ar
Feedback
Ethiopian SDA Songs

Ethiopian SDA Songs

الذهاب إلى القناة على Telegram

Ethiopian Seventh day Adventist Church songs are uploaded here. So you can get over 900+ songs from old to new when ever and where ever you are. So please share it. Disclaimer - We don't own any of the content in this channel.

إظهار المزيد
4 693
المشتركون
+424 ساعات
+197 أيام
+5930 أيام
أرشيف المشاركات
የዛሬው የ "ከመዝሙሩ በስተጀርባ" የተሰኘው የውይይት ጊዜ ይሄንን ይመስል ነበረ። በቀጣይ በሌላ እንግዳ እስከምንገናኝ ሰላም ቆዩልኝ። ስለፕሮግራሙ ያላችሁን አስተያየት፣ ቢሻሻል፣ ይሄ ቢሆን የምትሉትን እንዲሁም እንዲጠየቅላችሁ የምትፈልጉትን ዘማሪ ከስር በcomment ወይም በinbox @simera1 ላይ ልታስቀምጡ ትችላላችሁ። ቀጣይ እስክንገናኝ የጌታ ሰላም ለሁላችሁም ይብዛ።
      sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

ጥያቄ:- ካለህ የተጣበበ ጊዜ ቀንሰህ ይሄንን የመሰለ ውይይት እንድናደርግ ፍቃደኛ ስለሆንክ በጣም አመሰግናለው። 🗣[በሱፍቃድ]:  "እኔም ይህ ዕድል ስለተሰጠኝ እና ስለተሳተፍኩ አመሰግናለሁ...እግዚአብሔር ይባርክህ 🙏" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- 📖 የምትወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "የምወደው ጥቅስ እንደማንኛውም ክርስቲያን ዮሀንስ 3:16ን በጣም ብወደውም፣ አሁን አእምሮዬ ላይ የመጣው ኤርምያስ 29፥11 "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።" የሚለው እግዚአብሔር የተናገረው ኤርሚያስ 29:11 በጣም ከምወዳቸው ጥቅሶች መካከል ነው እና እርሱን ማንሳት እፈልጋለሁ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- 🎹 የምትወደው የፒያኖ ተጫዋች? 🗣[በሱፍቃድ]:  "የምወደው የሙዚቃ ተጫዋች ያው በአጭር ለመመለስ ያው ብዙ አሉ ከአድቬንቲስት ውጪ ግን በቸርች ውስጥ የሚያገለግሉ ማለት ነው፥ አሉ ከውጪ ሀገር የምጠቅሳቸው ከነዛ ውጪ ግን አድቬንቲስት ውስጥ አንድ "William Murphy" የሚባል በGosple ዘማሪነት ይታወቃል፣ የሱ ሚስት "Dr. Gale Johnson" ትባላለች፤ 3ABN ላይ ድሮ ትጫወት ነበር በጣም ጎበዝ ናት። ሌሎችም አሉ የምጠቅሳቸው በልጅነቴ የክርስቲያን ቻናል በተለይ Hope Channel, 3ABN ላይ የምናያቸው። [ወደ አገር ውስጥ ልምጣ] ወደኛ ሀገር ስመጣ ከእነ "ሰብሉ ሴባ" ጀምሮ እነ "ትእግስቱ"፣ እግዚአብሔር ሚጠቀምባቸው በጣም ጎበዝ ሙዚቀኞች ናቸው፥ ግን በቅርብ ካሉት ግን፣ ስላየሁት ለኔም ከቅርበቱም አንጻር "አማን ቡሊ" በጣም የምወደው ሙዚቃ ተጫዋች ነው፥ በጣም skillful ነው፣ ብዙ ዓመት እግዚአብሔርን ያገለገለ በፍልውሃ ቤተ ክርስቲያን የተጫወተ ሙዚቀኛ ነው። እግዚአብሔር ያሳድግለት፣ እግዚአብሔር ያግዘው፣ በጣም የምወደው የሙዚቃ ተጫዋች የላይኞቹ እንዳሉ ሆነው እሱን ማንሳት እፈልጋለሁ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- 🎤 መዘመር ወይስ ሙዚቃ መጫወት? 