ru
Feedback
ግጥም

ግጥም

Открыть в Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

Больше
5 343
Подписчики
+924 часа
+697 дней
+18930 дней
Архив постов
ይኸ Airdrop በጣም አሪፍ ዋጋ ይኖረዋል እየተባለ ነው የቻላችሁትን ስሩ https://t.me/herewalletbot/app?startapp=7136088

#ሳይኖር_አለቀ !!! ከአለማነው ይልቅ የአጠፋነው በዝቶ የቃረምነው እውቀት በዜሮ ተባዝቶ ቁሳቁስ ተከብሮ ሰውነት ተናቀ ኖርነው ያልነው ህይወት ሳይኖር አለቀ የጋራነት ቀርቶ የግል ያልነው በዝቶ ጥሎ ማለፍ ሆነ እርስ በእርስ ተጋፍቶ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

መናገርን እንጂ ማድመጥን ማን ወዶ ጫጫታ ነው ህይወት ሁሉም በግል አብዶ ጆሮ በጠፋበት ምላስ ተርፎ ሲያደር ለካስ እብደት ማለት ያኔ ነው ግርግር። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_በዕውቀቱ ስዪም

Repost from N/a

#ካልዳሰስኩ_አላምንም ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ ያገር ልማድ ሆኗል እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ ፍቅር ስጋ ለብሶ በጁ ካላቀፈኝ ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ ኢምንት ነው ምንም ካልዳሰስኩ አላምንም @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_በዕውቀቱ ስዪም

#ፍቅር_የእውነት_ሲፈርድ የሳቅሽብኝ አልፎ መሳቅ መጀመሬ ሳፈቅርሽ ጠልተሽኝ ዛሬ መፈቀሬ ግዜ ዳኛ ሆኖ ፍቅር የእውነት ሲፈርድ ፈላጊው ሲፈለግ ተወዳጁም ሲወድ የህይወት አዙሪት በተራ መዟዟር የወደደው ጠልቶ የጠላው ሲያፈቅር ይኼ ነው ሚዛኑ በሰፈሩት ቁና ትላንት የገፋ ሰው ዛሬ ወድቋልና። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

🙌 አላችሁ? ናፈቃችሁኝ እኮ

የሰው ልጅ ታሪኩ ከውልደት እስከሞት በውል ተፈትሾ መጽሐፍ ቢጻፍለት ቁም ነገሩ ብቻ ተቆጥሮ ቢዳሰስ ከአንድ አንቀጽ አይዘልም ዘመኑ ቢጠቀስ በዋዛ ፈዛዛ ያሳለፈው ግዜ ይበልጣል ስፍረቱ ከኖረበት እድሜ የሰው ልጅ ህይወቱ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ወፍነት_አማረኝ ምነው ወፍ ባረገኝ በሰማይ በራሪ ከዛፍ ዛፍ መርጬ ነፃ ጎጆን ሰሪ! ሳልዘራ ሳላጭድ ሳልጨነቅ ነዋሪ በማለዳ ድባብ በፍቅር ዘማሪ ሰው ሆኜ ሰው ሆኖ መኖር ከከበደኝ እግዚአብሔር በቃሉ ምነው ወፍ ባረገኝ!!! በክፋት በተንኮል ሰው ሆኖ ከመኖር ወፍነት አማረኝ በነፃነት መብረር!!! @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

ሰው የሚሆን እንጅ የጠፋው ዘንድሮ ዘር የሚቆጥርማ ሞልቷል በየጓሮ እያደሩ ማነስ ሰው መሆን እረክሶ በስጋው ይመካል ለሚቀር በስብሶ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ብታመም_ነው_እንጂ!! የማይገኝ ነገር ያምረኛል ዘንድሮ ወተት ወተት አልኩኝ ገዛሁና ዶሮ በእኔ የደረሰው አይድረስባችሁ ዶሮ ገዝቶ ወተት ከቶ አያሰኛችሁ አወይ የእኔስ ነገር ለማን ይነገራል በቅሎ ስቶልድ ማየት አብዝቶ ያምረኛል ብታመም ነው እንጂ ብለከፍ ዘንድሮ እንዴት ሰው ይመኛል ወተትን ከዶሮ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Verified ሆኗል በደንብ ስሩት

#አበጀው_በያቸው አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ እኔ ያንቺ ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና የሚያንከራትተኝ ያው ፍቅርሽ ነውና ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

ጌታ መምጫኽ ዘመን ከመድረሱ በፊት ልቤን ልብ ስጠው መልሰው ከጥፋት ጴጥሮስን ከክህደት የመለሰው ዶሮ ለእኔም ላከውና ያንቃኝ ልቤን ሰብሮ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

#ነይ_አብረን_እንማ ባህል እንዲቀጥል በትውልድ ከተማ በፌስቡክ በቲክቶክ ነይ አብረን እንማ የጥንቱ ዘምኖ ከጀበና እርቆ ሀሜት ዲጂታል ነው ትውልዱ ተራቆ በቀጥታ ግቢ ከሀሜት ከተማ በተሻሻለው ህግ ነይ አብረን እንማ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

7 ቀን ብቻ ነው የቀረው የቻላችሁትን ሰብስቡ https://t.me/Gleam_AquaProtocol_Bot/app?startapp=cmM9ODdkNTk2OWU

ትማራለች ብዬ ሙያ ከጎረቢት አግብቻት ነበረ አድልቼ ለውበት እንኳንስ ልትማር የምታውቀው ጠፋት ሽንኩርት ግዛ አለችኝ ገንፎ ለማገንፋት። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Eyeserachut new?