uz
Feedback
SparkRise Academy

SparkRise Academy

Kanalga Telegram’da o‘tish

Welcome to SparkRise Academic Channel! Igniting curiosity, inspiring growth, and guiding you to reach your highest potential. Join us for expert tutoring!!

Ko'proq ko'rsatish
431
Obunachilar
-224 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
Iyul '26
Iyul '26
+11
0 kanalda
Iyun '26
+7
0 kanalda
Get PRO
May '26
+4
0 kanalda
Get PRO
Aprel '26
+4
0 kanalda
Get PRO
Mart '26
+2
0 kanalda
Get PRO
Fevral '26
+3
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '26
+3
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '25
+3
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '25
+9
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '25
+9
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '25
+8
0 kanalda
Get PRO
Avgust '25
+10
0 kanalda
Get PRO
Iyul '25
+61
0 kanalda
Get PRO
Iyun '25
+23
0 kanalda
Get PRO
May '25
+32
0 kanalda
Get PRO
Aprel '25
+13
0 kanalda
Get PRO
Mart '25
+17
0 kanalda
Get PRO
Fevral '25
+18
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '25
+40
2 kanalda
Get PRO
Dekabr '24
+25
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '24
+35
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '24
+64
1 kanalda
Get PRO
Sentabr '24
+51
1 kanalda
Get PRO
Avgust '24
+26
0 kanalda
Get PRO
Iyul '24
+16
0 kanalda
Get PRO
Iyun '24
+36
0 kanalda
Get PRO
May '24
+41
0 kanalda
Get PRO
Aprel '24
+55
0 kanalda
Get PRO
Mart '24
+38
1 kanalda
Get PRO
Fevral '24
+216
0 kanalda
Sana
Obunachilarni jalb qilish
Esdaliklar
Kanallar
15 Iyul0
14 Iyul0
13 Iyul0
12 Iyul0
11 Iyul+1
10 Iyul0
09 Iyul0
08 Iyul+2
07 Iyul+1
06 Iyul+1
05 Iyul+2
04 Iyul+3
03 Iyul0
02 Iyul+1
01 Iyul0
Kanal postlari
ቀጣይ 12ኛ ክፍል ለምትሆኑ ተማሪዎች ፤ ኢንትራንስ ላይ ከፍተኛ ውጤት የሚያገኙ ተማሪዎች (550+) የሚያመሳስላቸው ዋና ነገሮች 1. ካሁን ከክረምት ጀምሮ የሚጠኑበት ጊዜ ማንኛውም ተማሪ ትንሽ ሰዓት እያጠና ኢንትራንስ ላይ እንደጠቀስነው አይነት ከፍተኛ ውጤት ሊያገኝ አይችልም፡፡ ምናልባት በትንሽ ወር ውስጥ ትልቅ ውጤት አመጣን የሚሉ ተማሪዎች ሰምታቹ ሊሆን ፤ እነሱ ከመጀመሪያም ሲያጠኑ የነበረ ሲሆን፡፡ Simply ፈተናው ሲደርስ የሚያጠኑበት Intensity ነው የጨመሩት፡፡ 2. ከዚህ በፊት ያላቸው መሰረት(base) ከ 9 - 11ኛ ክፍል ጥሩ መሰረት ያላቸው ተማሪዎች ፤ እነዚህን ክፍሎች እንደአዲስ ሳይሆን revise ነው የሚያደርጉት፡፡ ይህ ትልቅ ጊዜ ይቆጥላበቸው፡፡ እነዚህ ላይ ጥሩ መሰረት የሌለው ተማሪ ፤ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ይበልጥ መልፋት ይኖርበታል፡፡ 3. ጥያቄዎችን መስራት ማንበብ ብቻውን በቂ አይደለም ፤ ጥያቄዎችን መስራት አለባቹ  በተለይ የኢንትራንስ ፈተናዎችን፡፡ ጠቀሜታው  ✅ ምንን ያህል እንዳወቃቹ ታዩበታላቹ ✅ ጥያቄ ስትሰሩ ፤ ይበልጥ እንድታስታውሱ ይረዳችኃል ✅ አጠያየቃቸው ተመሳሳይ ሆኖ ትንሽ ልዩነት ያላቸው ጥያቄዎች ታገኛላቹ  4. ትክክለኛ የሆነ የጥናት እቅድ ማውጣት እቅድ የሚያስፈልገው በሚቀራቹ ጊዜ ፤ ስታነቡ ለአንዱ ምእራፍ የምትሰጡት ጊዜ balanced እንዲሆን ነው፡፡ ለአንዱ ከልክ ያለፈ ጊዜ ፤ ሌላኛው ትንሽ ጊዜ ብቻ እንዳትሰጡ ይረዳችኃል፡፡ እንደዚህ ስታደርጉ በሳምንት ምን ያህል ምእራፍ ማንበብ እንዳለባቹ ታቃላቹ  እቅድ ስታወጡ ✅ ከ 9 - 11 revise የምታደርጉበትን ጊዜ ✅ የት/ቤት ክፍል ውስጥ የምትማሩበትን ✅ የ12ኛ ክፍል የምታነቡበትን ✅ ጥያቄ የምትሰሩበትን ያማከለ መሆን አለበት፡፡ —————————————-—————— እነዚህ 4ቱ ዋነኛ ምክንያት ናቸው፡፡ ከላይ ካልናቸው ውጪ ፤ ውጤታቹን በትልቁ የሚቀየር ነገር የለውም፡፡

2
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  የ2019 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት ዘመን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ልኳል። በዚህም የ2019 ትምህርት ዘመን የአዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከነሐሴ 26/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑ ታውቋል። በመላው ሀገሪቱ ትምህርት መስከረም 05/2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል። (ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅቶ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የላከው ሙሉ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ካሌንደር ከላይ ተያይዟል።) Via @tikvahuniversity
99
3
+2
Matn yo'q...
