ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
323
Obunachilar
+124 soatlar
-77 kun
+5830 kun
Ma'lumotlar yuklanmoqda
O'xshash kanallar
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
Oktabr '26Okt '26
Oktabr '26
+85
3 kanalda
Sentabr '26
+302
1 kanalda
| Sana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
| 15 Oktabr | +2 | |||
| 14 Oktabr | +2 | |||
| 13 Oktabr | 0 | |||
| 12 Oktabr | 0 | |||
| 11 Oktabr | +2 | |||
| 10 Oktabr | 0 | |||
| 09 Oktabr | +2 | |||
| 08 Oktabr | +8 | |||
| 07 Oktabr | +7 | |||
| 06 Oktabr | +21 | |||
| 05 Oktabr | +5 | |||
| 04 Oktabr | +2 | |||
| 03 Oktabr | +8 | |||
| 02 Oktabr | +24 | |||
| 01 Oktabr | +2 |
Kanal postlari
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ዛሬ አንዱን ወዳጄን በጨዋታ መሃል «ማሻ በጣም አምሮብሃል!» አልኩት። እርሱም ፈገግ ብሎ እንደ ቀልድ «ሰሞኑን ለይል ላይ ቆም እያልኩ ነበር፤ ምናልባት እሱ ይሆናል» አለኝ።
እውነቱን ነው... ቀልድ ቢመስልም ጥልቅ እውነት አለው። የለይል ሶላት በፊት ላይ የማይደበቅ፣ በልብ ውስጥም የማይጠፋ ልዩ «ኑር» ያጎናጽፋል።
ታላቁ ታቢዒይ ሐሰን አል-በስሪ «የለይል ሰጋጆች ፊታቸው ከሁሉ በላይ እንዲህ የሚያበራው ለምንድን ነው?» ተብለው በተጠየቁ ጊዜ፤ «በሌሊት ጨለማ ከአል-ራሕማን ጋር ለብቻቸው ተገናኙ፤ እርሱም ከራሱ ብርሃን አለበሳቸው» በማለት የመልካቸውን ሚስጥር ገልፀውታል። በእርግጥም ፈጅርን በጀመዓ ተነስቶ የቀኑን በረካ የተጎናጸፈ ሰውና አርፍዶ በስንፍና የነቃ ሰው የቀን ውሏቸው ፈጽሞ አንድ አይሆንም። ሌሊቱን በከፊልም ቢሆን ከፈጣሪው ጋር ተነጋግሮ ያነጋና በእንቅልፍ ማዕበል ተውጦ ያደረ ሰው ፊታቸው እኩል አይፈካም።
ጉዳዩ የረጅም ሰዓታት ድካም ሳይሆን የቁርጠኝነትና የፍላጎት ጉዳይ ነው፤ ከፈጅር አዛን ቀደም ብለን አስር ደቂቃ እንኳ ብንነሳ፣
ልባችንን ሰብረን የምንሰግዳቸው ሁለት ረከዓቶች የልብን ሰላም፣ የቀንን ስኬትና የፊትን ብርሃን ለመላበስ በቂ ናቸው።
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
| 2 | የጀርቡዕና የለተሞ መንጋ ሙሪድነት ተጧጥፎ ቀጥሏል። በመሰረቱ ሐቀኛ የመሆን መመዘኛው የእውቀት ብዛትና ማነስ ሳይሆን ቁርአንና ሐዲሥን በቀደምቶች አረዳድ መገንዘብና በዚያም ላይ መፅናት ነው። በጣም የሚገርመው በዚህ አይነት የሙሪድነት ትብታብ የተጠፈሩ ሰዎች ሁሌም ስለሚደግፉት አካል መጮኽ እንጅ የራሳቸው የዕውቀት ፍለጋ ጉዳይ አጀንዳቸው አይደለም። ስማቸውን እንኳ አስተካክለው ሳይፅፉ ነው እንደዚህ የሰውን እውቀት ገምጋሚ፣ ከርካሚና ፈላጭ ቆራጭ ሁነው የተቀመጡት።
ተመልከቱ ጀርቡዒዩ الله ولي المتقين ለማለት ፈልጎ ይመስላል ሁለት ዋው መርቆላቸው ከዓረበኛ ይልቅ ቻይነኛ ፅሁፍ አስመስሎታል። የእነ ሲሉ ሰማሁ ብየ የልጅ ልጅ ደግሞ "Idris" ለማለት አንድ ኑን ጨምራለት "Endris" ብላ ሰጅላለች። እስኪ መጀመሪያ የሰዎችን ትካሻ ከማለካካት በፊት እኔ ማን ነኝ? የዕውቀት ደረጃየ ምን ያክል ነው? እውቀት ፍለጋየስ አጥጋቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመልከት። አረ ተው ልብ አድርጉ። እንዲሁ ስላመቸ ብቻ አትለቅልቁ።
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy | 8 |
| 3 | ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡
ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!
(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)
"ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡" [አልሐጅ፡ 46]
በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!
ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና! አቡበክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች በተለየ የላቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!
ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሞቷል? ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ "ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም" አይደል ያለው ኻሊቁ?
አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor | 8 |
| 4 | Matn yo'q... | 10 |
| 5 | ሶብርና ውጤቱ!
