قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Open in Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
902
Subscribers
-424 hours
-167 days
+4030 days
Posts Archive
Repost from قَنَاةُ أَبِــي حَسَان عَلْي بن يُوسُف
ጊዜህን ተቆጣጠር፣ ሕይወትህን ቀይር፡ ምርታማነትን የምታሳድግባቸው ወርቃማ መርሆዎች
ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ ከምንም በላይ ውድ እና ሊመነዘር የማይችል ሀብት ነው። አንዴ ካለፈ በኋላ ተመልሶ የማይመጣ ሲሆን፣ እንዴት እንደምንጠቀመው ደግሞ የኑሮአችንን ጥራት፣ ስኬታችንን እና የእርካታ ደረጃችንን ይወስናል። ብዙዎቻችን ግን ጊዜያችንን በአግባቡ ባለመጠቀም፣ በቀን ተቀን እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሰጥመን፣ ዋና ዋና ግቦቻችንን ለማሳካት እንቸገራለን። ታዲያ ይህን ውድ ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ምርታማ፣ ተረጋግቶና ትርጉም ባለው ሕይወት ለመኖር የሚያስችሉ ወርቃማ መርሆዎች እነሆ፦
* የጊዜ አጠቃቀምህን ተረዳ (Track Your Time):
ምንም ነገር ከማስተካከልህ በፊት አሁን ያለውን ሁኔታ መረዳት ወሳኝ ነው። ለተወሰነ ጊዜ (ለምሳሌ ለአንድ ሳምንት) የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችህን በዝርዝር አስፍር። የትኞቹ ተግባራት ምን ያህል ጊዜ እንደወሰዱ፣ ጊዜህን የት እንዳጠፋህ በትክክል ስታውቅ፣ ለአባካኝ ተግባራት የሚውለውን ጊዜ ቀንሰህ ለአስፈላጊ ነገሮች ማዋል ትችላለህ።
* ግልጽ እና ሊለኩ የሚችሉ ግቦችን አውጣ (Set Clear & Measurable Goals):
ጊዜህን ለምን ዓላማ እንደምትጠቀም ማወቅ ግልጽ መንገድ ያበጅልሃል። ግቦችህ SMART (Specific-ግልጽ፣ Measurable-ሊለካ የሚችል፣ Achievable-ሊደረስበት የሚችል፣ Relevant-አግባብነት ያለው፣ Time-bound-የጊዜ ገደብ ያለው) መሆን አለባቸው። ትናንሽ ግቦችን በማስቀመጥ እና እነሱን በማሳካት ለትላልቅ ስኬቶች መዘጋጀት ትችላለህ።
* ተግባራትን ቅድሚያ ስጥ (Prioritize Your Tasks):
ሁሉም ተግባራት እኩል አስፈላጊ አይደሉም። አስቸኳይ እና አስፈላጊ የሆኑትን (ለምሳሌ የጊዜ ገደብ ያላቸው ፕሮጀክቶች)፣ አስፈላጊ ግን አስቸኳይ ያልሆኑትን (ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ ስኬት የሚረዱ ዕቅዶች)፣ አስቸኳይ ግን አስፈላጊ ያልሆኑትን (ለምሳሌ የተወሰኑ ኢሜይሎች) እና አስቸኳይም አስፈላጊም ያልሆኑትን (ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም) በመለየት ሥራህን አደራጅ። የአይዘንሃወር ማትሪክስ (Eisenhower Matrix) ይህንን ለመለየት ይረዳል።
* ከአባካኝ ነገሮች ራቅ (Avoid Distractions):
ስልኮች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማሳወቂያዎች፣ ኢሜይሎች እና አላስፈላጊ ንግግሮች የጊዜ ሌቦች ናቸው። ለአንድ ተግባር ስታተኩር እነዚህን ከጎን አስወግድ። ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በአንድ ነገር ላይ በማተኮር (ለምሳሌ የፖሞዶሮ ቴክኒክ) ምርታማነትህን ማሳደግ ትችላለህ። የስራ ቦታህ ንጹህ እና የተደራጀ መሆኑም ትኩረት እንዳይሰረቅ ይረዳል።
* የጊዜ አጠቃቀም መሳሪያዎችን ተጠቀም (Utilize Time Management Tools):
የቀን መቁጠሪያዎች (ዲጂታልም ሆኑ በእጅ የሚያዙ)፣ የዕቅድ ደብተሮች (planners)፣ የሞባይል አፕሊኬሽኖች (to-do list apps, reminder apps) እና ሌሎች መሳሪያዎች ተግባራትህን እንድትከታተል፣ ቀጠሮዎችህን እንዳትረሳ እና ጊዜህን በአግባቡ እንድታስተዳድር ያግዙሃል። የሚስማማህን መሳሪያ መርጠህ በቋሚነት ተጠቀምበት።
* ውክልና መስጠትን ተለማመድ (Practice Delegation):
ሁሉንም ነገር ራስህ ማድረግ አይጠበቅብህም። ሌሎች ሰዎች ሊያከናውኗቸው የሚችሉ ተግባራት ካሉ፣ በብቃት እና በሙሉ እምነት ውክልና መስጠትን ተማር። ይህ የእራስህን ጊዜ ለበለጠ አስፈላጊ እና ውስብስብ ተግባራት እንድታውል ይረዳሃል።
* እረፍት መውሰድ እና ራስን መንከባከብን አትርሳ (Don't Forget Breaks & Self-Care):
ያለ እረፍት በከፍተኛ ፍጥነት መስራት፣ በመጨረሻ ምርታማነትን ከመቀነስም በላይ ቃጠሎ (burnout) ያስከትላል። አጭር እረፍቶች መውሰድ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ከጓደኞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ የአእምሮ እና የአካል ጤናህን ይጠብቃል፤ ይህም ለተሻለ ምርታማነት መሠረት ነው።
* በየጊዜው ገምግም እና አስተካክል (Review & Adjust Regularly):
የጊዜ አጠቃቀምህ ፍጹም ላይሆን ይችላል። በየሳምንቱ ወይም በየወሩ የጊዜ አጠቃቀምህን እና ግቦችህን ገምግም። የትኞቹ ስልቶች እንደሰሩልህ፣ የትኞቹ እንዳልሰሩ እና ምን ማሻሻል እንዳለብህ ለይተህ እቅድህን አስተካክል። መማር እና ማደግ ቀጣይ ሂደት ነው።
ጊዜን በአግባቡ ማስተዳደር ማለት ሁሉንም ደቂቃ በሥራ መሙላት ማለት አይደለም። ይልቁንም፣ ለእራስህ፣ ለቤተሰብህ፣ ለስራህ እና ለግል እድገትህ ትርጉም ባለው መንገድ ጊዜ መመደብ ማለት ነው። ጊዜህን በስትራቴጂያዊ መንገድ ስትቆጣጠር፣ ውጥረትን በመቀነስ፣ ግቦችህን በማሳካት እና እርካታ የተሞላበት ሕይወት በመኖር የሕይወትህን መሪ ትሆናለህ። ዛሬውኑ እነዚህን መርሆዎች በመተግበር፣ ወደምትመኘው ምርታማ እና ሚዛናዊ ሕይወት ጉዞህን ጀምር!
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
Repost from Werabe university muslim students union
የሱና ሰዎች ለሌሎች መመራት ይጨነቃሉ እንጂ በሌሎች መሳሳት አይደሰቱም!!
ሀቅን የያዝከው በአሏህ ፍቃድ እንጂ በራስህ ብልህነት, እውቀት, ጉልበት… አይደለም: ስለሆነም በያዝከው ሀቅ ቀጥ ትል ዘንድ ጠዋት ማታ አሏህን መለመን ግድ ነው!
እንዲሁም በሌሎች መመፃደቅ, መሳለቅና በእነሱ ላይ ፈፅሞ ዱኣ ማድረግ የለብህም በል የነሱ መንገድ መሳት ሊያሳዝንህ ሊያስከፋህ እና ብሎም ዱኣ ልታደርግላቸው ነው ሚገባው ቀደምት ሰለፎች ይታወቁ የነበረው በእዝነት በትህትና በመምከርና ለሌሎች ዱኣ በማድረግ ነበር!
