uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

Ethio - ዜና 🇪🇹

Ethio - ዜና 🇪🇹

Kanalga Telegram’da o‘tish

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን Ethio ዜና ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Ethiozenaa_bot

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Ethio - ዜና 🇪🇹 analitikasi

Ethio - ዜና 🇪🇹 (@ethio_zena23) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 100 302 obunachidan iborat bo'lib, Rasm toifasida 75-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 314-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 100 302 obunachiga ega bo‘ldi.

07 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -1 001 ga, so‘nggi 24 soatda esa -96 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 2.87% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 3.01% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 2 879 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 3 018 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 21 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን Ethio ዜና ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Ethiozenaa_bot”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 08 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Rasm toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

100 302
Obunachilar
-9624 soatlar
-3687 kun
-1 00130 kun
Postlar arxiv
በሚኒስቴሮች ላይ የሚደረገው ሚስጢራዊ ክትትል‼️ በነባሩ ካቢኔ አባላት እና ሚኒስትር ድኤታዎች ላይ ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚሰጥራዊ ክትትል ሲደረግ እንደቆየ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተና
በሚኒስቴሮች ላይ የሚደረገው ሚስጢራዊ ክትትል‼️ በነባሩ ካቢኔ አባላት እና ሚኒስትር ድኤታዎች ላይ ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚሰጥራዊ ክትትል ሲደረግ እንደቆየ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ዛሬ በተሾሙት ሚኒስትሮች ላይም ክትትል እና ግምገማው ቀጥሎ በስራቸው ውጤታማ ባልሆኑት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ የዛሬው የካቢኔ ሹም ሽር የተካሄደው ብዙ ነገሮች ከግምት ገብተው በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሹመቱ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱ አስተያየቶችን መሰረት አድርገው በሰጡት ማብራሪያ ፤ በነባሩ የካቢኔ አባላት እና ሚኒስትር ድኤታዎች ላይ ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። በሀገር ውስጥ እና በውጪ የነበራቸው እንቅስቃሴ ፤ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸው አማካይነት ጭምር ከየትኞቹ ሀብታሞች ጋር ይገናኛሉ የሚለውን ስንከታተል ነበር ብለዋል። ክትትል ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ሚኒስትር ስሙ በሚነሳበት ጉዳይ አስተያየቱን ተጠይቋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ምንም ዓይነት የጥርጣሬ ዝንባሌ የታየባቸውን ግን የካቢኔ አባል አላደረግናቸውም ሲሉ አክለዋል፡፡ በተሾሙት ሚኒስትሮች ላይ አሁንም ክትትል እና ግምገማ ይደረጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጤታማ ያልሆኑት እየታዩ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ብለዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በጠ/ሚንስትሩ የትምህርት ሚንስትር ፕሬዘዳንት ሁነው እንዲቀጥሉ በድጋሚ ታጭተዋል !
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በጠ/ሚንስትሩ የትምህርት ሚንስትር ፕሬዘዳንት ሁነው እንዲቀጥሉ በድጋሚ ታጭተዋል !

የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸው ተሰማ! የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ያነጋገሯቸውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል። ይሁንና ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ
የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸው ተሰማ! የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ያነጋገሯቸውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል። ይሁንና ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከላከያም ሆነ የትግራይ ሰላም ሃይል ወደ ከተማዋ ያልገቡ ሲሆን እየመጡ ነው የሚል ወሬ እንደሰሙና ዝርፊያ እንዳይፈጸም በመፍራት ሁሉም ሱቁንና ቤቱን ዘግቶ እየተጠባበቀ እነደሆነ ገልጸዋል።

