uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
907
Obunachilar
-224 soatlar
-127 kun
+4630 kun
Postlar arxiv
​«የወዲያኛዋን ዓለም (የአኼራን) እውነተኛ ሁኔታ የተረዳ ሰው፤ የዚህችን ዓለም መለያየት ቀላል ሆኖ ይታየዋል።» ይህ አባባል ከታላቁ እስላማዊ ምሁር ከኢብኑ አል-ቀይም (رحمه الله) «አል-ፈዋኢድ» የተወሰደ ሲሆን፤ የዚህችን ዓለም ጊዜያዊነት እና የወዲያኛዋን ዓለም (አኼራ) ዘላለማዊ ክብር የተገነዘበ ሰው፣ የዓለማዊ ነገሮችን እና መለያየትን በቀላሉ ሊያልፋቸው እንደሚችል ይገልጻል።

የሶሪያው ድል በየመን ይደገማል፣ ኢንሻአላህ። የራፊዷ እግር ይነቀላል። የኢራን ቀኝ እጅ ይቆረጣል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

​📢 ልዩ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም! ❝ሰይድ ቁጥብ ማን ነው? ለተሳሳቱ ውዳሴዎችና ማደናገሪያዎች የሚሰጥ ምላሽ❞ ​🎙 አቅራቢ፦ ኢብኑ ሙነወር 🗓 ቀን፦ ነገ ማክሰኞ ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀም
​📢 ልዩ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም! ❝ሰይድ ቁጥብ ማን ነው? ለተሳሳቱ ውዳሴዎችና ማደናገሪያዎች የሚሰጥ  ምላሽ❞ ​🎙 አቅራቢ፦ ኢብኑ ሙነወር 🗓 ቀን፦ ነገ ማክሰኞ ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ◇ የቀጥታ ስርጭት አድራሻ👇 t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

«ኢብኑ ሙነወር» አንተ ስለ ኢኽዋን ታስጠነቅቃለህ፡ ራቋቸው ብለህ ታስተምረናለህ፡ መረጃ ላይ ሆነህ መልስ ትሰጣለህ፡ መንጋው ከኢኽዋን ጋር እያለ ያማሀል፡ ጩኸታቸው ሁሉ ላንተ ይሰማሀል!? እንገረማለን እኛ በዚህ መሀል፡ በጉጉት በስስት እንጠብቅሀለን፡ ያለ ድንበር ማለፍ አወ እንወድሀለን፡ በአካል ቀርቤ እጂግ ስለማውቅህ፡ ንግግሬ አንድ ነው አሏህ ይጠብቅህ፡ በስሜት ቢሰክሩም ሐቅን በመታወር፡ ደጋግመው ቢጮሁም ሳምንታትና ወር፡ ሐቅ ላይ እስካለ ጀግና ነው ሙነወር፡ .....ኸላስ.... 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 "በሰሞኑ የሰይዪድ ቁጥብ ጉዳይ ከተመቸኝ ዛሬ ከመግሪብ በኋላ በድምፅ ለመግባት አስቤያለሁ" ብዬ ነበር። አሁን ላይ ስላልቻልኩኝ ከቻልኩ ምሽት 3:00 ላይ በቴሌግራም ቻናሌ ( https://t.me/IbnuMunewor ) በቀጥታ (live) ለማቅረብ እሞክራለሁ ኢንሻ አላህ።

