሙሉ ወደ ግቢያችን መምጣታችሁን በጉጉት እና በፍቅር እየተጠባበቅን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን:: ለማንኛውም መረጃ እና ስትመጡም ለመቀበል ዝግጅታችንን ጨርሰናል።ከስር ባለው ስልክ በመደወል የ fellowship አስተባባሪዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።        1.ወ/ም ደሳለኝ (0980408831)        2.እ/ት አዝመራይ ( 0967815485)        3.ወ/ም ቢንያም( 0936447466)        4.ወ/ም እስራኤል (0948603911)               🙏ተባረኩ🙏

የማለዳ ትምህርት      በጽድቅ የበረታ ሰው ክፍል ስምንት የቅድስና ሕይወት " ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16) 📖 በጽድቅ የበረታ ሰው ዘመኑን ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅድስና ይኖራል ። 💠 የቅድስና ሕይወት ማለት በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በፍጹምነት መመላለስ ማለት ነው ። " አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና። እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፥ እጅግም አበዛሃለሁ አለው። አብራምም በግምባሩ ወደቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው። እነሆ፥ ቃል ኪዳኔ ከአንተ ጋር ነው፤ ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ። " (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 17 ፥ 1-4) 👤 አብርሃም በጽድቅ የበረታ ሰው ስለሆነ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በፍጹምነት ተመላለሰ ። ከዚህም የተነሳ ጽድሆኖ ተቆጠረለት ። 🚹ኢዮብም በጽድቅ ስለበረታ በአምላኩ በእግዚአብር ፊት ፍጹምና ቅን እግዚአብሔርን የምፈራ ከኃጢአትም የራቀ ሰው ተባለ ። ከዚህም የተነሳ ለግዜው በሰይጣን ብፈተንም በስተመጨረሻ በእጥፍ ተባረከ " ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ። " (መጽሐፈ ኢዮብ 1:1) ⛎ የእግዚአብሔር ቃል "በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ" ስለምለን እኛም እንደ ወጣት መልከም አጋጣሚዎችን ሁሉ ለጽቅ ስራ መጠቀም ይኖርብናል ። ይህ ማለት እንተርኔትም ጨምሮ የምንጠቀምባቸውን ነገሮች ሁሉ ለመልካም ዓላማ በመጠቀም በጽንድቅ መበርታት እንዳለብን ያሳየናል ። ውሸት መጻፍም ሆነ ማንበብ ከቅድስና የራቁ ነገሮች ላይ ማደፈጥ ፤ አዘውትሮ መጠቀም በጽድቅ እንዳንበረታ በቅድስና ሕይወታችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳርፋል ። 💠 ከአለባበሳችን አንስቶ እስከ አይናችንና እስከ ምላሳችን ያለው ሁሉ ነገራችን በጽድቅ እንድበረታ የቅድስና ፍሬዎችን ማመንጨት አለባቸው ። የቅድስና ሕይወት እንድረጋገጥ በፊሪያችን እራሳችን እየመዘነን ለተቄን በውጫዊም ሆነ በውስጣዊ ቅድስና መበርታት አለብን ። ⚠️ በጽድቅ እንበረታ ዘንድ ፣ በቅድስና ሕይወታችን እንድንተጋ ክፉና አጸያፊ ነገርን አይተን በዛ ነገር ተስበን እንዳንወድቅ እንደ ኢዮብ ዘወትር ከዓይናችን ጋር ቃልኪዳን መግባት አለብን ። " ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤ " (መጽሐፈ ኢዮብ 31:1) 💟 በዚህ በርኩስና በጠማማ ትውልድ መካከል በጽድቅ እንበረታ ዘንድ ጌታ ኢየሱስ ፍሬ ያለውን የቅድስና ሕይወት በማደል ይርዳን ❗️ አሜን ። ይቀጥላል......... @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH inbox @Thaddyapostolic group @marantawoch

Melkam Laderege.m4a14.15 MB