በህይወት ጉዟችን ውስጥ ብዙ መንገዶችን እንጓዛለን፤ ብዙ ውጣ ውረዶችንም እናስተናግዳለን። ከገጠሙን ፈተናዎች ሁሉ ፊት ቆመን የምንማረው እና ህይወታችንን የሚመራው ትልቁ ትምህርት ግን “ሶብር” (ታጋሽነት) ነው። ነገሮች ሲከብዱ፣ የኑሮ ኪሎ ሲከብድ፣ ተስፋ ሲቆረጥ፣ እና መውጫው ጨርሶ ሲጠፋ ጸንቶ መቆም ከባድ ፈተና ነው። ግን ደግሞ እውነተኛው የድል ጥሰት የሚጀምረው ከዚህ አሳሳቢ ነጥብ ላይ ነው።
ታጋሽነትን በህይወት ማዘወትር ዋጋ ያስከፍላል፤ ዝምታን፣ መዋጥን እና መጽናትን ይጠይቃል። ነገር ግን የሚያስገኘው ውጤት ከፍ ያለና ዘላቂ ነው።
"ትዕግስት መሠበር አለው፤ ፍሬው ግን ጣፋጭ ነው።"
1. የሶብር ትርጉም እና ትግል
ሶብር ማለት ዝም ብሎ ችግርን ተሸክሞ ዝም ማለት ብቻ አይደለም። ሶብር ማለት ሁኔታዎች ሲጨልሙ፣ የጊዜው ሁኔታ ከኛ ጋር ሳይሆን ሲቀር፣ ውስጣችን ሲያርር እንኳን ተስፋ ሳይቆርጡ በቁርጠኝነት መስመር ላይ መገኘት ነው።
በዚህ ጉዞ ላይ ብዙዎቻችን እንሰናከላለን፤ እንወድቃለን። ነገር ግን ድክመትን አምኖ ከወደቁበት መነሳት፣ በችግር ጊዜ ራስን መግታት እና ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ በማመን መትጋት የእውነተኛ ታጋሽ መገለጫ ነው።
2. በሶብር ምን ይገኛል?
ውስጣዊ ሰላም፡ አእምሮን ከከንቱ ጭንቀት ነፃ አድርጎ ነገሮችን በረጋ መንፈስና በጥበብ ለማየት ያስችላል። ፈጣን ውሳኔዎችን ስህተት ከመሥራት ይታደጋል።
የጠነከረ ስብዕና፡ ፈተናዎች ሲያልፉ, የቀድሞውን ሰው እንድንተካና የበለጠ ብቁና ጠንካራ ሆነን በህይወት እንድንቀጥል ይረዱናል።
የተሻለ እና የረጅም ጊዜ ውጤት፡ አንግቦ በመሮጥ ከሚገኝ ጊዜያዊ ስኬት፣ በትዕግስት እና በጥበብ የተገነባ ውጤት ለረጅም ጊዜ ዘልቆ ይቆያል፤ መሰረቱ ጠንካራ ነው።
3. የውጤቱ ቀን ሲደርስ...
ዛሬ ላይ የገጠመዎት ፈተና፣ የደከሙበት ነገር የዘገየ ይመስልዎ ይሆናል፤ ጥረቱ ዋጋ አላስገኘም ብለው አንዳንዴ ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ መታገሻ ቀን ለትልቅ ድል እየቀረቡ መሆኑን ማሳያ ነው።
ዛሬ በዝምታ የዋጡት ትግል እና የሰሩት ስራ ሁሉ በከንቱ አይቀርም። ጊዜው ሲደርስ የሶብር ፍሬ ከየትኛውም በላይ ጣፋጭ ሆኖ ይመጣል።
አቡ ዑበይዳ | 13 |
| 6 | የተከበሩ ሼኽ አላህ መልካም ነገር ይግጠመዎትና ይሄ ጠያቂ እንዲህ ይላል
ሀሜትን መስማት ኢንካር ሳያደርጉ ወንጀል ያገኘዋልን??
መልስ
አዎ
ሀሜትን መስማት ኢንካር የማያደርግ ከሆነ
ወንጀሉን ይጋራል
ይሄ ሙንከር ነው
ግዴታ ነው ሙንከርን ኢንካር ማድረግ
ስለዚህ ሰዎቺን ሊሆን ይቺላል ግለሰብም ሊሆን ይቺላል ያን ሰው በመጥፎ እየተነሳ እሱ በማይወደው
ነገር መዞለም መስማት ወንጀል ያገኘናል አላህ ፍሩ ሰዎቺን አትሙ እስካላልን ዲረስ
ይሄን ማድረግ ካልቻልን ከቦታው ተነስተን መሄዲ አለብን መስማት የለብንም።
መጥፎን ነገር ካዬን በጃቺን ማስቆም ካልቻልን በምላሳቺን ካልቻልን ከዛ ቦታ ለቆ መሄዲ።
ስንቶቻቺን ነን ሰዎቺን የምናማው ወይም ሲታሙ የምንሰማው ራሳቺንን እንፈትሺ?
ሰዎቺን ማማት መዞለም
ኢስቲግፋር ተውበት ማድረግ በቂ አይደለም ተቀባይነት የለውም ሸርጡ ካልተሟላ።
አላህ በሰዎቺ ሀቅ ላይ አይገባም።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Anwar8seid | 14 |
| 7 | السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ
በ 2019 ዓ.ል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አድስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ!!
ዩኒቨርሲቲያችን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 9 እና 10 አዲስ የፍሬሽማን ተማሪዎችን ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በመሆኑም
የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ ለሁላችሁም የ «እንኳን ደህና መጣችሁ!» መልዕክቱን እያስተላለፈ ፣ ወደ ግቢ በምትገቡበትና በምትደርሱበት ወቅት ምንም ዓይነት እንግልትና ምቾት የሚነሳ ነገር እንዳይገጥማችሁ ሙሉ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
በመሆኑም ስለ ዩኒቨርሲቲው፣ ስላለው ሁኔታና ማንኛውም ዓይነት አካዳሚያዊ ወይም ዲናዊ መረጃ ለሚፈልግ አዲስ ተማሪ ከታች በተቀመጡት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ሙሉ እገዛና መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን፦
📞 ለወንድሞች የመረጃና እገዛ መስመሮች፦
• 📲 ወንድም መስዑድ ሰይድ፦ 0975292817
• 📲 ወንድም ዑመር አወል፦ 0946505128
• 📲 ወንድም ሙሀመድ ሀሰን፦ 0924033273
• 📲 ወንድም ሀቢብ ማህሙድ፦ 0903830776
• 📲 ወንድም ሙሀመድ አወል (Qafar)፦ 099 337 5010
• 📲 ወንድም ሙኒር ሙሀመድ (Afan oromo)፦ +251946878432
📢 ልዩ ማሳሰቢያ ለእህቶቻችን፦
እህቶቻችን ቀጥታ የአጋዥ እህቶችን ስልክ ቁጥር ለማግኘት በ📲 0990333299 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ፦
📌 ወደ ኸይር ያመላከተ የሰሪውን ያክል ምንዳ ያገኛል !