"የኛዎቹ"ም ቢሞክሩት ~ ዛምቢያዊው ፓስተር ጀምስ ሳካራ "እንደ እየሱስ በሶስተኛው ቀን መቃብር ፈንቅዬ እነሳለሁና ከነ ህይወቴ ቅበሩኝ" በማለት ተከታዮቹን ባዘዘው መሰረት ከነ ነፍሱ ይቀብሩታል፡፡ ከሶስት ቀን በኋላ ቢመለሱ መቃብር ቆፍሮ አልወጣም። ሲቆፍሩ ጊዜ ሞቶ አገኙት። አሁን የዛምቢያ ፖሊስ ይህን ድርጊት የፈፀሙትን ማምሻውን ሰብስቦ ዘብጥያ ማውረዱ እየተዘገበ ነው፡፡ አጠፉ እንዴ ጎበዝ?! . እዚህ ላይ አንዲት እናት ከአመታት በፊት ደሴ ከተማ ውስጥ ስታወራ የሰማኋት ነገር ትዝ አለኝ። አንዷ ቅጥ ያጣ የሴቶች መብት ስብከት ሰለባ የሆነች ሴት አንዱን ገበሬ ከፍ ዝቅ አድርጋ ህዝብ ፊት ታከላፍተዋለች። "ኧረ እረፊ!" ብሎ ቢያስጠነቅቅ "እስኪ ጫፌን ንካኝ። ዛሬ እንደ ድሮው መስሎሃል!" እያለች ተንጣጣችበት። ያላሰበውን አሳሰበችው። አሁንም ቢያስጠነቅቅ በጣቷ ወደ ግንባሯ እየጠቆመች "እስኪ ይቺን ንካኝ" አለችው። ድንገት እራሱን መቆጣጠር አቃተውና በያዘው ዱላ የጠቆመችው ቦታ ላይ በዱላ መታት። "እሪሪይ!" ብላ መጮህ። "እየባሰ ሄደ! ምን አጠፋሁ ጎበዝ?! 'እዚህ ላይ' አለችኝ፣ እዚያው ላይ መታሁ። ቦታ ሳትኩ'ንዴ?" አለ ሰውየው። ፖሊስ መጥቶ "ምራ!" ሲለው እንደለመደው፡ "እየባሰ ሄደ!" ይላል። ፖሊሶች፡ "ጭራሽ ሊስፈራራን ነው ወይ 'እየባሰ ሄደ!' የሚለው?" ብለው ይቆጣሉ። ተሰብሳቢው ሰው፡ "ኧረ ሲያወራ ልምድ ሆኖበት እንጂ ለናንተ ብሎ አይደለም" ይላሉ። ፖሊሶች እያዋከቡ ወደ እስር ቤት ወሰዱት። . እና እነዚህ በፖሊስ የታሰሩ ዛምቢያውያን ጉዳይ ገርሞኝ ነው። የዚህን ጣጠኛ አጭቤ ነቢይ ትእዛዝ ፈፅመው ተአምር ሲጠብቁ ካቴና አጠለቁ። ጉድና ጅራት በስተኋላ ነው አሉ። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 2/2014) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ " ﻭﺃﻣّﺎ ﻛﺜﻴﺮٌ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﻓﻬﻮ ﻣﻊ ﺍﻟﺤﻖ ﺇﺫﺍ ﻭﺍﻓَﻖَ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻭﺿﺪّﻩ ﺇﺫﺍ ﺧﺎﻟﻒ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻓﻬﻮ ﻓﻲ ﺍﻟﺤﻘﻴﻘﺔ ﻣﺎ ﺍﺗَّ
ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ " ﻭﺃﻣّﺎ ﻛﺜﻴﺮٌ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﻓﻬﻮ ﻣﻊ ﺍﻟﺤﻖ ﺇﺫﺍ ﻭﺍﻓَﻖَ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻭﺿﺪّﻩ ﺇﺫﺍ ﺧﺎﻟﻒ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻓﻬﻮ ﻓﻲ ﺍﻟﺤﻘﻴﻘﺔ ﻣﺎ ﺍﺗَّﺒَﻊَ ﺇﻻ ﻫﻮﺍﻩ " "ብዙ ሰው ከስሜቱ ጋር ሲገጥምለት ከሐቅ ጋር ይሆናል። ከስሜቱ ጋር ሲቃረንበት ደግሞ በተቃራኒው ይሆናል። ይህ ማለት በተጨባጭ ስሜቱን ብቻ እንጂ የሚከተል አይደለም ማለት ነው።" [አት-ተዕሊቃቱል ባዚያህ ዐላ ሸርሒ አጥ-ጦ ሐዊየህ፡ 1253] = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የሀራም ፍቅር መነሻው «ስሜት»፣ መድረሻው ደግሞ «ክህደት» ነው። የአንዳንዱ ወንድ ውሸታም ናፍቆት ኒቃብሽን አስገልጦ የተሸፈነውን እስኪያይ ድረስ ብቻ ነው፤ በሀራም መንገድ ፊትሽን አይቶ ጉጉቱ ሲበ
የሀራም ፍቅር መነሻው «ስሜት»፣ መድረሻው ደግሞ «ክህደት» ነው። የአንዳንዱ ወንድ ውሸታም ናፍቆት ኒቃብሽን አስገልጦ የተሸፈነውን እስኪያይ ድረስ ብቻ ነው፤ በሀራም መንገድ ፊትሽን አይቶ ጉጉቱ ሲበርድ ግን «ይህች ናት እንዴ?» ብሎ ድራሹ ይጠፋል። እህቴ ሆይ! በሀራም መንገድ ኒቃብሽን የሚያስወልቅሽ ሰው የፈለገው የተከለከለውን ስሜቱን እንጂ አንቺን አይደለም። ውበትሽም ሆነ ክብርሽ የሚገባው በኒካህ ለሚያከብርሽ ለሀላልሽ ብቻ ነው! t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

ይልቁን አሁንም በድጋሜ ሳይመሽ ወደ አላህ ልትመለሱ ይገባል።አላህን ልትፈሩ ስሜትን ከመከተልና ከአጉል ኩራትና መኮፈስ እራሳችሁን ልታቅቡ  ይገባቹሃል ።  በመጨረሻም ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር እና ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ ከጥንት እስከዛሬ እናንተን በዉይይት ፣ በፁህፍ እና ተከታታይ እርምቶችን በመስጠት መክረችኋል እና ኩራታችሁን ወዲያ አዉልቃችሁ ጣሉና ምክሩን ተቀበሉ። ኩራት ለኢብሊስም አልበጀ!

