ግጥም
Ir al canal en Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Mostrar más4 814
Suscriptores
+1324 horas
+617 días
+23730 días
Archivo de publicaciones
4 814
#እንዴውም_አትምጭ
ትመጫለሽ ብዬ ቁማር አሲዣለሁ
እንዳትቀሪ ፍቅሬ እረታብሻለሁ
በፍቅርሽ ቀለበት ተወራርጃለሁ
የቀረሽ እንደሆን ቃል ኪዳን አጣለሁ
ባትቆይም አንዴ ነይ
ዓይኖችሽን እንዳይ
ትመጫለሽ ብዬ ልቤን አሲዣለሁ
ጨክነሽ ከቀረሽ እጎዳብሻለሁ
አትቀርም ብዬ ተወራርጃለሁ
የቀረሽ እንደሆን ልብ አልባ እሆናለሁ
እንዴውም አትምጭ ልሸነፍ ልበላ
ሰው ልቡን ከሰጠ ምን ሊቀረው ሌላ
የምወድሽ ቢሆን ለፍቅር የታመንኩኝ
በውርርድ ሰበብ ባንቺ ባልቆመርኩኝ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
4 814
#ፍቅር_ሲደናበር
ባለርስቱ አባትሽ አልይህ ይሉኛል
ቅምጥል እናትሽ በአሽሙር ይልጡኛል
ወንድምሽ በዛቻ መቆም ከልክሎኛል
ደግሞ ያንቺ ፍቅር ሁሉን ቻል ይለኛል።
ፍቅር ታውሮ እንጂ ከአንቺ ላይ የጣለኝ
ከቤተሰብሽ ጋር ወስዶ ያላተመኝ
ጥንትስ ድህነቴ መቼ ዘነጋሁት
እኔን ተወት አርገው ፍቅርን ይክሰሱት።
ፍቅር ሲደናበር በውበት ታውሮ
ከጌታ ልጅ ጣለኝ ሰውነት አክብሮ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
የSpaceX አውቶማቲክ የቁጥር አሰራር ስርዓት ዝቅተኛውን የዲጂታል ምንዛሪ መሸጫ ዋጋ እንደ BTC፣ ETH፣ USDT፣ ወዘተ ባሉ ዋና ዋና ልውውጦች ላይ በመፈለግ በፍጥነት በሰከንዶች ውስጥ መግዛት ይችላል።
1. USDT በቁጥር ይገለጻል፣ እና የገንዘብ ማስቀመጫዎች እና ገንዘቦች ወዲያውኑ ይመጣሉ።
2. መጠናዊ VIP1-VIP10፣ መጠናዊ ገቢ 19%-40%
3. የመልቲ-ምንዛሪ ብልህ የኢንቨስትመንት ገቢ ከ15% -28%
4. መጠኗ በየ24 ሰዓቱ አንድ ጊዜ ይዘጋጃል፣ እና እያንዳንዱ ሰው በቀን አንድ ጊዜ በቁጥር ግብይት ትርፍ መሳተፍ ይችላል።
5. የቁጥር ግብይትን እና የሶስት-ደረጃ ወኪሎችን ያስተዋውቁ (የ13% ሽልማት ለኤ፣ 3% ሽልማት ለቢ፣ 2% ሽልማት ለ C = 18% ሽልማት)
የ24-ሰዓት ያልተቋረጠ መረጃ መሰብሰብ፣በእጅ የገበያ ሁኔታን አለመከታተል፣ ቀልጣፋ እና የተረጋጋ ትርፍ። ይህ የSpaceX xAI አውቶሜትድ የቁጥር ስርዓት ነው።
የቴሌግራም የደንበኞች አገልግሎት https://t.me/Spacex_XAI
SpaceX xAI ኦፊሴላዊ ድር ጣቢያ፡ https://sp-xai.com
የአባል ምዝገባ አገናኝ፡ https://sp-xai.com/#/register?i=876761
4 814
መልስና ጥያቄ ሳይተዋወቁ
ከኢትዮጵያ ጋራ እንደተራራቁ
በአሽሙር በብሽሽቅ ዓመታት አለቁ
ዜጎች መልስን አጥተው እየተጨነቁ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
4 814
#ህይወቴ
ፍቅሬ ፍቅሬ እያልኩ ልጥራሽ
የመኖሬ ትርጉም ህይወቴ ነሽ
የልቤ ትርታ የነፍሴ ዕፎይታ
የእኔነቴ ምስጢር የአምላኬ ስጦታ
እንዲህ እንዲያ እያልኩ ብጠራሽ
እንዴት ሆኖ እንዴትስ ይመጥንሽ
ፍቅሬ ፍቅሬ እያልኩ ልጥራሽ
ሆሄያት ቢደረደሩ ቃላቶች ቢጣመሩ
ከቶ እንዴት ይቻሉ እንዴትስ ይድፈሩ
ቃላቶች ያልቻሉ ሆሄያት ያልሰየሙሽ
ታዲያ ምን ነሽ አንቺ አንደበት ማይገልፅሽ
ደከምኩልሽ ሆዴ ቃላቶች አጣሁኝ
በቃ በቃ !! ህይወቴ ነሽ አልኩኝ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
የጋበዝሽኝ ዘፈን በደብዳቤ ጠቅሰሽ
አደመጥኩት ያልኩሽ መልሼ ጽፌልሽ
ውዴ ውሸቴን ነው ቴፑ ተበላሽቷል
የመረጥሽው ዘፈን ተነክሶ ተበልቷል ።
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
4 814
....... ✍ #ፃፍኩልሽ 💌 .......
አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል
አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
ዛሬ ግን.....
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
አሞኛል አሞኛል መድኃኒቱን እንጃ
እፎይ!! አበዛለሁ ለስንዝር እርምጃ !!!
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
#ልሂድልሽ_በቃ
እንድንኖር እንጅ በፍቅር በደስታ
አጭሯ ዕድሜያችን በተስፋ ተሞልታ
ባንች ተደስቼ በእኔ ተፍለቅልቀሽ
ዕንባሽን አብሼ ሀዘኔን አርቀሽ
ግና……
አስተውሎ ኑሮ አልሆንልሽ ካለሽ
ነገ ከራቀብሽ ዛሬ ካታለለሽ
ልሂድልሽ በቃ አንችም ካሻሽ ድረሽ
ለማይፀና ፍቅር ተቃቅፈን እንዳይመሽ
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
ከመቃብር በላይ ዘላለም ለመኖር
በጎ ተግባር ከውን በሰብዐዊ ፍቅር
ስምህ እንዲነሳ መቃብርን ፈንቅሎ
በህይወት እያለህ መብላት ነው ተካፍሎ።
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
#ሁላችን_ከንቱ_ነን!
የልብ አማኝ ጠፍቶ የአፍ አማኝ ከበዛ
በእውነት አመንጭቶ ፍቅርን ካልገዛ
መማር ከየት ይምጣ ልብ ተቆልፎ
የሰው ልጅ ካልጣለ ማስመሰልን ገፎ
ባንደበቱ ጌታን በልቡ ገንዘብን
አፉ አሜን እያለ በውስጡ ተንኮልን
ምላስ አምላክ ጠርቶ
ልብን ገንዘብ ሞልቶ
የስም ፃድቅ ሰፍቶ
በነብይ ተሞልቶ
ምህረት ከየት ይምጣ
እንዴት ይብረድ ቁጣ!
ጠዋት ክርስቶስን
ከሰአት ሰይጣንን
በግፍ ተሸፍኖ ልባችን በቀልን
የተንኮል አሽክላ አስልተን እየጣልን
ማረን እንላለን እንዴትስ ይማረን
በሁለት ቢለዋ አስብተን እያረድን
ዳዊት ከደገመ ጠዋት ምላሳችን
ማታ ላይ ስድብን ለምዶ አንደበታችን
ሊምረን ቢመጣ ቁጣውን ሊያበርደው
ምላስ ብቻ ቀርቷል ለካስ ልብ ባዶ ነው
በሐይማኖት ጥላ ተሸሽገን ከርመን
እምነት ግን ሲጠየቅ ሁላችን ከንቱ ነን
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
ሪሞት ቢኖረው ግዜ የእጅ ስራ
ማሳለፍ መመለስ በተራ በተራ
ደጉን ወደሗላ ክፉውን ወደፊት
መቆጣጠር ነበር ፊልም ብትሆን ህይወት ።
✈️ @gitm_post ✈️
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 814
#በጣም_ታምሪ_ነበር
ሠው ሰራሹ መልክሽ አፍጥጦ ባይውጣ
በጅንስ ታፍኖ ዳሌሽ ባይቀጣ
ጡትሽ ቤቱ ቢኖር ልታይ ባያበዛ
ፀጉርሽ ያንቺው ቢሆን ከሱቅ ባይገዛ
ጊዜ ባይቀይርሽ በቃልሽ ብታድሪ
ህሊናሽ ቢገዛሽ በሥጋሽ ባትኮሪ
የሴትነት ክብሩ ቢገባሽ በልኩ
ሲጠሩሽ ባ'ሮጭ በርሽን ሲያኳኩ
አስተዋይ ብትሆኝ ምግባርሽ ቢከበር
ሔዋን ሙች ልንገርሽ በጣም ታምሪ ነበር።
🚀@gitm_post 🚀
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