የቻናል ባለቤት የሆናችሁ ይህ መልዕክት አዲስ ለሚገቡትና እርዳታ ለሚፈልጉት ወንድምና እህቶቻችን ሁሉ እንዲደርስ Share በማድረግ አጅሩን እንዲትጋሩ በትህትና እንጠይቃለን።
✨ የጀማዓችን ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል፦
👉 https://t.me/wdumuslimstu
✨ የጀማዓችን ይፋዊ ቴሌግራም ግሩፕ፦
👉 https://t.me/WDUMStudent
وَالسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ | 22 |
| 8 | ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ነብዩሏህ ሱለይማን ነው ። | 24 |
| 9 | አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ 🌙✨
የዳዕዋ ጥሪ 📢
ውድ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ (የሜይን እና ቴክኖ ካምፓስ) ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ (በተለይ አዲስ ገቢ ፍሬሽማን ወንድምና እህቶቻችን) 👋🎓
በመጀመሪያ ደረጃ እንኳን ወደ ሁለተኛው ቤታችሁና ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ እንኳን በሰላም መጣችሁ! 💐✨ የትምህርት ዘመናችሁ የስኬት፣ የሰላም እና የበረካ እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን መልካም የአቀባበል መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
በመቀጠልም ይህንን አዲስ የካምፓስ ህይወታችሁን በደስታና በጥንካሬ እንድትጀምሩ የሚረዳችሁ ትልቅና ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል! 🎁🎉
ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ 🕌 ልዩ ልምድ ባላቸው ኡስታዛችን የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል። 🌟
በዕለቱ የዩኒቨርሲቲ ቆይታን (University Life) በብቃት ማሳለፍ፣ የዕለት ተዕለት ጭንቀቶችን (Tension) መቋቋም፣ ዲናችንንና ዱንያችንን እንዴት ጎን ለጎን አብረን ማስኬድ እንዳለብን ጥልቅ ማብራሪያ ይሰጥበታል። 📚💡
በግቢ ቆይታቸው ብዙ ልምድ ባላቸውና ራሳቸውም የዩኒቨርሲቲ ህይወትን ባሳለፉት በተከበሩት ኡስታዝ ኸድር የሚቀርብ በመሆኑ፣ ልብ የሚነካና እጅግ አስተማሪ ፕሮግራም ይሆናል! 🎙️❤️
👥 ማን ሊገኝ ይችላል? ሴቶችም ወንዶችም (ሁሉም ተማሪዎች በክብር ተጋብዛችኋል!)
📍 ቦታ፡ የተማሪዎች መስጅድ (አል-ሁዳ መስጅድ) 🕌
⏰ ሰዓት፡ ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ ወዲያውኑ 🌙
ሁላችሁም ሳትቀሩ እንድትገኙና የዚህ በረካ ተካፋይ እንድትሆኑ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! እንዳትቀሩ! 🤝
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን! 🤲
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዐ | 20 |
| 10 | አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ 🌙✨
የዳዕዋ ጥሪ 📢
ውድ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ (የሜይን እና ቴክኖ ካምፓስ) ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ (በተለይ አዲስ ገቢ ፍሬሽማን ወንድምና እህቶቻችን) 👋🎓
በመጀመሪያ ደረጃ እንኳን ወደ ሁለተኛው ቤታችሁና ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ እንኳን በሰላም መጣችሁ! 💐✨ የትምህርት ዘመናችሁ የስኬት፣ የሰላም እና የበረካ እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን መልካም የአቀባበል መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
በመቀጠልም ይህንን አዲስ የካምፓስ ህይወታችሁን በደስታና በጥንካሬ እንድትጀምሩ የሚረዳችሁ ትልቅና ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል! 🎁🎉
ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ 🕌 ልዩ ልምድ ባላቸው ኡስታዛችን የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል። 🌟
በዕለቱ የዩኒቨርሲቲ ቆይታን (University Life) በብቃት ማሳለፍ፣ የዕለት ተዕለት ጭንቀቶችን (Tension) መቋቋም፣ ዲናችንንና ዱንያችንን እንዴት ጎን ለጎን አብረን ማስኬድ እንዳለብን ጥልቅ ማብራሪያ ይሰጥበታል። 📚💡
በግቢ ቆይታቸው ብዙ ልምድ ባላቸውና ራሳቸውም የዩኒቨርሲቲ ህይወትን ባሳለፉት በተከበሩት ኡስታዝ ኸድር የሚቀርብ በመሆኑ፣ ልብ የሚነካና እጅግ አስተማሪ ፕሮግራም ይሆናል! 🎙️❤️
👥 ማን ሊገኝ ይችላል? ሴቶችም ወንዶችም (ሁሉም ተማሪዎች በክብር ተጋብዛችኋል!)
📍 ቦታ፡ የተማሪዎች መስጅድ (አል-ሁዳ መስጅድ) 🕌
⏰ ሰዓት፡ ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ ወዲያውኑ 🌙
ሁላችሁም ሳትቀሩ እንድትገኙና የዚህ በረካ ተካፋይ እንድትሆኑ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! እንዳትቀሩ! 🤝
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን! 🤲
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዐ | 1 |
| 11 | ለመሆኑ ማግባት ማለት የኪስ መንጠፍ፣ የጉልበት መድከም፣ የድህነትና የችግር መጥሪያ ይመስልሃልን? በፍጹም አይደለም! ይልቁንስ አንተ በቅን ልቦናና በሃላፊነት የጋብቻን ደጅ ስታንኳኳ፣ ያ ፈጣሪ ደግሞ ላንተና ለቤተሰብህ የሚሆን የሲሳይንና የበረከትን ትልቅ በር ወገግ አድርጎ ይከፍትልሃል።
እስኪ በጥልቀት አስተውለው፤ ወደ ቤትህ የምታስገባት ያቺ ሙሽራ እኮ ያንተን ጥቂት እንጀራ ልትጋራ፣ ኪስህን ልታጎድል አትመጣም። ይልቁንስ አምላክ ለሷ የጻፈላትን፣ ከሰማይ የወረደውን የራሷን አዲስ ርዝቅና በረከት ይዛ ነው ወደ ቤትህ የምትገባው!
