uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Amhara Revolution

Amhara Revolution

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህቺ ገፅ 17/04/2016 ተከፈተች። መረጃ ያድርሱን @heyab8 ✅የተመሠረተችው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራን ሕዝብ ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትሰራለች። ድል ለአፋብን💪

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Amhara Revolution analitikasi

Amhara Revolution (@minilik28) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 600 obunachidan iborat bo'lib, Siyosat toifasida 3 734-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 447-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 600 obunachiga ega bo‘ldi.

30 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 451 ga, so‘nggi 24 soatda esa 5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 16.75% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 13.83% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 2 443 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 017 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 15 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“ይህቺ ገፅ 17/04/2016 ተከፈተች። መረጃ ያድርሱን @heyab8 ✅የተመሠረተችው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራን ሕዝብ ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትሰራለች። ድል ለአፋብን💪”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 31 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Siyosat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

14 600
Obunachilar
+524 soatlar
+1047 kun
+45130 kun
Postlar arxiv
ትብብር ለህልውና ታሪካው ጥሪ አስተላለፈ ሙሉውን የማዬት ሊንኩን ይጫኑ። 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/dbj-BOmy6eZjNDE0
ትብብር ለህልውና ታሪካው ጥሪ አስተላለፈ ሙሉውን የማዬት ሊንኩን ይጫኑ። 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/dbj-BOmy6eZjNDE0

ዜና ምሽት!! በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል በ74ኛ ክ/ጦር ሶማ ሻለቃ በተፈፀመበት የተቀናጀ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል። ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ መድፍ እና ዙ-23 በመጠቀም ጥቃት ለማድረስ የተንቀሳቀሰው የ6ኛ ዕዝ ሰራዊት በ74ኛ ክ/ጦር ሶማ ሻለቃ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የገጠመው ሲሆን መነሻውን ደብረወርቅ ከተማ ያደረገው ጠላት በወፍና አብራጂት፣ ደብረወርቅ ሆስፒታል ፣ ሳፈቅዳ እና መጠያ አካባቢ በተወሰደበት የውጊያ የበላይነት አስክሬኑን ተሸክሞ ወደ መጣበት ተመልሷል። ሰፊ ቀጠና የሸፈነው የሶማ ሻለቃ ተጋድሎ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የጠላትን ወታደራዊ እቅድ በመመከት ድል መመዝገቡ ታውቋል። የጠላት ቀላልና ከባድ ቁስለኛም ደብረወርቅ ሆስፒታል እንደተወሰዱም ተረጋግጧል። በተመሳሳይ በእነማይ ወረዳ ለምጨን፣ ሰቀላና ዲማ የተንቀሳቀሰው ጠላት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ እንደቀጠለ ሲሆን 64ኛ ክ/ጦር በፈፀመው ጀብዱ፦ 1. ፊልማታ አብዱ 2. ሀብታሙ በየነ 3. ሙባረክ ሀጅ ይማም 4. አስማመው 5. ደረጀ ተስፋየ 6. ጫላ አደም 7. ኡመር ሙሀመድ 8. ገመቹ ሚሊከሳ 9. ግብርሀም እንዳሌ የተባሉ ከባድ ቁስለኞች በቢቸና ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በድንገተኛ ክፍል ህይወታቸው ያለፈ ቁስለኞች ሲኖሩ ወደ ጦርሃይሎች የተላኩ ከባድ ቁስለኞች መኖራቸውም ተረጋግጧል። ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