ዛሬ የኛን ሁኔታ ግን ከሰለፎች አንፃር ማገናዘቡ ያባት ይሁንና…
እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ አስመልክቶ ሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ:
"የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች በዓርሽ ጉዳይ፣ ቁርኣን የአሏህ ቃል በመሆኑ እና በአሏህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ መውረድ(ኑዙል) ጉዳይ ምክንያት በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱት በደል በበረታ ጊዜ፤ ወንድማቸው ሸይኽ ሸረፉዲን ተማጽኖ በማቅረብ በእነርሱ ላይ ዱዓ ማድረግ (እንዲጠፉ) ጀመረ።"
"ሸይኽ አል-ኢስላም ግን ከለከሉትና እንዲህ አሉት፦ 'በል እንዲህ በል፦ አላህ ሆይ! ወደ እውነት የሚመሩበትን ብርሃን ስጣቸው።'"
ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ይህን ንግግር አስመልክተው እንዲህ ይላሉ:
"ለአላህ ምስጋና ይሁንና! ይህ ምንኛ ታላቅ ስነ-ምግባር ነው! ምንኛ የላቀ ባህሪ፣ የነፍስ ዝቅታ (ትህትና) እና እውነትን መፈለግ ነው! በአላህ ይሁንብኝ! ይህች (ትምህርት) ብቻዋን ረጅም ጉዞ ሊደረግላት የሚገባት ፋይዳ ናት።"
"እኛ ካለንበት ሁኔታ ጋር ይህ ምንኛ ይራራቃል! ከእኛ መካከል አንዱ በትንሹ እንኳን ሲበደል ወዲያው ቁጣና ጥላቻ ይወርረዋል፤ በጠላቱ ላይም የዱዓ አይነቶችን ሁሉ ያዘንባል። አላህ ሆይ! ለእኛም ሆነ ስለ አንተ ብሎ ለበደለን ሰው ወደ እውነት የምንመራበትን ብርሃን ስጠን።"
አቡ ፈውዛን
Repost from Abdulkerim Hussein Channel
ደግ አንደበተ ርቱዑ ሼይኽ አዚዝ ቢን ፈርሃን አል-ዐነዚ አላህ ይጠብቃቸውና «ቢዩቱን ሙጥመኢንናህ» (የተረጋጉ ቤቶች) በተሰኘው ማራኪ ፕሮግራማቸው አማካኝነት የልባችንን እይታ የኑሯችንን ሁኔታ በጣፋጭ አንደበት በጥልቅ አይታ መቃኘታቸውን ቀጥለዋል።
«እረፍትን (ስኪናን) አታዘግዩ» በሚል ርዕስ ባቀረቡት ሦስተኛው ትምህርታቸው ውስጥ ከተናገሩት ምክር መካከል ይህ ላካፍላችሁ «ልጄ እህቴ ሆይ! ቤቶች የሚገነቡት በይስሙላና በውጫዊ ገፅታ ሳይሆን በተረጋጋ መንፈስና በሰኪናህ እንደሆነ እወቂ! ቤቶች በሀብት ብዛት ሳይሆን በኢማን በረካ ፀንተው ይቃናሉ።
ስለዚህም (ልጄ) አንቺ ልትፈልጊው የሚገባው ትልቁ ነገር የበዛ ሀብት ያለውን ሰው ሳይሆን፣ አላህን አብልጦ የሚፈራውን ሰው ነው! አንድ ወጣትም ሊፈልገው የሚገባው ትልቁ ነገር ውብ ፊትን ሳይሆን፣ ውብ ልብን ነው! እንዲሁም ቤተሰብ በአጠቃላይ ለልጃቸው ሊመርጡ የሚገባው ከአጪዎች መካከል እጅግ ሀብታሙን ሳይሆን፣ አደራ ጠባቂውንና አላህን ፈሪውን ነው...»
ወላሂ እጅግ ጠቃሚ ቁም ነገር ከምታገኙባቸው የህይወት ቅርስ ስለሆነ ፕሮግራሙን እየገባችሁ ተከታተሉ! ሸይኹን አላህ ይጠብቃቸው፤ መልካም ምንዳን ይክፈላቸው፤ በእውቀታቸውና በሥራቸውም በረካ ያድርግላቸው...!
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
-
የአላህ መጽሐፍ ቁርአን ወደ እኛ መቅረቡ እንዴት ያለ የሚያምርና ማራኪ ነው፣ ልባችን ግን ከእሱ የራቀ ነው! ቁርዓንን ማስተንተን ትልቅ ጸጋ ነው፣ ዋጋውን የተነፈጉ ሰዎች ግን በትክክል የማያቁት ናቸው።
አንቀጾቹን የሚያዩ ዓይኖች ብቻ አይደሉም፣ ነገር ግን ልብ መመሪያውን ቆም ብሎ በማሰብ፣ ምክሩን ማስተንተን፣ በብስራቶቹና በማስጠንቀቂያዎቹ መነሳሳት፣ እና በዚህ ሕይወትና በመጨረሻው ዓለም ውስጥ አንድን ሰው የሚጠቅመውን ማግኘት ነው።
ቁርዓን የልብ ጓደኛ፣ የነፍስ ምንጭ እና የመንገዱ ብርሃን ነው። አንድ ባሪያ ከቁርዓን ጋር ባለው ጓደኝነት የበለጠ ውብ በሆነ ቁጥር፣ አላህ ትርጉሞቹንና መመሪያዎቹን የበለጠ ይከፍትለታል፣ ልቡን ያድስለታል፣ ኢማኑን እና ግንዛቤውን ይጨምራል።
አላህ ሆይ! ክቡር የሆነውን ቁርዓን የልባችን ብርሃን፣ የሐዘናችን ማስወገጃ እና ጭንቀታችንን የሚያስወግድ አድርግልን። ከቁርአን ሰዎች መካከልም አድርገን፣ የአንተ እና የመረጥካቸው ሰዎች አድርገን ያረብ!!
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
⭐️ ክፍል 🔢
🔢🔢 "እገሌን እገሌ ሙብተዲዕ ብሎታል እገሌ ደግም አላለውም ሙብተዲዕ ያላለውን ወደ ተባለው ታስጠጋዋለህ?" የሚለውን የኡስታዝ ንግግር ካሰፈርክ በኋላ ይህ ማለት "አንድን ሰው ሙብተዲዕ ለማለት የጋራ ስምምነት ያስፈልጋል ማለቱ ነው" በማለት የፃፍከው ያንተ የግንዛቤ ዝግጠት፣ ስርዓት አልበኝነትህና ሰዎችን የምታጠምበት ሴረኛ ብዥታህ ነው። እስኪ በአላህ ልጠይቅህ ፦ -የንግግሩ ተዘዋዋሪ መልዕክት ይህን ያስይዛል ብንል እንኳ- "የአንድ ሰው ንግግር ተዘዋዋሪ መልዕክቱ ባለቤቱ እስካላመነበት ድረስ እንደ ቀጥተኛ ንግግሩ አይወሰድም" የሚለውን መርህ አታውቅም ወይ? አላህን አትፈራም!? ሴራህን ምን ከባድ አደረገው!!
🔢🔢 "ኢብኑ ሙነወር ሙዋዘናን ለማስረፅ በረሱልﷺ ላይ ዋሽቷል" ትላለህ። አንተ አታላይ! ኢብኑ ሙነወር በዚያው የድምፅ ፋይል "ረድ ሲደረግ ሙዋዘና (እርምት በሚሰጥ ጊዜ መልስ የሚሰጥበትን አካል ጥሩና መጥፎ ጎኑን ማውሳት) አይፈቅድም" ብሎ መግለፁን አልሰማህም ነው? ስለዚህ ጉዳይ ዙሪያ በቻናሉም በቂ ማብራሪያ ሰጥቷል። ሲቀጥል "የተወሳው የረሱልﷺ ንግግር በኸዋሪጆች እንዳትሸወዱ ብሎ ይበልጥ ለማስጠንቀቅ ነው" እያለ በግልፅ ነውኮ የተናገረው። ድምፁ በሪከርድ ተቀምጦ ሳለ ለምን በዚህ ልክ መዋሸትና መቅጠፍ አስፈለገ!? ትንሽ እንኳ አታፍርም ፈጣሪህን!?
🔢🔢 ሌላው "ሸይኽ ረቢዕ አሻዒራዎችን አወድሰዋል ብሎ ዋሽቶባቸዋል" "ሸይኹል አልባኒ ሰይድ ቁጥብን አወድሰዋል" ብለህ ያወሳኻው ካንተው ከራስህ የሆነ ቅጥፈት ነው። ምክኒያቱም እነዚህ ሁለቱ ኢማሞችም ይሁኑ ሌሎች አኢማዎች በከፊል የቢድዓ ባለቤቶች ላይ አንዳንዴ የተገደበን ውዳሴ አንዳንዳንዴ ደግሞ ያለ ገደብ ማወደሳቸው በጣም የታወቀ ጉዳይ ነው።
ለምሳሌ፦ ሸይኹል አልባኒ ሰይድ ቁጥብን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦ "ይህ ታላቁ ኡስታዝ ሰይድ ቁጥብ ነው" [ሙኽተሰሩል ዑሉው - ገፅ 59] እንደዚሁ ሸይኽ ረቢዕ በአሽዓሪይነታቸው ታዋቂ የሆኑትን አስ'ሱዩጢይን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦ "በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ የፃፏቸው ድርሳናቶቻቸው (ኪታቦቻቸው) ተቀባይነት አላቸው" [መጅሙዑል ኩቱብ ወርረሳኢል 3/283] ምክኒያቱም የቢድዓ ሰዎችን እና ኪታቦቻቸውን በተገደበ መልኩ ማወደስ ወይም ልምድ ተደርጎ ሳይያዝ ያለምንም ገደብ ማወደስ ከሱና አያስወጣም። የቢድዓ ባለቤቶችን ያወደሰ ከሱና ውጭ የሆነ ሙብተዲዕ ነው አይባልም። እንዲሁ በዘፈቀደ ንግግሩ ልቅ አይደረግም።
🔢🔢 "ኢብኑ ሙነወር ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ኣደም ከቀርዷዊ ንግግር ይወስዳሉ" "ብሎ ዋሽቶባቸዋል" ያልከው ፀሃይ ረፋድ ላይ ለማንም ግልፅ እንደምትሆነው ፍንትው ያለ ቅጥፈትህ ነው። ቅጥፈትህን ምን የገዘፈ አደረገው!! ምን አይነት አይን ያወጣ ቀጣፊ ነህ ባክህ!? ሸይኹ ከቀርዷዊ ንግግር መውሰዳቸው በኪታባቸው [ዘኺረቱል ዑቅባ 22/171 - 172] ባቡ ዘካቲል ወሪቅ [ሐዲስ ቁጥር 2473] ን ሲያብራሩ ተፅፎ የተቀመጠኮ ነው። ኢብኑ ሙነወር በቻናሉ ይህንን እስከ ገፁ ድረስ ከማስፈሩ ጋር በርሱ ላይ በዚህ ልክ መቅጠፍህ ካመላከተ የሚያመላክተው በዚያ ኢላማውን በማይስተውና የመታው መዳኛው አዳጋች በሆነው ተወርዋሪ ቀስቱ ያደረሰብህን የህመም መጠንና ያንተ ብቸኛ አላማህ እንዲህ አይነት ፀያፍ ውሸት እስከመዋሸት ቢያደርስህም እንኳ እርሱን መጣልና መጣል ብቻ እንደሆነ ነው።
🔢🔢 "ሰለፊዮችን መዳኺላ ብሎ ተሳድቧል" ያልከው ካንተ የሆነ ውሸት ነው። ውድቀትህን ምን የበዛ አደረገው!? አዎ ኢብኑ ሙነወር ለማንም ይሁን ለማን ማንኛውንም አይነት ተዓሱብ (አጉል ወገንተኝነት) ይቃወማል። ከፊል ወጣቶች በሐቅም በባጢልም ለኸይኽ ረቢዕ ወገንተኝነትን ሲያንፀባርቁ "መድኸሊይ አትሁን!" ሲል መክሯል። ይህ የተስተካከለ ምክር ነው። ምንድነው የፈለግከው!? ይህ (አጉል ወገንተኝነትን መቃወም) የቀደምቶች መንገድ አይደለምን? ይህን ነው ከእርሱ ያየነው። ሲቀጥል ምን እንደፈለገበት በቻናሉ በበቂ መልኩ አብራርቷልኮ።
🔢🔢 ሌላው "ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲል መድኸሊይን ተችቷል" ያልከው በመጀመሪያ ይህም ካንተ የሆነ ውሸት ነው። እውነተኛ ከሆንክ ማስረጃህን አቅርብ። ሲቀጥል ሸይኽ ረቢዕኮ ብርቱ የሆነን ትችት በሸይኽ ሙሐመድ አልመድኸሊይ ላይ ሰንዝረዋል። ሸይኽ ረቢዕ ሙመይዕ ሙብተዲዕ ናቸው ትላለህ!? ትዳፈራለህ ወይ!?