ክፍል ሁለት፦ ‼️  من الذى جاء بمنهج جديد ؟  وبدل ما كان عليه ⭕️  አዲስን መንሃጅ በማምጣት ድሮ የነበረበትን የቀየረውና የተከረበተው ማነው ?       ከላይ በክፍል አንድ ለማውሳት እንደተሞከረው ከአመታት በፊት ከስድስት ሰዓት በላይ የወሰደ ዉይይት ተደርጎ ነበር። ይህ ዉይይት በዉስጡ አሁን ላለው ዉዢንብር መፍትሄ ስላለዉና  ማን ከነበረበትን አቋም እንደተከረበተ ማወቅ ስለሚያስችል  ስለ ዉይይቱ በአላህ እገዛ  የተወሰነ እንበል። የዉይይቱ አላማ ፦ 👉 በሰለፍዮች መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት መፍታት፦ የዉይይቱ ተሳታፊዎች፦ 1) ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ ያሲን 2) ኡስታዝ በሕሩ ተካ 3) ኡዝታዝ ዓሊ ሑሰይን 4) ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን 5) ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር 6) ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ 7) ኡስታዝ ሳዳት ከማል 8) ኡስታዝ ፉኣድ ሙሐመድ አወያይና ሽማግሌዎች ከባህር ዳር፦ 9)   ሸይኽ ሐሠን ገላዉ 10) ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ    እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መሻይኾች እና ኡስታዞች ዉይይቱን ሳዳምጥ መኖራቸዉን የተገነዘብኩት ሲሆን ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ።   አለመግባባት ከተፈጠረባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ ዋነኛው የሚከተለዉ ነው ፦ ከአንድ እስከ አራት የተጠቀሱት ኡስታዞች "የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ዋና ዋናዎቹ ሙብተዲዖች ናቸዉ" የሚል ብይን ሲሰጡ ከ አምስት እስከ ስምንት የተወሱት ደግሞ "ሙብተዲዖች አንልም ነገር ግን ስህተታቸዉን በማስረጃ እናጋልጣለን" ይላሉ። 👉 ዋናው የልዩነት አጀንዳ እነ ዓብዱል ሐሚድ የመርከዙን ሰወች መበደዓቸውና እነ ኢብኑ ሙነወር አለመበደዓቸው ሳይሆን። እነ ዓብዱል ሐሚድ በሰጡት ብይን እነ ኢብኑ ሙነወርን እኛ እንዳልነው በሉ በማለት "ኢልዛም" ማድረግ ይችላሉን? ወይስ ይህ የተብዲዕ ብይን "ኢጅቲሃዲይ" ( ጥረትን የሚያስተናግድ ) ነው? ለዚህ ወሳኝ ጥያቄና የልዩነት ነጥብ የጋራ ድምዳሚያቸው እንዲህ የሚል ነበር፦ "ከፊላችን የመርከዙን ሰዎች ሙብተዲዖች ናቸው ብንል ከፊላችን ደግሞ አይደሉም ብንል በመካከላችን የመንሃጅ ልዩነት አያመጣም። ምክኒያቱም ይህ አጀንዳ ኢጅቲሃድን የሚያስተናግድ ነውና" የሚል ነበር። በተለይ በተለይ አወያይ የነበሩት 👉ሸይኽ ሐሰን ገላው መስዓላው ኢጅቲሃዲይ እንደሆነ ከሰለፎች ምሳሌን እያጣቀሱ ደጋግመውና አስረግጠው ይናገራሉ። ለዚህም ትልቁ ማሳያ እና ማስረጃ የዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ መጨረሻ እንዲናገር እድል የተሰጠው ኡስታዝ ዓሊ ሑሴን የተናገረው የመደምደሚያ ሃሳብ ነው ይህንንም ንግግር የተናገረው ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር እንዲህ ብሎ ከተናገረ በኋላ ነበር፦ " በመጀመሪያ አላህ ከልፋታቹህ በላይ ይመንዳቹህ" ብሎ ለዉይይቱ ለመጡት ሰዎች ዱዓ ካደረገ በኋላ " 👉 ከአሁን በፊት ወደ ነበርንበት እንድንመለስ ከሚያግዙን ዉስጥ ስንወጣ የሚጠብቁን ሰዎች የት ደረሳቹህ ብለው ስለሚጠይቁን ለነሱ ምን ማለት እንዳለብን  ማውራቱ ወሳኝ ነው..... ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር  አውርቶ ከጨረሰ በኋላ "ዓሊ እጁን እያወጣ ነው እድል ስጠው ይላል" ። ኡስታዝ ዓሊ ሑሴንም  የዉይይቱ የመጨረሻ ሃሳብ ሰጭ ሲሆን እንዲህ ይላል ፦ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔴 ቃል በቃል ነው የሰፈረው   [[ ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም እኔ ሐቂቃ ዉጭ ያለውን ጉዳይ ማስተካከል ያስፈልጋል የሁላችንም አስተዋፅኦ ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ። ምንድን ነው አሁንም የደዕዋዉ ሂደት ላይ ስንሄድ ቅድም አዲስ አደረክ እንዳትሉኝ እንጂ ! እኛ ጋ የሆነ አቋም አለ እነሱ ዘንድ የሆነ አቋም አለ። ያ አቋም ኢጅቲሃዲይ ነው ብለን አምነንበታል ። እኛ ለምናደርገው አካሄድ ተደኹል መሆን (ጣልቃ መግባት) የለባቸዉም እነሱ በሚሄዱትም ተደኹል መሆን የለብንም ። ይህ በእናንተ እዚህጋ ባለው ወንድሞች የተስማማነው ነው ። ስለዚህ አሁን እንደ ጥያቄም ስንጠየቅ እኔ በራሴ ልለዉ የማስበው እነዚህ ሰዎች እንዴት ነው ? እናንተ ሙብተዲዖች ናቸው ስትሉ እነሱ አይደሉም የሚሉ ሰዎች ምናምን የሚለው ነገር ከተነሳ እኛ የነሱን አይመለከተንም እነሱ በዚህ ጉዳይ ላይ -ከመንሃጅ አስወጡ አላስወጡ - በዚህ ጉዳይ ላይ እንድትጠይቁን አንፈልግም ]] ሸይኽ ሐሰን ገላዉ በመካከል በመግባት (( መስኣላው ኢጅቲሃዲያ ነው በሉ )) ይላሉ። ዓሊ ሑሴንም እንዲህ ሲል ይቀጥላል ፦ [[ እኛ የራሳችን አቋም አለን። ከማስረጃ ከፈለክ ከኔጋ አውራ። ኢልያስ ሙብተዲዕ ነው ፤ ከመንሃጅ ወጡ አልወጡም ? ከኔጋ በመረጃ አውራ ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ኢብኑ ሙነወርን የሚመለከት ፉኣድን የሚመለከት ከሆነ ከእራሱ ጋ ሂድና አውራ። ስለዚህ አሁን ሙኻለፋዉ ላይ ተስማምተናል እነእርሱ (የመርከዙ ሰዎች) የተለያዩ ሙኻለፋ እንዳለባቸው ሁላችንም እናምናለን ]] ኢብኑ ሙነወር በመካከል እንዲህ ሲል ተናገረ (( ይህን ነጥብ የሚያጠናክር መጥቶ ጠየቀኝ አንድ ልጅ ተብዲዕ እያደረጉ ነው ሌሎች ለምን አታስቆሟቸውም? እናንተ ተብዲዕ ታደርጋላቹህ ወይ? አለኝ ። ከኛ ያየኸው ነገር አለ ወይ? አልኩት። እሽ የሚያደርጉትን ለምን አታስቆሙም አለኝ ። አናስቆምም ልክ ሊሆኑ ይችላሉ አልኩት .....)) ዓሊ እንዲህ ሲል ይቀጥላል ፦ [[ ስለዚህ አሁን በሆነው ነገር ምንድን ነው እኛና እነሱ (እነ ኢብኑ ሙነወር) አንድ ነን በነእርሱ (የመርከዙ ሰዎች) ላይ ረድ በማድረግ። እነእርሱን (የመርከዙን ሰዎች) ከመንሃጅ በማስወጣትና ሙብተዲዕ በማለት በአካሄድ ልንለያይ እንችላለን ። ግን ደዕዋው አንድ ላይ ነው ምናስኬደው ። በረድ ላይ አንድ ነን ፤ ተሕዚር በማድረግ ላይ አንድ ነን ስለዚህ በመካከላችን ልዩነት የለም የሚለውን ነገር በግልፅ እናወራለን .....አሁን በመካከል የነበረው ግርዶሽ ፈርሷል አልሐምዱሊላህ ......]] የዓሊ ንግግር በዚህ አለቀ። ሙሉ ቅጂው ከፈለግን ያሳለፍነው የኡስታዝ ዓሊ ሁሴን ንግግር 5:43  አምስት ሰዓት ከአርባ ሶስተኛው ደቂቃ ላይ እናገኘዋለን። የተከበራችሁ ውድ ሀቅ ፈላጊ ሰለፊይ ወንድም እህቶች ሆይ!፦ እንግዲህ ይህን ድምዳሜ እያሰፈረ  ያለው ዛሬ "መስዓላው ኢጅቲሃዲይይይ አይደለምምም" እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሚናገሩት ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ፊት ነበር። ታዲያ የዛኔ ለምን ዝም አሉ? የዛኔ ኢጅቲሃዲይ የነበረው ዛሬ እንዴት አይደለም ይባላል? ነው ወይስ የዛኔ በመንሃጅ ሰለፍ ጃሂሎችና እነርሱም #ሙመይዖች ነበሩ? እና አሁን ከ5/6 አመት ወዲህ ነው አለመሆኑ የተገለጠላቸው እንበል? ነው ወይስ የዛኔም ኢብኑ ሙነወር እና ፉኣድ በዛ መልኩ አጥበቀውና አጠንክረው "#ኢልዛም አለ የምትሉ ከሆነ በማስረጃ እዚሁ እናውራበት" ሲሏቸው "አላልንም ፤ አንልም" ሲሉ የነበሩት ሐቁን እያወቁ ደብቀው ነበር ዉሸት እያወሩ የነበሩት በውሸትም የተስማሙት  እንበል? 👉ነገሩን ከወገንተኝነት ፀድቶ ለተመለከተው ሰው እነ ዓብዱል ሐሚድና ከሱም ጋር ያሉት በመንሃጅ ስም የ "ካፈርኩ አይመልሰኝ"ን ጉዞ ነው የተናነቁት ። አንዴ ሙብተዲዕ ብለናል ብለናል በቃ!