🗣[በሱፍቃድ]:  "መዘመር ወይስ ሙዚቃ መጫወት ለሚለው እንደሙዚቃ ተጫዋችነቴ ሙዚቃ መጫወት ብል ደስ ይለኝ ነበር😁 ነገር ግን መዘመር ማለት ምንድነው የሚባለው፣ "The Human Voice is the most Powerful Instrument" እግዚአብሔር እንዲሁ የሰጠን ምንጠግነው ምንሰራው ምንቃኘው ገመድ የምንቀጥልለት ነገር የለም፣ እንዲሁም እግዚአብሔር በነፃ የመናገርን፣ የማመስገንን፣ ዜማን የመቀኘት ያው የማስተካከል፣ ያንን ነገር የማሳደግ ነገር ቢያስፈልግም: ነገር ግን የተሰጠን ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር ለመጠቀም ቀላሉ ነገር ድምጽ ነውና ደስ ያለው ደግሞ ምን ይበል? [ሙዚቃ ይጫወት ሊል ይችላል😁 ግን እግዚአብሔር ያንን እየከለከለ አይደለም] "ደስ ያለው ይዘምር" ያለበት በቃ ቅርብ ከሆነው ከተሰጠው ድምጽ እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እንድናመሰግነው አይደል የሚፈልገው? ለዚያ ድምፃችን ከሁሉ የተሻለ የቀረበ መሳሪያ ነው ብዬ አስባለሁና እሱ ይበልጣል።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- 🎹 Grand Piano ወይስ Digital Piano? 🗣[በሱፍቃድ]:  "Grand Piano ወይስ Digital Piano ለሚለው ጥያቄ ያው Digital Piano ያው ብዙ የsound ምርጫዎች አሉት ደስ ይላል፣ ይቀላል፣ ብዙ ሸክም የለውም፤ ግን ደግሞ Acoustic or Grand Piano natural ድምጹ የሆነ processed ያልሆነ የኤሌክትሪክ ያልሆነ sound ነው real የሆነ sound ነው የምንሰማውና ያ በጣም ደስ ይላል፣ እጅ ላይ ያለው feel, pedal ላይ ስንጫወተው በቃ ትንሽ ነገር ነክተን በቃ የምንሰማው ድምፅ processed ያልሆነ real nature ድምጽ ስለሆነ ያ በጣም ደስ ይላል እና ያን feeling አይበልጠውምና Grand Piano የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

የመጨረሻ አጫጭር ጥያቄዎች መልሰን ውይይታችንን እናበቃለን። ጥያቄ:- 🎹 ፒያኖ ወይስ 🎸ጊታር? 🗣[በሱፍቃድ]:  "ያው ሁለቱንም አልልም ማለትም ሁለቱም የራሳቸው ጥቅም አላቸው ሁለቱም አንድ ላይም ይሆናሉ ለየብቻም ደግሞ ለተለያየ የመዝሙር አይነቶች ዜማዎችና rhythmዎች የራሳቸው add የሚያደርጉት value አለ እዚያ ጋር፣ ግን ብዙ ኖቶች ስላሉት፣ ብዙ ሰአት ብንጫወተውም ስለማያም እና ብዙ rhythmic መጫወት ስለምንችል ና ደሞ የድምፁ ደግሞ ብዙ key ነው ብዙ variety አለው ብዙ harmonyዎችም ብዙ chordዎችም መያዝ ስለምንችል ፒያኖን እመርጣለው ማለት ነው። ግን still ሁለቱም የየራሳቸው advantage አላቸው፣ preferable ጊዜያቶች አላቸው።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- በስተመጨረሻ ይሄንን ውይይት እያነበቡ ላሉት ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት ካለ ጊዜው ላንተ ነው። 🗣[በሱፍቃድ]:  "በመጨረሻም ለሙዚቀኞች ለዘማሪዎች ማስተላለፍ የምፈልገው even, sound manዎች ሚክሰር ላይ የሚሆኑ በቤተክርስቲያን ተደብቀው ድምፅ ከፍ እና ዝቅ volumeዋን የሚያደርጉ፣ ድምፁ እንዲስተካከል የሚያደርጉ፣ LIVE የሚያሰራጩ እነዚህ ፕሮግራሞችም በሙሉ እነዚህ ተመሳሳይ አገልግሎት ነው የሚያደርጉት እና፣ ዓይኖቻችሁን ከሰው ላይ አንስታችሁ የጠራችሁን እግዚአብሔርን በሙላት እንድታገለግሉ እመኝላችኋለሁ። ሰዎች ላያመሰግኑ ይችላሉ በተለይ በኛ ቤተ ክርስቲያን ይታወቃል እግዚአብሔር የረዳቸው መልካም ሰዎች የገለጠላቸው ሙዚቀኞችን፣ ዘማሪዎችን ያበረታታሉ፣ ያመሰግናሉ፣ በሃሳብ፣ በፀሎት፣ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በተለያየ ነገር ያግዛሉ። አብዛኛው ሰው ግን [አንፈርድም] ያንን ካለመረዳት በቃ እዚያ ጋር የሚደረጉ ነገሮች valueless እንደሆነ ብዙ ጥቅም እንደሌለው ነው የሚያስበው። እና just እንደ ግዴታ የሚያስቡ ሰዎችም አሉና፡ እናንተ ግን አይኖቻችሁን አንስታችሁ ክርስቶስን ተመልከቱ የጠራችሁን ተመልከቱ፥ እርሱ ለትልቅ አላማ ነው የጠራችሁ፣ እርሱ እንድታከብሩት በቤቱ ያለመታከት ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ የተሻለ እንድትሆኑለት ህዝቡን ወደ እግዚአብሔር ሃልዎት ወደ እግዚአብሔር መገኘት እንድታቀርቡ ተጠርታችኋል። እና ደግሞ እግዚአብሔር እያንዳንዷ እስከ ዛሬ የሰራችኋትን ስራ፣ እያንዳንዱ የዘመራችኋትን መዝሙር፣ እያንዳንዱ የተጫወታችኋትን መዝሙር፣ ዜማ፣ የተናገራችኋትን ቃልን፣ በቤተክርስቲያን ያሳለፋችሁትን ጊዜ፣ ሚክሰር ላይም ሆናችሁ እያንዳንዱ ጊዜ ችግር ሲኖር ስብከቱ በትክክል እንዲተላለፍ ያስተካከላችሁትን ነገር እግዚአብሔር አይቷል፣ እግዚአብሔር ያንን ነገር ደግሞ ቆጥሯል፣ በህይወታችሁ በረከትን ያመጣልና። በእግዚአብሔር ላይ የተስፋ አትቁረጡ፣ የጠራችሁን እስከመጨረሻው እንድታገለግሉ፣ መልዕክት ላስተላልፍ እፈልጋለሁ። ለእኛ ባይመስለንም በሰውኛ የማይታይ ነገር አንዳንዴ የሚታይ ለውጥ progress አንዳንዴ ያለ ባይመስለንም በስራዎቻችን በቤተክርስቲያን በምናደርገው አገልግሎታችን ተስፋ ብንቆርጥም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በእኛ ተስፋ መቼም አይቆርጥም። እግዚአብሔር ሁሌም ደስተኛ ነው፣ እግዚአብሔር ሁሌም ሊያበረታታን ይፈልጋል፣ እና እሱን በማየት አይኖቻችንን ከሰው አንስተን እርሱን እንደ ዳዊት በቤቱ ብጣልም እስከማለት ድረስ ማገልገል ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን ያ ነው ምክሬ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- የሙዚቃ እና የመዝሙር ተሰጥኦዎቻቸውን ለእግዚአብሔር ክብር መጠቀም ለሚፈልጉ ወጣቶች ምን ምክርን ትሰጣለህ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "የሙዚቃና መዝሙር ተሰጥዖን ለእግዚአብሔር ክብር ማዋል ለሚፈልጉ ወጣቶች የምመክረው ነገር ቢኖር ቅድም እንዳልኩት የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ሁሌም ከፍ ለማድረግ ሞክሩ፥ ቃሉ እንደሚናገረው ብትበሉም ብትጠጡም ሁሉንም ለምን ክብር አድርጉት? ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉትና፣ አንዳንዴ ሰዎች ሲያበረታቱን ከተለያዩ ቦታዎች ዕድሎች ሲመጡ አንዳንዴ ለእግዚአብሔር ክብር እንዳንናውል ለራሳችን ጥቅም እንድናውል የሚያጓጉ ነገሮች ሊመጡ ይችላሉ፥ ነገር ግን በመጀመሪያ በጸሎት ገና ስጦታዎቻቸውን ላላወቁ፣ ስጦታቸውን አውቀው ለሚፈሩ በጸሎት፣ በድፍረት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ነገር ከትንሽ ጉባኤ በመጀመር ከአርብ እሮብ ፕሮግራሞች መጀመር ተሰጥዖዋቸውን እንዲያወጡ በጸሎት ደግሞ እግዚአብሔርን እንዲጠይቁ እንዲያሳድግላቸው፣ ከዚያ ደሞ ራሳቸው ላይም እንዲሰሩ ያንን ነገር እንዲያስተካክሉት እንዲቀርፁት፣ ከዚያ ደግሞ ጥሩ ደረጃ ላይ ደሞ ሲደርሱ ገና ትንሽ አንድ ስቴፕ ሲራመዱ አይ እዚህ ላይ በቃኝ ማለት የለባቸውም። ጳውሎስ የተናገረው ለዚህም ይሆናል "የኋላዬን እየረሳሁ ወደፊት እዘረጋለው"፣ እና በአገልግሎታችን እስከ ዛሬ ድረስ ያገለገልነው አይበቃም፣ ለጌታ እንደገና መዘርጋት እንደገና አንድ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ ማለት አለብን እና ሁሌ ራሳቸው ላይ እየሰሩ አዲስ ነገርን እየተማሩ የእግዚአብሔር ቃል እያጠኑ አዳዲስ እውቀቶችን እየጨመሩ እንዲያድጉ፣ inspire ላረጋቸው ላበረታታቸው እወዳለው። እኔም ያንን ነው በህይወቴ የተረዳሁት፥ መቼም ቢሆን እዚጋ በቃኝ ማለት የለብንም እግዚአብሔር የሚሰጠንን ነገር ለራሱ ክብር እያዋልን፣ እያደግን፣ እየሰፋን እርሱ የሚፈልግብን ደረጃ ድረስ መድረስ ይኖርብናልና ያንን መረዳት እንችል እግዚአብሔር ይርዳን።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- ሰዎች ስለሙዚቀኛም ሆነ ስለዘማሪያን ቢያውቁት ኖሮ ብለህ የምትመኘው፣ ምናለ ይሄንን ነገር ቢረዱት ኖሮ ብለህ የምትለው ነገር አለ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "ሰዎች ስለ ሙዚቀኞች እና ስለ ዘማሪያን ይህን ቢያውቁት ብዬ ማስበው ነገር፣ [በደንብ ልብ ካለማለት ይመስለኛል እንጂ ሳያውቁት ቀርተው አይመስለኝም] ግን ሙዚቀኞችና ዘማሪዎች ብዙ ጊዜ ከፊት ነው የሚሆኑት፥ ይታያሉ በአገልግሎት ላይ፣ እግዚአብሔርን ከፍ ለማድረግ ወክለው ስለሚወጡ በቃ ተጋላጭ ናቸው። Physical appearance ይታያል፣ አክሽኖቻቸው ይታያል፣ እእእ... ከዛ ደግሞ እዛው ሲወጣም ቸርቹ ጋር ውጪም ይታያልና አንዳንዴ ሰዉ ሰው መሆኑን ይረሳል፣ እና በሆነ ኃጢአት ቢወድቅ፣ በቃ የሆነ ደካማ ሰው ስለሆነ ቢወድቅ ቀጥታ መጠቋቆሚያ ነው የሚሆነው፣ ቀጥታ በቃ ሀሜት ነው የሚጀምረው ስለዛ ሰው መጥፎ ነገር ማውራትን ነው የሚጀምረው እና፥ እና ልክ ሆኖ እራሱ እንደዛ መሆን የለበትም፤ ብዙ ጊዜ ደግሞ ልክ ያልሆኑ ነገሮች በወሬም በአሉባልታም ብዙ ነገሮች አሉ። እነዚ እነዚህ ነገሮች ሙዚቀኞችን ወይ ዘማሪዎችን ከእግዚአብሔር ቤት ያርቃቸዋል፥ ማለት እግዚአብሔርን ማገልገል እየፈለጉ ግን በሰው ምክንያት ከሰውም ጋር ከእግዚአብሔርም ጋር ይጣላሉ። ከእግዚአብሔር ጋር ያልተጣሉት ደግሞ በቤት ያመልካሉ ወይም ሌላ ቦታ አመልካለው ብለው ለመውጣት ያስባሉ እና አሁን ደግሞ በእኛ ቤተክርስትያን ሙዚቀኛው በፈቃዱ ነው እንጂ የሆነ እንደስራ ተወስዶ፣ ተከፍሎት፣ በደንብ ክብር ተሰጥቶት ምናምን አይደለም ሚያገለግለው እና፣ ያ ያም ስለሌለ በሌላ ቦታ ያለው ነገር ይስባቸዋል፥ ሌላው በደንብ treat ሲያደረጋቸው በደንብ ሲንከባከባቸው እኛ ደግሞ ጣት ስንጠቁም፣ እኛ ደግሞ እንከን ስንፈልግ፣ እነዛን ሙዚቀኞችና ዘማሪያንን ወዳልሆነ መንገድ እንወስዳቸዋለን እና፥ ሰው በተቻለ መጠን ለመታገስ ከተሳሳቱም ቀስ ብሎ ለማረም በተለይ ደግሞ ለመጸለይ እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉት ለእነዚህ ለ አገልጋዮች [Ministerial ነው የሚሏቸው አይደል በእንግሊዝኛ ... ከመቅደስ ሆኖ የሚያጥኑ እንደካህናት አይነት ነገሮች ናቸው። እንደዚያ ልንወክላቸው እንችላለን] እና ቢጸልዩላቸው፣ ቢያግዟቸው ብዙዎችን መታደግ ይቻላል ብዬ አስባለሁ፥ ሰው ያንን ቢረዳ፣ ቢፀልይላቸው፣ ቢያግዛቸው፣ ለመረዳት ለማገዝ ቢሞክር የተሻለ ነው፣ ይሄንን ቢያውቁ ይሄንን ቢረዱ ይሄንን ልብ ቢሉ መልካም ነው ብዬ አስባለሁ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- በአድቬንቲስት ቤተክርስትያን ዝማሬ ውስጥ በሙዚቃም ሆነ በዝማሬ ምን አይነት እድገት እና መሻሻልን ማየት ትፈልጋለህ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "በአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የዝማሬና የሙዚቃ አገልግሎት ላይ ማየት የምፈልገው እድገትና መሻሻል እእእ... መዝሙርም በቃሉ የተመሰረተ ነው፤ ፀሎትም ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ከቃሉ ጋር ባለን ንግግር የምንሰጠው ምላሽ ነው። እና መዝሙር ሁለቱንም መያዝ ስለሚችል ያው እንደ ሙዚቀኛ ብዙ ጊዜ የምንለው ነገር አለ እንደ ዘማሪ፣ ለመዝሙር ትንሽ ጊዜ ነው የሚሰጠው እንላለንና ያ እውነታ ነው፣ እውነታውን እየካድን አይደለም፤ ግን እንደዛ ማለት ብቻ ሳይሆን የአምልኮ አንድ ክፍል መሆኑን በመረዳት ማለት፣ [መዝሙር እንዲዘመር የበለጠ ብዙ ሰአት እንዘምር ከሚል motive የተነሳ ሳይሆን]፣ ህዝቡ አስተውሎ እንዲዘምር አንድም መዝሙር ዘመረ ሁለትም፣ ሦስትም፣ አራትም የተዘመረውን ያህል [ፀሎትም ስብከትም የራሱ role እንዳለው ሁሉ] መዝሙር የራሱ role እንዳለው በቤተክርስቲያናችን ሊታወቅ እና በደንብ ግንዛቤው ሊኖር ይገባል ብዬ አስባለውና፣ አሁን ቅዳሜ መጥተን አንድም ጸሎት ሳንፀልይ ብንሄድ በጣም ይከፋናል አይደለም እንዴ ዛሬ ቸርች አይደል እንዴ የመጣሁት እንላለን፣ ስብከት ዛሬ የለም በቃ ወይ ሰንበት ትምህርት ብቻ ተወያይተን እንሄዳለን ቢባልም በጣም ይከፋናል። ግን ሳይዘመር ቢኬድ ብዙ ሰው ምንም ላይመስለው ይችላል፣ በቃ አልተዘመረም፣ ፕሮግራም ስለረዘመ ነው ምናምን ሊባል ይችላል። ነገር ግን ወጣቱ መዝሙር ይወዳል፣ በእድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ደግሞ ስብከትን ይወዳል በሚል አስተሳሰብ ሳይሆን አምልኮ ነው፣ እግዚአብሔር በሰማይ የሚቀበለው ነውና በሰማይ ያልቀረን እኛ ለምን በምድር እናስቀረዋለን? እና ሰዉንም ደግሞ በዜማ ሆኖ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ውስጡ የሚገባበትን መንገድ:, አንዳንዴ ስብከት ማይደርስበት ቦታ አለ። ሙዚቃም የማይደርስበት ቦታ ሊኖር ይችላል፣ አንዳንዴ በፀሎት ብቻ እግዚአብሔር የምናወራበት እና ለሁሉም ጊዜ አለው ያለው ሰለሞን እውነቱን ነውና፣ በመዝሙር ህዝቡን ምንደርስበትን መንገድ እኛ ምንነካበትን ሰው ሁሉ የሚነካበትን መንገድ እና ደግሞ የአምልኮ አንድ ትልቁ ክፍል የሆነ ነገር ነውና ያንን በደንብ ብንገነዘብና እዚያ ላይ ብንሰራ ብናሳድገው: እግዚአብሔር የሚሰጠንን ዝማሬዎች በደንብ ብናወጣ፣ እንደ ዘማርያን እንደ ሙዚቀኞችም በደንብ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ነገር ለማቅረብ ተግተን ብንሰራ ብዬ አስባለሁና እግዚአብሔር ይርዳን። ያንን ነው በህይወቴ የተረዳሁት፥ ያንን በቤተክርስቲያኔ ማየት እፈልጋለሁ።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- እንደ እናንተ በግሩፕ የማገልገል ፍላጎት ያላቸው ከእናንተ መማር እና አስቀድመው ማወቅ ያለባቸው ነገር ምንድነው? 🗣[በሱፍቃድ]:  "እና በዚሁ አጋጣሚ ለሌሎችም ግሩፖች መምከር የምፈልገው ሃሳብ ቢኖር በግሩፕ ማገልገል መልካም ነው፥ በሶሎ ከማገልገል ቅድም እንዳልኳችሁ የተሻለ ነው በአንድነት መዘመር በብዙ ነገር፣ ከመንፈሳዊ influence ያ ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው በክርስቲያን መንፈስ ስለምንመላለስ፣ ነገር ግን የharmonyው ከሚታየው ከዜማውም በላይ ያለው ጠቀሜታ መልካም ስለሆነ ግን ያ ግሩፕ በአንድ ላይ የማይጸልይ፣ አንድ ላይ የማይተጋ፣ እግዚአብሔር በስራም፣ በምንም እንዳይበትነው ስራዎቹንም ቅርብ እንዲያደርግለት፣ ትምህርትም ያለበት ትምህርቱንም ቅርብ አከባቢ እንዲሆን፣ ያ ግሩፕ እንዳይለያይ እንዲያግዘው እለት ከእለት ካልጸለየ ያንን ማስቀጠል ይከብዳል፥ ጊዜ እንኳን ቢኖር መስራት፣ መትጋት ይፈልጋልና መዝሙሮችን መፃፍ፣ ዜማዎችን ማውጣት፣ እንደዚህ እንደharmony፣ instrumentም እዚያ ላይ መስራት የሆነ time ላይ ሊከብድ ይችላልና በዚያ ነገር ተስፋ ሳይቆርጡ መትጋት ያስፈልጋልና፣ ያንን ልመክር እወዳለው። በግሩፕ ማገልገል የምትፈልጉ ሰዎች ያንን ነው እኔ የተማርኩት እና፣ ፅናትን፣ ብርታትን የሚሰጠውን እግዚአብሔርን የጠየቅን ግሩፓችንን እንዲያበረታ ላለመራራቅ፣ ለመበርታት፣ ለመትጋት መሞከር ያስፈልጋል ማለት ነው።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- ዘ ሺማ እና የአሜን ዜማ አመሰራረት እንዴት እንደሆነ እና ለመጀመር ያሳለፋችሁት ውጣውረድ ምን ይመስላል?  🗣[በሱፍቃድ]:  "የዘ-ሺማ እና የአሜን ዜማ አመሰራረቱ: አሜን ዜማ በኮቪድ ጊዜ ነው፣ ስራዎቻችንን አቁመን ከቤት እየሰራን ባለንበት ሰአት መዝሙሮችን ስናጠና ስንዘምር ስንለማመድ ሆፕ ቻናል ላይም ስንዘምር እግዚአብሔር ግሩፕ እንድናቋቁም አሳሰበን፥ ወንድማችን "ይድኔ"፣ " አማን"፣ እኔ ሌሎቹም ተሰባሰብን፣ እነዚህን መዝሙሮች ስናጠና እግዚአብሔር ያንን ሃሳብ በውስጣችን አመጣ፣ ታሪኩን ለማሳጠር [ሌላ ጊዜም እንግዲህ በሰፊው የምናነሳው ይሆናል]፣ ያ ግሩፕ ተቋቁሞ ማገልገል ጀመርን ማለት ነው እና የነበረው ውጣውረድ ያው መገናኘት ነው። ያኔ ብዙ ውጣውረድ አልነበረም፣ ግን በቃ በስራ በተለያዩ ነገሮች መለያየት፣ መራራቅ ሲመጣ እንደ ቀድሞ ለመገናኘት እየከበደ ይመጣልና Consistent መሆን ይከብዳል፣" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- ዘማሪ ሆነህ ሙዚቃ መጫወት መቻልህ በተለየ ሁኔታ ጠቅሞኛል የምትልበት ምክንያት አለህ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "ዘማሪነትና ሙዚቃ ተጫዋችነት አንድ ላይ የሚሄዱ ናቸው ብዬ አስባለሁ ቅድም እንዳልኩት ከአምልኮ አንፃር ማለት ሁሉም ለእግዚአብሔር ክብር ስለሆነ just ሙዚቃውን ብቻ ሳይሆን በኖቶቹም ውስጥ እግዚአብሔር አለ። በወፎችም ዜማ በተፈጥሮም፣ ሳይንሱ ደሞ waveዎች soundዎች ይሉታል አይደለ፣ Nature እራሱ የራሷ sound አላትና ይላሉ ይመራመራሉ። እዛ ውስጥ አንገባም ግን ዜማዎችም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ ግን ደግሞ በቃሉ አማካኝነት በሰጠን በራሱ በቅዱስ ቃሉ አማካኝነት ደግሞ ዜማ እዛ ላይ ሲጨመር ልዩ በረከትን ይሰጣልና አንድ ሙዚቀኛ መዘመር ከቻለ እግዚአብሔርን ማመስገን ከቻለ፣ ማለት አያይዞ ከሄደ ለአምልኮም ብቻ ሳይሆን ለስጦታውም ይጠቅማል skillኡን እንዲያሳድግ ይረዳዋል፡ አብሮ ሲዘምር። ማይዘምር ሙዚቀኛ እንዴት ሰዎች ማስገባት እንዳለበት፣ key እንዴት መስጠት እንዳለበት፣ እንዴት ለህዝቡ የሚመች key መስጠት እንዳለበት አያውቅም። እንዴት ህዝቡ እንደሚዘምር፣ እንዴት ከአንድ መዝሙር ወደ አንድ መዝሙር ሲሸጋገር እንዴት የሆነ፣ ሰው እግዚአብሔርን እያመሰገነ ባለበት ሰአት ድንገተኛ ነገር አያስገባም flow የሚባለውን ነገር ያውቃል። እና አንድ ሙዚቀኛ ዘማሪ መሆን አለበት፥ ማለት ሶሎ ላይዘምር ይችላል ግን በውስጡ ከጉባኤው እኩል መዘመር አለበት ብዬ አስባለው።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- ሙዚቃ መጫወት ተሰጥኦን ለእግዚአብሔር ክብር መጠቀም ላንተ ምን ማለት ነው? 🗣[በሱፍቃድ]:  "ሙዚቃን የመጫወት ተሰጦ ለእግዚአብሔር ክብር መጠቀም ማለት እኔ እንደምረዳው ሙዚቀኛ just ሙዚቃ ብቻ የሚጫወት አይደለም፣ እርሱም እግዚአብሔርን የሚያመልክ መሆን አለበት በአምልኮ ጊዜ ህዝቡን ብቻ የሚያስጠጋ እሱ በተሰጠው ስጦታ ብቻ ተጠቅሞ ከጉባኤ ውጪ ሆነህ ሳይሆን ከጉባዔው እኩል እግዚአብሔርን የሚያመልክ እግዚአብሔርን የሚያከብር መሆን አለበት ብዬ አስባለሁና፤ እና ደግሞ እንደ ጊዜያችን ከ7ቱ ቀን አንዱን ቀን ለእግዚአብሔር እንደምንሰጥ፣ አስራት አንድ አስረኛ እንደምንሰጥ፣ ሙዚቀኛ ደሞ አንድ 10ኛው ወይም የአንድ ሰባተኛውን ሳይሆን ሙሉውን ለሰጠው ለራሱ ለእግዚአብሔር እንዲጠቀምበት መልሶ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ። ህያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገን ተሰጥዖዋችንን፣ ስጦታዎቻችንን፣ skillአችንን ለእግዚአብሔር ከሰጠን እሱ ደግሞ ህዝቡን ወደ እርሱ ሃልዎት ለማቅረብ ይጠቀምበታልና፣ እኛ ተለውጠን እኛ በምንጫወተው ደግሞ ህዝቡን ልክ ዳዊት ሳኦልን እንዳገዘው፣ ከክፉ መንፈስ እንዳራቀው እኛም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንፈስ የሚጠራ፣ ክፉውን የሚያርቅ ስጦታ ነው የተሰጠን። ስጦታው እግዚአብሔር ሲገኝበት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን በመጋበዝ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ስናስረክብና ለእርሱ ስንሰጥ ያኔ ነው ለእግዚአብሔር ሰጠን የሚባለውና ያንን በህይወታችን ማየት እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- በህዝብ ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሙዚቃ የተጫወትክበትን ጊዜ ታስታውሰዋለህ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ፊት ሙዚቃ የተጫወትኩበት ጊዜ I think 9ኛ ክፍል እያለው ይመስለኛል በሲኤምሲ ቤተ ክርስቲያን እያለን ከላይም እንዳነሳሁት እህታችን ሜርሲ እድል ትሰጠን ነበር ለታዳጊዎችና አንዴ እድል ሰጥታኝ ለህዝቡ የሆነ የውዳሴ መዝሙር እንደተጫወትኩ "🎵አስረክባለው🎵" ይሁን ወይ "🎵እየሱስ የልቤ ወዳጅ🎵" ይሁን ወይ "🎵ና አንተ የበረከት ምንጭ🎵" ከሦስቱ አንዱ እንደሆነ አርግጠኛ ነኝ። ተጫወትኩ ከዛ gainህን አስተካክል ስትለኝ ትዝ ይለኛል ግን ብዙዎች የሚያቁት ቪድዮዬን ያዩት ደሞ ከአንድ ወንድሜ ጋር አሁን በጀርመን ሀገር ነው ያለው፣ ካሌብ ከሚባል ከአንድ ወንድሜ ጋር የተጫወትነው ቪድዮ ቀረፃ አለ እና ሁልጊዜ የማስታወሻ ሲወጣ እርሱ ይወጣል እና 😁 እርሱ ጊዜ ነበረ። ከዚያ በፊት ግን አንድ ሁለት ሦስቴ I think ተጫውቻለው፣ ያው በቪድዮ በማስረጃ የተቀመጠው እሱ ነው ለዛ ነው 😊 ያኔ ነው የተጫወትኩት ከዛ በኋላ እንግዲህ እየቀጠለ አሁን ደርሰናል ማለት ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። ወደኋላ ሳስታውሰው በቃ እግዚአብሔር ያን እድል ስለሰጠኝ እጅግ አድርጌ አመሰግናለው።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

ጥያቄ:- 🎤 የምትወደው የአድቬንቲስት ዘማሪ? 🗣[በሱፍቃድ]:  "የምወደው የአድቬንቲስት ዘማሪ ... ይሄም ያው ይከብዳል። መዝሙር variety ነው እና በሁሉ aspect ስለሚናገር እንዳልኩት የደስታ አለ፣ የምስጋና አለ በቃ celebrate ለማድረግ የሚሆኑ መዝሙሮች፣ የንስሃ መዝሙሮች አሉና በዚህ ረገድ አሁን ስለንስሃ ብዙ የጻፈ፣ ወይ የምስጋና መዝሙር ብዙ የጻፈ፣ ስለ ሰማይ ብዙ የጻፈ እያልን ብናያቸው ካልሆነ በስተቀር የምንጊዜም አንድ ብቻ አይደለምና ቅድም ከጠቀስኳቸው [አልበም ባይኖረውም በቅርብ እግዚአብሔር ቢፈቅድ አልበም ይኖረዋል] ብዙ መዝሙሮችን ለቤተክርስቲያናችን ያበረከተ ወንድማችን "ብሩክ ፈለቀ" ከቅርበትም አንፃር በጣም የሚባርከኝ እግዚአብሔር የሚጠቀምበትየምወደውም ዘማሪ ነው። ከዛ ውጪ እነ"ማሞ ጴጥሮስ"፣ እነ"ሰላሙ"ን፣ እነ"ፓስተር ተስፋዬ" በጣም የሚባርኩኝ ዘማሪያን ናቸው፣ "ደረጄ ኩራባቸው"ም ሌሎችም። ከሁሉም መዝሙር በቃ የሆነ ውስጤ የሚቀሩ መዝሙሮች አላቸው ሁሉም እና ሌሎችም ብዙ የምጠቅሰው ይኖራል፥ ግን እነዚህ ዘማሪዎች እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸውና መዝሙሮቻቸው በጣም የሚባርኩኝ ዘማሪያን ናቸውና፥ ብዙ ሌሎችም አሉ ግን አንድ ሰው ብቻ አይደለም ለማለት ነው። ግን at least እነዚህ ዘማሪዎችን በፈር ቀዳጅነት አነሳለው።" #ከመዝሙሩ_በስተጀርባ

#ፍቅርህ_ነው #Biruk_Feleke