🔢🔢 "እርሱ የአላህን ንግግር ጠምዝዟል" ትላለህ ሱብሓነላህ!! ለአላህ ያለህን ፍራቻ ምን አናሳ አደረገው!! ይህ አንተ ከአደብ እጣ እንደሌለህ ነው የሚያሳየው። ለአላህ ጥራት ይገባው ኡስታዝ የእርሱን ንግግር ከመጠምዘዝ። ልጠይቅህ ፦ ሚዛን የሚደፋ ጥቅም ወደ ሙስሊሞች እስካመጣ ድረስ ከማንም አካል ጋር ትብብር ማድረግ እንደሚቻል ከማመላከት አንቀጿን ያስወጣት ምንድነው?
🔢🔢 በክር አቡ ዘይድ፣ ሸይኽ ረቢዕንና ሰይድ ቁጥብን በተመለከተ ያወሳሃውማ ካንተ የእውር ድንብር ጉዞና መድረቅረቅ ጭምር ነው። ይህን በተመለከተ የተከበረው ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ አልከሚሲ በቂና ምጡቅ ማብራሪያ ስለሰጠህ ከዚህ ወሬን ማስረዘም አልሻል።
🔢🔢 "የጀርሕ እና የተዕዲልን ባለቤትነት ከዑለማኦች ውድቅ አድርጓል" ትላለህ። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ካንተና አንተን ከመሰሉ እውተኛ አንደበት የሌላቸው፣ የአላህ ፍራቻ የሳሳባቸው፣ የመጣላቸውን ሁሉ የሚናገሩና ስለራሳቸው -ልክ እንደ እብድ- "ማይክ በሚጨብጡና ወንበር ላይ በሚወጡ ጊዜ የሚናገሩትን እንደማያውቁ" የገለፁ ከሆኑት ጉዶች ነው ውድቅ ያደረገው።
✅ በመጨረሻም "እነዚህ ኢብኑ ሙነወር ከሙብተዲዖች ሰልፍ እንደሆነ የሚጠቁሙ ከፊል ጥመቶቹ ናቸው" ትላለህ። የት አሉና!? እንዲሁ ካንተ የሆነ ደረቅ ሙግት፣ ውሸትና ቅጥፈት ሰለፊዮችን ከሙብተዲዖች ሰልፍ ያደርጋል እንዴ!? ዓቅልህ የት ሄደ ሰውየ!? ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለም ወይ!?
✅ የሰለፊያ ወጣቶች ሆይ! በምቀኝነት እሳት ከተቀጣጠለችው ልቦቻቸው የመነጨ የሆነን የወደቀና ፈር የለቀቀ የኢጅቲሃዳቸውን ውጤት ካልተሸከማቹህ እያሉ ሰዎችን ሱሪ ባንገት የሚሉትን፣ የአህለሱናዎችን ጀማዓ መበታተንና ወጣቶችን የሙሪድነት ምርኮኛ ማድረግ የሚፈልጉትን አዲሶችን ሓዳዲዮች ተጠንቀቁ!! ተጠንቀቁ!! እላቹኋለሁ።
🤲 በሐቅ ላይ አንድ እንዲያደርገንና በሱና ላይ እንዲያፀናን የታላቁን ዓርሽ ባለቤት ተከበረውን አላህ እለምነዋለሁ። በመልዕክተኛው ﷺ በባልደረቦቻቸውና በተከታዮቻቸው ላይ የአላህ ውዳሴውና ሰላሙ ይስፈን።
✍️ የሰለፍዮች ወዳጅ አቡ ዒምራን
📆 ታህሳስ 05/2018 ዓ.ል
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
🔢🔢أما قولك "فلان بدعه فلان الخ" ثم قولك "يعني لا بد من اشتراط الإجماع فى التبديع الخ" فهذا من قلة فهمك وسوء أدبك ومن تلبيساتك الخادعة المضلة، أسألك بالله! - على فرض كونه هذا لازمَ قوله - أما تعلم أن لازم القول ليس بقول ما لم يلتزمه القائل!؟ ألا تتقي الله يا حسين!؟ ما أعظم مكيدتك!!
🔢🔢أما قولك إنه كذب على الرسول👑الخ فيا غشاش أما علمت أن ابن منور قد بيّن فى ذاك المقطع نفسه أن الموازنة فى حال الرد لا تجوز فضلا عن أن يقررها، وبين هذا الأمر فى قناته بيانا كافيا، وأيضا هو قد وضح أن كلامه👑 هذا على الخوارج لزيادة التحذير والتنفير من الاغترار بهم، لما ذا الكذب والبهتان -وصوته مسجل- ؟ أما تستحي من الله!؟
🔢🔢وأما ما ذكرته من أنه "كذب على الشيخ ربيع المدخلي 📍 بأنه أثنى على الأشاعرة" "وأنه كذب على الإمام الألباني بأنه أثنى على سيد قطب الخ" فهذا أيضا من كذباتك أنت، فثناء هذين الإمامين وغيرهما من الأئمة على بعض أهل البدع ثناء مقيدا تارة ومطلقا أخرى معروف جدا،
فمثلا يقول الشيخ الألباني عن سيد قطب "فهذا هو الأستاذ الكبير سيد قطب" [مختصر العلو ٥٩] وكذلك الشيخ ربيع يقول فى ترجمة السيوطي الأشعري "...وتصانيفه في كل فن من الفنون مقبولة..،" [مجموع الكتب والرسائل ٢٨٣/٣] لأن الثناء على أهل البدع وكتبهم ثناء مقيدا، أو مطلقا من غير اتخاذه عادة له لا يخرج من السنة، فالذي يثني على أهل البدع لا يقال إنه مبتدع خارج من السنة، ما يطلق الكلام هكذا على عواهنه يا رجل، ما هكذا يا سعد تورد الإبل!!
🔢🔢وقولك "إنه كذب على العلامة محمد علي آدم الإتيوبي بأنه ينقل عن القرضاوي" كذب واضح منك وضوح الشمس فى رابعة النهار، ما أعظم فريتك يا كذاب! فنقل الشيخ 🤎 عن القرضاوي ثابت مسطر فى كتابه ذخيرة العقبى بشرح المجتبى [٢٢/ ١٧١ - ١٧٢] فى باب زكاة الورق حينما يشرح حديثا رقمه ٢٤٧٣، وافتراءك على الأستاذ مع أنه أثبت هذا مع ذكر صحيفته فى قناته إن دل إنما يدل على قدر ألمك بسهمه الثاقب الذى قل من يبرأ إذا أصابه، وعلى أنك إنما تريد مجرد إسقاطه ولو أداك إلى مثل هذا الكذب الفاحش،
🔢🔢وقولك "إنه رمى السلفيين بأنهم مداخلة الخ" أيضا كذب منك، ما أكثر زلاتك!! فنعم ابن منور 🇧🇼 ينكر أيّ تعصب لأيّ شخص من الأشخاص، ونصح الشباب حين رأى بعض من يتعصب له بالحق والباطل فقال لا تكن مدخليا!! وهذا نصح سديد منه، ما هذا الذى تريده يا هذا أليس هذا - أعني عدم التعصب لأي كان - منهج السلف؟ وهذا الذي رأيناه منه ووضح ما أراده فى قناته بما يشفى ويكفي،
🔢🔢وما ذكرته من أنه طعن فى الشيخ محمد هادي المدخلي الخ " أولا هذا أيضا كذب منك هات برهانك إن كنت صادقا، وثانيا الشيخ ربيع طعن أشد الطعن فى الشيخ محمد بن هادي المدخلي فهل تتجرأ فتقول إن ربيعا مميع ومبتدع!؟
🔢🔢أما قولك "إنه حرف كلام الله الخ" فيا سبحان الله ما أقل ورعك أيها الطائش!! وهذا قد يدل على كونك لا حظ لك من الأدب، حاشا لله من أن يحرف الأستاذ الكريم كلام الله، أسألك ما الذي أخرج الآية عن عمومها إذا كان في التعاون مع أي كان مصلحة راجحة عائدة للمسلمين!؟
🔢🔢وأما ما ذكرته بما يتعلق ببكر أبو زيد والشيخ ربيع مع سيد قطب، من تخبطاتك وتعنتاتك التي قد بينها لك الأستاذ الفاضل خضر أحمد الكميسي 🇧🇼 بساطع البيان فلا أريد إطالة الكلام حوله،
🔢🔢وقولك "إنه نفى أهلية الجرح والتعديل الخ" إنما نفى أهلية الجرح والتعديل منكم ومن أمثالكم الذين لا صدق ولا ورع عندهم، ويتكلمون بكل ما بدا لهم، والذين أفصحوا عن أنفسهم أنهم لا يدرون ما يقولون حين صعود المنبر -كالمجانين- وأخذ ميكرافون،
✅وأخيرا تقول "هذه بعض انحرافاته الدالة على انضمامه إلى صفوف المبتدعة الخ" أين هي!؟ هل مجرد الادعاء والكذب والبهتان منك يجعل السلفيين من صفوف المبتدعة، أين ذهب عقلك؟ أليس منكم رجل رشيد!؟
✅ أقول لكم يا شباب السلفيين الحذر الحذر من الحدادية الجدد الذين يلزمون الناس بنتائج اجتهاداتهم الخاطئة الهابطة الصادرة من قلوب اشتعلت بنار الحسد والحقد، ويريدون تمزيق جماعة أهل السنة والجماعة وجعل الشباب أسير التقليد،
🤲أسأل الله الكريم رب العرش العظيم أن يجمع شملنا على الحق ويرزقنا الثبات على السنة وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم،
🖊كتبه محب السلفيين أبو عمران الأثري
رابطة القناة⬅
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲
🛜❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
☪☪☪☪☪
⭐️ ክፍል 🔢
✔️ ይህ ከለተሞ አጋፋሪዎች አንዱና የውሸት ካዝና የሆነው ሑሰይን ስልጤ -እንደእርሱ አስተሳሰብ- ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከሱና ውጭ ስለሆነባቸው ነጥቦች ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ላይ የተሰጠ እርምት ነው።
1️⃣ በመጀመሪያ በንግግሩ መግቢያ "ቀደምቶች -ወደ አላህ መቃረብን በማሰብ- የቢድዓ ሰዎችን መጥላትና ከእነርሱ መራቅ ላይ የጋራ ስምምነት አላቸው" ሲል ያወሳው ንግግር ምንም እንከን የሌለበትና እኛም እስከዛሬም ይሁን ወደፊት የምናምንበት ነው ኢንሻአላህ። ነገር ግን ልጠይቅህና ሑሰይን፦ ኢብኑ ሙነወር ይህንን መሰረት ነቅፎ የቢድዓ ሰዎችን መውደድና መቅረብ ይፈቀዳል ብሏል ወይ? በፍፁም! ካላለ ለምንድነው ይህን ንግግር ያጣቀስከውና አስከትለህም "ይህንን የተቃረነ..." ብለህ የፃፍከው? "አይ ብሏል" ካልክ ደግሞ ማስረጃህን ማቅረብ ይጠበቅብሃል።
2️⃣ "የቢድዓ ሰዎችን ያወደሰ ወደ እነርሱ ይጠጋል" የሚለው ከታላቁ ዓሊም ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ይዘህ ያጣቀስከው ንግግር በውስጡ ሰፊ ዝርዝር ያለበትና በቦታው የተዳሰሰ ጉዳይ ነው። ቀደም ሲል በዚህ ዙሪያ እዚህ ከመድገም በሚያብቃቃኝ ልክ ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ ሐፊዘሁላሁ በቂ ማብራሪያ ልኮልሃል ብየ አስባለሁ። (17ኛው ነጥብ ላይ በስሱ ተወስቷል)
3️⃣ "ኢብኑ ሙነወር በተብዲዕ እና በጀርሕ ወተዕዲል ነጥብ ተፈትኗል" ያልከው (ከዕውነት የራቀ ጉዳይ ነው።) በእውነቱ "በነዚህ ነጥቦች የተፈተኑ" ለመባል ተገቢዎቹ ከሰለፊዮች ይልቅ እናንተው ናቹህ። ይህ አላህ ሐቅን ከማየት አይኑን የጋረደውና ልቡን ያወረበት ሰው ካልሆነ በስተቀር ለማንም አካል ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።
4️⃣ ኢብኑ ሙነወርንና ከእርሱ ጋር ያሉትን በአላዋቂነት መግለፅህ ካንተ እና አንተን ከመሰሉ ሐቅን ከመቀበል በኩራትና ምቀኝነት የተበረዘ መሃይምነት የከለከላቸው፣ በተቃረናቸው አካል ላይ በዒልምና በአደብ መልስ መስጠት ከተሳናቸው መንገድ የሳቱ አካሎች የተለመደ ጉዳይ ነው። እንዲህ አይነቱ አካል የበርካቶች የሂዳያ ሰበብ የሆኑትን አንፀባራቂ ኮከቦች በአላዋቂነት ማንቋሸሹ የሚደንቅ አይደለም።
5️⃣ "ኢብኑ ሙነወር ከኢብኑ መስዑድ መርከዝ ተከላክሏል" ያልከው ግልፅ ቅጥፈት ነው። ይልቁን ከእርሱ የምናውቀው ሐቅን በግልፅ መናገርና ከእነርሱም ይሁን ከማንኛውም የቀደምቶችን ጎዳና ከታቀረነ አካል ማስጠንቀቁን ነው። እርግጥ ነው እርሱ እንደናንተ ልማድ መልስ ሲሰጥ የሌለባቸውን በመለጠፍ መሆን የለበትም የሚል አቋም አለው። ሌላው "ሸይኹን አናቀውም.." ስትል በጣም አስደነቅከኝ። ቆይ አንተ እና መሰሎችህ የእርሱን ሸይኽ አለማወቃቹህ "ሸይኽ የሌለው ጠማማ ሙብተዲዕ ነው" ያስብላል ማለት ነው!? ሱብሓነላህ!!
6️⃣ "ዑለማኦችን ይተቻል" ስትል የሌለባቸውን በመለጠፍ ከሆነ ፍላጎትህ ይህ ገሃድ የወጣ ቅጥፈት ነው። ያለባቸውን ጥመት ማጋለጡንና ያመጡትን ቢድዓ በማብራራት ለወጣቶች ማስገንዘቡን ከሆነ "ዑለማኦችን ተችቷል" የምትለው ይህ ሊመሰገንበት የሚገባው መልካም ስራው እንጅ ሊወገዝበት ፈፅሞ አይገባም።
7️⃣ "ከመርከዙ ሰዎች በመከላከል ብዙ ፅሁፎችን ፅፏል" ያልከውም ግልፅ ቅጥፈት ነው። ብዙ ፅሁፎች ይቅርና አንድም ፅሁፍ አልፃፈም። በዕውር ድንብሩ በሚፈነጨው የለተሞ መንጋ ላይ የሰጠውን እርምት ከሆነ "ከመርከዙ ሰዎች መከላከል" እያል የምትጠራው ይህ የግንዛቤህ ችግር ነው። (አረዳድህ በዚህ ልክ ከሆነ) አንተ መንሃጅህ ይቅርና አዕምሮህ እራሱ መጠገኑ አስቸጋሪ የሆነ ክፍተት እንዳለበት ነው የሚጠቁመው። ነቃ በልና ጊዜው ሳያልፍብህ ነፍስህን አድናት።
8️⃣ "የቢድዓ ሰዎችን ማወደስ ከሱና አያስወጣም ይላል..." ያልከው ከዕውቀትህ አናሳነትና ተከታዮችህን የምታምታታበት ብዥታህ ነው። በዚህ ዙሪያ ቀደም ሲል ጠቁሜሃለሁ ኡስታዝ ኸዲር የላከልህን ማብራሪያ ተመልከት። ሌላው ኢብኑ ሙነወር በብዙ ዑለማኦች ላይ ቀጥፎባቸዋል ስትል የቀጣጠፍከው ወደፊት በዝርዝር ስታወሳው እመጣበታለሁ ኢንሻአላህ።
9️⃣ "ኢብኑ ሙነወር መጀመሪያ ላይ የመርከዙ ሰዎች ወደ ኢኽዋኖች ተጠግተዋል ሲል ገልፆ ነበር" ስትል የእነርሱን ሑክም ይሰጣሉ ብሏል ማለት ከሆነ ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው። አይ ያስጠነቅቅ ነበር ለማለት ከሆነ የፈለግከው አሁንምኮ ባቅሙ ልክ እያስጠነቀቀ ነው ያለው። ደግሞ ሌሎችን "ንቁ!" ትላለህ! ልትነቃኮ የሚገባህ አንተው ነበርክ።
1️⃣0️⃣ሌላው "በእነርሱ ላይ ረድ ከመስጠት አቁሟል" ትላለህ። መች አቆመና ይልቁን በዚህ አመት እራሱ ፅፎባቸዋልኮ። ነገር ግን የእርሱ ረድ እንደናንተ ረድ አሰጣጥ በስድብ፣ ሰውን በማንቋሸሽና በጉራ የተበረዘ ሳይሆን ሲቀር "ረድ አቁሟል" በማለት ከሰስከው። ደግሞኮ ረድ መስጠት የነፍስ ወከፍ ግዴታ አለመሆኑንና እርሱ ከእናንተ በፊት የነዚህን አካሎች ጥፋት ማጋለጡን ጠንቀቅህ ታቃለህ።
በመሰረቱ ዝም ቢልም እንኳ ሊወቀስ አይገባውም። ምክኒያቱም ዝም ማለቱ በከፊል ወንድሞቹ ረድ እና ማብራሪያ በመደገፍ ወይም በመማር ማስተማር እና አሕባሽን በመሰሉ በጥመት አንጃዎች ላይ ረድ በማድረግ ቢዚ በመሆኑ ነውና። ልጠይቅህና (እንዳስፈላጊነቱ መልስ ከመስተጠት አላቆመም) ነገር ግን ዝም ቢል ይህ ዝምታዝው ከሱና ያስወጣዋል ወይ?