74
4
Matn yo'q...
1
5
🔔 የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት የ2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን ማለፊያ ውጤቱ 50% (ለአካል ጉዳተኞች 45 እ+1
🔔 የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት የ2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን ማለፊያ ውጤቱ 50% (ለአካል ጉዳተኞች 45 እና ከዚያ በላይ) እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የደረሰው የትምህርት ቢሮው መረጃ በሚያሳየው መሰረት ለፈተና ከተቀመጡ 85 ሺሕ 737 ተማሪዎች መካከል 82 ሺሕ 193 (95.85%) የሚሆኑት 50 እና ከዚያ በላይ ማለፊያ ውጤት አምጥተዋል። ከተፈታኞቹ መካከል 3 ሺሕ 544 የሚሆኑት ማለፊያ ውጤት አላመጡም። የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 96.25 ሲሆን ይህን ያመጣውን አንድ ተማሪ ነው። 60 ተፈታኞች 93% ውጤት አምጥተዋል። 1 ሺሕ 316 ተፈታኞች 90% እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ታውቋል። የዘንድሮው ውጤት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስላል ? በ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት 70 ሺሕ 525 ተፈታኞች፣ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 62 ሺሕ 639 (88.8%) ሲሆኑ፣ 7 ሺሕ 886 ተፈታኞች ማለፊያ ውጤት አላመጡም ነበር። የዘንድሮ የተፈታኞች ብዛት ከአምናው በ15 ሺሕ 212 የጨመረ ሲሆን፣ ማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተፈታኞች ደግሞ፣ ከአምናው በ4 ሺሕ 342 ቀንሷል። ዘንድሮ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 96.25 በአንድ ተማሪ ብቻ ሲሆን፣ በ2017 ዓ/ም ግን 113 ተማሪዎች 94% ውጤት አምጥተው ነበር። በአንጻሩ፣ ዘንድሮ 90% እና በላይ ያመጡት ተፈታኞች 1 ሺሕ 316 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ በ2017 ደግሞ ይህን ውጤት ያመጡት 712 ተማሪዎች ናቸው። በዚህም የዘንድሮው የ604 ብልጫ አለው። በተያያዘ መረጃ፣ ዘንድሮ ተማሪዎቻቸውን ካስፈተኑ 669 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 441ዱ 100% ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል። እንዲሁም በከተማ ደረጃ ከ93% በላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡት 60 ተማሪዎች ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
100
6