#ጤናማ_የእርስ_በእርስ_ግንኙነት፧ 1⃣ እርስ በእርሳችሁ አትሟገቱ ...................📖1ኛ ቆሮ 6:7... 2⃣ እርስ በእርሳችሁ አትናደዱ....................📖1ኛ ጢሞ 6:4-5... 3⃣ እርስ በእርሳችሁ አትጣሉ ......................📖ዘፍ 45:24... 4⃣ እርስ በእርሳችሁ አትዋሹ.........................📖ቆላ 3:9... 5⃣ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ.............................📖ማር 9:50... 6⃣ እርስ በእርሳችሁ ክብር አትፈልጉ................📖ዩሐ 5:44... 7⃣ እርስ በእርሳችሁ አታንጎራጉሩ....................📖ዩሐ 6:43... 8⃣ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ.............................📖ዩሐ 13:34... 9⃣ እርስ በእርሳችሁ አትበዳደሉ..........................📖ሐዋ 7:26... 🔟 እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ..........................📖ሮሜ 12:10... 1⃣1⃣ እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ........................📖ሮሜ 15:7... 1⃣2⃣ እርስ በእርሳችሁ ተገሳጸጹ......................📖ሮሜ 15:14... 1⃣3⃣ እርስ በእርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ........📖1ኛ ጴጥ 5:14... 1⃣4⃣ እርስ በእርሳችሁ ተጠባበቁ...............📖1ኛ ቆሮ 11:33... 1⃣5⃣ እርስ በእርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ.............📖ገላ 5:13... 1⃣6⃣ እርስ በእርሳችሁ አትነካከሱ....................📖ገላ 5:15... 1⃣7⃣ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር ታገሱ.................📖ኤፌ 4:2... 1⃣8⃣ እርስ በእርሳችሁ ቸሮችና ርኀሩኆች ሁኑ.......📖ኤፌ 4:32... 1⃣9⃣ እርስ በእርሳችሁ ትዕግሥት አድርጉ.........📖ቆላ 3:13... 2⃣0⃣ እርስ በእርሳችሁ አስተምሩና ገስጹ.........📖1ቆላ 3:16... 2⃣1⃣ እርስ በእርሳችሁ ተጽናኑ.............📖1ኛ ተሰ 5:12-13... 2⃣2⃣ እርስ በእርሳችሁ ተመካከሩ............📖ዕብ 3:13... 2⃣3⃣ እርስ በእርሳችሁ በሰላም ሁኑ...........📖1ኛ ተሰ 5:12-13... 2⃣4⃣ እርስ በእርሳችሁ መልካም አድርጉ.......📖1ኛ ተሰ 5:15... 2⃣5⃣ እርስ በእርሳችሁ እንግድነት ተቀባበሉ.......📖1ኛ ጴጥ 4:9... 2⃣6⃣ እርስ በእርሳችሁ አገልግሉ...........📖1ኛ ጴጥ 4:10... 2⃣7⃣ እርስ በእርሳችሁ ተዋረዱ አትተማሙ.......📖1ኛ ጴጥ 5:5... 2⃣8⃣ እርስ በእርሳችሁ አትተማሙ......  .📖ያዕ 4:11... 2⃣9⃣ እርስ በእርሳችሁ አታገረምርሙ..............📖ያዕ 5:9... 3⃣0⃣ እርስ በእርሳችሁ ተናዘዙ......................📖ያዕ 5:16... 3⃣1⃣ እርስ በእርሳችሁ አታምጹ................📖ዘፍ 11:3... 3⃣2⃣ እርስ በእርሳችሁ አትለያዩ..................📖ዘፍ 13:11... 3⃣3⃣ እርስ በእርሳችሁ በክፉ አትመካከሩ......📖ዘፍ,ዘኀ 14:4... 3⃣4⃣ እርስ በእርሳችሁ ስጦታ ተሰጣጡ...........📖አስ 9:19... 3⃣5⃣ እርስ በእርሳችሁ ተቀራረቡ..........📖እዮብ 41:8... 3⃣6⃣ እርስ በእርሳችሁ ከንቱ ነገር አትነጋገሩ..............................📖መዝ 12:2... 3⃣7⃣ እርስ በእርሳችሁ በክፉ አትስማሙ...........................📖ማቴ 21:28... 3⃣8⃣ እርስ በእርሳችሁ ተጠያየቁ..............................📖ማር 9:10... 3⃣9⃣ እርስ በእርሳችሁ አትዘባበቱ..............................📖ማር 15:31... 4⃣0⃣ እርስ በእርሳችሁ አትከፍፉ..............................📖ሐዋ 15:39...                                    4⃣1⃣ እርስ በእርሳችሁ አትከራከሩ............................📖ሐዋ 28:29... 4⃣2⃣ እርስ በእርሳችሁ አትቀዋወሙ..........................📖ገላ 5:17... 4⃣3⃣ እርስ በእርሳችሁ ተገማግመሙ..........................📖ዮናስ 1:7...   4⃣4⃣ እርስ በእርሳችሁ አትመሰቃቀሉ.....................📖ናሆም 1:10...                                                    4⃣5⃣ እርስ በእርሳችሁ ጤናማ ንግግር ተነጋገሩ.........................📖ሚል 3:16...                                                   4⃣6⃣ እርስ በእርሳችሁ ፍቅራችሁ ይጨምር...............................📖1ኛ ተሰ 3:13...  ይህን ሁሉ እንድናደርግ እግዚአብሔር  ይርዳን @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH

ብዙ ወንድሞችና እህቶች የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪዎች እየጠየቁኝ ስለሆነ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪዎች አሳወቁኝ

የ2019 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ ፌሎሽፕ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝርና ስልክ ቁጥራቸው፦ 1, Jigjiga University 1 Br Genetu tamire 0948392666 2 Sis Eyeruselem alemayehu 0940742184 2, Haramaya University ቄስ በትሩ -091 208 5326        አስተባባሪዎች Main campus ወንድም ይድድያ 0986040441 እህት ፅዮን 0954041445 Gendeje/Tecno campus ወንድም ዮሴፍ  0990389146 Station/veterinary campus ወንድም ሰለሞን 0978728261 ወንድም ይድድያ 0986040441 3, Ambo University HACHALU CAMPUS BR. ANTIYE +251 954 721 886 BR. KERAJ +251 991 986 630 SIS. AYANTU +251 991 151 555 MAIN CAMPUS BR. JHON +251 934 398 886 BR. SAMUEL +251 902 845 631 SIS. ZION 0960 338 547 4, WERABE UNIVERISTY   KES DAGNACHEW MERSHA   0925308499 Wm TEMESGENTESEMA 0948246053 WM YOHANES BELAYCHEW 0991409486 5, Debre birhan University 0939498551 br Biniam 0929914032 eht Rahel 6, ወልቂጤ ዮንቨርሲት - ወ/ም ዳንኤል ይልማ 0979940819 - ወ/ም ማርክነህ ማርቆስ 0919594899 - ወ/ም ብሩክ ደሳለኝ +251901647377 7, Wollaga University 1. Bro Robe-0942503619 2. Bro Zenebe- 0916325859 8,Wechamo university dureme campus. 093 917 8718 b/r sinte 9, አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ➡️6 ኪሎ ምስክር0938558830  መረርቱ 0977939503  ➡️4 ኪሎ ኖህ 0976370736  ናሆም 0922457651  ➡️ሠፈረ ሰላም ሶፎንያስ 0926532536  ቶለዋቅ 0985819796  10, Jimma University kes Dereje 0985045805 አስተባባሪዎች > main gib 1, wm Fikre Fiseha 0927473341 2, eht mihret Tlahun 0996033155 > JIT (techno campus) 1 Wm melaku matewos 0989507236 2, Wm Obsan Habtamu 0945424754 > Agri campus 1, Wm Amon Abera 0986951124 2, Esayas Agago 0922676078 -> Agaro campus kes Demissew 0917312994 11, Dire Dawa university Bro Bereket Zeleke 0925617717 Bro Anteneh Assefa 0931477057 Sis Ariyam Abera 0933138082 12, Gambella University Kes Desalegn Yonas 0916575228 Br.Mengesha  0952610101 Sis.Martha   0926726815 13, Dilla Univeristy 1 Br Getachew Lechamo     0948289063 2 Br Simon Shiferaw     0928806774 3 Br Melaku   0926871920 4  Br Biniyam Abti     0987054107 14, jinka university 1,B/r Temesgen albazo 0961853236 2 Br Lew kusse  +251 98 562 3195 15, አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  (ASTU)        1.ወ/ም ደሳለኝ (0980408831)        2.እ/ት አዝመራይ ( 0967815485)        3.ወ/ም ቢንያም( 0936447466)        4.