fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Amhara Revolution

Amhara Revolution

رفتن به کانال در Telegram

ይህቺ ገፅ 17/04/2016 ተከፈተች። መረጃ ያድርሱን @heyab8 ✅የተመሠረተችው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራን ሕዝብ ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትሰራለች። ድል ለአፋብን💪

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Amhara Revolution

کانال Amhara Revolution (@minilik28) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 14 585 مشترک است و جایگاه 3 744 را در دسته سیاست و رتبه 2 454 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 14 585 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 28 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 463 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -7 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 17.71% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 14.33% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 2 574 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 082 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 17 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“ይህቺ ገፅ 17/04/2016 ተከፈተች። መረጃ ያድርሱን @heyab8 ✅የተመሠረተችው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራን ሕዝብ ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትሰራለች። ድል ለአፋብን💪”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 29 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته سیاست تبدیل کرده‌اند.

14 585
مشترکین
-724 ساعت
+387 روز
+46330 روز
آرشیو پست ها
ምስራቅ ግንባር ምኒልክ ዕዝ አመረቂ ውጤት አስመዘገበ ዝርዝሩን ለማዬት ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/XmQk0y7Ay-czNTZk
ምስራቅ ግንባር ምኒልክ ዕዝ አመረቂ ውጤት አስመዘገበ ዝርዝሩን ለማዬት ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/XmQk0y7Ay-czNTZk

መሰደድ ብቻውን አይበቃም መራብ መጠማትም ቢሆን አይፈቀድም ላስቲክ ለብሶ ድንጋይ ተንተርሶ ማደርም ከእሳት አያተርፍም ጊዜ ይገለባበጣል ያ ቀን ይመጣል! እስከዛው ከአይዞን ሌላ የተሻለ ቃል የለም አይዞን💔

ቀን 19/02/2019 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር የተሰጠጠ መግለጫ ~~''~~~~ እንደሚታወቀው የአሸባሪው አብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን
+2
ቀን  19/02/2019 ዓ.ም      ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር  የተሰጠጠ መግለጫ   ~~''~~~~      እንደሚታወቀው የአሸባሪው አብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ጅምላ ጭፍጨፋ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል ከዚህም አልፎ አማራ በሄደበት ሁሉ እንደ ጠላት ተቆጥሮ በአቀናት ሀገር ላይ መኖር አትችልም ተብሎ በየጊዜው ይፈናቀላል ይገደላል። በዚያም የአማራ ፈኖን ምት መቋቋም ያልቻለው ገዳይ ስረዓት አማራን በኢኮኖሚ ለማድቀቅ ያመቸው ዘንድ የከተማ ቦታዎችን በመሸጥ ላይ ይገኛል ።   ስሞኑንሞ  በተለያዩ የክልላችን ከተሞች ለአብነትም በአዋባል ወረዳ ወጀል  ከተማ ላይ የብልፅግና ቅለብ ካድሬዎች የሊዝ ቦታ እንሸጣለን በሚል ሰበብ ከባለሀብቶች እና የከተማው ነዋሪዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ  ማስታወቂያ በመለጠፍ ለማጫረት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ስለዚህ 1ኛ, ማንኛውሞ ግለሰብ በዚህ ጊዜ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር እንጅ ቤት የምንሰራበት የገንዘብ መጠን የምናሳድግበት ጊዜ ስላልሆነ ፋኖ ከተደራጀበት ከሃምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመደራጀት እና የባንዳን ቤትና መሬት መግዛት ከህግ አግባብ ዉጭ መሆኑን እንዲያውቅና አማራን እየጨፈጭፈ ላለው ስርዓት ተባባሪ መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ ድርጊቱ እንደታቀብ እናሳስባለን። 2ኛ, ይህን አማራ ጠል ስርዓት ተባብሮ መጣል ሲገባ የሊዝ ቦታ የሚገዛ ማንኛው ተቋምም ሆነ ግለሰብ የገዛው ቦታ እንደሚወረስና እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንዳዉቅና ከድርጊቱ እንድታቀብ። ይህን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ግለስብ ሆነ ተቋም  የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