በትክክለኛው የንግድ ቦታ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ! 📍( ፒያሳ አደዋ 00) ✅ ፒያሳ ጊዮርጊስ ፊትለፊት በ 1 አመት ውስጥ ተረክበው ቢፈልጉ ማከራየት ወይም እራሶ መነገድ የሚችሉበት አዋጭ ኢንቨስትመንት
በትክክለኛው የንግድ ቦታ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ! 📍( ፒያሳ አደዋ 00) ✅ ፒያሳ ጊዮርጊስ ፊትለፊት በ 1 አመት ውስጥ ተረክበው ቢፈልጉ ማከራየት ወይም እራሶ መነገድ የሚችሉበት አዋጭ ኢንቨስትመንት አማራጭ ከቴምር እሪል እስቴት 2B+G+5 ዘመናዊ የንግድ ሞል ስፋት=ከ20 ካሬ ጀምሮ ጠቅላላ ዋጋ እና አከፋፈል ✅3ኛ ፎቅ- 5.3 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ-  1.7 ሚልዮን ብር ✅4&5ኛ ፎቅ- 4.8 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ ቅድመ ክፍያ- 1.4 ሚልዮን ብር ✅Semi basement በ ወስጥ በኩል- 8 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ- 3.3 ሚልዮን ብር ✅Semi basement በ ውጭ በኩል  - 11 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ- 4.5 ሚልዮን ብር ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 09 -81-85-88-35

ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ከ ኢትዮጵያ ቴሌኮም ወደ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር https://t.me/Ethio_Zena23 https://t.me/Ethio_Zena23
ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ከ ኢትዮጵያ ቴሌኮም ወደ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር https://t.me/Ethio_Zena23 https://t.me/Ethio_Zena23

አሜሪካ በ #ኢትዮጵያ «ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ» ስትል የደህንነት ማስጠንቀቂያ አወጣች‼️ አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል፣ በተያዘው የፈረንጆቹ
አሜሪካ በ #ኢትዮጵያ «ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ» ስትል የደህንነት ማስጠንቀቂያ አወጣች‼️ አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል፣ በተያዘው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር «በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት» ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ በሚል በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች። አሜሪካ ረቡዕ ምሽት ባወጣችው መግለጫ «በጥቅምት ወር [እ.አ.አ.] በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች ደርሰውኛል» ብላለች። አሜሪካ አክላም ዜጎቿ «አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና»  ባለሥልጣናት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስባለች። አሜሪካ ማምሻውን ባወጣችው የደህንነት ማስጠንቀቂያ በተጨማሪም ዜጎቿ «በማንኛውም ምክንያት» ወደ #አማራ ክልል (#ላሊበላን ጨምሮ)፣ ወደ #ትግራይ ክልል ወይም ወደ #ዓፋር ክልል ከማንኛውም ዓይነት ጉዞ እንዲቆጠቡ መክራለች። ቀደም ሲል በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎቿ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከሆነ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ፣ ካልሆነ ደግሞ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ ድረስ ባሉበት ቦታ እንዲጠለሉ አሳስባለች።

«በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች በፌዴራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ቆሰሉ፤ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አለፈ» ​በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ጉቢቻ ቀበሌ የጉምሩክ ጥበቃ የሚያደርጉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በከፈቱት ተኩስ ንጹሃን ሰዎች መመታታቸው ተገለጸ። የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ «ኮንትሮባንድ እቃ ይዛለች» ባሏት አንድ ባጃጅ ላይ በከፈቱት ተኩስ ጥቃቱ መከሰሱ ተገልጿል። በተከፈተው ተኩስ ወደ ስፖርት በመሄድ ላይ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በማድረስ ላይ የነበሩ የእድሜ ባለጸጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች በጽኑ ቆስለዋል። ተጎጂዎቹ ምንም የማያውቁ ንጹሃን መሆናቸውንና በባጃጇ ተጭኖ የነበረውም እቃ ኮንትሮባንድ ሊባል የማይችል እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