ብቸኝነት ያረከሰውና ያበላሸው ጥረትህ፣ በጋብቻ ቅዱስ ማዕሰር ሲታሰር ሙሉነትን ያገኛል። ወንድ ልጅ ባገባ ጊዜ ወገቡን አጥብቆ የመስራት ወኔው ይነሳሳል፤ አእምሮው ይረጋጋል፤ ቤቱም በፍቅር፣ በሰላምና በበረከት ይሞላል። ጋብቻ የድህነት ምክንያት ሳይሆን፣ ለሀብትና ለብልጽግና መከፈቻ የሆነ የጸጋ ቁልፍ ነው!
ስለዚህ ያን የፍርሃትና የጥርጣሬ አረንቋ አራግፈህ ጣለው። በፈጣሪህ ቸርነት ላይ ሙሉ እምነት ይኑርህ፤ ወኔህን አዘጋጅተህ የፍቅርን መንገድ ተከተል ... ሲሳይማ አጅባህ በእግረ-መንገዷ ትከተልሃለች! | 20 |
| 12 | 🤙ሕይወት አስተምራኛለች
ስለችግሬ ለማንም ማሰማት እንደሌለብኝ
ምክንያቱም ከአላህ ውጭ ለሌላ አካል ማሰማት ውርደት ነው እና
እናም ፈገግ እላለሁ ምንም ያህል ብጎዳም እንኳን | 20 |
| 13 | ተዘጋበት ጊዜ ውስጥ መደረጉ ነው፡፡
ከነዚህ መስፈርቶች አንዱን ያጓደለ ተውበቱ ትክክለኛ አይደለም፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ ሃሜት ላይ በወደቅን ቁጥር እውነተኛ የሆነን ተውበት ብናደርግ በቀጣይ ተመሳሳይ ጣጣ ውስጥ ላለመግባት እንጠነቀቃለን፡፡
⑨ ከወንድም ክብር ላይ መከላከል ያለውን ፋይዳ ማሰብ፡- ወንድምህ ሲታማ ከሱ መከላከልህ ላንተ ትልቅ ሽልማት አለው፡፡ ነብዩ ﷺ “ከወንድሙ ክብር ላይ የተከላከለ አላህ በቂያማ ቀን ከፊቱ እሳትን ያርቅለታል” ይላሉ፡፡ ስለዚህ ይሄ ሽልማት እንዳያመልጥህ ከወንድምህ ተከላከል፡፡ አንድ ሽልማት፡፡ ይሄ ተግባርህ ሃሜት ላይ የሚወድቅ ወንድምህንም ከጥፋት ስለሚያቅበው ሌላም ሽልማት አለህ፡፡ ያለበለዚያ ግን ከአፍታ በኋላ እራስህን የሃሜቱ አካል ሆነህ ልታገኘው ትችላለህ፡፡
①∅ ሆደ ሰፊ መሆን፡- ለሃሜት ከሚገፉን ነገሮች አንዱ በሌሎች ላይ የሚኖረን ቅሬታ ነው፡፡ ታጋሽና ይቅር ባይ ብንሆን ግን ስለሰዎች ክፉ እንዳናስብና በክፉ እንዳናነሳቸው ይረዳናል፡፡
①① ሃሜት የሚፈቀድባቸውን ሁኔታዎች ጠንቅቆ መለየት፡- የሰዎችን ድክመት ወይም ጥፋት መናገር የሚፈቀድባቸው ወይም ግዴታ የሚሆንባቸው ውስን ሁኔታዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ እነዚያ ሁኔታዎች ለአስገዳጅ ምክንያት ብቻ የሚፈቀዱ ስለሆነ ያለ አግባብ እየመነዘርናቸው እንዳይሆን መጠንቀቅ አንዱ ከሃሜት መራቂያ ስልት ነው፡፡ አንዳንዱ በሸሪዐዊ ምክንያቶች አስታኮ የግል ቂሙን የሚያወራርድ፣ ተያያዥነት በሌላቸው ግለሰባዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘልቆ የሚገባ፣ አልፎም አካላዊቅርፅን ሳይቀር እያነሳ የሚያንቋሽሽ ያጋጥማል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጥፋት እራስን መሸወድ ካልሆነ በስተቀር ሃሜት የሚፈቀድባቸውን ሁኔታዎች ማጣቀስ አያዋጣም፡፡ የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን ላይ ይሁን።
@IbnuMunewor | 17 |
| 14 | ከሃሜት ለመራቅ የሚያግዙ #11 ነጥቦች፦
👉 አላህ ያደለው በጣም ጥቂት ሰው ካልሆነ በስተቀር ከሃሜት ወንጀል የሚተርፍ የለም፡፡ እንዲያውም “እነ እከሌ ሃሜተኞች ናቸው” እያሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ ሰዎች እራሱ በአብዛሀኛው እራሳቸውም ሃሜተኞች ናቸው፡፡ ልዩነቱ ለሃሜት የሚገፋው ምክንያትና የሚታማው አካል መለያየት ብቻ ነው፡፡ #ስለዚህ ይሄ ችግር አብዛሀኞቻችን የተዘፈቅንበት ነው፡፡ በዚህ ረገድ አጋዥ የመሰሉኝን ጥቂት ነጥቦች እንደሚከተለው አሰፍራለሁ፡፡
① የሃሜትን ምንነት መረዳት፡-
ብዙ ሰዎች ሰዎችን እያሙ ነገር ግን “ይሄ እውነት ነው፤ ሃሜት አይደለም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይሄ ስለሃሜት ያላቸውን የግንዛቤ ክፍተት የሚያሳይ ነው፡፡ ሃሜት ማለት ነብዩ ﷺ እንደገለፁት “ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው፡፡” “የማነሳው ነገር ከወንድሜ ዘንድ ካለስ?” ተብለው ሲጠየቁ “የምትለው ነገር ከወንድምህ ዘንድ ከኖረ በርግጥም አምተኸዋል፡፡ የምትለው ነገር ከሌለበት ግን በእርግጥም ቀጥፈህበታል” አሉ፡፡ [ሙስሊም የዘገቡት] አንዳንዱ ወንድሙን እያማ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” ይላል፡፡ ይሄ ግን ሐቂቃውን አይቀይረውም፡፡ እንዲያውም ከፊቱ እየተናገረ ቅስሙን ሲሰብር ወይ ተጨማሪ ወንጀል ይደርባል፡፡ አለያ ደግሞ ተጣልቶ ፊትና ያቀጣጥላል፡፡ እንዲያውም አንዳንዱ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” የሚለው ሃሜተኛ እንዳይባል ለአድማጮቹ የሚሰጠው ጉቦ ነው እንጂ ውሸቱን ነው የሚያወራው፡፡ ጉዳዩን ከሚታማው ሰው ዘንድ ቢያወራ እንኳን በሌለበት በሚያወራው መልኩ አይሆንም፡፡
② የሃሜትን አስከፊነት መገንዘብ፡- አብዛሃኞቻችን ሃሜት ምን ያክል #አስከፊ እንደሆነ በሚገባ አናውቅም፡፡ አንድ ሁለት ምሳሌ ብቻ ብንመለከት የጉዳዩን አስፈሪነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡
ምሳሌ አንድ፡- የመጀመሪያው ሃሜት ልክ የሞተ ወንድምን ስጋ እንደመብላት ነው የሚለው ቁርዓናዊ መልእክት ነው፡፡ ትኩረት ብንሰጠው ይሄ እጅግ ቀፋፊ ነገር ነው፡፡ እስኪ አስቡት አንድ ጨካኝ ገዢ “ሰዎችን በሃይል እየደበደበ የሞቱ ሰዎችን ስጋ እንዲበሉ አደረጋቸው” የሚል ዜና ከምስል ጋር ብንመለከት ምን ይሰማናል?! ሰቅጫጭ ነው አይደል?! የሆኑ ሰዎች የሰው ስጋ እየመተሩ፣ እየዘለዘሉ ሲበሉ ብንመለከትስ ምን ይሰማናል?! በቃ ጌታችንም ሃሜት ማለት የሞተ ወንድምን ስጋ እንመብላት ነው አለን፡፡ ሰው ባማን ቁጥር በአይነ ህሊናችን ጥርሳችን የተቦጫጨቀ የሰው ስጋ እንደያዘ ወይም እያኘከ እንደሆነ ብንስለው ዘግናኝ ምስል ይታየናል፡፡ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ይህን ምሳሌ የሰጠው የሞተን መመገብ አፀያፊ የሆነ ሐራም ስለሆነ ነው፡፡ ሃሜትም እንዲሁ በሃይማኖት የተወገዘ፣ ከነፍስ ዘንድ የሚያፀይፍ ነው፡፡”
ምሳሌ ሁለት፡- ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው፡፡ “በእርግጥም አንድ ሰው ደንታ ሳይሰጠው በተናገረው ንግግር ሰባ አመት ወደ ጀሀነም ይምዘገዘጋል!!” አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡
ምሳሌ ሶስት፡- ነብዩ ﷺ በሁለት ቀብሮች ዘንድ አለፉ፡፡ ሰዎቹ በቀብራቸው ውስጥ የሚቀጡ ናቸው፡፡ “አንዱ ሰዎችን ያማ የነበረ ነው” አሉ፡፡ [ሶሒሑል ኣደብ አልሙፍረድ፡ 275]
እነዚህ ምሳሌ ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎችም አስፈሪ መረጃዎችን አልፎ አልፎ ብንመልከትና ደዕዋዎችን ብናዳምጥ ጠቃሚ ነው፡፡
③ ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶችን መለየት፡- በአብዛሀኛው ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡-
ስራ መፍታት፡- ስራ ፈቶች በብዛት ሃሜተኞች ናቸው፡፡ እራሳችንን በስራ መጥመድ አንድ ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ ስለሆነም አእምሯችንን ስለሰዎች ከማሰብ ዞር በሚያደርጉን ስራዎች ላይ መጥመድ ፋይዳው ድርብርብ ነው፡፡ በተጨማሪም ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር በማድረግ፣ ጠቃሚ ፅሁፎችን በማንበብ፣ ሙሓዶራዎችን ወይም ደዕዋዎችን በማዳመጥ ትርፍ ጊዜያችን ከሃሜት በመራቅ በጠቃሚ ነገር ላይ ማሳለፍ እንችላለን፡፡ ዑለማዎቻችን እንደሚሉት ምላስ በጥሩ ነገር ካልጠመድናት ያለ ጥርጥር በመጥፎ ነገር መጠመዷ አይቀርም፡፡
ወሬ ማብዛት፡- ወሬው የበዛ ሰው ያለ ጥርጥር ለጥፋት የቀረበ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ዝም ያለ ተረፈ” ይላሉ፡፡ ስለዚህ በዝምታ ውስጥ ያሉ ፋይዳዎችን ልናስተነትን ይገባል፡፡ ባጭሩ ወሬ መቀነሳችን ለሃሜት ከምንጋለጥባቸው መንገዶች ዋናውን መቀነስ ነው፡፡
የጓደኛ ጣጣ፡- መቼም ሃሜት የጋራ ወንጀል ነው፡፡ ሃሜት የሰማ ሰው በመቃወሙ የሚከተል አደጋ ካልኖረ በስተቀር መቃወም ግዴታው ነው፡፡ ይህን ያልቻለ ቢያንስ በልቡ ሊጠላ ይገባዋል፡፡ ያለበለዚያ አድማጩም እንደተናጋሪው ተጠያቂ ነው፡፡ መቼም እራሳችንም ሆንን ጓደኛችን በቀላሉ ነገሮችን ወደ ሃሜት የሚለውጥ አይጠፋም፡፡ ይህን ችግር አሰተውሎ ለህክምናው መታገል ብልሃት ነው፡፡ ችግሩ ከኛ ከሆነ ተቅዋን መላበስ ሁነኛ መፍተሄ ነው፡፡ ከጓደኞቻችንም ለዚህ ጥፋት የሚያጋልጡንን ከቻልን ግልፅ መመካከር ኖሮ ተያይዞ ከጥፋት በመራቅ ወደ ኸይር መጓዝ፡፡ ካልሆነ ግን በመራቅም ቢሆን ቢያንስ እራስን ከጥፋት ማትረፍ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡ ይሄ ውሳኔ ለአንዳንዶቻችን ትልቅ መስዋእትነት ሊጠይቅ ቢችልም የሚከተለውን መዘዝ ማሰባችን ጉዳዩን ያቀለዋል፡፡
የልብ መድረቅ፡- እንዲያውም ቁልፉ እዚህ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ተቅዋችን ይጨምር ዘንድ ልንታገል ይገባል፡፡
④ ሙራቀባ፦
(በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ ዘወትር አላህን ማሰብ)፡- “ከሱ ዘንድ ረቂብና ዐቲድ ቢኖሩ እንጂ አንድም ንግግር አይናገርም” የሚለውን አስፈሪ ቁርኣናዊ መልእክት ማሰብ ጥሩ ነው፡፡
⑤ ነፍስን መቆጣርና መተሳሰብ፡- ህይወትን በግምት መግፋት አይገባም፡፡ ለራሳችን ከሐራም ነገሮች ያለንን ርቀት፣ ከግዴታ ነገሮች ያለንን መዘነጋት የምንገመግምበት ፋታ ልንሰጥ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን እራሳችንን ሳናስተውለው በቀላሉ ከማንመለስበት ርቀት ላይ ልናገኘው እንችላለን፡፡
⑥ የመልካም ቀደምቶችን አርአያ መከተል፡- ሌላው ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሰለፎች አቋም ምን ይመስል እንደነበር ተግባራዊ ተሞክሮዎችን ማጥናት ጠቃሚ ዘዴ ነው፡፡ ምን ያክል ሃሜትን ይፀየፉ እንደነበር፣ ለሃሜተኛ ምን አይነት መልስ ይሰጡ እንደነበር መመልከት፡፡ ይሄ ለሚያስተውል ሁሉ በራሱ ማንነት እንዲሸማቀቅ በማድረግ በተጨባጭ የሚታይ ውጤት የሚያስከትል ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘዴ ነው፡፡
⑦ ዱዓ፡- አላህ ምላሳችንን ከሃሜት እንዲጠብቅልን መማፀን አንዱ ከሃሜት መራቂያ መንገድ ነው፡፡
⑧ እውነተኛ ተውበት፡- ለምንፈፅመው የሃሜት ጥፋት እንዲሁ የዋዛ ፈዛዛ “አስተግፊሩላህ” ሳይሆን መስፈርት የሚያሟላ እውነተኛ ተውበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ያለ አግባብ የወሰደው የሰው ሐቅ ካለ በዚህ ጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ የሚያስፈልጉ የተውበት መስፈርቶች አሉ፡፡ እነሱም
አንደኛ፡- አላህን ብቻ በማሰብ መመለስ- ኢኽላስ፡፡ አላህን አስቦ እስካልተመለሰ ድረስ ከጥፋቱ መራቁ ብቻውን ቀድሞ ከተፈፀመው ጥፋት ከመጠየቅ አያተርፈውም፡፡
ሁለተኛ፡- ስለፈፀመው ጥፋት መፀፀት (ጉዳዩን አቅልሎ ሊያይ አይገባምና)
ሶስተኛ፡- ከጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ መራቅ (የሰው ሐቅ ካበት መመለስ)
አራተኛ፡- ዳግም ወደዚያ ጥፋት ላይመለስ ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረግ
አምስተኛ፡- ተውበቱ የተውበት በር ባል | 16 |
| 15 | سنن_النسائي_بتخريج_الألباني_ت_مشهور.pdf | 17 |
| 16 | ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸዉ እና እንድህ ይላሉ
"أنه إذا كثرت الأحزاب في الأمة فلا تنتم إلى حزب، فقد ظهرت طوائف من قديم الزمان مثل الخوارج والمعتزلة والجهمية والرافضة، ثم ظهرت أخيرًا إخوانيون وسلفيون وتبليغيون وما أشبه ذلك، فكل هذه الفرق اجعلها على اليسار وعليك بالأمام وهو ما أرشد إليه النبي في قوله: فَعَلَيْكُمْ بِسْنِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ .
የሙስሊም ቡድኖች ከበዙ ወደ ማንም ቡድን አትቀላቀል፤ ከጥንት ጀምሮ እንደ ኸዋሪጅ፣ ሙዕተዚላ፣ ጀህሚያ እና ራፊዷ የመሳሰሉ ክፍሎች(ጀመዓወች) ታይተዋል፤ ከዚያም በኋላ የኢኽዋኖች፣ ሰለፍዮች፣ ተብሊጊዎች እና የመሳሰሉት ታይተዋል፤ ስለዚህ እነዚህን ቡድኖች ሁሉ በግራ በኩል ተዉዋቸው እና አንተ ወደፊት (ቀጥተኛው መንገድ) ላይ ፅና፤ ይህም ነቢዩ (ሱ.ዐ.ወ) ያመላከቱት ነው፡- «የኔን ሱና እና በቅን መንገድ የተመሩ ምትኮችን ሱና ያዙ» በማለት።
ولا شك أن الواجب على جميع المسلمين أن يكون مذهبهم مذهب السلف لا الانتماء إلى حزب معين يسمى السلفيين، فهناك طريق السلف وهناكحزب يسمى السلفيون والمطلوب اتباع السلف، إلا أن الإخوة السلفيين هم أقرب الفرق إلى الصواب ولكن مشكلتهم كغيرهم أن بعض هذه الفرق يضلل بعضًا ويبدعه ويفسقه، ونحن لا ننكر هذا إذا كانوا مستحقين، لكننا ننكر معالجة هذه البدع بهذه الطريقة، والواجب أن يجتمع رؤساء هذه الفرق، ويقولون بيننا كتاب الله عز وجل وسنة رسوله فلنتحاكم إليها لا إلى الأهواء والآراء، ولا إلى فلان أو فلان، فكل يخطئ ويصيب مهما بلغ من العلم والعبادة ولكن العصمة في دين الإسلام..