👉 ከዳተኛው እና አጭበርባሪው የለተሞ መንጋ፡ {{ وَقُلْ جَاءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَاطِلُ إِنَّ ٱلْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا }}  الإسراء ٨١ [[ በልም "እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና ]] ኢስራእ 81 " النصحُ السديدُ لِمن نَحَا نحوَ ما نحا إليه عبدُ الحميد " "የተስተካከለ ምክር ዓብዱል ሐሚድ ያዘነበለበትን አቅጣጫ መሄድ ላሰቡ ሰዎች" ክፍል አንድ፦ "الخيانة بئست البطانة" 📌 "ከዳተኝነት"     ከዳተኝነት እንደሚታወቀው ሙስሊሞች ይቅርና ከሃዲያኖች የሚፀየፉት ቆሻሻ ተግባር ነው። ይሁን እንጂ አሁን አሁን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ እራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉና ለሱና ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አካሎች ላይ እንመለከተዋለን።        ይህን ስንል በማስረጃ ነዉ። ከአመታት በፊት ማለትም እነ ዓብዱል ሐሚድ  እነ ኢብኑ ሙነወርን "ሙብተዲዕ" ብለው ብይን ከመስጠታቸዉ በፊት ከነ ኢብኑ ሙነወር ጋር  ከስድስት ሰዓት በላይ የወሰደ "ጀልሰህ" (መቀማመጥ) አድርገው ነበር።     በዚህም "ጀልሰህ" የተለያዩ ርዕሶች ተነስተዋል። እናም ዉይይቱ ከተጀመረ በኋላ ከቤቱ የዉይይት ስርዓት አልታይ ሲልና ጫጫታ ፣ አለመሰማማት እና አንዱ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላኛው ጣልቃ እየገባ የዉይይት አደብ አልሰፍን ሲል ድምፃቸዉ እየተቀዳ ስለነበር ይህ ነገር ሪከርድ ተደርጎ ለህዝብ መዉጣቱ አስነዋሪ ስለሆነ ባይደረግ የሚል ሃሳብ ከከፊል ወንድሞች ተነሳ ከዚያም በዚህ የተነሳ (ሪከርድ መደረግ አለበት እና የለበትም በሚል)  ለረዢም ሰዓት ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻ ድምፁ መቀዳት እንደሌለበትና የተቀዳዉንም በመሰረዝ ተስማምተው  ዉይይቱን ቀጠሉ።    👉 አሳዛኙ ነገር ግን ከነ ኢብኑ ሙነወር በኩል የነበሩት ሰዎች ሀሉም ሪከርደሩን ቢዘጉም ከነ ዓብዱል ሐሚድ በኩል የነበሩ ሰዎች ግን የገቡትን ቃል በማፍረስ ድምፁን ቀድተው ይዘው ወጡ። ከትንሽ ጊዜ በኋላም "ከኛ ጋር የተቀዳ ድምፅ አለ" እያሉ ብቅ አሉ። ይህ ከዳተኝነት እንኳን ከሱና ኡስታዝና ሸይኽ ተብየ ይቅርና ከተራ ሙስሊም የማይጠበቅ የሙናፊቅ ተግባር ነው።     👉 እነዚህ ሰዎች ለኛ ማስረጃ የሚሆንበት ቀን ይኖራል ብለዉ ሪከርድ ቢያደርጉቱም አላሁ ተባረከ ወተዓላ ግን ነገሩን ገለበጠባቸውና ማስረጃዉ ለእነርሱ ሳይሆን በነእርሱ ላይ ሆነባቸው።     ለዚህም ትልቁ ማሳያ የዉይይታቸው ማጠቃለያና ጭብጥ ሃሰብ እንዲህ የሚል መሆኑ ነዉ። "የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ሰዎችን በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ ቢኖረንም መበታተን ፣ መለያየትና ከፊላችን ከፊላችንን #ሙብተዲዕ ማለት አይገባም።''     እንግዲህ ይህን የተስማሙበትን ቃል ያፈረሱና የነበሩበትን አቋም የቀየሩት እነ ዓብደል ሐሚድ ወይስ እነ ኢብኑ ሙነወር??? መልሱን ለአንባቢ እንተወው። ይህ "ከዳተኝነት" እንግዲህ ከነዚህ ሰዎች ከተገኙ ከባባድ እና ቀደም ካሉ ጥፋቶች ዉስጥ አንዱ ነው።

