قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Kanalga Telegram’da o‘tish
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
907
Obunachilar
-224 soatlar
-127 kun
+4630 kun
Postlar arxiv
👉 የለተሞው መንጋ የውሸት ካዝና አጋፋሪያቸው ሑሰይን ስልጤ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ላይ የቀጣጠፈውን ፅሁፍ ሲፈተሽ፦
🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲
🎤❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
☪☪☪☪☪
↩️ رد على أحد المفترين من زعماء اللتميين المسمى بحسين السلطي فى ما كتبه جوابا لمن سأله -بزعمه- عن أسباب خروج الأستاذ ابن منور 🤩 تعالى عن السلفية وانحرافه عن الجادة،
1️⃣أولا: ما ذكره فى مبدأ جوابه من اتفاق السلف على بغض أهل البدع والبعد عنهم تقربا لله فهذا لا غبار عليه وهو الذى ندين الله به من قبل ومن بعد 🛒🌟تعالى، ولكن أسألك يا حسين هل ابن منور يخالف هذا الأصل فيجوّز محبة المبتدعة والقرب منهم!؟ حاشا وكلا! وإلا فلِم ذكرته فأردفته بقولك "فمن خالف الخ"!؟ وإن كنت تزعم هذا فأتنا ببرهانك،
2️⃣أما ما ذكرته من العلامة ابن باز 🌟 من أن من أثنى على أهل البدع يلحق بهم" ففيه تفصيل عريض مذكور فى موضعه، أرى أن الأستاذ خضر أحمد الكميسي 🇧🇼 تعالى قد أهدى لك من هذا التفصيل من قبل بما يغني عن إعادته هنا،
3️⃣وأما قولك إن ابن منور قد ابتلي بمسألتي التبديع والجرح والتعديل فالأجدر بأن يوصف بذاك الابتلاء حقيقة أنتم ممن ذكرت من السلفيين، وهذا أمر مشاهد لكل أحد إلا لمن أعمى الله بصره وطمس بصيرته،
4️⃣وأما تجهيلك لابن منور ولمن معه من السلفيين فهذا شيء معهود منك ومن أمثالك التائهين الذين منعهم من قبول الحق الجهل الممزوج بالكبر والحسد والحقد، وعجزوا من الرد على مخالفيهم بالعلم والأدب، فلا غرابة مَن هذا بعض نعوته أن يجهّل مصابيح الدجى ومنار الهدى،
5️⃣وأما قولك "إن ابن منور تصدى بالدفاع عن مركز ابن مسعود" فهذا بهت بحت، بل المعروف منه الصدع بالحق والتحذير منهم ومن كل من أظهر خلاف ما عليه السلف الصالح، نعم هو لا يتجاوز الحد فى الرد عليهم فيرميَهم بما ليس فيهم كما هو عادتكم أيها اللتميون، وقولك "لا ندري شيخه الخ" من عجائبك، فهل يلزم من كونك لا تعلم أنت وأمثالك شيوخه أنه لا شيخ له وأنه ضال مبتدع!؟ فيا سبحان الله!!
6️⃣وما ذكرته من أنه يطعن فى العلماء إن كان مرادك بما ليس فيهم فهذا أيضا كذب واضح كوضوح الشمس فى رابعة النهار، أما بيان انحرافاتهم وتوعية الشباب بما أحدثوه من البدع والمنكرات فهذا من مكروماته فلا ينبغي أن يذم عليه أصلا، بل يمدح به،
7️⃣أما قولك إنه كتب كتابات فى الدفاع عن هؤلاء فهذا كذب بحت فهو لم يكتب كتابا واحدا فضلا عن الكتابات وإن كنت تسمي الرد على اللتميين المتهورين دفاعا عن أصحاب المركز فهذا من سوء فهمك بل يدل على أن فى عقلك خللا صعب المسد فضلا عن منهجك، فأفق وداوِ نفسك قبل فوات الأوان،
8️⃣وقولك إنه قرر أن الثناء على أهل البدع الخ من قصور علمك، وتلبيساتك على أتباعك، وقد أحلتك آنفا فارجع إليه إن شئت، أما تقوّلك على ابن منور بأنه افترى على عدد من العلماء فسيأتي الرد عليه حين تذكره إن شاء الله تعالى،
9️⃣أما ما ذكرته بعد تنبيهك لغيرك -وأنت خليق بالتنبّه من من سواك- من أن ابن منور كان فى أول أمره بيّن "أن أصحاب المركز انضموا إلى الإخوان المسلمين" فإن كان مرادك بالانضمام كونهم مثلهم فى الحكم فهذا بهتان عظيم وافتراء وخيم، وإلا فما زال يرد عليهم ويحذر الناس منهم إلى الآن قدر المستطاع،
0️⃣1️⃣وأما ما ذكرته "من أنه توقف عن الرد عليهم،" فلم يتوقق بل إنه كتب في هذه السنة، ولكن لما كان رده عليهم ليس على أسلوب ردكم الممزوج بالشتم وتنقص الغير والتطاول على المردود عليه لمزته بأنه ساكت، مع أنك تعلم أن الرد فرض كفاية وأنه رد وزيّف أباطلهم قبلكم.
ولو سكت -فرضا- لا يلام عليه لأن سكوته إما اتكالا على رد وبيان بعض إخوته، وإما لشغله بالتدريس والرد على الملحدين المعاندين من الأحباش وغيرهم كما هو مشاهد، وأسألك يا هذا لو سكت هل سكوته يخرجه من السلفية؟
🔢🔢وأما قولك "وبدأ يعتذر لمركز ابن مسعود" فإن كان مرادك أنه اعتذر لهم بالحق والباطل فهذا كذب محض، وإلا فرده عليكم بقوله ألا تغلوا فی دینكم غیر الحق وفى الكلام على الناس ولو على أهل البدع والأهواء فهذا حق لا ريب فيه نقول به أولا وآخرا،
🔢🔢وأما قولك "وبدأ بالطعن فى مشايخ السنة كالشيخ عبد الحميد ... وألحقهم بالحدادية" فهذا من نظره الثاقب وصدعه بالحق لأن فيهم من صفات الحدادية الشيء الكثير، سأذكرها 🛒🌟 فى بحث آخر،
🔢🔢أما قولك إنه "بدأ ينشر قواعد المبتدعة الخ" فهذا من كذباتك الفاحشة، فابن منور ما برح منذ شبابه منافحا ومكافحا عن حمى دين الإسلام وسنة سيد المرسلين ⏩️، هذا الذي نشهد 👆 عليه، ولا نعلم منه إلا خيرا، نحسبه كذلك والله حاسبه ولا نزكي على الله أحدا،
🔢🔢وأما ما ذكرته من أنه قرر أن الجرح والتعديل اجتهادي -وبعبارة أحسن منها- يدخله الاجتهاد ولا إلزام فيه" فهذا حق حقيقي وعليه السلف والخلف من علماء السنة ومن كبار المحدثين، ما جاء ابن منور بشيء جديد، وإن أردت النقاش حول هذا فباب السلفيين مفتوح، ولكن أنتم الغاية فى الجبن،
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጠጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
ሰለፍያ!
የዚህን ድንቅና ግዙፍ ስም እውነተኛ ትርጉም፣ ገዝፎ የተሸከመውን ታሪካዊ ክብደትና የተከበረ ቦታ በትክክል ለመረዳት፣ ስሙን ብቻ ማንበብ በቂ አይደለም። ይህን ስም ለመረዳት ከጀርባው የተዘረጋውን የዘመናት ታሪክ፣ በዚያ ጎዳና ላይ የተከፈለውን የእውቀትና የደም ዋጋ፣ ከተዛቡ እምነቶችና ከቢድዓ ጋር የተደረገውን የረጅም ዘመን ትንቅንቅ የአቂዳ ኪታቦችን ከፍቶ በደንብ ማስተዋል ያስፈልጋል።
ይህ ስም በሆነ ቀን የተሰበሰቡ ሰዎች የተሰጠ የቡድን መጠሪያ ስም አይደለም። እንዲሁም ለአንድ ሰው፣ ለአንድ ሸይኽ ወይም ለአንድ ድርጅት የሚያገለግል የግል መለያ አይደለም። ከዚያ የበለጠ ሰፊና ጥልቅ ትርጉም ይዟል። የቀደምት ሰለፎች የእምነትና የመረጃ መንገድ እንዳይደለዝ፣ እንዳይበረዝና ከትውልድ ወደ ትውልድ በንፅሕና እንዲደርስ የተደረገውን ትልቅ ትግል የሚወክል ስም ነው።
የእስልምናን መሰረታዊ እምነት ከግል አስተሳሰብ፣ ከፍልስፍናዊ ማምታቻና ከተዛቡ ትርጓሜዎች ለመጠበቅ፤ ቁርዓንና ሐዲስን እንደመሰረታዊ መረጃ ለመያዝ፤ የቀደምት ሰለፎችን መንገድ ከሰርጎ ገብ ለመጠበቅ የተደረገው የዘመናት ገድል በዚህ ስም ውስጥ ይንፀባረቃል።
ከጥንቱ የኸዋሪጆች ፊትና ጀምሮ፣ በየዘመኑ በተለያዩ መልክ የተነሱ የጥመትና የቢድዓ አስተሳሰቦች ሲያቆጠቁጡ፣ በሐቅ መረጃ ቀንድ ቀንዳቸውን እያለ ልክ ሲያስገባቸው፣ የተዛቡ ያተንጋደዱ እምነቶች በማስረጃ ሲመለሱ ሲቃኑ፣ የእስልምና አቂዳ ከመደበላለቅ ከመበረዝ ሲጠበቅ የመጣውን ረጅም ተጋድሎ ስትመለከት፣ የዚህ ስም ክብደት ይበልጥ ይገለጥልሃል።
ስለዚህ ይህንን ስም #አደራህን....!#አደራህን....! #አደራህን...! ከአንድ ሰው ጋር ብቻ አታስተሳስረው። ከአንድ ሸይኽ ጋር ብቻ አትገድበው። ለአንድ ቡድንም የግል ንብረት አታድርገው። የስሙን ታሪክና ክብደት ሳታውቅ ለግለሰብ ማንነት መለያ ማድረግ፣ ስሙን ከትልቁ ትርጉሙ ማሳነስ ነው።
ይህ ስም ከግለሰቦች የሚበልጥ፣ ከቡድኖች የሚሰፋ፣ ከዘመናት የሚሻገር ትርጉም የያዘ ስም ነው።
✍️ አብዱል ከሪም ሑሴን
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
ሙሐዶራዎችን በቀላሉ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1-የተቃጠሉ መስጅዶች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
2-ሱፍዮች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
3-መርከቧ ላይ ማን ተሳፈረ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
4-ትክክለኛ እምነት በኡስታዝ ሳዳት ከማል
5-ጀነት መግቢያ ከእሳት መጠበቂያ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
6-አህሉ ሡና ከአህሉል ቢድዓ የተለዩ ናቸው በኡስታዝ ሳዳት ከማል
7-የሺርክ ስንኝ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
8-የሽርክ ስንኞች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
9-የቦረናው ሸህ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
10-አርሽ ዙሪያ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
11-ሽርክ ስንኝ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
12-ለአህባሾችና መሪዎቻቸው የተሰጠ መልስ በኡስታዝ ሙሐመድ ሢራጅ
13-የኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ ሙሀዶራዎች
14-ከአንድ እስከ መቶ (1-100) ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
15-ከመቶ አንድ እስከ ሁለት መቶ (101-200) ድረስ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
16-ከሁለት መቶ አንድ እስከ ሶስት መቶ (201-300) ድረስ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
17-ከሶስት መቶ አንድ (301) በላይ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
18-አህባሾችን የተመለከቱ ሙሐዶራዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
19-አህባሾች በአላህ ስምና ባህሪ ላይ ያላቸው አቋም በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
20-ጀርሕ ወተዕዲል የተመለከቱ ሙሐዶራዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
21-ከአህባሾች ጋር የተደረገውን ውይይት ለማግኘት በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
22-ሀጃዊራወችን የተመለከቱ ረዶች
23-ጥናት መንዙማ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
24-ሸይኽ ሙሀመድ ገዛል ሙሓዶራዎች ቁጥር 1
25-ስለ አኼራ የተደረገ ሙሀዶራዎች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
26-የአቡ ዓኢሻ አወል ኹጥባዎች
27-የአቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም ኹጥባዎች
28-የአቡ ሙዓዝ ሀሠን እንድሪስ ኹጥባዎች
29-የአብዱ ሽኩር ኹጥባዎች
30-የኡስታዝ ሑሴን አሊ ሙሐዶራዎች
31-የአቡ አዩብ ኹጥባዎች
32-ተውሒድን የተመለከቱ ሙሀዶራወች
33-የተለያዩ ሙሐዶራዎች
34-የሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሙሓዶራዎች
35-የሼይኽ አቡ ዓማር አወል ቢን አህመድ ሙሓዶራዎች
36-የኡስታዝ ኢብን ሙነወር ሙሓዶራዎች
37-የኡስታዝ አቡ ሙስሊም ሙሓዶራዎች
38-የኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሠን እንድሪስ ሙሓዶራዎች
39-የሸይኽ ሙሐመድ መኪን ሙሐዶራወች
40-የሸይኽ አህመድ አወቀ ሙሓዶራዎች
41-የሸይኽ ሙሐመድ አሚን ሙሓዶራዎች
42-የሸይኽ ሙሐመድ ገዛል ሙሓዶራዎች ቁጥር 2
43-የኡስታዝ አብዱ ሽኩር አቡ ፈውዛን ሙሓዶራዎች
44-የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐዶራዎች
45-የአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም ሙሓዶራዎች
46-የኡስታዝ አቡ ሡፍያን ሙሓዶራዎች
47-የአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን ሙሓዶራዎች
48-የሙሐመድ አወል የሺርክ መንዙማዎች በአቡ ዑሰይሚን
49-የኡስታዝ ሳዳት ከማል ቀሪ ሙሓዶራዎች
50-የኡስታዝ አቡል ዓባስ ናስር ሙሐመድ ሙሓዶራዎች
51-የኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ ሁሴን ዒስማዒል ሙሓዶራዎች
https://t.me/yedaewachannel
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
✅የሸይኽ አወል አህመድ አልኸሚሴ ሙሓዶራዎችን እና ፈትዋዎችን ለማግኘት 🫰በዚህ በኩል
📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/1499
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/1499
+1
🔴✈️ 👉🔴
🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎
ውድ እና የተከበራችሁ "ሰለፍያ እህት ወንዲሞች ባረከላሁ ፊኩም"" በራሳችሁ ቻናል ከፍታችሁ የቢዳአ አንጃዎችን
⓵ ቻናል♨️ ⓶ ግሩፕ እንደት ታስተዋውቃላችሁ???!!