ያለምንም ጥርጥር በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግደታዉ ፣አካሄዳቸዉ የቀደምቶች አካሄድ እንጂ 'ሰለፊዎች' የሚባል የተወሰነ ፓርቲ (ወይም ቡድን) አባል መሆን አይደለም። በመሆኑም የሰልፍ መንገድ አለ፣ 'ሰለፊዎች' የሚባል ፓርቲም አለ፤ የሚፈለገው ግን የሰልፍን መንገድ መከተል ነው። ነገር ግን ሰለፊ ወንድሞች ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ችግራቸው ግን እንደ ሌሎች ሁሉ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዳንዶቹ ሌሎችን ስተዋል፣ ሙብተድዕ ፣ ወይም ፋሲቅ ማለታቸው ነው። እኛም ይህ የሚገባቸው ከሆነ እንሱን አንቃወምም፣ ነገር ግን እነዚህን ፈጠራዎች (ቢድዓዎች) በዚህ መንገድ ማከቸውን(ማስተካከላቸዉን) እንቃወማለን። የነዚህ ቡድን መሪዎች መሰብሰብ እና 'በእኛ መካከል የአላህ መጽሐፍ እና የነቢዩ ሱና አለ፤ ወደ እነርሱ እንጂ ወደ ፍላጎቶችና ሐሳቦች፣ ወይም ወደ እገሌ እና እገሌ ፍላን ( አመለካከት)አንመለስም' ማለት ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም የቱንም ያህል በእውቀትና በአምልኮ የገፋ ቢሆንም እያንዳንዱ ሰው ይሳሳታል፣ ትክክልም ይሆናል፤ ጥበቃ (ዒስማ) ግን በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው።"
شرح أربعين النووية
በወንድም አቡበከር ሰዒድ
https://t.me/wdumuslimstu
https://t.me/wdumuslimstu
https://t.me/wdumuslimstu | 18 |
| 17 | ሀብት ለጊዜው ዓይንን ያደምቃል ዲንና አኽላቅ ግን ለዘላቂ ሕይወት ብርሃን ይሆናሉ። በትዳር መንገድ ላይ ቁሳቁስና ገንዘብ አካፋይ እንጂ የመሠረት ያህል ጥንካሬ የላቸውም። ትዳር ማለት የሁለት ነፍሶች ውህደት እና የሁለት ልቦች ሰላም ወደ አላህ የሚያደርስ መንፈሳዊ ጉዞ ነው።
አላህ በታላቁ ቃሉ ውስጥ ትዳርን ሲገልጽ በገንዘብና በቁሳቁስ መለኪያ ሳይሆን በሰላምና በመረጋጋት ነው የገለፀው ለዚህም(لتسكنوا) የሚለውን ቃል ተጠቀመ ይህም ማለት ልብ ከውጭ ዓለም ውዥንብር አርፋ የምትታደስበት ነፍስ የምትረጋጋበት ማለት ነው። ገንዘብ አልጋ ይገዛል እንጂ እውነተኛ እንቅልፍና መረጋጋትን አይገዛም። ቁሳቁስ ትልልቅ ቪላዎችን ይገነባል የልብ ሰላምን ግን የሚገነቡት መወዳህ እና ረሕማ ናቸው። እነዚህ ደግሞ የሚመነጩት ከአላህ ዲን እና ከመልካም አኽላቅ ብቻ ነው።
ነብዩ ﷺ የትዳር መሠረት ምን መሆን እንዳለበት ሲያስተምሩ ከቁሳቁስ ባሻገር ያለው እውነተኛ ሀብት ዲን መሆኑን በግልጽ አስምረውበታል።
ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ስትባል ትገባለች ለሀብቷ ለዘሯ ለውበቷ እና ለዲኗ የዲን ባለቤት የሆነችውን ያዝ ያ ካልሆነ እጆችህ ይክሰሩ:: ቡኻሪና ሙስሊም
በሌላም ሀዲስ ነብዩ ﷺ ልጆቻችንን ለምን አይነት ሰው መዳር እንዳለብን ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:-
ዲኑንና አኽላቁን የምትወዱት ሰው ለእጮኛነት ከመጣችሁ አግቡት ይህንን ካላደረጋችሁ በምድር ላይ ትልቅ ፈተናና ታላቅ ብልሹነት ይከሰታል። ቲርሚዚ
ነቢዩ ﷺ ሀብቱ ስንት ነው? በሉ አልሉም «ዲኑና አኽላቁ እንዴት ነው በሉ» አሉ እንጂ። ምክንያቱም ገንዘብ በሌሊት መጥቶ በጠዋት ሊጠፋ የሚችል አላፊ ነገር ነው። ዲን ያለው ሰው ግን በሀብት ጊዜ አላህን ያመሰግናል በችግር ጊዜ ይታገሳል። ሚስቱን ቢወዳት ያከብራታል ባይወዳት እንኳ አላህን ስለሚፈራ አይበድላትም አያዋርዳትም ሀቋን ይጠብቃል በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያግዛታል::
የቀደምት መልካም ሰለፎች ለትዳር አጋር መረጣ የነበራቸው ሚዛን ቁሳቁሳዊ ሳይሆን ዲናዊ ነበር።
አንድ ሰው ወደ ታላቁ ዓሊም ሐሰን አል-በስሪ መጥቶ፦ ሴት ልጅ አለችኝ ብዙ ሰዎች ለእጮኛነት ጠይቀዋታል፤ ለማን ልዳራት? ብሎ ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ አሉት:- አላህን የሚፈራን ሰው አጋባት ምክንያቱም ቢወዳት ያከብራታል ቢጠላት እንኳ አላህን ስለሚፈራ አይበድላትም።
ከእዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ድንቅ ታሪክን ማውሳት እንችላለን::
የዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ አባት ሙባረክ በአንድ ባለሀብት የአትክልት ስፍራ ውስጥ ተቀጣሪ ዘበኛ ነበር። የቦታው ባለቤት አንድ ቀን መጥቶ ጣፋጭ ሮማን እንዲያመጣለት ጠየቀው። ሙባረክ ያመጣለት ሮማን ግን መራራ ሆነ። ባለቤቱም ተናዶ እዚህ ሁሉት አመት እየሰራህ ጣፋጩንና መራራውን አታውቅም እንዴ አለው።