1️⃣1️⃣ "ለመርከዙ ሰዎች ምክኒያት ይደረድር ጀመር" ስትል አሁንም የፈልግከው በሐቅም በባጢልም ማለትህ ከሆነ ይህም የወጣለት ውሸት ነው። ካልሆነ እናንተ መረን ስትዘሉ "በዲናቹህ ያለአግባብ ድካ አትለፉ፣ በሰዎች ላይ ስትናገሩ የቢድዓ ባለቤቶችም እንኳ ቢሆኑ ወሰን አትለፉ" ብሎ እርምት መስጠቱ ይህ አሁንም ወደፊትም የምንናገርበት የሆነ ጥርጥር የሌለበት እውነት ነው።
1️⃣2️⃣"እነ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድንና መሰል የሱና መሻኢኾችን ተችቷል ... ወደ ሓዳዲያም አስጠግቷቸዋል" ያልከው ይህ ከመጠቅ እይታውና ሐቅን ግልፅ ከማድረጉ ነው የሚቆጠረው። ምክኒያቱም እነዚህ አካሎች ጥቂት የማይባሉ የሓዳዲያ መገለጫዎች ይንፀባረቅባቸዋልና። በዚህ ዙሪያ በሌላ ጥናት እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ።
1️⃣3️⃣"ከዚያም የሙብተዲዖችን መርሆች ማሰራጨት ያዘ" ያልከው ከፀያፍ ቅጥፈቶችህ አንዱ ነው። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ቢድዓን ማሰራጨት ይቅርና) ከወጣትነቱ ጀምሮ ከኢስላምና ከረሱልﷺ ሱና ዘብ ቁሞ ከመከላከል ተወግዶ አያቅም። ይህ አላህ ፊት የምንመሰክርበት ጉዳይ ነው። ከእርሱ ኸይርን እንጅ አናውቅም። እኛ እንዲህ ነው የምናስበው። የውስጡን መርማሪው አላህ ነው። በአላህ ላይ ማንንም አናጥራራም።
1️⃣4️⃣ሌላው "ጀርሕ እና ተዕዲል ጥረትን (ኢጅቲሃድን) ያስተናግዳል፤ በዚህም ሰዎችን ማስገደድ (ኢልዛም ማድረግ) አይገባም" ብሏል ያልከው። ይህ ቀደምቶችም የኋለኞችም የሱና ዑለማኦችና ታላላቅ የሐዲስ ሊቆች የሄዱበት ፍንትው ያለ እውነት ነው። ኢብኑ ሙነወር አዲስን ነገር አላመጣም። በዚህ ዙሪያ ውይይት ከፈለግክ የሰለፊዮች በር ክፍት ነው። ነገር ግን እናንተ የፍርሃት ጥጎች ናችሁ እንጅ።
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy
👉 የለተሞው መንጋ የውሸት ካዝና አጋፋሪያቸው ሑሰይን ስልጤ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ላይ የቀጣጠፈውን ፅሁፍ ሲፈተሽ፦
🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲
🎤❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
☪☪☪☪☪
↩️ رد على أحد المفترين من زعماء اللتميين المسمى بحسين السلطي فى ما كتبه جوابا لمن سأله -بزعمه- عن أسباب خروج الأستاذ ابن منور 🤩 تعالى عن السلفية وانحرافه عن الجادة،
1️⃣أولا: ما ذكره فى مبدأ جوابه من اتفاق السلف على بغض أهل البدع والبعد عنهم تقربا لله فهذا لا غبار عليه وهو الذى ندين الله به من قبل ومن بعد 🛒🌟تعالى، ولكن أسألك يا حسين هل ابن منور يخالف هذا الأصل فيجوّز محبة المبتدعة والقرب منهم!؟ حاشا وكلا! وإلا فلِم ذكرته فأردفته بقولك "فمن خالف الخ"!؟ وإن كنت تزعم هذا فأتنا ببرهانك،
2️⃣أما ما ذكرته من العلامة ابن باز 🌟 من أن من أثنى على أهل البدع يلحق بهم" ففيه تفصيل عريض مذكور فى موضعه، أرى أن الأستاذ خضر أحمد الكميسي 🇧🇼 تعالى قد أهدى لك من هذا التفصيل من قبل بما يغني عن إعادته هنا،
3️⃣وأما قولك إن ابن منور قد ابتلي بمسألتي التبديع والجرح والتعديل فالأجدر بأن يوصف بذاك الابتلاء حقيقة أنتم ممن ذكرت من السلفيين، وهذا أمر مشاهد لكل أحد إلا لمن أعمى الله بصره وطمس بصيرته،
4️⃣وأما تجهيلك لابن منور ولمن معه من السلفيين فهذا شيء معهود منك ومن أمثالك التائهين الذين منعهم من قبول الحق الجهل الممزوج بالكبر والحسد والحقد، وعجزوا من الرد على مخالفيهم بالعلم والأدب، فلا غرابة مَن هذا بعض نعوته أن يجهّل مصابيح الدجى ومنار الهدى،
5️⃣وأما قولك "إن ابن منور تصدى بالدفاع عن مركز ابن مسعود" فهذا بهت بحت، بل المعروف منه الصدع بالحق والتحذير منهم ومن كل من أظهر خلاف ما عليه السلف الصالح، نعم هو لا يتجاوز الحد فى الرد عليهم فيرميَهم بما ليس فيهم كما هو عادتكم أيها اللتميون، وقولك "لا ندري شيخه الخ" من عجائبك، فهل يلزم من كونك لا تعلم أنت وأمثالك شيوخه أنه لا شيخ له وأنه ضال مبتدع!؟ فيا سبحان الله!!
6️⃣وما ذكرته من أنه يطعن فى العلماء إن كان مرادك بما ليس فيهم فهذا أيضا كذب واضح كوضوح الشمس فى رابعة النهار، أما بيان انحرافاتهم وتوعية الشباب بما أحدثوه من البدع والمنكرات فهذا من مكروماته فلا ينبغي أن يذم عليه أصلا، بل يمدح به،
7️⃣أما قولك إنه كتب كتابات فى الدفاع عن هؤلاء فهذا كذب بحت فهو لم يكتب كتابا واحدا فضلا عن الكتابات وإن كنت تسمي الرد على اللتميين المتهورين دفاعا عن أصحاب المركز فهذا من سوء فهمك بل يدل على أن فى عقلك خللا صعب المسد فضلا عن منهجك، فأفق وداوِ نفسك قبل فوات الأوان،
8️⃣وقولك إنه قرر أن الثناء على أهل البدع الخ من قصور علمك، وتلبيساتك على أتباعك، وقد أحلتك آنفا فارجع إليه إن شئت، أما تقوّلك على ابن منور بأنه افترى على عدد من العلماء فسيأتي الرد عليه حين تذكره إن شاء الله تعالى،
9️⃣أما ما ذكرته بعد تنبيهك لغيرك -وأنت خليق بالتنبّه من من سواك- من أن ابن منور كان فى أول أمره بيّن "أن أصحاب المركز انضموا إلى الإخوان المسلمين" فإن كان مرادك بالانضمام كونهم مثلهم فى الحكم فهذا بهتان عظيم وافتراء وخيم، وإلا فما زال يرد عليهم ويحذر الناس منهم إلى الآن قدر المستطاع،
0️⃣1️⃣وأما ما ذكرته "من أنه توقف عن الرد عليهم،" فلم يتوقق بل إنه كتب في هذه السنة، ولكن لما كان رده عليهم ليس على أسلوب ردكم الممزوج بالشتم وتنقص الغير والتطاول على المردود عليه لمزته بأنه ساكت، مع أنك تعلم أن الرد فرض كفاية وأنه رد وزيّف أباطلهم قبلكم.