💗 የገረመኝ ደግሞ አዋቂ ናቸው ከምንላቸው ኡስታዞች፣ እና እህቶች ቤት ነው እንደዚህ አይነት ዲብልቅልቅ ያለ ነገር እያየን ያለነው። ሰውንም አዛ አታዲርጉ ምንም አይነት ጥቅም የ'ለለው wave "እያንጋጋችሁ።
ታርጌታችሁ ምንዲነው?!!!!
🌟 ቻናላችሁን እና ግሩፖችሁን ማሳደግ?!
🌟 ወለስ ዳዕወተ ሰለፍያን ማስፋፋት?!!
ምንም የማያቀው ሰው እዚያ እየሄደ ይቀላቀላል ከዚያም የነሱ ወጥመድ ሰለባ ይሆናል ለምን??!
weve "ስትገቡ አታጣሩም ?!
ከኢኽዋኑም፣ ከለተሜውም፣ከሀጃዊሪያውም እንዳው ዝም ብሎ መነዳት አላሁል ሙስተአን።
እባካችሁ አብዛሀኛዎች ዌቭ የሚሰሩ ሰዎች ኢኽዋኖች እና ሀጃዊራዎች ናቸው ።አላህ እንፍራ :: ብዛትን ሳይሆን ጥራትን ፈልጉ።
⬅በየ ቦታው እያየናቸው ያሉ ዌቮች ናቸው ተጠንቀቁ ፣ራሳችሁ በነሱ መረብ አስገብታችሁ ሌላውንም አታስጠምዱ።
ሸርርርር አርጉ ባረከላሁ ፊኩም
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣5️⃣6️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 475፣ ሐዲሥ ቁ. 1376
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
🧦
ካልሲ (ሁፍ) ላይ ስለ ማበስ ምን ያህል እናውቃለን⁉️
✍አንድ ሰው ውዱዕ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ለማበስ ከፈለገ……
💫ካልሲውን ሲለብሰው ዉዱዕ ያለው ሆኖ መልበስ አለበት።
💫ካልሲው ከነጃሳ የጠራ ንፁህ መሆን አለበት።
💫ካልሲው የእግሩ ለውዱዕ የሚታጠበውን ቦታ መሸፈን መቻል አለበት; ቢያንስ ቁርጭምጭሚቱን የሚሸፍን መሆን አለበት።
💫ካልሲው ላይ ማበስ የሚችለው ዉዱዕ በሚያደርግ ጊዜ ብቻ ነው; ለጀናባ እና ለመሳሰለ ትጥበት የሚታጠብ ከሆነ ማበስ አይችልም።
💫ካልሲው የተቀደደ ቢሆንም ማበስ ይችላል።
💫ካልሲው ቀጭን ቢሆንም ማበስ ይችላል።
💫በሚያብስ ጊዜ እጆቹ ላይ አንድ ጊዜ ውሀውን አፍስሶ ከደፋው በኋላ ጣቶቹን ይዘረጋቸውና በሁለቱ እጆቹ ሁለቱ እግሮቹ ላይ ያብሳል። በቀኝ እጁ ቀኝ እግሩ ሲያብስ; በግራ እጁ ግራ እግሩ ያብሳል።
★ሲያብስ በእጆቹ ብቻ ያብሳል እንጂ ውሃው ካልሲው ላይ አይረጭም።
★ሲያብስ የእግሩ የላይኛው ክፍል ብቻ ያብሳል እንጂ የውስጥ እግሩን አያብስም አይነካካም።
💫ካልሲው የለበሰው ውዱእ ላይ ሆኖ ከነበረ ቀጣይ ውዱእ ሲያደርግ “እግሬን ማጠብ አለብኝ” ብሎ ካልሲውን ለማውለቅ መቸገር የለበትም።
💫ካልሲውን ካበሰበት በኋላ ቢያወልቀው ውዱውን አይበላሽበትም አይፈርስበትም; ካልሲው ካበሰ በኋላ ቢያወልቀውም ባደረገው ውዱእ መስገድ ይችላል።
💫አንዴ በለበሰው ካልሲ ማበስ የሚችለው;
★መንገደኛ ለ3 ቀናት ማበስ ይችላል።
★መንገደኛ ካልሆነ ግን ቀንና ማታ (24 ሰዓት) ነው ማበስ የሚችለው።
💫የማበሻ ጊዜው የሚቆጠረው ካልሲው ከለበሰው ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
ለምሳሌ፦
ሰኞ ቀን ዙሁር ላይ ውዱእ አድርጎ እግሩን ታጥቦ ካልሲውን ቢለብሰው። እስከ መግሪብ ድረስ ውዱእ ሳይፈታ ቆየና መግሪብ ላይ ውዱእ ተበላሽቶበት ውዱእ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ቢያብስ; ይህ ካልሲ የማበሻ ጊዜው መቁጠር የሚጀመረው ከመግሪብ ሰዓት ጀምሮ ነው። በዚህም መሰረት ማክሰኞ ቀን ልክ የመግሪብ ወቅት ሲደርስ በዚህ ካልሲ ላይ ማበስ አይችልም ያበቃል ማለት ነው።
★ልብ ይበሉ
ይህንኑ ሰውዬ ማክሰኞ መግሪብ ከመድረሱ በፊት ውዱእ አድርጎ በካልሲው ላይ አብሶ ከሆነና ይህንን ውዱእ መግሪብም ላይ ካልተበላሸበት የካልሲው ማበሻ ጊዜ በማለቁ ብቻ ውዱኡውን አይበላሽበትም። ማበስ አይችልም እንጂ የነበረው ውዱእ እስካልፈታ ድረስ መስገድ ይችላል።
★መንገደኛ የሆነውም ሰው ምሳሌው አሁን ባየነው መልኩ ከለበሰበት ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ቀናቶች ይቆጠሩለታል።
★★★★★★★★★★★★
📚ጀሪር ቢን ዐብደላህ አልበጀሊ ባስተላለፈው;
«رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم بالَ، ثم توضأَ ومسحَ على خُفَّيْهِ»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ተፀዳድተው ውዱእ ሲያደርጉ ሁፋቸው ላይ ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።» ይላል።
📚ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ ባስተላለፈው;
«كنت مع النبي صلى الله عليه وسلم في سفر، فأهويت لأنزِع خفيه، فقال: (دَعْهُما، فإني أدخلتهما طاهرتين»
«ከአላህ መልእክተኛﷺ ጋ በጉዞ ላይ ነበርኩኝ, ሁፋቸውን ላወልቅላቸው ዝቅ ስል "ተዋቸው ውዱእ ላይ ሆኜ ነው ያደረኳቸው" አሉኝ።» ይላል።