ጥቆማ‼ ነጻ የክረምት ስልጠና ይከታተሉ! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ለሆነ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና አዘጋጅቷል። የክረምት ስልጠና መስኮች፦ ● ፋንዳሜንታልስ ኦፍ ኤ.አይ. ● ፕሮግራሚንግ ● ማሽን ለርኒንግ ● ሮቦቲክስ እና IOT ● ዳታ ሳይንስ የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇 ሰኔ 30/2018 ዓ.ም በተከታዩ የጉግል ፎርም ይመዝገቡ 👇 https://forms.gle/uDGPmQsiZcWWeNuRA
132
7
❤️የመምህር ሚና ከምንም በላይ ነው የፑቲን እና የቀድሞ መምህርቱ አስደናቂ ገጠመኝ‼️ 1960ዎቹ አጋማሽ ይህ ወቅት በመጎርመስ ላይ ያለው ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ ካሉ አስቸጋሪ ልጆች ጋር ገጥሞ እንደ መፈንዳት ያለበት ጊዜ ነበር ። ..... እና ከማይሆኑ ልጆች ጋር ጓደኝነት በመመስረቱ ባህሪው እየተቀየረ መሆኑን ያየች የፑትን የጀርመንኛ ቋንቋ መምህርት እና የክፍል ሀላፊው በተማሪዋ ላይ ያየችውን የባህሪ ለውጥ ዝም ብላ ማለፍ አልፈለገችም ። ስለዚህ ትከታተለው ትመክረው እና ልክ እንደወላጅ ትቆጣጠረው ጀመር ። .... አንተ ዝም ብሎ ሰው ለመሆን አልተፈጠርክም ። በውስጥህ ታላቅ የሆነ ስብእና ያለው ሰው ነው የሚታየኝ ፡ ከራሱ አልፎ ሀገርን የሚጠቅም ጎበዝ ልጅ ። ... እያለች. ....ከማይሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ  ልቡ እንደማበጥ ያለበትን ትንሹን ፑቲን ለመመለስ ሞከረች ። .... እና ተሳካላት ። .... ቭላድሚር ፑቲን በመምህሩ እገዛ ከመጥፋት   ከመበላሸት ድኖ ትምህርቱ ላይ ማተኮር ጀመረ ። ... ለዛም ነው ቭላድሚር ፑቲን ስለ ህይወት ልምዱ ሲናገር ፡ በወጣትነት እድሜዬ ቬራ ዲሚትሪቭና ን  የመሰለ መምህር ባላገኝ ፡ አሁን የደረስኩበት ደረጃ ላልደርስ እችላለሁ ሲል የሚናገረው ። ........ እና ፡ እኚህ በአንድ ወቅት የቭላድሚር ፑቲን መምህርት የነበሩት ቬራ ዲሚትሪቭና ፡ ከትናንት ወዲያ ምሽት በክሬምሊን ቤተመንግስት  ተካሂዶ በነበረው አንድ የእራት ግብዣ ላይ እንዲገኙ ፡ ውለታውን አስቦ ለአመታት ሲደግፋች በቆየው ቭላድሚር ፑቲን በኩል ተጋብዘው ነበር ። ...... በመሆኑም ካሉበት ከተማ ተጉዘው ሞስኮ በሚገኝ አንድ ሆቴል በማረፍ የግብዣው ሰአት እስኪደርስ እየተጠባበቁ እያለ የሩሲያ ምርት የሆነ ጥቁር አውረስ V8 ከሆቴሉ በር ላይ  ቆመ ። .... የአውረሱ መኪና ነጂ ቭላድሚር ፑቲን ነበሩ ። እና ከመኪናው ከወረዱ በኋላ በእጃቸው ትልቅ አበባ ይዘው የዘጠና አመቷ የልጅነት መምህራቸው ወዳሉበት ቦታ ሄደው አገኘኟቸው ። .....   የሩሲያን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን ታላቅ የእራት ግብዣ ላይ እንዲካፈሉ የተጋበዙትን መምህርት ቬራ በሾፌር ወደ ቤተመንግስት  እንዲመጡ ከማድረግ ይልቅ  ፡ ራሳቸው ፕሬዝደንት ፑቲን መምህርቷን ይዘው መምጣት ስለፈለጉ ነበር  እየነዱ እዚህ ድረስ የመጡት  ። ... እና. . ቭላድሚር ፑቲን ሰኞ እለት  ባደረጉት በዚህ ነገር ውስጥ ትህትና ፡  ውለታን አለመርሳትና    ቅንነት ይህ ሁሉ አለበት ።
135
8
Matn yo'q...