ولو سكت -فرضا- لا يلام عليه لأن سكوته إما اتكالا على رد وبيان بعض إخوته، وإما لشغله بالتدريس والرد على الملحدين المعاندين من الأحباش وغيرهم كما هو مشاهد، وأسألك يا هذا لو سكت هل سكوته يخرجه من السلفية؟
🔢🔢وأما قولك "وبدأ يعتذر لمركز ابن مسعود" فإن كان مرادك أنه اعتذر لهم بالحق والباطل فهذا كذب محض، وإلا فرده عليكم بقوله ألا تغلوا فی دینكم غیر الحق وفى الكلام على الناس ولو على أهل البدع والأهواء فهذا حق لا ريب فيه نقول به أولا وآخرا،
🔢🔢وأما قولك "وبدأ بالطعن فى مشايخ السنة كالشيخ عبد الحميد ... وألحقهم بالحدادية" فهذا من نظره الثاقب وصدعه بالحق لأن فيهم من صفات الحدادية الشيء الكثير، سأذكرها 🛒🌟 فى بحث آخر،
🔢🔢أما قولك إنه "بدأ ينشر قواعد المبتدعة الخ" فهذا من كذباتك الفاحشة، فابن منور ما برح منذ شبابه منافحا ومكافحا عن حمى دين الإسلام وسنة سيد المرسلين ⏩️، هذا الذي نشهد 👆 عليه، ولا نعلم منه إلا خيرا، نحسبه كذلك والله حاسبه ولا نزكي على الله أحدا،
🔢🔢وأما ما ذكرته من أنه قرر أن الجرح والتعديل اجتهادي -وبعبارة أحسن منها- يدخله الاجتهاد ولا إلزام فيه" فهذا حق حقيقي وعليه السلف والخلف من علماء السنة ومن كبار المحدثين، ما جاء ابن منور بشيء جديد، وإن أردت النقاش حول هذا فباب السلفيين مفتوح، ولكن أنتم الغاية فى الجبن،
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጠጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
ሰለፍያ!
የዚህን ድንቅና ግዙፍ ስም እውነተኛ ትርጉም፣ ገዝፎ የተሸከመውን ታሪካዊ ክብደትና የተከበረ ቦታ በትክክል ለመረዳት፣ ስሙን ብቻ ማንበብ በቂ አይደለም። ይህን ስም ለመረዳት ከጀርባው የተዘረጋውን የዘመናት ታሪክ፣ በዚያ ጎዳና ላይ የተከፈለውን የእውቀትና የደም ዋጋ፣ ከተዛቡ እምነቶችና ከቢድዓ ጋር የተደረገውን የረጅም ዘመን ትንቅንቅ የአቂዳ ኪታቦችን ከፍቶ በደንብ ማስተዋል ያስፈልጋል።
ይህ ስም በሆነ ቀን የተሰበሰቡ ሰዎች የተሰጠ የቡድን መጠሪያ ስም አይደለም። እንዲሁም ለአንድ ሰው፣ ለአንድ ሸይኽ ወይም ለአንድ ድርጅት የሚያገለግል የግል መለያ አይደለም። ከዚያ የበለጠ ሰፊና ጥልቅ ትርጉም ይዟል። የቀደምት ሰለፎች የእምነትና የመረጃ መንገድ እንዳይደለዝ፣ እንዳይበረዝና ከትውልድ ወደ ትውልድ በንፅሕና እንዲደርስ የተደረገውን ትልቅ ትግል የሚወክል ስም ነው።
የእስልምናን መሰረታዊ እምነት ከግል አስተሳሰብ፣ ከፍልስፍናዊ ማምታቻና ከተዛቡ ትርጓሜዎች ለመጠበቅ፤ ቁርዓንና ሐዲስን እንደመሰረታዊ መረጃ ለመያዝ፤ የቀደምት ሰለፎችን መንገድ ከሰርጎ ገብ ለመጠበቅ የተደረገው የዘመናት ገድል በዚህ ስም ውስጥ ይንፀባረቃል።
ከጥንቱ የኸዋሪጆች ፊትና ጀምሮ፣ በየዘመኑ በተለያዩ መልክ የተነሱ የጥመትና የቢድዓ አስተሳሰቦች ሲያቆጠቁጡ፣ በሐቅ መረጃ ቀንድ ቀንዳቸውን እያለ ልክ ሲያስገባቸው፣ የተዛቡ ያተንጋደዱ እምነቶች በማስረጃ ሲመለሱ ሲቃኑ፣ የእስልምና አቂዳ ከመደበላለቅ ከመበረዝ ሲጠበቅ የመጣውን ረጅም ተጋድሎ ስትመለከት፣ የዚህ ስም ክብደት ይበልጥ ይገለጥልሃል።
ስለዚህ ይህንን ስም #አደራህን....!#አደራህን....! #አደራህን...! ከአንድ ሰው ጋር ብቻ አታስተሳስረው። ከአንድ ሸይኽ ጋር ብቻ አትገድበው። ለአንድ ቡድንም የግል ንብረት አታድርገው። የስሙን ታሪክና ክብደት ሳታውቅ ለግለሰብ ማንነት መለያ ማድረግ፣ ስሙን ከትልቁ ትርጉሙ ማሳነስ ነው።
ይህ ስም ከግለሰቦች የሚበልጥ፣ ከቡድኖች የሚሰፋ፣ ከዘመናት የሚሻገር ትርጉም የያዘ ስም ነው።
✍️ አብዱል ከሪም ሑሴን
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
ሙሐዶራዎችን በቀላሉ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1-የተቃጠሉ መስጅዶች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
2-ሱፍዮች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
3-መርከቧ ላይ ማን ተሳፈረ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
4-ትክክለኛ እምነት በኡስታዝ ሳዳት ከማል
5-ጀነት መግቢያ ከእሳት መጠበቂያ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
6-አህሉ ሡና ከአህሉል ቢድዓ የተለዩ ናቸው በኡስታዝ ሳዳት ከማል
7-የሺርክ ስንኝ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
8-የሽርክ ስንኞች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
9-የቦረናው ሸህ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
10-አርሽ ዙሪያ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
11-ሽርክ ስንኝ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
12-ለአህባሾችና መሪዎቻቸው የተሰጠ መልስ በኡስታዝ ሙሐመድ ሢራጅ
13-የኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ ሙሀዶራዎች
14-ከአንድ እስከ መቶ (1-100) ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
15-ከመቶ አንድ እስከ ሁለት መቶ (101-200) ድረስ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
16-ከሁለት መቶ አንድ እስከ ሶስት መቶ (201-300) ድረስ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
17-ከሶስት መቶ አንድ (301) በላይ ያሉ ፈተዋዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
18-አህባሾችን የተመለከቱ ሙሐዶራዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
19-አህባሾች በአላህ ስምና ባህሪ ላይ ያላቸው አቋም በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
20-ጀርሕ ወተዕዲል የተመለከቱ ሙሐዶራዎች በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
21-ከአህባሾች ጋር የተደረገውን ውይይት ለማግኘት በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል-ከሚሲይ
22-ሀጃዊራወችን የተመለከቱ ረዶች
23-ጥናት መንዙማ በኡስታዝ ሳዳት ከማል
24-ሸይኽ ሙሀመድ ገዛል ሙሓዶራዎች ቁጥር 1
25-ስለ አኼራ የተደረገ ሙሀዶራዎች በኡስታዝ ሳዳት ከማል
26-የአቡ ዓኢሻ አወል ኹጥባዎች
27-የአቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም ኹጥባዎች
28-የአቡ ሙዓዝ ሀሠን እንድሪስ ኹጥባዎች
29-የአብዱ ሽኩር ኹጥባዎች
30-የኡስታዝ ሑሴን አሊ ሙሐዶራዎች
31-የአቡ አዩብ ኹጥባዎች
32-ተውሒድን የተመለከቱ ሙሀዶራወች
33-የተለያዩ ሙሐዶራዎች
34-የሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሙሓዶራዎች
35-የሼይኽ አቡ ዓማር አወል ቢን አህመድ ሙሓዶራዎች
36-የኡስታዝ ኢብን ሙነወር ሙሓዶራዎች
37-የኡስታዝ አቡ ሙስሊም ሙሓዶራዎች
38-የኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሠን እንድሪስ ሙሓዶራዎች
39-የሸይኽ ሙሐመድ መኪን ሙሐዶራወች
40-የሸይኽ አህመድ አወቀ ሙሓዶራዎች
41-የሸይኽ ሙሐመድ አሚን ሙሓዶራዎች
42-የሸይኽ ሙሐመድ ገዛል ሙሓዶራዎች ቁጥር 2
43-የኡስታዝ አብዱ ሽኩር አቡ ፈውዛን ሙሓዶራዎች
44-የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐዶራዎች
45-የአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም ሙሓዶራዎች
46-የኡስታዝ አቡ ሡፍያን ሙሓዶራዎች
47-የአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን ሙሓዶራዎች
48-የሙሐመድ አወል የሺርክ መንዙማዎች በአቡ ዑሰይሚን
49-የኡስታዝ ሳዳት ከማል ቀሪ ሙሓዶራዎች
50-የኡስታዝ አቡል ዓባስ ናስር ሙሐመድ ሙሓዶራዎች
51-የኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ ሁሴን ዒስማዒል ሙሓዶራዎች
https://t.me/yedaewachannel
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
✅የሸይኽ አወል አህመድ አልኸሚሴ ሙሓዶራዎችን እና ፈትዋዎችን ለማግኘት 🫰በዚህ በኩል
📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/1499
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/1499
+1
🔴✈️ 👉🔴
🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎
ውድ እና የተከበራችሁ "ሰለፍያ እህት ወንዲሞች ባረከላሁ ፊኩም"" በራሳችሁ ቻናል ከፍታችሁ የቢዳአ አንጃዎችን
⓵ ቻናል♨️ ⓶ ግሩፕ እንደት ታስተዋውቃላችሁ???!!