photo content

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና ምክር ቤት ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ከጥቅምት 20 እስከ 21/ 2019 ዓ.ም አካሂዷል። ምክር ቤቱ የትብብሩ መመስረት በይፋ ከታወጀ በኋላ ባካሄደው በዚህ የመጀመርያ ስብሰባ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ የኃይል አሰላለፍ ሁኔታዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የትብብሩን የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ያፀደቀ ሲሆን በሌሎች ልዩ ልዩ አጀንዳዎችም ላይ ተወያይቷል። በምክር ቤቱ ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በአምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ ስር የወደቀች፣ የዜጎች መፈናቀል እንዲሁም የከፋ ድህነትን መገለጫዋ ያደረገች ሀገር ሆናለች። በትግራይ፣ በአማራ፤ በኦሮሚያ እና  በሌሎች ሕዝቦች ላይ በይፋ ባወጀው ጦርነት ምክንያት ዜጎች እንደሰው የመኖር ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው የተገፈፈ እንዲሁም እንደሕዝብ የመኖር ሕልውናቸው አደጋ ውስጥ የወደቀ ሆኗል። በተጨማሪም በሕዝቦች መሃል የእርስ በርስ ግጭቶችን በመፍጠር በሞያሌ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ፣ በሱማሊ፣ በአፋር፣ በሲዳማና በሌሎች አከባቢዎች እንደታየው ሞት፣ እልቂትና ከፍተኛ ውድመትን በመፍጠር ዘረ-ፈጁ አገዛዝ የሕዝቦች የህልውናና የደህንነት ጠንቅ ሆኖ ቀጥሏል። አገዛዙ ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን እየበላ ያለውን ጦርነት የመግታት፣ ዘላቂ ሰላም የማምጣት፣ የዜጎችን ፍላጎት  የማድመጥና የማረጋገጥ፣ ሕግና ሥርዓትን የማስፈን፣ ድህነትንና ኋላቀርነትን እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ችግሮችን የመፍታት ባህሪ፣ አቅምና ፍላጎት ስለሌለው ውስጣዊ ችግሮችን ለመደበቅ በአይዞህ ባዮቹና በላኪዎቹ ፍላጎት መሰረት በሀገር ውስጥ የቀሰቀሳቸውን ጦርነቶች በማስፋት ቀጠናዊ ጦርነት ለማድረግ የጎረቤት ሀገራትን መውጋትና መተንኮስን ተያይዞታል። ይህም የሀገሪቱንና የሕዝቦቿን ሕልውና ከድጡ ወደማጡ የሚከት፣ የቀጠናውን ሀገራት ሰላምና እድገት የሚያውክ፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ ነው። የትብብሩ ምክር ቤት ሰፊና ጥልቅ ወቅታዊ ግምገማ ካካሄደ በኋላ የሚከተሉትን መሰረታዊ መርሆዎችን አጽንቷል። 1. የብልጽግና አገዛዝ ለሕዝቦች ሰላምና ደህንነት፣ ማሕበራዊ ውልና ባህላዊ መሰረት፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በፍጹም ግድ የሌለው የሀገርንና የሕዝቦችን ሕልውና አደጋ ውስጥ በመክተት የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም የሚፈልግ አገዛዝ ነው። ስለሆነም በስልጣን ላይ ያለው አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ጠላት ነው። 2. የትብብር ለህልውና መሰረታዊ ዓላማ የብልጽግናን አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ ከስልጣን በማስወገድ ላይ የተገደበ ትብብር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝቦች ህልውና ለማረጋገጥ የተመሰረተ ስትራተጂካዊ ትብብር ነው። ትብብር ለህልውና ኢትዮጵያን ለዘመናት ተብትቦ የያዛትን የጦርነት አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስበር የሕዝቦችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ምዕራፍ መክፈት ጽኑ አቋሙ ነው። ይህ ታሪካዊ ተልዕኮም በትብብር ለህልውና ብቻ የሚፈጸም እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በሽግግሩ ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራትና የልዩ ልዩ ሕዝባዊ ተቋማት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ንቁና ቀጥተኛ ተሳትፎ መተኪያ የሌለውና ወሳኝ ጉዳያችን መሆኑን እናረጋግጣለን። 3. የአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ ልማትና ትብብር የኢትዮጵያ የመጪው ዘመን የፖለቲካ፣ የማህበረ-ኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ምሰሶዎችን የሚያጠናክር መሆኑን ትብብር ለህልውና ያምናል። ይህንን ወሳኝ ጉዳይ ተግባራዊ ለማድረግ ትብብሩ በቀጠናችን ሕዝቦችና ሀገራት መካከል የኖረውን የጋራ መግባባትንና አብሮነትን ለማስፈንና ወዳጅነትን ለማጠናከር ካለመታከት ይሰራል። የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በግልፅ በመረዳት፣ ባስቀመጣቸው መርሆች በመመራትና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የትብብሩ ምክር ቤት የሚከተለውን የመካከለኛ ጊዜ የተግባራት ዕቅድ አጽድቋል።  1. ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕልውና የሚያካሄደውን ዘርፈ-ብዙ ትግል ማጠናከር፤ 2. በሀገር ውስጥና በዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚካሄደውን ህዝባዊና ዲፕሎማሲያዊ ትግል ማበረታታትና ማቀናጀት፤ 3. የትብብር ለህልውና አባል ድርጅቶችን አቅም ማጠናከርና በአገዛዙ ላይ ውጤታማና ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ፤ 4. የትብብሩን ዓላማና ግብ ለማሳካት ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማሕበራትና ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ተቋማት እንዲሁም ከትብብሩ ዓላማ ጋር ከቆሙ ምሁራንና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ተሰሚነት ካላቸው እውቅ ግለሰቦች ጋር በቅርበት መስራት፤ 5. ከአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦችና መንግስታት ጋር ወዳጅነትና ትብብርን ማጠናከር፤ 6. የዲፕሎማሲና የሚድያ ሥራዎችን ማጠናከር፤ ከዘህ በመነሳት የትብብር ለሕልውና ምክር ቤት የሚከተሉት ጥሪዎች ያስተላልፋል፤ ለመላው ህዝቦቻችን የብልጽግና አምባገነናዊ ዘረ ፈጅ-አገዛዝ ዋና ዓላማ ተፈጥሯዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችህን በመቀማት፣ ሕልውናህን አደጋ ውስጥ በመክተት፣ የሀገርንና የህዝብን ጥቅም በመሸጥ በስልጣን የመቆየትና የላኪዎቹን ፍላጎት ማሳካት ነው። ስለሆነም ከህዝባዊ ኃይሎች ጋር በመሆን እያደረግክ ያለኸውን ትግል አጠናክረህ እንድትቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለመላው የትብብር ለሕልውና አባል ድርጅቶች የህዝቦቻችንን የሕልውና አደጋ የመቀልበስ፣ በኢትዮጵያውያን መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የሽግግር ምዕራፍ የመከፈት፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ሥራዎች የሚወሰኑት ሰራዊታችን በሚከፍለው የማይተካ መስዋዕትነት ነው። በመሆኑም የየድርጅቶቻችን ሰራዊት እርስ በርስ በመተሳሰር በጋራና በአንድነት የጠላትን አከርካሪ በመስበር የአገሪቱንና የህዝቦችዋን ሕልውናና ሰላም ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተግተንና ተናበን በመሥራት ታሪካዊ ኃላፊነታችንን በተግባር እንደምንወጣና የድል ባለቤቶች እንደምንሆን እናረጋግጣለን። ለቀጠናውና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ መላው የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብ የብልፅግና አምባገነናዊ ዘረ ፈጅ አገዛዝ በቀጠናው ጦር ሰባቂና ግጭት ጠማቂ በመሆን በሀገሪቱ ህዝቦችም ሆነ በአከባቢው አገራት የሕልውናና የሰላም ደህንነት ጠንቅ በመሆን እየተጫወተ ላለው አፍራሽ ሚና በተገቢው መንገድ በመረዳትና ከትብብር ለሕልውና ኃይሎች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ለማድረግ እንዲሰራ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን።    የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሃይሎች ትብብር ለህልውና (ትብብር ለህልውና) ምክር ቤት ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ኢትዮጵያ