112
9
📌 በኢንተርኔት ዓለም ውስጥ "ኩኪዎች" (Cookies) ምንድን ናቸው? ለምንስ የግላዊነት ጥያቄ ያስነሳሉ? ብዙዎቻችን የተለያዩ ድረ-ገጾችን ስንከፍት "ይህ ድረ-ገጽ ኩኪዎችን ይጠቀማል፣ ትቀበላለህ?" የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይገጥመናል። አብዛኛው ሰው ዝርዝሩን ሳያነብ "Accept" የሚለውን ይጫናል፤ ነገር ግን እነዚህ ትናንሽ ፋይሎች በዲጂታል ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው። ኩኪ (HTTP Cookie) ማለት አንድን ድረ-ገጽ ስንጎበኝ ያ ድረ-ገጽ ወደ ስልካችን ወይም ኮምፒውተራችን የሚልከው በጣም ትንሽ የሆነ የጽሁፍ ፋይል (Data) ነው። ይህ ፋይል ድረ-ገጹ እኛን ለይቶ እንዲያውቀንና ቀጣይ ስንመለስ ምርጫዎቻችንን እንዲያስታውስ የሚያገለግል እንደ "ዲጂታል መታወቂያ" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የኩኪዎች ዋነኛ ጥቅም ለተጠቃሚዎች ድረ-ገጾችን ምቹና ፈጣን ማድረግ ነው። ለምሳሌ፣ በአንድ ድረ-ገጽ ላይ አካውንታችንን ከፍተን ከገባን በኋላ (Login)፣ በየደቂቃው ድጋሚ የይለፍ ቃል እንዳይጠይቀን የሚያደርጉት እነዚህ ኩኪዎች ናቸው። እንዲሁም በቋንቋ፣ በገጽ ቀለም ወይም በሌሎች የግል ምርጫዎች ደረጃ የሰጠናቸውን ትዕዛዞች በቃላቸው ይዘው በመቆየት፣ በቀጣይ ጉብኝታችን ድረ-ገጹ በትክክል እኛ በፈለግነው መልኩ ተስተካክሎ እንዲጠብቀን ያደርጋሉ። ያለ ኩኪዎች አጠቃቀም፣ የኢንተርኔት ቆይታችን አሰልቺና በእያንዳንዱ እርምጃ መረጃን ደጋግመን የምናስገባበት ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ኩኪዎች ከጥቅማቸው ጎን ለጎን "ለምን ህግና ጥበቃ አስፈለጋቸው?" የሚለው ጥያቄ በስፋት ይነሳል። ምክንያቱም አንዳንድ ኩኪዎች የእኛን የኢንተርኔት እንቅስቃሴ (Browsing History) በዝርዝር የመከታተል አቅም አላቸው። በተለይ "Third-party cookies" የሚባሉት፣ ከአንድ ድረ-ገጽ አልፈው በሌሎች ገጾች ላይ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በመከታተል ምን አይነት ምርቶችን እንደምንፈልግ መረጃ ይሰበስባሉ። ይህ መረጃ ደግሞ ለትልቅ የማስታወቂያ ኩባንያዎች ተላልፎ ስለሚሰጥ፣ በፌስቡክ ወይም በዩቲዩብ ላይ የግል ፍላጎታችንን የሚመስሉ ማስታወቂያዎች ተከታትለው እንዲመጡብን ያደርጋል። ይህ ሁኔታ የሰዎችን የግል ሚስጥርና ነፃነት ይጋፋል ተብሎ ስለሚታመን፣ እንደ አውሮፓ ህብረት (GDPR) ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድረ-ገጾች ማንኛውንም መረጃ ከመሰብሰባቸው በፊት የተጠቃሚውን ፈቃድ እንዲጠይቁ በህግ አስገዳጅ አድርገዋል። ለማጠቃለል ያህል፣ በድረ-ገጾች ላይ የሚመጡ የኩኪ ምርጫዎችን ስናይ በዘፈቀደ ከመጫን ይልቅ አማራጮቹን ማየት ተገቢ ነው። ድረ-ገጹ በትክክል እንዲሰራ የሚያስፈልጉ (Essential) ኩኪዎችን መፍቀድ የግድ ቢሆንም፣ የእኛን የግል መረጃ ለንግድና ለማስታወቂያ የሚጠቀሙ ኩኪዎችን ግን የመከልከል መብት አለን። በዲጂታል ዘመን ስለ ቴክኖሎጂው አሠራር በቂ ግንዛቤ መያዝ፣ የግላዊነት መብታችንን ለማስከበር የመጀመሪያውና ዋናው እርምጃ ነው። #ShareThisPost ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት! Mohammed Seid #Technology #Cookies #DigitalPrivacy #CyberSecurity
137
10
Matn yo'q...