📚ሹረይህ ቢን ሃኒ የማበሻ ጊዜው ምን ያህል እንደ ሆነ ልጠይቃት ወደ ዓኢሻ ስሄድ "ወደ ኢብን አቡ ጧሊብ ሂድና ጠይቀው, እሱ ከረሱልﷺ ጋ ጉዞ ያበዛ ነበር" አለችኝ። ሄጄ ስጠይቀው;
«جعل رسول الله صلى الله عليه وسلم ثلاثة أيام ولياليهن للمسافر، ويومًا وليلة للمقيم»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ለመንገደኛ ሶስት ቀናቶች ከሌሊታቸው ጋ ሲያደርጉ ቋሚ ለሆነ ሰው ደግሞ ቀንና ሌሊት አደረጉለት አለኝ።» ይላል።
📚ሰፍዋን ቢን ዓሳል ባስተላለፈው;
«كان رسول الله صلى الله عليه وسلم يأمُرُنا إذا كنا سَفْرًا [مسافرين] أن لا ننزِع خِفافنا ثلاثة أيام ولياليهن، إلا من جنابة، ولكن من غائط وبول ونوم»
«መንገደኛ በሆንን ጊዜ የአላህ መልእክተኛﷺ ለሶስት ቀናት ሁፋችን እንዳናወልቅ ያዙን ነበር; ጀናባ ከሆንን በስተቀር; በውሃ ሽንት፣ በሰገራ ወይም በእንቅልፍ [ውዱእ ከፈታን ግን አናወልቅም]።» ይላል።
📚ዓልይ አላህ ስራውን ይውደድለት እንዲህ ይላል ነበር;
«لو كان الدين بالرأي لكان أسفل الخف أولى بالمسح من أعلاه، وقد رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يمسح على ظاهر خفيه»
«ዲን በሰዎች ዕይታ (ራዕይ) ቢሆን የሁፍ የታችኛው ማበስ የላይኛው ከማበስ የበለጠ የተገባ ይሆን ነበር; በእርግጥም የአላህ መልእክተኛﷺ በላይኛው ሁፋቸው ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።»
★★★★★★★★★★★★
💚ልብ ይበሉ‼️
💫ያለንበት ወቅት በጣም ብርዳማ ከመሆኑም ጋ አብዘሃኛው ሙስሊሞች እንዴት ማበስ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ስለ ማያውቁ ማበስ እየቻሉም ካልሲያቸውን አውልቀው እግራቸው ለማጠብ ሲደክሙ ይስተዋላሉ። በመሆኑም ይህንን አላህ ገር ያደረገው አማራጭ አውቀው እንዲጠቀሙ ሼር አድርጉላቸው።
Repost from የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪወች ጀመዓ ቻናል
✍ ይድረስ ሁለት ፊት ላላቸው አጨብጫቢዎች፦
አንዳንዴ እኛ ጥሩ ነው ብለን ያሰብነው ነገር በፍፁም መልካም የማይሆንበት አጋጣሚ አለ
ለምሳሌ በሂወትህ ውስጥ ጥሩ ቦታ ልትሰጠው ያሰብከውን ሰው አሏህ ግን ላንተ መልካም እንዳልሆነ ስለሚያውቅ ንቅል ያደርግልሃል።
አላህ እኮ ሁሉን አዋቂ የሆነ ጌታ ነው። የሰው ልጅን ብንዋሽ አላህን መዋሸት አንችልም ።የሰው ልጆችን ብናታልል አላህን ማታለል አንችልም።ለሰው ልጆች የኛን ማንነት ባናሳይ በመልካም ማንነታችን ብንቀርብ አላህ ግን የኛን ትክክለኛ ማንነት ፍንትው አድርጎ ያውቃል‼️‼️‼️
👉 ለሰው ስንቀርብ መልካም መስለን የተማርን የቀራን የሓፈን ... ወዘተ .... እውነታው ሲታይ በተቃራኒው ወንድሜ ሆይ‼️ እህቴ ሆይ‼️ ይህ ውሸት እና ማጭበርበር አንድ ቀን ተነቅቶብን መዋረዳችን የማይቀር እውነታ ነው።
ሲቀጥል፦ ሙስሊም አይዋሽም ብለዋል ነብዩ ﷺ ታዲያ ለአንዳንድ ሰዎች ለዛው አዋቂነን ከሚሉ አንዳንድ አካላት የለለ የውሸት ቀደዳ እናያለን አይኑን ያፈጠጠ ጥርሱን ያገጠጠ ውሸት ታዲያ ምኑ አዋቂነት ነው?!?!
👉 አንዳንዶች በሂወትህ ሊጫወቱ እንደ አማራጭ ድልድይ አድርገው ይይዙሃል።ወዳንተ ሲመጡ ላንተ ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ይነግሩሃል።ጉሮሯቸው እስኪቀደድ ድረስ ከዛ በተቀራኒው ካንተ ሲለዩ ከሌላ ጋር ሲሆኑ ግን የነሱን ምንነትን በደንብ ያራምዳሉ። አጅብ ነው!!!አላህን እናታልለው ይሆን👈
አንተን በመጥፎ የሚያነሱ ላንተ ምንም ቦታ እንደለላቸውና ስምህን ለማጉደፍ አንደኛ ፊት ለፊት ተሰላፊዎች እነሱን ሁነው ታገኛቸዋለህ።
ምን አይነት ጭራቅነት ነው ይሄ ባህሪ ???
ማንኛውም ሰው ሁሌም ራሱን ነው መምሰል ያለበት እንጅ ሌላ ሰው መምሰል የለበትም ይህ ራስን አለማወቅና በራስህ ማንነት ማፈር ነው የሚሆነው.....
🔶 የራሷ እያረረባት የሰውን ታማስላለች እንደሚባለው ነው ነገሩ...
👉 እነዝህ ሰዎችን በብዙ መንገድ ላንተ ያለህን ቦታ ለማወቅ ስትፈትናቸው ምን አለፋህ ወንድሜ አመድ ይሆናሉ ነው የምልህ።አንተ የምታሰባቸውና እነሱ ላንተ ያላቸው ቦታ ሰማይና ምድር ሁኖ ታገኘዋለህ።
ስለዚህ የምትቀርባቸውን ሰዎች አስተውል ወደሂወትህ የምታስገባቸውን ሰዎች በደንብ ፈትሽ.......
ምንም ሁን ምንም ሰውን ስትቀርብ በራስህ ባህሪ መሆን አለበት አዛኝ ሳትሆን አዛኝ መስለህ, እውነተኛ ሳትሆን እውነተኛ መስለህ ሳትሓፍዝ ሓፍዣለሁ ብለህ,ወዳጅ ሳትሆን ወዳጅ መስለህ, ልጅ ሳትሆን እድሜህን ዋሽተህ, ዝርክርክ ያሉ ሁነው እንደ ቁጥብ ሲያጫውታቸው,👉እረ ስንቱን ልጥቀስ....
ሙስሊም አይዋሽም ሲባል ነበር የምናውቀው ዘንድሮ ግን የውሸት ቋት የሆነን ሰው በአይኔ አሳየኝ..ዓጅብ አላህ ይሰትረኝ ይሰትረን።
✍ አቡ ዑሠይሚን
http://t.me/abuUseyminabdurehman
http://t.me/abuUseyminabdurehman
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
አቡ ሙዓዝ ሆይ! መልስ መስጠት ከቻልክ እጠይቅሃለሁ፦
~ ክልክል የሆኑ ነገሮችን ለመፈጸም የሚያስገድደው አጣብቂኝ ችግር (ዶሩራ) በእጅ፣ በአንገት፣ በእግር መቆረጥ ወይም በሞት ብቻ የተገደበ ነውን? ይህንን ማን አለህ? ከእውነተኞቹ ከሆንክ ማስረጃህን አምጣ። ከቁርአንና ከሱና የተቀዳውንና የታወቀውን "አስገዳጅ ሁኔታዎች ክልክል ነገሮችን ያስፈቅዳሉ" የሚለውን የሸሪዓ ደንብ (ቃዒዳ) በእጅና በእግር መቆረጥ ወይም በግድያ ብቻ የገደበው ማን ነው?
~ አቡ ሙዓዝ ሆይ! ዑለማኦች 'አድ-ደሩሪያት አል-ኸምስ' ብለው የሚጠሯቸውን አታውቅምን? ለመሆኑ ዲናዊ ጉዳት 'አደጋ' ክልክል ነገሮችን ለመፈጸም ከሚያስፈቅዱት ውስጥ አንዱና ዋነኛው አይደለምን? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ደዕዋችንን ለማስጠበቅና የነቢያዊ ፈለግ ምንጭ፤ የብዙ ሺህ ሱንዮች የዐይን ማረፊያ የሆኑትን የሰለፊያ መስጂዶችና መርከዞችን ለመጠበቅ መቀመጥ እግርህ ወይም እጅህ እንዳይቆረጥ ፈርተህ ከእነርሱ ጋር ከመቀመጥ የተሻለና በላጭ አይደለምን?
~ እንዲሁ በቅጡ ሳናስተነትን ከመቀባጠራችን በፊት የራሳችንን አቅምና የአስተሳሰብና የግናዛቢያችንን ምጥቀትና ጥልቀት ማወቅና መፈተሹ ለእኛ የተሻለ ነው። እንዲህ ተብሏልና፦ "ዓዋቂ ማለት መልካምን ከክፉ የሚለይ አይደለም፤ ይልቁንም ከሁለት መልካም ነገሮች የተሻለውን፣ ከሁለት ክፉ ነገሮች ደግሞ አነስተኛውን የሚያውቅ ነው። የሸሪዓ መሰረቱም ጥቅምን ማስገኘትና ማሟላት፣ ጉዳትን ደግሞ ማስቀረትና መቀነስ እንደሆነ የሚያውቅ ነው። ይህ ካልሆነ ግን በመስራትና በመተው መካከል ያለውን ሚዛን የማይጠብቅ ሰው፤ ግዴታዎችን ሊተውና የተከለከሉ ነገሮችን ሊፈጽም ይችላል፤ ይህንንም እንደ ጥንቃቄና ደግነት (ወረዕ) ይቆጥረዋል።"
7. በመጨረሻም እንዲህ ትላለህ፦ "እስኪ ንገሩኝ፤ ከእኛ መካከል ትክክለኛው ማን ነው? ሰዎችን ለስሜት ባለቤቶች ፍቅር እንዲኖራቸውና ለእነርሱ እንዲለዝብ የሚያነሳሳው? ወይስ እንደ ቀደምቶች ከቢድዓ ባለቤቶች እንዲጠነቀቁና ከመንገዳቸው እንዲርቁ የሚያነሳሳው?"
እልሃለሁ፦ "ትክክለኛው መልስ ያለምንም ጥርጥር ሁለተኛው ነው። ነገር ግን ሰዎችን የስሜት ባለቤቶችን በመውደድ ላይና በመለዘብ ላይ ያነሳሳው ማን ነው? ይህንን የምታደርግ ከነበርክ አንተ በእርግጥም የጠፋህ 'ሙመዪዕ' ነህ፤ ከእርሱ መመለስህም ላንተ በላጭ ነው። አንተ "አብሬያቸው ነበርኩ" የምትላቸው ሰለፊዮች ግን ከምትለው ነገር በጣም የራቁ ናቸው። ይልቁንም ከእነርሱ ዘንድ የሚታወቀው ከቢድዓና ከባለቤቶቿ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ መስጠት ነው።
ታላቅና የተከበረው የዓርሽ ባለቤት የሆነው አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራንና ከእርሱ ጋር እስከምንገናኝበት ቀን ድረስ በእርሱ ላይ እንዲያጸናን እለምነዋለሁ። እርሱ የዚህ ባለቤትና በእርሱም ላይ ቻይ ነውና።
በታናሹ ወንድምህ አቡ ዑምራን አል-አሰሪ ተፃፈ።
ትርጉም: ሙሐመድ አያሌው
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
#ይህ መልእክት ወደ አማርኛ ሲመለስ የሚከተለውን ይመስላል፦
~ ይድረስ ለኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሆይ! በቻናልህ የለጠፍከውን አዋጅ አንብቤ የሚከተለውን ላቀርብልህ ወደድኩ፦
1. እንዲህ ብለሃል፦ "ወደ ሐቅ መመለስን የለገሰኝን አላህ አመሰግነዋለሁ። በዲን ጉዳዮች እና በሰለፊያ መርሆች ላይ ከነበረብኝ የ'ተምዪዕ' (ለዘብተኝነት) እና የመዘናጋት አካሄድ እውነተኛ ተውበት ማድረጌን አውጃለሁ። አላህ ያለፈውን ስህተቴንና ጥፋቴን እንዲምረኝ እለምነዋለሁ።"
እልሃለሁ:- "ቀደም ሲል ራስህን እንደገለጽከው መንገድ የሳትክ ሙመይዕና በሰለፊያ መርሆች ላይ ቸልተኛ ከነበርክ በእርግጥም ለተውበት ተገቢ ነህ። እኛ ሰለፊዮች ግን -ለአላህ ምስጋና ይገባውና- በቻልነው መጠን በሰለፊያ መርሆች ላይ አንድም ቀን አላለሰለስንም፣ አልተዘናጋንምም። ነገር ግን ከለተሚዮች በኩል የሚመነጩ ብይኖችን አለመቀበላችንን ከሆነ 'ተምዪዕ' እና 'መዘናጋት' ብለህ የምትጠራው ይህ ግልጽ ስህተት ነው። ካልሆነማ አንተ ራስህ እንደምታውቀውና ውስጥህ እንደሚያረጋግጠው እኛ አልተዘናጋንም፤ ይልቁንም የነቢዩንﷺ መንገድ በተቃረኑት በሱፊዮች፣ ኢኽዋኒዮች፣ ሱሩሪዮች፣ ሙመዪዓዎችን፣ የተክፊሪያ ሐዳዲዮች፣ የለተሚያ ሐዳዲዮችና ሌሎችም ላይ ሁሉ መልስ (ረድ) ከመስጠት ቦዝነን አናውቅም። ባይሆን ይህን የምናደርገው ከቁርአንና ከሱና በተቀዳ ዘዴ (ኡስሉብ) እንጂ በሐዳዲዮች ስልት አይደለም።
2. እንዲህም አልክ፦ "እንዲሁም ደግሞ የቀደምቶችን መንገድ እና መርሆቻቸውን ወደ ማፍረስ የሚያደርሱ በሆኑ ከፊል መርሆች በተለይ ከአህሉስ-ሱና መርሆች አንዱ በሆነው በ 'ባቡል ወላዕ ወል በራእ' (ለአላህ ብሎ መውደድና መጥላት ዘርፍ) መሸንገሌንና መታለሌን አምናለሁ፤ አረጋግጣለሁም። እኔና አምሳያዎቸ በጥቅል መልኩም ይሁን በተናጥል ደረጃ ግልጽ ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ መስጠት በሚገባቸው ቦታዎች ላይ ዝም በማለታችንና በመዘናጋታችን ተሸንግለናል።"