💗 የገረመኝ ደግሞ አዋቂ ናቸው ከምንላቸው ኡስታዞች፣ እና እህቶች ቤት ነው እንደዚህ አይነት ዲብልቅልቅ ያለ ነገር እያየን ያለነው። ሰውንም አዛ አታዲርጉ ምንም አይነት ጥቅም የ'ለለው wave "እያንጋጋችሁ።
ታርጌታችሁ ምንዲነው?!!!!
🌟 ቻናላችሁን እና ግሩፖችሁን ማሳደግ?!
🌟 ወለስ ዳዕወተ ሰለፍያን ማስፋፋት?!!
ምንም የማያቀው ሰው እዚያ እየሄደ ይቀላቀላል ከዚያም የነሱ ወጥመድ ሰለባ ይሆናል ለምን??!
weve "ስትገቡ አታጣሩም ?!
ከኢኽዋኑም፣ ከለተሜውም፣ከሀጃዊሪያውም እንዳው ዝም ብሎ መነዳት አላሁል ሙስተአን።
እባካችሁ አብዛሀኛዎች ዌቭ የሚሰሩ ሰዎች ኢኽዋኖች እና ሀጃዊራዎች ናቸው ።አላህ እንፍራ :: ብዛትን ሳይሆን ጥራትን ፈልጉ።
⬅በየ ቦታው እያየናቸው ያሉ ዌቮች ናቸው ተጠንቀቁ ፣ራሳችሁ በነሱ መረብ አስገብታችሁ ሌላውንም አታስጠምዱ።
ሸርርርር አርጉ ባረከላሁ ፊኩም
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣5️⃣6️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 475፣ ሐዲሥ ቁ. 1376
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
🧦
ካልሲ (ሁፍ) ላይ ስለ ማበስ ምን ያህል እናውቃለን⁉️
✍አንድ ሰው ውዱዕ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ለማበስ ከፈለገ……
💫ካልሲውን ሲለብሰው ዉዱዕ ያለው ሆኖ መልበስ አለበት።
💫ካልሲው ከነጃሳ የጠራ ንፁህ መሆን አለበት።
💫ካልሲው የእግሩ ለውዱዕ የሚታጠበውን ቦታ መሸፈን መቻል አለበት; ቢያንስ ቁርጭምጭሚቱን የሚሸፍን መሆን አለበት።
💫ካልሲው ላይ ማበስ የሚችለው ዉዱዕ በሚያደርግ ጊዜ ብቻ ነው; ለጀናባ እና ለመሳሰለ ትጥበት የሚታጠብ ከሆነ ማበስ አይችልም።
💫ካልሲው የተቀደደ ቢሆንም ማበስ ይችላል።
💫ካልሲው ቀጭን ቢሆንም ማበስ ይችላል።
💫በሚያብስ ጊዜ እጆቹ ላይ አንድ ጊዜ ውሀውን አፍስሶ ከደፋው በኋላ ጣቶቹን ይዘረጋቸውና በሁለቱ እጆቹ ሁለቱ እግሮቹ ላይ ያብሳል። በቀኝ እጁ ቀኝ እግሩ ሲያብስ; በግራ እጁ ግራ እግሩ ያብሳል።
★ሲያብስ በእጆቹ ብቻ ያብሳል እንጂ ውሃው ካልሲው ላይ አይረጭም።
★ሲያብስ የእግሩ የላይኛው ክፍል ብቻ ያብሳል እንጂ የውስጥ እግሩን አያብስም አይነካካም።
💫ካልሲው የለበሰው ውዱእ ላይ ሆኖ ከነበረ ቀጣይ ውዱእ ሲያደርግ “እግሬን ማጠብ አለብኝ” ብሎ ካልሲውን ለማውለቅ መቸገር የለበትም።
💫ካልሲውን ካበሰበት በኋላ ቢያወልቀው ውዱውን አይበላሽበትም አይፈርስበትም; ካልሲው ካበሰ በኋላ ቢያወልቀውም ባደረገው ውዱእ መስገድ ይችላል።
💫አንዴ በለበሰው ካልሲ ማበስ የሚችለው;
★መንገደኛ ለ3 ቀናት ማበስ ይችላል።
★መንገደኛ ካልሆነ ግን ቀንና ማታ (24 ሰዓት) ነው ማበስ የሚችለው።
💫የማበሻ ጊዜው የሚቆጠረው ካልሲው ከለበሰው ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
ለምሳሌ፦
ሰኞ ቀን ዙሁር ላይ ውዱእ አድርጎ እግሩን ታጥቦ ካልሲውን ቢለብሰው። እስከ መግሪብ ድረስ ውዱእ ሳይፈታ ቆየና መግሪብ ላይ ውዱእ ተበላሽቶበት ውዱእ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ቢያብስ; ይህ ካልሲ የማበሻ ጊዜው መቁጠር የሚጀመረው ከመግሪብ ሰዓት ጀምሮ ነው። በዚህም መሰረት ማክሰኞ ቀን ልክ የመግሪብ ወቅት ሲደርስ በዚህ ካልሲ ላይ ማበስ አይችልም ያበቃል ማለት ነው።
★ልብ ይበሉ
ይህንኑ ሰውዬ ማክሰኞ መግሪብ ከመድረሱ በፊት ውዱእ አድርጎ በካልሲው ላይ አብሶ ከሆነና ይህንን ውዱእ መግሪብም ላይ ካልተበላሸበት የካልሲው ማበሻ ጊዜ በማለቁ ብቻ ውዱኡውን አይበላሽበትም። ማበስ አይችልም እንጂ የነበረው ውዱእ እስካልፈታ ድረስ መስገድ ይችላል።
★መንገደኛ የሆነውም ሰው ምሳሌው አሁን ባየነው መልኩ ከለበሰበት ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ቀናቶች ይቆጠሩለታል።
★★★★★★★★★★★★
📚ጀሪር ቢን ዐብደላህ አልበጀሊ ባስተላለፈው;
«رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم بالَ، ثم توضأَ ومسحَ على خُفَّيْهِ»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ተፀዳድተው ውዱእ ሲያደርጉ ሁፋቸው ላይ ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።» ይላል።
📚ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ ባስተላለፈው;
«كنت مع النبي صلى الله عليه وسلم في سفر، فأهويت لأنزِع خفيه، فقال: (دَعْهُما، فإني أدخلتهما طاهرتين»
«ከአላህ መልእክተኛﷺ ጋ በጉዞ ላይ ነበርኩኝ, ሁፋቸውን ላወልቅላቸው ዝቅ ስል "ተዋቸው ውዱእ ላይ ሆኜ ነው ያደረኳቸው" አሉኝ።» ይላል።
📚ሹረይህ ቢን ሃኒ የማበሻ ጊዜው ምን ያህል እንደ ሆነ ልጠይቃት ወደ ዓኢሻ ስሄድ "ወደ ኢብን አቡ ጧሊብ ሂድና ጠይቀው, እሱ ከረሱልﷺ ጋ ጉዞ ያበዛ ነበር" አለችኝ። ሄጄ ስጠይቀው;
«جعل رسول الله صلى الله عليه وسلم ثلاثة أيام ولياليهن للمسافر، ويومًا وليلة للمقيم»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ለመንገደኛ ሶስት ቀናቶች ከሌሊታቸው ጋ ሲያደርጉ ቋሚ ለሆነ ሰው ደግሞ ቀንና ሌሊት አደረጉለት አለኝ።» ይላል።
📚ሰፍዋን ቢን ዓሳል ባስተላለፈው;
«كان رسول الله صلى الله عليه وسلم يأمُرُنا إذا كنا سَفْرًا [مسافرين] أن لا ننزِع خِفافنا ثلاثة أيام ولياليهن، إلا من جنابة، ولكن من غائط وبول ونوم»
«መንገደኛ በሆንን ጊዜ የአላህ መልእክተኛﷺ ለሶስት ቀናት ሁፋችን እንዳናወልቅ ያዙን ነበር; ጀናባ ከሆንን በስተቀር; በውሃ ሽንት፣ በሰገራ ወይም በእንቅልፍ [ውዱእ ከፈታን ግን አናወልቅም]።» ይላል።
📚ዓልይ አላህ ስራውን ይውደድለት እንዲህ ይላል ነበር;
«لو كان الدين بالرأي لكان أسفل الخف أولى بالمسح من أعلاه، وقد رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يمسح على ظاهر خفيه»
«ዲን በሰዎች ዕይታ (ራዕይ) ቢሆን የሁፍ የታችኛው ማበስ የላይኛው ከማበስ የበለጠ የተገባ ይሆን ነበር; በእርግጥም የአላህ መልእክተኛﷺ በላይኛው ሁፋቸው ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።»
★★★★★★★★★★★★
💚ልብ ይበሉ‼️
💫ያለንበት ወቅት በጣም ብርዳማ ከመሆኑም ጋ አብዘሃኛው ሙስሊሞች እንዴት ማበስ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ስለ ማያውቁ ማበስ እየቻሉም ካልሲያቸውን አውልቀው እግራቸው ለማጠብ ሲደክሙ ይስተዋላሉ። በመሆኑም ይህንን አላህ ገር ያደረገው አማራጭ አውቀው እንዲጠቀሙ ሼር አድርጉላቸው።
Repost from የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪወች ጀመዓ ቻናል
✍ ይድረስ ሁለት ፊት ላላቸው አጨብጫቢዎች፦
አንዳንዴ እኛ ጥሩ ነው ብለን ያሰብነው ነገር በፍፁም መልካም የማይሆንበት አጋጣሚ አለ
ለምሳሌ በሂወትህ ውስጥ ጥሩ ቦታ ልትሰጠው ያሰብከውን ሰው አሏህ ግን ላንተ መልካም እንዳልሆነ ስለሚያውቅ ንቅል ያደርግልሃል።
አላህ እኮ ሁሉን አዋቂ የሆነ ጌታ ነው። የሰው ልጅን ብንዋሽ አላህን መዋሸት አንችልም ።የሰው ልጆችን ብናታልል አላህን ማታለል አንችልም።ለሰው ልጆች የኛን ማንነት ባናሳይ በመልካም ማንነታችን ብንቀርብ አላህ ግን የኛን ትክክለኛ ማንነት ፍንትው አድርጎ ያውቃል‼️‼️‼️
👉 ለሰው ስንቀርብ መልካም መስለን የተማርን የቀራን የሓፈን ... ወዘተ .... እውነታው ሲታይ በተቃራኒው ወንድሜ ሆይ‼️ እህቴ ሆይ‼️ ይህ ውሸት እና ማጭበርበር አንድ ቀን ተነቅቶብን መዋረዳችን የማይቀር እውነታ ነው።
ሲቀጥል፦ ሙስሊም አይዋሽም ብለዋል ነብዩ ﷺ ታዲያ ለአንዳንድ ሰዎች ለዛው አዋቂነን ከሚሉ አንዳንድ አካላት የለለ የውሸት ቀደዳ እናያለን አይኑን ያፈጠጠ ጥርሱን ያገጠጠ ውሸት ታዲያ ምኑ አዋቂነት ነው?!?!