ሙባረክም ጌታዬ ሆይ አንተ እንድጠብቅ እንጂ እንድቀምስ አልፈቀድክልኝም ስለዚህ አንድም ፍሬ ቀምሼ አላውቅም አለው።
ባለቤቱ በሙባረክ አላህን ፈሪነትና ታማኝነት እጅግ ተደነቀ። ባለቤቱ አንዲት ውብና ሀብታም ልጅ ነበረችው። ከየአቅጣጫው ያሉ ሀብታሞችና ባለስልጣናት ለትዳር ይጠይቋት ነበር። ባለቤቱ ሙባረክን ልጄን ለማን ብድራት ይሻላል ብሎ ጠየቀው።
ሙባረክም እንዲህ አለው፦
የጃሂልያ ሰዎች ለትዳር ዘርን ይመረጡ ነበር አይሁዶች ሀብትን ይመረጣሉ ነሷራዎች ውበትን ይመረጣሉ የዚህ ኡመት ሙስሊሞች ግን ዲንና አኽላቅን ይመረጣሉ። ስለዚህ የምትከተለውን ምረጥ::
ባለቤቱ የሙባረክን ጥበብና አላህ ፈሪነት አይቶ ውድ ልጁን ለደሃው ዘበኛ ለሙባረክ ዳረለት። አላህም ከዚህ ትዳር ለኡመቱ ታላቅ ብርሃን የሆኑትን ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክን ሰጣቸው:: ምን ግዜም ቢሆን አላህን ከሚፈራ ሰው የሚወጣው ዘር ከአላህ እገዛ ጋር የተባረከ እና በኸይር ላይ ያለ ነው::
ሀብት ውበት የትዳርን በር ያደምቃሉ የቤቱን ምሰሶ ግን አያቆሙም። የቤቱን ምሰሶ አጽንተው የሚያቆሙት ማዕበል ሲነሳ መርከቧን የሚያጸኗት የባል እና የሚስት ሶብር እና መልካም አኽላቅ ብቻ ናቸው። ይህ ደሞ የሚገኘው ትዳር መጀመሪያ ላይ አላህን በመፍራት እና በአኽላቅ ላይ ከተመሰረተ ነው::
ገንዘብ ተለዋዋጭ ነው ዛሬ ያለ ነገ ሊጠፋ ይችላል። ውበት አላፊ ነው በዕድሜና በጊዜ ሂደት ይረግፋል። ዲንና አኽላቅ ግን ዘላቂ ሀብቶች ናቸው!
ዲን ያለው/ላት አጋር ወደ ጀነት የሚያቀናን መንገድ ይመራል በኢባዳ በመልካም ስራ ያግዛል በችግር ጊዜ እንደ አለት ይቆማል።
አኽላቅ ያለው/ላት ድካም ይረዳል ስህተት በጥበብ በሶብር ያልፋል ቤትን በፈገግታና በሰላም ይሞላል።
ስለዚህ ለትዳር ዋነኛው መሰረት ልናረግ የሚገባን ዲን እና አኽላቅ ነው::
በእዚህ ግዜ እየተስተዋለ ያለው ግን በወርቅና በብር ትዳር እየተመዘነ ዲን እና አኽላቅ እየተዘነጋ ነው::
ትዳርን በወርቅና በብር ሚዛን ሳይሆን በዲን በአኽላቅ ሚዛን መመዘን በሰላም በሙሀባ የተሞላ ሕይወት ለመኖር ዋና ቁልፍ ነው።
አኽላቅ የሌለውን በሀብቱ ማግባት ወይም በውበቷ ተማርኮ ብቻ ማግባት መርዛም እባብን በወርቅ ሰንሰለት አጋይጦ እንደመያዝ ነው። ወርቁ ያምራል መርዙ ግን ገዳይ ነው።
ዲን እና አኽላቅ መሰረታችን ይሁን!!!
كتبه الفقير إلى عفو ربه ابو عبدالله
https://t.me/Abbu_Abdillah | 12 |
| 18 | 👉ለወቅታዊ የሀገራችንን ሰላም መታወክ የሻይኽ አብዱረዛቅ ብኑ አብደል ሙህሲን ሪሳላ ልጠቁማችሁ ተጠቀሙ በት።
أَمْنُ البِلادِ: أَهميَّتُه وَوَسائِلُ تَحقيقِه وحِفظِه
የሃገር ደህንነት: አሳሳቢነቱና የማረጋገጫ መንገዶቹ || አምኑል_ቢላድ
📝 ዝግጅት፡ ዐብዱረዛቅ ብኑ ዐብዲል ሙሕሲን አልበድር
🇸🇦 ቋንቋ: ዐረብኛ
📄 ገፆች፡ 43
🗂 የፋይል መጠን: 526.64 KB
📂 የፋይል አይነት፡ PDF
=
🍃👉https://t.me/abujemila25
🍃👉https://t.me/abujemila25 | 12 |
| 19 | 🌿🌿🌿በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት 🌿🌿🌿
عقيدة اهل السنة والجماعة
አቂደቱ አህለ ሱናቲ ወልጀማአ
▬▬▬▬▬▬ተ
▬▬▬▬▬▬▬ጀ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬ም
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ሯ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ል
🎙በኡስታዝ አቡ ዑሰይሚን ኢብኑ ሻፊ
ሐፊዘሁላሁ ተዓላ
➝➝➝➝ገባ
➝➝➝➝ገባ በሉ
🔔በሉ በደንብ ሸር ሸር አድርጉ
📱ቀጥታ ስርጭት ተጀምሯል አሁኑኑ እቺን ነክተው ይግቡ ይፈጠኑ 👇
https://t.me/YekelelaWetatoce_gemah?videochat=fc09c36af668fbaa16 | 23 |
| 20 | 🇪🇹 አይ ሀገሬ ማሳዘኖ በራስሽ መዥ ገር ሮች ተበሳ ቆልሽ።
ልጆችሽ አላዩሽ እነ ቢላል ( ኢብኑ ረባህ ) እነ ኡሙ አይመን፥ እነ ኢማሙ አህመድ አል_ጋዚ እነ ሀጅ ጦላሀ ጀእፈር።
አች የኔ ሀገር ኢትዮጲያ አሳዘሽኝ ዛሬስ የሶሀቦች ተቀባይ የነ ሩቅያ ቢንተ ረሱለ ሏሂ ﷺ እነ ጀእፈር አቢጦሊብን ተቀብለሺ በፍቅር ያስተና ገድሺ ነበር ሺኮ ሀገሬ።
አላህ ሆይ በቃበለን ስኪ ምህረቱን ወፍቀን ተጎዳን አልቻልንም ጌታየ በቃበለን።
🍃👉https://t.me/abujemila25
🍃👉https://t.me/abujemila25 | 17 |