ወ/ም እስራኤል (0948603911) 16, WACHEMO UNIVERSITY        main campus 1,Br Medane Tariku 0953369922 2,Br Maranata Dangiso 096265 8250 3,Sr Bezawit Girma 097657 7427 17,Dire Dawa university Bro Bereket Zeleke 0925617717 Bro Anteneh Assefa 0931477057 Sis Ariyam Abera 0933138082 18,Bule hora university br Esrael  +251923685228 19,Salale university Br  melkamu mamo 0975052868 Br Tomas Dira 0928802911 20,Hawassa university Br Abenezer Alemu 0934524811 Br zergawu 0921686164 Br Belete Bezabhi 0926434527 Br josh 0955810141 Sr Bereket mehamed  0994037179 21,Arsi University Apostolic Church Students Fellowship 1) ወንድም ኢዮስያስ ሲሳይ       09 45 03 85 29 2) ቄስ ደቀባ ቱፋ      09 66 99 07 76 3) ዲንሾ ካምፓስ ለምትመደቡ      ወንድም ገመዳ ተሰማ      09 34 46 41 68 4) አርዱ ካምፓስ ለምትመደቡ     ወንድም ካሌብ በሻዳ     09 02 29 76 12 የቀሩትንም በመላክ ተባበሩልን!! inbox @Thaddyapostolic @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH

ከላይ እንዳነብነው አንድ ሰው በጽድቅ እየበረታ ስሄድ ወደ መዳንና ወደ መንግስተ ሰማይ ቅርብ እየሆነ ይሄዳል ፤ የእግዚአብሔርም እጅ ያያል ፤ ድምጹንም ይሰማል ፤ ለዚህ ደግሞ ማሳያው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን መቀበሉ ነው ። በጽድቅ የበረታ ሰው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያገኘው ወይም ወደ ሙላቱ የሚደርሰው በመንፈስ ቅዱስ ደረጃ ጽድቁን እየጨመረ ፤ በጽድቅም እየበረታ ስለሄድ እንደሆነ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል ። (ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 47) 1፤ ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር። 2፤ በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፤ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፤ እነሆም፥ ውኃው በቀኙ ወገን ይፈስስ ነበር። 3፤ ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ። 4፤ ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። 5፤ ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ። 6፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ። 7፤ በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ። 8፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል ወደ ዓረባም ይወርዳል ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃው ይፈወሳል። 9፤ ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል። ይህ ውሄ የምያሳየን መንፈስ ቅዱስን ነው እኛ በጽድቅ በበረታን ቁጥር አንድ አንድ ሺህ እየለካ ይሄዳል ይጨምራል ። የጽድቅን ጫፍ ስንደርስ ልንሻገር የማንችለው ወንዝ ይሆንና ሁለ ነገራችንን በቁጥጥር ስር ያደርጋል ። ልክ ወንዝ ውሃ አብጦ ከዋጠን በኋላ ከድንጋይ ፤ ከእንጨትም ጋር እያላተምን እኛም በፈቃዳችን ጥሰን ለመውጣት ብንፍጨረጨርም ሳያወጣም ውጦ እንደምበላን ፤ ገድሎም በፈቃዱ እንድምመራን ሁሉ የእግዚአብሔርም መንፈስ በሙላት በላያችን ላይ ዘንቦ ከዋጠን በኋላ የሥጋ ፈቃዳችንን ገድሎ በፈቃዱ ያስገዛናል ማለት ነው ። ለዚህ ደግሞ ማሳያ የምሆነው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በላያችን በሙላት መታየታቸው ነው ። " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" ገላትያ 5:22 ፍሬ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስ ይስጠን ። አሜን ❕ ይቀጥላል ..... @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH inbox @Thaddyapostolic group @marantawoch