▣ በድብቅ የተቀዳው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ⌚️ 6:08:38 ሰዓት 📌 ለእውነት ፈላጊዎች ይቺ ፋይል በቂ መረጃና ማስረጃ ናት! ➩ አድምጣችሁ ፍረዱ ማን እንደተቀየረ ➩ ለተሚዮች የኡስታዞቻችሁ ውሸት ተገንዘቡ በምን እንደተስማሙ አድምጡ - እንደ መርከዙ ሰዎች ያሉ ሰዎች ላይ መለያየት ኢጅቲሓዲይ ነው - የመርከዙ ሰዎች ተብዲዕ ማድረግ አለማድረግ ሊያጣላን አይገባም ◍ O Altemiyun Listen the lies of your Teachers https://t.me/Menhaje_Selef/21 https://t.me/Menhaje_Selef/

ስለ ድግምት (ሲህር )የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች  ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት  ማዳመጥ ይችላሉ ➋➋ አከባቢ ሙሓደራወች
በተለይ ቋግሜን ሲህር መተት የሚሰራበት ነው በሀገራችን እና ጠተንቀቁ ራቁ ከዚህ ከባድ ወንጀል ከማስራትም ከመስራትም
ድግምት እና አደገኝነቱ ድግምት እና አህባሽ በሞባይል ጥንቆላ ድግምት ብይኑ እና ቅጣቱ ስለ ሲህር ድግምት እከፋ መጥቶል በከተማ በገጠር ከሲህር መጠንቀቅ ትዳር እዳትይዝ /እዳይዝ የሚደረግ ሲህር ሲህር ምንድነው ሲህር የሚሰራ ሰው መዘዙ ድግምት የሚሰራ ሰው ቅጣቱ የድግምት መድሀኒት የድግምተኝ ሰው መለያዎች ስለ ድግምት ጥያቄዎች አሲቂኙ ጠንቆይ አርባ ያሲን መቅራት ስለ ድግምት እና ጠንቆይ የሲህር አደጋዎች ወደ ጠንቆይ መሂድ ቃልቻ እና ጠንቆይ ጠንቆይ የሚፈራ ሰው ደፋር ጠንቋዮች