ቀደም ሲል እንዳልኩህ እልሃለሁ፦ "በጠቀስካቸው ነገሮች የተሸነገልክ፣ የሰለፎችን መንሀጅና መርሆች አፍራሽ፣ እንዲሁም ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ቦታዎች ዝም የምትልና የምትዘናጋ ከነበርክ፤ እውነት ነው ሞት ከመምጣቱ በፊት ወደ ቅናቻው መመለስህ የተገባ ነው። እኛ ሰለፊዮች ግን ተሸንግለን መንገድ አልሳትንም። ነገር ግን ተማርንና አወቅን እንጅ። መርሆችንም አላፈረስንም። የሰለፎችን መርህ አፍርሰን ከዲን ውጭ ከመሆን በአላህ እንጠበቃለን። ነገር ግን በእኛ ብልሃትና ሃይል ሳይሆን የአላህ ማግራት ሁኖ (መርሆችን) ገነባን፣ አስተካከልን፣ በእነርሱም ላይ ተጓዝን፤ በአላህ ፈቃድ በእነርሱ ላይ እንሞታለን። ማድረግ እየቻልን ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ብዙ ቦታዎች ይቅርና አንድ ቦታ ላይ እንኳ ዝም አላልንም።
ነገር ግን እጠይቅሃለሁ፦
~ የሰለፎችን መንሀጅና መርሆች ወደ ማፍረስ የሚያመሩትና አንተ የተታለልክባቸው እነዚያ 'ቃዒዳዎች' (ደንቦች) ምንድን ናቸው?
~ ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ቦታዎች ዝም ያሉትና የተዘናጉት እነዚያ 'አንተን መሰል' ሰዎችስ እነማን ናቸው?
3. እንዲህም ብለሃል፦ "ቀደም ሲል ከቢድዓ ባለቤቶችና ፈር ከለቀቁት ጋር ከመቀመጥ እንዲሁም እነርሱን ከመስማት በሚገባ እናስጠነቅቅ ነበር፤ ነገር ግን ከቆይታ በኋላ ዝም አልን፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አሰኘን። በዚህም የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን አቀለጥን ፣ ቀደም ሲል ኢኽዋኖች እንደገደሉት እኛም ልንገድለው ተቃርበን ነበር።"
እልሃለሁ፦ "ከቢድዓ ባለቤቶችና ከፈር ከለቀቁ ጠማማዎች ጋር መቀመጥንና ለእነርሱ ጆሮ ከመስጠት ማስጠንቀቅን ትተህ ከነበርክ፣ እንደዚሁም ዝም ብለህና ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አሰኝተህ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን አላልተህና ልትገድለው ተቃርበህ ከሆነ፤ ይህ ያንተ ብቻ ግልጽ ስህተትና ገሃድ የወጣ ጥመት ነው። እኛ ግን በአቅማችን ልክ ከቢድዓ ባለቤቶችና ከጠማማዎች ጋር ከመቀመጥና እነርሱን ከመስማት እያስጠነቀቅን ነው። ዝም አላልንም፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አላሰኘንም፣ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅንም አላቀለጥንም። በምንለው ነገር ላይ አላህ ምስክር ነው።
በድጋሜ እጠይቅሃለሁ፦
~ እነዚያ ከአንተ ጋር የነበሩት፣ ዝም ያሉ፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም ያሰኙ፣ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን ያላሉና ሊገድሉት የተቃረቡት እነማን ናቸው?
4. እንዲህ ብለሃል፦ "እኔ ዛሬ እውነቱ ከተገለጸልኝ በኋላ፣ ቀደም ሲል ወደ ነበርኩበት የመጀመሪያው አቋሜ ከመመለስ ውጭ ሌላ አላደረግኩም። ይህም ከቢድዓ ባለቤቶች መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ፣ ከእነርሱ ጋር አለመቀመጥና እነርሱን አለመስማት ነው፤ ይህንንም ያደረግኩት ቀደምቶች -አላህ ይዘንላቸውና- የነበሩበትን መንገድ ለመያዝ ነው።"
በአጭሩ የምልህ፦ "እኛ -ችሮታም ይሁን ልግስና 'መመፃደቅ' ለአላህ ነውና- አቋማችን፤ ከዚህ ቀደምም ይሁን ወደ ፊት -በአላህ ፈቃድ- ከቢድዓ ባለቤቶች መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ፣ ከእነርሱ ጋር አለመቀማመጥና እነርሱን አለመስማት፣ እንዲሁም የሰለፎችን መንገድ አጥብቆ መያዝ ነው። ነገር ግን ብይኖችን ያለ በቂ ማስረጃ አንቀበልም፣ ለማንም ጯሂ ቦታ አንሰጥም፣ የሐዳዲዮችም ጩኸት አያስደነግጠንም፤ እነርሱ ወሰን እንዳለፉት እኛ ወሰን አናልፍም።
5. እንዲህ ብለሃል፦ "በአላህ እምላለሁ! እኔ እንደተገነዘብኩት ብትገነዘቡ ኖሮ፤ የኛ ጉዳይ በዚህ አቋም ከቀጠለ "ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር አብሮ መስራትና ግንኙነት ማድረግ ይቻላል" በማለታችንና አንዳንዴም ከእነርሱ ጋር እንዳንቀመጥ የሚከለክሉንንና የሚያስጠነቅቁንን ሰዎች በመተቸት፤ ቢድዓንና ባለቤቶቹን እንዲወዱ በማድረጋችን ሰዎችን እንደጎዳን ታውቁ ነበር።"
እልሃለሁ፦ "ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ የምታደርግ ከነበርክ፣ ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር ግንኙነት ማድረግ በደፈናው ይቻላል የምትል ከነበርክና ከእነርሱ ጋር እንዳይቀመጡ የሚከለክሉትን የምትነቅፍ ከነበርክ፤ ይህ ካንተ ጥመቶች ውስጥ አንዱ ነበር ማለት ነው። አዎ! በዚህ መንገድህ ብትቀጥል ኖሮ አንተን የሚሰሙትን ትጎዳ ነበር። እኛ ግን ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ አላደረግንም። -እኛ ይህንን እንድንሰራ ከማድረግ አላህ የጠራ ነው- ይልቁንም እኛ -ቅርቡም ሩቁም ዘንድ እንደሚታወቀው- ከሁሉም የቢድዓ አይነቶችና ከባለቤቶቿ እናስጠነቅቃለን። ከእነዚህ ሰዎች ጋር ሸሪዓው ባስቀመጣቸው ገደቦች እንጅ ግንኙነት ማድረግ አንድም ቀን ይቻላል ብለን አናውቅም። ከዚህ የሚከለክልንም አልነቀፍንም፤ ነገር ግን ስህተት በሰራ ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ወሰን የሚያልፉትን በእውቀትና በግልጽ ማስረጃ መለስን እንጅ።
አሁንም በድጋሜ ልጠይቅህና፦
~ በዚህ አቋምህ ላይ ከአንተ ጋር የነበረውና ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ ያደረገው ማን ነበር?
~ ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር ግንኙነት ማድረግን በደፈናው የፈቀደውስ ማን ነበር?
~ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ የሚከለክሉትንና የሚያስጠነቅቁትን የተቸውስ ማነው?
6. እንዲህ ብለሃል፦ "ይህ አካሄድ አጣብቂኝ (ዱሩራ) ነው። ስለሚባለው አባባል የምለው፦ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር መቀመጥን ብንተው እጃችንን፣ አንገታችንን ወይም እግራችንን የሚቆርጥብን ወይም የሚገድለን አለን?! ይህ ቸልተኝነትና መዘናጋት ብቻ ነው። አላህ ይቅርታውንና ደህንነትን እንዲሰጠን እንለምነዋለን።"
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
فأسألك يا أبا معاذ: إن كنت مجيبا:
~ هل الضرورة الملجئة إلى ارتكاب المحظور منحصرة في قطع الأيدي أو الأعناق أو الأرجل، أو القتل؟ من قال لك هذا؟ هات برهانك إن كنت من الصادقين، من الذي قيد لك القاعدة المقررة المستمدة من الكتاب والسنة قاعدة "الضرورات تبيح المحظورات" بقطع الأيدي والأرجل أوالقتل؟
~ أما تدري يا أبا معاذ ما يسميها العلماء بالضروريات الخمس؟ أليس الضرر الديني أولى وأحرى ما تستباح به المحظورات؟ أليست المجالسة مع هؤلاء لأجل حماية دعوتنا ووقاية مساجد ومراكز السلفيين التي هي منبع منهاج النبوة، وقرة عيون آلاف الألوف من أهل السنة خيرا من مجالستهم خوفا على قطع رجلك أو يدك؟
~ وأيضا أن نعرف قدرنا ومدى فكرتنا خير لنا من نتفوه بادي الرأي، فإنه قد قيل "ليس العاقل الذي يعلم الخير من الشر، وإنما العاقل الذي يعلم خير الخيرين وشر الشرين، ويعلم أن الشريعة مبناها على تحصيل المصالح وتكميلها، وتعطيل المفاسد وتقليلها، وإلا فمن لم يوازن ما في الفعل والترك، فقد يدع واجبات ويفعل محرمات، ويرى ذلك من الورع،"
7. وأخيرا قلت: "وأخبروني: من المصيب منا؟ أَمَن يحثّ الناس على مودة أهل الأهواء والتساهل معهم، أم من يحثّ على الحذر من أهل البدع والبعد عن طرائقهم كما كان عليه السلف؟"
فأقول: الجواب المتعين هو الثاني بلا شك، ولكن من الذي حث الناس على مودة أهل الأهواء والتساهل معهم؟ إن كنت تفعل هذا فأنت مميع تائه حقا، فرجوعك منه خير لك، أما السلفيون الذين تزعم أنك كنت معهم فهم بعيدون مما تقول، بل المعروف منهم التحذير العلمي من البدع وأهلها،
أسأل الله العظيم رب العرش الكريم أن يهدينا الصراط المستقيم، ويثبتنا عليه، إلى يوم لقائه، إنه ولي ذلك والقادر عليه،
كتبه أخوك الصغير أبو عمران الأثري
=
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ إلى أستاذ أبي معاذ وفقه الله
يا أستاذ أبا معاذ! قد قرأت ما أعلنته فى قناتك فأردت أن أوجه لك ما يلي:
1. قلتَ "فإني أحمد الله تعالى الذي منّ عليّ بالرجوع إلى الحق وأُعلن توبتي الصادقةَ مما كنتُ عليه من منهج التمييع والتساهل في أمور الدين وأصول السلفية وأسأل الله أن يغفر لي ما مضى من زلل وخطأ."
أقول: إن كنت من قبل كما وصفت نفسك بأنك مميع ضال ومتساهل فى أصول السلفية فأنت حقيق بالتوبة، ولكن نحن معشر السلفيين -ولله الحمد- ما ميعنا وما تساهلنا يوما ما من أصول السلفية قدر المستطاع، أما إن كنت تسمي عدم قبولنا للأحكام الصادرة من قِبل اللتميين تمييعا وتساهلا فهذا غلط بين، وإلا نحن كما تعلم أنت وتقر به نفسك ما تساهلنا، بل وما برحنا نرد على كل من خالف منهاج النبوة من الصوفية والإخوانية والسرورية والمميعة والحدادية التكفيرية والحدادية اللتمية ووو، ولكن على أسلوب مستمد من الكتاب والسنة لا على أسلوب الحدادية.