የማለዳ ትምህርት በጽድቅ የበረታ ሰው ክፍል ሰባት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 6) " 33፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። 34፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። " አንድ ሰው በጽድቅ እየበረታ ስሄድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ያገኛል ፤ እንድሁም ደግሞ በጽድቅ ስበረታ መንፈስ ቅዱስን በሙላት ያገኛል ። የእግዚአብሔር ቃልም በማቴዎስ 6 ፥ 33 እንደተጻፈው ከሁሉ አስቀድመን የእግዚአብሔርን ጽድቅና መንግስትን ስንፈልግ ለመንግስት የሚያበቃን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም እንቀበላለን አልፎም ተርፎ እንሞላለን ወዴ ሙላትም እንሻገራለን ። ለዚህም ምሳሌ እንዲሆነን በጽድቅ የበረታውን በቂሣሳርያ የአህዛብ አለቃ የነበረውን የቆርኔሌዎስን ታሪክ እናንብብ (የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 10) 1፤ በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። 2፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ። 3፤ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። 4፤ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ። 5፤ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። 6፤ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል። 7፤ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሎዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥ 8፤ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው። 9፤ እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ። 10፤ ተርቦም ሊበላ ወደደ፤ ሲያዘጋጁለት ሳሉም ተመስጦ መጣበት፤ 11፤ ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤ 12፤ በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት። 13፤ ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ። 14፤ ጴጥሮስ ግን። ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ አንዳች ርኵስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና አለ። 15፤ ደግሞም ሁለተኛ። እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ። 16፤ ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፥ ወዲያውም ዕቃው ወደ ሰማይ ተወሰደ። 17፤ ጴጥሮስም ስላየው ራእይ። ምን ይሆን? ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤ 18፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው። ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን በዚህ እንግድነት ተቀምጦአልን? ብለው ይጠይቁ ነበር። 19፤ ጴጥሮስም ስለ ራእዩ ሲያወጣ ሲያወርድ ሳለ፥ መንፈስ። እነሆ፥ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል፤ 20፤ ተነሥተህ ውረድ፥ እኔም ልኬአቸዋለሁና ሳትጠራጠር ከእነርሱ ጋር ሂድ አለው። 21፤ ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ። እነሆ፥ የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድር ነው? አላቸው። 22፤ እነርሱም። ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርንም የሚፈራ በአይሁድም ሕዝብ ሁሉ የተመሰከረለት የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ወደ ቤቱ ያስመጣህ ዘንድ ከአንተም ቃልን ይሰማ ዘንድ ከቅዱስ መልአክ ተረዳ አሉት። 23፤ እርሱም ወደ ውስጥ ጠርቶ እንድግድነት ተቀበላቸው። በነገውም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ወጣ፥ በኢዮጴም ከነበሩት ወንድሞች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ። 24፤ በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር። 25፤ ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት። 26፤ ጴጥሮስ ግን። ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው። 27፤ ከእርሱም ጋር እየተነጋገረ ገባ፥ ብዙዎችም ተከማችተው አግኝቶ። 28፤ አይሁዳዊ ሰው ከሌላ ወገን ጋር ይተባበር ወይም ይቃረብ ዘንድ እንዳልተፈቀደ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኵስና የሚያስጸይፍ ነው እንዳልል አሳየኝ፤ 29፤ ስለዚህም ደግሞ ብትጠሩኝ ሳልከራከር መጣሁ። አሁንም በምን ምክንያት አስመጣችሁኝ? ብዬ እጠይቃችኋለሁ አላቸው። 30፤ ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው። በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና። 31፤ ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ። 32፤ እንግዲህ ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤ እርሱ በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ እንግድነት ተቀምጦአል አለኝ። 33፤ ስለዚህ ያን ጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፥ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን። 34-35፤ ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ። እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ። 36፤ የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ። 37፤ ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ። 38፤ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ 39፤ እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት። 40፤ እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤ 41፤ ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን። 42፤ ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን። 43፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል። 44፤ ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። 45፤ ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤ 46፤ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና። 47፤ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ። 48፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።

Choir_Worship_2026_አለ_የተባለ_Gospel_Mezmur_ACIFNA_2026_Denver360p.mp38.39 MB

የትጋት ፍሬ ✍ ክፍል አንድ በየዘመኑ የአንድ አገር፣ የአንድ ቤተሰብ እንዲሁም የቤተከርስቲያን ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ተስፋ የሚጣልባቸው ወጣቶች ናቸው። የሰዎች የወጣትነት ዘመን የኃይል፣ የትጋት እና ራዕይን ለማሳካት መሰረት የሚጣልበት የእድሜ ክፍል ነው። በዚህ የጉልበት ዘመን የተዘራ ዘር በቀጣይ ዘመን ፍሬ ያፈራል፤ የሚገነባውም መሠረት የሕይወትን አቅጣጫ ይወስናል። ዛሬ ላይ እውን ሆነው የምናያቸው ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ከጊዜያት በፊት በተለያዩ ሰዎች ልብ ውስጥ በተወለዱ ራእዮች የተጀመሩ ናቸው። ያ ራእይ ግን ያለ ትጋት ወደ እውነት አልተለወጠም፡፡ በዘመናችንም ቢሆን ብዙ ወጣቶች ትልቅ ሕልም አላቸው፤ ነገር ግን ሕልምን