አፋብን በላይ ዘለቀ ፫ኛ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ (፩ኛ) ኮር ጉና ክፍለ ጦር አንዳቤት ብርጌድ ለተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸው የጤና መኮንኖችን አስመረቀ [ጥቅምት 19/02/2018/ዓ.ም] በክፍለ ጦሩ የመጀመሪያ የሆኑትን በጤና ትምህርት ስልጠና እንዲሁም በመጀመሪያ የህክምና ርዕዳታ ልምድ ባከማቹ የህክምና ባለሙያዎች አስተባባሪነት ላለፉት ወራት ሲሰጥ የቆየው የአጭር ጊዜ ስልጠና በሰላም መጠናቀቁን የስልጠናው አስተባባሪ ፋኖ ፲/አ ጌታሰው አዳነ ተናግረዋል። ሥልጠናው የአጭር ጊዜ ሂደትም ቢሆን ከዚህ በፊት ሲያጋጣሙ የነበሩትን ህፀፆች በተቻለ መጠን ማስተካከል ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም የአፋብን ምክትል ሰልጠና መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ሙላቴ ሲሳይ፣ የአፋብን ምክትል ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን፣ የሜ/ጀ/ውባንተ ፩ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ አበበ ሞገስ፣ የኮሩ ምክትል ዘመቻ መሪ ወጣቱ ፋኖ ሃብታሙ አጠቃ፣ የጉና ክፍለ ጦር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ወንዱአንተ አሰፋ፣ ሌሎች በየደረጃው ያሉ የፋኖ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ለተመራቂ የጤና መኮንኖች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፤ የፋኖ ተጋድሎ እንዲሁም ትብብር ለህልውና አሁናዊ የደረሰበትን ደረጃ አጫጭር መልክቶች ማስተላልፍ ተችለዋል። በመጨረሻም ለተመራቂ የጤና መኮንኖች የዕውቅና የምስክር ወረቀቶችን አበርክቶ በመስጠት በቀጣይ ለነባርና ለአዳዲስ የጤና መኮንኖች ከማብቃት ባሻገር ተተኪ ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በመርሃ-ግብሩ ተመላክቷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ አፋብን በላይ ዘለቀ ፫ኛ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ (፩ኛ) ኮር ጉና ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፋው

photo content
+6

ሰበር በቀጥታ ከትግራይ ግምባር ‼️ TDF በተለያዩ ግምባሮች ከባድ የተባሉ ውጊያዎችን ማድረጉን አስታውቋል። በሰየምት አድያቦ በቲዲኤፍ በተከፈተ ጥቃት የብልፅግና ሠራዊት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ ተገለጸ። የአገዛዙ ጦር በትግራይ ሀይሎች በተከፈተበት ውጊያ በርካታ ወታደሮቹ የተደመሰሱ ሲሆን ቀላል የማይባል የሜካናይዝድ ንብረቶቹ ወድመዋል ተብሏል። TDF የአገዛዙን ሰራዊት ልክ በምስጥ እየተበላ እንዳለ እንጨት ቦርቡሮ ሊጨርሰው ነው ሲሉም ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል። TDF ዋና የማእበል የመልሶ ማጥቃት ያለውን ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት አሁን በየአቅጣጫው እያደረገው ባለው ውጊያ በርካታ ድሎችን እያገኘ ሲሆን የብልፅግና ጦር ከወዲሁ መሰላቸቱም እየተነገረ ነው። በዚህ ግምባር ያለቀው የወታደር ብዛት ቁጥሩ ለ300 የሚጠጋ መሆኑን የገለፁት ምንጮች ከባድ መሳሪያዎቹም በእሳት መንደዳቸው ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ህውሃት ባንዳ ብሎ በጠራቸው እንደ ጀነራል ጆን መዲድ ባሉ በባንዳዎች ጥቆማ ጀነራል ድንኩልን እደመስሳለሁ ብሎ ለ2 ቀን ከባድ ውጊያ ሲያደርግ የነበረ የብልፅግና ጦር በማእከላዊ ትግራይ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተነግሯል። ጀነራል ድንኩልን ከበን ደመሰስነው እንዲሁም ማረክነው የሚሉ የአገዛዙ ፕሮፖጋንዳዎችም ፈፅሞ ሀሰት መሆናቸው ተረጋግጧል ! በውሪ እና በወርቃምባ እንዲሁም በጭላ በተደረጉ ለ2 ቀን ያክል በተቀጣጠለ ውጊያ አገዛዙ ያለ የሌለ ጦሩን አሰልፎ በቀጠናው ያለውን የTDF ጦር ለመደምሰስ የሞት ሽረትን አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ በጀነራል ድንኩል የሚመራው የTDF ጦር በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በዚህ 2 ቀን ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰው ከታንክ ጀምሮ ሌሎች ከባባድ መሳሪያዎች ወደ አመድነት ተቀይረው የአገዛዙ ከበባ ሙሉ በሙሉ ተሰብሮ በአፀፋ ምላሽ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተነግሯል። ጀነራል አብረሃ ተስፋዬ ድንኩል ደምስሰነዋል እንዲሁም ማርከነዋል  በማለት የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ሰራዊት ሚዲያውን አጥለቅልቀውት ነበር አዲሱ የአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊት መሪ ጀዋር መሀመድ ሳይቀር ጀነራል ድንኩል ተማርኳል ሲል በፌስቡክ ገፁ በመፃፍ  መረጃ አስረጭቶ እንደነበረ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ ይህ መረጃ ሃሰት እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች ጀነራል አብርሃ ድንኩል በአዲሱ የቲዲኤፍ አደረጃጀት የማዕከላዊ ግንባር አዛዥ ሆነው የብልጽግናን ጦር እየተዋጉ ናቸው ብለዋል። ​ሰሞኑን የኦህዴድ ፕሮፓጋንዳ ሚሊሻዎች ደምስሰናቸዋል አንዳንዶቹ  ደግሞ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል እያሉ የጻፉባቸው ጀነራል አብርሃን ድንኩል ከአምስት አመታት በፊትም እንዲሁ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገድለናቸዋል ብለዋቸውም ነበር።  የብልጽግናው ሰዎች ያልገደሉትን ገደልን ያልያዙትን ያዝን ማለት ልማዳቸው ቢሆንም ይባስ ብሎ ነገሩን ያከበደባቸው ግን ከደልነው አልያም ማረክነው ያሉት ጀነራል ድንኩል ሰራዊታቸውን በሺዎች በ2 ቀን ብቻ መጨረሱ ናላቸውን አዙሮታል ነው የተባለው። ከዚህ በተጨማሪ ከአገዛዙ ጋር ንግግር በማድረግ ወደ አገዛዙ የተቀላቀለው ጀነራል ጆን መዲድ የሴንትራል ኮማንድ አባላት መሪዎች እነ ደብረፂዮን ጨምሮ ፈትለወርቅ እና ሌሎች የህውሀት መሪዎች የሚገኙበን ቦታ ከአገዛዙ ጋር በገባው ስምምነት መሰረት የተናገረ ሲሆን እነዚህን አመራሮች እንይዛለን ብሎ የተንቀሳቀሰ የአገዛዙ ጦርም እንደቅጠል ረግፎ ገና መንገድ ከመጀመሩ የመንገዱን 1/4ኛ እንኳን ሳይጓዝ መመለሱ ተረጋግጧል ! @ዜማ ቱዩብ

photo content

ይሸሸጉበት ጥግ፣ ይጠለሉበት ጓዳ የሌላቸው፡ ነፍሳቸው የትንኝ ነፍስን ያህል ዋጋ ያጣው የወለጋ አማራዎች! የብልፅግናው አገዛዙ ከውጭ የሚያስገባቸውን አዳዲስ የጦር መሣሪያዎችን መሞከሪያና መፈተሻ አድርጓቸው የቀሩት የወለጋ አማራዎች! ከሞቀ፣ ከሞላው ከደላው ቤታቸው በብልፅግናው አገዛዝ ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያው ቁራሽ እንጀራ፣ እፉኝ ቆሎ እየለመኑ ተቀምጠውም ሞት የቀናባቸው የወለጋ አማራዎች! አገዛዙ ያፈናቀላቸውን አማራዎች "ከሞት ለምን ተረፋችሁ?" በሚል፡ ተፈናቃዮቹ እርዳታ እንዳይደርሳቸው በማድረግ ቁጭቱን በረሃብ አለንጋ በመግረፍ ሲወጣ ቢቆይም፡ ይህም የጥላቻ ጥሙን ሊቆርጥለት ስላልቻለ በድሮን ይጨፈጭፋቸው ገባ።

ኧረ ተው አንተ ሰው ሲወርድ አታባረው: መሮት የዞረ ቀን ዳገቱ ለአንተ ነው::
ኧረ ተው አንተ ሰው ሲወርድ አታባረው:   መሮት የዞረ  ቀን ዳገቱ ለአንተ ነው::

ጀግናው የት ነው??? ​ ለአማራ ህዝብ መብት እና ደህንነት የነበራቸው ቁርጠኝነት ​የሰሜኑ ጦርነት እና በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ተከተሎ፣ ኮሎኔል አሰግድ የህዝባቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ ወደ ፊት ወጥተዋል። ​የፋኖ መሪነት፡ የአማራ ፋኖ የሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ ሆነው በመስራት፣ አደረጃጀቱን በወታደራዊ ህግ እና ስትራቴጂ ለመምራት ጥረት አድርገዋል። ​የቀደመ ልምድን ለህዝብ ጥቅም ማዋል፡ የነበራቸውን የጦር አዛዥነት ልምድ በመጠቀም ወጣቶችን ማደራጀት፣ ማሰልጠን እና የራስን የመከላከል አቅም እንዲገነቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ​የብዕር ጀግንነት (ደራሲነታቸው) ​የኮሎኔል አሰግድ ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ የተወሰነ አልነበረም። የሀገራቸውን እና የህዝባቸውን ታሪክ፣ የጦርነት ተሞክሮዎችን እና ስትራቴጂዎችን በመጽሐፍ መልክ በማቅረብ ይታወቃሉ። ​በመጽሐፎቻቸው አማካኝነት የወታደራዊ ህይወት ምስጢራትን፣ የታሪክ እውነታዎችን እና የሀገር ፍቅርን ለትውልድ ማስተላለፍ ችለዋል። ​ይህ ደግሞ በብዕራቸውም ሆነ በመሳሪያቸው ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የቆሙ አርበኛ እንደሆኑ ያሳያል። ​ጽናት እና የመስዋዕትነት ዝግጁነት ​ከምቾት ህይወት ይልቅ የህዝብን አደራ እና እምነት በመምረጥ በዱር በገደሉ ከባድ የውጊያ እና የችግር ጊዜያትን አሳልፈዋል። ​ያመኑበትን አላማ ለማስፈጸም የነበራቸው ቁርጠኝነት፣ በውጊያ ወቅት የሚያሳይዎትን ጽናት እና ፍርሃት አልባነት ደጋፊዎቻቸው እንደ ትልቅ የጀግንነት ምሳሌ ያነሱታል። ​ማጠቃለያ፡ ኮሎኔል አሰግድ መኮንን በብዙዎች ዘንድ በወታደራዊ ብቃታቸው፣ በደራሲነታቸው እንዲሁም ለአማራ ህዝብ መብትና ህልውና ባሳዩት የጸና አቋም እና አመራር ጀግና በመሆናቸው ከህዝቡ ልብ ውስጥ ገብተዋል ። የሆነው ሁኖ ሰውየው የት ነው???

photo content
+1

ማኅበረ ቅዱሳን የአርሲውንና በተለያዩ ቦታዎች እየተካሄደ ያለውን የኦርቶዶክሳውያንን እልቂት በሚመለከት ጥልቅ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚህ መግለጫው የመንግሥትን፣ የሚድያን እንዲሁም የመላውን ምእመን ድርሻና የሚጠበቅበትን ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡ ምናልባትም በቀጣይ ይህንኑ መግለጫ በእንግሊዘኛና በሌሎች ቋንቋዎችም ማውጣት ይጠበቅበታል፡፡ የሀገር ውስጡ ሚዲያ አፉን ቢለጉም የውጭ ሚዲያዎች ማስረጃና እየተደረገ ያለውን ነገር ያውቁት ዘንድ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች መግለጫዎች መውጣት አለባቸው፡፡ ይኸንን ማድረግ ደግሞ የሚከብድ አይደለም፡፡ ሰሞኑን ሲኖዱሱና ሀገረ ስብከቱ መግለጫ በማውጣታቸው ነው ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ዐለምአቀፍ ሚዲያዎች ጉዳዩን የዘገቡት፣ ታዋቂ ሰዎችም የተቀባበሉት፡፡ በጨለማ ውስጥ ለዓመታት የቀጠለውን የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ለማስቆምና ፍትሕን ለማስፈን ሁሉም በየፊናው መረባረብ አለበት፡፡ ይኸው ነው፡፡

photo content
+3

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በሀይቅ ዙሪያ ጃሪ የሚባል የተፈናቃዮች ካምፕ (የቱርክ ካምፕ የነበረ) ላይ ከወለጋና አዲስ አበባ ተፈናቅለው የመጡ ስደተኞችን በተጠለሉበት አገዛዙ 3 ጊዜ ድሮን በመጣል ጨፍጭፏቸዋል።

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በዳባት ወረዳ የተሳካ ኦፕሬሽን ፈጸመ! ​ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነው ምስጋናው አጠኔ ብርጌድ በዳባት ወረዳ አስደናቂ ድል አስመዝግበዋል። ​መነሻውን ዳባት ከተማ አድርጎ በሌሊት ወደ ማስካር ቀበሌ ተንቀሳቅሶ የነበረውን የአገዛዙን ኃይል ብርጌዱ በደፈጣ ውጊያ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶበታል። ​የአገዛዙ ሚሊሻ ኃይል በሌሊት በመጓዝ ለማፈን ቢሞክርም፣ ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የምስጋናው አጠኔ ብርጌድ አባላት መግደያ ወረዳ ላይ ደፈጣ በመጣል ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመውበታል። በዚህ የደፈጣ ጥቃት 9 የጠላት ኃይሎች የተደመሰሱ ሲሆን 4 ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነው ወደመጡበት ለማፈግፈግ ተገደዋል ሲል መረጃውን ያደረሰን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ነው። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

photo content
+1

በለቅሶ የሚመጣ ነገር የለም መጀመሪያ ነገር እርር ድብን ብለህ እንድታለቅስ እኮ ነው አሰቃቂ የግድያ ድርጊቱን ፈፅመው ሲያበቁ ቪዲዮ ቀርፀው የሚልኩልህ። በዚህ ዘመን ሰው ይደርስልኛል ብለህ ከሆነ አልገባህም። ማን ነው የሚደርስልህ? የጨነገፈው የዩነቨርሲቲ ተማሪ አስተማሪ? የመንግስት ሰራተኛው ወዛደሩ ገበሬው? ማንም አይደርስልህም። ጅብ እንኳ አዳኞች ለመግደል ሲያሯሩጡት እና አንዴ በጦር ከተወጋ መሞቱን ካወቀ ወደ እሚያባርሩት ሰዎች ዙሮ መናከስ ይጀምራል ካገኘም ይዞ ይወድቃል እንጂ ብቻውን አይሞትም። እንኳን እንባ ደም ብታለቅስ መፍትሄ አታገኝም። አዳሜ ለሁለት ቀን ያህል አትግደሉን እስከመቼ መሞት በቃን የምትል ቀልድ እየለጠፈ የመፍትሄ ሀሳብ የተናገረ የሚመስለው የጨነገፈ ትውልድ ነው እየታየ ያለው። ልንገርህ ወዳጄ ፌስቡክ ላይ እኔ ማየት የምፈልገው እነዚያን ሞት መፈናቀል በጅምላ መሞት በቃ ብለው ነፍጥ አንስተው ገዳዮችን ለመፋለም ዱር ቤቴ ያሉትን አንበሳ የወለጋን ፋኖ ጀግኖችን ነው ማየት የምፈልገው። ማየት የምፈልገው ለዘመናት ሲገደል ሲፈናቀል ሲዘረፍ የኖረውን የአማራ ህዝብ ሰቆቃ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመታደግ ጫካ የገባውን የአንበሶችን መንጋ የአማራን ፋኖን ነው ማየት የምፈልገው እንጂ ያንተን የፈሪ እንባ ለአለፉት ስምንት አመታት በየቀኑ ማየት የአእምሮ ቀውስ ከማምጣት ውጭ ምንም አይፈይድም። አንተን የመሰለ ወጣት እየየ ድረሱልኝ እያልህ በዚህ በፋኖ ዘመን ማልቀስ ይደብራል ያማል። በባዶ እጁ ከጠላቱ ማርኮ ትጥቁን ያሟላ የአንበሳ መንጋ በየሰፈርህ እየተገማሸረ አንተ ስታለቅስ ማየት ያሳፍራል እንጂ አያሳዝንም። ከዚህ በላይ ምን በደል ሊመጣ ነው ለዚያውም በገዳዮችህ ፊት ቆመህ እየየ የምትለው? እንዴት 60 ሰው ሲሞት አንድ እንኳ ከገዳዮች አይሞትም? እንዴት ነው ወንድ ልጅ ሆነህ ገጀራ እንኳ ቤትህ ውስጥ አይኖርህም? ከዚህ በኋላ ለቅሶ ለኔ ዜና አይደለም ለኔ ዜና የሚሆነው ሊገድልህ የመጣውን አውሬ መግደልህን ስሰማ ነው ፌስቡኬን ከፍቸ በጀግንነትህ እየተደመምሁ የማለቅሰው። ያንን ጅንኑን አማራ የጎንደር የጎጃም የወሎ እና የሸዋን ያማራውን የአንበሳ መንጋ ፋኖን አይተኸው አታውቅም ማለት ነው። ለቅሶህ እማ ለገዳዮችህ ምርጥ ሙዚቃ ነው የሚደሰቱበት። እውነቱን ለመናገር ገዳዮችህ በአንተ የጣር ድምፅ በጣም ነው የሚዝናኑብህ። ሙዚቃ ሲያምራቸው እና መደሰት ሲፈልጉ አንድ ሻለቃ ገጀራ እና ክብሪት የታጠቀ ገዳይ ቡድን ልከው ያስጨፈጭፉሀል ቤትህን አቃጥለው የእምነትህን ቦታ አቃጥለው ዘርፈው እና አዋርደው እሬሳህን አስይዘው ደም እንባ እያለቀስህ ከአካባቢው ስትሰደድ ያኔ ልክ ሙዚቃን የሰሙ ያክል ይደሰታሉ። ለመሆኑ ለማን ነው የምታለቅሰው? መጀመሪያ ነገር ገዳዮችህ እኮ እንድታለቅስ ብቻ አይደለም ተወልደህ ያደግህበትን መሬት ለቀህ እንድትሰደድ ነው ቢላዋውን እየሳለ የሚያርድህ። ምርጫው ያንተ ነው አንደኛው በየቀኑ ማልቀስ በየቀኑ መታረድ በየቀኑ መሳቀቅ በየቀኑ የታረዱ የሰው ልጆችን ማየት አንደኛው ምርጫ ሲሆን። ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ እንደጀግኖቹ የወለጋ ፋኖ የደቡብ ፋኖ የአማራ ፋኖ በልበሙሉነት ተደራጅተህ ህይወትህን ማትረፍ። ከዚህ ውጭ ያንተን የእንባ ጎርፍ በየፌስቡኩ እየለጠፈ አካኪ ዘራፍ የሚል አዛኝ ቂቤ አንጓች ምንም አይፈይድም። ከሁለት ቀን የሆይ ሆይ ወሬ በኋላ ያንተ የደም እንባ ፈሶ ይቀራል እና ይረሳል ማለትም ሌሎች እስኪታረዱ ከዚያ ደግሞ አርሲ ላይ ሰው ታረደ ተብሎ በፌስቡክ አካኪ ዘራፍ ይባላል እያለ እሽክርክሪቱ ይቀጥላል አንተ በቃኝ ካላልህ። ወንድሜ እረኛውም የመንጋው ጠባቂም ምቾቱን በአንተ በፈሪው ምክንያት ማጣት አይፈልግም።ዛሬ እኮ አብዛኛው የበጎች እረኛ ነን ባዮች በሰይጣን መሀረብ ተሸፍነው የበጎችን መታረድ ማየት ማለት ከሚያማልለው አለማዊ ኑሮ ስለሚያወርዳቸው አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ ቢበዛ የአዞ እንባ ያነባሉ እሱንም ገዳዮች እንዳያዩአቸው ተደብቀው። በመጨረሻም የደም ፅዋው ሞልቶ የእንባ ጎርፍ የፈጣሪን በሮች እስከሚያንኳኳ ድረስ አንተ ለቅሶህን ተው እና ነፍጥህን አንሳ። የማትዋሸው እና ጠላትን የምታደባየው ነፍጥህ ብቻ ነች። ለአርሲ ሰመአታት ነፍስ ይማር

በንፁሃን አማራዎች ላይ የድሮን ጥቃት ተሰነዘረ!! ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ አረመኔዊ ድርጊት እየፈፀመ የሚገኘው የብልፅግና አገዛዝ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም በደቡብ/ወሎ ዞን ጃሪ ተፈናቃዮች ካፕ ላይ 4ግዜ የድሮን ጥቃት በመፈፀም በርካታ ተፈናቃይ ካፕ የሚኖሩ ሰደተኞች የሞት ሲሳይ ሁነዋል ምንም አይነት የታጠቀ ሃይል በለለበት ተፈናቃዮች ካብ ላይ የድሮን ጥቃት በፈፀመው የድሮን ጥቃት ንፁሃን አማራዎች መገደላቸው ተረጋግጦል።

አሳዛኝ ዜና! በጃሪ መጠለያ ካንፕ በንፁሃን ዜጎች ላይ የድሮን ጥቃት በአገዛዙ ተፈጸመ! ​የብልፅግና አገዛዝ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ የድሮን ድብደባ አሁንም አድማሱን አስፍቶ ቀጥሏል። አገዛዙ ላለፉት ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመው ባለው ስልታዊ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ሲጨፈጨፉ በሚሊዮን የሚገመት ንብረቶቻቸዉ መዉደማቸዉ ይታወቃል ፣ ዛሬም ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም በጃሪ መጠለያ ካንፕ ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ከፍተኛ የድሮን ድብደባ ፈጽሟል። ​ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፈናቅለው በካንፑ ውስጥ በነበሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ በተጣለው ድሮን በርካታ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና የሃይማኖት አባቶች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቁስለኛ ሁነዋል። ​መጠላያ ጣቢያወቹ ላልታጠቁ ዜጎች መኖሪያዎች ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚደረግላቸው ቢሆንም፣ አገዛዙ ግን ሰብአዊ ሕግጋትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ በችግር ላይ ባሉ ወገኖች ላይ ጥቃቱን ማወረዱ አሰቃቂነቱን የባሰ አባብሶታል። ​በድብደባው የሞቱትና የቆሰሉት ዜጎች ትክክለኛ ቁጥር አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም፣ በቦታው ላይ የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ አሳሳቢ አድርጎታል። ድርጊቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን የጫረ ሲሆን፣ የአገዛዙ የጭካኔ ዘመቻ በንፁሃን ላይ ያለ እረፍት አጠናክሮ ቀጥሎበታል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ! ጥቅምት 19/ 2019 ዓ/ም