⛔️~ ዑዝር ቢል'ጀህል ~(ክፍል 8)    በሀገራችን የዑዝር ቢል'ጀህልን መስአላ መሸሸጊያ በማድረግ የተለያዩ ፊትናዎችን የሚያራግቡ አካሎች እንዳሉ ይታወቃል። ከነዚህ አላዋቂነት ከወለደው መጤ አስተሳሰብ ውስጥ፦ አንድ ሙስሊም ካለማወቅ ትልቁ ሽርክ ላይ ቢወድቅ ለምሳሌ ከአሏህ ውጭ ያለን አካል ቢለምን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሑጃ ሳይቆምበት ይከፍራል ይላሉ። እዚህ ጋ ቢቆሙ በበቃቸው ነበር።  ነገር ግን እነዚህ አካሎች ከዚህ አለፉና የዚህ አይነቱን አካል ልክ እንደነሱ ካፊር ብሎ ያልፈረደን ሰው በኢርጃእ ይወርፋሉ።   ከዚህም ከፍ በማለት የእነሱን ኢጅቲሃድ ስላልተቀበለ ብቻ እና ብቻ ምንም አይነት ኩፍር ተግባር ሳይገኝበት "አንተም ሑጃ ከቆመብህ በኋላ ካፊር ነህ" ይሉታል። ለዚህም የተንሻፈፈ ግንዛቤያቸው  .... من لم يكفر الكافر የሚለውን ቃዒዳ ያለቦታው ያጣቅሳሉ። በዚህ ዙሪያ -ኢንሻ አሏህ- በክፍል 09 የሙሐደራ ፕሮግራም እመለስበታለሁ። ሸይኽ ፈውዛን عقيدة الإمام محمد بن عبد الوهاب የተሰኘችውን ኪታብ ሲያስተምሩ እንዲህ ከሚለው የሸይኹ ንግግር ይደርሳሉ፦ وقوله: «وإني أكفر البوصيري لقوله: يا أكرم الخلق» ، -"ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲል ወሃብ በሳቸው ላይ የተቀጠፉባቸውን ውሸቶች እየዘረዘሩ ነው ያሉት - - ከዋሸብኝ ሰውየ ቅጥፈቶች ውስጥ - እኔ "ቡ'ሲ'ሪይን" «يا أكرم الخلق» በሚለው ስንኙ ምክኒያት ከሃዲ ብየ እንደፈረድኩበት -የተናገረው ውሸት ይገኝበታል-። ሸይኽ ፈውዛን ሸርሕ ሲያደርጉ (ሲያብራሩ) እንዲህ ይላሉ፦ " ... تكفير المعين كأن الشيخ ما يرى تكفير المعين، البوصيري كلامه كفر لقوله: يا أكرم الخلق ما لي من ألوذ به ... - يعني الرسول عليه الصلاة السلام - يا أكرم الخلق ما لي من ألوذ به سواك عند حلول الحادث العمم إن لم تكن في معادي آخذا بيدي فضلا وإلا أقل يا زلة القدم فإن لي ذمة منه بتسميتي محمدا وهو أوفى الخلق بالذمم إلى آخر ما قال فى البردة، هذ كفر، لكن الشخص قد يكون إنه ما بلغته الحجة، قد يكون ما بلغته الحجة متأول ما بلغته الحجة فلا يُكفّر حتى يقام عليه الحجة، البوصيري كأنه لم تقم عليه الحجة، الشيخ ما يدري عنه فلذلك لا يكفره لكن يقول هذا الكلام كفر، أما الشخص فإن كانت بلغته الحجة ولكنه أصر فهو كافر، أما إن كان ما بلغته الحجة فهو لا يُكفَّر لا بد من التفصيل، "ይህ የተለየን ሰው ከሃዲ ብሎ የመፍረድ ጉዳይ ነው። ሸይኹ የተለየን ሰው ካሃዲ ማለትን አያምኑም ይመስላል። ... - (ሑጃ እስካልተቆመበት ድረስ ማለት ነው ወደ ፊት የሚመጣው ንግግራቸው እንደሚጠቁመን) - ... ቡ'ሲ'ሪይ ንግግሩ ክህደት ነው። ምክኒያቱም እንዲህ ብሏልና፦ - ረሱልን ﷺ ነው እንዲህ የሚለው - # የፍጡሩ ሁሉ የበላይ የሆንኩት ሆይ!!... አዳራሽ የሆነ መከራ የሰፈረብኝ ጊዜ ካንቱ ውጭ ለኔ መጠጊያ ማን አለኝና!? # # የትንሳኤ ዕለት አንቱ በችሮታሁ እጀን ካልያዝኩኝ!! ወይ ጥፋቴ አወዳደቄ ከፋ ማለቴ አይቀርም # - እያለ ይቀጥላል - አል'ቡርደህ የተሰኘው ኪታቡ ላይ እንዲህ እያለ ይቀጥላል። ይህ ክህደት ነው። ነገር ግን የተለየ የሆነ አካል ሑጃ ያልደረሰው ሊሆን ይችላል። ማስረጃ ያልደረሰው (ሙተአዊል) ሊሆን ይችላል። -የዚህ አይነቱ አካል- ሑጃ እስኪቆምበት ድረስ ከሃዲ ተብሎ አይፈረድበትም። ቡ'ሲ'ሪይ ሑጃ ያልቆመበት ሊሆን ይችላል። ሸይኹ -ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲልወሃብ- ስለዚህ አካል አያውቁም። ለዚህም ሲባል ካፊር አላሉትም። ነገር ግን ይህ ንግግር ክህደት ነው ይላሉ። የተለየ አካል ግን ሑጃ ደርሶት በዛው ላይ ከዘወተረ ይህ አካል ከሃዲ (ካፊር) ነው። ሑጃ የደረሰው ካልሆነ ግን ይህ ከሃዲ አይባልም። -በዚህ ነጥብ ላይ- ለያይተን ማየታችን አይቀሬ ነው።" የፈውዛን ንግግር እዚህ አበቃ! 🔖 ስስ ዳሰሳ፦ ~ እነዚያን አካሎች በቃዒዳቸው መሰረት ስንዳኛቸው ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲል ወሃብ እና ሸይኽ ፈወዛን ከሙርጅአዎች ወይም ካፊሮች ናቸው ማለት ነው እነሱ ዘንድ።   ምክኒያቱም ከአሏህ ውጭ ነቢዩንﷺ የተጣራን አካል ሑጃ ስላልቆመበት ካፊር አንልም እያሉ ነውና። እናንተ ደግሞ ሽርክ የሰራን ሰው ሑጃ ባይቆምበትም ካፊር ሙሽሪክ ያላለ አካል ሙርጂእ ወይም ካፊር ነው እያላቹህ ስለሆነ በሉ ፈውዛን እና ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲል ወሃብ ላይ ፍርድ ስጡ ሃ!! ይህን የማትሉ ከሆነ ቃዒዳቹህ ብልሹ ነው ማለት ነው። ~ የሹቡሃ ካዝና የሆኑ አስተማሪ ተብየዎቿቹህ "ይህኮ ቅጣትን ነው የሚመለከተው" ሲሏቹህ በጭፍን ግርርር ብላቹህ ተከትላቹህ ከመጮህ ጠይቋቸው። ከነ መሰረቱ ቅጣት የሚባል ነገር የት ተወሳና!? ብላቹህ ጠይቁ!! እስልምና ክርስትና አይደለም ጠይቅ ይግባህና ትከተለዋለህ። ~ እንዲህ የሚለውን ንግግር ጆሯቹህን ከፍታቹህ አድምጡት እስኪ፦ فإن كانت بلغته الحجة ولكنه أصر فهو كافر، أما إن كان ما بلغته الحجة فهو لا يُكفَّر لا بد من التفصيل، የተለየ አካል ግን ሑጃ ደርሶት ነገር ግን በዛው ላይ ከዘወተረ ይህ አካል ከሃዲ (ካፊር) ነው። ሑጃ የደረሰው ካልሆነ ግን ይህ ከሃዲ አይባልም። -በዚህ ነጥብ ላይ- ለያይተን ማየታችን አይቀሬ ነው። ~ ፈውዛን እያወሩ ያሉት ካፊር ብሎ ስለ መፍረድ እንጅ ስለ ቅጣት አይደለም። ሸይኹምኮ በመሰረቱ ተዋሸብኝ ብለው ሲዘረዝሩ ቡ'ሲ'ሪይ ይቀጣል ብለሃል ሳይሆን ካፊር ትለዋለህ ብሎ ዋሽቶብኛል ነው እያሉ ያሉት። አዕምሯቹህን አሰሩት እንጅ ወገን!! ~ ነቢዩንﷺ መለመን ኸፊይ ሁኖ ይሆን እንዴ ሸይኽ ፈውዛን ይህን አካል ካፊር ለማለት ሑጃ መቆምን መስፈርት እያደረጉ ያሉት!? እናንተ ሑጃ ማቆም የሚያስፈልገው መስአለተል ኸፊያ ላይ ብቻ ነው'ማ የምትሉት!? ሽርክ ደግሞ ኸፋእ አይመጣበት! እናንተ ዘንድ! ዓጂጂጂብ ~ ቡ'ሲ'ሪይ ማለት حادث العهد ወይም ببادية بعيدة የሚኖር ሳይሆን አል'ቡርደህ የተሰኘን የሽርክ ኪታብ ያዘጋጀ ዓሊም ነኝ ባይ መሆኑ ይሰመርበት። አሏህ በሐቅ ላይ ይሰብስበን!! https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy

​ታላቅ የክረምት የምርቃት ፕሮግራም ለከተማችንና ለአካባቢያችን ማህበረሰብ በሙሉ የቀረበ ጥሪ! ​ << ኑር መድራሳ >> ​በ2018 ዓ.ም በኑር መድራሳ በቁርኣን እና በተለያዩ የሸ
​ታላቅ የክረምት የምርቃት ፕሮግራም ለከተማችንና ለአካባቢያችን ማህበረሰብ በሙሉ የቀረበ ጥሪ! ​ << ኑር መድራሳ >> ​በ2018 ዓ.ም በኑር መድራሳ በቁርኣን እና በተለያዩ የሸሪዓ ዕውቀቶች ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎቻችንን ውጤት የምናስመርቅበት ታላቅ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ​በዕለቱ ሁሉም የአካባቢያችን ማህበረሰብ፣ የተማሪ ወላጆች እና የእስልምና ዕውቀት ወዳጆች በሙሉ ታድመው የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል። ​📅 ቀን፦ እሁድ መስከረም 03/01/2018 ዓ.ል ⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ዙሁር 📍 ቦታ/አድራሻ፦ በቡታጅራ ኑር መድራሳ ግቢ ውስጥ ኡስታዞች፣ወላጆች፣ወጣቶች፣ታላላቅ አባቶችና እናቶች፣ የእስልምና ዕውቀት ወዳጆች እንዲሁም ማንኛውም የማህበረሰባችን አባል በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ በመገኘት የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።ጥሪው ሁልአቀፍ ነው! ​መድራሳችንን የማታውቁት ለማወቅ፦ ▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼ ▮ ◆ t.me/nurmedrsa/872 ◆ ▮ ▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲▲ ​

ያ ወዱድ!... ስሞችህን ልጥራ - ደግሜ ደግሜ ኢላሂ!... ልበልህ - ሁሌ ደጋግሜ ያረሂም! ልበልክ - ሁሌም እንዳቅሜ ፈውስ እንዲሆነኝ - ላልሻረው ህመሜ t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

📌حب الصحابة للخير قال الصحابي ابن عبّاس رضي الله عنهما: " إني لأمرُّ بالآية من القرآن فأفهمها، فأودُّ أن الناس كلهم فهموا منها ما أفهمُ". [فتح الباري، لابن رجب ٧٨/١] t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

«ኢኽዋን ማለት ይህ ነው ።» የሱዳን ምድር ፈርጥ የካርቱም ድምቀት ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂሪ ሀፊዞሁሏህ ስሟቸው ይህን ጀግና t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

«አሁን የመጡት መሪያችን (ዶር አብይ አሕመድ ዓሊ) የአባታቸውና የአያታቸው ስም የእኛ እምነት ስለማይመስል ከተመረጡ ጀምሮ እንቅልፍ አልወሰደንም» የአፓርታይዷ ቄስ የኢትዮጵያን መሪ ስሙ ከሱ ስም ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት፣ መለየት የለበትም ብሎ ያምናል😎 ለማንኛውም ከእነዚህ ጋር ነው እየኖርን ያለነው። እነዚህ በሙስሊሙ ላይ በአከባቢያቸው እየፈጸሙት ያለ ግፍ መፈጠርን ያስጠላል። መረጃው ከ ትግራይ ሙስሊም ሚድያ ገፅ የተወሰደ ነው። ህወሓትም ቢሆን ከዚህ የተሻለ አመለካከት የለውም። በፌዴራል መንግስት ተገፍቻለሁ እያለ ዞሮ የክልሉን ሙስሊሞች በሃይማኖታቸው ሰበብ በያይነቱ የግፍ አይነት ያወርድባቸዋል። አቅሙ በቀለለበት በዚህ ጊዜ በደል ከመፈፀም ያልተመለሰ ድርጅት ያለ ተቀናቃኝ አገር ቢቆጣጠር ክፋቱ ከዚህም የባሰ ነው የሚሆነው። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor