Ethiopian SDA Songs
Відкрити в Telegram
Ethiopian Seventh day Adventist Church songs are uploaded here. So you can get over 900+ songs from old to new when ever and where ever you are. So please share it. Disclaimer - We don't own any of the content in this channel.
Показати більше4 841
Підписники
+724 години
+127 днів
+10630 днів
Архів дописів
4 841
መንገዴን አቅና ጌታዬ በእጅህ
ስራኝ እንደገና እንደሀሳብህ
ጣልቃ አልገባም እኔ በስራህ ላይ
ፈቃድህ ይፈፀም ጌታ በኔ ላይ
ትችላለህ ይህንን ልታደርግ ትችላለህ
አበጃጅተህ ዳግም ልታቆመኝ አንተ ሀይል አለህ
መልካም ቀን
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
ልብ የሚነኩ የንስሃ መዝሙሮች ስብስብን በመልቀቅ ጀምረናል። በቀጣይ የራሳችንንም non stop playlist እና ተመሳሳይ መልዕክት እና Genre ያላቸውን እየሰበሰብን የምንለቅ ይሆናል።
በእነዚህ መዝሙሮች ተባረኩበት።
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
ሰላም እንዴት ናችሁ
በቅርቡ Zemari Media ላይ ያሉትን non stop መዝሙሮች በaudio አድርጌ እዚሁ ለመልቀቅ አስቤ ነበር። ምን ሃሳብ አላችሁ? እራሱ ይለቀቅ ወይስ አዲስ playlist ይሰራ?
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
ሙላን (Mulan) - ጎቶንያል የዝማሬ ቡድን (Gotonyal singers)
YouTube link
ካንተውጭ መንገዱ የሚጎዳ
ጠል የሌለው ደረቅ ነው ምድረበዳ
የሆነ ነው መልካምነት የጎደለው
በህልውናህ ድክመታችንን ሸፍነው(2X)
ሙላን(2X) በመንፈስህ
ንካን(2X) በጉጠትህ
አንችልም(2X) ካላንተማ
ሙላን(2X) እንደገና
እኛ ልጆችህ ቆመናል በፊትህ
መሞላት ፈልገን በመንፈስህ
የአንተ ሸክላዎች አድርገን
በመንፈስ ዘይትህ ጌታ ሙላን
ሙላን(2X) በመንፈስህ
ንካን(2X) በጉጠትህ
አንችልም(2X) ካላንተማ
ሙላን(2X) እንደገና
ካንተውጭ መንገዱ የሚጎዳ
ጠል የሌለው ደረቅ ነው ምድረበዳ
የሆነ ነው መልካምነት የጎደለው
በህልውናህ ድክመታችንን ሸፍነው(2X)
መረባችን ጥለን እንከተልህ
አይጠቅመንምና አሳ ከእንግዲህ
ትሆናላችሁ የሰዎች አጥማጅ
ብለኸናል አባ እንኑር ባንተደጅ
ምርጫችን(2X) እናድርግህ
በኛላይ(2X) ኑር እባክህ
ካላንተ(2X) ወዴት እንሄዳለን
አባታችን(2X) ያዘን እንላለን
ካንተውጭ መንገዱ የሚጎዳ
ጠል የሌለው ደረቅ ነው ምድረበዳ
የሆነ ነው መልካምነት የጎደለው
በህልውናህ ድክመታችንን ሸፍነው(2X)
ምርጫችንን እንደማርያም
እናድርግ በፊትህ እንቁም
አድርገን ያንተ ልጆች ጌታ
ካላንተ እንዳናይ ሌላ
ሙላን(2X) በመንፈስህ
ንካን(2X) በጉጠትህ
አንችልም(2X) ካላንተማ
ሙላን(2X) እንደገና
#Mulan
#ሙላን
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
ድንቅ የማለዳ የምስጋና መዝሙሮች ስብስብ || A Wonderful Collection of Morning Praise Songs
ድንቅ የማለዳ የምስጋና መዝሙሮች ስብስብ || A Wonderful Collection of Morning Praise Songs
ወደፊት የሚለቀቁ የበፊት እና አዳዲስ መዝሙሮችን ለማግኘት የYouTube ቻናላችንን subscribe በማድረግ ቤተሰብ በመሆን አበረታቱን።
በይበልጥ መዝሙሮችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Lm5i2mTEGWU
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
ኢሳይያስ 58 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ “እግሮችህ ሰንበትን እንዳይሽሩ ብታሳርፍ፣ በተቀደሰው ቀኔ የልብህን ባታደርግ፣ ሰንበትን ደስታ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን የተከበረ ብለህ ብትጠራው፣ በገዛ መንገድህ ከመሄድ፣ እንደ ፈቃድህ ከማድረግና ከከንቱ ንግግር ብትቈጠብ፣
¹⁴ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድር ከፍታዎች ላይ እንድትጋልብ፣ የአባትህን የያዕቆብን ርስት ጠግበህ እንድትበላ አደርግሃለሁ” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
መልካም ሰንበት
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
መዝሙሩን ገምቱ
Guess the Song Name21ኛ ... ካላንተ እንዳናይ ሌላ ... ዘማሪውን እና የመዝሙሩን ርዕስ ገምቱ።
4 841
ቁጥሮች ቢናገሩ ኖሮ…
በሂሳብ ውስጥ ያሉ ቁጥሮች መናገር ቢችሉ ኖሮ፣ አንዳንዶቹ ዜሮ (0) እና አንድ (1)ን ይከሱ ነበር።
“ለምን ዜሮንና አንድን እንከሳለን?” ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ።
ማንኛውም ቁጥር በዜሮ ሲባዛ ውጤቱ ያው ዜሮ ይሆናል።
ለምሳሌ፦
20,000,000 × 0 = 0
ዜሮ ትልቅ ቁጥሮችን እንኳን ወደ ምንም ነገር ሊቀይር ይችላል።
አንዳንድ ሰዎችም እንደ ዜሮ ናቸው። ከእነሱ ጋር ከተቀራረብክ፣ የአንተ ዋጋ ምንም ያህል ታላቅ ቢሆንም፣ ወደ ዜሮ ሊያወርዱህ ይችላሉ።
አንድ (1)ስ?
ማንኛውም ቁጥር በአንድ ሲባዛ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ ቁጥሩ እንዳለ አንድ ሆኖ ይቀራል። ቁጥሩ ምንም ያህል ትልቅ ቢሆንም አይለወጥም።
ለምሳሌ፦
20,000,000 × 1 = 20,000,000
አንዳንድ ሰዎችም እንደ አንድ ናቸው። በሕይወትህ ላይ ምንም ያህል ቢነኩህ አንተ በነበርክበት ትቀራለህ። አታድግም፣ አትሻሻልም፤ ባለህበት ቆመህ ትቀራለህ።
ስለዚህ አንተ ምን ዓይነት ሰው ነህ? እና የምትቀርባቸው ሰዎችስ ምን ዓይነት ናቸው?
እግዚአብሔር የአንድ (1) እና የዜሮ (0) መንፈስ ካላቸው ሰዎች እንዲንለይ ይርዳን።
እንዲሁም እግዚአብሔር እንድናድግና ከአንድ በላይ እንድንሆን ይርዳን። ስለዚህ በሌሎች ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ ስናሳርፍ፣ ዋጋን እንድንጨምርላቸው ጌታ ይርዳን።
ተባረኩ፤ ለሌሎችም በረከት ሁኑ። እንዲሁም የምትገኙበትን ድርጅት እና ተቋም በመልካም ተጽዕኖአችሁ የበለጠ ዋጋ ያለው አድርጉት። ተባረኩ!!
@pastor NEGASH PETROS
4 841
🔴ይገባሃልና
አስደናቂ ፍቅርህን አየነው
በመስቀል ላይ ሞተህ ገለጽኸው
ከዘላለም ጥፋት ስላዳንከን
በሞትህ ህይወትን ስላገኘገን
ይገባሃልና እጅግ ብዙ አምልኮ
ፍጥረት የሚያከብርህ ፊትህ ተንበረክኮ
ይገባሃልና እጅግ ብዙ እልልታ
ለባለውለታችን ለሠራዊት ጌታ
አመታት አለፍን በምህረትህ
በእጆችህ ይዘኸን እየመራኸን
ስለ ማዳንህ ድንቁ ስራ
ስላሸጋገርከን መከራ
ይገባሃልና...
ስራህ ግሩም ቃላት ማይገልፀው
ፍጥረት ቢደረደር አውቆ አይችለው
በሰማይ በምድር ስልጣን ያለህ
ከቶ የሚያቅትህ ምንም የለህ
ይገባሃልና...
በዘመናት ሁሉ የምትኖር
መከታ የምትሆን ለሚጠራህ
መቼም አታሳፍር የታመነህን
ስለምታከብረው ሞገስ ሆነህ
ይገባሃልና...
#ይገባሃልና
#Hossana_Natanim_Choir
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
+1
የአድቬንቲስት ውዳሴ ደብተር መተግበሪያ Wudase አሁን በዘመናዊ መልክ ቀርቦላችኋል!
የጌታ ረድኤት ታክሎበት፣ በርካታ አዳዲስ አገልግሎቶችን በውስጡ የያዘው የውዳሴ ደብተር Wudase መተግበሪያ ለአጠቃቀም በሚመች መልኩ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ከያዛቸው አዳዲስ ግልጋሎቾችን ጥቂቶችን ለመግለፅ ያህል፡
ፈጣን ፍለጋ፦ መዝሙራትን በርዕሳቸው ወይም በውስጣቸው ባሉ ቃላት በቀላሉ መፈለግ የሚያስችል
የሙዚቃ ኖታ፦ የእያንዳንዱን መዝሙር ኖታ አብሮ የያዘ
ምቹ አቀራረብ፦ የፅሁፉን መጠንና ቅርፅ እንደ ፍላጎትዎ ማስተካከል የሚችሉበት
እና ሌሎችም በርካታ አዳዲስ ባህሪያትን አካቷል። ዛሬውኑ ከplay store አውርደው ይጠቀሙ!
ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wudase.hymn
@wudaseapp
4 841
አፋን ኦሮሞ መስማት ለምትችሉ ይሄን ድንቅ መዝሙር ጋብዣችኋለው።
Si Wajjin Ta'uun Koo - Faarfataa Boonaa Fiqaaduu
ከእንተ ጋር መሆኔ - ዘማሪ ቦና ፍቃዱ
https://youtube.com/watch?v=MM73YJ4eZQw&si=29uDlaEUV23Xvo70
ትርጉሙ ይኸው
ከአንተ ጋር መሆን ለእኔ ሰላም ነው
ከአንተ ጋር መሆን ለእኔ መልካም ነው
አንተ የምተማመንበት አምላኬ ነህ
አንተ ተስፋ የማደርገው የቅርብ ጓደኛዬ ነህ
የእረፍት ጥላ ነህ በውስጡ የምታደስበት
...
በምንም አይነት ሁኔታና ችግር ውስጥ ያልረሳኝ
አስቸጋሪው ባህሪዬን አይቶ እኔን ያልሰለቸኝ
አንተ ለእኔ አለኝ የምለው ሁሉ ነገሬ ነህ
እራሴን በአንተ ላይ ጥዬ አረፍኩ መደገፊያዬ ሆነህልኛል
ልጄ ትለኛለህ ከሁሉም በላይ ታዝንልኛለህ
ፍቅርህ የውሸት አይደለም በእውነት ትወደኛለህ
እንደዚሁ ትተህ ረስተኸኝ አልፈኸኝ አታልፍም
ታማኝ ጓደኛ አንተ ነህ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ
ሰላም፣ ሰላም ነው ከአንተ ጋር መሆኔ
ለእኔ፣ ለእኔ መልካም ነው ከአንተ ጋር መሆኔ
ከሁሉ በላይ ሰላም፣ ሰላምን ይሰጠኛል
ሙሉ አካላዊ እና መንፈሳዊ እረፍት አግኝቻለሁ
ልክ እንደ ጤዛ ለዛሬ ታይቶ ለነገ የሚያልፈው የምድር ሀብት
ጥበብ ተብሎ የሚቆጠረው የሰው ሞኝነት
ከዚህ ሁሉ ይልቅ አንተን ማግኘት ለእኔ ጥበብ ነው
ከሁሉም ነገሮች በላይ አንተን ማግኘት ለእኔ ጥበብ ነው
አንተን ማግኘት ለእኔ ጥበብ ነው
አንተን ማወቅ ለእኔ ጥበብ ነው
አንተን ማግኘት ለእኔ ጥበብ ነው
4 841
መዝሙሩን ገምቱ
Guess the Song Name20ኛ ... መቼም የማታሳፍር የታመንህ ... ዘማሪውን እና የመዝሙሩን ርዕስ ገምቱ።
4 841
#onevoice27
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
🔴አዳነን
ህያው ላደረገን ህይወቱን ሰጥቶ
በፊቱ ላቆመን ዘይት ቀብቶ
እናከብረዋለን በደስታ
እዚህ ላቆመን ለጌታ
አዳነን ለእኛ ሞቶ
በመስቀል ህይወቱን ሰጥቶ
ህያዋን አደረገን ደሙን ለእኛ አፍስሶ
ህይወቱን ለእኛ ሰጥቶ በደሙ እኛን ወርሶ
ክብር እና ውዳሴ ለእርሱ እናቀርባለን
በፊቱ ሁልጊዜ በደስታ እንቀርባለን
ያደረገልን ብዙ ከአዕምሯችን በላይ
ያመሰግኑታል ምድር እና ሰማይ
ዛሬ በነጻነት እኛ እንኖራለን
የሚያሰጋን የለም አለ እርሱ አብሮን
ለእያንዳንዳችን ሆኖናል ቅጥር
አያሰጋንም አለን እግዚአብሔር
አዳነን ለእኛ ሞቶ ...
#አዳነን
#Wudassie_Hawassa_SDA_Choir_Song_Album_2
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
4 841
የዛሬው የ "ከመዝሙሩ በስተጀርባ" የተሰኘው የውይይት ጊዜ ይሄንን ይመስል ነበረ። በቀጣይ በሌላ እንግዳ እስከምንገናኝ ሰላም ቆዩልኝ።
ስለፕሮግራሙ ያላችሁን አስተያየት፣ ቢሻሻል፣ ይሄ ቢሆን የምትሉትን እንዲሁም እንዲጠየቅላችሁ የምትፈልጉትን ዘማሪ ከስር በcomment ወይም በinbox @simera1 ላይ ልታስቀምጡ ትችላላችሁ።
ቀጣይ እስክንገናኝ የጌታ ሰላም ለሁላችሁም ይብዛ።
sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ 👇JOIN OUR CHANNEL👇 ▷ @SDAEnglish ◁ ▷ @SDAsong◁ ▷ @SDAInstrumentals ◁ ▷ @SDASongLyrics◁ 👇JOIN OUR GROUP👇 ▷ @SDAinstrumental ◁ 👇👇Inbox Chat 👇👇 ▷ @Simera1 ◁