ወደ እውነት የሚቀይረው ትጋት፣ ሥርዓት እና ታማኝነት እንጂ ምኞት ብቻውን አይደለም። ነገር ግን ዛሬ ባለንበት ዘመን፥ በብዙዎች ዘንድ የሰዎች ማንነት የሚለካው ባላቸው ሀብት፥ ንብረት እና ዝና እየሆነ መምጣቱ እና ሰዎችን በከፍተኛ የፉክክር ተጽእኖ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉ ለዘመናችን ወጣቶች ትልቅ ፈተና ሆኗል። በቀላሉ ሀብት ለማግኘት እና ያለ ትጋት ስኬትን ለማሳየት መሞከር እንደ መደበኛ ነገር እየተወሰደ መጥቷል። በዚህም ምክንያት ብዙ ወጣቶች ራዕያቸውን በሂደት እና በትጋት በማሳካት የሚገኝ ውጤትን በመናቅ፥ ትጋትን ከመውደድ ይልቅ ፈጣን ውጤትን በመፈለግ፥ በአቋራጭ መንገድ መበልጸግን እንደ አማራጭ ይወስዳሉ። ነገር ግን ምሳሌ 13፥11 “በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።” በማለት ዘላቂነት ያለው ነገር የሚገኘው በሂደት እና በትጋት ውስጥ እንደሆነ የሚመክረን ሲሆን፥ በተቃራኒው  ደግሞ በምሳሌ 28፥20 “የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።” በማለት በአቋራጭ መንገድ በችኮላ የምንሰበስበው ነገር ሁሉ ጉዳት እንዳለው ያስረዳናል። በአንዳንድ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ ሥራን እና ልፋትን ከኃጢአት ውጤት ጋር ሲያያይዙት ይስተዋላሉ። አዳም እና ሔዋን በገነት በነበሩበት ጊዜ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር “..በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ ” (ዘፍጥረት 3፥ 17 – 19) በማለት ከገነት የመባረራቸው ውጤት ስራ እና ልፋት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ እውነቱ ግን እንዲህ አይደለም። አዳም በሀጢአት ከመውደቁ በፊት ገነትን እንዲያበጃት እና እንዲጠብቃት እግዚአብሔር እንዳዘዘው በዘፍጥረት 2፥15 ላይ ማየት ይቻላል። ይህ የሚያሳየው ሥራ ቅጣት ሳይሆን የሰው ክብር መገለጫ መሆኑን ነው። በዘፍጥረት 2፥2 ላይ “እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።” የሚለው ቃል፥ ሥራ መሥራት የእግዚአብሔርን ባህርይ ከምንካፈልባቸው ነገሮች አንዱ መሆኑን ያመላክታል። ሰው የተፈጠረው እግዚአብሔርን በሥራው እንዲያከብር ነው፡፡ በመሆኑም ለክርስቲያን ወጣት አንዱ የሕይወት መለያው እምነቱን በሥራው ማሳየት ሲሆን፤ የሥራ ትጋት አማራጭ ሳይሆን የጥሪው አንዱ አካል ነው። ወጣትነት የትጋት ዘመን ወጣትነት የሚመለስ ዘመን አይደለም። የሚባክን ቀን አይመለስም። ሰለሞንም በመክበብ 12፥1 ላይ “በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ" በማለት እግዚአብሔርን ለማምለክም ቢሆን የወጣትነት እድሜ መልካም መሆኑን ይመክረናል። በህይወታችን ጥቂት ዘመናት ውስጥ አብዛኛውን ነገር የምናከናውንበት የወጣትነት ዘመናችንን ነው። ወጣትነት መሰረት የሚጣልበት እና የሚገነባበት ጊዜ ነው። የባህርይ ግንባታ፣ የሙያ ዝግጅት፣ የመንፈሳዊ እድገት፣ የቤተሰብ እሴቶችና የአገልግሎት መሠረቶች በወጣትነት ዘመን ይጣላሉ። ወጣትነትን በትጋት ያሳለፈ ሰው በእርጅናው የጥረቱን ፍሬ እንደሚሰበስብ፥ በስንፍና ያሳለፈው ግን ብዙ ጊዜ በጸጸት ይኖራል። ምሳሌ 6፥6 “አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች"። ጉንዳን መሪ የላትም፤ ስራ ለመስራትም የሚያስገድዳት የለም፡፡ ነገር ግን በምድር ላይ ለምትኖረው ጥቂት እድሜ ያለመታከት ትዘጋጃለች። ይህ ለወጣቶች ትልቅ ትምህርት ነው። ትጉህ ሰው ነገሮችን እንዲያከናውን እስኪነገረው አይጠብቅም፤ ኃላፊነቱን ራሱ በመውሰድ በትጋት ያከናውናል። ዕድልን ተስፋ በማድረግ ከመጠበቅ ይልቅ ራሱን ለተለያዩ ዕድሎች ያዘጋጃል። በዚህ ዘመን የሚፈልጉትን አይነት ስራ ባለማግኘታቸው “ሥራ የለም” ብለው ተስፋ የሚቆርጡ ወጣቶች ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚመለከተው ጥቂትም ቢሆን ያገኘነውን ዕድል በታማኝነት መጠቀማችንን ነው። በትንሹ ታማኝ የሆነ ሰው ለትልቅ አደራ ይታመናልና። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትጋታቸው እና በታማኝነታቸው ለወጣቶች አርአያ የሚሆኑትን ጥቂት ምሳሌዎች እንመልከት፡፡ @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH