uz
Feedback
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

Kanalga Telegram’da o‘tish

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ከስነ-ፅሁፍ ዓለም analitikasi

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም (@ethiobooks) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 10 296 obunachidan iborat bo'lib, Kitoblar toifasida 3 705-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 3 234-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 10 296 obunachiga ega bo‘ldi.

03 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 11 ga, so‘nggi 24 soatda esa 1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 10.64% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 3.06% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 095 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 315 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 8 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 04 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Kitoblar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

10 296
Obunachilar
+124 soatlar
-77 kun
+1130 kun
Postlar arxiv
ዊሊያም ዊልበርፎርስ - 2 የመጨረሻው!

ዊሊያም ዊልበርፎርስ - 1

▶ ዊሊያም ዊልበርፎርስ ━━━━━━━━ «የባሪያዎች ጠበቃ» @ethiobooks
+1
▶   ዊሊያም ዊልበርፎርስ ━━━━━━━━ «የባሪያዎች ጠበቃ»              @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

እሳትና ጥበብ ══✦══ ✍ ሄኖክ በቀለ ' ሰዎች እንዲህ ናቸው              °        የትዕዛዝ ዳዴ ይጎትትህና - ስትጀምር መራመድ እሳት ይሰጡሃል - ሸፋፍነው በአመድ              °        ከሩቅ ይሆኑና ...        ከቤትህ ቃጠሎ ... የሚግተለተል ጢስ - ይጠባበቃሉ        ግማሹ ተቃጥሎ ግማሹን አተረፍን - አጠፋነው ሊሉ              °        ብልጥ ከሆንክ ግን ከምላስ 'ሚወጣ - ፍሙንም ተቀበል ከድርጊት 'ሚመጣ - ግለቱን ተቀበል አመዱን ገላልጠህ - ጥበብ አክልበት ሊያቃጥሉህ ሲሹ - አንተ ብሰልበት። ═══════ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ም ላ ስ 👅 👅 👅 ምላስ ይቀባል፣ ጥርስ ይወጋል። 👅 ምስጢረኛ ምላስ የለውም። 👅 ምላስ ከጥርስ፣ እጅ ከልብስ። 👅 የተቀማጭ፣ ምላሱ ምላጭ። 👅 ምላሱ አይታጠፍም። 👅 የባለስር፣ ምላሱ አ
ም ላ ስ 👅 👅 👅 ምላስ ይቀባል፣ ጥርስ ይወጋል። 👅 ምስጢረኛ ምላስ የለውም። 👅 ምላስ ከጥርስ፣ እጅ ከልብስ። 👅 የተቀማጭ፣ ምላሱ ምላጭ። 👅 ምላሱ አይታጠፍም። 👅 የባለስር፣ ምላሱ አስር። 👅 ምላስ ቢጥም፣ ቀዶ ይጠቅም። 👅 መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች። 👅 ባንድ ራስ፣ ሁለት ምላስ። 👅 ምላስ ያስቀጣል፣ ስለት ይቆርጣል። 👅 ቀይ ምላሱ፣ ጥቁር ራሱ። 👅 በምላስ የተወጋ፣ ቢታከም አይድንም። 👅 ያላረፈች ምላስ፣ ሸማ ትልስ። 👅 የሰው ምላስ መንታ፣ አንዱ ለሙገሳ አንዱ ለሐሜታ። 👅 ምላስ አጥንት የለው፣ ግን አጥንት ይሰብራል። 👅 👅 ነገር በምሳሌ @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች ━━━━━✦━━━━━ ✍ ከበደ ሚካኤል ' እናቱ በጣም አድርጋ የምትወደው አንድ ልጅ ነበር። እሱም ከዐጥር ግቢያቸው ውስጥ ከሚገኙት የኮክ ዛፎች ላይ እየወጣ ፍሬውን ሲቆርጥ እናቱ ብዙ ጊዜ ታየው ነበርና ከዛፉ ላይ ወድቆ አደጋ ያገኘዋል በማለት ስለሰጋች እንዳይወጣ መላልሳ ብዙ ጊዜ ከልክላው ነበር። አንድ ቀን ከቤት ውስጥ ሆና እንደ ልማዱ ከኮኩ ዛፍ ላይ ፍሬ ሲለቅም በመስኮት አየችው። ከቤት ሲገባ ጠርታው "ከዛፍ ላይ አትውጣ ብዬ ከልክዬህ አልነበረምን? ለምንድን ነው ዛሬ ደግሞ የወጣኸው?" ብላ ጠየቀችው። እሱ ግን ደንግጦ "አልወጣሁም" ብሎ ካደ። እሷም በጣም ተቆጣችና "ደግሞ ከማጥፋትህ መዋሸትህ ይባስ። ባይኖቼ እያየሁህ ትክደኛለህ?" ብላ ልትመታው ተነሣች። እሱም አሳዛኝ የሆኑትን ዐይኖቹን እያንከራተተ ለዛ ባለው አንደበቱ "እማማ እወድሀለሁ ትዪኛለሽ፣ እንደምትዪኝም እውነትም የምትወጂኝ ከሆንሽ ባይኖችሽ ካየሽው ይልቅ እኔ የምነግርሽን አብልጠሽ ማመን ይገባሻል" አላት። ደማሙ ልጅ ይህን ማለቱ 'ስለ እኔ ፍቅር ብለሽ ያየሽውን እንዳላየሽ አድርገሽ አሳልፊው እንጂ በጥፋቴ ለምን ትሞግቺኛለሽ?' ብሎ መለማመጡ ነው። እናቱም በዚህ ለዛ ባለው ንግግር ከቁጣዋ በርዳ በመምታት ፈንታ ልጅዋን አቅፋ ሳመችው። ዐይኖችዋም ዕንባ አቅርረው ይታዩ ነበር። ━━━━━━━━━━ 📔 ታሪክና ምሳሌ - ፩ኛ መጽሐፍ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

• ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ • በምስጋና የምታጭዱት ማሳችሁ ነው ━━━━━✦━━━━━ ✍ ካህሊል ጅብራን ' አንድ ወጣትም አለው፦ «ስለ ጓደኝነት ንገረን?» እሱም እንዲህ በማለት መለሰለት፦ «ጓደኞቻችሁ ለፍላጎቶቻችሁ ምላሽ ናቸው። ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው። ገበታችሁና የምትሞቁት እሳታችሁም ነው... «በራባችሁ ጊዜ ወደ እሱ የምትሄዱትን ያህል በሰላም ጊዜስ አትፈልጉትምን?... «ጓደኛችሁ ከአዕምሮው ጋር ሲነጋገር በገዛ አዕምሯችሁ ውስጥ ስላለው ‹አሉታ› አትስጉ። ‹አዎንታ›ንም አትንፈጉት። ዝም ባለ ጊዜ ልባችሁ፣ ምኞቶችና ተስፋዎቻችሁ ሁሉ ቃላትን መጠቀም ሳያስፈልግ ያለ ሆታና ጭብጨባ ተወልደው በወዳጅነት የምትጋሯቸው ነገሮች ናቸውና... «ከጓደኞቻችሁ ስትለያዩ አትዘኑ። ለተራራ ወጪ ሰው ተራራው በግልጽ የሚታየው ከሜዳው ላይ ሆኖ እንደሆነ ሁሉ፣ ከሁሉ አስበልጣችሁ በምትወዱት ሰው ውስጥ ያለው ብዙ ተወዳጅ ነገር የበለጠ ግልጽ ሆኖ የሚታያችሁ እሱ በሌለበት አይደለምን?... «እናም በጓደኝነት ውስጥ ከመንፈስ ጽናት በስተቀር ሌላ ምንም አላኖራችሁም... «የገዛ ራስን ምስጢር (ምኞት) ለመፍታት ከመሻት በስተቀር ሌላን የማይፈልግ ፍቅርስ ዋጋ ቢስ ነገሮችን ብቻ ለማጥመድ ወደ ባህር የተወረወረ መረብ እንጂ ፍቅር ሊሆን ይችላልን?... «ደግሞም ለጓደኛችሁ የተቻላችሁን ያህል መልካም ሁኑለት። የልባችሁን ባህር የማዕበል ሞገድ ማወቅ ካለበት የውኃ ሙላቱን (ጎርፍንም) ጭምር ይወቅ... «በጣዕረ ሞት (በመቀበሪያ) ጊዜያት ልትፈልጉ የሚገባችሁ የቱን ጓደኛችሁን ነው? ሁልጊዜም በፍስሃ (በሕይወት) ጊዜያት ፈልጉት። ባዶነታችሁን ሳይሆን ፍላጎታችሁን መሙላት የሚገባው እሱ አይደለምን?... «በጓደኝነት ጣፋጭ ጊዜያት ውስጥ ሳቅና ደስታን መጋራት ይኑር። ልብ ንጋቱን (ብርሃኑን) አግኝቶ የሚታደሰውስ በጥቃቅን ነገሮች ጤዛ ውስጥ አይደለምን?» ━━━━━━━━━━ 📔 የጠቢባን መንገድ ትርጉም ➢ ሀብታሙ ተስፋዬ 📄 40 - 41 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ቅዱስ መርቆርዮስ - 2 የመጨረሻው!

ቅዱስ መርቆርዮስ - 1

▶ ቅዱስ መርቆርዮስ ━━━━━━ «ባለ ሁለት ሰይፉ ሰማዕት» @ethiobooks
+1
▶   ቅዱስ መርቆርዮስ ━━━━━━ «ባለ ሁለት ሰይፉ ሰማዕት»              @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

በራ፤ የመስቀል ደመራ ═══ ❖ ═══ ✍ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ' የአደይ ችቦ እየፋመ ፥ እየጋመ ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ የመስቀል ደመራ በራ። በራ የአዲስ ዘመን ችቦ በመስከረም ሰብል አብቦ ከዋ
በራ፤ የመስቀል ደመራ ═══ ❖ ═══ ✍ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ' የአደይ ችቦ እየፋመ ፥ እየጋመ ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ የመስቀል ደመራ በራ። በራ የአዲስ ዘመን ችቦ በመስከረም ሰብል አብቦ ከዋክብቱን ፈነጠቀ ርችቱን አንፀባረቀ ተኳለ አዲስ ደመቀ መስኩን በቀለም አዝርዕት፥ በጥበብ አጥለቀለቀ ሸለቆው ተንቆጠቆጠ ፥ ተራራው አሸበረቀ ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ። ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ ፈካ ፥ ፀደይ አረብቦ ሌሊቱ እንደ ጎህ ቀደደ ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ እንደ ውቅያኖስ ዕፅዋት ፥ እንደ ጠፈር ኮከብ ደራ ምድር ስጋጃ ለበሰ ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ ሰማይ በእልልታ አስተጋባ ኢ ዮ ሃ  መስከረም ጠባ። ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች የምስራች አዝርዕቷን ፥ አዲስ ቡቃያ ወለደች የአደይ አበባን ለገሠች ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን ፥ አዲስ መስከረም ገበየች። ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ ፈካ ፥ ፀደይ አረብቦ በራ፣ የመስቀል ደመራ። ═════════ 🗓 መስከረም ፲፱፻፷፫       መስቀል አደባባይ 📖 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

የአጼ መስቀል የደመራ በዓል 1922 ዓመተ ምሕረት ━━━━ ❖ ━━━━ የአጼ መስቀል በዓል መስከረም 10 ቀን 1922 ዓ.ም. ዓርብ በግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱና በግርማዊ ንጉሥ ተፈሪ ፊት በቤተ መንግሥት ተከበረ። ሊቀ ጳጳሳቱ፣ እጨጌው፣ ሚኒስትሮች፣ መኳንንት የዲፕሎማቲክም ሰዎች በበዓሉ ላይ ነበሩ። የምራቱ ተረኞች የጽርሐ አርያም ካህናት ባለፈው ወር በአየር እየበረረ የመጣውን የአውሮፕላን ታሪክ ለመጥቀስ ሲሉ "ወረሰየ ደመና ወከየዶ ዘየሐውር በክንፈ ነፋስ ዘርየስዬሙ ለመላእክቲሁ መንፈስ።" የሚለውን ምስባክ አሰበኩ። የዘመኑን ታሪክ በተመሳሳይ ጥቅስ ማቅረብም የተለመደ ነገር ነበር። ከዚህም በኋላ ተቀጸሊ ጽጌ አስካለ ማርያም ሐጼጌ "እቴጌ አስካለ ማርያም ሆይ፣ አበባን ተቀዳጂ" እያሉ እንደ ተለመደው አሸብሽበውና ሊቀ ጳጳሱ አሳርገው የበዓሉ ፍጻሜ ሆነ። አስካለ ማርያም የንግሥት ዘውዲቱ የክርስትና ስም ነው። ሁልጊዜም ተቀጸል ጽጌ ሲባል የሚጠራው ይህ ስም ነበር። የደመራ በዓልም መስከረም 16 ቀን 1922 ኀሙስ በ9 ሰዓት በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በአደባባዩ ላይ በወታደር ሰልፍ ተከበረ። በዚህ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች በአየር ላይ እያንዣበቡ የመገለባበጥ ትርእይት ስላሳዩ ሕዝቡ ብርቅ ነገር ሆኖበት ሽቅብ ሽቅብ ተመለከተ። ደግሞም የወረቀት አበባና የወረቀት ጽሑፍ ለሕዝቡ በተኑለት። ከግጥሙ ቃል የማስታውሰውን በሚከተለው እገልጻለሁ፦
የመስቀሉ በዓል ምንኛ ገነነ፣ ከአምና ዘንድሮ የበለጠ ሆነ። ንግሥትና ንጉሥ በዙፋን ሆነው፣ ጀግናው ተሰልፎ መኳንንት ከበው። በግራና በቀኝ በራስጌ በግርጌ፣ አምስት ጳጳሳት ስድስተኛ እጨጌ። ደግሞም ተንዣበበ በስተላይ ባየር፣ ተጓደኞቹ ጋር የተፈሪ ንስር፣ አበባ ሊነዛ በዓሉን ሊያከብር። በዘንድሮው መስቀል በዛሬው በዓል፣ እጅግ ደስ ይበለን እልል እንበል። ብርሃንን እንልበስ ሰላምን እንውደድ፣ ንስረ ተፈሪ ነው በጨለማ እንሂድ። በአየር ላይ ሆኖ አበባን ሲዘራ፣ ከተከታዮቹ ከመላእክት ጋራ፣ እንቁጣጣሽ ይላል የተፈሪ አሞራ።
 ሰልፉም እንደተፈጸመ ግርማዊ ንጉሥ በሠራዊት ታጅበው ወደ ግቢያቸው ተመለሱ። ━━━━━━━━━━ 📔 የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ✍ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ 📄 376 - 377 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም - Telegram kanali @ethiobooks statistikasi va tahlili