👉 አንዳንዶች በሂወትህ ሊጫወቱ እንደ አማራጭ ድልድይ አድርገው ይይዙሃል።ወዳንተ ሲመጡ ላንተ ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ይነግሩሃል።ጉሮሯቸው እስኪቀደድ ድረስ ከዛ በተቀራኒው ካንተ ሲለዩ ከሌላ ጋር ሲሆኑ ግን የነሱን ምንነትን በደንብ ያራምዳሉ። አጅብ ነው!!!አላህን እናታልለው ይሆን👈
አንተን በመጥፎ የሚያነሱ ላንተ ምንም ቦታ እንደለላቸውና ስምህን ለማጉደፍ አንደኛ ፊት ለፊት ተሰላፊዎች እነሱን ሁነው ታገኛቸዋለህ።
ምን አይነት ጭራቅነት ነው ይሄ ባህሪ ???
ማንኛውም ሰው ሁሌም ራሱን ነው መምሰል ያለበት እንጅ ሌላ ሰው መምሰል የለበትም ይህ ራስን አለማወቅና በራስህ ማንነት ማፈር ነው የሚሆነው.....
🔶 የራሷ እያረረባት የሰውን ታማስላለች እንደሚባለው ነው ነገሩ...
👉 እነዝህ ሰዎችን በብዙ መንገድ ላንተ ያለህን ቦታ ለማወቅ ስትፈትናቸው ምን አለፋህ ወንድሜ አመድ ይሆናሉ ነው የምልህ።አንተ የምታሰባቸውና እነሱ ላንተ ያላቸው ቦታ ሰማይና ምድር ሁኖ ታገኘዋለህ።
ስለዚህ የምትቀርባቸውን ሰዎች አስተውል ወደሂወትህ የምታስገባቸውን ሰዎች በደንብ ፈትሽ.......
ምንም ሁን ምንም ሰውን ስትቀርብ በራስህ ባህሪ መሆን አለበት አዛኝ ሳትሆን አዛኝ መስለህ, እውነተኛ ሳትሆን እውነተኛ መስለህ ሳትሓፍዝ ሓፍዣለሁ ብለህ,ወዳጅ ሳትሆን ወዳጅ መስለህ, ልጅ ሳትሆን እድሜህን ዋሽተህ, ዝርክርክ ያሉ ሁነው እንደ ቁጥብ ሲያጫውታቸው,👉እረ ስንቱን ልጥቀስ....
ሙስሊም አይዋሽም ሲባል ነበር የምናውቀው ዘንድሮ ግን የውሸት ቋት የሆነን ሰው በአይኔ አሳየኝ..ዓጅብ አላህ ይሰትረኝ ይሰትረን።
✍ አቡ ዑሠይሚን
http://t.me/abuUseyminabdurehman
http://t.me/abuUseyminabdurehman
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
አቡ ሙዓዝ ሆይ! መልስ መስጠት ከቻልክ እጠይቅሃለሁ፦
~ ክልክል የሆኑ ነገሮችን ለመፈጸም የሚያስገድደው አጣብቂኝ ችግር (ዶሩራ) በእጅ፣ በአንገት፣ በእግር መቆረጥ ወይም በሞት ብቻ የተገደበ ነውን? ይህንን ማን አለህ? ከእውነተኞቹ ከሆንክ ማስረጃህን አምጣ። ከቁርአንና ከሱና የተቀዳውንና የታወቀውን "አስገዳጅ ሁኔታዎች ክልክል ነገሮችን ያስፈቅዳሉ" የሚለውን የሸሪዓ ደንብ (ቃዒዳ) በእጅና በእግር መቆረጥ ወይም በግድያ ብቻ የገደበው ማን ነው?
~ አቡ ሙዓዝ ሆይ! ዑለማኦች 'አድ-ደሩሪያት አል-ኸምስ' ብለው የሚጠሯቸውን አታውቅምን? ለመሆኑ ዲናዊ ጉዳት 'አደጋ' ክልክል ነገሮችን ለመፈጸም ከሚያስፈቅዱት ውስጥ አንዱና ዋነኛው አይደለምን? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ደዕዋችንን ለማስጠበቅና የነቢያዊ ፈለግ ምንጭ፤ የብዙ ሺህ ሱንዮች የዐይን ማረፊያ የሆኑትን የሰለፊያ መስጂዶችና መርከዞችን ለመጠበቅ መቀመጥ እግርህ ወይም እጅህ እንዳይቆረጥ ፈርተህ ከእነርሱ ጋር ከመቀመጥ የተሻለና በላጭ አይደለምን?
~ እንዲሁ በቅጡ ሳናስተነትን ከመቀባጠራችን በፊት የራሳችንን አቅምና የአስተሳሰብና የግናዛቢያችንን ምጥቀትና ጥልቀት ማወቅና መፈተሹ ለእኛ የተሻለ ነው። እንዲህ ተብሏልና፦ "ዓዋቂ ማለት መልካምን ከክፉ የሚለይ አይደለም፤ ይልቁንም ከሁለት መልካም ነገሮች የተሻለውን፣ ከሁለት ክፉ ነገሮች ደግሞ አነስተኛውን የሚያውቅ ነው። የሸሪዓ መሰረቱም ጥቅምን ማስገኘትና ማሟላት፣ ጉዳትን ደግሞ ማስቀረትና መቀነስ እንደሆነ የሚያውቅ ነው። ይህ ካልሆነ ግን በመስራትና በመተው መካከል ያለውን ሚዛን የማይጠብቅ ሰው፤ ግዴታዎችን ሊተውና የተከለከሉ ነገሮችን ሊፈጽም ይችላል፤ ይህንንም እንደ ጥንቃቄና ደግነት (ወረዕ) ይቆጥረዋል።"
7. በመጨረሻም እንዲህ ትላለህ፦ "እስኪ ንገሩኝ፤ ከእኛ መካከል ትክክለኛው ማን ነው? ሰዎችን ለስሜት ባለቤቶች ፍቅር እንዲኖራቸውና ለእነርሱ እንዲለዝብ የሚያነሳሳው? ወይስ እንደ ቀደምቶች ከቢድዓ ባለቤቶች እንዲጠነቀቁና ከመንገዳቸው እንዲርቁ የሚያነሳሳው?"
እልሃለሁ፦ "ትክክለኛው መልስ ያለምንም ጥርጥር ሁለተኛው ነው። ነገር ግን ሰዎችን የስሜት ባለቤቶችን በመውደድ ላይና በመለዘብ ላይ ያነሳሳው ማን ነው? ይህንን የምታደርግ ከነበርክ አንተ በእርግጥም የጠፋህ 'ሙመዪዕ' ነህ፤ ከእርሱ መመለስህም ላንተ በላጭ ነው። አንተ "አብሬያቸው ነበርኩ" የምትላቸው ሰለፊዮች ግን ከምትለው ነገር በጣም የራቁ ናቸው። ይልቁንም ከእነርሱ ዘንድ የሚታወቀው ከቢድዓና ከባለቤቶቿ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ መስጠት ነው።
ታላቅና የተከበረው የዓርሽ ባለቤት የሆነው አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራንና ከእርሱ ጋር እስከምንገናኝበት ቀን ድረስ በእርሱ ላይ እንዲያጸናን እለምነዋለሁ። እርሱ የዚህ ባለቤትና በእርሱም ላይ ቻይ ነውና።
በታናሹ ወንድምህ አቡ ዑምራን አል-አሰሪ ተፃፈ።
ትርጉም: ሙሐመድ አያሌው
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