photo content
+4

ፈጣሪ ይቆጣኛል እንጅ እምለዉ ብዙ ነገር ነበር😁😷

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ነበልባሉ ፎገራ 23ኛ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ዙር ኮማንዶዎችን በታላቅ ድምቀት አስመረቀ ​ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ​አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ፣ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ነበልባሉ ፎገራ 23ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ ወራት ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ሁለተኛ ዙር ኮማንዶዎች በድምቀት አስመርቋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የድርጅት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የዕዝ፣ የኮር እና ሌሎች የተቋም አመራሮች ተገኝተዋል። ​ኮማንዶ ምሩቆቹ በቆይታቸው ጠንካራ የአካል ብቃት፣ ዘመናዊ የሽምቅ ውጊያ ክህሎቶች እና ጥልቅ የፖለቲካ ትምህርቶችን በጽናት የተከታተሉ ሲሆን ፤ ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በብቃት በመቋቋም የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ዳር ለማድረስ በከፍተኛ ስሜትና ፍቅር ተቀላቅለዋል ። ይህ ስልጠና ድርጅታችን አፋብን እና ተቋማችን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ በዕቅድ የያዙት ዘመናዊ ጦር የመገንባት ስትራቴጂካዊ ግብ አካል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ትልቁ እና ቁልፍ ተግባር መሆኑን ተገልጿል። ​በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተመራቂዎቹ በወታደራዊ ሥልጠናና በዲሲፕሊን ታንጸው ህዝባቸው የሚገባውን ክብርና ነጻነት እስከሚያጎናጽፉ ድረስ በቁርጠኝነት እና በጽናት ለመታገል በትግሉ ሰማዕታት ስም ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም  ለሰማዕታት ክብር በሰጠ ስነ-ሰርዓት ተጀምሮ፣ በድምቀት በተከናወኑ ወታደራዊ ሰልፎች፣ የውጊያ ትርኢቶች፣ እንዲሁም የዕውቅና ሽልማቶችና ምስጋናዎች ተካተውበት ፕሮግራሙ በደመቀ ስነ ስርዓት ተጠናቋል ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

photo content
+2

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ነበልባሉ ፎገራ 23ኛ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ዙር ኮማንዶዎችን በታላቅ ድምቀት አስመረቀ ​ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ​አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ፣ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ነበልባሉ ፎገራ 23ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ ወራት ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ሁለተኛ ዙር ኮማንዶዎች በድምቀት አስመርቋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የድርጅት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የዕዝ፣ የኮር እና ሌሎች የተቋም አመራሮች ተገኝተዋል። ​ኮማንዶ ምሩቆቹ በቆይታቸው ጠንካራ የአካል ብቃት፣ ዘመናዊ የሽምቅ ውጊያ ክህሎቶች እና ጥልቅ የፖለቲካ ትምህርቶችን በጽናት የተከታተሉ ሲሆን ፤ ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በብቃት በመቋቋም የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ዳር ለማድረስ በከፍተኛ ስሜትና ፍቅር ተቀላቅለዋል ። ይህ ስልጠና ድርጅታችን አፋብን እና ተቋማችን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ በዕቅድ የያዙት ዘመናዊ ጦር የመገንባት ስትራቴጂካዊ ግብ አካል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ትልቁ እና ቁልፍ ተግባር መሆኑን ተገልጿል። ​በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተመራቂዎቹ በወታደራዊ ሥልጠናና በዲሲፕሊን ታንጸው ህዝባቸው የሚገባውን ክብርና ነጻነት እስከሚያጎናጽፉ ድረስ በቁርጠኝነት እና በጽናት ለመታገል በትግሉ ሰማዕታት ስም ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም ለሰማዕታት ክብር በሰጠ ስነ-ሰርዓት ተጀምሮ፣ በድምቀት በተከናወኑ ወታደራዊ ሰልፎች፣ የውጊያ ትርኢቶች፣ እንዲሁም የዕውቅና ሽልማቶችና ምስጋናዎች ተካተውበት ፕሮግራሙ በደመቀ ስነ ስርዓት ተጠናቋል ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ሰበር የድል ዜና ዲማ ጊዮርጊስ ‼️ 64ኛ ክ/ጦር ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ~~~~~~~ ድርጅቱ አፋብን በምስራቅ ግንባር ደቡብ ወሎ የሰጠውን ግዳጅ በብቃት የተወጠው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ወረራ ለመፈፀም እና ለማውደም የመጠው ዘራፊ እና አውዳሚው የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ አድርጓል። ከአገዛዙ ብልፅግና አጀንዳ የተቀበሉት ኮሎኔል አለምሰገድ እና ነጋሲ ከደ/ማርቆስ እስከ ሞጣ የሚገኘው 6ኛ ዕዝ የሚገኙ ክ/ጦሮች በማንቀሳቀስ የታላቁ ዲማ ጊዮረጊስ ገዳምን ለመዝርፍና ለማውደም መካናይዝድ፣ 2 መድፍ፣ 107 BM፣ 2 ዙ 23፣ 3 ዲሽቃና በርካታ የእግርኛ ሰራዊት በመያዝ በዲማና አካቢው ወረራ ለመፈፀም ጨለማን ተገን አድርገው እንቅስቃሴ ያደርጉ ቢሆንም ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አናብስቶች በአደረጉት ውጊያ የአገዛዙ ሻለቃ መሪ ከእነ አጃቢዎቹ እና በርካታ የሰራዊት አባላት ሲደመሰሱ በርካቶች ቁስለኛ ሆነዋል። አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር በታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ በአደርገው አውደ ውጊያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ ሬዲዎ መገናኛ፣ ስናይፐር ክሻፋ፣ የደረት ትጥቅ፣ ከዘና ከእነ ተተኳሹ አና አገዛዙ ይጠቀምባቸው የነበሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ገቢ በማድርግ በዲማ ጊዮርጊስ ታላቅ ጀብድ ሰርቷል። በአውደ ውጊያው:- ✍️7 ክላሽ መሳሪያ የተማርከ ✍️1 የስናይፐር ክሻፋ የተማርከ ✍️4 ካዘና የተማረከ ✍️1 የሬድዎ መገናኛ የተማርከ ✍️ የሻለቃ መሪው ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ተደምስሰዋል። ለግዜው በቁጥር ማወቅ ያልቻልናቸው የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ቁስለኛ ሆነዋል። ድል ለአማራ ህዝብ!! ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአማራ ህዝብ ህልውና ተጋሃድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!ለአማራ ህዝብ!! ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 20ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