"የኢሳይያስ ጸጸቶች እና የአሁኑ ጦርነት ግብ" ጀዋር መሃመድ ኢሳይያስ "ሁለት ታሪካዊ ስህተቶችን ፈጽሜያለሁ" በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ይጸጸታል። ይህንኑ ስህተት ለሶስተኛ ጊዜ ላለመድገምም ጽኑ ውሳኔ
"የኢሳይያስ ጸጸቶች እና የአሁኑ ጦርነት ግብ" ጀዋር መሃመድ ኢሳይያስ "ሁለት ታሪካዊ ስህተቶችን ፈጽሜያለሁ" በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ይጸጸታል። ይህንኑ ስህተት ለሶስተኛ ጊዜ ላለመድገምም ጽኑ ውሳኔ ላይ ደርሷል። አንደኛው ጸጸቱ፡ እ.ኤ.አ. በ1991 መለስ ዜናዊን ደግፎ አራት ኪሎ ካስገባው በኋላ፣ ባልጠበቀው ሁኔታ ከአምስት ዓመታት በኋላ ተመልሶ መወጋቱ ነው። ሁለተኛው ጸጸቱ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ከህወሓት ጥቃት ታድጎ ካተረፋቸው በኋላ፣ ውለታውን በመካድ ከህወሓት ጋር መታረቃቸው እና አልፎ ተርፎም የባህር በር ጥያቄ በማንሳት ስጋት መፍጠራቸው ነው። ከእነዚህ ተሞክሮዎች በመነሳት፣ አራት ኪሎን የሚቆጣጠር ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ውሎ አድሮ ለእርሱ ጠላት መሆኑ እንደማይቀር በጽኑ ያምናል። በመሆኑም ያንን ስህተት ለሶስተኛ ጊዜ ላለመድገም ቆርጦ ተነስቷል። ለዚህም ያስቀመጠው የመጨረሻ መፍትሄ የአራት ኪሎን ስርዓት ሙሉ በሙሉ ማፍረስ ነው። የአራት ኪሎ ስርዓት ስንል የኢትዮጵያን የመንግስት (state) መዋቅር ማለታችን ነው። ይህ የምነግራችሁ ጉዳይ ተራ ግምት አይደለም። በአይን ያየነው እና በጆሮ የሰማነው ገሃዳዊ እውነት ነው!

🚨 «በህወሓት ከመሬት በታች የተገነባ ትልቅ የመሣሪያ ዴፖ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ዋለ» ​በህወሓት ከመሬት በታች በድብቅ የተገነባ ትልቅ የወታደራዊ መሣሪያዎች ዴፖ በሀገር መከላከያ ሠራዊት
+5
🚨 «በህወሓት ከመሬት በታች የተገነባ ትልቅ የመሣሪያ ዴፖ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ዋለ» ​በህወሓት ከመሬት በታች በድብቅ የተገነባ ትልቅ የወታደራዊ መሣሪያዎች ዴፖ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መዋሉን የዜና ምንጮች ዘገቡ። ​🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​የዴፖው አደረጃጀት፦ ከመሬት በታች የተገነባው ይህ መጋዘን ድልድይ በሚመስል የተደበቀ መግቢያ የተሠራና ከፍተኛ መጠን ያለው የወታደራዊ ቁሳቁስ ማከማቸት የሚችል እንደሆነ ተገልጿል። ​የተገኙ የመሣሪያ ዓይነቶች፦ በመጋዘኑ ውስጥ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት ተገዝተው የተከማቹ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች እና የወታደራዊ ትጥቅ ዓይነቶች ተገኝተው በመከላከያ ሠራዊቱ እጅ መግባታቸው ተመላክቷል።

በሰሜን ሸዋ በመኃል ሜዳ እና ዘመሮ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተገለጸ ​በሰሜን ሸዋ ዞን በመኃል ሜዳ እና በዘመሮ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ቀበሌዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ
በሰሜን ሸዋ በመኃል ሜዳ እና ዘመሮ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተገለጸ ​በሰሜን ሸዋ ዞን በመኃል ሜዳ እና በዘመሮ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ቀበሌዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የአንኳር ዜና ምንጮች ገልጸዋል። ​የተኩስ ልውውጥ መከሰት፦ በሰሜን ሸዋ ንጋት ላይ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ የተጀመረ ሲሆን፣ በአካባቢው አልፎ አልፎ የከባድ መሣሪያ ድምፅ እንደሚሰማ ተመላክቷል። ​የአካባቢው ሁኔታ፦ የፋኖ ታጣቂዎች በመኃል ሜዳ እና ዘመሮ ከተሞች እንዲሁም በአቅራቢያ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል። ​የምስል መረጃ፦ የተላከው ምስል በዘመሮ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ታጣቂዎች የተገኙበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።

