Ethio~Campus
Відкрити в Telegram
🇪🇹 2018 FRESHMAN~GC FRESHMAN~GC 2018/2025 On this channel ~~you will get😍😍 🔶የሬሚዲያል ሞጅል(module) 🔷የሬሚዲያል ፈተና(MOE Exam) 🔶የፍሬሽማን ሞጁል(module) 🔷የፍሬሽማን (PPT,PDF 🔶የፍሬሽማን (Mid &Final exam) 🔷የዲፓርትመት (PPT,MODULE, EXAM) #your_success_our_mission
Показати більше7 670
Підписники
+424 години
-77 днів
-18430 день
Архів дописів
7 670
የ2018 ዓ.ም 3ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሠጠት ጀምሯል።
በዚህ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በወረቀት እና በኦንላይን ፈተናቸውን ከዛሬ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይወስዳሉ።
@Ethio_campus1
7 670
ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ !
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።
የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።
ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል።
768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@Ethio_campus1
7 670
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ በመላ ሀገሪቱ መሠጠት ጀምሯል።
የሁለተኛ ዙር የኦንላይን ተፈታኝ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለሦስት ቀናት (አርብ፣ ሰኞ እና ማክሰኞ) የሚወስዱ ይሆናል።
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በስድስት ዙሮች በኦንላይን እና በወረቀት እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል
@Ethio_campus1
7 670
ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የመጀመሪያ ዙር ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
የሁለተኛ ዙር ፈተና ነገ ሰኔ 26/2018 ዓ.ም መሠጠት የሚጀምር ሲሆን፤ ተፈታኞች ወደሚወስዱበት ተቋማት ገብተዋል።
ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ደንቦችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ገለጻ (Orientation) ዛሬ ተሰጥቷል።
የሁለተኛ ዙር የኦንላይን ተፈታኝ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለሦስት ቀናት (አርብ፣ ሰኞ እና ማክሰኞ) የሚወስዱ ይሆናል።
@Ethio_campus1
7 670
#ከርዕስ_ውጭ
ከዛሬ ጀምሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግብያ ፈተና በሁሉም የሀገሪቱ ቦታዎች መሰጠት ጀምሯል ።
በ ቻናላችን ውስጥ ላላችሁ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኞች ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን::
በድጋሚ መልካም እድል🤍
@Ethio_campus1
7 670
#AddisAbaba
የ2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ዛሬ ሰኔ 22/2018 ዓ/ም ከሰዓት እንደሚለቀቅ፣ የ6ኛ ክፍል ውጤት ደግሞ ከሳምንት በኋላ እንደሚለቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ ዘላለላ ሙላቱ (ዶ/ር)፣ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቀዋል።
ምን ያክል ተማሪዎች እንዳለፉና ምን ያክል ማለፊያ ውጤት እንዳላመጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው ኃላፊው፣ " እሱ ገና ነው አልታወቀም። በኋላ ይለቀቃል " ሲሉ ጠቁመዋል።
የ6ኛ ክፍል የፈተና ውጤት መቼ እንደሚለቀቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘለለም (ዶ/ር)ን ጠይቋል።
በምላሻቸው " ዛሬ የሚለቀቀው የ8ኛ ክፍል ውጤት ብቻ ነው። የ6ኛ ክፍል ውጤት ከሳምንት በኋላ ነው የሚለቀቀው" ብለዋል።
የ8ኛ ክፍል ውጤት የማለፊያ ነጥብ 50% የተቆረጠ ሲሆን ቢሮው ፥ " ፈተናው በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው " ብሏል።
(የ8ኛ ክፍል ውጤት መመልከቻው ይፋ ሲደረግ የምናጋራ ይሆናል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም
@Ethio_campus1