ሰበር!...በ32ኛ ክ/ጦር የ4ኛ ሬጅመንት አዛዥን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ተደመሰሱ! ዛሬ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም እለተ ቅዳሜ ዲማ ጊዮርጊስ ወረራ ለመፈፀም ተንቀሳቅሶ የነበረው የ6ኛ ዕዝ ሰራዊት በ64ኛ ክ/ጦር ተደመሰሰ። በሁሉት መድፍ፣ BM ፣ ሁለት ዙ-23 ፣ሶስት ሞርተር ድጋፍ እየተሰጠው ከደብረ ማርቆስ እስከ ሞጣ ተውጣጦ በእነማይ ወረዳ ዲማ ጊዮርጊስ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል በ64ኛ ክ/ጦር ተደመስሷል። ከደብረ ማርቆስ አካባቢ መነሻዋን ያደረገችው የ602ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦር በነበረው ትንቅንቅ ወታደራዊ አመራሩን ጨምሮ በርካታ ሠራዊት እንደቅጠል መርገፉ ተረጋግጧል። የወገን ኃይል ውጊያውን በበላይነት የተወጣ ሲሆን 7 ክላሽ መገናኛ ሬዲዮ እና በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች በመማረክ ድል ማስመዝገቡ ተገልጿል። የኮሎኔሎ አለምሰገድ 32ኛ ክ/ጦር 4ኛ ሬጅመንት አዛዥ በውጊያው መካከል የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞች ወደ ቢቸና መወሰዳቸው ተረጋግጧል።

photo content
+3

ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በዋሮ ከተማ ከአባት አርበኞችና ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት አደረገ! ​ በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ በዋሮ ከተማ ከአባት አርበኞችና ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ። ​በውይይቱ መድረክ ላይ የአሁናዊ የሀገሪቱ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም የፋኖ ትግል የደረሰበት የዕድገት ደረጃ በሰፊው ተዳሷል። በተጨማሪም የአማራ ፋኖ ጊዜያዊ መንግስት የሲቪል አስተዳደር ሕግ እና ሥርዓት ሁኔታዎች ለተሳታፊዎች በዝርዝር ተብራርተዋል። ​በመድረኩ የተገኙ የከተማዋ ነዋሪዎችና አባት አርበኞች በሰጡት አስተያየት፤ የፋኖን አጠቃላይ የትግል አውድና ዓላማ በጥልቀት መረዳታቸውን እና ከፋኖ ጋር በመሆን ይህን አንባገነን ስርዓት ከስሩ ለመንቀል እንታገላለን ብለዋል። ከዚህም ባለፈ በሀገሪቱ የሚገኙ የታጣቂ ኃይሎች ትብብርና አብሮነት ሀገርን ከህልውና አደጋ ለመታደግ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ! ጥቅምት፦ 21/ 2019 ዓ/ም

photo content
+3

አስቸኳይ መረጃ‼ 🥷🥷🥷 ደብረታቦር በ አሁኑ ሰዓት ማለትም 6:30 ጀምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ አፈሳ ስላለ ወጣቶች እንድትጠነቀቁ እናሳስባለን!🥷🥷🥷

