ግጥም
Kanalga Telegram’da o‘tish
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Ko'proq ko'rsatish5 343
Obunachilar
+924 soatlar
+697 kun
+18930 kun
Postlar arxiv
5 343
ይኸ Airdrop በጣም አሪፍ ዋጋ ይኖረዋል እየተባለ ነው የቻላችሁትን ስሩ
https://t.me/herewalletbot/app?startapp=7136088
5 343
#ሳይኖር_አለቀ !!!
ከአለማነው ይልቅ የአጠፋነው በዝቶ
የቃረምነው እውቀት በዜሮ ተባዝቶ
ቁሳቁስ ተከብሮ ሰውነት ተናቀ
ኖርነው ያልነው ህይወት ሳይኖር አለቀ
የጋራነት ቀርቶ የግል ያልነው በዝቶ
ጥሎ ማለፍ ሆነ እርስ በእርስ ተጋፍቶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
መናገርን እንጂ ማድመጥን ማን ወዶ
ጫጫታ ነው ህይወት ሁሉም በግል አብዶ
ጆሮ በጠፋበት ምላስ ተርፎ ሲያደር
ለካስ እብደት ማለት ያኔ ነው ግርግር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_በዕውቀቱ ስዪም
5 343
#ካልዳሰስኩ_አላምንም
ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን
ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን
ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ
ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ
ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ
ያገር ልማድ ሆኗል
እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ
ፍቅር ስጋ ለብሶ በጁ ካላቀፈኝ
ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ
ኢምንት ነው ምንም
ካልዳሰስኩ አላምንም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_በዕውቀቱ ስዪም
5 343
#ፍቅር_የእውነት_ሲፈርድ
የሳቅሽብኝ አልፎ መሳቅ መጀመሬ
ሳፈቅርሽ ጠልተሽኝ ዛሬ መፈቀሬ
ግዜ ዳኛ ሆኖ ፍቅር የእውነት ሲፈርድ
ፈላጊው ሲፈለግ ተወዳጁም ሲወድ
የህይወት አዙሪት በተራ መዟዟር
የወደደው ጠልቶ የጠላው ሲያፈቅር
ይኼ ነው ሚዛኑ በሰፈሩት ቁና
ትላንት የገፋ ሰው ዛሬ ወድቋልና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
የሰው ልጅ ታሪኩ ከውልደት እስከሞት
በውል ተፈትሾ መጽሐፍ ቢጻፍለት
ቁም ነገሩ ብቻ ተቆጥሮ ቢዳሰስ
ከአንድ አንቀጽ አይዘልም ዘመኑ ቢጠቀስ
በዋዛ ፈዛዛ ያሳለፈው ግዜ ይበልጣል ስፍረቱ
ከኖረበት እድሜ የሰው ልጅ ህይወቱ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
#ወፍነት_አማረኝ
ምነው ወፍ ባረገኝ በሰማይ በራሪ
ከዛፍ ዛፍ መርጬ ነፃ ጎጆን ሰሪ!
ሳልዘራ ሳላጭድ ሳልጨነቅ ነዋሪ
በማለዳ ድባብ በፍቅር ዘማሪ
ሰው ሆኜ ሰው ሆኖ መኖር ከከበደኝ
እግዚአብሔር በቃሉ ምነው ወፍ ባረገኝ!!!
በክፋት በተንኮል ሰው ሆኖ ከመኖር
ወፍነት አማረኝ በነፃነት መብረር!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
ሰው የሚሆን እንጅ የጠፋው ዘንድሮ
ዘር የሚቆጥርማ ሞልቷል በየጓሮ
እያደሩ ማነስ ሰው መሆን እረክሶ
በስጋው ይመካል ለሚቀር በስብሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
#ብታመም_ነው_እንጂ!!
የማይገኝ ነገር ያምረኛል ዘንድሮ
ወተት ወተት አልኩኝ ገዛሁና ዶሮ
በእኔ የደረሰው አይድረስባችሁ
ዶሮ ገዝቶ ወተት ከቶ አያሰኛችሁ
አወይ የእኔስ ነገር ለማን ይነገራል
በቅሎ ስቶልድ ማየት አብዝቶ ያምረኛል
ብታመም ነው እንጂ ብለከፍ ዘንድሮ
እንዴት ሰው ይመኛል ወተትን ከዶሮ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
#አበጀው_በያቸው
አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው
እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው
በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ
ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ
ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ
እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ
እኔ ያንቺ ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ
እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ
እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ
በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ
ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና
የሚያንከራትተኝ ያው ፍቅርሽ ነውና
ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው
የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
ጌታ መምጫኽ ዘመን ከመድረሱ በፊት
ልቤን ልብ ስጠው መልሰው ከጥፋት
ጴጥሮስን ከክህደት የመለሰው ዶሮ
ለእኔም ላከውና ያንቃኝ ልቤን ሰብሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
#ነይ_አብረን_እንማ
ባህል እንዲቀጥል በትውልድ ከተማ
በፌስቡክ በቲክቶክ ነይ አብረን እንማ
የጥንቱ ዘምኖ ከጀበና እርቆ
ሀሜት ዲጂታል ነው ትውልዱ ተራቆ
በቀጥታ ግቢ ከሀሜት ከተማ
በተሻሻለው ህግ ነይ አብረን እንማ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 343
ትማራለች ብዬ ሙያ ከጎረቢት
አግብቻት ነበረ አድልቼ ለውበት
እንኳንስ ልትማር የምታውቀው ጠፋት
ሽንኩርት ግዛ አለችኝ ገንፎ ለማገንፋት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