95
11
በነዳጅ ጉዳይ የምትጠቅም አንድ ሲስተም ላስተዋውቃችሁ‼ ============================== ✍️ ያው ሰሞኑን የነዳጅ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኖ የለ። በማደያዎች ላይ የሚታየው ረጃጅም ሰልፍ አድካሚ ነው፣ በየትኛው ማደያ ናፍጣ ወይም ቤንዚን እንዳለ፤ በአካል እዛ ተሂዶ ካልሆነ በስተቀር አድካሚ ነው። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ24 ሰዓት ቆይታ በፌስቡክ ገፁ የሚለቀው መረጃ አለ፣ በየትኛው የአዲስ አበባ 132 ገደማ ማደያዎች ምን ያክል መጠን ያለው ነዳጅ እንዳለ የሚጠቁም። ግን 24 ሰዓት ረጅም ነው፣ የንግድ ቢሮውን የፌስቡክ ገፅ የማይጠቀሙም ይኖራሉና የመረጃ ክፍተት ይኖራል። ይህንን ችግር ለመፍታት "EthioFuel" የተሰኘውን አዲስ የዲጂታል መፍትሄ ይዤ ብቅ ብያለሁ። EthioFuel ምንድን ነው? ይህ ስርዓት የነዳጅ አቅርቦትን ከነበረው የተዘበራረቀ እና በእጅ የሚሰራ አሰራር ወደ ዘመናዊ፣ ዳታን መሰረት ያደረገ እና ፈጣን ስርአት የሚቀይር የነዳጅ ክትትል እና የወረፋ መጠበቂያ ሲስተም ነው። ከተወሰኑ ፌቸሮቹ መካከል፦ ✅ የነዳጅ ክምችት እና ሎኬሽን (Live Map): ማደያው ነዳጅ አለው ወይስ የለውም? ምን ያህል ቀርቶታል? ያ ማደያ የሚገኘው አሽከርካሪው ካለበት በምን ያክል ርቀት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች በስልክ ብቻ በቀጥታ ማግኘት ይቻላል። ✅ ነዳጅ ለመቅዳት ስታስቡ በኦንላን ወረፋ ቀድሞ መያዝ(Virtual Queue): መንገድ በመዝጋት ሰልፍ መጠበቅ ይቀራል። በስልክ ቁጥር ብቻ ወረፋ በመያዝ፣ ከፊት ለፊታችሁ ስንት መኪና እንዳለ ማወቅ ይቻላል። በቦታው ስትደርሱም ወረፋ ስትይዙ ሲስተሙ የሰጣችሁን QR Code ስካን ያደርግና የማደያው ተቆጣጣሪ፣ ይቀዳላችኋል። ✅ የማጭበርበር መከላከል: የነዳጅ ስርቆትን ወይም ያለአግባብ መጠቀምን ለመቆጣጠር መኪኖችን በታርጋ እና በታንከር መጠናቸው ይቆጣጠራል። አንድ አሽከርካሪ የሆነ ማደያ ቀድቶ ሂዶ፣ በህገ ወጥ መምገድ ሽጦና ቶሎ ጨርሶ ወደ ሌላው ሂዶ እየቀዳ የሌላውን እድል እንዳያጣብብ፣ ሲስተሙ በቀላሉ በኤአይ ፌቸሩ ይለየዋል። ✅ ለባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ዳሽቦርድ: Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration እና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በቀጥታ ስርጭት (Real-time) መረጃን በመከታተል የተሻለ ውሳኔ እንዲወስኑ ያግዛቸዋል። ይህ አሽከርካሪዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ወይም የመንግስት አካላት ከሆናችሁ፡ ❓ በዚህ ዘርፍ ሌላ ምን አይነት ችግር አለ? ❓ ምን አይነት ፌቸር ቢጨመር ትፈልጋላችሁ? ሀሳባችሁን አጋሩኝ። ሞክሩት፡ 📲 ethiofuel.muradtadesse.com እንደ አሽከርካሪ ሆናችሁ ለማየት: ስልክ: 0912345678 ፓስወርድ: 12345678 OTP የሚልከውን ቀለል ያደረግኩት፣ ለእያንዳንዱ ኦቲፒ ክፍያ ስላለው ነው። ትክክለኛ ኦፊሲያል ለተግባር ሲውል፤ በዛ መልኩ ይስተካከላል። ከአዲስ አበባ ባሻገር፣ በየትኛውም ክልል የሚገኝን ማደያ ወደ ሲስተሙ ማስገባት ይቻላል። የማደያ ዝርዝር የተጠቀምኩት የአዲስ አበባዎቹን ነው። ሎኬሽን ጦር ኃይሎች ያለውን ኖክ ማደያ ነው ለሁሉም ያደረግኩት፤ ምክንያቱም በቀላሉ የሌሎቹን ማደያ ሎኬሽን ማፕ ላይ ላገኘው አልቻልኩም። ወደ ሲስተሙ የተመዘገበ የዛ ማደያ ተቆጣጣሪ ትክክለኛውን የራሱን ማደያ ሎኬሽንና መሰል መረጃ በትክክል ማስገባት ይችላል። https://www.linkedin.com/posts/muradtadesse_ethiofuel-techforgood-activity-7449476550158168064-pyP-?utm_source=share&utm_medium=member_desktop&rcm=ACoAACaUP2oB3u_jeD6TvqRssom8jDTi6earRyc
0