ሰበር ዜና! የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ! የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች
ሰበር ዜና! የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ! የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ  የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ” እየተጓዙ መሆናቸውን በአዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ገልጸዋል። የአዲግራት ከተማ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።ወታደሮቹ ከአዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። https://t.me/Ethio_Zena23 https://t.me/Ethio_Zena23

በትክክለኛው የንግድ ቦታ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ! 📍( ፒያሳ አደዋ 00) ✅ ፒያሳ ጊዮርጊስ ፊትለፊት በ 1 አመት ውስጥ ተረክበው ቢፈልጉ ማከራየት ወይም እራሶ መነገድ የሚችሉበት አዋጭ ኢንቨስትመንት
በትክክለኛው የንግድ ቦታ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ! 📍( ፒያሳ አደዋ 00) ✅ ፒያሳ ጊዮርጊስ ፊትለፊት በ 1 አመት ውስጥ ተረክበው ቢፈልጉ ማከራየት ወይም እራሶ መነገድ የሚችሉበት አዋጭ ኢንቨስትመንት አማራጭ ከቴምር እሪል እስቴት 2B+G+5 ዘመናዊ የንግድ ሞል ስፋት=ከ20 ካሬ ጀምሮ ጠቅላላ ዋጋ እና አከፋፈል ✅3ኛ ፎቅ- 5.3 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ-  1.7 ሚልዮን ብር ✅4&5ኛ ፎቅ- 4.8 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ ቅድመ ክፍያ- 1.4 ሚልዮን ብር ✅Semi basement በ ወስጥ በኩል- 8 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ- 3.3 ሚልዮን ብር ✅Semi basement በ ውጭ በኩል  - 11 ሚልዮን ብር ሙሉ ክፍያ 👉ቅድመ ክፍያ- 4.5 ሚልዮን ብር ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 09 -81-85-88-35

ኢቦላ ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ገባ‼️ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ያለው የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ወረርሽኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ኬንያ ደርሷል። የኬንያ ዜጋ የሆነ እና በኮንጎ ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ከኮንጎ በኡጋንዳ በኩል ተጉዞ ጥቅምት 3 ቀን 2026 ናይሮቢ ደርሷል። በኋላም ምርመራ ተደርጎለት የቡንዲቡግዮ ቫይረስ መያዙ ተረጋግጦ በናይሮቢ ሕይወቱ አልፏል። ከታካሚው ጋር ቅርበት የነበራቸው 28 ሰዎች ተለይተው በክትትል ላይ ሲሆኑ፣ ከእርሱ ጋር በአንድ በረራ የተጓዙ 23 ተሳፋሪዎችና 4 የበረራ ሠራተኞች እየተፈለጉ ነው። የኬንያ ባለሥልጣናት በመግቢያ ነጥቦች የጤና ምርመራን አጠናክረዋል፤ WHO ደግሞ ለኬንያ የኢቦላ ምርመራ ኪቶችና የግል መከላከያ መሣሪያዎች ማቅረቡን ገልጿል። WHO እንደገለጸው፣ የቡንዲቡግዮ ኢቦላ በተለይ ከታመመ ሰው ደም ወይም ሌሎች የሰውነት ፈሳሾች ጋር በቀጥታ ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል። በአሁኑ ጊዜ ለዚህ ዝርያ የተፈቀደ የተለየ ክትባት ወይም ሕክምና የለም፤ የሕክምና እና የክትባት ሰጭዎች ግን በምርምር ላይ እንደሆኑ ተገልፆአል።