ከሠም ፪ኛ ኮር የተሃድሶ መርሃ ግብር ማከናወኑ እና አዲስ ክፍለ ጦር መደራጀቱን በከሠም የዕዙ ስምሪት ቡድን ገለፀ!!        ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሥር የሚገኘው ከሠም ፪ኛ ኮር ከአመራር እስከ ሠራዊቱ አባላት ድረስ ሙሉ የተሃድሶ እና የሪፎርም መርሃ ግብር ማጠናቀቁን እና አንድ አዲስ ክፍለ ጦር አደራጅቶ ለተጨማሪ ግዳጅ መዘጋጀቱን በከሠም፡ የዕዙ ስምሪት ቡድን አካላት አስታወቀ።  ከሠም ፪ኛ ኮር ቀደም ሲል በአራት ክፍለ ጦሮች ተዋቅሮ ሰፊ ቀጠናን በመሸፈን እና ግዙፍ ሠራዊትን በማስተባበር የሚታወቅ ታላቅ ኃይል ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ካለው የሰው ኃይል ብዛትና ከፍ ያለ የወታደራዊ ብቃት አንፃር አቅሙን በማሳደግ ክፍለ ጦሩን ከአራት ወደ አምስት ከፍ አድርጎ አደራጅቷል። ይህ እርምጃ የኮሩን የቀጣይ ግዳጅ እና ቀጠናዊ ሽፋንን ይበልጥ ለማስፋት ታስቦ የተወሰደ ግዙፍ ድርጅታዊ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል።   በዚህ መሠረት ከሠም ፪ኛ ኮር አሁን ላይ የሚከተሉትን አምስት ክፍለ ጦሮች ማለትም፡ ነበልባል ክፍለ ጦር፣ ቡልጋ ክፍለ ጦር፣ ኃ/ማሞ ክፍለ ጦር፣ አክሊሉ ኃ/ወልድ ክፍለ ጦርና አስማረ ዳኜ ክፍለ ጦርን አቀናጅቶ ተዋቅሯል። ይህ ግዙፍ ኮር ከእግረኛ እስከ መካናይዝድ ጦር ድረስ የጠላትን ኃይል በመፋለም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠላትን ከጥቅም ውጪ በማድረግ እንዲሁም የጠላትን ኃይል ከአባል እስከ ከፍተኛ አመራሮችን በመማረክና በማስከዳት እጅግ ድንቅና ታሪካዊ ጀብዶችን በመፈጸም ይታወቃል።   ኮሩ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በዕዙ የስምሪት ቡድን አካላት አማካኝነት ጥልቅ የሆነ ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ካሁን በፊት ያጋጠሙትን የአሠራር ክፍተቶችና የአመራር ድክመቶችን በመፈተሽ፣ አስፈላጊ የሆኑ የአመራር ሪፎርሞችን በማከናወን እና የተጣለበትን ሕዝባዊ ግዴታና ድርጅታዊ ኃላፊነት በላቀ ሁኔታ ለመወጣት ራሱን አዘጋጅቷል።   በመጨረሻም፣ የግምገማና የሪፎርም መርሃ ግብሩ ሲጠናቀቅ የአመራር መተካካትን በማድረግ እና የአዲሱን ክፍለ ጦር አመራሮች በመሠየም አጠቃላይ የኮርና የክፍለ ጦር አመራሮችን በስልጠና በማብቃት እና ለተሰየሙት አዲስ አመራሮችም የተጣለባቸውን ሕዝባዊ አደራ በኃላፊነት፣ በታማኝነትና በቅንነት እዲወጡ ቃለ መሀላ በመፈፀም የተሃድሶ መርሃ ግብሩ በድምቀት ተጠናቋል።   " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

photo content
+6

አስቸኳይ መረጃ‼ inbox ባህርዳር በርካታ የሬሽን መኪና በአንድ ዙ 23 ታጅበው ወደ ጎንደር ወጠዋል የሰው ሀይል የላቸውም ተቀባይ ከሌላቸው እየመጡ ነው