2. قلت: "أُقرّ وأعترف أيضا أني قد اغتررتُ ببعض القواعد التي تؤدي إلى هدم منهج السلف الصالح وأصولهم، لا سيما في باب الولاء والبراء، وهو أصل من أصول أهل االسنة . وقد اغتررت أنا وأمثالي حيث سكتنا وتساهلنا في مواطن يجب فيها البيان والتحذير. إما بالجنس وإمابالتعيين"
أقول: كما قلت لك آنفا إن كنت مغترا بما ذكرت وهادما منهج السلف الصالح وأصولهم وساكتا ومتساهلا فى مواطن يجب فيها البيان والتحذير فأنت جدير بالرجوع إلى رشدك قبل حضور أجلك، أما نحن -معشر السلفيين- فما اغتررنا فجهلنا، ولكن تعلمنا فعلمنا، وما هدمنا الأصول ونعوذ بالله من أن نهدم أصول السلف فنمرق من الدين، ولكن بَنَينا وأصلحنا وسرنا عليها بتوفيق من الله لا بحول منا ولا قوة وعليها نموت إن شاء الله، وما سكتنا فى موطن يجب البيان فيه والتحذير -ونحن قادرون- فضلا عن المواطن،
ولكن أسألك:
~ ما هي القواعد التي اغتررت بها التي تؤدي إلى هدم منهج السلف الصالح وأصولهم؟
~ ومن هم أمثالك الذين سكتوا وتساهلوا فى مواطن يجب فيها البيان والتحذير؟
3. قلت: "وكنا قبل نُحَذِّر من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم، كما ينبغي ولكن بعد حين سكتنا وأسكتنا الناس والطلاب فميعنا منهج الولاء والبراء وكدنا أن نقتله كماقتلته الإخوانية قبل"
فأقول: لك أيضا إن كنت تركت أنت التحذير من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم، كما ينبغي وسكت وأسكت الناس والطلاب فميعت منهج الولاء والبراء وكدت أن تقتله كما قلت فهذا خطأ واضح وضلال فاضح منك فحسب، أما نحن فما زلنا نُحَذِّر من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم حسب الطاقة، ما سكتنا ولا أسكتنا الناس والطلاب ولا ميعنا منهج الولاء والبراء، والله على ما نقول وكيل.،
وأسألك أيضا:
~ من الذين كانوا معك وسكتوا وأسكتوا الناس والطلاب وميعوا منهج الولاء والبراء وكادوا أن يقتلوه؟
4. قلت: "وإني اليوم، بعد أن تبيّن لي الحق، ما صنعتُ إلا الرجوع إلى موقفي الأول الذي كنتُ عليه من الحذر والتحذير من أهل البدع وعدم مجالستهم أو الاستماع إليهم، التزامًا بما كان عليه سلف الأمة رحمهم الله."
أقول: لك مختصرا نحن ولله الفضل والمنة موقفنا من قبل ومن بعد -إن شاء الله- هو الحذر والتحذير من أهل البدع وعدم مجالستهم والاستماع إليهم، والتمسك بما كان عليه السلف الصالح، ولكن لا نقبل الأحكام إلا بأدلتها، ولا نلتفت إلى كل ناعق وناهق، ولا يزعجنا صراخ الحدادية، فنغلو كما غلوا،
5. قلت: "ووالله لو تذكرتم كما تذكرتُ أنا لعلمتم أنه لو استمر أمرنا على هذا الموقف لأضررنا بالناس، حيث حببنا إليهم البدع وأهلها، حيث قلنا بجواز المعاملة مع الصوفية والإخوانية بل وربما جرحنا من ينهانا عن مجالستهم ويحذرنا من ذلك"
فأقول: إن كنت تحبب إلى الناس البدع وأهلها وقلت بجواز المعاملة مع الصوفية والإخوانية على الإطلاق كما هو المتبادر وجرحت من ينهى عن مجالستهم ويحذر من ذلك، فهذا أيضا من ظلاماتك وضلالاتك أنت، فنعم لو استمر أمرك على هذا لأضررت بمن يصغي إليك، أما نحن فما حببنا إلى الناس البدع وأهلها، -حاشا لله- بل -كما هو معلوم لدى القريب والبعيد- نحذر من أصناف البدع وأهلها، وما قلنا يوما ما بجواز المعاملة مع هؤلاء إلا بالضوابط المقررة ليس هذا موضع بسطها، وما جرحنا الناهي عن المجالسة والمحذر منها، ولكن رددنا بعلم وبصيرة على من يجاوز الحد في الرد على من أخطأ،
وأيضا أسألك:
~ من الذي كان معك فى موقفك هذا وحبب إلى الناس البدع وأهلها؟
~ ومن الذي أجاز المعاملة مع الصوفية والإخوانية إطلاقا؟
~ من الذي جرح من ينهى عن مجالسة أهل البدع ويحذر من ذلك؟
6. وقلت: "وأما القول بأن هذا المسلك ضرورة، فأقول: هل عندنا من يقطع أيدينا أو أعناقنا أو أرجلنا، أو يقتلنا لو تركنا مجالسة أهل البدع؟! إنما هو تهاون وتفريط، نسأل الله العفو والعافية"
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ፖለቲካዊ ስጋቶችን ጠዋት ማታ ማስጠንቀቁን ከተውሒድ ትምህርት በላይ የሚያደርግ ሰው ማስተማር ሳይሆን ቀድሩን አውቆ መማር ነው ያለበት። የሙታን አምልኮን፣ መሰረታዊ የዐቂዳ ልዩነትን አቅልሎ በመመልከት በጥቃቅን ነገሮች ልንለያይ አይገባም የሚል ሰው መሰረታዊ የግንዛቤ ችግር ያለበት ሰው ነው። ተውሒድ የሌለበት አንድነት ዋጋ የለውም።
ኢስላም፣ ኢማን፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ ከቃላት ያልፋል። በተግባር ያልተገኘ ላ ኢላሀ ኢለላህ ባዶ መፈክር ነው። ከአላህ በስተቀር የሐቅ አምላክ የለም ብሎ የመሰከረ ሰው ምስክርነቱ በተግባር መገኘት አለበት። ላ ኢላሀ ኢለላህ እያለ ለጭንቅ ለመከራው እነ ጫሊን፣ አብሬትን፣ ቃጥባሬን፣ ገታን፣ አባድርን፣ ደገርን፣ ወዘተ. የሚማፀን ከሆነ በምላሱ የሚናገረው ከልቡ የለም። ባዶ መፈክር ምን ይሰራል?! እነዚህ አካላት ደካማ ፍጡሮች ናቸው። ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉም ልጅና ዝናብ አይሰጡም። ቀጥታ ከአላህ መጠየቅ እየቻልክ ማርያምን፣ ገብረኤልን፣ ሚካኤልን እንደሚማፀኑ ኦርቶዶክሶች አትሁን። በኢስላም እየሱስን ብቻ ሳይሆን ሙሐመድንም ማምለክ አይቻልም። (ሰላም በሁለቱም ላይ ይሁን።)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 13/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢብኑ ተይሚያህ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦
ومن اعتادَ الانتِقام ولم يصبِر لا بُدَّ أن يقَع في الظُّلم
"በቀልን የለመደና የማይታገስ ሰው፣ በደል ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።"
[ቃዒደህ ፊ'ሶብር፡ 102]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ድርሻህን ነዉ የምትኖረዉ።ስለዚህ ባለፈዉ አትዘን ፣በሚመጣዉም አትስጋ፣ የጀሊሉ ዉሳኔ ሁሌም መልካምነዉ።
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
"ሁሉም ሰው የርሱ ታሪክ ባልሆነ ነገር ላይ ጠቢብ ነው።" [ዓባስ አል-ዒቃድ]
በመከራው ያልተገረፈ ሰው ስለትዕግስት ለማውራት ጠቢብ ይሆናል። የድህነትን ህይወት ያላየ ሰው ድሆችን ስለሀብትና ድህነት በመንገር ሊቅ ይሆናል። ፈተናውን ያልተቋደሰ ሰው ስለፅናት በመምከር አዋቂ ይሆናል። ሁሉም ባልደረሰበት የችግር ህይወትና ታሪክ ውስጥ ጉምቱ ጠቢብ ነው።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