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ሆና ሳለ፣ ህብረቱ ግን የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ለማስተናገድ አልቻለም።" ሲሉ ፓንአፍሪካን በማቀንቀን የሚታወቁት ፕሮፌሰር ሉሙምባ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ሆና ሳለ፣ ህብረቱ ግን የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ለማስተናገድ አልቻለም።" ሲሉ ፓንአፍሪካን በማቀንቀን የሚታወቁት ፕሮፌሰር ሉሙምባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያቀረበችው ጥያቄ ተገቢ ነው፣ኢትዮጵያ አሰብ እና ምፅዋን ብትጠቀም ኤርትራ በብዙ እንድትጠቀም ገለፀዋል።

የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ እንዲሰባሰቡ መንግስት ጥሪ አቀረበ   የብሔራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ አካባቢ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል እንዲሰባሰቡና ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።   ምክትል ኮሚሽነሩ በቪዲዮ በተሰራጨው አጭር መልዕክታቸው፤ የመንግሥት ጥሪን በመጠበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ታጣቂዎች እንዳሉ ገልጸው፣ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል መግባት እንደሚቻል አስታውቀዋል።   ጄኔራሉ፤ ለመልሶ ማቋቋምና ተሃድሶ (ዲ.ዲ.አር) ፕሮግራም የተዘጋጁ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሰላም ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በርካታ ታጣቂዎች በየአካባቢው በሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች እጅ እየገቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።   ምክትል ኮሚሽነሩ መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስፈላጊውን በጀት መመደቡንና ኮሚሽኑም ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተጨማሪም የትግራይ ወጣቶች ከጦርነት እሳት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኩል ከፍተኛ ድጋፍ መኖሩን አስረድተዋል።   በመሆኑም ታጣቂዎች በየአካባቢው ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች በግለሰብም ሆነ በተደራጀ መንገድ ሪፖርት በማድረግ፣ የጦር መሣሪያና ወታደራዊ ቁሳቁሶቻቸውን በማስረከብ በመቀሌ አካባቢ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።   ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ በመግለጫቸው “ወጣቱ ለተወሰኑ ጽንፈኞችና ግለሰቦች ዓላማ ተብሎ በጭፍን ማለቅ የለበትም፤ ሁሉም ጨለማ አይደለም፣ ብርሃን አለ” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም መጀመሪያ ላይ በራሳቸው ፍላጎት የተቀላቀሉም ሆነ በኋላ ላይ ተገድደውና ታፍሰው የገቡ ወጣቶች አማራጭ እንዳለ አውቀው ወደ መንግሥት እንዲገቡ አሳስበዋል።   በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ወደ ተሃድሶ ማዕከላት በመግባት ተሃድሶ ከወሰዱ በኋላ፣ በመልሶ ማቋቋምና በመልሶ ማደራጀት ሥራ ውስጥ ተካተው የራሳቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን፣ የትግራይ ክልልን እንዲሁም የሀገርን አቅም መገንባት እንዲችሉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል መግባት እንደሚቻል ተገልጻል።

"ውጊያው አልቋል" ጀኔራል ሳሞራ የኑስ የቀድሞው የጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም ጀኔራል ሳመራ የኑስ ከኤን ቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ:- 📌ውጊያው መጀመሪያውኑ እንዳለቀ ማወቅ ያስፈልጋል። ከእንግዲህ
"ውጊያው አልቋል" ጀኔራል ሳሞራ የኑስ የቀድሞው የጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም ጀኔራል ሳመራ የኑስ ከኤን ቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ:- 📌ውጊያው መጀመሪያውኑ እንዳለቀ ማወቅ ያስፈልጋል። ከእንግዲህ በኋላ ጦርነቱን መቀጠል መቁሰልን፣ መቆሰስንና የሞት ቁጥርን ከመጨመር ባለፈ ምንም ዓይነት ዘላቂ ወይም አዎንታዊ ውጤት ሊያመጣ አይችልም። 📌 የመከላከያ ኃይሉ ያሳየው ፍጥነት፣ የዝግጁነትና የመዋጋት ብቃት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። 📌 ጦርነቱን የትግራይ ህዝብም ሆነ አብዛኛው ወታደር እንደማይደግፈው፤ የሕዝቡ ዋና ፍላጎት ሰላምና ልማት መሆኑን ተናግረዋል። 📌ይህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ አጀንዳ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ከሚፈልጉ የውጭ ጠላቶችና የሻዕቢያ/የግብፅ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ጋር የተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል። 📌 ውጊያው ስለአለቀ ወታደሩ/ታጣቂው ወደ ህዝቡ መቀላቀል፣ ወደ ቤቱ መመለስ ወይም እጁን መስጠት አለበት።   📌መሪዎች፣ ፖለቲከኞችና ጄነራሎች ይኸው እውነታ ተረድተው የህዝቡን እልቂት ለማስቀረት ወደ ሰላም መንገድ መምጣት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ልዩ መረጃ‼️ በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ሆቴል ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የዶ/ር ደብረጽዮን ጠባቂዎችን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመቐለ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ በዓድዋ ከተማ በሚገኘው "ሶሎዳ ሆቴል" ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ዒላማ ያደረገ ነበር። በጥቃቱ ወቅት የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፣ የእርሳቸው ጠባቂዎች ግን በዚሁ የድሮን ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። በጥቃቱ በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የታጠቁ የጥበቃ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ቀሪዎቹ ሦስቱ በወቅቱ በሆቴሉ ያረፉ/ሲስተናገዱ የነበሩ ሲቪሎች ሲሆኑ፣ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ዶ/ር ደብረጽዮንን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ከፍተኛ ኃላፊዎች በሆቴሉ ስለመኖራቸው እስካሁን የወጣ ይፋዊ መረጃ የለም። የዘገባው ዳራ (የመከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በዓድዋ ከተማ ሆቴሎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ከ4 ጊዜ በላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ይህም እርምጃ አመራሮቹ ያሉባቸውን አቅጣጫዎች ዒላማ ካደረገ የአየር ላይ ክትትል ጋር ተያይዞ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

photo content

#ይህ ወንጀል ነው፣ድርጊቱም አሳፋሪ ነው‼️ የሽንት ቤት ቆሻሻን በወንዝ ውስጥ የለቀቁ ግለሰቦች ተያዙ! በደብረ ብርሃን ከተማ የሽንት ቤት ቆሻሻን በበሬሳ ወንዝ ውስጥ በመልቀቅ የአካባቢ ብክለት የፈ
+1
#ይህ ወንጀል ነው፣ድርጊቱም አሳፋሪ ነው‼️ የሽንት ቤት ቆሻሻን በወንዝ ውስጥ የለቀቁ ግለሰቦች ተያዙ! በደብረ ብርሃን ከተማ የሽንት ቤት ቆሻሻን በበሬሳ ወንዝ ውስጥ በመልቀቅ የአካባቢ ብክለት የፈጠሩ ግለሰቦችን  የከተማው ደንብ ማስከበር ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት መኪኖችን አድኖ የመያዝ ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን እስካሁን 3ቱ መኪኖች የተያዙ ሲሆን ከድርጊቱ አስከፊነት አንፃር ቀሪ መኪኖቹን የመፈለግ ስራ  ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ነብዩ አሰፋ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማው ውስጥ የሚከሰቱ አጠቃላይ ህገ ወጥ ተግባራት ዙሪያ እንደተቋም ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራን እንገኛለን ያሉት ኃላፊው  በተለይ አሁን ከተከሰተው ከወንዝ ብክለት ጋር አጋር ተቋማት በተለይም አካባቢ ጥበቃ መ/ቤትና ጤና መምሪያ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። በመጨረሻም ህብረተሰባችን እንደዚህ ዓይነት ህገ ወጥና ለአካባቢ በተለይም ለውሃ ልማት የማይጨነቁ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  በማሳሰብ ህብረተሰባችን የተለመደ ጥቆማውን ቢያደርሰን ፈጥነን የምንሰራና የምናስተካክል መሆኑን እንገልፃለን ብለዋል። አሁንም ቢሆን በተያዙ መኪናዎች ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል። መረጃው የከተማው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ነው።

በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 6
በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ 2019 በጀት ዓመት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበይት ተግባራ እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት የሀገሪቱን የኃይል ተደራሽነት 65 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።